ማስታዋሻ ቁጥር 6፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለእምነት አባቶች የሰጡት እምነትን በስራ ትምህርት!
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን (ኢኦተቤ) ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመገናኘት በስደት ከሚኖረው ከዲያስፖራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አመራሮች ጋር ዕርቀ ሰላም እንዲያወርዱ በአጽንኦ ተማጽነዋል፡፡ ይህንንም በማስመልከት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እንዲህ ብለዋል፡ “በኃይማኖት መሪዎች መካከል በተለያዩ ምክንያቶች በርካታ ልዩነቶች ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን ሊፈቱ የማይችሉ ልዩነቶች አይደሉም፡፡ የቤተክርስቲያን መሪዎችን…