Amharic Translations Archive

ኢትዮጵያ፤ ወደ ዴሞክራሲ የመጓዣው ጎዳና ካርታ ላይ

ባለፈው ሳምንት በሲያትል ከተማ የኢትዮጵያን ራዕይ በተመለከተ ሰፊ ሕዝባዊ ውይይት፤ ክርክር፤ ለማካሄድ በተመሰረተ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ፎረም ላይ (EPFS)ላይ ተጋብዤ ተገኝቼ ነበር:: በዚህምስብሰባ ላይ በቅርቡ ሳቀርባቸው በነበሩት የኢትዮጵያን ከፈላጭ ቆራጭ ግዛት ወደ ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ሽግግርን በተመለከተ ማብራሪያ እንድሰጥ ተጠይቄ ነበር፡፡ እኔ በኢትዮጵያ ከፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ሊካሄድ ስለሚገባው የሽግግር ሁኔታ የማቀርባቸው

የኢትዮጵያ ሽግግር ወደ ዴሞክራሲና የማንነት ፖለቲካ

ባለፈው ሳምንት የአሜሪካን ድምጽ የአማርኛው ፕሮግራም ዘገባ ከሃገሪቱ ደቡባዊ ክፍል በግዳጅ ከቀዬአቸው የተፈናቀሉትን በርካታ ኢትዮጵያዊያንን የሚመለከት ነበር፡፡ በዘገባው መሰረት፤ ከዚሁ ከደቡባዊ ክልል በጉራ ፈርዳ በግብርና ይተዳደሩ የነበሩ በርካታ የአማራ ተወላጆች በአካባባዊ ባለስልጣናት ንብረታቸውን ይዘው በአስቸኳይ ከአካባቢው ለቀው ወደ ‹‹ሞት ወረዳ›› የቀድሞ ቀያቸው እንዲሄዱ ለዳግም ስደት ተዳርገዋል፡፡ ለአሜሪካን ድምጽ በሰጡት የአቤቱታና የሰሚ

ለኢትዮጵያዊያን፤ የጨለመው ስደት በኖርዌይ

በሃገራቸው ባለው ጨካኝና አረመኔያዊ አገዛዝ ሳቢያ፤ገዛዙ በፈጠረው የኑሮ ውድነት፤ የነጻነት እጦት፤በችጋሩ፤ በሙስና፤ አረመኔው መንግሥት ሆን ብሎ፤ አውቆ፤ ፍጥረቱ ለጥፋት ተልእኮው በኢትዮጵያዊያን ላይ ስደትናእንግልትን ማደርጀት ነው፤ በሚፈጽመው የዲያቢሎስ ተግባር ሃገራቸውን ጥለው የተሰደዱት ኢትዮጵያዊያን በሰሜን አፍሪካ፤በመካከለኛው ምስራቅ በሌሎችም የአፍሪካ ሃገራት ለባሰ መከራና ስቃይ እየተዳረጉ ነው፡፡ ኢትዮጵያውስጥ መኖር ሳይሆን ለመኖር ማሰብ እንኳ ችግር ሆኖባቸው ስደትን ቢመርጡም

እሪ ይበል ወንዙ፤ እሪ ይበል ሃይቁ! ከዓለማየሁ ገብረማርያም

የአፍሪካ ግፈኛ ገዢዎች፤ ሕዝቦቻቸው በችጋር ሲያልቁና መኖር ጣር ሲሆንባቸው፤ግድብ ማስገንባትን፤አብረቅራቂ ህንጻዎችን ማስገንባትን ይወዳሉ፡፡ይህን የሚያደርጉት ግላዊ ሃብትን ለማካበት፤መኮፈሳቸውን ለመጨመር፤ተስፋ ያጣ ህልማቸውንና ምኞታቸውን ለማሟላት፤ ድክመታቸውንና ችሎታ ቢስነታቸውን ለመሸፈን የቻሉ እየመሰላቸው ነው፡፡በደም የተጨማለቀ እጃቸውን ያጸዱ እየመሰላቸውና በስልጣን ላይ ለዘለቄታው ለመቆየት የሚያስችላቸው እየመሰላቸው ነው፡፡እርቀኑን የቀረ ግፈኛ የአገዛዝ ማንነታቸውን በማይጨበጥና በማይታይ ልማታዊ እቅድና፤እድገት ለመሸፈን ይሞክራሉ፡፡...

ለዶናልድ ፔይን የሰብአዊ መብት ችሮታ – ከዓለማየሁ ገብረማርያም

ድንገተኛ መለየታቸው ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ የነጻነት የዴሞክራሲና የሰብአዊ መብት ትግል ማዝገምን ያስከትልብናል፡፡ሆኖም ግን ፔይን ትተውልን የሄዱት የሰብአዊ መብት፤ጥብቅናና ለረጂም ዓመታት በፍትጊያና በትግል ውስጥ የነበረውን ሂደት ነው፡፡አሁን ደሞ የዚህ ፍትጊያ እጣ ፈንታ በኛ ላይ ተጥሏልና፤ ሸክሙ የኛ የሞራል ግዴታችን ነው፡፡ይህንንም ችሮታቸውን አጠናክረን፤ በሰፊው ሙግቱን አቀነባብረን፤የውጤቱን ጊዜ ማፋጠን ግዴታችንም፤አደራም፤ያውም ታላቅ የመብት ተሟጋቹ ጥለውብን ያለፉት አደራ ነው፡፡

እስክስ! ጅቡ ከደራጎኑ ጋር፣ አይ ጉድሽ አፍሪካ!

የቻይናው ደራጎን (ጭራቅ)ከአፍሪካውያን ጅቦች ጋር አሸሸ ገዳሜ ጭፈረውን እያስነካው ነው፡፡ለዚህ ደራጎን አፍሪካ በምንም መልኩተስማሚ ሁኔታ አትፈጥርለትም፡፡ታሪክ እንደሚያስረዳው በአንድ ወቅት የአፍሪካውያን መኩሪያና መመኪያ የነበረችው ምድር አሁን የጅቦች መሰባሰቢያ ትልቅ ዋሻ ፈጥራ (የአፍሪካ ሕብረት) የጅቦቹ መፈንጪያ መናሃርያ ሆናለች፡፡ለዚህ የጅቦች መገናኛ፤መዶለቻ፤መለመኛ፤ሕዝባዊ ማነቆ መፍተያው ሁሉ ለሚከናወንበት ግንባታ የሚያስፈልገውን ወጪ 200 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የተሸፈነው በቻይና ነው፡፡ ሲባልም፤ ይህ

ዶናልደ ፔይን፡- ስንብት ለሰብአዊ መብት ቀደምት ተሟጋች!

ፔይን ለአፍሪካ የነበራቸው ያልተቆጠበ ጥረት ታሪካዊና የማይዘነጋ ነው፡፡በ2008 በርካታው መጠን ለአፍሪካ በዓመስት ዓመታት ሂደት በተግባር ላይ የሚወጣውን የ 48 ቢሊዮን ዶላር የድጋፍ ችሮታ(ለኤይድስ መቆጣጠርያ) ኮንግሬስ እንዲፈቅድ በቀረበበት ወቅት ፔይን ከፍተኛ ሚና ተጫውተው እንዲፈቀድ አድርገዋል፡፡በዳርፉር በሰብአዊ መብት ረገጣና ዘር በማጥፋት ላይ የተሰማሩትን ተጠያቂዎች አስመልክቶ በሱዳን ላይ የተጣለው እቀባ እንዲወሰንም ያደረጉት ጥረትና ተሳትፎ ቀላል አልነበረም፡፡ በሱዳን የተደረሰውን

ኢትዮጵያ፣ ከፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲ

የሰብ ሰሃራ አፍሪካም ፈላጭ ቆራጮች ሲንሸረተቱና መቀመጫቸውን ሲለቁ ታይተዋል፡፡ኮተ ዲቩዋሩም ሎራንት ባግቦ ከመኮፈሻው የሽቅርቅር ነጭ ኮሊታው ሸሚዙ ተለያይቶ በቤተመንግሥቱ ከተወሸቀበት ጓዳው ተይዞ በፈጸመው የሰብአዊ መብት ጥሰትና ግድያ ለፍርድ ለዓለም የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ተላልፏል፡፡ የኒጀሩ ማማዱ ታንጃ ሕገመንግሥታዊ የስልጣን ገደብን በመጣስ በሥልጣን ላይ ለመቆየት ቢፍጨረጨርም የኒጀር ጦር አሽቀንጥሮ አውርዶታል፡፡የማማዱ ታንጃም ቀንደኛ ተወዳዳ በሕዝባዊ ምርጫ ሥልጣኑን ተረከበ፡፡በቅርቡም፤የሴኔጋሉ

የአንዱዓለም አራጌና የሌሎችም የፖለቲካ እስረኞች ግፍና መከራ

ስቃይና መከራ፤ በደልና ግፍ፤ በኢትዮጵያ ፖሊሶችና ወታደሮች በተለይም የደህንነት አባላት፤ የጠረጠሯቸውን የህብረተሰብ አባላት፤የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን፤የተቃዋሚ ሃይሎችን አባላት፤የሌሎችንም ደጋፊ ናቸው ብለው የሚጠረጥሯቸውን በሚስጥራዊ መንገድና ቦታ በወታደራዊ ካምፖችና በልዩ ልዩ ሰውር ቦታ በተዋቀሩ ጎሬዎች አስረኞችን ማጎር የደህነንቱ የተለመደ ተግባር ነው፡፡