ማስታዋሻ ቁጥር 5፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በኢትዮጵያ የሰዎችን የሕግ የበላይነት በማስወገድ እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በማንሳት የሕግ የበላይነትን ተቋማዊ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፣

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም 

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ  

“…የደንብ ልብሶችን የለበሱ እና ኮፍያዎችን/መለዮዎችን ያደረጉ የደህንነት ኃይሎች ስራቸው ህዝቦችን ከሁከት ወይም ከጦርነት መከላከል እና ሰላም እንዳይደፈርስ መከላከል ነው፡፡

የደህንነትኃይሎችስራቸውንሞያውበሚጠይቀውመልኩበአግባቡመስራትየማይችሉከሆነእነዚህኃይሎችስራቸውንአያውቁትም

ወይም ስራቸውለምንአስፈላጊእንደሆነአይገነዘቡትምማለትነው፡፡ወይምደግሞየክልልባለስልጣኖችለእነዚህየደህንነትኃይሎችተገቢየሆነሞያዊእናግብረገባዊስልጠናሳይሰጧቸውቀርተውሊሆንይችላል፡፡ሆኖምግንእንደዚህያለውሞያዊስራጉድለትያለበትሀገርአቀፍችግርነው፡፡

ጥቂትሰዎችየደንብልብሶችንሲለብሱእናክላሽንኮቮችንሲይዙኃይልይሰማቸዋል፤እናምበማህበረሰቡውስጥበሚኖሩደካሞችላይስልጣናቸውንከሕግአግባብውጭይጠቀማሉ፡፡እንደዚህዓይነቱድርጊትከዚህቀደምምስናገርላቸውከቆየሁባቸውአውዳሚየሆኑልማዶችመካከልአንዱነው፡፡ደካሞችንመርዳትእናመደገፍተገቢነው፡፡ሆኖምግንስልጣንንከሕግአግባብውጭመጠቀምሕገወጥነትነው፡፡በተለይምከዚህቀደምእንደተናገሩትአባትበጣምአስከፊየሆነስልጣንንከሕግአግባብውጭመጠቀምማለትነው፡፡ምርጫውአንደኛማስተማርሲሆንሁለተኛውደግሞጥፋትፈጽሟልተብሎየተጠረጠረንሰውበሕግአግባብተጠያቂማድረግነው፡፡ማንምቢሆንበሌሎችሰዎችላይከሕግአግባብውጭስልጣኑንመጠቀምአይችልም፡፡ሕጉለደካሞችምለኃይለኞችምእኩልየሚያገለግልመሆኑንማሳየትመልካምነገርነው፡፡የክልልመንግስታትየሕግየበላይነትንበተግባርማሳየትአለባቸው፡፡ ስልጣንእናጠብመንጃያለንሰዎችየእኛንፍላጎቶችበሌሎችላይለመጫንእንድንችልሕጉንልንጠቀምበትየምንችልነገርማለትአይደለም፡፡ሆኖምግንሕጉአመራርየሚሰጡትትክክለኛብይንየሚሰጡበትእንደዚሁምደግሞበሕጉየሚተዳደሩሰዎችበትክክለኛውመንገድብይንየሚያገኙበትማለትነው፡፡በደካሞችእናበኃይለኞችላይበእኩልነትተግባራዊየሚደረግእናሕጉምፍትሀዊበሆነመልኩበስራላይመዋሉንበእርግጠኝነትከልብየምንናምንበትመሆንአለበት፡፡እንግዲህመደረግ  ያለበትበእንደዚህዓይነትአካሄድነው፡፡በሕግፊትሁሉምበእኩልመታየትአለባቸው፡፡ ኃይልያላቸውሰዎችሕጉንለእራሳቸውመጠቀሚያየሚያደርጉትከሆነአይሰራም፡፡ዜጎችስህተትሲሰሩእናሕግንሲተላለፉ“ሕግንተላልፊያለሁእናምበሕጉተጠያቂመሆንአለብኝ“በማለትበሕጉፍትሀዊነትላይእምነትሊኖራቸውይገባል፡፡ሕጉፍትሀዊበሆነመልኩሁላችንንምበእኩልተጠያቂማድረግየሚችልነገርመሆንአለበት፡፡እርግጠኛነኝየክልልአመራሮችይህንንለማረጋገጥአስፈላጊውንነገርሁሉእንደሚያደርጉተስፋአደርጋለሁ፡፡“ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እ.ኤ.አ ግንቦት 2 ቀን 2018 ዓ.ም ከተናገሩት ተወስዶ በጸሀፊው የተተረጎመ።

ኢትዮጵያበትክክለኛውጎዳናላይበመጓዝላይናት፡፡በኢትዮጵያየሕግየበላይነትእናየሰብአዊመብትመከበርከፍተኛውደረጃላይደርሰናል፡፡በዋናነትይህችሀገርየሕዝቦችዴሞክራሲያዊመብቶችየተከበሩባትሀገርናት፡፡” መለስ ዜናዊ፣ እ.ኤ.አ ጥቅምት 2011 ዓ.ም የተናገረው

ኢትዮጵያ ከአምባገነናዊነት ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የምታደርገው ሽግግር ከኢፍትሀዊነት የሕግ አገዛዝ ወደ ፍትሀዊ የሕግ አገዛዝ ስርዓት ሽግግር ማለት ነው፡፡ መንግስት ሁልጊዜ ዜጎችን በሚፈራበት ጊዜ እና ዜጎች በምንም ዓይነት መንግስትን መፍራት የማይችሉበትን ድፍረት በሚቀዳጁ ጊዜ በኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት በጥልቀት ስር የሰደደ መሆኑን አምናለሁ፡፡ ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም፣ “የሕግ የበላይነት ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሽግግር“ በሚል ርዕስ እ.ኤ.አ ሚያዝያ 2012 ዓ.ም ካቀረቡት ጽሁፍ የተወሰደ

የሰው ልጆችን ስብዕና ከፍ የሚያደርግ ማንኛውም ሕግ ፍትሀዊ ነው፡፡ የሰው ልጆችን ስብዕና የሚያዋርድ ማንኛውም ሕግ ኢፍትሀዊ ነው፡፡ ማንኛውም ሰው ለፍትሀዊ ሕጎች መገዛት ብቻ ሳይሆን ለሕጎቹ የመገዛት የሞራል ስብዕና ኃላፊነትም አለበት፡፡ በሌላ በኩል ማንኛውም ሰው ፍትሀዊ ላልሆኑ ሕጎች ላለመገዛት የሞራል ስብዕና ኃላፊነት አለበት ለኢፍትሀዊ ሕግ ምንም ዓይነት ሕግ እንደሌለ ይቆጠራል፡፡ ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ፣ “ከቢርሚንግሀም እስር ቤት የተላከ ደብዳቤ” በሚል ርዕስ እ.ኤ.አ 1963 ዓ.ም ከጻፉት የተወሰደ

የጸሀፊው ማስታዋሻ፡ በተደጋጋሚ እንዲህ እላለሁ፣ ለበርካታ ዓመታት ያቀረብኳቸው ትችቶቼ “የሕግ የበላይነት” በሚል በአንድ መሰረታዊ መርህ ላይ የተዋቀሩ ናቸው::

ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በኢትዮጵያ ውስጥ የሕግ የበላይነትን ተቋማዊ የማድረግ አስፈላጊነት አስቸኳይ እንደሆነ ጥልቅ ምልከታ አቅርበዋል፡፡ የእርሳቸውን የንግግር ዓረፍተ ነገሮች በምተረጉምበት ጊዜ አባባላቸውን በትክክል ሳልከትብ ቀርቼ የትርጉም ልዩነት ሰርቼ እንደሆነ ወይም ደግሞ የቃላት አመራረጥ ላይ ክፍተት ፈጥሬ ከሆነ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡

በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ስለሕግ የበላይነት መከበር አስፈላጊነት እና ሕጉን ለማክበር ቃለ መሀላ ለሚፈጽሙት አጽንኦ በመስጠት ያስተላለፉት መልዕክት ያረካኝ እና ያስደሰተኝ ነገር ነው፡፡ ከላይ በጥምህርተ ጥቅስ ያስገባኋቸው እና እርሳቸው ያስተላለፏቸው መልዕክቶች እኔ በአሜሪካ ሀገር ውስጥ የሕግ የበላይነት እንዲከበር ሳራምደው የቆየሁትን የእራሴን ዘመቻ አስታወሰኝ፡፡

ከ20 ዓመታት በፊት በዛሬው ወር ገደማ አካባቢ አሁን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እየተናገሩላቸው ካሉት መርሆዎች ጋር አንድ ዓይነት የሆኑ መርሆዎች በካሊፎርኒያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንዲተገበሩ ስሞግት ነበር፡፡ በዚያ ጉዳይ በዩኤስ ሕገ መንግስት አምስተኛው ማሻሻያ ክስ ሳይመሰረት እና የጥፋተኝነት ውሳኔ በፍርድ ቤት ሳይወሰንባቸው ጥፋተኛ በሚባሉ ሰዎች ላይ የሕግ የበላይነት እንዲከበር ስሟገት ነበር፡፡ ከሕግ አግባብ ውጭ ጥፋት የሚሰራው ፖሊስ እንደሆነ እና በቃለ መጠይቅ ሰበብ ተጠርጣሪውን በእስር ቤት መብቱን የሚረግጠው ፖሊስ ነው በማለት ፍርድ ቤቱ ከእኔ ጋር ተስማምቷል፡፡ በሌላ አባባል በወንጀል የተጠረጠረ ሰው በሚጠየቅበት ጊዜ ለዚሁ ጉዳይ ተብሎ የሕግ ባለሞያ አብሮ ያለመኖር የሀገሪቱ የሕግ የበላይነት ሊታገሰው የማይገባ ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ጉዳይ እንዲኖር የዩኤስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እ.ኤ.አ በ2004 ዓም ትዕዛዝ ሰጥቶበታል፡፡

እ.ኤ.አ. በ2003 ዓ.ም እኔ እየተከራከርኩለት የነበረውን ጉዳይ የካሊፎርኒያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፖሊስ ሆን ተብሎ የተጠርጣሪን መብት የሚገፈውን አሰራር ሕጋዊ እንዳይሆን አድርጓል፡፡

ፍርድ ቤቱ እንዲህ በማለት ገልጿል፤

ባለስልጣኖች የተጠረጠሩ ሰዎችን በማቆያ ቤት አድርገው በሚጠይቁበት ጊዜ በሕጎቹ ብቻ መጠቀም እንዳለባቸው ፍጹም የሆነ ግዴታ አለባቸው፡፡ እናም ይህንን ጉዳይ ሆን ብለው በቸልታ የሚያልፉት ከሆነ ከባድ የሆነ የስነ ምግባር እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ሊገነዘቡት ይገባልነጻ በሆነ ማህበረሰብ ውስጥ ፖሊስን ልዩ በሆነ ስልጣን ላይ እናስቀምጣለን፡፡ ሆኖም ግን ይህንን የምናደርገው ሕጉን ለማስከበር የተቻላቸውን ሁሉ በማድረግ በሚያስደንቅ እና ፍትሀዊ በሆነ መልኩ ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋሉ፡፡ ውጤታማ በሆነ መልኩ የመስራት ችሎታቸው በዚያ በሚጫወቱት ሚናቸው ላይ ባላቸው ታማኝነት ላይ ይወሰናል፡፡ ማህበረሰቡ ባለስልጣኖች ቃለ መሀላ በሚገቡበት ወቅት ቃል የገቡበትን ያከብራሉ እናም ሆን ብለው መደበኛውን ሕግ ይጥሳሉ የሚል እምነት የለውም፡፡ ፖሊስ ትክክለኛውን አሰራር ማክበር በማይችልበት ጊዜ ማህበረሰቡ በፖሊስ ላይ እና ከዚያም ባለፈ በሕጉ ላይ ያለውን ክብር ዝቅ ያደርገዋል፡፡

በማንኛውም ረገድ እና እኔን በሚያስደንቀኝ ሁኔታ በዚያን ጊዜ የአሜሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ለአሜሪካውያን ይነግሯቸው እንደነበረው ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ በአሁኑ ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለኢትዮጵያውያን ተናግረዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መልዕክት ይህ ነው፣ የኢትዮጵያ የሕግ አስፈጻሚ አካላት ቃለ መሀላ የፈጸሙበትን የሕግን የበላይነት በማያከብሩበት ጊዜ ህብረተሰቡ ለፖሊስ እና ለሕጉ ለእራሱ የሚሰጠው ክብር ይሸረሸራል፡፡ ሕጉን ለማስፈጸም ቃለ መሀላ የፈጸሙት ሕግ አልባ ከሆኑ ይህ ሁኔታ ዜጎችም ሕግ አልባ እንዲሆኑ ይጋብዛቸዋል፡፡ በዚያን ጊዜ እንግዲህ ትክክለኛነት ወደ ኃይልነት ይሸጋገራል እናም ፍትህ ወይም ሕግ ሳይሆን ምንጊዜም ኃይል ትክክል ይሆናል፡፡

የአሜሪካውያንን ጠቃሚ ሕገ መንግስት ሕግ ለማስከበር እጅግ ከፍተኛ የሆነ ክብር እና ሞገስ ይሰማኛል፡፡

ሆኖም ግን ትልቅ ቅሬታም ይሰማኛል፡፡ እ.ኤ.አ በ2015 ዓ.ም የማግና ካርታ ሊበርታተም 800ኛ ዓመት በዓል በሚከበርበት ጊዜ እንዳስተዋልኩት ከ800 ዓመታት በፊት በእንግሊዞች በተጻፈው እና በአሁኑ ጊዜ እንኳ ሕግ ሊባል በማይችለው የነጻነት ሰነድን  እጅግ በጣም ሳወድስ ነበር፡፡ ሆኖም ግን ከ20 ዓመታት በፊት የአዲስ ዘመን ነጻነት፣ ፍትህ እና እኩልነት ተብሎ በተጻፈው የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት ሀፍረት እንጂ ኩራት አልተሰማኝም፤ ምክንያቱም ሕገ መንግስቱ የተጻበትን ወረቀት ያህል እንክዋን ዋጋ ስለሌለው፡፡

ለወደፊት እንደሚታየው የኢትዮጵያ ማግና ካርታ ነጻነት (ታላቁ የኢትዮጵያውያን የነፃነት ሰነድ) ሳስብ ከፍተኛ የሆነ ደስታ ይሰማኛል፡፡

በሕግ የበላይነት ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጠንካራ አቋሞች ለምን አስፈላጊ እንደሆኑ፣

በኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሕግ የበታች በሚሆንበት ጊዜ በሕግ የበላይነት ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ምልከታዎች ልዩ ትርጉም እና ጠቀሜታ ይኖራቸዋል፡፡

በሕግ የበላይነት ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ይፋ መግለጫዎች በጎዳናዎች ላይ ላለ የፖሊስ መኮንን ብቻ የቆሙ አይደሉም፡፡ ሆኖም ግን ሌላ የፖሊስ ስራ ለሚሰራው “ለኮማንድ ፖስት” ጭምር ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የደንብ ልብስ የለበሱ እና ክላሽንኮቮችን ያነገቱ የተወሰኑ ሰዎች የሀገሪቱን ጠቅላይ ሕግ አሽቀንጥረው በመጣል ስልጣናቸውን ከሕግ አግባብ ውጭ በመጠቀም ላይ ያሉ መሆናቸውን ያመላክታል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው “ኮማንድ ፖስት” የሀገሪቱን ጠቅላይ ሕግ ወደ ጎን ገሸሽ በማድረግ ስልጣኑን በማስፋፋት በህይወት እና በሞት የራሱን ፍርድና ፍትህ አልባ ስራ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አይደግፉም፡፡

ይህም ማለት በመጀመሪያ ደረጃ ስልጣን ከያዙበት ጊዜ ጀምሮ ስለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በማንኛውም መንገድ ስመደገፍም ሆነ ስለመንቀፍ ምንም ያሉት ነገር ያለመኖር ለእውነታው ማረጋገጫ ነው፡፡ ስለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በዚህ ትንታኔዬ በቀጣይ በስፋት የምመለስበት ይሆናል፡፡

ስለየሕግ የበላይነት መግለጫቸው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ሶስት ጠቃሚ ነጥቦችን አንስተዋል፡፡ እነርሱም፣

1ኛ) ሕጉን እንዲያከብሩ እና እንዲያስከብሩ ቃለ መሀላ ፈጽመው ወደ ስራ በሚገቡት ሰዎች ዘንድ የሕግ የበላይነትን ያለማክበር እና ስልጣናቸውን ከሕግ አግባብ ውጭ የመጠቀም ሀገር አቀፋዊ ችግር እንዳለ ምንም ሳይሸፋፍኑ በግልጽ በመናገር አምነዋል፣

2ኛ) የሕግ አስፈጻሚ አካላት ትምህርት እየተሰጣቸው እና ሞያቸውን ከፍ የሚያደርግ ስልጠና እየተሰጣቸው የሕግ የበላይነትን ተቋማዊ ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነ በመግለጫቸው ላይ አስምረውበታል፣

3ኛ) ኢትዮጵያ ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ስኬታም ሽግግር እንድታደርግ የሕግ የበላይነትን የሚያከብር አዲስ ባህል ሊመሰረት እንደሚገባ ጠንከር ያለ ንግግር አድርገዋል፡፡

ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር በጣም አስማማለሁ፡፡

ከሕግ የበላይነት ውጭ ምንም ዓይነት ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ሊኖር አይችልም፡፡ የሕግ የበላይነት ከሌለ ደግሞ ሊኖር የሚችለው አምባገነናዊነት ስለሆነ አምባገነናዊነትን መታገል ዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ መብት ነው፡፡

ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌ ሰነድ በመግቢያው ክፍል እንዲህ ይላል፣ የሰው ልጅ በአምባገነንነት እና በጭቆና ላይ ለማመጽ ብቸኛ አማራጩ በመሆኑ ላይ የሚገደድ ከሆነ  አመፁን የሚያስቀረው ሰብአዊ መብቶች በሕግ የበላይነት መጠበቅ ብቻ ነው፡፡“

የአሜሪካ የነጻነት ድንጋጌም በተመሳሳይ መልኩ እንዲህ በማለት አንድ ዓይነት አባባል አስቀምጧል፣ ማንኛውም ዓይነት መንግስት  ለእነዚህ ዓላማዎች [ህይወት፣ ነጻነት እና በደስታ የመኖር] አውዳሚ በሚሆንበት ጊዜ ሕዝቡ መንግስቱን መቀየር ወይም ደግሞ ማስወገድ መብቱ ነው፡፡ እናም የህዝቡን ደህንነት እና ደስታውን የሚያስጠብቅ አዲስ መንግስት ማቋቋም ይችላል፡፡“

በቀላሉ ማለት የተፈለገው የሕግ የበላይነት የሌለ ከሆነ የሕዝቡ ሌላው አማራጭ አመጽ ወይም ደግሞ አብዮት ማካሄድ ነው፡፡ እኔ ደግሞ በዚህ ዝርዝር ውስጥ ሕዝባዊ እምቢተኛነት እና ከመንግሥት ጋር ያለመተባበር የሚሉትን እጨምራለሁ፡፡

ይህ ማስታዋሻ ለማን እንደተጻፈ፣

ይህ ማስታዋሻ በተለይ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እንዲደርስ ዓላማ አላደረግሁም፣ ምክንያቱም እርሳቸው ስለሕግ የበላይነት በበቂ ሁኔታ ያውቃሉ፡፡ ይህንን ማሳታዋሻ በተለይ ዓላማ አድርጌ የጻፍኩት በእርሳቸው አስተዳደር ውስጥ ነን እያሉ በአሁኑ ጊዜ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አስፈላጊ እና መደረግ ይኖርበታል ለሚሉት አክራሪዎች ነው፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በኢትዮጵያ ውስጥ የሕግ የበላይነት ተቋማዊ መሆን አለበት በሚለው የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መልዕክት ላይ ተጨማሪ ኃይል በመሆን ስለወደፊቷ ኢትዮጵያ የሚጨነቁትን የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን፣ ጋዜጠኞችን እና ልሂቃንን ለመቀስቀስ አሳብ ስላለኝ ነው፡፡

ሆኖም ግን የሕግ የበላይነት ለተወሰኑ ጥቂት ልሂቃን ብቻ የሚተው ጉዳይ አይደለም፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ማህበረሰብ እንዲገነባ ለሚፈልጉ ሁሉ በኢትዮጵያ ውስጥ የሕግ የበላይነትን ተቋማዊ ለማድረግ እና ጠንካራ የሕግ የበላይነት ባህል ለመፍጠር እያንዳንዱ ግለሰብ እና አካል የድርሻውን መስራት እና ማገዝ አለበት፡፡

የሕግ የበላይነት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ወይም በፓርላማው መመሪያ ወይም ትዕዛዝ የሚከናወን ቀላል እውነታ ያለመሆኑን ሁላችንም መገንዘብ አለብን፡፡ ይኸ ጉዳይ የጠቅላላው ማህበረሰብ ጉዳይ ነው፡፡ የሕግ የበላይነት የህይወት መንገድ ነው፡፡ የሕግ የበላይነት ነገሮችን የመስራት ስልት ነው፡፡ የሕግ የበላይነት በማህበረሰቡ ውስጥ አንዳችን ከሌላችን ጋር እንድንገናኝ እንድንጣመር የሚያደርገን ቀና መንገድ ነው፡፡

እነዚህ ነገሮች ምናባዊ ከመሰሉ መገመት የሚያስፈለገው የደንብ ልብሶችን ለብሰው እና ክላሽንኮቮችን አነግተው በማህበረሰቡ ውስጥ የሚኖሩት “ሕገ መንግስት” የሚል ትንሽ ሰነድ የያዙትን ሰዎችን ሲያዩ እንዴት እንደሚፈሯቸው በማሰብ ነው፡፡

በሕግ አምላክ፡ የሕግ የበላይነት ለኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ እንደ ታሪካዊ የጀርባ አጥንት፣

ጌታቸው በቀለ “የንጉሡ ልብሶች“ በሚል ርዕስ እ.ኤ.አ በ1993 ዓ.ም በጻፉት መጽሐፋቸው በንጉሠ ነገሥት አጼ ዮሐንስ 4ኛ ዘመነ መንገሥት የሕግ የበላይነት እንዴት አድርጎ የኢትዮጵያውያን የፖለቲካ እና ማህበራዊ ህይወት መሰረት እና የጀርባ አጥንት እንደነበር እንዲህ በማለት ይገልጻል፣

“… ቀደምት አባቶቻችን በመሬት እና በሰማይ ላይ ያለውን ሁሉን ነገር ፈጣሪ በሆነው በአምላክ ላይ በጽኑ ያምኑ እና እምነቱንም በጽኑ ይከተሉ እንደነበር፣ ፍጥረቶቹን የሚገዛው አምላክም ሕግን ለፍጥረቶቹ የሚሰጥ መሆኑን፣ የእርሱን ሕጎች እንዲያስፈጽሙ ከሕዝቡ መካከል መሪዎችን የሚሾም እና በእያንዳንዱ ሰው እና በህብረተሰቡ መካከል ሰላም እና ፍቅር እንዲኖር ፍትህን እንዲያሰፍኑ የሚያደርግ እንደሆነ በጽኑ ያምኑ እና እምነቱንም ይከተሉ ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ነበር ለሕዝቡ ዋና መሪ ስዩመ እግዚአብሄር ንጉሠ ነገሥት የሚል የመጠሪያ ርዕስ ይሰጠው የነበረው፡፡ በሕግ የበላይነት ላይ የነበረው እምነት እጅግ በጣም ትልቅ ስለነበር በሕግ አምላክ ሲባል እንኳን ሰው ወራጅ ወንዝ ያቆማል ይባል ነበር፡፡

በአጼ የሐንስ 4 ዘመነ መንግሥት ፍትሀዊ አስተዳደር ለእያንዳንዱ ሰው የቤት እንስሶችን ጨምሮ ደርሶት ነበር፡፡ ንጉሠ ነገሥቱ በአስተዳደራቸው ስር ላለው ሕዝብ ተገቢው ፍትህ ስለመዘርጋቱ ከልብ ይጨነቁ ነበር፡፡ ፍትህ ተጓድሎም ከሆነ እያንዳንዱ ሰው ያለምንም ችግር በቀላሉ ወደ እርሳቸው በመሄድ አቤቱታውን እንዲያቀርብ ያደርጉ ነበር፡፡ ከእርሳቸው ቤተመንግሥት አጠገብ በቅርብ ርቀት ላይ ደወል እንዲሰቀል ትዕዛዝ በመስጠት የእርሳቸውን ትኩረት የሚስብ ነገር ሲከሰት ደወሉ እንዲደወልላቸው ያስደርጉ ነበር፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ደወሉ በተንጠለጠለበት ቋሚ ላይ አንድ አህያ ጀርባውን ሲያሻሽ ደወሉ እንዲደወል ሆነ፡፡ ንጉሠ ነገሥቱ ደወሉን የደወለውን ሰው ይዞ እንዲያመጣላቸው አንዱን አገልጋያቸውን አዘዙት፡፡ ሆኖም ግን ትዕዛዙ የተሰጠው አገልጋይ መልዕክተኛ ወደ ንጉሡ ተመልሶ በመሄድ በአካባቢው ምንም ዓይነት ሰው የለም፣ በደወሉ ማንጠልጠያ ቋሚ ስር አንድ አህያ ብቻ ቆሞ እንዳገኘ ለንጉሠ ነገሥቱ አስረዳ፡፡ ትንሽ አየር ሳብ አደረጉ እና ንጉሠ ነገሥቱ ደህና በማለት አገልጋያቸውን ተመልሰህ ሂድ እና አህያውን አምጣው በማለት አዘዙት፡፡ ሊያሰማው የሚችለው ቅሬታ ሊኖረው ይችላል አሉ፡፡ እንደተባለው አህያው ወደ ንጉሠ ነገሥቱ ተይዞ በቀረበ ጊዜ ንጉሠ ነገሥቱ የአህያው ጀርባ ላይ ቁስል ተመለከቱ፡፡ ከዚያ በኋላ ንጉሠ ነገሥቱ ይህ አህያ ጀርባው ሙሉ በሙሉ እስከሚድን ድረስ ጥንቃቄ እየተደረገለት እንዲቆይ እናም ለባለቤቱ እንዳይሰጥ የሚል ትዕዛዝ አስተላለፉ፡፡ በኋላ አህያው ወደ ባለቤቱ እንዲመለስ በተደረገ ጊዜ ከድርጊቱ ትምህርት በመውሰድ ከዚያ በኋላ እንስሳቱን በተገቢው ሁኔታ እንዲንከባከብ ትምህርት ሆኖት የንጉሠ ነገሥቱን በተግባር የተቀመረ ምክር ተግባራዊ ማድረግ ጀመረ፡፡ እንግዲህ ቀደምቶቻችን ስለፍትህ እና ስለሰብአዊነት የነበራቸው ጭንቀት እስከዚህ ድረስ ነበር

የእኔ የሕግ የበላይነት ጥበቃ በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ፣

የሕገ መንግስት የሕግ ባለሞያ ዋና ተግባሩ የሕግ የበላይነትን መጠበቅ ነው፡፡ ባለፉት 25 ዓመታት ውስጥ እንደ አሜሪካ የሕገ መንግስት የሕግ ባለሞያ በአሜሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች የሕግ የበላይነት እንዲጠበቅ ጥረት በማድረግ ወደ ሕግ አውጭው አካል እንዲተላለፍ በማድረግ እንዲሁም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ አስተምሬበታለሁ፣ ምርምር በማድረግ በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ጥበቃ ለውትወታ ስራ እንዲውል ተጠቅሜበታለሁ፡፡

እንደ ሕገ መንግሥት ባለሞያ ያለኝን ተሞክሮ በኢትዮጵያ ውስጥ የሕግ የበላይነት እና የሰብአዊ መብት እንዲከበር ሁልጊዜ ሰኞ እና አንዳንድ ጊዜም በሳምንት ሶስት ወይም አራት ጊዜ ረዥም ትችቶችን በማዘጋጀት ለ13 ዓመታት ገደማ ያህል ስጠቀምበት ቆይቻለሁ፡፡

እ.ኤ.አ በ2006 ዓ.ም “ዋና የፖሊስ መኮንኖች፣ አቃብያነ ሕጎች እና ዳኞች በፖሊስ መንግሥት“ በሚል ርእስ   ለመጀመሪያ ጊዜ ያዘጋጀሁት ትችት በኢትዮጵያ ውስጥ የሕግ የበላይነት በዘፈቀደ የሚጣስ መሆኑን ግልጽ አድርጊያለሁ፡፡ በቃሊቲ ተከሳሾች ላካዮች ላይ እየተፈጸመ ያለውን ሸፍጥ፣ በእጅ ጣት እየተመረጡ ለይስሙላ የሚሰየሙትን ዳኞች፣ የሸፍጥ ክስ ምስረታን፣ አጭበርባሪ የሆኑ አቃብያነ ሕጎችን፣ በሚመለከት ግልጽ አድርጌ ነበር፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ያሰራር ስርዓት እንደሌለ እና ውጤቱ ምን እንደሚሆን አስቀድሞ የሚታወቅ እና ይኸውም አንድ ነገር ፍትህን ማጨናገፍ እንደሆነ ግልጽ አድርጊያለሁ፡፡

እ.ኤ.አ በ2007 ሙስና በሚል ውንጀላ የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ መስራቸ አባል እና የቀድሞው የቅድመ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አገዛዝ የመከላከያ ሚኒስትር እና የማህበረ ረድኤት ትግራይ (Endowment for the Rehabilitation of Tigray) ሊቀ መንበር በነበረው በስዬ አብርሃ ላይ ተመስርቶ የነበረውን የውንጀላ ክስ እና ክሱን ተከትሎም ለ6 ዓመታት በእስር ቤት እንዲማቅቅ መደረጉን በማስመልከት የሕግ የበላይነትን የጣሰ መሆኑን በማስረጃ በማረጋገጥ ተከራክሪያለሁ፡፡ ስዬ ከማንኛውም የህወሀት አባል የበለጠ ወይም ያነሰ ሙሰኛ አልነበረም፡፡

አንድ የቆየን ተመሳስሎ በማሻሻል ይኸ ለእኔ እንዲህ የሚልን መልዕክት የሚያስተላልፍ ነበር፣ “የመለስ የጀበና ማሰሮ የስየን ማንቆርቆሪያ ጥቁር ብሎ ይጠራዋል፡፡“ የሙስና ክስ ውንጀላዎች ስዬን በፖለቲካ ለማግለል በስራ ላይ እንዲውሉ የተደረጉ መሳሪያዎች እንደሆኑ አምናለሁ፡፡ ሆኖም ግን  እኔ ስለስዬ ጥፋት ለመከላከል ወይም ደግሞ ነጻ መሆን ለመናገር አልነበረም፡፡ ሆኖም ግን እኔ የተናገርኩት ዋና ዳህራ የሚያጠነጥነው በይስሙላው ዝንጀሮ ፍርድ ቤት ስለመከሰሱ ጉዳይ ነበር፡፡ በእያንዳንዱ ጉዳይ በሚባል መልኩ በጣም ስምምነት ከሌለኝ ሰዎች ጋር ቢሆንም ቅሉ ለሕግ የበላይነት መርህ መከበር ጉዳይ ነበር የተከራከርኩት፡፡

እ.ኤ.አ ሀምሌ 2009 ዓ.ም አቅርቤው በነበረው ትችት ባራክ ኦባማ ጋና በመሄድ አስተላልፎት በነበረው እና እንዲህ በሚለው መልዕክት ላይ ጠንካራ ትችት አቅርቤ ነበር፣ ማንም ሰው ቢሆን የሕግ የበላይነት መንገዱን ለጭካኒያዊ አገዛዝ እና በሙስና ለተዘፈቀ ስርዓት በመስጠት መኖርን አይፈልግም፡፡ ይኸ ዴሞክራሲ አይደለም፡፡ ይልቁንም ይኸ ጭቆና ነው፡፡ እናም አሁን እንደዚህ ያለው ሁኔታ የሚያበቃበት ጊዜ ነው፡፡“ ያው ራሱ ኦባማ የቅድመ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አገዛዝን እ.ኤ.አ በ2015 በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠውን በማለት የስላቅ ፍረጃውን አውጇል፡፡ በቅድመ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አገዛዝ ከፍተኛ እና ዝቅተኛ ባለስልጣኖች ዘንድ አስደንጋጭ እና በእብሪት የተሞሉ የሕግ የበላይነት ጥሰቶች ነበሩ፡፡

እ.ኤ.አ ግንቦት 2010 ተደርጎ በነበረው የይስሙላ የፓርላማ ምርጫ አሁን በህይወት የሌለው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ ለአንድ ከፍተኛ የአሜሪካ ዲፕሎማት የተቃዋሚ ቡድኖች አመጽን ቢያካሂዱ እና የምርጫውን ተቀባይነት ጥላሸት የሚቀቡ ከሆነ በማለት እንዲህ ብሎ ነበር፣ “በሙሉ ኃይላችን እንደመስሳቸዋለን፡፡ እናም እንደ ብርቱካን ሚደቅሳ በእስር ቤት ውስጥ ለዘላለም ይበሰብሳሉ፡፡“

በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት የፖለቲካ መሪ የነበረችው ብርቱካን ሚደቅሳ ያለምንም ምክንያት ሆኖም ግን ከእስር ቤት በይቅርታ አልተፈታንም ብላለች በሚል ውንጀላ ብቻ ነበር የታሰረችው፡፡

እ.ኤ.አ መስከረም 2010 ዓ.ም መለስ ዜናዊ በኒዮርክ በኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ሰፊ የሆነ ሕዝባዊ ተቃውሞ እየተደረገበት ባለበት ሁኔታ መናገር ይችላል መብቱ ነው በማለት እኔ ስከራከርለት ነበር፡፡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን የመናገር መብት እያፈነ እና ጋዜጠኞችን እያሰረ ላለ ሰው እንዴት የመናገር መብቱ ሊጠበቅለት ይገባል በማለት ልትከራከርለት ትችላለህ? በማለት ተጠይቄ ነበር፡፡ የእኔ  ምላሽ ግን እንዲህ የሚል ቀላል መልስ ነበር፣ በአሜሪካ የመናገር ነጻነት መብት የሕግ የበላይነት  በስነ መንግስቱ የተረጋገጠ ነው፣ እናም በአሜሪካ ምድር ላይ የመናገር ነጻነት ለአፍሪካ አምባገነኖችም  የተሰጠ ነው የሚል ነበር፡፡

መለስ በተደጋጋሚ እና በይፋ የተቃዋሚ አመራሮች፣ ጋዜጠኞች እና ሌሎች ጉዳያቸው በይስሙላው የዝንጀሮ ፍርድ ቤት ለሚታዩት ንጹሀን ዜጎች ከዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ሕጎች እና ስምምነቶች ውጭ በዘፈቀደ ያለምንም ማስረጃ ጥፋተኞች ናቸው በማለት ይፈርጃቸው ነበር፡፡

እ.ኤ.አ ጥቅምት 2011 ዓ.ም መለስ የስዊድን ዘጋቢ ጋዜጠኛ የነበረውን ማርቲን ሽብዬን እና የፎቶግራፍ ጋዜጠኛ የነበረውን ጆህን ፔርሰንን እንዲህ በማለት ገልጿቸው ነበር፣ ቢያንስ የሽብርተኞች ታላላኪዎች ናቸው፡፡ እነርሱ ጋዜጠኞች ናቸው ከተባሉ እኔ ሽብርተኛ ምን እንደሆነ አላውቅም ማለት ነው፡፡“ ይኸ በማስረጃ ያልተደገፈ ጭፍን የሆነ ፍረጃ ክስ የተመሰረተበት ማንኛውም ሰው ጥፋተኝነቱ በማስረጃ በፍርድ ቤት እስካልተረጋገጠ ድረስ ነጻ ነው” የሚለውን የኢትዮጵያን ሕገ መንግሥት አንቀጽ 20 የሚጻረር ግልጽ ነገር ነበር፡፡ እናም እነዚህ ጋዜጠኞች ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተዋል በማለት የረዥም ጊዜ እስራት ተበይኖባቸው የነበሩ ቢሆንም በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ያልተቋረጠ ጥረት እስራታቸው እንዲቀነስ ሆኖ ከእስር ሊለቀቁ ችለዋል፡፡

ሆኖም ግን ይህ የሕግ የበላይነትን የመደፍጠጡ ሁኔታ በመለስ ዝቅተኛ ባለስለጣኖችም ላይ ደርሶ በመተግበር ላይ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ የካቲት 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አንድ የክፍለ ከተማ የፖሊስ ኃላፊ አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ከሚገኘው ከአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ስልክ በመደወል ጥያቄ ቀርቦለት የነበረ የፖሊስ ኃላፊ የሰጠውን አስደንጋጭ መልስ በማቅረብ ውይይት አድርጌበት ነበር፡፡ እርሱነቱን ይፋ ለማድረግ በመደበቅ የፖሊስ ኃላፊ ተብየው እንዲህ የሚል የማስፈራሪያ መልስ ነበር የሰጠው፣ አንተ ዋሽንግተን ቀርቶ ቤተሰማያት ብትኖር ደንታ የለኝም፡፡ የትም ብትሆን አታመልጠኝም፡፡ እዚህ አምጥቼ በቁጥጥር ስር አውልሀለሁ፡፡ ይህንን ማወቅ አለብህ ነበር ያለው አጼ በጉልበቱ፡፡

እ.ኤ.አ ነሐሴ 2013 ዓ.ም “ሙስና በኢትዮጵያ የፍትህ ዘርፍ ውስጥ“ በሚል ርዕስ አቅርቤው በነበረው ትችቴ የፍትህ ስርዓቱ በገበያ ቦታ በአንድ ሰው ጠቅላይነት እና በጥቂት ስምየለሽ፣ ፊትየለሽ፣ እና ብቃት የለሽ ሰዎች ደጋፊነት በስልጣን መንበር ላይ እራሳቸውን ደብቀው የፍትህ ስርዓቱን እንደሚገዛ እና እንደሚሸጥ ዕቃ በማድረግ ከዚህ አድርገው ሲጠቀሙበት እንደቆዩ እና ብዙም እንደማይሻል የክርክር ጭብጤን አቅርቤ ነበር፡፡ ዓለም አቀፍ የሕግ መርሆዎች እና ፍትህ ችላ የተባሉበት፣ ስህተት በሆነ መልኩ የተተረጎሙበት፣ የተጭበረበሩበት የፍትህ ስርዓት ነው፡፡

ድሆች፣ የተገለሉ ሰዎች፣ ተስፋ ያላቸው ጋዜጠኞች፣ እምቢተኞች፣ የተቃዋሚ እና የሲቪክ ማህበራት መሪዎች ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ትችት ቢያቀርብ እና ቢጮህም ቅሉ በሕጋዊ ሞት እንዲሞቱ የሚያደርግ ስርዓት ነው፡፡  የአገዛዙ መሪዎች፣ ቤተሰቦቻቸው፣ ጓደኞቻቸው እና የእነርሱ ግብረ አበሮች ከሕግ በላይ በመሆን ሕግን የእራሳቸው መጠቃሚያ መሳሪያ ሕግ ማለት እኛ ነን የሚሉበት ስርዓት ነው፡፡

እ.ኤ.አ ሀምሌ 2014 ዓ.ም “ ኢትዮጵያ፡ ልዩ የሆነ የወንጀል ድራማ“ በሚል ርዕስ የቅድመ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አገዛዝ በአንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የፈጸመውን አሳፋሪ እና ህገ ወጥ ጠለፋ በማውገዝ ጽፊያለሁ፡፡ አንዳርጋቸው ጽጌ ግንቦት ሰባት ለፍትህ፣ ለነጻነት እና ለዴሞክራሲ እየተባለ የሚጠራው የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ቡድኖች ዋና ጸሀፊ ነው፡፡ በዚያ ትችቴ ላይ የሕግ የበላይነት ትግል በኋላቀርነት፣ በጨካኝነት፣ በጉቦኝነት እና በኢሰብአዊነት የሚካሄድ የማያልቅ የሰለጠነ ትግል መሆኑን ጠቁሚያለሁ፡፡ በሕግ የበላይነት ላይ የሚደረግ ኋላቀርነት ዓይናቸውን ባፈጠጡ ገዳይ አሸባሪዎች ላይ ብቻ የሚወሰን አይደለም፡፡ ከዚህ ጋር በተመሳሳይ መልኩ የሕግ የበላይነትን ትተው የዘረፋ ሕግ የበላይነትን የሚተገብሩትም ከዚህ ጋር አንድ ናቸው፡፡

እ.ኤ.አ ግንቦት 2015 አቅርቤው በነበረው ትችት ፕሬዚዳንት ኦባማ በመንታ ምላሱ “በስልጣን ቦታው ላይ ተጣብቆ ለመቆየት በጨዋታው ግማሽ ላይ የጨዋታውን ሕግ የሚቀይር መሪ“ እና “ይህችን ሀገር አንድ አድርጎ የሚይዝ ሰው እርሱ ብቻ እንደሆነ አድርጎ የሚናገር መሪ“ በማለት ለአፍሪካ ህብረት መሪዎች ባቀረበው ንግግር ላይ የክርክር ጭብጤን አቅርቢያለሁ፡፡ በዚያው ትንፋሽ ፕሬዚዳንት ኦባማ እንዲህ ብሎ ነበር፣ “የኢትዮጵያ መንግሥት ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ የተመረጠ ነው፡፡“

እ.ኤ.አ ግንቦት 2016 “በአፓርታይድ ኢትዮጵያ ‘ሕግ’ እንደ መንግሥታዊ ሽብርተኝነት“ በሚል ርዕስ አቅርቤው በነበረው ትችቴ የሕግ የበላይነት እንዴት ባለ ሁኔታ ወደ ጭቆና ሕግ እና እምቢተኞችን ወደ ማሰቃየት ሕግ የበላይነት እንደተሸጋገረ ግልጽ አድርጊያለሁ፡፡ መንግሥት ሕጉን እምቢተኛ አመጸኞችን ጸጥ ለማድረግ እና በኃይል ለማስወገድ እምቢተኞችን፣ የተቃዋሚ አመራሮችን እና አባላትን ለብቻ ነጥሎ ያስራል፣ ነጻውን ፕሬስ ይጨቁናል፣ ጋዜጠኞችን በዘፈቀደ በቁጥጥር ስር ያውላል፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን ያለምንም ተጠያቂነት ያስወግዳል፣ የሕግ የበላይነትን ያጣምማል እናም በሕገ መንግሥት ተጠያቂነት ላይ ዘለፋ ያቀርባል፡፡ እናም ረዥም ጊዜ የሚቆይ የሕግ የበላይነት የለም፣ ያለው የአሸባሪ መንግሥት የሕግ የበላይነት ነው በማለት ተከራክሪያለሁ፡፡

እ.ኤ.አ የካቲት 2017 ዓ.ም “አሜሪካ የሕግ የበላይነትን ትርጉም ለዓለም ሕዝብ ያስተማረችበት ቀን“ በሚል ርዕስ አቅርቤው በነበረው ትችት የአሜሪካ ነጻ የፍትህ ስርዓት ስለ የሕግ የበላይነት ትርጉም ለዓለም ሕዝብ እንዴት እንዳስተማረ አሳይቻለሁ፡፡ ያንንም ያልኩት ግልጽ በሆነው ቀላል በሆነው የአገላለጽ ቋንቋ ነው፡፡ የአሜሪካ የፌዴራል የፍትህ ስርዓት የዩናይትድ ስቴትን ፕሬዚዳንት ትዕዛዝ ከሀገሪቱ ሕጎች በይበልጥም ደግሞ ከሕገ መንግሥቱ ጋር በተጣጣመ መልኩ ተግባራዊ መሆናቸውን በማያወላውል ሁኔታ ያረጋግጣል፡፡ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሀገሪቱ ጠቅላይ ሕግ ጋር ትንሽ የመተዋወቅ ችግር ይታይባቸዋል፡፡ እንደ ዋና አስፈጻሚ እና እንደ ዋና አዛዥ ፖሊሲዎችን በዘፈቀደ ያዝዛሉ፡፡ ሆኖም ግን የፌዴራል ግዛት ፍርድ ቤቶች የእርሳቸውን ትዕዛዞች አንድ በአንድ ውድቅ ያደርጓቸዋል፡፡ እንደ አፍሪካ አምባገነኖች ቃላቸው እና የጣት ቅሰራቸው ሕግ እንደሆነው ሳይሆን የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት አምባገነናዊ ትዕዛዝ ለመስጠት ስልጣን የለሽ በመሆኑ የፌዴራል ፍርድ ቤቶችን ትዕዛዝ መቀበል እና ውሳኔዎቻቸውንም መከተል አለበት ግዴታ ነው ፡፡ የአስፈጻሚው እና የሕግ አውጭው ስራዎች ለፍርድ ቤቶች ለግምገማ በሚቀርቡበት ጊዜ የሕግ የበላይነት ድል አድራጊ ይሆናል፡፡

እ.ኤ.አ በ2015 የዜጎችን መብቶች ያጎናጸፈው ሰነድ (ማግና ካርታ) 800ኛ ዓመት በዓል እኔ በማስተምርበት ዩኒቨርስቲ ግቢ ከተማሪዎቼ ጋር በሚከበርበት ጊዜ (በጠቅላላ አሜሪካ ዩኒቭርስቲዎች በዓይነቱ ብቸኛ የሆነው በዓል ያከበርንበት) ጥልቅ በሆነ ኩራት እንድሞላ አድርጎኛል፡፡ በ800ኛ ዓመት ክብረ በዓል ዕለት በማግና ካርታ ኮሚቴ ድረ ገጽ ላይ በይፋ ተለቆ የነበረው “ለኢትዮጵያ ማግና ካርታ” በሚል ርዕስ አቅርቤው የነበረው ትችቴ ለእኔ ልዩ ክብር ሰጥቶኝ ነበር፡፡

እ.ኤ.አ ሀምሌ 2017 ዓ.ም አቅርቤው በነበረው ትችቴ የታደሰ ብሩ ኬርሳሞ በእንግሊዝ አገር ውስጥ የሽብርተኝነት ውንጀላ ከምንም ጥርጣሬ በላይ የሸፍጥ የውንጀላ ክስ እንደሆነ በሕግ አደባባይ ምንም ዓይነት ጠንካራ ምርመራ ሊደረግበት የማይችል እንደሆነ ግልጽ አድርጌ ነበር፡፡ በዚያ ትችቴ የመጨረሻው ዓረፍተ ነገር ላይ እንዲህ የሚል የክርክር ጭብጥ አቅርቤ ነበር፣ “ታደሰ ብሩን የሽብርተኝነት ውንጀላ በምክንያታዊነት እና በእውነታ ላይ በመመስረት በመወንጀሉ ረገድ በሺዎች የሚቆጠሩ ጥርጣሬዎች አሉ“ ብዬ ነበር፡፡ ከኮምፒውተሩ በነጻ በማውረድ ወይም ደግሞ ከኢንተርኔት በቀላሉ ሊገዙ የሚችሉ ሰነዶችን በመያዝ ታደሰ ብሩ ጥፋተኛ ነው በማለት የሚወስን ምክንያታዊ የሆነ ምንም ዓይነት ፍርድ ቤት በእንግሊዝ ሀገር ውስጥ እንደማይኖር አውቂያለሁ፡፡ እ.ኤ.አ ታህሳስ 2017 ዓ.ም ትክክለኛ መሆኔ ተረጋገጠ፡፡ ታደሰ በየትኛውም መለኪያ በእንግሊዝ ፍርድ ቤት ጥፋተኛ ያለመሆኑ ታወቀ፡፡

እ.ኤ.አ ጥር 2018 ዓ.ም ተከታታይነት ባላቸው ትችቶቼ አማካይነት ሀገራቸውን ከአናሳ የጎሳ አፓርታይድ አገዛዝ ነጻ ለማውጣት የመጨረሻውን ከፍተኛ መስዋዕትነት በመክፈል በኢትዮጵያ የእውነት እና የዕርቅ መድረክ በማዘጋጀት የሕግ የበላይነትን መሰረት ያደረገ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲመሰርቱ ለኢትዮጵያ ወጣቶች በሙሉ በማሳወቅ እራሴን አሰማርቻለሁ፡፡

ላለፉት አስራ ሶስት ዓመታት ገደማ ያህል በኢትዮጵያ ውስጥ እንደ መዥገር በስልጣን ኮርቻ ላይ ተጣብቆ ለሚገኘው አውሬ አገዛዝ ስለሕግ የበላይነት ወንጌል ስሰብክ ቆይቻለሁ፡፡ ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የወንጌል መስበኩን ተግባር የተቀላቀሉኝ ስለሆነ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለምን መነሳት እንዳለበት የቀረቡ አስራ አምስት ምክንያቶች፣

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የመቀጠሉ ሁኔታ ለኢትዮጵያ ወጣት ሕዝቦች እና ለጠቅላላ የሀገሪቱ ሕዝቦች እንዲሁም ለዓለም አቀፋ ማህበረሰብ የቁጣ መንስኤ ሆኗል፡፡ ከዚህ በኋላ ምንም ዓይነት የሚፈጽመው ተግባር የለም፡፡ አሁኑኑ መነሳት አለበት፡፡ እዚህ ላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለምን መነሳት እንዳለበት 15 ምክንያቶችን (አስፈላጊ ሆኖ ከተገኛ መቶ ምክንያቶችን መስጠት እችላለሁ) እነሆ፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መነሳት የለበትም በማለት የሚጠይቁትን ወገኖች ለማሳመን ማንኛውንም ዓይነት ትክክለኛ የሆነ የመከራከሪያ ጭብጥ ለማቅረብ ሞክሬአለሁ፡፡ በመጨረሻም እንዲህ የሚለውን የኢትዮጵያውያን የቆየ አባባል አቀርባለሁ፣ “ምከረው ምከረው እምቢ ካለ መከራው ይምከረው፡፡“

ምክንያት ቁጥር 1 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ (martial law) ለሕግ የበላይነት ፍጹም በሆነ መልኩ ተጻራሪ ነው፡፡

የወታደራዊ ሙዚቃ ለሙዚቃ እንደሆነ ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁም ለሕግ የበላይነት ነው፡፡ ጥቂቶች  የወታደራዊ ሙዚቃ የእውነተኛ ሙዚቃ  ብለው ይቆጥሩታል፡፡

የሕግ የበላይነት ህይወትን፣ ነጻነትን እና ንብረትን ብቻ በሕግ አግባብ ማዳን እንደሚቻል ይፈቅዳል፡፡ ስህተት ናቸው ተብለው የሚገመቱ ነገሮች ሁሉ ፍትሀዊ በሆነ ችሎት እና ለማንም አድልኦ በማያደርግ የዳኛኝነት ስርዓት ሂደት መታየት አለባቸው፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሰዎችን በዘፈቀደ በቁጥጥር ስር ለማዋል፣ ለማሰር እና በአንድ ባለስልጣን ወይም በቡድን ባሉ ባለስልጣኖች (ኮማንድ ፖስት) የዘፈቀደ ግድያ እንዲፈጽሙ ይፈቅዳል፡፡ ለሕግ የበላይነት የመጨረሻ ተቃራኒው ነው፡፡ የሕግ የበላይነት ማንም ሰው የፈለገውን ያህል ከፍተኛ ስልጣን ያለው ባለስልጣን ቢሆንም ሕጉ የፈለገውን ነገር እንዲያደርግ በፍጹም አይፈቅድለትም፡፡

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ የሕግ የበላይነት የጠብመንጃ የሕግ የበላይነት እና ኮማንድ ፖስቱን የሚያዝዙት የሕግ የበላይነት ነው፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይን አባባል በመዋስ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ የደንብ ልብሶችን በለበሱ፣ ኩፍያዎችን ባደረጉ እና የክላሽንኮቭ ጠብመንጃዎችን ባነገቱ ሰዎች መገዛት ማለት ነው፡፡ የጠብመንጃ የሕግ የበላይነት ስልጣን ከሕግ የበላይነት ስልጣን የበለጠ ነው፡፡

ምክንያት ቁጥር 2 የሕግ የበላይነት ለመልካም አስተዳደር አስፈላጊ ሲሆን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መግዛት ደግሞ ፍጹም መጥፎ ዓይነት የሆነ አስተዳደር ነው፣

የሕግ የበላይነት በፖለቲካ አስተዳደር ውስጥ ፍትሀዊ እና መደበኛ በሆነ የፍትህ አስተዳደር ሂደት በማለፍ ተጠያቂነት እና ግልጸኝነትን ይጠይቃል፡፡

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ ሕዝብን ለመግዛት ብቸኛው ነገር ጠብመንጃ ነው፡፡

ቅዱሱ መጽሐፍ እንዲህ ይላል፣ “ሰይፍ የሚመዙ ሁሉ በሰይፍ ይሰየፋሉ፡፡“ በጠብመንጃ በሚገዙት ላይ ምን ሊከሰት ይችላል?

ምክንያት ቁጥር 3 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ይወድቃል፣ ምክንያቱም የኒውተንን 3 ሕግ ይጻረራል፣

የኒውተን 3ኛ ሕግ እንዲህ ይላል፣ “ለእያንዳንዱ ድርጊት እኩል የሆነ እና ተጻራሪ የሆነ ተመጣጣኝ ምላሽ አለ፡፡“ ይህም ማለት በእያንዳንዱ መስተጋብር ላይ በሁለቱ መስተጋብራዊ ነገሮች ላይ ጥንድ የሆኑ ኃይሎች አሉ፡፡ በመጀመሪያው አካል ላይ ያሉት ኃይሎች መጠን በሁለተኛው አካል ላይ ካሉት ኃይሎች መጠን ጋር እኩል ነው፡፡

በፖለቲካ ውስጥ ይህ ማለት አገዛዙ በሕዝብ ላይ የጭቆና ኃይል በሚጭንበት ጊዜ በአንድ ግዜ  ሕዝቡ ለተጫነበት ኃይል ተመጣጣኝ እና ተቃራኒ የሆነ ኃይል ይጭናል፡፡ አገዛዙ ሕዝቦችን በሚጨቁንበት ጊዜ ሕዝቡ ያንን ጭቆና ለመቋቋም ሲል እኩል የሆነ ኃይል ይጭናል፡፡ የመቋቋሚያ ኃይሉ ግልጽ የሆነ አመጽ ሊሆን ይችላል፡፡ ሕዝባዊ እምቢተኝነት ሊሆን ይችላል፡፡ ከጨቋኙ አገዛዝ ጋር ያለመተባበር ሊሆን ይችላል፡፡ ሆኖም ግን ሕዝቡ አንድ ሺ እና አንድ የሆኑ መንገዶችን በመያዝ ሊገዳደር ይችላል፡፡

በኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ እንደሚታየው ለኒውተን 3ኛ ሕግ የእኔ ተጨማሪ ሕግ “የኢትዮጵያ ወጣቶች ከተባበሩ በምንም አይነት አይሸነፉም” የሚል ነው፡፡ የተባበሩትን የኢትዮጵያ ወጣቶች ኃይል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ ሊያሸንፍ የሚችል በአምላክ አረንጓዴ ምድር ላይ ምንም ዓይነት መንገድም ኃይልም የለም፡፡

ምክንያት ቁጥር 4 እነሱን (የኢትዮጵያን አቦሸማኔ፣ ወጣቱን ትውልድ) ማሸነፍ ካልቻልክ ተቀላቀላቸው፣

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ የእኛን ወጣት ሕዝቦች ማሸነፍ አስፈላጊ አይደለም፡፡ የስነ ልቦና ችግር ያለባቸው ወላጆች ብቻ ልጆቻቸውን እስከሚሞቱ ድረስ ይደበድባሉ፣ ያስራሉ እንደዚሁም ማሰቃየት ይፈጽማሉ፡፡ መልካም ወላጆች ልጆቻቸውን በጥሞና ያዳምጣሉ በመልካም ሁኔታም ይመክሯቸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ መልካም ወላጆች ልጆቻቸው የወደፊቱ የእነርሱ እንደሆነ ግንዛቤ ይወስዳሉ፡፡

እውነታው ግልጥልጥ ብሎ ሲታይ ግን በአስቸኳጊዜ አዋጅ የሚያምኑ የእኛን ወጣቶች በቁጥጥር ስር በማዋል፣ በማሰር እና በመግደል አካሎቻቸውን እና መንፈሶቻቸውን እንደሚሰብሩ ያምናሉ፡፡  ሆኖም ግን ፍጹም ፍጹም አያሸንፉም፣ በቁጥጥር ስር አያውሉም፣ አያሰቃዩም እና በመግደል እጅ እንዲሰጡ ሊያደርጉ በፍጹም አይችሉም፡፡ ምክንያቶቹ ወጣቶቹ ግልጾች ናቸው፡፡የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማቆየት ከሚጠይቁት የበለጠ አሳቢዎች ናቸው፡፡ በጣም ተገዳዳሪዎች ናቸው፣ እናም የበለጠ ኃይል እና ጽናት አላቸው፡፡ ሊታመን በማይችል መልኩ የፈጠራ ሰዎች ናቸው፡፡ የሚፈልጉትን ለማግኘት ወደህዋላ አይሉም፡፡ የእነርሱን ዕድል እና ዕጣ ፈንታ ለመቆጣጠር ስምምነት አይኖርም፡፡ ለእነርሱ ይኸ የሞት እና የሽረት ጉዳይ ነው፡፡ ነጻነታቸውን ለማስከበር ማንኛውንም ነገር እና እያንዳንዱን ነገር ያደርጋሉ፡፡ ወይ ይሞታሉ ወይ ነጻ ይሆናሉ ሌላ ምርጫ የላቸውም፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲቀጥል የሚጠይቁት እንደዚህ ያሉ ችግሮችን ነው የፈጠሩት፡፡ የአቦ ሸማኔ ትውልዱን ልታሸንፉ የምትችሉበት ምንም ዓይነት መንገድ የለም እላለሁ፡፡ ስለሆነም ተቀላቀሏቸው!

ምክንያት ቁጥር 5 በኃይል፣ በመግደል እና ስቃይ በማድረስ የመግዛት ጊዜው አልፏል፡፡ ሕዝቦች ፍርሀቶቻቸውን ሲያስወግዱ በኃይል መግዛት ይከስማል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በአሮጌው ጊዜ ዓይነት በመግደል፣ በማሰር እና ስቃይን በማድረስ ኢትዮጵያን መግዛት የሚቻልበት ጊዜ አልፏል በማለት በተደጋጋሚ ይናገራሉ፡፡ ኢትዮጵያ በሚገዙት ሕዝቦች ስምምነት እንጅ በኃይል በፍጹም አትገዛም ብለዋል፡፡ ይህም ማለት በአሁኑ   ጊዜ እና ለዘላለም ኢትዮጵያን መግዛት የሚችል ብቸኛው መንግሥት በመግደል እና ሽብር በመፍጠር በጠብመንጃ በሚጠቀሙ ሰዎች ሳይሆን በሕገ መንግሥት ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የኢትዮጵያውያንን የልብ ትርታ ያዳምጣሉ፡፡ አስደናቂ የሆነው እና እንዲህ የሚለው የአባ ገዳ በየነን የጥያቄ መልዕክት ሰምተዋል፣ አንድ የኮማንድ ፖስት ወታደሮች ከመቶ ሚሊዮን በላይ የሚሆነውን የኢትዮጵያን ሕዝቦች ማመቅ ይችላሉን? የለም አይችሉም…“ ነበርያሉት፡፡

ሮበርት ሆልምስ የታሪክን የማይሞት ሕግ እንዲህ በማለት ገልጸውታል፣ ሕዝቦች ፍርሀቶቻቸውን ሲያስወግዱ በኃይል የመግዛት ስልጣን ይከስማል፡፡ አንተን የማይፈሩህን ሰዎች አሁንም ልትገድላቸው ትችላለህ፣ ሆኖም ግን እነርሱን ለመቆጣጠር አትችልም፡፡ የፖለቲካ ስልጣንን ስቃይን እና ችግርን በሚፈሩ እና የሁከት መሳሪያዎችን በተቆጣጠሩት ኃይሎች ፍላጎት ለመገዛት እምቢ የማይል ታዛዥነትን ይጠይቃል፡፡ ያም ኃይል ሕዝቦች ፍርሀትን እንደጉም በማትነን ሲያጠፉ ያም ስልጣን አብሮ ይጠፋል፡፡

ኢትዮጵያን በኃይል የመግዛት ጊዜው ተጠናቋል፡፡ ሕዝቦች በጨቋኞቻቸው ላይ ያላቸው ፍርሀት እንደጉም ተኗል፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲቀጥል የሚፈልጉት የወታደራዊ እና የደህንነት ኃይሎች ስልጣን ቢኖርም ኮማንድ ፖስቱ በኢትዮጵያ ቅን ትብብር እና ድጋፍ ካልሆነ በስተቀር ለመግዛት አይችልም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝቦች በሕዝባዊ እምቢተኝነት፣ በሰላማዊ መገዳደር እና ከአገዛዙ ጋር ባለመተባበር የማይበገረውን እምቢተኝነታቸውን አሳይተዋል፡፡

ኢትዮጵያን በኃይል የመግዛት ጨዋታዎች ተጠናቀዋል!

ምክንያት ቁጥር 6 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የአስቸኳይ ጊዜው እንዲራዘም የሚጠይቁት በፍርሀት ሁኔታ ላይ ለመኖራቸው ግልጽ ማረጋገጫ ነው፣

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጠቅላላ በሆነ መልኩ የሚቆጣጠር መሆኑን ዓላማ ታሳቢ በማድረግ መልዕክት ለማስተላለፍ ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡ እውነታው ፍርጥርጥ ተደርጎ ሲታይ ግን በተቃራኒው የተቃራኒውን ምስል የሚያስተላልፍ ሆኖ ይገኛል፡፡ አገዛዙ ጠቅላላ የመቆጣጠር ስዕል ያለው እንደሆነ ከሚያሳየው ይልቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አገዛዙ በፍርሀት ቆፈን ውስጥ ተወሽቆ የሚገኝ መሆኑን ያሳያል፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በመደበቅ አስተሳሰብ ውስጥ በስነ ልቦና የአስቸኳይ ጊዜ ውስጥ ሽባ ሆኖ የሚገኝ መሆኑን ያመላክታል፡፡ አገዛዙ በጠላቶች ተከቦ እንደሚገኝ እና ከእያንዳንዱ እና በእያንዳንዱ ሰው አደጋ ተደቅኖበት የሚገኝበት ዓይነት ስሜት እየተሰማው ይገኛል፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በብረታማ ጡንቻው እና የጠብመንጃ ምላጭ በሚይዝባት አመልካች ጣቱ ቀጥቅጦ ለመግዛት ይፈልግ የነበረው በፍርሀት ተቀፍድዶ ወደ ሞት ጥላ እያመራ መሆኑን ያመላክታል፡፡ በሌሊት መተኛት የማይችል እና በቀን ብርሀን ደግሞ ትከሻውን እየነፋ ለማሳየት የማይችል አገዛዝ መሆኑን ይወክላል፡፡ ምክንያቱም በፍትህ የዳኝነት ወንፊት የመበጠሪያ ቀን እየመጣች ስለሆነ ነው!

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲቀጥል የሚፈልጉት ለለውጥ ከፍተኛ የሆነ የማይናወጥ ተግዳዳሮት ያለባቸው ሕዝቡን በተለይም ደግሞ ወጣቱን ይፈራሉ፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በየቀኑ በስራ ላይ በማዋል ለወጣቱ ደፋር መስለው ለመታት ይፈልጋሉ፡፡ ይልቁንም ከባለክላሽንኮቮቹ ይልቅ በተቃራኒው ምንም ዓይነት የመሳሪያ ትጥቅ የሌለው ወጣቱ የበለጠ ኃይለኛ ሆኖ ይታያል፡፡

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለመግዛት የሚፈልጉ ሁልጊዜ እራሳቸውን በማያቋርጥ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ ያገኙታል፡፡ ሰይፍን የሚመዙ ሁሉ በሰይፍ ይሞታሉ፡፡ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሕዝብን የሚገዙ ሁሉ ምን ሊሆኑ ይችላሉ?

ምክንያት ቁጥር 7 የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በተቃራኒ ነው፣

የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በተቃራኒ ነው፡፡ ትላልቆቹ የኢትዮጵ የገንዘብ እርዳታ ለጋሾች ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በተቃራኒው ናቸው፡፡ የዩኤስ ኤምባሲ እንዲህ በማለት አውጇል፣ “ በመንግስት እየተገለጸ ያለውን ነገር የምንጋራው እና የሚያሳስበን ጉዳይ ነው፡፡ …ሆኖም ግን ምለሹ መሆን ያለበት ትልቅ ነጻነት መስጠት እንጅ ያነሰ መሆን የለበትም፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የበለጠ አሳታፊ የፖለቲካ ምህዳር ለመፍጠር በቅርቡ ተደርገው የነበሩትን አዎንታዊ እርምጃዎች የሚያቀጭጭ ነው…“ የአውሮፓ ህብረትም በተመሳሳይ መልኩ ከዚህ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተቃራኒ ነው፡፡

ምክንያት ቁጥር 8 በሌሎች ላይ የሚፈርዱ ሁሉ አንድ ቀን በእራሳቸው ላይ ይፈረዳል፣

ቅዱሱ መጽሐፍ እንዲህ ይላል፣ በሰዎች ላይ የሚፈርዱ ሁሉ በእራሳቸው ላይ ይፈረድባቸዋል፡፡ በሰፈሩት ቁና ይሰፈርላቸዋል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ እንዲህ ይላል፣ ሁሉም የዘራውን ያጭዳል እናም እንዲህ በማለት ያስጠነቅቃል፣ አባቶች በልጆች ላይ የሚፈጽሟቸው ኢፍትሀዊነት ወይም የሞራል ስብዕና ጉድለቶች ወደ ሶስተኛ እና አራተኛ ትውልድ ልጆች ላይ ይተላለፋል እንዲሁም ኃጢያተኞች ተስፋ ያጡትን ድሆች እና ያጡትን ሰዎች ለመግደል ሰይፎቻቸውን በመምዘዝ ደጋኖቻቸውን ይወድራሉ፡፡ ሰይፎቻቸው በእራሳቸው ልቦች ውስጥ ይገባሉ፣ ደጋኖቻቸውም ይሰባበራሉ፡፡“

ጋንዲ እንዲህ ብለው ነበር፣ “በታሪክ ሂደት ውስጥ  ለጊዜው ጨቋኞች እና ገዳዮች ይኖራሉ፣ እናም የማይበገሩ መስለው ይታያሉ፡፡ ሆኖም ግን በመጨረሻው ጊዜ ይወድቃሉ ሁልጊዜ፡፡“ አሁን በሰለጠነው ዘመን እንዲህ ይባላል፣ አሁን እዩኝ እዩኝ የሚል ሁሉ ኋላ ደብቁኝ ደብቁኝ የሚልበት ጊዜ ይመጣል፡፡“

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መቀጠል አለበት ብለው የሚጠይቁ ሰዎች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምን እንደሚሰሩ እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እነርሱን የሚጎዳ አይደለም ሆኖም ግን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስቀጠል ከእነርሱ ውሳኔዎች ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌላቸውን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ንጹሀን ዜጎችን እንደሚጎዳ በውል ሊያጤኑት ይገባል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲራዘም ለብዙ ጊዜ በጠየቁ ቁጥር የአስቸኳይ ጊዜ እያወጁ ሲፈርዱባቸው በኖሩት ሕዝቦች በአንድ ቀን ሊፈረድባቸው እንደሚችል እርግጠኛ መሆን አለባቸው፡፡

እንዲህ እላለሁ፣ “ወደፊት እየተራመድክ ባለህ ጊዜ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጸሐይ እንድትጠልቅ አትፍቀድ፡፡ የፍርድ ቀን አንድ ቀን እንደ ሌባ በሌሊት ከተፍ ይላልና፡፡“

ምክንያት ቁጥር 9 ምንም ዓይነት ደም መፋሰስ ሳይኖር በሰላማዊ መንገድ ለውጥ እንዲመጣ ወጣቶችን አስተምር፣ ወጣቶችን ተስፋየለሾች እና በታላቅ ጭንቀት ውስጥ እንዲገቡ በመግፋት ቆራጦች እንዲሆኑ አታድርግ፣

ዶ/ር ማርቲን ኪንግ እንዲህ ብለው ነበር፣ ሁከት  ድምፃቸው ያልይተሰማ ህዝብ ቋንቋ ነው፡፡ እናም አሜሪካ ለመስማት ያልቻለችው ወድምፅ ምንድን ነው?  የጥቁር ድሆችን ስቃይ አልሰማችም … የነጻነት እና የፍትህ ቃል ኪዳኖች ተግባራዊ መደረጋቸውን አልሰማችም ፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ስለፍትህ እና ስለሰብአዊነት የበለጠ ከመጨነቅ እና ደረጃቸውን በእኩል ዓይን ለመጠበቅ ከመበርታት ይልቅ ትልቅ ክፍል የሚሸፍኑት ለነጭ ማህበረሰቦች ሰላማዊ ሁኔታ ብቻ በመጨነቅ ስለሌሎች ሰዎች ትኩረት  አልሰጠችም ፡፡“

እኔም እንደዚሁ አንድ ዓይነት ነገር እናገራለሁ፡፡ በኢትዮጵያ እየተደረጉ ያሉ ተቃውሞዎች ባለመሰማት ቋንቋ ምክንያት የኢትዮጵያ ወጣቶች በመናገር ላይ ናቸው፡፡ ስቃዮቻቸውን በእግሮቻቸው እና በእጆቻቸው በመናገር ላይ ናቸው፡፡ ከወጣቶች ጋር ተነጋገሩ፡፡ ተንከባከቧቸው፡፡ ለእነርሱ መንገድ ቀይሱላቸው፡፡ አበረታቷቸው እናም እቀፏቸው፡፡

የዘራኸውን ታጭዳለህ:: ስልጣን በሚኖርህ ጊዜ ወጣቶችን በማሰቃየት የምታስተናግድ ከሆነ ስልጣንየለሽ በምትሆንበት ጊዜ እነርሱም በተራቸው ያሰቃዩሀል፡፡ ስልጣን ተለዋዋጭ ነገር ነው፡፡ ለማግኘት ቀላል ነው ለማጣት ደግሞ የበለጠ ቀላል ነገር ነው፡፡ ወጣት በነበርችበት ጊዜ የምትረሳት ከሆነ በኋላ ይቅርታ ልታደርግልህ አትችልም፡፡

ምክንያት ቁጥር 10 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲቀጥል በሚጠይቁት ላይ ቀጥተኛ ጨዋታ ይጫወታል፣

ወጣት ተቃዋሚዎች በሕዝባዊ እምቢተኝነት ሀገሪቱ ልትገዛ እንደማትችል ትምህርት ወስደዋል፡፡ በመንገዶች ላይ የትራፊክ ፍሰትን በመዝጋት የትራንስፖርት ስርዓቱን ማሰተጓጎል ይችላሉ፡፡ የውጭ መዋዕለ ንዋይ አፍሳሾችን ማስፈራራት ይችላሉ፡፡ ሕዝባዊ ቁጣን ለመቀስቀስ እና የበቀል እርምጃ ለመውሰድ ይችላሉ፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲቀጥል የምትጠይቁት ይብቃችሁ አለዚያ ትሰጥማላችሁ፡፡ ወጣቶች የመሰማት ስሜት እንዲሰማቸው ፍቀዱ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በተለያዩ ብዙ አጋጣሚዎች የወጣቶችን ድምጽ ሰምተዋል፡፡ መልዕክቶቻቸውንም ያገኛሉ፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲቀጥል የሚጠይቁ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር መቀላቀል አለባቸው፤ እናም ወጣቶች የተሻሉ እንዲሆኑ መፍቀድ አለባቸው፡፡

ምክንያት ቁጥር 10 ምንም ከሌለህ ምንም አታጣም፣

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወጣቶች ነጻነታቸውን እንዳጡ፣ ዕድል እንደሌላቸው እና ምንም ዓይነት የወደፊት ብሩህ ተስፋ እንደሌላቸው ይሰማቸዋል፡፡

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ 75 ሚሊዮን የሚሆኑት ወጣቶች እንደማይታዩ፣ እንደተዘለፉ፣ እንደታሰሩ እና ጠቃሚ እንዳልሆኑ ይሰማቸዋል፡፡ ወጣቶች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲቀጥል የሚጠይቁ ሰዎች የወጣቶችን የወደፊት ዕጣ ፈንታ እንደነጠቁ ዓይነት ሆነው ይሰማቸዋል፡፡

የእነርሱን ሁኔታ እንዲህ የሚሉት የቦብ ዲላን የግጥም ስንኞች በተሻለ ሁኔታ ይገልጻሉ፣ ካልነበረበት ቦታ ላይ ሆኖ ስታገኘው ሁኔታው ከባድ አይሆንም፡፡ ከአንተ ላይ ሁሉንም ነገር ከወሰደ በኋላ ሊሰርቅ ይችላል/ምንም ነገር በማታገኝበት ጊዜ በአሁኑ ጊዜ የማትታይ ሰው ነህ፣ የምትደብቀው ምንም ነገር የለም…/“

ወጣቶች ምንም ነገር እንደማያገኙ በማሰባቸው እና በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ መኖር ምንም ዓይነት ጠቀሜታ የሌለው መሆኑን በማወቃቸው ምክንያት ህይወቶቻቸውን ለማጣት ፈቃደኞች ናቸው፡፡

ምክንያት ቁጥር 11 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲቀጥል የሚጠይቁ ከማኪያቬያሊ ትምህርት መውሰድ ይገባቸዋል፡፡ ስልጡኖች ሁኑ!

ማኪያቬሊ እንዲህ በማለት ጽፏል፣

ሁለት ዓይነት የውጊያ መንገዶች እንዳሉ ማወቅ አለብህ፡፡ አንደኛው በሕግ ሌላኛው ደግሞ በኃይል፡፡ የመጀመሪያው መንገድ በሰዎች የሚካሄድ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በአውሬዎች የሚደረግ ነው፡፡ ሆኖም ግን የመጀመሪያው መንገድ ሁልጊዜ በቂ ባለመሆኑ ወደሁለተኛው መሄድ አማራጭ ነው፡፡ ስለሆንም ሁለቱንም የሰውንም ሆነ የአውሬዎችን መንገዶች እንዴት መጠቀም እንደሚቻል ማወቅ ጠቃሚ ነገር ነው ልዑል ሁለቱንም መንገዶች እንዴት እንደሚቀም ማወቅ አለበትልዑሉ የበለጠ ስለአውሬ እንዲያውቅ የሚገደድ ከሆነ ስለቀበሮ እና ስለአንበሳ የበለጠ ማወቅ ይኖርበታል፣ ምክንያቱም አንበሳ ከወጥመድ እና ቀበሮም ከተኩላዎች እራሱን መከላከል አይችልምና፡፡ አንድ ሰው ወጥመዱን ለማስታወስ ቀበሮ መሆን አለበት፣ እንደዚሁም ሁሉ ተኩላዎችን ለማስፈራራት አንበሳን መሆን አለበት፡፡ አንበሳን ለመሆን ብቻ የሚመኙ ይህንን ነገር አይገነዘቡትም፡፡ ስለሆነም ትክክለኛ ገዥ ይህንን በማድረግ ከፍላጎቱ በተቃራኒ መሆን አይፈልግም፡፡ እናም ምክንያቶቹ ወደፊት ህልውናውን እንዲያጣ ያደርጉታል፡፡ ቀበሮውን ለማነሳሳት የሚሞክሩት በተሻለ ሁኔታ ስኬታማ ይሆናሉ፡፡“

የአስቸኳ ጊዜ አዋጁ እንዲቀጥል የምትጠይቁ እንደ ጫካ አውሬ ለመሆን አትሞክሩ ወይም ደግሞ በጭካው ሕግ ለመኖር አትሞክሩ፡፡ በአሁኑ ጊዜ በሰለጠነው ህብረተሰብ መካከል ነው በመኖር ላይ ያላችሁት፡፡ ጨካኞች አትሁኑ፡፡ ስልጡኖች ሁኑ፡፡ በጫካው ወይም ደግሞ በደኑ  ሕግ ሳይሆን በሕግ የበላይነት በመመራት ኑሩ፡፡

ምክንያት ቁጥር 12 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የስድሰት ወራት ኃላፊነቱን ከፈጸመ በኋላ በሀምሌ መጨረሻ ይጠናቀቃል፡፡ ለምን በአሁኑ ጊዜ እንዲቆም በማድረግ ድልን አታውጁም!

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲቀጥል የሚጠይቁ በአሁኑ ጊዜ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲቆም በማወጅ ሁሉንም ነገር ያገኛሉ እናም የሚያጡት ነገር የለም፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አመራርነት ሰጭነት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከሕግ የበላይነት በተጻረረ መልኩ አላስፈላጊ መሆኑ እየታወቀ በሀገሪቱ መቀጠል የለበትም፡፡

በአሁኑ ጊዜ ምን አስገዳጅ ምክንያት ቢኖር ነው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲቀጥል የሚፈለገው? በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አመራ ሰጭነት ሀገሪቱ የተረጋጋ ሁኔታን አግኝታለች፡፡ እናም የእርሳቸው አመራር ሰጭነት የሕጋዊ ቅቡልነት ያለው መሆኑን ያመላክታል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ገና በሁለት ወሩ በእንጭጩ አቁሙት እናም ድልን አውጁ!

ምክንያት ቁጥር 13 ማንም ፍትሀዊ ላልሆኑ ሕጎች ላለመገዛት የሞራል ስብዕና ኃላፊነት አለበት፣

ዶ/ር ማርቲን ሉተር እንዲህ ብለው ነበር፣ የሰዎችን ስብዕና ከፍ የሚያደርግ ማንኛውም ሕግ ፍትሀዊ ሕግ ነው፡፡ የሰዎችን ስብዕና የሚያዋርድ ማንኛውም ሕግ ፍትሀዊ ሕግ አይደለም፡፡ ማንም ሰው ለፍትሀዊ ሕጎች ለመገዛት ሕጋዊ ኃላፊነት ብቻ አይደለም ያለው፡፡ ሆኖም ግን የሞራል ስብዕና ኃላፊነትም አለበት፡፡ በሌላ በኩል ፍትሀዊ ላልሆኑ ሕጎች ላለመገዛት ማንም ቢሆን የሞራል ስብዕና ኃላፊነት አለበትፍትሀዊ ላልሆኑ ሕጎች ምንም ዓይነት ሕግ የለም፡፡“

የአስቸኳይ ገዜ አዋጁ ፍትሀዊ ሕግ አይደለም፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ያለመታዘዝ የሞራል ስብዕና አላቸው፡፡ እናም ማንኛውንም ድርጊት ሁሉ በመጠቀም አዋጁን ማሽመድመድ እና እንዲወገድ ማድረግ አላባቸው፡፡

ምክንያት ቁጥር 14 ማንም ከጠላቶቹ የሚማረው ታላቅ ጉዳይ አለ፡፡ በጥሞና አዳምጡኝ!

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲቀጥል በሚጠይቁ ሰዎች ላይ እየቀለድኩ አይደለም፡፡ ከሁሉም በላይ 13 ዓመታት ገደማ ያህል ከእነርሱ ጋር አንዳንዶች እልህ አስጨራሽ እና በተጠናከረ መልኩ ብለው በሚጠሩት ሁኔታ ስታገል ቆይቻለሁ፡፡ በእኔ ትችት እነርሱ በኢትዮጵያ ሕዝቦች ከሕግ አግባብ ውጭ ሰብአዊ መብቶቻቸውን በመደፍጠጥ እና የሕግ የበላይነትን በማጥፋት ካደረሱት ስቃይ ባልበለጠ መልኩ እኔም በእውነታ ላይ በተመሰረተው ትችቴ ሳይተኙ አንድያድሩ አድርጌአቸዋለሁ፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲቀጥል የሚጠይቁ ሰዎች የእኔን ማቋረጫ የሌላቸውን የሕግ የበላይነት እና የሰብአዊ መብት መጠበቅ መልዕክቶች ይጠላሉ፡፡ እኔን የዲያስፖራ ጽንፈኛ በማለት ይጠሩኛል፡፡ የእኔን የነጻነት፣ የዴሞክራሲ እና የሰብአዊ መብቶች ዓላማ እና ትግል የሚደግፉ ሁሉ ጀግና ይሉኛል ፡፡

እኔ ጀግናም አይደለሁም፡፡ የጭራቅነት ባህሪም የለኝም፡፡ እኔ በስልጣን ላይ ላሉት እና ስልጣናቸውን ከሕግ አግባብ ውጭ ለሚተገብሩት፣ ለስልጣን ለሚቋምጡት እና ለስልጣን የለሾች እውነትን የምናገር ሰው ነኝ፡፡ ማንም ቢሆን ከጠላቱ የሚማረው ታላቅ ነገር አለ፡፡ በጥሞና አዳምጡኝ!

ምክንያት ቁጥር 15 እንደገና መልካም አጋጣሚን ላለማጣት መልካም አጋጣሚን አትጡ!

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲቀጥል ለሚጠይቁ በአሁኑ ጊዜ ወደ እርቅ እና የሰላማዊ ሽግግር ጎዳና በመግባት ነገሮችን ሁሉ ትክክል የሚያደርጉበት መልካም አጋጣሚ አለ፡፡ ስልጡን በሆነ አነጋገር አታመሰቃቅሉት!

ህልሞች እና ርዕዮች

ባለፉት 13 ዓመታት ገደማ ያህል በርካታ ትንበያዎችን አድሪጊያለሁ፡፡ በርካታዎቹ ትንበያዎቼ ተግባራዊ እየሆኑ አልፈዋል ብዬ አምናለሁ፡፡ ይህንን በመናገር ላይ ያለሁት ለእራሴ የእንኳን ደስ አለኝ መልዕክት ለማስተላለፍ አይደለም፡፡ ይህ እውነታ በተጨባጭ የተመሰከረለት ጉዳይ ነው፡፡

በጣም የምወደው እና ትልቅ ዋጋ የምሰጠው “የኢትዮጵያ አቦሸማኔዎች (ወጣቱ ትውልድ) ከተባበሩ በምንም አይነት አይሸነፉም ” የሚለው ነው፡፡ ይህንን ትንበያ ያደረግሁት እ.ኤ.አ ጥር 2013 ዓ.ም ነው፡፡

እ.ኤ.አ በ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ አቦሸማኔዎች፣ ቄሮዎች፣ ፋኖዎች፣ ዘምራዎች እና ሌሎችም እኔ ትክክለኛ መሆኔን አረጋገጡ!

እ.ኤ.አ በ2013 ዓ.ም በመጽሀፍ ቅዱስ የተጠቀሰውን በመውሰድ እንዲህ ብዬ ነበር፣ “በሰዎች ላይ ችግር የሚፈጥሩ ሁሉ ጉምን ይዘግናሉ፡፡“

እ.ኤ.አ በ2018 ዓ.ም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲቀጥል የሚጠይቁ እና በኢትዮጵያ ሕዝቦች ላይ ችግሮችን የሚፈጥሩ ሁሉ ጉምን ይዘግናሉ በማለት እተነብያለሁ!

ሆኖም ግን አሁንም ቢሆን ትክክለኛውን ነገር ለማድረግ እና ኢትዮጵያን ለመጠበቅ ጊዜ አለ፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጃችሁን በነጻነት፣ በዴሞክራሲ እና በሰብአዊ መብት አጠባበቅ አዋጆች ተኩት፡፡

“ወንዶች እና ሴቶች ልጆች ይመኛሉ፣ ሽማግሌዎች ያልማሉ፣ ወጣቶች ርዕዮችን ያያሉ“ ተብሎ ተጽፏልና፡፡

ሰላሟ የተረጋጋ ኢትዮጵያን አልማለሁ፡፡

ወጣቶች እንደ አፍሪካ ጸሐይ የሚያበራውን የኢትዮጵያን ርዕይ እውን ሆኖ ለማየት ያልማሉ!

ኦ፣ አዎ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን የማግና ካርታ (የሁሉም ኢትዮጵያውያን የነጻነት ሰነድ) ላይ እስከ አሁንም ድረስ በመስራት የሕግ የበላይነት እውን ሆኖ ለማየት እታገላለሁ!

ኢትዮጵያዊነት ዛሬ፡፡

ኢትዮጵያዊነት ነገ፡፡

ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም፡፡

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!    

ግንቦት 7 ቀን 2010 .