በፕሮፌሰር መስፍን “አዳፍኔ“ መጽሐፍ ላይ አንዳንድ የሀሳብ ፍንጣቂዎች፡ ኢትዮጵያውያንን ከእራሳቸው መጠበቅ?
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ አሁን ከቅርብ ጊዜ በፊት “አዳፍኔ፡ ፍርሀት እና መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ“ በሚል ርዕስ የተዘጋጀው እና ታትሞ የወጣው የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም የአማርኛ መጽሐፍ የኢትዮጵያ ህዝቦች በብልሹ አስተዳደር፣ በአምባገነናዊነት የጭቆና አገዛዝ እና በሞራል ስብዕና መብከት ምክንያት ተዘፍቀው ከሚገኙበት የኃጢአት ባህር ውስጥ እራሳቸውን በንስሀ በማደስ ከሀጢአት እንዲጸዱ የማያዳግም እርምጃ እንዲወስዱ የሚያሳስብ ነው፡፡ ፕሮፌሰር…