Amharic Translations Archive

2014፡ የኢትዮጵያ የአቦ-ጉማሬው ትውልድ ዓመት

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ (ክፍል አንድ) 2014 የኢትዮጵያ የአቦ –ጉማሬው ትውልድ የሚነሳሳበት ዓመት፣ እ.ኤ.አ በ2013 በመጀመሪያው ሳምንት ባቀረብኩት ሳምንታዊው ትችቴ ዓመቱ “የኢትዮጵያ የአቦሸማኔው (የወጣቱ ትውልድ) ዓመት ይሆናል “የሚል ትንበያ ሰጥቼ ነበር፡፡ እንደትንበያውም ዓመቱ የኢትዮጵያ የአቦሸማኔው (ወጣቱ) ትውልድ ታላቅ የስኬት ዓመት ሆኖ ተጠናቅቋል፡፡ 2014 ደግሞ “የኢትዮጵያ የአቦ-ጉማሬው ትውልድ ዓመት ይሆናል” የሚል ትንበያ እሰጣለሁ፡፡  የአቦ-ጉማሬው

የ2013 ዓመት የኢትዮጵያ የአቦሸማኔው (ወጣቱ ትውልድ) መነሳሳት ሲገመገም፣

ከፕሮፌሰር  አለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ እ.ኤ.አ በጃንዋሪ 2013 “እ.ኤ.አ 2013 የኢትዮጵያ የአቦሸማኔው ትውልድ ዓመት ይሆናል“ በማለት ትንበያ ሰጥቸ ነበር፡፡ እንዲህ ስልም ቃል ገብቸ ነበር፣ “የኢትዮጵያ ወጣቶች ለፍትህና ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የሚያደርጉትን ትግል ለመደገፍ እና ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ እንዲል የእራሴን ሙሉ አስተዋጽኦ እንደማደርግ እንዲሁም ትግሉ ወደ አዲስ ምዕራፍ እንዲሸጋገር ወጣቱ ትውልድ እንዲነሳሳ ሳደፋፍር ነበር፡፡”

ለኢትዮጵያ ሰማያዊ ፓርቲ ምስክርነት

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ ሰማያዊ ፓርቲን እንደፖለቲካ ድርጅት/ፓርቲ ለምን እንደምደግፈው፣ እ.ኤ.አ ዴሴምበር 15/2013 ከዋሽንግተን ዲሲ ወጣ ብላ በምትገኘው አርሊንግተን ከተማ የስብሰባ አዳራሽ በተዘጋጀው የሰማያዊ ፓርቲ የመጀመሪያ ስብሰባ ላይ ተገኝቼ  ንግግር እስካደረግሁባት ዕለት ድረስ በበርካታ ጥያቄዎች እወጠር ነበር፡፡ አንደኛው ተደጋግሞ የሚጠየቀው ጥያቄ ለበርካታ ዓመታት ገለልተኛ ሆኘ እና ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ወይም ቡድን ጋር ሳልወግን

የማንዴላ መልዕክት ለኢትዮጵያውያን ወጣቶች፣ “በፍጹም እጅ እንዳትሰጡ !…”

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም       ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ የአፍሪካው ብልህ አንበሳ እና እረፍትየለሾቹ የኢትዮጵያ አቦ ሸማኔዎች – በፍጹም እጅ እንዳትሰጡ፣ ፍቅር የነገሰበትን የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ለመገንባት ጥረታችሁን ቀጥሉ! እ.ኤ.አ ዴሴምበር 15/2013፣ ለእኔ የዓመቱ ታላቁ የኃዘን ዕለት ነው፡፡ ኔልሰን ሮሺስላሽላ ማንዴላ በደቡብ አፍሪካ በምስራቅ ኬፕ ግዛት በምትገኘው ኩኑ በምትባል ትንሽ የገጠር የትውልድ መንደራቸው በርካታ የአገር መሪዎች በተገኙበት ግብዓተ መሬታቸው

የተከበሩ አፍሪካዊ ኔልሰን ማንዴላ ስንብት!

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም ከነጻነት ለሀገሬ ኔልሰን ሮሺስላሽላ ማንዴላ ለነጻነት የሚያደርጉትን ረዥሙን ጉዞ እ.ኤ.አ በ2013 መገባደጃ ወር ላይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ደመደሙ፡፡ ፀሐይ የደቡብ አፍሪካን ሕዝብ ከአፓርታይድ የጭቆና አገዛዝ ነጻ ባወጡት ኔልሰን ማንዴላ ላይ የመጨረሻ ማህለቋን ጣለች፡፡ ኔልሰን ማንዴላ ፈለግ አቸዉን ትተውልን አልፈዋል፡፡ በጥላቻ በተዘፈቀው ዓለም፣ በማያቋርጥ ሁኔታ በፍርሃት ተሸብቦ በሚገኘው ህዝብ፣ በአምባገነኖች በሃይል ተይዞ

የሳውዲ አረቢያው ቀውስ መከሰት ለኢትዮጵያውያን ዲያስፖራ

 በፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም ከነጻነት ለሀገሬ የሳውዲ አረቢያው ቀውስ መከሰት ለኢትዮጵያውያን/ት ዲያስፖራ ፍቅርና አንድነት ትምህርት ሰጥቶ ይሆን? በአረብ አገር በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን/ት ስደተኛ ሠራተኞች ላይ የሚደረገው ህገወጥ የማሰቃየት እርምጃ በአስቸኳይ ይቁም! በአሁኑ ወቅት በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን/ት ስደተኛ ሰራተኞች ላይ በሪያድና በአዲስ አበባ ከተሞች ባሉ ገዥ አካሎች እየተፈጸመ ያለው የሰብአዊ መብት እረገጣ ከፍተኛ ቁጣን የቀሰቀሰ ከመሆኑም በላይ

ከኢትዮጵያ እሳት ወደ ሳውዲ አረቢያ እረመጥ፤ከድጡ ወደ ማጡ

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም ከነጻነት ለሀገሬ ባለፉት አስርት ዓመታት በመቶሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች በአገራቸው ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አህጉር በተለየ መልኩ ተንሰራፍቶ እየተፈጸመ ካለው ጭካኔና ርህራሄ የጎደለው አምባገነናዊ ስርዓት ለማምለጥ ሲሉ እግራቸው ወዳመራቸው አገር በመሰደድ ላይ ይገኛሉ፡፡ የኢትዮጵያ “ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር” እንደዘገበው ከሆነ እ.ኤ.አ በ2012 በግምት 200,000 ኢትዮጵያውያት ሴቶች በውጭ አገር በአብዛኛውም በመካከለኛው ምስራቅ አገሮች የውጭ

ኢትዮጵያ፣ በህዳርና በ… ሁልጊዜ አስታውሳለሁ!!

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገ/ማርያም ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ               የህዳር ወር በኢትዮጵያውያን በአሰቃቂነቱ ሁልጊዜ ሲታወስ ይኖራል፡፡ እ.ኤ.አ ኖቬምበር 2013 ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በቃላት ለመግለጽ በሚዘገንን መልኩ በኢትዮጵያውያን/ት ላይ ሰቆቃ የተፈጸመበት ወር ነው፡፡ ላለፉት ጥቂት ዓመታት በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ፣ በሚሰሩና የፖለቲካ ጥገኝነት ለመጠየቅ ጥረት በማድረግ ላይ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን/ት ላይ ስልታዊ የሆነ ጥቃት

ኢትዮጵያ፣ የመንቀሳቀስ ነጻነት የተገደበባት አገር

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም ከነጻነት ለሀገሬ ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያው ገዥ አስተዳደር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስራ ፍለጋ ወደ ውጭ አገር በሚሰደዱት ኢትዮጵያውያን/ት ላይ እገዳ በመጣል የሚከተለውን አውጇል፤ “ስራ ፍለጋ በሚል አገር ጥለው በሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮያውያት ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ የመጣውን የጉልበት ብዝበዛና የውርደት ማዕበል ለማስቆም ሲባል ለስራ በሚል ሰበብ ወደ ውጭ አገር በኢትዮጵያውያን/ት በሚደረግ

የማዕድን ሙስና በኢትዮጵያ

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም ከነጻነት ለሀገሬ በዚህ ዓመት በኢትዮጵያ ሙስናን አስመልክቶ ይሀ ለሰባተኛ ጊዜ ያቀረብኩት ትችት በማዕድኑ ዘርፍ ላይ ያተኮረ ነው፡፡ በሙስና ላይ ያቀረብኳቸውን ሌሎችን ትችቶች “Al Mariam’s Commentaries” የሚለውን ድረ ገጽ በማየት ግንዛቤ መውሰድ ይቻላል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ መዋቅራዊ ባህሪ እየያዘ በመጣው ዘርፈ ብዙ ሙስና ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት ነቅቶ እንዲጠብቅ ለማስቻል በጉዳዩ ላይ አሁንም