ጥላቻ ጥላቻን፣ ኃይል ኃይልን፣ ሕግ አልባነት ስርዓተ አልበኝነትን ይወልዳል፣
[For an English version of this post, click HERE.] ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ በዚህ ባለፈው ሳምንት አሜሪካውያን መንፈሳቸውን በሚፈታተን ክስተት ውስጥ ወድቀዋል፡፡ አሜሪካውያን አጅግ በጣም አዝነዋል፡፡ አሜሪካውያን በጥንቃቄ በማሰብ ስቃይ ውስጥ ተዘፍቀው ይገኛሉ፡፡ ሁለት አፍሪካ አሜሪካውያን ዜጎች በሁለት እምነተ ቢስ የፖሊስ ኃላፊዎች ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ መገደላቸውን ተመልክተናል፡፡ እምነተ ቢስ የፖሊስ ኃላፊዎች የሚለውን ሀረግ ላሰምርበት…