በደቡብ አፍሪካ የተፈጸመውን የሻርፕቪሌን ዕልቂት ማስታወሻ (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)
የአጣሪ ኮሚሽኑ የምርመራ ውጤቶች አስደንጋጭ እና ዘግናኝ ነበሩ፡፡ አጣሪ ኮሚሽኑ ባደረገው የማጣራት ስራ የሚከተሉት ተጨባጭ እውነታዎች መገኘታቸውን ይፋ አድርጓል፡
Amharic translations of Al Mariam’s Commentaries
የአጣሪ ኮሚሽኑ የምርመራ ውጤቶች አስደንጋጭ እና ዘግናኝ ነበሩ፡፡ አጣሪ ኮሚሽኑ ባደረገው የማጣራት ስራ የሚከተሉት ተጨባጭ እውነታዎች መገኘታቸውን ይፋ አድርጓል፡
በጋምቤላ በ99 ዓመታት በተገባው የመሬት ኪራይ ውል በደሳለኝ ዕይታ መሰረት ካሩቱሪ የሚጠበቁበት ዝርዝር ነገሮች ምንድን ናቸው? የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሁሉንም ነገር ደብቅ ስለሚያደርግ እውነታዎችን ለማረጋገጥ የምችልባቸው እውነታዎቸ የሉም፡፡
በሲባጎ እንደታሰረ አሻንጉሊት ተይዘው የሚንቀሳቀሱት እና እጅ እና እግር በሌለው አደናጋሪ ንግግራቸው የሚታወቁት “ጠቅላይ ሚኒስትር” ኃይለማርያም ደሳለኝ እ.ኤ.አ በ2015 የሚካሄደው ምርጫ “እንከንየለሽ” እንደሚሆን ያውቃሉ፡፡
(ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም) የዓለም ባንክ ይዋሻል፣ ኢትዮጵያ እጅግ በጣም አስቸጋሪ በሆነ እና “ጥላቻን፣ ንቀትን ወይም ደግሞ መከፋትን በሚቀሰቅስ ዕዳ” ውስጥ በመዘፈቅ በመሞት ላይ ትገኛለች…
(የፀሐፊው ማስታወሻ — ይህን ፅሁፍ በነጻነት ለሀገሬ ስም ለአማርኛ አንባቢዎቼ አቀርባለሁ። የነፃነት ለሀገሬ ትርጉሞች የረቀቁና የተጣሩ ናቸው። የነፃነት ለሀገሬን ድጋፍ በማግኘቴ ታላቅ ደስታና ክብር ይሰማኛል። ነፃነት ለሀገሬ ያልተዘመረለት/ያልተዘመረላቸው የኢትዮጵያ ጀግና/ጀግኖች ናቸው። ከፍተኛ ክብርና አድናቆቴን ለነፃነት ለሀገሬ አቀርባለሁ/አቀርብላቸዋለሁ! ትግሉ ይቀጥላል ለነፃነት ለሀገሬ!!!)
የሩቢዮ የኩባን ከዩኤስ አሜሪካ ጋር ያላትን ግንኙነት ወደ ቀድሞ ግንኙነት የመመለሱን ሁኔታ የመቃወማቸው አመክንዮ መረጃ ላለመስጠት በደብቅነት ወይም ደግሞ በየዋሀነት ያደረጉት ይንሁን አይሁን እርግጠኛ አይደለሁም፡፡
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ ባለፈው ሳምንት በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን/ት ቤተሰቦች ከዘመዶቻቸው እና ከጓደኞቻቸው ጋር በመሆን በኢትዮጵያ ታሪክ በመጥፎ ገጽታው ሲታወስ የሚኖረውን እ.ኤ.አ ኖቬምበር 14/1974 በኢትዮጵያውያን ላይ የተፈጸመውን የእልቂት ሰለባዎች ለማስታወስ በአንድ ላይ ተሰባስበው የጸሎት ስርዓት አድርገዋል፡፡ በዚያ የጥላቻ ዕለት የወታደራዊው አምባገነን ስብስብ ተራ ስብሰባ በማድረግ 60 ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣኖችን፣ የመንግስት…
እጅግ በጣም የተለዬ ችሎታ ያላት ወጣት ኢትዮጵያዊት የኪነ ጥበብ ባለሙያ የሆነችው ሜሮን ጌትነት ባለፈው ሳምንት “ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ጠንካራ የሆነ የአማርኛ ግጥም በዩቱቢ ድረ ገጽ በመልቀቅ እንዲነበብ አድርጋለች፡፡ ሜሮንን ለመጨረሻ ጊዜ “ያየኋት” በዚህ አሁን በያዝነው ዓመት መስከረም ወር በአንዲት ኢትዮጵያዊት ልጃገረድ ላይ በተደረገው የጠለፋ ጋብቻ ወንጀል ላይ ተመስርቶ የተሰራውን ተውኔት (ፊልም) በማስታወቂያነት እንዲያገለግል በቪዲዮ ተቀርጾ የቀረበውን ምስል ባየሁበት ጊዜ ነበር፡፡ በሀገሪቱ በስልጣን ላይ እንደ መዥገር ተጣብቆ የሚገኘው ገዥ አካል ለዚህ ጉዳይ ጆሮ ዳባ ልበስ ስላለ ያ አስቀያሚ የጠለፋ ጋብቻ ወንጀል ድርጊት አሁንም ቢሆን እንደቀጠለ ይገኛል፡፡ ድፍረት በሚለው ተውኔት ላይ ሜሮን የማትበገር የህግ ባለሙያ ገጸ ባህሪን በመላበስ ወሳኝ ሚናን በመጫወት የጥቃቱ ሰለባ ለሆነችው ልጃገረድ ነጻነት ብቻ ሳይሆን እርሷ እንደሴትነቷ የራሷን እና የሌሎችን ሴቶች ክብር ለማስጠበቅ ስኬታማ የሆነ ተውኔት ሰርታለች፡፡
መቀመጫውን በኢትዮጵያ ያደረገ አንድ ታዋቂ የአሜሪካ የዜና አውታር በቅርቡ ኮካኮላ በኢትዮጵያ እንዳይጠጣ በሚል ያሰራጨሁትን ጽሁፍ በማስመልከት የተሰማውን ቅሬታ አስመልክቶ አንድ የኢሜይል መልዕክት ላከልኝ፡፡ እንዲህ የሚል ጽሁፍ ጻፈ፣ “በድፍረት ልናገርና ሆኖም ግን ኮካኮላ እንዳይጠጣ ለማሳሰብ ስለተጻፈው ጽሁፍ ገቢራዊነት እምነት የለኝም፣ ይህንንም ጽሁፍ በማዘጋጀት በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ባለው ‘ሰይጣናዊ’ ገዥ አካል እና በ’ቅዱሳኑ በተባበሩት የተቃዋሚ ኃይሎች’ መካከል ባለው የፖለቲካ ውዝግብ በሚሊዮን ከሚቆጠሩ በጥቂቱ አንባቢዎችህን ሊያሳስት እንዲችል የታለመ ዓላማን ያዘለ ነው“ በማለት አስተያየቱን አጠቃሏል፡፡
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ በየጊዜው ተስፋቢስነቷ እየጨመረ የመጣው የአፍሪካ የወደፊት ዕጣ ፈንታአወዛጋቢ ሁኔታን ፈጥሯል፡፡ አንዳንዶቹ ጨለምተኝነትን በሚያንጸባርቅ መልኩ በሙስና በተዘፈቁ መሪዎቿ እና ሥር በሰደደው ጥልቅ ድህነት ሳቢያ በመጥፎ ሁኔታ ላይ ተንጠልጥላ ያለች ዕድለቢስ አህጉር በማለት ሲፈርጇት ሌሎቹ ብሩህ ተስፋ የሚታያቸው ሰዎች ደግሞ በአህጉሩ ለውጥ ለማምጣት ተስፋቸውን በወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል ላይ ጥለዋል፡፡ (የጸሐፊው ማስታወሻ፡ ይህ ትችት የአፍሪካ አህጉር ዕጣ ፈንታ በያዝነው ምዕተ ዓመት አጋማሽ ምን እንደሚመስል ለመገምገም ተዘጋጅቶ በፓምባዙካ…