ማስታዋሻ ቁጥር 13፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ  ዳያስፖራ ተግዳሮዎቾን ተቀብሏል፣ ተልዕኮዉን ግብ አናደርሳለን!

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

…በምዕራቡ ዓለም አንድ ስኒ ሚያኪያቶ (ቡና በወተት) 3 ወይም 4 የአሜሪካ ዶላሮች ያወጣል፡፡ ሆኖም ግን የዲያስፖራውን ማህበረሰብ አጥብቄ የምማጸነው ከዕለታዊ የማኪያቶ ፍጆታ ወጪያቸው አንድ ዶላር በመቀነስ ለሀገራቸው እንዲሰጡ ነው፡፡

የአደራ ገንዘብ/ፈንድ (Trust Fund) መመስረት እና በኢትዮጵያ እና/ወይም በአሜሪካ ሂሳቦችን መክፈት እንችላለን፡፡ እያንዳንዱ የዲያስፖራው ማህበረሰብ አባል በየዕለቱ ለማክያቶ  ከሚያወጣው ወጭ እየቀነሰ አንድ ዶላር ቢሰጠን በአንድ ቀን ውስጥ አንድ ሚሊዮን ዶላሮችን ልናገኝ እንችላለን ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት በአንድ ወር ውስጥ 30 ሚሊዮን ዶላሮችን ልናገኝ እንችላለን ማለት ነው፡፡ ይህ ገንዘብ የመንግስት በጀት አካል የሚሆን አይደለም፡፡ የአደራ ገንዘብ/ፈንድበእራሱ ገለልተኛ ቦርድ የሚተዳደር ይሆናል፡፡

በአንድ ወር ውስጥ 30 ሚሊዮን ዶላሮችን የምናገኝ ከሆነ ይህ ማለት በአካባቢው የሚገኙ እና ለእንስሳት እንኳ የማይመጥነውን ቆሻሻ ውኃ የሚጠጡ እናቶች ንጹህ የመጠጥ ውኃ ሊያገኙ ይችላሉ ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት በመኃኒት እና በአምቡላንስ እጥረት ምክንያት ህይወታቸውን የሚያጡ እናቶች አይሞቱም ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት በአንድ ሚሊዮን ዶላሮች ወይም በ30 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር አንድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መገንባት እንችላለን ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት በዲያስፖራ ገንዘብ እርዳታ በየዕለቱ አንድ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይገነባል፡፡ በአንድ ወር ውስጥ ደግሞ 30 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ይገነባሉ ማለት ነው፡፡ ይህንንም በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ አባዙት… ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እ.ኤ.አ ሀምሌ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ከፓርላማው ፊት በመገኘት ካደረጉት ንግግር የተወሰደ፡፡

“አንድ ነገር በተግባር እውን እስከሚሆን ድረስ ሁልጊዜ የማይቻል ይመስላል… አንድ ሰው ትልቅ ተራራን ከወጣ በኋላ ሌሎች በርካታ ትናንሽ ረብታዎችን መውጣት እንዳለበት ይገነዘባል፡፡” ኔልሰን ማንዴላ

                                           እንደመር!  አንቀነስ!  እንባዛ!  አንከፋፍል! 

የጸሀፊው ማስታዋሻ፣

ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እያንዳንዱ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበረሰብ አባል በቀን አንድ ዶላር እንዲያዋጣ እና በጣም ወሳኝ የሆኑ ተቋማትን ለመገንባት እና ለኢትዮጵያ ሕዝቦች አስፈላጊ የሆኑትን አገልግሎቶች ማቅረብ እንዲችል በአጽንኦ ጠይቀዋል፡፡

በዚህ ማስታዋሻ የኢትዮጵያን ዲያስፖራ መልካም ነገር እና እምነት በመወከል የሚቀርበውን ተግዳሮት እቀበላለሁ፡፡ እያንዳንዱ እና ማንኛውም መልካም ለቦና ያለው የኢትዮጵያ ዲያስፖራ የሚመጣውን ተግዳሮት ሁሉ እንደሚቀበል በሙሉ ልብ ላረጋግጥላችሁ እፈለጋለሁ፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ተግዳሮት በእያንዳንዱ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ በተቻለ መጠን ከፍተኛ ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ኢትዮጵያ አጥንቷ እስኪቀር ገንዘቧ የተጋጠ በመሆኑ ለከፍተኛ ተግዳሮት ተዳርገዋል፡፡ ኢትዮጵያ ፍጹም በሆነ የገንዘብ ቀውስ እና ውድመት በቋፍ ላይ ትገኛለች፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ኢትዮጵያን በከፍተኛ ደረጃ ያጋጠማት የውጭ ምንዛሬ እጥረት ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ይወገዳል በማለት በተደጋጋሚ አውጀዋል፡፡ ምንም ዓይነት የውጭ ምንዛሬ የለም ማለት ምንም ዓይነት ወደ ውጭ የሚወጣ ምርት የለም ማለት ነው፡፡ ምንም ዓይነት ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባ ምርት የለም እናም ከሌሎች ሀገሮች ጋር ምንም ዓይነት የንግድ ልውውጥ የለም ማለት ነው!

እ.ኤ.አ በ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ የውጭ ዕዳ 40 ቢሊዮን ዶላር ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ዕዳ እ.ኤ.አ በ2016 ዓ.ም ከሀገር ውስጥ ምርት/GDP 54.9% ደርሷል፡፡ በዩኤስ አሜሪካ፣ በቻይና፣ በአውሮፓ ህብረት እና በሌሎች ሀገሮች መካከል እየተጋጋለ ከመጣው የንግድ ውድድር ውስጥ ኢትዮጵያ የምትቀላቀል ከሆነ በቀጣዮቹ ሁለት እና ከዚያ በላይ ዓመታት ውስጥ አውዳሚ በሆነ የኢኮኖሚ ቀውስ ልትገባ ትችላለች፡፡

የፖለቲካ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አይኖረንም፡፡ ሆኖም ግን በእርግጠኝነት የኢኮኖሚ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በይፋ ያልተነገረለት ዉስጥ ነው ያለነው ፡፡ ከፍተኛ እና ስር የሰደደ ስራ አጥነት፣ ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ኢፍትሀዊ ክፍፍል፣ ከፍተኛ የሆነ የኑሮ ውድነት፣ ዝቅተኛ የኢንቨስትመንት መጠን፣ ዝቅተኛ የሆነ የወጭ ምርት አቅርቦት፣ እየጨመረ ያለ የገቢ ምርት አቅርቦት፣ የመግዛት አቅሙ የዳሸቀ/የወደቀ ገንዘብ እና የተሟጠጠ የውጭ ምንዛሬ ከሚጠቀሱት ጥቂቶች ናቸው፡፡ ይህ በጣም አደገኛ የሆነ ሁኔታ ነው፡፡

እኛ ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ “ብሄራዊ የነብስ አድን ምላሽ ሰጭ ቡድን“ መሆን አለበት፡፡

አደጋ በተከሰተ ጊዜ አስቸኳይ ምላሽ እንደሚሰጥ እንደማንኛውም የነብስ አድን ምላሽ ሰጭ ቡድን በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ላይ ተጋርጦባት ከሚገኘው የውጭ ምንዛሬ አደጋ ለማዳን የሕዝብ ባንኮችን በመጠቀም የኋላ ገንዘብ/remittance ለመላክ ዝግጁ መሆን አለብን፡፡ ታሪካዊ ጠላቶቻችን ድርቅ እና ረሀብ ሁልጊዜ እንደሚያደርጉት ሁሉ አሁን በቅርቡ ከእኛ ጋር መነጋገር ይኖርባቸዋል፡፡ ይህንን ከአድማስ ባሻገር እያንዣበበ ያለውን አደጋ ምላሽ መስጠት አለብን፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የአስተዳደር ጊዜ ውስጥ የሚነሱት የአስቸኳይ ጊዜ አደጋዎችን ዝርዝር ለማቅረብ የሚያስቸግር እና እጅግ በጣም ብዙ ነው፡፡

በትክክል ለማስቀመጥ የዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን በቀጥታ ተሳትፎ ማድረግ እና ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ አሁን እውን በሆነችው ተስፋ ያላት ኢትዮጵያ እና ለዘመናት በማያቋርጥ መልኩ የዓለም ሀገሮች ለማኝ ሆና በኖረችው ኢትዮጵያ መካከል ልዩነት ያመጣል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከታሪካዊ እና አስገራሚ ተግዳሮቶች ጋር ተፋጥጠዋል፡፡

እርሳቸው የማይቻለውን ሁሉ አድርገዋል፡፡

ከአንድ መቶ ቀናት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ያለማንም እገዛ ተራራዎችን አነቃንቀዋል፡፡

ከአንድ መቶ ቀናት ባነሰ ጊዜ ውስጥ አብዛኞቹ የአፍሪካ መሪዎች እድሜ ልካቸውን በሙሉ ካልሰሯቸው ስራዎች የበለጠ በርካታ ስራዎችን ሰርተዋል፡፡ ማስረጃው ደግሞ ማንም ሊያየው የሚችለው ግልጽ ነገር ነው፡፡

ስለሆነም በግል ለእኔ እና ለዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን በሙሉ መልዕክቱ እንዲህ የሚል ነው፡

“አብይ አህመድ ከ100 ቀናት ባነሰ ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ ግዙፍ ተራራዎችን ማንቀሳቀስ ከቻሉ እኛ ኢትዮጵያውያን የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት የአንድ ዶላር ቢል የያዙ ትናንሽ ኮረብታዎችን በ365 ቀናት ውስጥ ማንቀሳቀስ እንችላለንን? ትንሽ ሳንቲም በማውጣት እና ይህንንም በ10፣ በ50፣ በ100 እና በ1,000 በማባዛት የእርሳቸውን ተግዳሮት ማስወገድ እንችላለንን?

እስቲ ነገሮችን ከጊዜ ቀመር አካሄድ አንጻር ላስቀምጥ፡፡

እ.ኤ.አ በ2013 ዓ.ም ወደ 22,000 ገደማ አካባቢ የተማሪ ብዛት የነበረው ሀርቫርድ ዩኒቨርስቲ 6.5 ቢሊዮን ዶላር ገንዘብ የማሰባሰብ ዘመቻ አድርጎ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ በ2016 ዓ.ም ዩኒቨርስቲው ካስቀመጠው ግብ በመብለጥ ተፈጻሚ ሆኗል፡፡ በዚሁ ተመሳሳይ ጊዜ 1,100 የተማሪ ብዛት ብቻ የነበረው የሀርቫርድ ኬኔዲ የመንግስት ትምህርት ቤት/Harvard Kennedy School of Government  570 ሚሊዮን ዶላር አሰባስቧል!

እ.ኤ.አ በ2016 ዓ.ም በባልቲሞር ሜሪላንድ ትንሹ ታሪካዊ የጥቁር ኮሌጅ የሆነው ሞርጋን ስቴት ዩኒቨርስቲ 7,700 የተማሪ ብዛት የነበረው ሲሆን የገንዘብ ማሰባሰብ ዘመቻ በማድረግ 250 ሚሊዮን ዶላር አሰባስቧል፡፡ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የዚያን ገንዘብ መጠን 70 በመቶ (170 ሚሊዮን ዶላር) መሰብሰብ ችለው ነበር፡፡

እ.ኤ.አ በ1998 ደቡብ ኮሪያ ጥልቅ የሆነ የኢኮኖሚ ቀውስ ላይ ወድቃ በነበረችበት ጊዜ የደቡብ ኮሪያ ሕዝቦች ሀገራቸውን ለማዳን ተነሱ፡፡ የግላቸውን ወርቅ በመስጠት እንዲቀልጥ እና ቅርጽ እንዲወጣለት እየተደረገ ለዓለም አቀፍ ገበያዎች ለሽያጭ እንዲቀርብ ሆኗል፡፡ ደቡብ ኮሪያውያን በዚህ ዓይነት መንገድ ሀገራቸውን ከውድቀት አድነዋል፡፡

እ.ኤ.አ በ1998 ዓ.ም ደቡብ አፍሪካውያን ለሀገራቸው ካደረጉት ባላነሰ ሁኔታ እ.ኤ.አ በ2018 ዓ.ም ኢትዮጵያውያን ሀገራቸውን ይወዳሉን? ደቡብ ኮሪያውያን የቤተሰባቸውን ምርጥ ወርቅ ከቤታቸው እያወጡ ሲሰጡ ኢትዮጵያውያን ዲያስፖራ በቀን ቁራጭ ሳንቲም መክፈል ከፍተኛ ሊሆንባቸው ይችላሉን?

እኛ በውጭ ሀገር የምንገኝ ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን ብዙ የተንዛዛ ወጭ ባለማድረግ እና በመቆጠብ ለሀገራችን በማዋጣት እ.ኤ.አ ሀገራችንን ለማዳን እንነሳለንን?

በዲያስፖራው ውስጥ ከ1 – 3 ሚሊዮን የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን አሉ፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይን የውጭ ምንዛሬ እጦት ተግዳሮት ለማስወገድ በቀን ቁራጭ ሳንቲም ለማዋጣት ጥያቄ ሊቀርብ ይችላልን?

ፍጹም በሆነ መልኩ ግልጽ እንሁን፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለአንድ ወይም ለሁለት ዓመታት ለመሞከር እኛን እየለመኑን ነው፡፡

ቁራጭ ሳንቲም ባለማውጣት እኒህን ወገን ወዳድ መሪ ማስከፋት ይኖርብናልን?

ከእርሳቸው ዘንድ ፊታችንን በማዞር “እናዝናለን፣ ቁራጭ ሳንቲም አንሰጥዎትም” ማለት ይኖርብናልን? ብዙም ደስ የማያሰኝ እና ከፍ ያለ ዋጋ የተጣለበት አንድ ሲኒ ሚኪያቶ ለልጆቻችን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከመገንባት ወይም ደግሞ በድህነት ለሚማቅቁት እናቶቻችን የውኃ ጉድጓድ ከመቆፈር የበለጠ ጠቃሚ ነገር ነውን?

ለአደራ ገንዘቡ/Trust Fund ቁራጭ ገንዘብ የማያዋጣ አንድም ኢትዮጵያዊ ወንድ፣ ሴት ወይም ልጅ ይኖራል ብዬ አላምንም፡፡

ለዚህም ነው እጅግ በጣም ኩራት በተመላበት መንፈስ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እንዲህ የምላቸው፣ “ከእርስዎ ተግዳሮት ጋር ብቻ የምንጋፈጥ አይደለንም፡፡ ሆኖም ግን ከዚያም ባለፈ መልኩ እጅግ ፈጣን በሆነ መልኩ ምልሽ እንሰጥዎታለን!”

እ.ኤ.አ በ2016 ዓ.ም ወደኋላ መለስ በማለት የህዋላ ገንዘቡን/remittance በምመለከትበት ጊዜ ወዲያዉኑ ማልቀስ ነበር የፈለግሁት!

እንደ ዓለም ባንክ ዘገባ እ.ኤ.አ በ2016 ዓ.ም 93 ሚሊዮን ሕዝብ የነበራት ቬትናም 6.6 ቢሊዮን ዶላር፣ 6.5 ሚሊዮን የሕዝብ ብዛት የነበራት ኤል ሳል ቫዶር 4.1 ቢሊዮን ዶላር እና 10.6 ሚሊዮን የሕዝብ ብዛት ያላት የዶሚኒካን ሬፐብሊክ 4 ቢሊዮን ዶላር ተቀብለዋል፡፡ 102 ሚሊዮን የሕዝብ ብዛት ያላት ኢትዮጵያ የተቀበለችው 241 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነበር!!!

በእውነት ይኸ በታም አሳዛኝ ነገር ነው!

ለዚህም ነው እንግዲህ እንባዬን አውጥቸ ማልቀስ የፈልገሁት፡፡

ሆኖም ግን አላደርገውም ምክንያቱም በግል ማድረግ የምችለውን ማንኛውንም ነገር ሁሉ ማድረግ እችላለሁ፡፡ እናም ከፍተኛ ጥረቶችን በማድረግ ሀገራቸውን የሚወዱ እና መልካም ፈቃደኝነት እና እምነት ያላቸው ዲያስፖራዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲነሱ፣ በአንድነት እንዲቆሙ፣ እንዲደመሩ እና እንዲከፍሉ አደርጋለሁ፡፡ ቁራጭ ሳንቲም ለሀገራችሁ ክብር እና ለወገናችሁ ፍቅር ስትሉ ክፈሉ፡፡ መጀመሪያ አምስት ሳንቲም፣ ከዚያም አስር ሳንቲም፣ ከዚያም አንድ ዶላር፣ ከዚያም…

“እኔ ለምንድን ነው የማድርገው?” ለምትሉት (ላለፉት አስራሶስት ዓመታት ሙሉ እኔን “ለምንድን ነው በየሳምንቱ እየጻፍክ ጊዜህን የምታባክነው?” እያሉ ሲጠይቁኝ እንደነበሩት ዓይነት ማለት ነው፡፡ ያ ሁሉ ትግል ለውጥ እንዳላመጣ ለማየት አትችልም ይሉኝ ነበር። ለዚህ ምላሹ እንዲህ የሚል ጥያቄ ነው፣ “እኔ ካላደርግሁት ማን ያደርገዋል?” እኔ አደርገዋለሁ ምክንያቱም የወደፊቷ ኢትዮጵያውያን ትውልዶች የለማኝ ሀገር ዜጎች እየተባሉ በመጠራት ክብራቸውን እንዲያጡ ስለማልፈልግ ነው፡፡

ከዚህ ስሜት አንጻር ብቻዬን እንዳልሆንኩ አውቃለሁ፡፡ እኔ እንደማስበው ሁሉ እነርሱም ጉዳዩን በጥልቅ የሚያስቡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ወገኖች አሉኝ፡፡ የማስተባበሩን ስራ በበላይነት አንድ ሰው በግንባር ቀደምትነት እንዲይዘው ስለሚፈልጉ ብቻ ነው፡፡

ትክክለኛውን ነገር ለማድረግ ትክክለኛ ያልሆነ ጊዜ በፍጹም የለም፡፡

እ.ኤ.አ አሁን በያዝነው በሀምሌ ወር በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጉብኝት ጊዜ ለእያንዳንዱ ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን በተለይም በአሜሪካ ለሚኖሩ ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን ለመገናኘት ብቻ ሳይሆን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ተግዳሮት ከ365 ቀናት ለሚበልጥ ጊዜ ሊረዳ የሚችል የገንዘብ እገዛ እንድናደርግ ጥሪዬን የማቀርብ ይሆናል፡፡

እርሳቸው ከአንድ መቶ ቀናት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ተራራዎችን መውጣት የሚችሉ ከሆነ እኛ ደግሞ ቁራጭ ሳንቲሞችን በመስጠት በ365 ቀናት ውስጥ ትናንሽ ኮረብታዎችን እንውጣ!

ስለሆነም ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን ዘመቻ 100/365 (ዲኢዘ 100/365) እያልኩ ለምጠራው እራሴን ዝግጁ አድርጊያለሁ፡፡

ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ተግዳሮት በላይ የበለጠ ውጤት ሊያመጣ በሚችል መልኩ አፋቸው ባለበት ቦታ ላይ ገንዘባቸውን ያስቀምጣሉ ለሚለው መርህ እራሴን አስገዛለሁ፡፡

የጸሀፊው ግልጽ የስሜታዊነት እውቅና፣

ሁሉም ሰው ለእራሱ ግልጽ የስሜታዊነት እውቅናዎች መስጠት ከባድ ነገር ነው፡፡ የእኔም ከዚህ የተለዬ አይደለም፡፡

ዲያስፖራ ኢትዮጵያውን በቀን አንድ ዶላር ከማኪያቶ መጠጫ ሂሳባቸው በመቀነስ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ተግዳሮት ለማስወገድ ለኢትዮጵያ የገንዘብ እርዳታ እንዲሰጡ የሚለውን በምሰማበት ጊዜ እንዴት እንባየን አውጥቼ እንዳለቀስኩ ግልጽ ማድረግ አለብኝ፡፡

እውነታው ግን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እኛን አላፋጠጡንም ነበር፡፡ ቁራጭ ገንዘብ በማዋጣት የኢትዮጵያን ስቃይ እንድናግዝ (1፡38 ሰዓት የሚፈጀውን የቪዲዮ ምስል ለማየት እዚህ ጋ ይጫኑ) ቁራጭ ገንዘብ እንድናወጣ ነበር እንዲህ በማለት የለመኑን፡

በምዕራቡ ዓለም አንድ ስኒ ሚያኪያቶ (ቡና በወተት) 3 ወይም 4 የአሜሪካ ዶላሮች ያወጣል፡፡ ሆኖም ግን የዲያስፖራውን ማህበረሰብ አጥብቄ የምማጸነው ከዕለታዊ የማኪያቶ ፍጆታ ወጪያቸው አንድ ዶላር በመቀነስ ለሀገራቸው እንዲሰጡ ነው፡፡

እኔ የምጮህ ዓይነት ሰው አይደለሁም፡፡  እራሴን ጠንካራ ሰው አድርጌ እቆጥራለሁ፡፡ እንዲያውም ችግሮች በሚከሰቱበት ጊዜ የላይኛውን ከንፈሩን አክሮ እንደሚያዝ ቆፍጣና ዓይነት ወንድ፡፡ ጎበዝ ልጆች አያለቅሱም እየተባልኩ ነው ያደግሁ፡፡ ነገሮች እየከረሩ ሲሄዱ ጠንካራ ሰው እየጠነከረ እና እየጨመረ ነው የሚሄደው፡፡

ሆኖም ግን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በፓርላማው ፊት በመገኘት ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን ቁራጭ ሳንቲም እንዲሰጡ ሲለምኑ በምሰማበት ጊዜ ሁሉንም ነገር ወዲያውኑ እረሳሁት!

እኔን በጣም ጥልቅ በሆነ መልኩ የሚያሳዝነኝ እውነታ ሶስት ወር ላልሞላ ጊዜ በቢሮ ውስጥ ያልቆዩ ወጣት መሪያችንን ለማኝ የማድረጋችን ሁኔታ ነው፡፡

የአደራ ገንዘብ ሀሳብ እና ተነሳሽነት ከእኛ በዲያስፖራ ከምንኖረው በተለይም በርካታ ክህሎቶች እና ሀብቶች ካሉን ሰዎች መምጣት ነበረበት፡፡

ሆኖም ግን ተነሳሽነት ለመፍጠር ተነሳሽነቱን አንወስድም፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በማፋጠጥ ተነሳሽነቱን ወስደዋል፡፡

ኳሷን እንደጣልናት እና እንዳላነሳናት ዓይነት ስሜት ተሰምቶኛል፡፡ ሆኖም ግን ይህንን ነገር መወሰን እንችላለን!

ከዚህ የምንወስደው ትምህርት ከዚህ በኋላ ተነሳሽነቱን መውሰድ እና ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በአጠቃላይ እንዲገቡበት ማድረግ እና ለኢትዮጵያ ማድረግ የምንችለውን ሁሉ ማድረግ ነው፡፡

ከዚህም በተጨማሪ አለቅሳለሁ ምክንያቱም በስሜት ተውጨ ነበር እናም በሁኔታው ግራ ተጋብቼ ነበር፡፡

በስሜት ተውጨ ነበር ምክንያቱም ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ ሕዝብ እና እንደ ሀገር እንዴት ከታች እንደወደቅን አየሁ እና ተሰማኝ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ቁራጭ ሳንቲም ሲለምኑን መስማት ጥቂት ምሁራን በጥልቅ ስሜት እንደሚወድቁት ነገር አልነበረም፡፡ የእኛ ወጣት (42 ዓመት ዕድሜ) ጠቅላይ ሚኒስትር ሲለምኑን ዲያስፖራዎች ለሕዝቦቻችሁ አስር ሳንቲም ማጥፋት አትችሉምን?

የእርሳቸው ቃላት ከልቤ ውስጥ ጥልቅ የሆኑ ስሜቶችን እና እንቆቅልሽ የሆኑ ጥያቄዎችን ያጭርብኛል፡፡

እርሳቸው ቁራጭ ሳንቲም የሚጠይቁን ለምንድን ነው?

ከቁራጭ ሳንቲሞች በላይ የሚጠይቁን ከሆነ በእኛ ላይ ችግር ወይም መከራ እንደሚጭኑብን  ወይም ደግሞ እንደሚፈጥሩብን ያስባሉን? ለዓመት ያህል የሚዘልቅ የሳምንት ደምዎዝስ ለምንድን ነው በድፍረት ያልጠየቁን?

ምን እንደማስብ አላውቅም፡፡

ምንም ዓይነት ገንዘብ የማናጠፋ እና ከቁራጭ ሳንቲሞች በላይ የማንሰጥ አድርገው አስበውናልን? ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን እርዳታ የሚሰጥ፣ ለሰብአዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች እርዳታ የሚሰጥ የዋህ እና ለጋስ ሕዝብ መሆኑን አያውቁምን? ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ  በርካታዎቻችን ለሁሉም ዓይነት ጉዳዮች ገንዘብ የማሰባሰብ ልምድ እንዳለን የሚያውቁ ከሆነ የሚገርመኝ ይሆናል፡፡

ብዙዎቻችን ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ ውስጥ ለበጎ አድራጎት ገንዘብ የመስጠቱ ሀሳብ ከአእምሯችን ውስጥ ጠፍቷል፡፡ ለዚህም ምክንያቱ ማንኛውም የምንሰጠው ገንዘብ ሁሉ በቅድመ ጠቅላይ ሚኒስትር ጊዜ በነበረው አገዛዝ ግንኙነት ባላቸው ሰዎች በቀጥታም ሆነ ቀጥታ ባልሆነ መንገድ ይሰረቅ ስለነበረ ነው፡፡

ሆኖም ግን የእኛ ጭንቀት በአውነታ ላይ የተመሰረተ ነበር፡፡

እ.ኤ.አ ጥር 2017 አቅርቤው በነበረው ትችቴ እንደ ዩኤስኤአይዲ የምግብ እርዳታ መረጃ በኢትዮጵያ ለሰብአዊ እርዳታ ዋና አጋር የሆነው ማህበረ ረድኤት ትግራይ/Relief Society of Tigray እና የቅድመ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አገዛዝ ክንፍ የነበረው ለበርካታ አስርት ዓመታት የሰብአዊ እርዳታንውን እየቀለበሰ፣ ሙስና እና ገንዘብን ህገወጥ በሆነ መልኩ ወደ ውጭ በማስወጣት በሀፍረት የታሪክ መጎናጻፊያ ተጀቡኖ ይገኛል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መልካም የሆነ ማፋጠጥ በሕዝብ ግንዛቤ እና የቀድሞው አገዛዝ የዕርዳታ ሙስና ልምድ በተጽእኖ ስር የሚወድቅ ከሆነ በጣም የሚገርመኝ ይሆናል፡፡

ብዙ አቅም ያለንን እና ብዙ መክፈል የምንችለውን ሰዎች ለምን እንዳልጠየቁን ገርሞኛል፡፡ በእርግጥ ብዙ ከተሰጣቸው ብዙ እንደሚጠበቅ ማወቅ አለባቸው፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ላይ እንዲህ በማለት ለመጠየቅ እፈልጋለሁ፣ “እርሰዎ ከለመኑን 100 በላይ ማውጣት የሚችል ማን ነው! እርስዎ ለጠየቁት ቁራጭ ሳንቲም ለወገኖቻችን ከመቶዎች ከሺዎች ዶላር በላይ በመስጠት ተግዳሮትዎን እናስወግዳለን፡፡“

ሆኖም ግን ለእርሳቸው ልነግራቸው አልችልም ምክንያቱም እርሳቸው በ8,000 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኙ ናቸው፡፡

በዚህ ወር መጨረሻ ወደ ዩኤስ አሜሪካ በሚመጡበት ጊዜ በእርግጠኝነት ያን ገዜ እንዲህ በማለት እነግራቸዋለሁ፣ “እርስዎ ሳንቲሞች ጠየቁን እኛ ግን በሺዎች እንሰጥዎታለን!”

ይህንን እናገራለሁ ምክንያቱም ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን ያለምንም ጥርጣሬ ይረዳሉና፡፡

በነገራችን ላይ!

በእነዚህ ጥያቄዎች እራሴን እያብሰለሰልኩ ባለሁበት ጊዜ አንድ ደስ የሚል መረጃ ግልጽ ሆነልኝ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በመለመን የሚያገኙት ገንዘብ እኔ እንደማለቅሰው ሳይሆን እያንዳንዷ ቀራጭ ሳንቲም በአንድ ማሰሮ ውስጥ እንድተግባ ሆኖ ኢትዮጵያ ዳግመኛ ለማኝ እንዳትሆን በሚያደርግ መልኩ በስራ ላይ የሚውል እንደሆነ ስገነዘብ ግልጽ ሆነልኝ፡፡

ቁራጭ ሳንቲሞችን፣ አምስት ሳንቲሞችን እና አስር ሳንቲሞችን ካዋጣን እና ከሰጠን ሀገሮችን እና መንግስታትን መለመን የለብንም፡፡

በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለሲዳማ ሕዝብ ባሰሙት ንግግር እንዲህ ብለው ነበር፣ “ኢትዮጵያ ለማኝ ሀገር ናት፡፡ የውጭ ሀገሮች እንዲረዱን እንለምናለን፡፡ ለዘላለም ለማኝ ላለመሆን ጥላቻን ማቆም አለብን፡፡ እኔ፣ እኔ፣ እኔ… ማለት ማቆም አለብን፡፡ ሲዳማ በፍጹም አይለምንም በማለት አናስመስል፡፡“ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ቁራጭ ሳንቲሞችን በፍጹም አይለምኑም ነበር፡፡ ሆኖም ግን የለመኗቸውን ቁራጭ ሳንቲሞች በአንድ ላይ በማስቀመጥ በክብር በእራሳችን እግሮች እንድንቆም እና እራሳችንን እንድንችል ትምህርት ለመስጠት ነው፡፡

ታላቅ ፈገግታ እንባዬን ጠረገው፣

እ.ኤ.አ መጋቢት 2013 ዓ.ም በቅድመ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አገዛዝ ዘመን ኢትዮጵያ ለማኝ ሀገር የመሆኗን እውነታ ስሰማ ሀፍረቴን የማምንበትን ጊዜ ከእራሴ ሲሰነዘሩ የነበሩትን ቃላት አስታውሳለሁ፡፡

እ.ኤ.አ ጥቅምት 12 ቀን 2014 ዓ.ም አቅርቤው በነበረው ትችቴ ኢትዮጵያን ሊገልጹ የሚችሉ  ሀረጎችን ቀምሪያለሁ፣ “በኢትዮጵያ የሌባ መንግስት መነሳት እና መውደቅ“፡፡ የወሮበላ ዘራፊ መንግስት (የሌባ መንግስት) ሀብታሟን እና ጸጋ የነበራትን ሀገር ሙጥጥ አድርጎ በመጋጥ የምጽዋት ሀገር እንድትሆን አድርገቷል በማለት ጽፌ ነበር፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ሲለምኑ በምመለከትበት ጊዜ ኢትዮጵያ በቅድመ አብይ አገዛዝ ስር በአሰቃቂ ሁኔታ ላይ የነበረችበት ጊዜ ለእኔ በጣም አውዳሚው ነገር የነበረ እና ታዋቂው የናይጀሪያ ብሄርተኛ ጸሀፊ እና ቃል አቀባይ የነበሩት አለቃ አባፌሚ አዎሎዎ አስጠንቅቀውን እንደነበረው ዓይነት ነው፡፡

እ.ኤ.አ በ1967 ዓ.ም በ4ኛው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የመሪዎች ጉባኤ አለቃ አዎ በማያሻማ መልኩ እንዲህ በማለት አስጠንቅቀው ነበር፡

በአሁኑ ጊዜ አፍሪካ የተፎካካሪ ለማኝ ሀገሮች አህጉር ናት፡፡ ከቀድሞ ቅኝ ገዥ አለቆቻችን ከሚደረግልን አድልዎአዊ አሰራር እርስ በእርስ እንመቃቀናለን፡፡ እናም ሆን ብለን ኒዮ ኮሎኒያሊስቶችን ወደ ተለያዩ ግዛቶቻችን እንዲመጡ እና በኢኮኖሚያችን ዕጣ ፈንታ ላይ ተቆጣጣሪ እንዲሆኑ ለመጋበዝ አንዳችን በአንዳችን ላይ እንወድቃለን…

… ሉዓላዊነት የሰጠንን ስልጣን እና ተጽዕኖ ፈጣሪነት እንደዚሁም ሁሉ ዓለም አቀፉ ዲፕሎማሲ ህጋዊ ያደረጋቸውን ስልቶች እና የስልጣኔ እንቅስቃሴዎች ከግንዛቤ በማስገባት  ከደጋፊዎቻችን ብዙ እርዳታ ለማግኘት እንጥራለን፣ በእርግጥም እርዳታ ማግኘቱን ለመቀጠል መብት አድርገን እንገፋበታለን፡፡ ሆኖም ግን ስሩን ሰድዶ ያለው ጭራቃዊነት በዚያው ይቀራል እናም ከማንም ሳይሆን ከእኛው ጋር ይቀራል፡፡ ለማኝ ካልተወገደ እና ፊቱን ካላዞረ የልመና ባህሉ ዘላለማዊ ሆኖ ይቀራል፡፡ ለብዙ ጊዜ በሚለምንበት ጊዜ  የተነሳሽነት እጥረትን፣ ድፍረትን እና በእራስ የመተማመን ባህልን በማጥፋት የለማኝነት ባህሪያትን ያዳብራል፡፡

 ላፉት 27 ዓመታት ኢትዮጵያ በአፍሪክ ቁጥር 1 ለማኝ ሀገር ሆና ቆይታለች፡፡

አሁን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እንዲህ ይላሉ፣ “ምንም ዓይነት ልመና አይኖርም! ገንዘባችንን በመሰብሰብ እራሳችንን እናግዛለን፡፡

ስለሆነም በሙሉ የእራስ መተማመን ስሜት የሁሉንም ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን ማህበረሰብን በመወከል ምላሽ ለመስጠት እንዲህ የሚለውን ነጻነት ወስጃለሁ፡

“ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ፣ የእርስዎን ቀላል የሆነ የሳንቲም ቁራጭ ጥያቄ ብቻ አይደለም ምላሽ የምንሰጥዎ፡፡ ሆኖም ግን ከዚህም በተጨማሪ እጅግ በጣም አስቸኳይ በሆነ መልኩ ተግባራዊ እናደርገዋለን!”

ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን ከመጠን በላይ ተደስተዋል! ለመሄድ ዝግጁ ናቸው፣

አታምኑንምን?! ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን የእኛን ስራ ሲሰሩ ተመልከቱ!

ከመጠን በላይ ተደስተናል እናም ለመሄድ ዝግጁ ነን!

የሀምሌ 6/2018 የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን ፍጥጫ፣

ETHIOPIAN DIASPORA - FIRED UP! READY TO GO!

ETHIOPIAN DIASPORA – FIRED UP! READY TO GO!

(በጸሀፊው የተተረጎመ)

ለዲያፖራ ኢትዮጵያውያን ባቀረቧቸው ጠንካራ ስሜቶች ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እንዲህ ብለው ነበር፡

(1፡38፡50 ጊዜ የሚፈጀውን ኪሊፕ እዚህ ጋ ይጫኑ)

“… በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚኖሩ እና ሀገራቸውን ለመርዳት ፍላጎት ያላቸው ኢትዮጵያውያን ምሁራን እና ፕሮፌሽናሎች አሉ፡፡ ወደ ተግባር እንዲተረጎም አሁን እኔ እያቀረብኩ ያለሁትን ሀሳብ/ፕሮፖሳል ጉባኤው እና ሕዝቡ የሚቀበለው ከሆነ በሚቀጥሉት ዓመታት በጣም የተሻለ ልማት እናስመዘግባለን በማለት በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁ፡፡ ከፍተኛ የሆነ የልማት ዕድገት መጣኔ ለማስመዝገብ እንድንችል የሚያደርጉ መልካም አጋጣሚዎች አሉ፡፡

አንደኛ፡ ዲያስፖራው: መልካም ዕድል ያላጋጠማቸው የኢትዮጵያ ልጆች በተለያዩ ምክንያቶች በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ተሰራጭተው ይገኛሉ፡፡ በሚያጋጥሟቸው ተግዳሮቶች ምክንያት ከእኛ በሀገር ውስጥ ከምንገኘው ሕዝቦች በብዙ መልኩ የተሻለ የስራ ስነምግባር አዳብረዋል፡፡ በአረብ ሀገሮች፣ በምዕራብ እና በአፍሪካ የሚገኙ ዲያስፖራዎች ሌት እና ቀን ይሰራሉ፡፡ በዲያስፖራው ወደ ሶስት ሚሊዮን አካባቢ የሚገመቱ ኢትዮጵያውያን ይኖራሉ ተብሎ ይገመታል፡፡ ይኸ ቁጥር እርግጠኛ ባለመሆኔ ምክንያት ይህንን ቁጥር ወደ አንድ ሶስተኛ ልቀንሰው እና አንድ ሚሊዮን ዲያስፖራ ኢትዮጵያውን በማለት ልጥራው፡፡

 እነዚህ አንድ ሚሊዮን የሚሆኑ ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን በዜግነት ግዴታቸው መሰረት በተለያዩ መንገዶች በህዝብ ባንኮች በመጠቀም የህዋላ ገንዘብ/remittanceወደ ሀገራቸው ይልካሉ፡፡

ለምን?

ገንዘቡን ለመላክ ባንኮችን የምትጠቀሙ ከሆነ ያንን ገንዘብ በውጭ ምንዛሬነት ያለምንም ችግር መድሃኒት፣ ነዳጅ እና ስንዴ እንገዛበታለን፡፡

ወደ ሀገር ቤት የምትልኩትን ገንዘብ መንግሰት ለሌላ ጉዳይ ይጠቀምበታል በማለት በህገ ወጥ መንገድ የምትመርጡ ከሆነ ልትገነዘቡት የሚገባው ነገር የመንግስት ሌቦች እና ገንዘብ ያላቸው ሰዎች የምትልኩትን ገንዘብ ሁልጊዜ ያገኙታል ምክንያቱም የእናንተን ዶላር በ40 አን በ50 ብር የመቀየር ችግር የለባቸውም፡፡ ስለሆነም በህገወጥ መልክ የምትልኩት ገንዘብ በተዘዋዋሪ መንገድ እነርሱን ሲደግፍ ድሆችን ግን ይጎዳል፡፡

ሁለተኛ ህጋዊውን የምንዛሬ ተመን የምትጠቀሙ ከሆን ከአንድ ዶላር ልታጡ የምትችሉት አንድ ወይም ሁለት ብር ው፡፡ ይህም ማለት ኢትዮጵያ በከፍተኛ ሁኔታ ልታድግ ከምትችልበት ሁኔታ ጋር ሲነጻጸር እና ኢትዮጵያውያንን ከመርዳት አኳያ ምንም ማለት አይደለም፡፡

 ቀደም ሲል እንደገለጽኩት የኢትዮጵያ የመንግስት ሰራተኞች አንድ ወር ሙሉ ሰርተው የሚከፈላቸው በዲያስፖራው ያሉት ሰራተኞች በጥቂት ቀናት ወይም ሰዓታት ከሚያገኙት ክፍያ ጋር እኩል ነው፡፡ እነዚህ ሰራተኞች ለተሻለ ህይወት ወደ ውጭ ሀገር የማይሄዱ ብቻ አይደሉም ሆኖም ግን ለመውጣት እና ለመስራት የሚችሉትን ጭምር ያካትታል፡፡ በጣም ዝቅተኛ በሆነ ክፍያ የምንሰራበት ምክንያት ሀገራችን አድጋ ስናያት ከምናገኘው እርካታ አንጻር ነው፡፡ ሁላችንም እዚህ ያለነው በጣም ዝቅተኛ በሆነ ክፍያ መስራት ተገቢነት የለውም፡፡ ስለሆነም ዲያስፖራዎች በባንኮች ከሚልኩት ገንዘብ/ህዋላ ትልቅ ጠቀሜታ አለ፡፡ በመጀመሪያ በባንክ ገንዘብ መላክ በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን ወንጀለኝነት (የኮንትሮባነድ ንግድን) ይቀንሳል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ የሀገራችን የልማት ግቦች ስኬታማ እንዲሆኑ ያግዘናል፡፡ ስለሆነም ይህንን ጥያቄ ዲያስፖራዎች ይተባበራሉ እናም ተግባራዊ ያደርጉታል በሚል እሳቤ (ገንዘብ በባንኮች የመላኩን ሁኔታ) አነሳዋለሁ፡፡

 ሶስተኛ …በምዕራቡ ዓለም አንድ ስኒ ሚያኪያቶ (ቡና በወተት) 3 ወይም 4 የአሜሪካ ዶላሮች ያወጣል፡፡ ሆኖም ግን የዲያስፖራውን ማህበረሰብ አጥብቄ የምማጸነው ከዕለታዊ የማኪያቶ ፍጆታ ወጪያቸው አንድ ዶላር በመቀነስ ለሀገራቸው እንዲሰጡ ነው፡፡

 የአደራ ገንዘብ/ፈንድ መመስረት/Trust Fund እና በኢትዮጵያ እና/ወይም በአሜሪካ ሂሳቦችን መክፈት እንችላለን፡፡ እያንዳንዱ የዲያስፖራ አባል በየዕለቱ ለሚያካቶ ከመሚያወጣው ወጭ እየቀነሰ አንድ ዶላር ቢሰጠን በአንድ ቀን ውስጥ አንድ ሚሊዮን ዶላሮችን ልናገኝ እንችላለን ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት በአንድ ወር ውስጥ 30 ሚሊዮን ዶላሮችን ልናገኝ እንችላለን ማለት ነው፡፡ ይህ ገንዘብ የመንግስት በጀት አካል የሚሆን አይደለም፡፡ በእራሱ ቦርድ የሚተዳደር የአደራ ገንዘብ ነው፡፡

በአንድ ወር ውስጥ 30 ሚሊዮን ዶላሮችን የምናገኝ ከሆነ ይህ ማለት በአካባቢው የሚገኙ እና ለእንስሳት የማይመጥነውን ቆሻሻ ውኃ የሚጠጡ እናቶች ንጹህ የመጠጥ ውኃ ሊያገኙ ይችላሉ ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት በመኃኒት እና በአምቡላንስ እጥረት ምክንያት ህይወታቸውን የሚያጡ እናቶች አይሞቱም ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት በአንድ ሚሊዮን ዶላሮች ወይም በ30 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር አንድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መገንባት እንችላለን ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት በዲያስፖራ ገንዘብ እርዳታ በየዕለቱ አንድ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይገነባል፡፡ በአንድ ወር ውስጥ ደግሞ 30 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ይገነባሉ ማለት ነው፡፡ ይህንንም በአንድ ዓመት ውስጥ አባዙት፡፡ 

በሁለት ዓመታት ውስጥ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፍላጎታችንን ሙሉ በሙሉ ያሟላል ማለት ነው፡፡ 

በዚህ መንገድ ዲያስፖራዎች ለሀገራቸው ታላቅ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ለእራሳቸው ይሰራሉ፡፡ 

ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያንን እየተማጸንኩ ያለሁት በዚህ ዓይነት መንገድ ለአንድ ወይም ደግሞ ለሁለት ዓመታት ያህል እንድትረዱን ነው፡፡ አንድ ሳንቲም እንኳ እንደማይባክን ወይም ደግሞ ያለአግባብ በስራ ላይ እንደማይውል እና ለታቀደለት ዓላማ እና ጉዳይ ብቻ እንደሚውል ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ፡፡ 

የኢትዮጵያን የልመና ባህል ለማስወገድ ዋናው መንገድ ይኸ ይሆናል፡፡ አብዛኛው ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን ይህንን ለማድረግ እንደሚፈልግ ምንም ዓይነት ጥርጣሬ የለኝም፡፡ ጥንቃቄ በተመላበት ጥናት እና ዕቅድ ይህንን ማምጣት የምንችል ከሆነ ምንም ዓይነት ልመና አናደርግም፡፡ 

 ይህ ዓይነቱ እርዳታ ወይም የተቀበልነው (ባለፈው ጊዜ) ያየአይነቱ 

እርዳታ በግብርና እራሳችንን እንድንችል አያደርገንም፡፡ የእራሳችን እርዳታ ግን ያንን ነገር ሁሉ ይቀይረዋል፡፡ ስለሆነም የኢትዮጵያ ዲያስፖራ በዚህ ዓይነት መንገድ እንዲያግዘን እጠይቃለሁ…“ 

አሁን ጊዜው ጠንክሮ የመስራት ነው፣ ምንም ዓይነት ማቋረጥ ሳይኖር ለዘለቄታው ጠንክሮ መስራት ነው፣ እናም ዓይናችንን ከውዱ ነገር (የአደራ ገንዘብ) ላይ ማድረግ አለብን! 

አብይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆኑ ጊዜ ጀምሮ ትንሽ ከመቶ ቀናት በላይ እኔ እና አንድ መቶ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ስለአብይ አህመድ ፍቅር የስነልቦና ችግር ውስጥ ተዘፍቀን ያለን ሲሆን ስለእርሳቸው መናገራችንን ግን ማቆም አልቻልንም፡፡ በጧት እንነሳለን እናም መረጃ ለማግኘት የኢንተርኔት መረብን እንበረብራለን፡፡ እያንዳንዱን እንጠራ እና እንዲህ በማለት እንጠይቃለን፣ “ዛሬ ምን ሰሩ?“ ለእርሳቸው እንዲጸልይ እያንዳንዱን እንጠራለን፡፡ ሁልጊዜ ንግግሮቻችንን እንዲህ በሚል ጥያቄ እንደመድማለን፣ “እግዚአብሄር ጸሎቶቻችንን ሰማ፡፡“

ባለፉት 100 ቀናት የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ቡድን በኢትዮጵያ ውስጥ ስላመጣው አዎንታዊ ለውጥ በጣም ደስተኛ ያልሆነ ወይም ያልተመሰጠ በዲያስፖራው ውስጥ ይኖራል ብዬ አላስብም፡፡

አሁን ጊዜው ጠንክሮ የመስራት ነው፣ ምንም ዓይነት ማቋረጥ ሳይኖር ጠንክሮ መስራት ነው፣ እናም ዓይናችንን ከውዱ ነገር (የአደራ ገንዘብ) ላይ ማድረግ አለብን!

እያንዳንዱ/ዷ ዲያስፖራ ኢትዮጵያዊ/ውያት ስለአደራ ገንዘብ እንዲህ የሚል እና መጠየቅ ያለበት አንድ ጥያቄ አለ፡ “እኔ ካልሰራሁት እና ገንዘብ ካላሰባሰብኩ ማን ሊያደርገው ነው?“

በእኔ አመለካከት አብይ አህመድ ያለማንም ድጋፍ ተራራዎችን ወጥተዋል፡፡ ሊፈነዳ ተዘጋጅቶ የነበረን እሳተ ገሞራ ሊፈነዳ ጥቂት ሳምንታት ሲቀሩት ወሰኖችን እና ውቅያኖሶችን በማቋረጥ በጎረቤት ሀገሮች መካከል ሰላም ለማምጣት ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል፡፡ በሞት ጥላ ስርም ተጉዘዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከመቶ ቀናት ባነሰ ጊዜ ውስጥ የማይቻሉ ነገሮችን አከናውነዋል፡፡

ስለሆነም ሁሉም ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን የሚከተሉትን ሁለት ጥያቄዎች መመለስ አለባቸው፡ እነርሱም

1ኛ) አብይ አህመድ ከ100 ቀናት ባነሰ ጊዜ ውስጥ የማይቻሉ የሚመስሉ ነገሮችን ማድረግ ከቻሉ እኛ በ365 ቀናት መደረግ የሚችሉትን ነገሮች እንዴት ማድረግ አንችልም?

2ኛ) አብይ አህመድ የእራሳቸውን ድርሻ እናም የማንንም እርዳታ ሳያገኙ በእራሳቸው ጥረት ተራራዎችን ማንቀሳቀስ ከቻሉ እኛ ደግሞ ለኢትዮጵያ የሚበጅ ሳንቲሞችን በማዋጣት ትንንሽ ኮረብታዎችን እንዴት ማንቀሳቀስ አንችልም?

የእኔ ምላሽ እንዲህ የሚል ነው፣ “አዎ እንችላለን አብይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆኑበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ የእርሳቸው ደጋፊ እንደሆንኩ እና እስከአ ሁንም ድረስ በዚሁ የሚቀጥሉ እስከሆኑ ድረስ ከጎናቸው ነኝ፡፡“

ደህና፣ ለአደራ ገንዘብ መሰባሰብ እውን መሆን እታገላለሁ፡፡ ተግባራዊ እንዲሆን የተጠየቅሁትን ማንኛውንም ነገር ሁሉ አደርጋለሁ!

ላለፉት 13 ዓመታት የእኔን የትችት አምዶች የሚያነቡ የእኔን ክንውኖች ሲከተሉ የነበሩ እና ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ እያንዳንዱ ዲያስፖራ ኢትዮጵያዊ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ድጋፉን እንዲሰጥ እጠይቃለሁ::

ባለፉት 13 ዓመታት በዲያስፖራው የቱንም ያህል ማህበራዊ እሴት ብሰበስብም በአሁኑ ጊዜ ሁሉንም ነገር ለአብይ አህመድ እና ለኢትዮጵያ ዲያስፖራ የአደራ ገንዘብ ማስተላለፍ አለብኝ፡፡

በማስታዋሻ ቁጥር 3 ትችቴ አብይ አህመድ ለኢትዮጵያ ምን እንደሰሩ አትጠይቁ ይልቁንም እናንተ ለኢትዮጵያ ምን ልትሰሩ እንደምትችሉ ጠይቁ ብዬ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ ሚያዝያ 29 ቀን 2018 ዓ.ም የሮበርት ኬኔዲን አባባል በመውሰድ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ሁለት ዓይነት አመለካከቶች እንዳሉ እንዲህ በማለት ተናግሬ ነበር፡ “ነገሮችን ሁሉ በአሉበት ሁኔታ የሚመለከቱ እና ለምን በማለት የሚጠይቁ እና ሁሉ በፍጹም እንዳልነበሩ እና ለምን አይሆንም ብለው የሚጠይቁ“ በማለት፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ነገሮች ሁሉ እንዳልነበሩ እና ለምን እንደማይሆኑ ለምን በማለት ሁለተኛውን ዓይነት አመለካከት በማራመድ የሚጠይቁ ሰው ናቸው፡፡

የዲያስፖራ የአደራ ገንዘብ ሀሳብ በማቅረብ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በኢትዮጵያ ነገሮች ሁሉ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ችግሮች ባሉበት መታየት እንደሌለባቸው ለምን በማለት መጠየቅ አስፈላጊ እንደሆነ ግልጽ አድርገዋል፡፡

የዲያስፖራ የአደራ ገንዘብ ሀሳብ በማቅረብ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ሁሉንም ሳንቲሞቻችንን በአንድ ቋት ማስገባት እንደምንችል እና ትምህርት ቤቶችን እንደምንገነባ፣ የውኃ ጉድጓዶችን እንደምንቆፍር፣ የመድኒኃት እና የህክምና አገልግሎቶችን ለፈላጊዎቹ እንደምናቀርብ እና ወጣቶች ዕድሎችን እንዲያገኙ እና ሌሎች በርካታ ነገሮች እንደሚሰሩ ይፋ አድርገዋል፡፡

ሆኖም ግን ይህንን ርዕይ እርሳቸው ብቻቸውን እውን ሊያደርጉት አይችሉም፡፡ የእያንዳንዱን ዲያስፖራ ኢትዮጵያዊ እገዛ ይፈልጋሉ፡፡

አምስት እና አስር ሳንቲም ብቻ እንድናዋጣ ብቻ አይደለም እየጠየቁን ያሉት ሆኖም ግን ጋን በጠጠር ይደገፋል ነውና አንድ ሳንቲምም እንኳ እንድናዋጣ ነው በመጠየቅ ላይ ያሉት፡፡

በሳንቲም ታላቁን ህልም እውን እንድናደርግ በመጠየቅ እያፋጠጡን ናቸው፡፡ በእርግጥ ሳንቲም፡፡

የአብይ አህመድን ህልም ሙሉ በሙሉ እጋራዋለሁ፡፡

በኢትዮጵያዊነት ላይ በጥልቀት ስር የሰደደ የኢትዮጵያዊ ህልም ነው፡፡

እ.ኤ.አ በ2017 ዓ.ም እያንዳንዱ ሰው ስለአዲሲቷ ኢትዮጵያ ከእኔ ጋር ነብያዊ ህልም በድፍረት እንዲያልም ዝርዝር ባለ ሁኔታ ጽፌ ነበር፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ኢትዮጵያ በዓለም ትነሳለች ለማኝ ሀገር ከነበረችበት ሁኔታ እናም እውነተኛውን ዕጣ ፈንታዋን ትኖራለች እናም የአፍሪካ አንጸባራቂ ወርቅ ትሆናለች በማለት አልመዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አንድ ቀን አሁን በቅርቡ ሁሉም ኢትዮጵያውያን በወንድማማችነት እና በእህትማማችነት ሁኔታ በአንድ ጠረጴዛ ላይ እንደሚቀመጥ እና በፍቅር፣ በይቅርባይነት እና በዕርቅ በአዲስ መንገድ እንደሚጓዝ ግልጽ አድርገዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በኢትዮጵያ ውስጥ ማንም ቢሆን በጎሳው፣ በቋንቋው፣ ወይም ደግሞ መፈረጃ እንደሌለበት እና መታየት ያለበት ባለው ውስጣዊ ስብዕናው እና በሚያራምደው ባህሪው ብቻ መሆን እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የኢትዮጵያ ምርጥ ቀኖች እየመጡ መሆናቸውን ተስፋ አድርገዋል፡፡ ወጣቶቿ በኢትዮጵያዊነት መንፈስ እየተነሱ እና ኢትዮጵያን ከወደቀችበት የተስፋ መቁረጥ እና የለማኝነት መንፈስ ያነሷታል፡፡

ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ እንዳሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ “ኢትዮጵያ ተስፋ ከቆረጠችበት የድንጋይ ተራራ በኢትዮጵያ ጥላቻ ወደሚወገድበት እና ወንድማማችነት ወደ ነገሰባት ቆንጆዋ ኢትዮጵያ ትሸጋገራለች“ በማለት ተናግረዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ህልም ሙሉ በሙሉ እጋራዋለሁ፡፡

የአብይ አህመድን ህልም እውን እናድርገው! የእኛም ህልም ነው! ለማኞች ሳንሆን ንገሶች እንደነበርን እናስታውስ!

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ኢትዮጵያ የለማኝ ሀገር እንደሆነች እና ኢትዮጵያውያን ዲያስፖራ ሳንቲም እንዲያዋጡ ሲማጸኑ ልቤ በጥልቅ ስሜት ይቆስላል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ዓለም ለማኝ እንደሆንን በመናገር ላይ ነው፡፡

ከእኔ ጋር ወደኋላ በትውስታ እንድትሄዱ እጠይቃለሁ፡፡

ንጉሶች የነበርንበትን ጊዜ ታስታውሳላችሁ (እንደ ብሪያን ሙዚቃ እና የድምጽ ቅላጼ?!)

በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ የሚደልቅ ከበሮ አለ፡፡

ቀጣይነት ያለው እና ጠንካራ የሆነ ሽንፈትን የማያውቅ፡፡

ድምጹን አውቀዋለሁ ጠንካራ ምት ነው፡፡

ኢትዮጵያዊነት እምነት፡፡

በእያንዳዱ ኢትዮጵያዊ ነብስ ማስታወሻ አለ፡፡

በረዥሙ ቆሟል እኛ ልንኮራበት የምንችለው፡፡

ልወድቅ አልችልም፣ አስታውሳለሁ፡፡

ታላቅ ሆነን ተወልደናል፡፡

እናም ረዥሙ ጦርነት (የኢትዮጵያውያን የልብ የአእምሮ እና የነብስ) ተካሂዶ በድል አድራጊነት ተጠናቅቋል፡፡

በአፍካ ጸሐይ ታላቅ ሆነን እንቆማለን፡፡

[ሙዚቀኞች:]

እናም አጆቻችንን እናነሳለን፡፡

ከዚያም ሰማይን እንዳስሳለን፡፡

ሁላችንም በአንድነት የወርቅ ካባችንን ለብሰን እንደንሳለን፡፡

እናም ዓለም ሁልጊዜ እንዲያስታውሰን እናደርጋለን፡፡

ንጉሶች በነበርንበት ጊዜ ንጉሶች በነበርንበት ጊዜ፡፡

አሁን ጊዜው ነው፡፡ ይኸው የተራራው ጫፍ፡፡

አንድ ሰው በሚወጣበት ጊዜ ሌሎቹ ከላይ ከቁንጮው ላይ ወጥተዋል፡፡

በእያንዳንዷ እርምጃ ከጫፍ ለመድረስ እየቀረብን ነው፡፡

ወደ ከፍተኛው የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ፡፡

ንጉሶች የነበርንበትን ጊዜ ታስታውሳላችሁ…

እናም ረዥሙ ጦርነት (የኢትዮጵያውያን የልብ የአእምሮ እና የነብስ) ተካሂዶ በድል አድራጊነት ተጠናቅቋል፡፡

በአፍካ ጸሐይ ታላቅ ሆነን እንቆማለን፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን እንቀላቀል፡፡ ሳንቲሞችን እናሰባስብ እና በአንድ ቋት እናስቀምጥ እና በአፍሪካ ጸሐይ ላይ ንጉሶች ሆነን እንቁም፡፡

ልዩ ምስጋና፡

ባለፈው ሳምንት ስለዚህ ለወገኖቻችን ስለአደራ ገንዘብ ማሰባሰብ ጉዳይ እኔን የቀረቡኝ እና (ሌሎችም) ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርብላቸዋለሁ፡፡ እናም እንዲህ በማለት ነግረውኛል፣ “መቆየት አንችልም! አሁኑኑ መጀመር እንፈልጋለን፡፡“

ለአደራ ገንዘብ ማሰባሰብ ጽኑ አቋማችሁ፣ ልዩ በሆነው እና ፈጠራ በተቀለቀለበት ተግባራችሁ እጅግ በጣም አመሰግናለሁ፡፡

ስለአደራ ገንዘቡ አሰባሰብ አደረጃጀት እና አወቃቀር ስለእንዲሁም ዝርዝር ጉዳዩ በኢትዮጵያ መንግስት እስከሚሰራ ድረስ ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በጉጉት እንድትጠባበቁ በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡ ገንዘቡ ከፍተኛ ኃላፊነት እና ተጠያቂነት ባለበት ሁኔታ ተይዞ ለታለመለት ዓላማ እንደሚውል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አረጋግጠውልናል፡፡ እነዚህም መዋቅራዊ አሰራሮች በቅርብ ጊዜ ውስጥ በስራ ላይ ይውላሉ፡፡ እስከዚያ ድረስ ከዛሬ ጀምሮ እና በየቀኑ ለ365 ቀናት እያንዳንዷን ሳንቲም ቆጥቡ፡፡

ልዩ ማስታወቂያ፡

ጥቂት እራስ ወዳድ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት የጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ተግዳሮት በማየት እና ኢትዮጵያን ለመርዳት የአደራ ገንዘብ አሰባሳቢ ተቋም እንዲቋቋም ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያንን ገንዘብ ሲጠይቁ የራሳቸውን ሱቅ እያቋቋሙ እንዳሉ ተገንዝቢያለሁ፡፡ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ሸፍጥ ለመስራት የሚሞክሩ ካሉ በንቃት መከታተል እና ለበጎ ነገር የታሰበው ለበጎው ነገር እንዲውል ጥረት ማድረግ ጠቃሚ ነው፡፡ ስለአደራ ገንዘቡ ሁኔታ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ወይም ከሌላ ከሚመለከታቸው ባለስልጣናት ቢሮ ይፋ መግለጫ እስካልተሰጠ ድረስ ለአደራ ገንዘቡ ተብሎ የሚደረግ ማንኛውም ዓይነት ገንዘብ የማሰባሰብ ድርጊት ሙሉ በሙሉ እንዲተው ወይም በተግባር እንዳይውል፡፡

“ተግባራዊ እስከሚደረግ ድረስ ሁልጊዜ የማይቻል ይመስላል… አንድ ሰው ትልቁን ተራራ ከወጣ በኋላ ሌሎች መወጣት የሚኖርባቸው በርካታ ትናንሽ ኮረብታዎች እንዳሉ ይገነዘባል፡፡“ ኔልሰን ማንዴላ

                                                እንደመር! አንቀነስ! እንባዛ! አንከፋፍል!  

ኢትዮጵያዊነት ዛሬ፡፡

ኢትዮጵያዊነት ነገ፡፡

ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም፡፡

 

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!     

ሀምሌ 11 ቀን 2010 ዓ።ም