ኢትዮጵያ፡- ምግብ ለችጋርና ለማሰብ!

Click here for PDF

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

በቅርቡ በዋሽንግቶን ዲሲ በጂ8 አባላት በተካሄደው፤የምግብ ዋስትና ስብሰባ ላይ በዋሽንግቶን ነዋሪ የሆነው ቆፍጣና ወጣት ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ አበበ ገላው በአዳራሹ መሃል ለመሃልWhen President Obama invited the leaders of Ghana, Tanzania, Benin and Zenawi to the Summit  on May 18, few expected any meaningful outcomes. ቆሞ ለፈላጭ ቆራጩ ጨካኝ ገዢ መለስ ዜናዊ “ነጣነትለተነፈገው ምግብ ትርጉም አልባ ነው” በማለት ሕዝባዊ ጩኸት አሰምቶ ነበር። እና የአበበ አስተያየት ልክ ነው?

ፕሬዜዳንት ኦባማ በዋሽብግቶን ዲሲ፤በሜይ 18 በተካሄደው የምግብ ዋስትና ስብሰባ ላይ በአፍሪካ ስላለው ሁኔታ ለማወያየት የጋናን፤የታንዛንያን፤የቤኒንን ፕረዚደንቶች እና መለስ ዜናዊን በጋበዙበት ወቅት፤ቁምነገር ያለው ውጤት ያመጣል ብለው ያሰቡት በጣም ጥቂት: ነበሩ። በሰሚቱ ላይ ከዋይት ሃዉስ በተ መንግስት የወጣው ዘገባ “ አዲሱ የምግብ ዋስትናና የተመጣጠነ ምግብ ጥምረት የተረጋጋና ወጥነት ያለው የእርሻ ልማት እድገት በማምጣት 50 ሚሊዮን ለችጋር የተዳረጉትን ነፍሶች፤ከችጋር አውጥቶ በሚቀጥለው 10 ዓመታት ውስጥ የአፍሪካን ገዢዎች ግዴታቸውን እንዲወጡ ለማድረግና፤ለየሃገራቸው የምግብ ዋስትና ውጤታማ እቅድ በመንደፍና የግሉ ኢንቬስትመንትም ሕብረት ሁኔታዎች በሚያመቹበት ኢንቬስትመንቱ እንዲጨምር የጂ8 ቃልም ተጠብቆ ለአፍሪካ ፈጣንና አቅመ ብዙ የሆነ ዘላቂነት ያለው የእርሻ ልማት ማስገኘት ነው::”

በዓለም  ታዋቂ ፤ታላላቅ  ህብረ ብሄራዊ  የሆኑ በርካታ የምግብ ኩባንያዎች <<እንደ ሽርክናው አካል>> ካርጊል፤ ዱፖንት፤ ሞንሳንቶ፤ ሲንጌንታ ኤጂ የአፍሪካን የእርሻ እድገት ለማገዝ የግሉ ዘርፍ የአፍሪካን የእርሻ ልማት ማገዣ የውል  ዴክሌሬሽን>> ፈርመዋል።  በ2010 በወጣው የዩ ኤስ ኤይድ መግለጫ መሰረት በኢትዮጵያ ውስጥ  በገጠሩ ከ10 ውስጥ ስምንቱ 0.93 ሄክታር ይዞታ ላይ ይኖራል።ይሄውም አናሳ የመሬት ይዞታ ለብዙሃኔ ኢትዮጵያውያን እጅጉን አስፈላጊውን ምርት የሚያርቡ ናቸው። አዲሱ ጥምረት ማለትም ካርጊል፤ ዱፖንት፤ ሞንሳንቶ፤ክራፍት፤ዩኒሊቨር፤ሲንጌንታ፤ኤጂ እና ሌሎችም የእርሻ ሕብረብሄራዊዎች አፍሪካን ከችጋር ለመታደግ፤ረሃብን ለመከላከል፤እና ራሳቸውን ለማስቻል የአፍሪካን ለም መሬቶች በሊዝ ይይዛሉ። ታዲያ ትንንሽ ቦታዎች የያዙት አፍሪካውያን የታላላቆቹን ኩባንያዎች የእርሻ ንግድ ሊቁዋቁዋሙት ይቻላቸዋል?

በኢትዮጵያ ወስጥ ያለውን የርሃብና የችጋር ሁኔታ በተመለከተ፤መደበኛ የሆነው የገዢው ፓርቲና ዓለም አቀፍ ረጂዎች ምላሽና መሸሻ መንገዳቸው፤በሃገሪቱ ያለውን እውነታ ችጋር ማር በመቀባት፤አለሳልሰውና አሳስተው፤ (ስር የሰደደ የተመጣጣነ ምግብ እጦት፤<<የምግብ ዋስትና>> ምናምን በማለት ይሸፋፍኑታል። “የአፍሪካ የችጋር ጨዋታ በካምፕ ዴቪድ” የሚለውን የኔን ጦማር ይመልከቱ።) የተፈጥሮ ሃይላትን በመውቀስ ማለቂያ የሌለውን ምጥዋት ማቅረብ። በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ለሚከሰተው ችጋርና የተራቡ ምስኪኖች እልቂት መጥፎ አስተዳደሩ አንድም ጊዜ ተወቃሽ ሆኖ አያውቅም ::  ባለፈው ሳምንት የዓለም አቀፉ የምግብ ፕሮግራም (WFP)  በኢትዮጵያ ዘገባው በሃገሪቱ ውስጥ <<3.2 ሚሊዮን ዜጎች ለምግብ እጦት ይዳረጋሉ፤ለዚህም  (WFP) የዓለም የምግብ ፕሮግራም ተጨማሪ 183 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለምግብ ዋስትናው ያስፈልገዋል።

የመለስ ዜናዊ የእርሻ ሃላፊ ምትኩ ካሳ የወቅቱን የምግብ ዋስትና እጦት በድርቅ ላይ፤ በዝናቡ መጥፋት፤በዝናቡ ወቅቱን ባለመጠበቁ አሳሰቦትል። “ይህን መሰሉ የመሸሻና ድክመትን የመደበቅ ሰበብ ደግሞ  ለእኛ አዲስ ነገር አይደለም። ባለፈው ዓመትም ከኢያም በፊት ተጋፍጠነዋል፤እና እስካሁንም እየተቁዋቁዋምነው ነው። በአሁኑ ጊዜ ሃገሪቱ ይህን ለማሸነፍ በቂ ሪሶርስና ዘዴም  አላት::”  ይህም ዘዴ ባለፉት በርካታ ዓመታት ሲደረግ እንደነበረው ሁሉ በሙያዊ ልመና ተሰማርቶ ምጥዋት መቅፈፍ ነው። ከወራት ባልበለጠ ጊዜ የአሜሪካን መንግስት ለኢትዮጵያና ለአፍሪቃ ቀንድ ተጨማሪ 200 ሚሊዮን ለችጋሩ ለመርዳት ወስኖአል።በ2011 የአሜሪካን መንግስት በአፍሪካ ቀንድ የተከሰተውን ችጋር ለመርዳት $1.1 ቢሊዮን ዶላር ሰብአዊ እርዳታ አድርጉዋል። በ2008 ኢትዮጵያ ከ$3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ተመጥውታለች።ይህም ኢትዮጵያን ክፈተኛውን የአፍሪካ የልማት እርዳታ ተቀባይ አድረጉዋታል።በኢትዮጵያ ማለቂያ የሌለው የምጥዋት ችሮታ!

ኢትዮጵያ ማለቂያ የሌለው “”የምግብ ዋስትና እጦት ይገጥማታል’’ ማለት ጠሃይ ነገ ትወጣለች ብሎ እንደመተንበይ  ነው። የምግብ ዋስትና እጦት በ2050 በጣም ይገዝፋል።የአሜሪካ ተንባይ ቢሮ በ2050 የኢትዮጵያ ሕዝብ ብዛት በሶስት እጥፍ በማደግ 278 ሚሊዮን ይደርሳል የሚለውን አስደንጋጭ ትንበያ  አሰምቶናል።ያንንም የሰማው መለስ ዜናዊ በማን አለብኝነቱና በአካኪ ዘራፍ ማን ያለ እኔ ባይነቱ በ2011 በችጋር ላይ ድልን እቀዳጃለሁ በማለት ያውጃል። “እራሳችንን ለመመገብና የተትረፈረፈ ምርት ላመስገኘት የሚያበቃን እቅድ አውጥተናልና በ2015 ከማንም እርዳታ ከየትም ምጥዋት አንሻም”” ይለናል።

በአዲሱ ለምግብና ለተመጣጠነ ምግብ ዋስትና አሜሪካና ሌሎቹ የጂ8 አባላት የአፍሪካን ችጋር ተጎጂዎች ለመርዳትና የአፍሪካን ፈላጭ ቆራጭ የሕዝብ ጠላቶች የሆኑ ገዢዎችን መርዳቱ የሚያስከትለውን የሞራል ውድቀት አልተገነዘቡትም አለያም አውቀውት ደንታ አልሰጡትም። የገጣሚውን ሩድ ያርድ ኪፕሊንግን ቃል በመዋስ፤በአፍሪካ ለተራቡና የችጋር ተጠቂ ለሆኑት ሕዝቦች ማለቂያ የሌለውን ምጥዋት መቸርን የራሳቸው “”ሸክም’’ አድወርገው ተቀብለውታል። ሆኖም ግን አሁን በመካሄድ ላይ ያለው ”አዲሱ የችጋር ጨዋታ” ትንሽ ረቀቅ ያለ ነው።ሕብረብሄራዊ የሆኑትን ዓለም አቀፍ የምግብ ኩባንያዎችአፍሪካን ”ለማዳን” በሚል ስም  1) እነዚህን ትላልቅ የእርሻ ኩባንያዎች የምርታቸውን ገበያ ያጣ ትርፍራፊያቸውን ችጋር ባጠቃቸው የአፍሪካ ሃገራት እንዲያፈሱ 2) በዓለም አቀፉ ገበያ ተፈላጊና እትራፊ የሆኑትን ምርቶች ለማምረትና ለገበያው ላመቅረብ መረ በአፍሪካ ያሉትን በመቶ ሚሊዮን ሄክታር የሚቆጠሩትን ለም መሬቶች በሊዝ ስም በመቀራመት ለዓለም ገበያ ለማቅረብ ።ይህ አዲሱ ጥምረት ለዘመናት ተረጂነትን ያጎለበተውን ስርአት በመጠበቅ፤ የምግብ እርዳታን ሱስ በአፍሪካ በማደርጀት አፍሪካውያንን አናሳ ገበሬዎች ከይዞታቸው እያፈናቀሉ ና የምርት አቅማቸውን በማዳከም ችጋርን በራሳቸው እንዲቁዋቁዋሙት ማድረግ ነው።

እውነትን ማረጋገጥ   

ሊታሰብበት የሚገባው በሂደቱ ውስጥ ካሉት ጥቂቶቹ አሜሪካንን ጨምሮ ወይም ዓለም አቀፉ ሚዲያ “ስለአዲሱ ጥምረት”አንዳችም ትኩረት አለመቸራቸው ነው። ሌላው ቀርቶ እርዳታን የኒያዳርሱት የሰብአዊ መብት ተሙዋጋቾች እንኩዋን እንደመልካም የማስታወቂያና የመቀስቀሻ መንገድ ነው የተመለከቱት።ኦክስፋም ግን አሻፈረኝ ባይ ሆንዋል። ሰበቡም “አዲሱ ጥምረት አዲስም አይደለም፤ደሞም ሃቀኛ ጥምረትም አይደለም” የሚል ነው።ግርግሩ አናሳ ገበሬዎችን በተለይም ሴቶችን ለጉዳት የሚጥል ነው።ጥምረቱ በእቅዱ ሴቶችን ወደ መድረኩ ማምጣት አለበት።”  የአክሽን ኤይድ ደግሞ አመራርነት ነበረው። “አዲሱ ጥምረት የግል ሴክተሩን የሚወክል እንደመሆኑ፤ ፕሬዜዳንት ኦባማ እንዳሉት፤ ይህ በጣም አነስተኛ የሆኑትንም የግብርና ዘርፎችን ማካተት አለበት።በአፍሪካ ግብርና ውስጥ ሴቶች ናቸው ቁልፉን ሚና የሚጫወቱት።ማንኛውም የግል ሴክተር ጥምረት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ሲንቀሳቀስ ሴቶችን ማካተቱ ግዴታ ሲሆን፤የአፍሪካን ሲቪል ማሕበረሰብም ማዕከል ሊያደርገው ይገባል::”

ልዩ ትኩረት የሚያስፈልገው ውይይት የተደረገበት የምግብ ዋስትና ነው እንጂ በሰሚቱ የተነጋገሩበት አይደለም። የዩ ኡስ ኤይድ አስተዳዳሪና የውይይቱ መሪ የነበረው ራጂቭ ካህን መለስ ዜናውን ለንግግር ሲጠራው የሚከተለውን በማለት ነበር።

በብዙ ሰዎች ሕሊና ውስጥ ተቀርጦ ያለው የኢትዮጵያ ምስል ከችጋር ጋር የተሳሰረ ነው።ከዚሁ ጋር ደግሞ በሕዝባዊ ድርጅቶች ውስጥ ባለው እንቅስቃሴና ጠንከር ያለ ኢንቬስትመንት በግብርናው በኩል በማበረታታት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያንን ከዘንድሮው ችጋር አድነሃል። አዲስ ጥምረት በምንፈጥርበትም ነአሁኑወቅት ቢሆንም ስለዚህ ጉዳይ ልትነግረን ትፈቀውዳለህ? በግላችን ባደረግነው ውይይት ቃላችንን ጠብቀን የግሉን ዘርፍ ማቀፍ እንዳለብን  በሕዝባዊ ኢንቬስትመንት በሕዝባዊ ድርጅቶች መታገዝ ምን ያህል ጠቀሜታ እንዳለው ልትነግረን ትችላለህ?

መለስ ሲመልስም:

በአፍሪካ የግብርና ትራንስፎርሜሽን በአናሳዎቹ ባለእርሻ ገበሬዎችናበግሉ ሴክተር መሃል የሚደረግ ጥምረት ነው። በዚህም ዋናውን ቦታ የሚይዙት አናሳ መሬት ያላቸው ገበሬዎች 70 በመቶውን (አበበ ገላው መለስ ዜናዊን ዲክቴተር.ፈላጭ ቆራጭ………. በማለት ከንግግሩ አናጠበው) በአፍሪካ ከሕዝቡ 70 በመቶው  በትንሽ ይዞታ ላይ የሚያርሱ ናቸው።ስለዚህም እነዚህን ትራነስፎርም በማድረግ የኖሩበትን ከመለወጥ በፊት ምንም አይነት የግብርና ተስፋ በአፍሪካ ሊኖር አይችልም።አሁን ባለንበት ደረጃ የግሉ ሴክተር ሚና አናሳውን የግብርና ባለቤት መደገፍ ነው። የገጠር መንገዶች ጥያቄ አለ፤የውሃ ችግር አለ፤የመስኖ ውሃ አዘረጋግ አለ። ይህ ሁሉ የሕብረተሰቡን አስተዋጥኦ ይፈልጋል። በእርግጥ ብዙ ያስፈልገናል። ከዚሁ ጋር የሕዝቡን ኢንቬስትመንትም እንሻለን። እኛ በአፍሪካ ያለነው አቅማችን የፈቀደውን እያደረግን ነው።እንዳልኩት አብዛኛዎቹ ሀገሮቻችን ከበጀታችን 10 በመቶውን በእርሻ ላይ እያዋልን ነው።ያም ሆኖ ተጉዋዳኞች ያስፈልጉናል። ዛሬ ጠዋት ፕሬዜዳንቱ (ኦባማ) ቃል ስለተገባው 22 ቢልዮኑ አኩዊላ ኢንሽዬቲቭ ሲናገሩ ነበር። ቃል የተገባልንን ገንዘብ ፕሬዜዳንቱ እንዳሉት እንፈልገዋለን። እንዲሁም የዳበሩት ሃገሮች በግብርናው በኩል ሊያደርጉ የሚገባቸው አለ፤ ምክንያቱም ገበሬዎቻችሁን ስትደጉሙ፤የኛ ገበሬዎች ደግሞ በድሆች ገዢዎቻቸው መደጎም ሳይችሉ በእኩል ደረጃ ሊወዳደሩ አይችሉም።ለምሳሌ በአውሮፓ ዩኒየን እያንዳነዱ ላም በቀን $2 ይሄ ደግሞ አንድ አፍሪካዊ ገበሬ በቀን ከሚያገኘው የበለጠ ነው። በመሆኑም ድጎማው የሚተገበርበት መንገድ ቢኖር ከድህነትና ከችጋር ማምለጫ መንገድ ይሆነናል።

መለስ ዜናዊ ”በሕዝባዊ ድርጅቶች ውስጥ ባለው እንቅስቃሴና ጠንከር ያለ ኢንቬስትመንት በግብርናው በኩል በማበረታታት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያንን ከዘንድሮው ችጋር አድነሃል…” የሚለው የካሃን ግምት ዝም ብሎ በዘፈቀደ የተሰነዘረ አስተያየት ነበር።ይህም የሚያሳየው ዩ ኤስ ኤይድ በኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው ምንያህል ተአማኒ መሆን አለመሆኑን ለማወቅ ደንታ ቢስ መሆኑን የሚያሳየው።በዩ ኤስ ኤይድ ኦዲት ሪፖርት መሰረት (ማርች 2010,  ገጽ 1). ኦዲቱ በዩ ኤስ ኤይድ/ኢትዮጵያ የቀረበው የድርጊት እቅድ እና ዘገባ ተቀባይነት ያለው ይሁን አይሁን የእርሻ ፕሮግራሙ አባላት የተጠቀሰው ውጤት ድጋፍ መስጠት አልቻሉም።በእርግጥም የኦዲት ቡድኑ የዘገባውን ውጤት ትክክለኛነት ከቀረበለት ማረጋገጫ የተባለ ሰነድ ላይ ለማመሳከር ሲሞክር በጥህፈት ቤቱም ሆነ ወይም ተግባሩን በሚያስፈጥሙት  ቢሮዎች በኩል ይህን ማድረግ አልተቻለም። ሙሉና ወቅታዊ ድርጊታዊ ዘገባ ሰነድ በሌለበት  የማኔጅመንት እቅድ፤ ዩ ኤስ ኤይድ ለመቆጣጠር የሚያስፈልገውን ዋነኛ መሳርያ የግብርናወ ፕሮግራም መተግበሩን ማረጋገጥ ጨርሶ አልተቻለም።

ከሃንና መለስ ዜናዊ ስለ “ሕዝባዊ ኢንቬስትመንት” እና “አነስተኛ መሬት ያለቸው ገበሬዎች”  ላሞቹ ወደጋጣው እስኪገቡ ሊያወሩ ቢችሉም፤ ዋናው የነገሩ ቁምነገር ግን ኢትዮጵያም ሆነች ሌሎቹ አፍሪካዊ ሃገራት፤ በሃገሪቱ ውስጥ በተንሰራፉት ፈላጭ ቆራጭ እኩይ ገዢዎች በሚያወሩት በምግብ እራስን የመቻል አርቲ ቡርቲ፤ ወሬያቸውና ከህበረብሄር ኮርፖሬሽኖች ጋር በሚፈጥሩት የነጋ አልነጋም የ ”ምግብ ዋስትና ማረጋገጫ” አዲስ ጥምረት ጠብ የሚል አንዳች ፋይዳ አይኖርም። በተኩላዎችና በጅቦች መሃል የአንድነት ህብረት ለጋዜል የሚተርፍ አንድም ጠብታ አይኖርም።

ባለፉት ስድስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ መለስ ዜናዊ (ለ99 ዓመታት ሊዝ በሚል) ለህንዶች፤ለቻይናዎች፤ለኮርያዊያን፤እና ለሳውዲ ኩባንያዎች  ምርቶቻቸውን ልጭ ገበያ እንዲያቀርቡ በሚሊዮን ሄክታር የሚቆጠሩ ለም መሬቶችን በሽርፍራፊ ሳንቲሞች ደረጃ ቸብችቦአል።  የመለስ ዜናዊ ገደብ የለሽ አካኪ ዘራፍ ቀረርቶ ከ36 በላይ ከሆኑ ሃገራት ጋር የመሬት ውል ገብቻለሁ በሚል ይጮሃል።እነዚህ መሬቶች ደግሞ አንዳችም መተኪያ አለያም መቁዋቁዋሚያ ትክም ሆነ ካሳ ካልተሰጣቸው አነስተኝ መሬት ያላቸው ገበሬዎች ተነጥቆ  ሲሆን የትላልቆቹ ኩባንያዎች ምኞትና የትርፍ ህልማቸው ምርታቸውን ለውጭ ገበያ በዳበረ ትርፍ መሸጥ ነው።

የእርሻ መሬት፤ጨርሶ የመሬት ባለቤት የመሆን መብታቸው በሕግ ተነፍጎ  ባለበት ሁኔታ ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ እነዴት ይቻላታል? በሃገር ውስጥ የምግብ እህልን እያመረቱ ሌላውን ሃገር የምግብ ዋስትና በማረጋገጥ የአምራቹ ሃገር ሕዝብ ግን  መጨረሻ በሌለው ችጋር ሲጠበስ የምግብ ማምረቱ ነገር ምን ትርጉም አለው?  ለም መሬቶችዋን ለካሩቱሪ፤ ሳውዲ ስታር፤ ካርጊል wezet በሊዝ ስም ሽያጥ ተካሂዶባት ባለችበት ሁኔታና እነዚህ ግዙፍ የሆኑ ኩባንያዎች ደግሞ ዓላማቸው ምርታቸውን ለትርፋመናነታቸው ማረጋገጫ ለውጭ ገበያ ማቅረብ ቀደምት ተግባራቸው በሆነበት ሁኔታ ኢትዮጵያ እነዴት ብላ ነው የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የምትችለው። 0.93 ሄክታር የሆነች አነስተኛ መሬት ላይ የሚያርሰውስ ገበሬ በምን አቅሙ ነው ከነሱ ጋር ተወዳድሮ ለነፍስ ማቆያው ያህል እንኩዋን የሚያመርተው? ነው ወይስ በችግሩና በታላላቆቹ የምርት ፋበሪካዎች እየተገፋና እየተጨፈለቀ ከጨዋታ ውጪ በመሆን ከአምራችነት ወደ ገዢነት  በታላላቆቹ የምርት ፋበሪካዎች እየተገፋና እየተጨፈለቀ ከጨዋታ ውጪ በመሆን ከአምራችነት ወደ ገዢነት ሊዘዋወር ነው? መለስ ዜናዊ

ያላዋቂ ሳሚ ሆኖ ችክክ ብሎ የመሬት ባለቤትነትን በመቃብሬ ላይ በማለት በዓለም አቀፍ አዋቂዎች የተመሰከረለትና የመሬት ባለቤትነት ለምግብ ዋስትና መረጋገጥ ዋነኛ መሳርያ መሆኑን በተለመደው ባህሪው ክዶአል።መለስ በ200 እንዳለው (እስከቅርቡም በዚሁ አቁዋሙ እንዳለ ነው)

አሁን ባለንበት ደረጃ መሬትን በግል ንብረትነት መፍቀድን ለመቀበል አንድም አሳማኝ ምክንያት አላገኘሁም።የህንን ተቀብሎ ተግባራዊ ለማድረግ ሰበቡ ይህ ነው የሚል ማስረጃም አላየሁም።መሬትን የግል በማድረግ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ይቻላል የሚልና ገበሬውን ከችግሩ የሚያላቀቀው ይሄው ብቻ መሆኑን በአሳማኝ ሰበብ ብረዳና ገበሬውም ይህን የሚፈቅድ ሆኖ ካገኘሁት የኛም ፖለቲካዊ ፍቃደኛነት ከዚህ የተለየ አይሆንም ነበር።ይሁንና ግን መሬትን የግል በማደረግ አርሶ አደሩ ለ፤ያገኝ የሚችለውንም ሆነ ወደፊትም ይህ በመሆኑ ሊያስከትልበት የሚችለውን ችግር ከወዲሁ በማመዛዘን መሬትን የግል ማድረጉን አንፈቅድም። ወደፊት በኢንዱስትሪው መስክ ላይ ማትኮር እንዳለብን እናምናለን፤እነዚህም አርሶ አደሮች በዚያ መስክ ከእርሻው ውጪ የመቀጠር እድል ማግኘት አለባቸው።

በ2012 “የአፍሪካን አነስተኛ አምራች ገበሬዎች ሕይወት የመለወጥን አስፈላጊነት መለስ ዜናዊ በድፍረት ተናግሮ ነበር። ወይም ”ከአነስተኛው አምራቹን ገበሬ ውጪ በግብርናው መስክ ምንም ተስፋ  እንደማይኖር መለስ ዜናዊ ደስኩሮ ነበር።ለኢትዮጵያ ታላቁ ለጋሽ ዩ ኤስ ኤይድ በ2010 ዘገባው (ምናልባትም ካህን ሳያነቡት ያለፉት) የተሳካ የምግብ ዋስትና ማረጋገጥና፤ የሰመረ የእርሻ ልማት እድገት ሊገኝ የሚችለው 100%  ገበሬው የመሬቱ ባለቤት ሲሆን ብቻ ነው። በሃገሪቱ ያለው ሁኔታና የመለስ አካሄድ ግን ገበሬውን ባለበት በመርዳትና የመሬት ባለቤትነት ዋስትና በመስጠት የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ፈንታ መሬቱን በሊዝ ስም፤ ኢንቬስተሮች በሚል ሽፋን በመሸጥ ባለመብቱን ከኖረበትና ተወልዶ ካደገበት አለያም ለዓመታት ጎጆ ቀልሶ ከሚኖርበት እያፈናቀለ ለስደትና ለውርደት መዳረግን ነው።

ነጣነት የሌለበት ምግብ ትርጉም አልባ ነው

የኢትዮጵያ የምግብ ተመጥዋችነት ባለፉት 4 አሰርት ዓመታት እንደነበረው ይቀጥላል።የሰብአዊ መብት ዓለም አቀፋዊ ዴክለሬሽን እና የሕጣናት መብት ኮንቬክሽን የማንኛውም ሰበአዊ ፍጡር ምግብ የማግኘት መብት የተጠበቀ ነው ይላል።የኢትዮጵያ ሕዝብ ገን በሁለት የችጋር መከራዎች ውስጥ ተዘፍቁዋል።የማይፋቅ ረሃብና ጥም የማይቆርጠው የነጣነት ረሃብ፤ ዴሞክራሲ፤የሰብአዊ መብት መከበር ጥማት።ኢትዮጵያዊያን ለዘህ ግፍና መከራ የተዳረጉት ግልጥነት በሌለው፤ ኢሰብአዊ በሆነ፤ አረመኔያዊ አስተዳደር ሳቢያ ነው።

በ2007 የዓለም የምግብ ቀን ላይ የጀርመን ፕሬዜዳንት ሆርስት ኮህለር ከተናገሩት ውስጥ

“……. ችጋር ሊያመልጡት የማይችሉት አጋጣሚ ነው። ሆኖም ግን በብልህና በሳል ፖሊሲ ሊወገድ ይችላል። ይህ ደሞ ሊሳካ የሚችለው ያልበለጠጉ ሃገራት መሪዎች ለሕዝቦቻቸው የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥን ቀደምት ተግባራቸው ሲያደርጉ ነው። የዴሞክአሲ ተሳትፎን ለሕዝቡ በመስጠትና ተግባራዊ በማድረግ እርግጠኛ የሆነ የሕዝብን ፍላጎት ማያው አዴ ነው።የሕንዱ ታዋቂና የተከበሩ ሎውሬት አማርቲያ ሴን በተደጋጋሚ እንዳሉት ምርጫ በሌለባቸውና ተቃዋሚም በሌለበት፤ ገዢዎች  በሃገራቸው ላይ በሚከሰተው ችጋር የተነሳ ስላጣናችንን እናጣለን ብለው መስጋትን አያውቁም።…መልካም አስተዳደርና እና በሃቅ ሕዝቡን ለማገልገል የቆሙ ተሹዋሚዎች፤ለኢኮኖሚ ፖሊሲው ቁልፍ  ሚና የሚጫወቱ ናቸውና የሕዝቡን ስሜትና ፍላጎት በመረዳት ቸጋርን ማጥፋት ይችላሉ።

ከይዞታ መሬቱ ላይ በተፈለገ ሰአትና ባልተጠበቀ ወቅት ሊባረር እንደሚችል በስጋት ውስጥ ያለ የአነስተኛ ምርት ገበሬ እንዴት ብሎ ነው ያለችውን ጥሪት አውጥቶ በእርሻው ላይና በእርሳ መገልገያ መሳርያ ላይ ሊያውል የሚችለው? ማንን እንዴት አምኖ? ለረጂም ተከታታይ ጊዜያት በእርዳታ መኖርን የለመደ ህብረተሰብ መረዳትን ባህሉ ያደርግና ከመስራት ይልቅ እርዳታን መተማመኛ ያደርገዋል። ችጋር እኮ ባልበለጠጉት ሀጋራትም ሆነ በሌሎቹም ምንግዜም የተሳሳተ የፖለቲካ አካሄድ ውጤት ነው።

ምናልባትም ይቺን የልመና ተምሳሌት የሆነችውን አፍሪካ ፕሬዜዳንት ኦባማ በመሰረታዊ በሆነው የዴሞክራሲ ፕሪንስፕል ቁርጠኝነት ላይ የተመሰረተ አዲስ ትስስር በመፍጠር ለውጥ ሊያስገኙ ይችሉ ይሆናል። “ምግብን በተመለከተ አፍሪካ ራስዋን የማትችልበት አንድም ሰበብ የለም።በመንደሮች ውስጥ የሚኖሩ የራሴ ቤተሰቦች አሉ።እነሱም ለረሃብ ተጋልጠው አያውቁም።የሚኖሩት ግን ችጋር በገሃድ ባለበት መንደር ውስጥ ነው።” በኢትዮጵያ ላለው ችጋር መፍትሄው የፖለቲካውን መዘውር በትክክለኛው ሁኔታ ለማሽከርከር ፈቃደኛ በመሆንና ዴሞክራሲያዊና ነጣ ምርጫ፤ተጠያቂነት፤ግልጥነት፤ለፖሌቲካው ሰፋ ያለ ክፍት ቦታ በመፍጠር፤ሰብአዊ መብትን በአግባቡ በማክበር ተግባራዊ ማድረግ ነው። ፕሬዜዳንት ኦባማ መለስ ዜናዊንና ሌሎቹንም አፍሪካዊ ገዢዎች “በመንደሩ ውስጥ የሚኖረው ለችጋር የተጋለጠው ሰው፤ችግር ለመፍጠር በቁጣ የነደደ መሆኑን ማሳሰብ አለባቸው።

ኢትዮጵያዊ ጋዘተጠኛ አበበ ገላው፤ በአዳራሹ ውስጥ ሕዝባዊ መከራና ስቃይ ገፋፍቶት በመነሳት ለፈላጭ ቆራጩ ግፈኛው መለስ ዜናዊ ……..””ያለነጣነት ምግብ ትርጉም የለውም” በማለት አሳሰበ።  አበበ ገላው ትከከል:  አይደለም?

ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮችን  ለማግኘት እዚህ ይጫኑ:: http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/category/al-mariam-amharic

Leave a Reply