ለኢትዮጵያ ሰማያዊ ፓርቲ ምስክርነት
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ ሰማያዊ ፓርቲን እንደፖለቲካ ድርጅት/ፓርቲ ለምን እንደምደግፈው፣ እ.ኤ.አ ዴሴምበር 15/2013 ከዋሽንግተን ዲሲ ወጣ ብላ በምትገኘው አርሊንግተን ከተማ የስብሰባ አዳራሽ በተዘጋጀው የሰማያዊ ፓርቲ የመጀመሪያ ስብሰባ ላይ ተገኝቼ ንግግር እስካደረግሁባት ዕለት ድረስ በበርካታ ጥያቄዎች እወጠር ነበር፡፡ አንደኛው ተደጋግሞ የሚጠየቀው ጥያቄ ለበርካታ ዓመታት ገለልተኛ ሆኘ እና ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ወይም ቡድን ጋር ሳልወግን…