በግድቡ ሕይወታቸው የተገደበ ኢትዮጵያውያንን ለማትረፍ የሚደረገው እርብርብ
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ ከሁለት ዓመታት በፊት በዚህ በያዝነው ወር “ግድቡ እና አደጋው፡ ግልገል ጊቤ ሦስት በኢትዮጵያ“ በሚል ርዕስ በደቡብ ኢትዮጵያ በኦሞ ወንዝ ሸለቆ ከሚካሄደው ልማት ጋር በተያያዘ መልኩ ግድቡ ሊያስከትል በሚችለው እንደምታ ላይ ትኩረት በማድረግ ትንታኔ አቅርቤ ነበር፡፡ በዚያ ትንታኔዬ በዚህ የልማት ሰበብ እየተካሄደ ያለው እንቅስቃሴ በአካባቢው ስነምህዳር ላይ የሚያስከትለውን አሉታዊ ተጽእኖ…