የነጻ ፕሬስና የዝንጀሮ ፍርድ ቤት በእትዮጵያ
ላለፉት ስድስት ዓመታት ኢትየጵያ ውስጥ ያለውን የፐሬስ ነጻነት ለማስከበር በሚደረገው ግብግብ ውስጥ የትግሉ ደጋፊ በመሆን በርካታ ጦማሮችን ጽፌያለሁ፡፡ በ2009 ባቀረብኩት ርእስ ስር የሰፈረው፤‹‹በኢትዮጵያ ነጻ ፐሬስ አኳያ ያለው የጦርነት ጥበብ›› የሚል ነበር፡፡ በነጻው ፕሬስ ላይ ይዥጎደጎድ የነበረውን የግፍ ጡጫ በተመለከተ ያደረብኝን መገረም ያመላከተም ነበር፡፡ “አንዲት ቢራቢሮን ለመግደል ትልቅ የድንጋይ መፍለጫ መዶሻ ማንሳት! ይሄ ነው እንግዲህ በነጻው ፕሬስ ላይ በ ግፈኛው ፈላጭ ቆራጭ ገዢ መለስ ዜናዊ አላዋቂ ጦር አዝማችነት አሁን የተሰነዘረው ጥቃት፡፡” በ2007 በጻፍኩት ርእስ ‹‹በዝንጀሮ ፍርድ ቤት የአንኮ ፍርድ›› የሚል ሲሆን ጉድለትን ማረሚያ ሃሳቦችን ላለመቀበልና ግድፈቶችን ለማስተካከል የሚሰነዘርን ሂስ ለማፈን በጥቅም ላይ የዋለውን ትርጉም የለሽ ሂደትና በነጻው ፕሬስ ላይ የተቃጣውን የ “ካፍካዊ” የአፈና ዘዴ የተመለከተ ነበር፡፡ ዝነኛው የፍራነስ ካፍካ የመጽሃፍ ጥራዝ፤ የፍርድ ሂደቱ በፍርዱ ውሳኔ ይጀምራል:: “የሆነ ሰው ስለ ዮሴፍ የፈጠራ ወንጀል ሲያወራ ነበር፡፡ አንድ እለት ጸሃይ ገና ስትፈነጥቅ ያለ አንዳች ወንጀልና ያለምንም የማስረጃ ጠብታ ተያዘ፡፡” ከየጌቶቻቸውን ቅዠት በሚያዳምጡትና በቅዠት በሚመሩት የዕውቀት ድሆች በሆኑ ዳኞች ፊት ለፍትህ ቅረብ ተባለ፡፡የዮሴፍ ጉዳይ ያለቀት መስተጋብር ነበር፡፡ የፍረዱ ሂደት ከጅምሩ እስከ መጨረሻው ምንነቱ የማይታወቅ ሚስጥር ነበር፡፡ከፍትሕ ወንበሩ በስተጀርባ በድፍረትና በማን አለብኝነት ማሃይምነታቸውን ተከናንበው፤ አሻንጉሊቶቹ ዳኞች ተብዬዎች ተወዝፈዋል፡፡ ዮሴፍ ክሱ ምን፤ ወንጀሉ ምን የት እንዴት የሚለውን ጨርሶ ስለማያውቅና የሚያውቀው ጉዳይ ቢኖር ንጽህናውን ብቻ በመሀኑ እነዚህ አገልጋዮች ላቀረቡት የፈጠራ ውንጀላ መከላከል አልቻለም፡፡ ምኑን ምን ብሎስ ይከላከል፡፡ ሊመሰክሩበት በሽርፍራፊ ጥቅማ ጥቅም ተገዝተው ስብእናቸውን ሸጠው ሊመሰክሩበት የተዘጋጁትን እቃዎች እንኳን መጠየቅ ማወቅም አልተፈቀደለትም፡፡ የዮሴፍ የፍርድ ሂደት በተደጋጋሚ እየተሰረዘ ይቀያየራል፤ ይዘገያል፡፡ ሕግም ሆነ ስርአት በሌለበት የክስ ሂደት ላይ ጠበቃው ጨርሶ ሊረዳው አልቻለም፡፡