2013 የኢትዮጵያ የአቦሸማኔ ትውልድ ዓመት ይሁን!
ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ የአቦሸማኔዎች ዓመት 2013 የኢትዮጵያዊያን አቦሸማኔዎች (የወጣቱ ትውልድ) ዓመት መሆን አለበት፡፡ ‹‹የአቦሸማኔው ዘመን የሚያመላክተው የአፍሪካን ጉዳይና ችግር በአዲስ መንገድና አመለካከት ማየት የሚችለውን አዲሱንና ቁጡውን ወጣት፤ አዲስ ተመራቂዎችንና ብቁ ባለሙያዎችን የሚመለከት ነው፡፡ ምናልባትም ‹‹ቁንጥንጥ ትውልድ›› ተብለው ሊጠቀሱ ይችላል:: ያም ሆኖ ግን የአፍሪካ አዲሶቹ ተስፋ ወጣቶቹ ናቸው፡፡ ግልጽነትን፤ ተጠያቂነትን፤ሰብአዊ መብትን፤ መልካም አስተዳደርን የቀለጠፈና…