ኦባማ ከትክክለኛው የ(ኢትዮጵያ)ታሪክ ምዕራፍ ጎን ተሰልፈዋልን?
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ የታሪክ ሸፍጥ ፕሬዚዳንት ኦባማ “በትክክለኛው የታሪክ ምዕራፍ” መሰለፍ አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦ ሰጥተው በመግለጽ እራስን በሚያወድስ መልኩ በተግባር ሳይሆን በንግግር ብቻ በማነብነብ እርሳቸው “በተሳሳተው የታሪክ ምዕራፍ” ተሰልፈዋል ብለው የፈረጇቸው ሰዎች አቋማቸውን እንዲያስተካክሉ በነገር ሸንቁጠዋቸዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ2012 በተደረገው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተቀናቃኛቸው ከነበሩት ከሚት ሮምኔይ ጋር ባደረጉት ክርክር ፕሬዚዳንት ኦባማ የእራሳቸውን ክብር…