ኢትዮጵያ እንደ ጋና መሆን የማትችለው ለምንድን ነው?
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ በአደባባይ በይፋ አምናለሁ፡፡ በጋናውያን ላይ መንፈሳዊ ቅናት አድሮብኛል፡፡ ባራክ ኦባማ የመጀመሪያ ጉዞውን ወደ አፍሪካ ባደረገበት ወቅት በአፍሪካ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ወዳላት እና የከፍተኛ የምጣኔ ሀብት ባለቤት ወደሆነችው ወደ ናይጀሪያ ለመሄድ አልመረጠም፡፡ በአሁጉሩ በምጣኔ ሀብት ደረጃዋ የሁለተኛነት ደረጃ ወደያዘችው የኔልሰን ማንዴላ ሀገር ደቡብ አፍሪካ ለመሄድ አልመረጠም፡፡ እንደዚሁም ደግሞ ኦባማ የወላጅ አባቱ የትውልድ ሀገር…