እሪ ይበል ወንዙ፤ እሪ ይበል ሃይቁ! ከዓለማየሁ ገብረማርያም

የአፍሪካ ግፈኛ ገዢዎች፤ ሕዝቦቻቸው በችጋር ሲያልቁና መኖር ጣር ሲሆንባቸው፤ግድብ ማስገንባትን፤አብረቅራቂ ህንጻዎችን ማስገንባትን ይወዳሉ፡፡ይህን የሚያደርጉት ግላዊ ሃብትን ለማካበት፤መኮፈሳቸውን ለመጨመር፤ተስፋ ያጣ ህልማቸውንና ምኞታቸውን ለማሟላት፤ ድክመታቸውንና ችሎታ ቢስነታቸውን ለመሸፈን የቻሉ እየመሰላቸው ነው፡፡በደም የተጨማለቀ እጃቸውን ያጸዱ እየመሰላቸውና በስልጣን ላይ ለዘለቄታው ለመቆየት የሚያስችላቸው እየመሰላቸው ነው፡፡እርቀኑን የቀረ ግፈኛ የአገዛዝ ማንነታቸውን በማይጨበጥና በማይታይ ልማታዊ እቅድና፤እድገት ለመሸፈን ይሞክራሉ፡፡…

ለዶናልድ ፔይን የሰብአዊ መብት ችሮታ – ከዓለማየሁ ገብረማርያም

ድንገተኛ መለየታቸው ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ የነጻነት የዴሞክራሲና የሰብአዊ መብት ትግል ማዝገምን ያስከትልብናል፡፡ሆኖም ግን ፔይን ትተውልን የሄዱት የሰብአዊ መብት፤ጥብቅናና ለረጂም ዓመታት በፍትጊያና በትግል ውስጥ የነበረውን ሂደት ነው፡፡አሁን ደሞ የዚህ ፍትጊያ እጣ ፈንታ በኛ ላይ ተጥሏልና፤ ሸክሙ የኛ የሞራል ግዴታችን ነው፡፡ይህንንም ችሮታቸውን አጠናክረን፤ በሰፊው ሙግቱን አቀነባብረን፤የውጤቱን ጊዜ ማፋጠን ግዴታችንም፤አደራም፤ያውም ታላቅ የመብት ተሟጋቹ ጥለውብን ያለፉት አደራ ነው፡፡