እሪ ይበል ወንዙ፤ እሪ ይበል ሃይቁ! ከዓለማየሁ ገብረማርያም
የአፍሪካ ግፈኛ ገዢዎች፤ ሕዝቦቻቸው በችጋር ሲያልቁና መኖር ጣር ሲሆንባቸው፤ግድብ ማስገንባትን፤አብረቅራቂ ህንጻዎችን ማስገንባትን ይወዳሉ፡፡ይህን የሚያደርጉት ግላዊ ሃብትን ለማካበት፤መኮፈሳቸውን ለመጨመር፤ተስፋ ያጣ ህልማቸውንና ምኞታቸውን ለማሟላት፤ ድክመታቸውንና ችሎታ ቢስነታቸውን ለመሸፈን የቻሉ እየመሰላቸው ነው፡፡በደም የተጨማለቀ እጃቸውን ያጸዱ እየመሰላቸውና በስልጣን ላይ ለዘለቄታው ለመቆየት የሚያስችላቸው እየመሰላቸው ነው፡፡እርቀኑን የቀረ ግፈኛ የአገዛዝ ማንነታቸውን በማይጨበጥና በማይታይ ልማታዊ እቅድና፤እድገት ለመሸፈን ይሞክራሉ፡፡…