2013 የኢትዮጵያ የአቦሸማኔ ትውልድ ዓመት ይሁን!
‹‹የአቦሸማኔው ዘመን የሚያመላክተው የአፍሪካን ጉዳይና ችግር በአዲስ መንገድና አመለካከት ማየት የሚችለውን አዲሱንና ቁጡውን ወጣት፤ አዲስ ተመራቂዎችንና ብቁ ባለሙያዎችን የሚመለከት ነው፡፡ ምናልባትም ‹‹ቁንጥንጥ ትውልድ›› ተብለው ሊጠቀሱ ይችላል:: ያም ሆኖ ግን የአፍሪካ አዲሶቹ ተስፋ ወጣቶቹ ናቸው፡፡ ግልጽነትን፤ ተጠያቂነትን፤ሰብአዊ መብትን፤ መልካም አስተዳደርን የቀለጠፈና ፈጣን አስተሳሰብን፤የሚረዱና ተግባራዊ እውነታንም የሚያስቀድሙ ናቸው›› የታወቀውና የተከበሩት ጋናዊው ኤኮኖሚስት ጆርጅ አይቴ አስረድተዋል:: ቀጥለዉም ሲናገሩ ‹‹ አብዛኛዎቹ አሁን በአፍሪካ በስልጣን ላይ ያሉት መሪዎቻቸው ከመጠን ባለፈ ምግባረ ብልሹ እንደሆኑና፤ የሚመሩትም መንገስት በስድብ የተካነ ግን በተግባራዊ መልካም ሀገርና ሕዝብን በሚጠቅም ጉዳይ እርባና ቢስ የሆኑ፤ ማለቂያ የሌለው የሰብአዊ መብት ድፍረትን የፈጸሙ መሆናቸውን ወጣቶቹ ጠንቅቀው ያውቃሉ››::