የአሜሪካ የሸፍጥ ዲፕሎማሲ “አስቂኝ የመድረክ ትወና”
እ.ኤ.አ ሜይ 2010 በኢትዮጵያ በተካሄደው ፓርላሜንታዊ ምርጫ በቅርቡ ያረፉት አቶ መለስ ዜናዊ 99.6 በመቶ ድምጽ በማግኘት አሸንፊያለሁ ብለው ሲያውጁ ዩናይትድ ስቴትስ ሁኔታው “የሚያሳስበን እና በጉዳዩም ላይ ያለንን ጥልቅ ስጋት እንገልጻለን” በማለት የተለመዱ እና አሰልች የግዴታ አይነት የቃላት መግለጫዎችን ከመስጠት በዘለለ ስለምርጫ ዘረፋው ህገወጥነት በተጨባጭ በመሬት ላይ የሚታይ ያደረጉት አንድም ድርጊት አልነበረም፡፡