ኢትዮጵያ፡ ሕብረት በዓምልኮት (ዓምልኮተ ሕብረት) ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ላለፉት ሁለት አሰርት ዓማታት ኢትዮጵያ የሰብአዊ መበት ጥሰት፤ የወንጀል እና ጸረ ተፈጥሮ፤ ድርጊት መታያ ሃገር ሆና ከርማለች፡፡ አሁን ግን የሃይማኖት አባቶች እስላም ክርሰቲያኑ በአንደነት በመቆም ዓምለኮታቸውን ለማስከበር ትግል ጀምረዋል፡፡ የሙስ ሊሙና የክርስትና ሃይማኖት መሪዎቻቸውና ተከታዮቻቸው፤ አንድነት በመሆንና ሕብረት በመፍጠር የሃይማኖት ነጻነታቸውን ለማስከበር እጆቻቸው ላለመላቀቅና ሕብር ሆነው ለመኖር ተያየዘው ህሊናዊ አስተሳሰባቸውብ በነጻነት ለመጠቀም እንዲችሉ ውህደታቸውን አረጋግጠዋል፡፡ይህንንም ለማክሸፍ ጠንካራ ጉልበቱን የተማመነ ሃይል ውህደታቸውን ለማፈራረስና አለመግባባት ለመፍጠር በተንኮል የተሳለ ምላሱን ጎልጉሎ ተጋርጦባቸዋል፡፡በቅርቡም ከማያልቀው የእርግምት አስተሳሰበ የተወለደ ሁለቱን በአንድነት የኖሩና በመሃላቸው እንከን ያለነበረባቸውን ሃይሞኖቶች ለማጋጨት እኩይ ነገር ተጭሮ ነበር፡፡ የገዢው ፓርቲ ቁንጮ ውሸት አይታክቴ ተንኮል ምሳ ራቱ፤ በፈቀደው መንገድ እየጎተተ ለሚመራውና ያሻውን ‹‹አዎን›፤እሺ›› ለሚያሰኘው ፓርላማው እንዲህ ብሎ ውንጀላ አቅርቦ ነበር፡፡