ፕሬዜዳንት ኦባማ በሁለተኛው ዙር ምርጫ ምን ይጠበቅባቸዋል
ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ ፕሬዜዳንት ኦባማ ሁለተኛውን ዙር የፕሬዜዳንትነት ምርጫ በማሸነፋቸው እንኳን ደስ ያለዎት ማለቱ አግባብ ነው፡፡ የአሜሪካንን መራጮች አብላጫ ድምጽ አግኝቶ ለማሸነፍ ብቃት ባለው አካሄድ ለድል በቅተዋል፡፡ ሚት ሮምኒም ለማይናቀው የምርጫ ግብግባቸው ሊመሰገኑ ተገቢ ነው፡፡ በማጠቃለያው የመለያያ ንግግራቸው ላይ ሚት ሩምኒ ግሩም የሆነ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ ‹‹በእንደዚህ አይነቱ ወቅት የደጋፊዎቻችንን ስሜታዊ ጫጫታ ማዳመጥ፤የፖለቲካ…