የዓለም ወንጀለኛ ፍርድ ቤትን (ICC) ከውድቀት አደጋ መከላከል
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ ፍትህ እንደገና ዘገየችን? እ.ኤ.አ በዚህ ዓመት በጃኗሪ ወር መጨረሻ አካባቢ “ኬንያታ በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (አይሲሲ/ICC): ዘግይቶ መቅረብ ፍትህ እንደተነፈገ መቆጠር የለበትምን?“ በሚል ርዕስ ትችት አቅርቤ ነበር፡፡ በዚያ ትችቴ ላይ ICC የኡሁሩ ሙጋይ ኬንያታን ጉዳይ አስመልክቶ በሄግ እያደረገ ያለው ተደጋጋሚ የፍትህ ሂደቱን የማዘግየት ስራ፣ በቀጠሮ የማሳለፍ እና “የውሸት…