ኢትዮጵያ የተሻሉ አማራጮችን አጥታ ነውን ?
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ እ.ኤ.አ ግንቦት 2015 “ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ የእራሱን ጥላ የሚፈራው ለምንድን ነው?“ በሚል ርዕስ ትችት አቅርቤ ነበር፡፡ በዚያ ትችት ላይ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ደጋፊዎች የወያኔው አመራሮች በግንቦት ስለሚካሄደው የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ በፍርሀት ቆፈን ውስጥ ተሸብበው የመገኘታውን እውነታ ሲነግሩኝ ለእኔ ይህ ሁኔታ በጣም እንቆቅልሽ እንደሆነብኝ ግልጽ አድርጌ ነበር፡፡ የተሰማኝን አግራሞት…