እስክስ! ጅቡ ከደራጎኑ ጋር፣ አይ ጉድሽ አፍሪካ!
የቻይናው ደራጎን (ጭራቅ)ከአፍሪካውያን ጅቦች ጋር አሸሸ ገዳሜ ጭፈረውን እያስነካው ነው፡፡ለዚህ ደራጎን አፍሪካ በምንም መልኩተስማሚ ሁኔታ አትፈጥርለትም፡፡ታሪክ እንደሚያስረዳው በአንድ ወቅት የአፍሪካውያን መኩሪያና መመኪያ የነበረችው ምድር አሁን የጅቦች መሰባሰቢያ ትልቅ ዋሻ ፈጥራ (የአፍሪካ ሕብረት) የጅቦቹ መፈንጪያ መናሃርያ ሆናለች፡፡ለዚህ የጅቦች መገናኛ፤መዶለቻ፤መለመኛ፤ሕዝባዊ ማነቆ መፍተያው ሁሉ ለሚከናወንበት ግንባታ የሚያስፈልገውን ወጪ 200 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የተሸፈነው በቻይና ነው፡፡ ሲባልም፤ ይህ ቻይና ለአፍሪካ የሰጠችው የሰው በላዎቹ (ጅቦች) የአፍሪካ መሪዎችልመና መልስ ነው በማለት ጅቦቹ የታላቁን ደራጎን ስጦታ ለማመስገን በተሰበሰቡበት ወቅት የተሰነዘረ አባባል ነው፡፡