ኢትዮጵያ፡ ወደ ሕገ መንግስታዊ ዴሞክራሲ ጎዳና

ላለፉት ጥቂት ወራት በኢትዮጵያ ከፈላጭ ቆራጭ መንግስት ወደ ዴሞክራሲ በሚል ርዕስ ስጽፍ ነበር፡፡ከነዚህ አስተያየቶች በመጨረሻው ጦማር ላይ ስጥፍ “በዴሞክራሲው መሸጋገርያ ድልድይ ላይ ስልጣንን በሚየነፈንፉ ግለሰቦችና ቡድኖች መሃል ግጭትና ግብግብ አይቀሬ ሲሆን፤ተራው የህብረተሰብ ክፍል ስልጣናቸውን በሚያኮላሹትና ለግል መጠቀሚያ በሚያደርጉት ላይና ሥልጣናቸውን የሙጢኝ ባሉት ፈላጭ ቆራጮች ተሰላችቷል መሮታልም፡፡ይህ ከፈላጭ ቆራጭ ስርአት ወደ ዴሞክራሲ በሚደረገው ሥግግር ወቅት የሚፈጠረው ግርግር ስልጣንን ለመጥለፍ ላቆበቆቡት መንገድ ይከፍትላቸዋል፤ ስለዚህም ዴሞክራሲን አስገድዶ በመጥለፍ በዴሞክራሲ ስም መልሰው ያን አረመኔያዊ ፈላጭ ቆራጭ ስርአትን ሊያስቀምጡ እንደሚተጉ አሳስቤ ነበር፡፡” በዚህኛው ጦማሬ ላይ ደግሞ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚፈጠረው ሕገመንግስታዊ ዴሞክራሲ ሕገመንግስታዊ ‹‹ቅድመ ውይይት›› አስፈላጊነት አተኩራለሁ፡፡

Ethiopia: On the Road to Constitutional Democracy

Alemayehu G Mariam Over the past few months, I have been penning occasional commentaries in a series I called  “Ethiopia’s transition from dictatorship and democracy”. In my last such commentary, I argued that “on the bridge to democracy, there is often a collision between individuals and groups doggedly pursuing power, the common people tired of those who…

ኢትዮጵያ፡- ምግብ ለችጋርና ለማሰብ!

በቅርቡ በዋሽንግቶን ዲሲ በጂ8 አባላት በተካሄደው፤የምግብ ዋስትና ስብሰባ ላይ በዋሽንግቶን ነዋሪ የሆነው ቆፍጣና ወጣት ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ አበበ ገላው በአዳራሹ መሃል ለመሃል ቆሞ ለፈላጭ ቆራጩ ጨካኝ ገዢ መለስ ዜናዊ “ነጣነትለተነፈገው ምግብ ትርጉም አልባ ነው” በማለት ሕዝባዊ ጩኸት አሰምቶ ነበር። እና የአበበ አስተያየት ልክ ነው?

Ethiopia: Food for Famine and Thought!

By Alemayehu G. Mariam The New Alliance for Food Security and Nutrition At the recent 2012 G8 Food Security Summit in Washington, D.C., Abebe Gellaw, a young Washington-based Ethiopian journalist, stood up in the gallery and thunderously proclaimed to dictator Meles Zenawi, “… Food is nothing without  freedom…” Is he right? When President Obama invited…

መለስ አለምላስ! – ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም

መለስ ዜናዊ አምባ ገነን (ዲክታተር) ነው፤ እስክንድር ነጋ ይፈታ፤የፖለቲካ እስረኞችን ፍታ:: መለስ ዜናዊ ዲክታተር ነህ!፤ሰብአዊ ክብርን እያዋረድክ ሰዎችን ለሞት የምትዳርግ ወንጀለኛ ነህ፡፡ ነጻነታችንን እየተገፈፍን ምግብ አያስፈልገንም፡፡ ከምግብ በፊት ነጻነታችን እንፈልገዋለን፡፡ ነጻነት! ነጻነት! ነጻነት! Abebe Gellaw

የመለስ ዜናዊ ድንቀኛ ተረቶች – ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም

ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ በተካሄደው በ‹‹ ዓለም አቀፉ የኤኮኖሚ ስብሰባ ላይ›› የግፍ ገዢው የፈላጭ ቆራጩ መለስ ዜናዊ አርቲ ቡርቲ መነባንብ: …በኔ እምነት በታሪክም ሆነ በቲዎሪ የኤኮኖሚ እድገትና ዴሞክራሲ ቀጥተኛ ግንኙነትም ሆነ ተዛምዶ የላቸውም፡፡ በኔ አመለካከት፤ በኤኮኖሚ እድገት ላይ የሚያስከትለውን ጫና ገሸሽ አድርገን ዴሞክራሲ በራሱ ጥሩ ነገር ነው፡፡በኔ አመለካከት አፍሪካውያን በጣም ስብጥሮች ነን፡፡ ስለዚህም ነው ብዬ አምናለሁ በመሃላችን ያለውን ግንኙነት ሰላማዊ የሚያደርገው፡፡እነዚህን ስብጥር ሰዎች በአንድነት ለማቆየት ያለው አማራጭም ዴሞክራሲ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ስለዚህም ዴሞክራሲን መዘርጋት ይኖርብናል: ያ ግን ለእደገት ብለን አይደለም፡፡ዴሞክራሲን መዘርጋት ያለብን ስብጥር የሆኑትን በአንድነት ለማቆየት እንድንችል ነው…

በካምፕ ዴቪድ የአፍሪካ የችጋር ትርኢት

ባለፈው ሳምንት የሁዋይት ሀውስ ቤተ መንግስት ቃል አቀባይ ጄይ ካርኒ ፕሬዜዳንት ኦባማ የጋናን፤ የታንዛንያን፤የበኒን ፕሬዜዳንቶችንና መለስ ዜናዊን የስምንቱን የኤኮኖሚ ሃያላን ሃገሮች (G8) ስብሰባ ላይ በካምፕ ዴቪድ ሜሪላንድ በሜይ 19 ስለ ምግብ ዋስትና በሚካሄደው ውይይት ላይ እንዲገኙ መጋበዛቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡ የአሜሪካን መንግሥት ለዘመናት ለአፍሪካ አህጉር የምግብ እርዳት ሲያደርግ መክረሙ ይታወቃል፡፡ አሁንም በድጋሚ አፍሪካን ‹‹የመረረ የችጋር ወቅት›› ገጥሟታል ይላሉ ፕሬዜዳንት ኦባማ፡፡ ኦክስፋም በበኩሉ ከአሁኑ አስፈላጊው ሁሉ ካልተደረገ በስተቀር በመታየት ላይ ያሉ ጠቋሚ ምልክቶች ሁሉ እጅጉን ዘግናኝ የሆነ መአት እንደሚከተል ያሳያሉ ይላል፡፡ የተባበሩት መንግስታት የምግብና የእርሻ ድርጅት በበኩሉ ባስተላለፈው የድረሱ ጥሪው፤ በሳሄል ምእራብ አፍሪካ ለ800,000 በችጋሩ ለተጎዱት ረሃብተኞች መርጃ የሚሆን 70 ሚለዮን የአሜሪካን ዶላር እንደሚያስፈልግ፤አስቀድሞ ማስጠንቀቂያው መተንበዩን መሰረት አድርጎ ኢትዮጵያና ሶማልያ በጉዳቱ ወደ አዘቀዘቀው ደረጃ እንደሚወርዱም ይፋ አድርጓል፡፡ የዝናቡ አናሳ መሆንም አስፈላጊውን ምርት ስለማያስገኝ የግጦሽ መሬትንም መልሶ ስለማያለማው፤በአጠቃላዩ አካባቢም የውሃ እጦት ሌላው ችግር በመሆኑ የደቡብ ኢትዮጵያውን ክፍል በእጅጉ የሚጎዳና ሕዝቡንም ለመረረ ችጋር ከብቱንም ለእልቂት የሚዳርግ ክፉ ቀን እንደሚመጣ ይተመናል:: ይህ ደሞ በገሃድ እየታየ ያለ በመሆኑ አደጋው ከአደጋዎች ሁሉ የባሰ በሆነ መልኩ ነው፡፡ አንባቢዎቼ እንደሚያስታዉሱት ሁሉ ባለፉት ሁለታ ዓመታትና ከዚያም ባለፈ በኢትዮጵያ ስለሚከሰተው ችጋር በርካታ አስተያየቶችን አስመልክቼ ጽፌ ነበር፡፡