የሠላም ራዕይ ለኢትዮጵያ – ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም

ሕልምና ቅዠት ስለ ውቧ ኢትዮጵያ

የሰብአዊ ተሟጋችና የምሁር ለሰሚ መናገር እውነትን ለስልጣን ያዦች መከሰትና ወደፊት ካለፈው ይሻላል የሚለውን ተስፋ ይዞ መጓዝ ነው፡፡ እውነተኛ የሰብአዊ መብት ተሟጋች የፖለቲካ ስልጣን ፍላጎት የለውም፡፡ የሰብአዊ መብት ፖለቲካ፤ የሰው ልጅ ክብርና ሞገስ መጠበቅ ፖለቲካ ነው፡፡ ስለ አይዲዎሎጂ አለያም ወገናዊነት ፖለቲካ ወይም የሥልጣን ሽሚያ አይደለም፡፡የሰብአዊ መብት ተሟጋች ስለወደፊት ተስፋ ነው የሚያተኩረው፡፡ ቫክላክ ሃቬል የቼክ ፕሬዜዳንትና ሰብአዊ መብት ተሟጋች ሲናገሩ ‹‹ተስፋ የአእምሮ ግንዛቤ ነው፡፡ በጥልቀት ስናየው ተስፋ የአእምሮ ግንዛቤ ነው፡፡ጠልቀን ስናየው ደግሞ ተስፋ መደሰት ማለት አይደለም፤ተስፋ አንድ ጥሩ ነገርን ማድረግ ነው ብለዋል፡፡አንድ የሰብአዊ መብት ተሟጋች፤በሚያደርገው ድርጊት ለሚያገኘው ለጥቅም ወይም የገነነ ስም አይደለም፡፡ የፈጠነ የፖለቲካ ለውጥም ይመጣል ብሎ አይደለም፡፡ ሃቫል እንዳሉት አንድ ጥሩ ነገርን ማድረግ፤ ያ ነገር በርግጥ ሁኔተኛ ይሆናል በማለት አይደለም፡፡ ባለፉት ዘመናት ስለ ሰብአዊ መብት በኢትዮጵያ ስጮህ ፈላጭ ቆራጮቹን ስቃወም፤የማደርገው ድርጊት ፈጣን ውጤት ያመጣል ብዬ አይደለም፡፡ወይም በአንድ ሌሊት መዋቅሩ ይለወጣል በማለት አይደለም፡፡ለረጂም ጊዜ ስለ ሰብአዊ መብት የተናገርኩት፤ የጻፍኩት፤የተሟገትኩት መልካም ጥሩ ነገር በመሆኑ ነው፡፡

እሪ! እንበል ለኢትዮጵያ (ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም)

በነጻነት መናገር የሁሉም የሰብአዊ መብቶች መሰረት ነው፡፡ በኔ ግምት፤የህብረተሰቡ ሃሳብን የመናገርን ነጻነት የሚሰጠው ዋጋ፤ ያ ሕብረተሰብ ነጻ መሆን አለመሆኑን የሚያረጋግጥበት መንገድ ነው፡፡ ግለሰቦች ያሻቸውን ለመናገር ፍርሃት ካደረባቸው፤ እንደህሊናቸው ፈቃድ ማሰብ፤ መጻፍ አለያም መንግስትን በመፍራት ከፈጠራ ተግባራቸው ከተገደቡ፤ ሊደርስባቸው በሚችል ማስፈራሪያና ዛቻ ወከባና እስር በመፍራት ያሰቡትን ማድረግ ካልቻሉ፤ያ ህብረተሰብ ነጻነቱን የተሰለበ ይሆናል:: ሃሳብን በነጻነት የማንሸራሸር መብት በአሜሪካን ሪፓብሊክ አመሰራረት ላይ ግዙፍ ቦታ ሊኖረው ስለተገባ፤ አሜሪካን የመሰረቱት ጨርሶ ሊነካ፤ ሊቀለበስና ልዩ ትርጉም ሊሰጠው የማይችል መሰረቱ የጸና ሕገ መንግስታዊ ድጋፍና ከለላ አደረጉለት፡፡ በዚህም ላይ በመመስረትና በእንግሊዝኛው ቋንቋ አማራጭ ትርጉም እንዳይኖረው በማድረግ ‹‹ኮንግሬስ በምንም መልኩ ቢሆን የመናገር ነጻነትን በሚጥስ መልኩ፤ወይም የፕሬስን መብት የሚገድብ ማንኛውንም ሕግ ሊያወጣ አይችልም›› በማለት ደምድመው አስከመጡት፡፡

ኢትዮጵያ የኛ፥ የምጽዋት ምርኮኛ? ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም

የዓለም አቀፍ ድጋፍ ሰጪ ደርጅቶችን፤የተባበሩት መንግስታትን የእርዳታ ኤጀንሲን፤ዩ ኤስ ኤይድስን፤የዓለም ባንክንና አይ ኤም ኤፍን ያካተተውን ‹‹ኢንዱስትሪ›› ግራሃም ሃንኮክ ‹‹የችጋራሞች ጌቶች›› በሚለው መጽሃፉ ምንነታቸውንና ማንነታቸውን ከነተግባራቸውና ከሃብታምነት ወይም የጌትነታቸውን መሰረት ቁልጭ አድርጎ አስነብቧል፡፡ደፋር አቀራረቡ ብዙዎችን ‹‹የዓለም አቀፍ መጽዋቾችን›› ቢያበሳጭም ሃቁን መካድና እውነትን መሸሽ የሚቻል አልሆነም፡፡የደራሲው መሰረታዊው ክርክሩ፤ ‹‹የዓለም አቀፍ እርዳታ የጊዜም፤የገንዘብም ብክነት›› ከመሆኑም አልፎ፤ተረጂ ምጽዋተኞችን የሚጎዳ በመሆኑ በአስቸኳይ፤ ሊቆም ይገባል ነው፡፡በ1989 የተመጸወተው 60 ቢሊዮን ዶላር ጉዳቱን ፤ለመድረስ በቂ መሳርያ ከመሆኑም አልፎ እጅጉን ጎጂና በፍላጎታቸው ላይም ጫና የሚፈጥር ማሰርያ ነው፡፡በከፍተኛ ደረጃም ከባቢውን አየር በማይታመን የጥፋት ዘመቻው አብክቶታል፤በተመጽዋቾቹ ላይ ሶምሶማ እየጋለበ የሚጨፍርባቸውን አስከፊ ገዚዎችንም ህጋዊነት እየሰጠ ሕዝቡን ግን በቸልታ በመመልከትና ለጩኸታቸውም ጆሮ በመንፈግ ይቅር የማይባል በደል አድርሶባቸዋል ይላል ሃንኮክ፡፡

Ethiopia in BondAid?

Alemayehu G. Mariam “Bondage” is the state of being bound by or subjected to some external power or control. When people are bound by debt, they are in “debt bondage”. When they are held in involuntary servitude, they are in “bondage slavery”. Before much of Africa became “independent” in the 1960s, Africans were held under…

የነጻ ፕሬስና የዝንጀሮ ፍርድ ቤት በእትዮጵያ

ላለፉት ስድስት ዓመታት ኢትየጵያ ውስጥ ያለውን የፐሬስ ነጻነት ለማስከበር በሚደረገው ግብግብ ውስጥ የትግሉ ደጋፊ በመሆን በርካታ ጦማሮችን ጽፌያለሁ፡፡ በ2009 ባቀረብኩት ርእስ ስር የሰፈረው፤‹‹በኢትዮጵያ ነጻ ፐሬስ አኳያ ያለው የጦርነት ጥበብ›› የሚል ነበር፡፡ በነጻው ፕሬስ ላይ ይዥጎደጎድ የነበረውን የግፍ ጡጫ በተመለከተ ያደረብኝን መገረም ያመላከተም ነበር፡፡ “አንዲት ቢራቢሮን ለመግደል ትልቅ የድንጋይ መፍለጫ መዶሻ ማንሳት! ይሄ ነው እንግዲህ በነጻው ፕሬስ ላይ በ ግፈኛው ፈላጭ ቆራጭ ገዢ መለስ ዜናዊ አላዋቂ ጦር አዝማችነት አሁን የተሰነዘረው ጥቃት፡፡” በ2007 በጻፍኩት ርእስ ‹‹በዝንጀሮ ፍርድ ቤት የአንኮ ፍርድ›› የሚል ሲሆን ጉድለትን ማረሚያ ሃሳቦችን ላለመቀበልና ግድፈቶችን ለማስተካከል የሚሰነዘርን ሂስ ለማፈን በጥቅም ላይ የዋለውን ትርጉም የለሽ ሂደትና በነጻው ፕሬስ ላይ የተቃጣውን የ “ካፍካዊ” የአፈና ዘዴ የተመለከተ ነበር፡፡ ዝነኛው የፍራነስ ካፍካ የመጽሃፍ ጥራዝ፤ የፍርድ ሂደቱ በፍርዱ ውሳኔ ይጀምራል:: “የሆነ ሰው ስለ ዮሴፍ የፈጠራ ወንጀል ሲያወራ ነበር፡፡ አንድ እለት ጸሃይ ገና ስትፈነጥቅ ያለ አንዳች ወንጀልና ያለምንም የማስረጃ ጠብታ ተያዘ፡፡” ከየጌቶቻቸውን ቅዠት በሚያዳምጡትና በቅዠት በሚመሩት የዕውቀት ድሆች በሆኑ ዳኞች ፊት ለፍትህ ቅረብ ተባለ፡፡የዮሴፍ ጉዳይ ያለቀት መስተጋብር ነበር፡፡ የፍረዱ ሂደት ከጅምሩ እስከ መጨረሻው ምንነቱ የማይታወቅ ሚስጥር ነበር፡፡ከፍትሕ ወንበሩ በስተጀርባ በድፍረትና በማን አለብኝነት ማሃይምነታቸውን ተከናንበው፤ አሻንጉሊቶቹ ዳኞች ተብዬዎች ተወዝፈዋል፡፡ ዮሴፍ ክሱ ምን፤ ወንጀሉ ምን የት እንዴት የሚለውን ጨርሶ ስለማያውቅና የሚያውቀው ጉዳይ ቢኖር ንጽህናውን ብቻ በመሀኑ እነዚህ አገልጋዮች ላቀረቡት የፈጠራ ውንጀላ መከላከል አልቻለም፡፡ ምኑን ምን ብሎስ ይከላከል፡፡ ሊመሰክሩበት በሽርፍራፊ ጥቅማ ጥቅም ተገዝተው ስብእናቸውን ሸጠው ሊመሰክሩበት የተዘጋጁትን እቃዎች እንኳን መጠየቅ ማወቅም አልተፈቀደለትም፡፡ የዮሴፍ የፍርድ ሂደት በተደጋጋሚ እየተሰረዘ ይቀያየራል፤ ይዘገያል፡፡ ሕግም ሆነ ስርአት በሌለበት የክስ ሂደት ላይ ጠበቃው ጨርሶ ሊረዳው አልቻለም፡፡

ኢትዮጵያ፡ ሕብረት በዓምልኮት (ዓምልኮተ ሕብረት) ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም

ላለፉት ሁለት አሰርት ዓማታት ኢትዮጵያ የሰብአዊ መበት ጥሰት፤ የወንጀል እና ጸረ ተፈጥሮ፤ ድርጊት መታያ ሃገር ሆና ከርማለች፡፡ አሁን ግን የሃይማኖት አባቶች እስላም ክርሰቲያኑ በአንደነት በመቆም ዓምለኮታቸውን ለማስከበር ትግል ጀምረዋል፡፡ የሙስ ሊሙና የክርስትና ሃይማኖት መሪዎቻቸውና ተከታዮቻቸው፤ አንድነት በመሆንና ሕብረት በመፍጠር የሃይማኖት ነጻነታቸውን ለማስከበር እጆቻቸው ላለመላቀቅና ሕብር ሆነው ለመኖር ተያየዘው ህሊናዊ አስተሳሰባቸውብ በነጻነት ለመጠቀም እንዲችሉ ውህደታቸውን አረጋግጠዋል፡፡ይህንንም ለማክሸፍ ጠንካራ ጉልበቱን የተማመነ ሃይል ውህደታቸውን ለማፈራረስና አለመግባባት ለመፍጠር በተንኮል የተሳለ ምላሱን ጎልጉሎ ተጋርጦባቸዋል፡፡በቅርቡም ከማያልቀው የእርግምት አስተሳሰበ የተወለደ ሁለቱን በአንድነት የኖሩና በመሃላቸው እንከን ያለነበረባቸውን ሃይሞኖቶች ለማጋጨት እኩይ ነገር ተጭሮ ነበር፡፡ የገዢው ፓርቲ ቁንጮ ውሸት አይታክቴ ተንኮል ምሳ ራቱ፤ በፈቀደው መንገድ እየጎተተ ለሚመራውና ያሻውን ‹‹አዎን›፤እሺ›› ለሚያሰኘው ፓርላማው እንዲህ ብሎ ውንጀላ አቅርቦ ነበር፡፡