በኢትዮጵያ ወቅቱ ወደፊት መራመጃ ነው (ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም)

በኢትዮጵያ ወቅቱ መጥረቢያውን ቀብሮ ወደፊት መራጃ ነው፡፡ ኔልሰን ማንዴላ እንዳስተማሩት ‹‹ከጠላትህ ጋር ሰላምን መመስረት ከፈለግህ፤ከጠላትህ ጋር አብረህ መስራት አለብህ በዚህን ጊዜ ጠላትህ አጋርህ ይሆናል፡፡›› እኔ ደግሞ ትንሽ ላክልበትና፤ጠላትህ ወዳጅህና ተባባሪህ ይሆናል፡፡ከታሪክ እንዳየነው፤ ብሔራዊ አሜሪካኖች (አሜሪካን ኢንዲያንስ) በመሃከላቸ ሰላምን ሲፈጥሩ፤መጥረቢያቸውን፤ መቁረጫቸውን በመሬት ውስጥ ይቀብሩታል:: ይህም በመሃላቸው ተነስቶ የነበረውን አለመግባባት መቋጨቱን ማረጋገጫ ነው፡፡ዛሬ ለኢትዮጵያውያን ሁሉ ያንን የጎሳ ክፍፍሉን፤የሃይሞኖት ልዩነቱን፤የሰብአዊ መብት ጥሰትን እርግፍ አድርገው ማጥፋታቸውን ለማረጋገጥ መጥረቢያቸውን መቅበር ይገባቸዋል እላለሁ፡፡ አሁን እጅ ለእጅ ተጨባብጠን፤እርስ በርሳችን ተቃቅፈን፤ሁለንተናችንን ለአዲሲቱ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ፤ የሕግ የበላይነት የተከበረባት ኢትዮጵያ፤ሰብአዊ መብት የተጠበቀባትና ዴሞክራቲክ ስነስራት የተከበሩባት ኢትዮጵያን ለመገንባት መዋል ይገባናል፡፡

አቶ መለስ እልፈት ስንብት (ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም)

መለስ ስለፈጸመውና ስላመለጠው ጉዳይ በሕይወት ዘመኑ እያለ በብቃት ያነሳሁት ስለሆነ አሁን ከህልፈቱ በኋላ ብዙም የምለው የለኝም፡፡ ሕልፈተ ሞቱ ያሳዝነኛል፤ ምክንያቱም፤ ጆን ዶን እንዳለው ‹‹የማንም ሰው ሞት ያሳንሰኛል፤ ምክንያቱም እኔም ቁጥሬ ከሰብአዊያን ጋር ነውና ፡፡ሞት ለሁላችንም በእኩል መንገድ መጪ ነው፡፡ሲመጣም ሁላችንንም በእኩል ደረጃ ያስቀምጠናል፡፡›› እንደ ሃቀኛ የሰብአዊ መብት ተሟጋች፤የለየለት ፈላጭ ቆራጭ ባለ ስልጣን ቢሞትም ያሳዝነኛል ምክንያቱም በሰብአዊ መብት ጉዳይ፤በፍትሕ ሚዛናዊነት ላይ፤በእኩልነት ላይእና በመሳሰሉት ላይ ሲጓደሉ ለሙግት በመሰለፌ ነው፡፡

Cheetahs, Hippos and Saving Ethiopia

George Ayittey, one of the foremost African public global intellectuals, metaphorically suggests that Africa’s destiny will be determined by the promise of the “Cheetah Generation” or the paralysis of the “Hippo Generation”. As he explains, The Cheetah Generation refers to the new and angry generation of young African graduates and professionals, who look at African issues…

ህገ መንግስታዊ ቀዉስ በኢትዮጲያ

ለአሜሪካ ድምጽ በቅርቡ በስጠሁት ቃለ ምልልስ ላይ በኢትዮጵያ ሕገ መንግስት መሰረት ጠቅላይ ሚኒሰተሩ በህመም፤ በእክል በሞት በአካለ ጉዳት በተለያዩ ሰበቦቸ በሰራው ላይ መገኘት ባይችል የስልጣን ዝውውሩ አንደት ይሆናል የሚል ጥያቄ ቀርቦልኝ ነበር ነበር። መልስ የሰጠሁት ብዙዎችን አሰግረምዋል፤ አሰደነግጦአል። ባጭሩ በኢትዮጲያ ሕገ መንግስት ስለ ስልጣን ዘውውር በግልጥ ያስቀመጠው ድነጋጌ ምንም የለም።