በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የኢትዮጵያ የፍቅር ባቡር ሁላችንም ተሳፍረናል!

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

እንደመር፦ አንቀነስ፦ እንባዛ፦ አንከፈል፦

 

እልም አለ የፍቅር ባቡሩ ሁላችንም ይዞ በሙሉ ፦

ለተግዋዥ  ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ፡፡ በአብይ አሕመድ የኢትዮጵያ የፍቅር ባቡር  ተሳፋሪዎች በሙሉ

የአብይ አሕመድ የኢትዮጵያ የፍቅር ባቡር ፍሬን የለውም፡፡ ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ባቡር ነው፡፡ በምንም አይነት ለማስቆም የማይቻል ነው! ከተሳፈራችሁ መውረድ አትችሉም፡፡ በፍቅር ወጥመድ ትገባላችሁ!

የኢትዮጵያን የፍቅር ባቡር ማንም ቢሆን ከሀዲዱ በፍጹም ሊያስወጣው አይችልም፡፡

ይህ ማስታዋሻ ስለኢትዮጵያ የፍቅር ባቡር ለመዘገብ ተብሎ የተዘጋጀ አልነበረም፡፡

ለዚህ ሳምንት ፍጹም ልዩ የሆነ ርዕስ ነበር በአእምሮዬ ውስጥ የነበረው፡፡

ሆኖም ግን የጨለማው ጎን ኃይሎች እ።ኤ።አ ሰኔ ፪፫ ቀን ፳፩፰ ዓ.ም በጠራራ ጸሐይ የኢትዮጵያ የፍቅር ባቡራችንን ወደ እነርሱ የጨለማ ምድር ጠልፈው ለመውሰድ አደጋ በመጣል ሙከራ አደረጉ፡፡

የጨለማው ጎን ኃይሎች የፍቅር እና የዕርቀ ሰላም ቀናችንን የብጥብጥ፣ የእልቂት፣ የሞት፣ የውድመት እና የእርስ በእርስ ጦርነት አውድማ ለማድረግ ሞክረዋል፡፡

ሆኖም ግን የፍቅርና የእርቅ ባቡራችን ሊቆም የሚችል አይደለም፦

ተጓዦቻችን፣ የኢትዮጵያ ሕዝቦች የማይበገሩ ናቸው፡፡

መሀንዲሳችን፣ አብይ አሕመድ የማይነኩ ጀግና ናቸው፡፡

የጨለማው ጎን ኃይሎች እ.ኤ.አ ሰኔ ፪፫ ቀን ፳፩፰ ዓ.ም ተንኮታኩተው ወደቁ፡፡ የጨለማው  ጎን ኃይሎች እ።ኤ።አ ከሰኔ ፪፫ ቀን ፳፩፰ ዓ.ም በፊትም ወድቀዋል፡፡ የጨለማው  ጎን ኃይሎች እ.ኤ.አ ከሰኔ ፪፫ ቀን ፳፩፰ ዓ.ም በኋላም ይወድቃሉ፡፡

ሰይጣናዊ ድርጊት ድልን ለመቀዳጀት የሚችለው መልካም ወገኖችና ዜጎች ምንም ነገር ማድረግ ሳይችሉ (እጃቸዉን አጥፈው ሲመለከቱ) ሲቀሩ ነው ይባላል፡፡

እ.ኤ.አ ሰኔ ፪፫ ቀን ፳፩፰ ዓ.ም ሁሉም የኢትዮጵያ መልካም ወንድሞች እህቶችና ልጆች በአዲስ አበባ በመስቀል አደባባይ እና በሌሎች ከተሞች በመውጣት እጅግ ታላቅ ነገርን ሰሩ፡፡

በሚሊዮኖች ሆነው በመውጣት እነርሱን በነጻነት በይቅርታ በእርቅ እና በሰላም ለሚመሯቸው መልካም ወገኖቻቸዉና መሪዎቻቸው ፍቅራቸውን፣ አድናቆታቸውን እና በእነርሱ ያላቸውን ክብር አካፈሉ፡፡

እ.ኤ.አ ሰኔ ፪፫ ቀን ፳፩፰ ዓ.ም የብርሀኑ ጎን ኃይሎች ፍቅር በጨለማው ጎን ኃይሎች ጥላቻ ላይ ድልን ተቀዳጀ፡፡

ሆኖም ግን ለድላችን ሊቆጠር የማይችል ዋጋን ከፈልን፡፡

ሁለት የፍቅር፣ የዕርቅ እና የይቅርባይነት ተዋጊ ወጣቶችን አጣን፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ከ፩፶ በላይ የሆኑ ሌሎች ወገኖቻችን የከባድ የአካል ጉዳት ሰለባ እና ቁስለኛ ሆኑ፡፡ እነዚህ ተወዳጇን ኢትዮጵያን ለመገንባት ለዚህ የተቀደሰ ዓላማ መስዋዕት የሆኑልን ጀግኖቻችን ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ የነጻነት እና የፍጥ ተጋድሎ መዝገብ ውስጥ ተመዝግበው ለዘላለም ሲታወሱ ይኖራሉ፡፡

ምንም ዓይነት የጥላቻ ድርጊት፣ ምንም ዓይነት የሽብር እና ኢሰብአዊ ድርጊት፣ ምንም ዓይነት የጭካኔ ድርጊት፣ ምንም ዓይነት የጥላቻ ደባ፣ ምንም ዓይነት ዲያብሎሳዊ ድርጊት ወይም ሰይጣናዊ ድርጊት ቢፈጽሙም የጨለማው ጎን ኃይሎች የኢትዮጵያን የፍቅር የባቡር ጉዞ ሊገቱት እንደማይችሉ ግልጽ ሊሆንላቸው ይገባል፡፡

ፍቅር፣ ይቅርባይነት እና ዕርቅ ምን እንደሆነ አብይን ሳይሆን የቆሰሉትን ጀግኖች የፍቅር ተዋጊዎቻችንን ፋንታዬ ደሳለኝን፣ እታፈራሁ ውብሸትን እና ወጣት ሰምነራ ስዩምን ጠይቁ፡፡

ጥቂት ሰዎች እንዲህ በማለት ይጠይቃሉ፣ “አብይ አሕመድ ፍቅር፣ ይቅርባይነት እና ዕርቅ ሲሉ ምን ማለታቸው ነው፧“

አብይን ለመጠየቅ ለምን ትቸገራላችሁ፧ ይልቁንም ፋንታዬ ደሳለኝን፣ እታፈራሁ ውብሸትን እና ሰምነራ ስዩምን ጠይቁ፡፡

የፍቅር፣ የይቅርባይነት እና የዕርቅ እውነተኛ ትርጉም የመጨረሻውን ዋጋ በከፈሉት እና በአሁኑ ጊዜ በሆስፒታል ገብተው ከቁስላቸው በማገገም ላይ ያሉት እንደገለጹት ከዚህ በታች እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡ (ከእንግሊዘኛ ፅሁፌ የተቶሮጎመ።) 

ፋንታዬ ደሳለኝ፣

ስለሀገሬ አስባለሁ፡፡ ብሞትም በሕይወት ብኖርም ጉዳዬ አይደለም፡፡ ሕዝቦች በሚኖሩበት ጊዜ ኢትዮጵያ ትኖራለች፡፡ አንድ ሰው በሕይወት የሚኖር ከሆነ ይህ ምንም ማለት አይደለም፡፡ አብይ ጀግና በመሆናቸው ምክንያት ለእርሳቸው የመጨረሻውን መስዋዕትነት እከፍላለሁ፡፡ አብይ አጥተነው የነበረውን ፍቅር የመለሱልን ሰው ናቸው፡፡ በእርሳቸው ቃላት ተፈውሰናል፡፡ የእርሳቸው ቃላት ታላቅ እምነትን ይሰጡናል፡፡ እግሮቼን ባጣም ቅሉ ምንም ማለት አይደለም፡፡ በእራሳቸው እርምጃ አካሎቻቸውን ያጡ በርካታዎቹ አሉ፡፡

በእኔ ላይ ምንም ነገር አልደረሰም፡፡ ሀገሩን የሚወድ ሰው ፈንጅ በወገቡ ስር ጠቅልሎ ሀገሩን እና ሕዝቡን ለማዳን ወደ ጦር ሜዳ ይሄዳል  የሚለው እውነት አይደለም፡፡

ይህንን ድርጊት (ቦምብ ማፈንዳቱን) የፈጸሙት ሰዎች በእራስ ወዳድ ስግብግብነት የሚነዱ እና ወገኖቻችንን እና ሀገራችንን ለማጥፋት ይፈልጋሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ለዚህ ላደረጉት ሰይጣናዊ ስራ ዋጋ ምንም ዓይነት ጠቃሚነት የሌለው ገንዘብ በመቀበል የህይወት እልቂት ፈጽመዋል፡፡ ለእነርሱ የስራ ዋጋ ክፍያ የሚፈጽምላቸው ሰብአዊ ፍጡር አይደለም፡፡ እግዚአብሔር በስራቸው ይቀጣቸዋል፡፡ አብይ ለገዳዮች እንኳ ሳይቀር ምህረትን ያደረጉ ሰው ናቸው፡፡

እጆቼን እና እግሮቼን በማጣቴ ለአንድ ቀንም እንኳ ቢሆን ወቀሳ ወይም ደግሞ ጸጸት የለብኝም፡፡

እድሉን የማገኝ ቢሆን ለአብይ ስልክ በመደወል እግሮቼን እና አጆቼን ማጣቴ ምንም ማለት አይደለም እላቸዋለሁ፡፡ ይህንን እላቸዋለሁ እና ቃሎቼን እሰጣቸዋለሁ፡፡

ለእናቴ እና ለአባቴ ብቸኛ ልጅ ነኝ፡፡ አንድ የአምላክ ልጅ ብቻ፡፡ ለእኔ ይህንን እውነታ ለመቀበል አስቸጋሪው ነገር ለእናቴ አንድ ብቸኛ ልጅ ከመሆኔ አንጻር በእግሮቼ ተሯሩጨ ሰርቼ ገንዘብ በማግኘት እንዳልረዳት የመሆኔ ጉዳይ ነው፡፡ ይኸ ብቻ ነው እኔን የሚያሳዝነኝ፡፡ ሆኖም ግን እኔን ሊረዱኝ የሚችሉ ወንድሞች አሉኝ፡፡ ሁሉም እዚህ በአጠገቤ በፍቅር ከብበውኝ የምትመለከቷቸው እኔን የሚረዱ ናቸው፡፡ የምሞት ከሆነ ፍቅር ኢትዮጵያን ያቆያታል፡፡ አብይ ታላቅ ሰው ናቸው፡፡ በእርሳቸው ላይ የተወረወረው ቦምብ በአንዲት ሴት እጅ አቅጣጫውን እንዲስት ሲደረግ ነው እኔ እግሮች ላይ የወደቀው፡፡ ይኸ ለእኔ ምንም ማለት አይደለም፡፡ ከወደቅሁበት ነቃሁ፣ እናም ከተጎዱት እግሮቼ ጋር ቀረሁ፡፡ አምቡላንስ መጣ፡፡ ሕይወቴን እንዲያተርፉ ጠየቅኋቸው፡፡ ሰንደቅ ዓላማዬን በአፌ ውስጥ ይዠዋለሁ፡፡ ከዚያም ወደ ሆስፒታል ተወሰድኩ፡፡ ሰንደቅ ዓላማዬን ከአፌ ውስጥ በፍጹም አላወጣሁትም ነበር፡፡ ወደ ሆስፒታል ከተወሰድኩ በኋላ ሰንደቅ ዓላማዬን ከአፌ ውስጥ አስወገዱት፡፡

እታፈራሁ ውብሸት፣

…ጠቅላይ ሚኒስትራችን አብይ አሕመድ ንጝራቸውን ከጨረሱ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ፍንዳታው ተከሰተ፡፡ ከህጻን ሴት ልጄ ጋር ነበርኩ፡፡ ፍንዳታው እንደተከሰተ እና ትርምስ እንደተፈጠረ በድጋፍ ሰልፉ ላይ አብራኝ የነበረችው ጓደኛዬ ህጻን ልጄን በመያዝ ሮጠ፡፡ እኔ ብቻዬን ቀረሁ፣ እናም ሕዝቡ በየአቅጣጫው ይጋፋ ጀመር፡፡ እኔ በግዮን ሆቴል አጥር ታገድኩ፡፡ በቆምኩበት አጥር ላይ ጉድጓድ ነበር፡፡ እንግዲህ በዚያ ጉድጓድ ገደል ላይ በመውደቅ ነው እግሬን የተጎዳሁት ፡፡ [ከዚያ ሰው ወድቆ የመትረፉ ሁኔታ ሊታመን የማይችል አስደናቂ ነገር ነው፡፡] ሆኖም ግን ተርፌያለሁ፡፡ አምላክ ደግ ነው፡፡ ሊከሰት ከሚችለው አደጋ አንጻር ሲታይ የእኔ ቁስሎች ያን ያህል ከባድ አይደሉም፡፡ ክርስቶስ ጠብቆኛል፡፡ አምላክ ልጆቹን አይጥልም…

ሰምነራ ስዩም፣

ንጝራቸውን እስከሚጨርሱ ድረስ በመጀመሪያ ሰላም ነበር፡፡ የመድረክ አስተባባሪው የፕሮግራሙን መጠናቀቅ እያስታወቀ ባለበት ጊዜ ፍንዳታው ተከሰተ፡፡ ከፍተኛ ጩኸት አልነበረም፡፡ በወረቀት ውስጥ የተጠቀቀለ ፈንጅ እንደሆ አድርጌ አስባለሁ፡፡ እንደ ቦምብ አይመስልም፡፡ በሰልፉ ላይ ያለው ሕዝብ ገፋኝ እናም እግሬ በቁራጭ ብረት ተጠለፈ እና ወደቅሁ፡፡ ሁለት የፌዴራል ፖሊሶች ነበሩ፡፡ ሆኖም ግን ስማቸውን አላስታዉስም ፡፡ እግዚአብሔር ይስጣቸው፡፡ እኔን ያዳኑኝ እነርሱ ናቸው፡፡ እነርሱ ይዘው ወደ ቢሮ ወሰዱኝ ከዚያም አምቡላንስ ወደዚህ ሆስፒታል አመጣኝ፡፡ እዚህ ቆንጆ የሕክምና ክብካቤ አገኘሁ፡፡ አሁን ደህና ነኝ፡፡ ማስተላለፍ የምፈልገው መልዕክት እንዲህ የሚል ነው፣ “በመካከላችን ፍቅር መኖር አለበት፡፡ እርስ በእርሳችን መዋደድ አለብን፡፡ አንድ ኢትዮጵያ ብቻ ናት ያለችን፡፡ ሌላ ምንም ነገር የለንም፡፡ እየኖርን እርስ በእርሳችን መዋደድ አለብን፡፡ እንደዚህ ዓይነቱን ሰይጣናዊ ድርጊት የፈጸሙትን አምላክ ይቅር ይበላቸው፡፡ ይህንን ድርጊት የፈጸሙ ምክንያቱም ስለማያውቁ ነው፡፡ የፍቅርን ትርጉም ምንነት አያውቁም፡፡ የፍቅርን ትርጉም ምንነት የሚያውቁ ቢሆን ኖሮ እንደዚህ ያለውን ድርጊት አይፈጽሙም ነበር፡፡ ይኸው ነው፡፡ ስለፍቅር የሚያውቁ ቢሆን ክርስቶስ ይቅርታ ያደርግልናል፡፡ በጣም አዝናለሁ ምክንያቱም በርካታ ቁስለኛ የሆኑ ሰዎችን አይቻለሁ፡፡  (እያለቀሰች ) እግዚአብሔር ይመስገን እኔ ደህና ነኝ፡፡ ደህና ነኝ፡፡ ሆኖም ግን ብዙ ደም ተመልክቻለሁ፡፡ በጣም አስደንጋጭ ነገር ነው፡፡ “  

እ.ኤ.አ ሰኔ ፪፫ ቀን ፳፩፰ ዓ።ም በደረሰው የቦምብ ፍንዳታ ስለሞቱት እና ስለቆሰሉት ወንድሞቼ እና እህቶቼ ሳስብ በልቤ ውስጥ ቁስል እንዳለ ያህል ይሰማኛል፡፡ ለእነርሱ አለቅሳለሁ፡፡ ለጠቅላይ ሚኒስትር የሚደርሰውን የእኔን መልዕክት የሚያደርሱልኝ እነርሱ ነበሩ፣ እንግዲህ መልዕክቴን ማን ሊያደርስልኝ ነው፡፡

ኃይልን መጠቀም የደካሞች መሳሪያ ነው፡፡ ሰላም ደግሞ ለሰላማዊ ሰዎች ነው፡፡ ማህተመ ጋንዲ ኃይል የፈሪዎች እና በጥላቻ ለተሞሉት ሰዎች ነው ብለዋል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ እና በእርሳቸው የአመራር ቡድን ላይ የተሞከረውን የአሸባሪዎች ጥቃት የቪዲዮ ክሊፕ እ።ኤ።አ ሰኔ ፪፬ ቀን ፳፩፰ ዓ።ም ጧት ለመጀመሪያ ጊዜ በተመለከትኩ ጊዜ በጥልቅ ሀዘን ላይ ወደቅሁ፡፡

በሰላማዊ ሰልፉ ላይ አደጋ ሊጣል እንደሚችል ግምቶች ነበሩ፡፡ ሆኖም ግን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድን ሊጠብቁ የሚችሉ ሚሊዮኖች ዓይኖች እንደሚኖሩ እና እርሳቸውን በመጠበቅ  እርምጃ መውሰድ የሚችሉ ሚሊዮኖች እጆች እንዳሉ ከመጠን በላይ በመተማመን ነገሩን ከቁብ አልቆጠርኩትም ወይም ደግሞ ትኩረት አልሰጠሁትም ነበር፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ በአብይ ላይ ምንም ዓይነት ነገር ለመፈጸም በፍጹም እንደማይፈቅድ በጥልቅ እገነዘባለሁ፡፡ እርሳቸውን ለመጠበቅ ሕይወታቸውን ይሰጣሉ፡፡ በዚህ እምነት ላይ እርግጠኛ በመሆን በምንም ዓይነት መልኩ የሚያሳስበኝ ጉዳይ አልነበረም፡፡

በተፈጸመው እኩይ ድርጊት እንደተመንኩት ቦምቡ በተጣለበት አካባቢ የነበሩ ወጣቶች አብይ አሕመድን ለማዳን ሲሉ ፈቃደኛ ሰብአዊ ጋሻዎች በመሆን የጨለማውን ጎን ኃይሎች ድል ያደርጉ ነበር፡፡

እነዚህ ክፋት የሚሰሩን የሰው ሰይጣኖች እግዚአብሔር ይቅር ይበላቸው፡፡

የቪዲዮ ክሊፑን በተደጋጋሚ በምመለከትበት ጊዜ ሀዘኔ ወደ ቁጣ ተቀየረ፡፡ ልብ እና አእምሮዬን የኃይል እና በቀልተኝነት ስሜቶች ለመቆጣጠር ይታገሉ ነበር፡፡

እራሴን የሰላም ሰው፣ የሰላም እና የእርቅ ሰባኪ አድርጌ እቆጥራለሁ፡፡ ሆኖም ግን የተጎዱ ወጣቶች በአስፋልቱ ላይ ተዘርረው፣ የነበረውን ሁከት እና ብጥብጥ የቪዲዮ ክሊፖችን በምመለከትበት ጊዜ በዚያ ጊዜ የነበረው ሁኔታ ለእኔ እጅግ በጣም ከባድ ነበር፡፡

ፍቅሮቻቸውን እርስ በእርሳቸው ለመለዋወጥ በተሰባሰቡት በእነዚያ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ምን ዓይነት ሰይጣን ነው እንደዚያ ያለ ጉዳት ሊያደርስ የሚችለው፡፡

እራሴን ኢሞራላዊ በሆነች ወደክፋት ምድር መንሸራተት ጀመርኩ ። የጨለማው ጎን ኃይል ሲጠራኝ ሰማሁ፡፡ የጨለማው ጎን ኃይል ወደ እርሱ እንድቀርብ ሲስበኝ ለመስማት ችያለሁ፡፡

የአእምሮዬን ጥቂት ክፍል ለዓለም ለመስጠት ፈለኩ፡፡ ግን ሰላም በአምሮዬ አልነበረም፡፡ እ።ኤ።አ ሰኔ ፪፬ ቀን ፳፩፰ ዓ።ም ጧት ላይ ሰላም በእኔ ልብ ወይም አእምሮ ውስጥፈጥሞ አልነበረችም፡፡

እንደዚያ ተበሳጭቼ እሳት ነበልባል በነበርኩበት ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ቲ፡ሸርት ለብሰው ስለደረሰው አደጋ ንጝር ሲያደርጉ ከሌላ የቪዲዮ ክሊፕ ጋር ተገናኘሁ፡፡

በጣም ተረጋግተው እና ስብዕናቸውን ጠብቀው ነበር ንጝር የሚያደርጉት፡፡ ምንም ዓይነት የቅስቀሳ ምልክት አላሳዩም፡፡ በተለካ የንጝር ድምጸት ክብር እና ሞገስን በተላበሰ መልኩ ነበር ንጝር የሚያደርጉት፡፡ እንደዚህ ያለ አስደንጋጭ ሁኔታ በተፈጠረበት ጊዜ ምንም ነገር ሳያሳዩ ሙሉ በሙሉ በተረጋገ መንፈስ ነበር የሚናገሩ፡፡ ምናልባትም እንደዚህ ያለ ሞገስ የብዙ ጊዜ ልምድ ካለው ተዋጊ የሚጠበቅ ነው፡፡ ሆኖም ግን የእኔ ነብስ በሰኔ ፪፬ ጧት ላይ ከምንም በላይ ተፈትናለች፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን በማዳምጥበት ጊዜ ከመግለጫቸው ቃል በቃል፣ ሀረግ በሀረግ እየመዘዝኩ በመውሰድ በብስጭቴ ላይ ተጨማሪ ብስጭትን ለመጨመር መፈለግ ጀመርኩ ፡፡

ሆኖም ግን የእርሳቸው መልዕክት በፍቅር፣ በይቅርባይነት እና በዕርቅ ላይ የሚያጠነጥኑ ነበሩ፡፡

የሽብር ጥቃት ቀጥተኛ ኢላማ ሆነው ስለሰላም ነበር የሚናገሩት፡፡

እኛ በይቅርባይነት እና እርቅ ጎዳና ላይ ጉዟችንን እንድንቀጥል ነበር በመናገር ላይ የነበሩት፡፡

መግደል መሸነፍ ነው አሉ ፡፡ መግደል ውርደት ነው፡፡ ከወረዱት ሰዎች ጋር ወደ ታች ወርደን ዝቅ በማለት ታናሾች አንሆንም፡፡ ኢትዮጵያውያን ታላቅ ሕዝቦች ናቸው፡፡ በዚህ አስጸያፊ እና እኩይ ድርጊት ምክንያት ኢትዮጵያ ለፍቅር፣ ለይቅርባይነት እና ለአንድነት የዘረጋቻቸው እጆቿ አይታጠፉም አሉ ፡፡

በጦፈ ንዴት ውስጥ እያለሁ “ምን አይነት አነጋገር ነው ጃል ፦” በማለት ጮህኩ፡፡ ግኡዙን የኮምፒውተር ማሳያ መስኮት  “ስለምን እያወሩ ነው እኚ ጠቅላይ ሚንስትር ፧” በማለት ጠየቅሁ፡፡

ለዚህ ዓይነቱ የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ በሆነ ሰው ላይ ለምን አልጮኹም፧  በኃይል ቃል አልተናገሩም፧ በእንደዚህ ያለው ዓይን ያወጣ እልቂት እና ውድመት ጥረት ላይ አኛ ደጋፊዎቻቸዉን በሃይል የሚገፋ ነገር እንክዋን አይናገሩም እንዴ እኚ ሰው ብዬ እራሴን ጠየቅኩ፡፡

ከአብይ ምንም ዓይነት እርዳታ አላገኘሁም፡፡ ሁልጊዜ እንደማደርገው ሁሉ እውነታውን መናገር አለብኝ፡፡ እ.ኤ.አ ሰኔ ፪፬ ቀን ፳፩፰ አብይ አሕመድ የእኔን ቁጣ እና ንዴት ሰረቁኝ፡፡

አብይ አሕመድ ሰኔ ፪፬ ቀን የሁሉንም ሕዝብ ቁጣ እና ንዴት እንደሰረቁ አምናለሁ፡፡

ያ በእሳት ነበልባል ተሞልቶ የነበረው ክስተት አሁን አልፏል፡፡ ከበቀልተኝነት እና ከጥፋተኝነት የሁላችንንም ልቦች እና አእምሮዎች በማለዘብ ወደ ከፍታው የፍቅር እና ይቅርባይነት ጎዳና ስለመሩን አብይን ማመስገን አለብን፡፡

እውነታውን አውጃለሁ፡፡ እ.ኤ.አ ሰኔ ፪፫ ቀን ፳፩፰ ዓ.ም የእኛን ንዴት እና ቁጣ በመስረቅ አብይ አሕመድ ከእርስ በእርስ ጦርነት አድነውናል፡፡ እናም የፍቅር፣ የይቅርባይነት እና የእርቅ ቀን እንዲመጣ እና በዘላቂነት ለዘላለም እንዲቀጥል ለሚመጣው ትውልድ ሳይቀር አስተምረዋል፡፡

ለዚህም ነው ባለፈው የመጨረሻው ትችቴ ላለፉት ፩፫ ዓመታት ያህል ሳደርገው እንደነበረው ባህሪዬ ዓይነት ግብረ መልስ ያልሰጠሁት፡፡ በጣም ጥቂት ነገር ብቻ ብያለሁ፡፡ ይህንንም ያልኩት ስለዚያ ድፍረት የተሞላበት ያፈጠጠ እና የቦቅቧቃ ፈሪዎች ድርጊት የምለው በማጣቴ ምክንያት አይደለም፡፡ ልቤ በጨለማ ተውጦ ነበር ፡፡ ሆኖም ግን በሳይበር ስፔስ እንደ ጨረር እንደሚለቀቀው በተመሳሳይ መልኩ በአብይ አሕመድ የፍቅር ኃይል ተሸንፊያለሁ፡፡

መንግስታት፣ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ድጋፋቸውን እየገለጹ እና ጥቃቱን በማውገዝ ላይ ባሉበት ሁኔታ ሕዝቡን “ለአንድ ቀን በቀል ጥሪ ” ጥራ የምትል በሹክሹክታ ኤምሮዬ ዉስጥ የምትናገር ድምፅ ነበረች ፡፡

ሆኖም ግን ጥሪውን ማስተላለፍ አልቻልኩም ምክንያቱም አብይ አሕመድ እ።ኤ።አ ሰኔ ፪፬ ቀን ፳፩፰ ዓ።ም ጧት ልቤን እና አእምሮዬን የሸፈነውን ጥቁር መጋረጃ በመግፈፍ የፍቅር የይቅርባይነት እና የእርቅ መልዕክትን በልቤና ኤምሮዬ ዉስጥ ሞሉበት ፡፡

ከዚያም ማንዴላ ያስተማሩንን እና እንዲህ የሚለውን አስታወስኩ፣ “ደፋር ሰዎች ለሰላም ሲሉ ይቅርታን አይፈሩም“፡፡ አብይ አሕመድ ለሰላም ሲሉ እ።ኤ።አ ሰኔ ፪፫ ቀን ፳፩፰ ዓ።ም ተቀጣጥሎ በነበረው እሳት ላይ እውነተኛ ደፋርነታቸውን አሳይተዋል፡፡

ለዚህም ነው ለጨለማው ጎን ኃይሎች የአጻፋውን ግብረ መልስ በመስጠት ፋንታ እርሳቸው በድጋፍ ሰልፉ እና የጥቃት አደጋውን ተክትሎ ያቀረቡትን ንጝር በመተርጎም በእኔ ትንሽ መንገድ እርሳቸውን ለማክበር የፈለግሁት፡፡

ከጨለማው ጎን ኃይሎች የደረሰባቸውን አደጋ እና በእራሳቸው አንደበት የተናገሯቸውን ቃላት (ቢያንስ በእኔ ጥንካሬ በጎደለው የአተረጓጎም ዘይቤ) በመተርጎም እንግሊዝኛ ተናጋሪው ዓለም አብይ አሕመድን እንዲሰማቸው ስለፈለግሁ ነው፡፡ እንግሊዝኛ ተናጋሪው ዓለም የእኛን ወጣት ማንዴላ እና አስደናቂ ሰው ቃላትን እንዲያነብም  ስለፈለግሁ ነው፡፡

በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ እንደዚህ ያለ ልዩ እና አስደናቂ ክህሎት ባላቸው ወጣት መሪ የተባረከጭና የታደለች አገር ናት፡፡

አብይ አሕመድን መግለጽ፣

ለመሆኑ አብይ አሕመድ ማን ናቸው?

እድሜዋ  ከስድስት ዓመት የማይበልጥ አብይ አሕመድን ፍጹም በሆነ መልኩ መግለጽ የሚትችል አንድ ልጅ ብቻ አለች ፡፡ ስለዚያች  ልጅ ጥበብ ወደፊት በማዘጋጀው ትችቴ  በሰፊው እጽፋለሁ፡፡ (ለማየት እዚህ ይጫኑ ሳዶርን አዳምጡ)

ሆኖም ግን ቢያንስ ለዚህ ሳምንት አብይ አሕመድን ለመግለጽ የሚያስችል እንዳገኘሁ ማሰብ እችላለሁ፡፡ (ሁልጊዜ በማስብበት ጊዜ ከእኛ የማሰብ ምዕናብ ውጭ የሆነ በርካታ አስገራሚ መልካም ነገሮችን ይዘው የሚቀርቡ መሆናቸውን መግለጽ እወዳለሁ፡፡)

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የፍቅር፣ የይቅርባይነት እና የሰላም ሚስጥራዊ ያልሆኑ መሳሪያዎቻቸው ምክንያት በስፋት ታዋቂ ሆነዋል፡፡

የውበት ንድፉን ለማስቀመጥ ሚካኤል አንጄሎ ይጠቀምበት እንደነበረው የመሞረጃ መሳሪያ ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ አብይም እነዚህን መሳሪያዎች ለአመራራቸው ስኬታማነት እና ውበት በዋና መሞረጃነት ይጠቀሙባቸዋል፡፡

አብይ አሕመድ በመርከብ ላይ ተጣብቀው እንደሚኖሩት የውኃ ውስጥ ህዋሳት ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ ሁልጊዜ ሌት እና ቀን በዘመናት ጥላቻ፣ ጠብ አጫሪነት እና ስቃይ ተሞልተው እና እንደ ኮሶ ትል ተጣብቀዉን የቆዩትን ከልቦቻችንን እና አእምሮዎቻችንን ሞርደውልናል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በድጋፍ ሰልፉ ንጝራቸው በጣም የመሰጠኝ እና ያስደነቀኝን አንድ ነገር እንዲህ ብለዋል፣ “ዛሬ በሀብት ስለበለጸገችው እና ታላቅ ዝናን ስለተጎናጸፈችው ሆኖም ግን የፍቅር ረሀብ ስላለባት ሀገራችን ልነግራችሁ ከፊታችሁ ቆሚያለሁ፡፡“

እንደዚህ ነው የጀግና ንጝር፦ ይደልዎ ብለናል፡፡

ለ፪፯ ዓመታት ያህል ሁላችንም ፍቅርን ተርበናል ምክንያቱም በግዴታ ጥላቻን እንድንመገብ ተገደናል፡፡

እ.ኤ.አ ሰኔ ፪፫ ቀን ፳፩፰ ዓ።ም በመስቀል አደባባይ የታዩት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩት ሰዎች በሙሉ የፍቅር ረሀብ ሰለባዎች ናቸው፡፡ ሆኖም ግን በዚያን ዕለት ኩባያዎቻቸው በፍቅር ተሞሉ፡፡ ከእርስ በእርሳቸው እና ከኢትዮጵያዊነት ጋር በመገናኘታቸው አልራባቸውም፡፡

ፍቅር በልብ ውስጥ ይኖራል ይባላል ፡፡

ላለፉት ፪፯ ዓመታት ጥላቻ፣ ልዩነት አና በቀልን በደም ስሮቻችን እና በልቦቻችን ስንጋት ኖረናል፡፡

ከአብይ አሕመድ ጋር በመምጣት ጥላቻን ከልባችን ውስጥ በማጥፋት ልቦቻችን በፍቅር እንዲሞሉ ሆነዋል፡፡ የኢትዮጵያዊነት ፍቅር፡፡ የሀገራችን ፍቅር፡፡ የእርቅ ትርጉም የሆነው የእርስ በእርስ ፍቅር፡፡ የእውነት ፍቅር፡፡ የፍጥ ፍቅር፡፡ የነጻነት ፍቅር፡፡ የዴሞክራሲ ፍቅር፡፡ የሕግ የበላይነት ፍቅር፡፡ ፍቅር፣ ፍቅር፣ ፍቅር…

ጓደኞቼ ይኸ ነገር የአብይ ታዕምራዊ ነገር ነው፡፡

በቶን የሚቆጠር ጥላቻን ወስደው ወደ ተጣራ ፍቅር መለወጥ የሚቻላቸው ብቸኛው ታዕምራዊው ኃይል እርሳቸው ናቸው፡፡

ድንጋይ ልብን በመውሰድ ወደ ወርቅ ልብነት መለወጥ ይችላሉ፡፡

በአሁኑ ጊዜ የጨለማው ጎን ልብየለሽ ኃይሎች ልቦቻቸው በጊዜ ሂደት በጥላቻ ከሚገባው በላይ የተሰበሩ እና መጠገን የማይችሉ በመሆናቸው የአብይን በር በማንኳኳት አዲስ ልቦች እንዲሰጧቸው እንደሚጠይቁ አልጠራጠርም፡፡ አብይ እግሮቻቸውን ስመው አዲስ ልቦችን በደስታ ለመስጠት እንደሚችሉ ላረጋግጥላቸው እወዳለሁ፡፡

ለዚህም ነው እንግዲህ አብይ አሕመድን መደገፍ ያለብን፡፡ ምርጥና መልካም  ነገሮችን ከዉስጣችን ያወጣሉ። የመጥፎነትንና ክፋትን መርዝ ካአምሮአችንና ከልባችን ያስወግዱልናል፡፡

የፋይናንሺያል ታይምስ ጋዜጣ አብይ አሕመድን “በአፍሪካ በጣም  ታዋቂ ፖለቲከኛ ዕ ሳይሆኑ አእቀሩም ብሎ ፃፈ ።” እናም “የኢትዮጵያው ማንዴላ” በማለት እንደሚጠራቸው ጽፏል፡፡

የሚገርም ነገር ነው እባካችሁ፦ በአፍሪካ አህጉር ይቅር እና አንድ በሀገሩ ውስጥ በውል የማይታወቅ ሰው ከሶስት ወራት ባነሰ ጊዜ ውስጥ እንዴት “በአፍሪካ በጣም ታዋቂ ፖለቲከኛ” ተብሎ ሊጠራ ይችላል፧ ይኸ ጉዳይ አመክንዮአዊ እና ምዕናባዊ ትንበያን ይክዳል፡፡

ሆኖም ግን በኢትዮጵያ ውስጥ “የአህጉሩ ታዋቂ ፖለቲከኛ” የእያንዳንዱ ሰው ልጅ፣ ወንድም፣ አጎት፣ የአጎት ልጅ፣ ጎረቤት፣ ጓደኛ እና የስራ ባልደረባ ናቸው፡፡ እንግዲህ በመንገድ ላይ የሚሄዱ ወንድ፣ሴት እና ልጅ ስለአብይ የሚያስቡት እንደዚህ ነው፡፡ ቅን እና የተግባር ሰው ናቸው፡፡ ታዕምራዊ የሆነ ስብዕና አላቸው፣ እናም የሰዎችን ቀልብ የመሳብ ኃይል አላቸው፡፡ ለምሳሌ ያህልም እኔን፡፡ እውነት ለመናገር አብይን እንደ ዕመሪዕ ለማየት ያስቸግረኛል ፡፡ እርሳቸውን እንደ ወንድሜ ነው የማያቸው፡፡ የእኛ ወንድም የእኛ ልጅ ናቸው ፡፡

እኔን የማታምኑኝ ከሆነ የስድስት ዓመቱቷ  ህጻን ሳድርን አዳምጡ፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣን በያዙ ስድስት ቀናት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ እንዴት “የኢትዮጵያ ወጣት መሪ አድርጌ እቆጥረዎታለሁ፡፡ ከእርስዎ ጋር ከጎንዎ ነኝ ” በማለት እንዴት እንደጻፍኩ ብዙ ሰዎች ሁልጊዜ ይጠይቁኛል፡፡

በጥቂት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ የአብይ አሕመድን ንጝሮች ክሊፖችን ብቻ በመመልከት ለጠቅላይ ሚኒስትርነት መመረጣቸውን ማጽደቄ እውነት ነው፡፡ ሌላ ምንም ነገር የለም፡፡ ሆኖም ግን በክሊፖች የሚያስተላልፏቸው መልዕክቶች ጠንካራ እና አሳማኝ፣ አስተሳሰባቸው ግልጽ፣ የክርክር ጭብጣቸው አመክንዮአዊነት ያለው እና የሚያሳምን፣ ባህሪያቸው ትሁት፣ ታማኝ እና ግልጽ ናቸው፡፡

ለእኔ ገና ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ አብይ አሕመድን ማግኘታችን ግልጽ ሆኖልኛል፡፡ ቪዲዮ ክሊፖችን ደግሜ እና ደጋግሜ በመመልከት ምንም ዓይነት ውዝግብ ውስጥ በማይከት መልኩ አብይ አሕመድ የወጣቱ ትውልድ (አቦሸማኔው) መሪ መሆናቸውን አውቂያለሁ፡፡ ላለፉት አስራ ሶስት ዓመታት ሳልም የቆየሁት የሳችዉን አይነት ወጣት መሪ ነበር ፡፡

እ.ኤ.አ በ፳፩፫ ዓ።ም “የኢትዮጵያ ወጣቶች ከተባበራችሁ በፍጹም አትሸነፉም” የሚል መፈክር አውጥቸ ነበር፡፡ በዚህም መሰረት እንደ አብይ አሕመድ ያለ ወጣት ከየትም በመውጣት ፯፭ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን አቦሸማኔዎችን (ወጣቱን ትውልድ) በጨቋኞች ላይ በማስነሳት ወደ ድል እና ወደ ነጻነት እንደሚመራ አውቅ ነበር፡፡

ትንሽ እራስን ከፍ የሚያድርግ ንጝር ነው በማለት ቅር እንዳትሰኙ አንባቢዎቼ ይቅርታ እንደምታደርጉልኝ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ አብይ አሕመድ የእኛ ማንዴላ እንደሆኑ የተናገርኩ እኔ እንጅ ፋይናንሻል ታይምስ፣ ኒዮርክ ታይምስ ወይም ደግሞ ሎስ አንጀለስ ታይምስ አይደሉም፡፡ ይህንን በሚመለከት እ።ኤ።አ ሚያዝያ ፩፭ ቀን ፳፩፰ ዓ።ም ያቀረብኩትን ማስታዋሻ ቁጥር ፩ን እንድታነቡ እጋብዛለሁ፡፡ የእኔን ድምዳሜ ለማጠናከር የማንዴላን ክህሎት የሚያንጸባርቁ የእኛው ማንዴላ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን እና የማንዴላ ዓይነት ባህሪዎች በአብይ አህመድ ስብዕና ውስጥ የሚታዩ መሆናቸውን በቁጥር እየዘረዘርኩ በማቅረብ ግልጽ አድርጊያለሁ፡፡

የመጀመሪያውን ማስታዋሻየን ለማጠቃለል አብይ አሕመድ የማንዴላን ኮቴዎችን በመከተል መስራት እንዲችሉ ስልጣኑ እና ልዩ የሆነ መልካም አጋጣሚ  ያላቸው ኢትዮጵያዊ ጀግና  መሆናቸውን በመግለጽ ጽፊያለሁ፡፡ ከዚህም አልፈው አፍሪካዊ ጀግና ይሆናሉ ብዬ ተነበይኩ ፡፡

አብይ አሕመድ እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ጀግና ይሆናሉ በማለት ትንበያ ሰጥቸበት የነበረው  ትንበያ ደርሷልን?

ከዚህም ባለፈ አብይ አሕመድ እውነተኛ የአፍሪካ ጀግና የሚሆኑ መሆናቸውን የሚጠራጠር ይኖራልን?

በሌላው ይቅር እና በእኔ ጉጉ ምዕናባዊ እሳቤ እንኳ ቢሆን ከ፺ ቀናት ባነሰ ጊዜ ውስጥ አብይ አሕመድ ከማንዴላ ከፍታ ላይ ይደርሳሉ ብዬ አላሰብኩም ፡፡ ምናልባትም ከጥቂት ዓመታት በኋላ፡፡ ሆኖም ግን ከ፺ ቀናት ባነሰ ጊዜ ውስጥ እንዴት ሊሆን ይችላል እያልኩ በመገረም እጮሃለሁ።

ስለዚህ ለነገሩ በአእምሮዬ ውስጥ ያለውን እና የሚከነክነኝን እንዲህ የሚል ጥያቄ እጠይቃለሁ፣(ትንሽ ተስገብግቤ እንደሆን ይቅርታ አድርጉልኝ፡፡) በአሁኑ ጊዜ የእኛ ማንዴላ አለን፡፡ እርሳቸውን ለቀሪው አፍሪካ ማካፈል ግዴታ አለብን?

ለእልቂቱ ጠርዝ እንዴት ቅርብ እንደሆንን፡ ከጥቃቱ ጀርባ ዕሶስተኛዕ ወገን ነበረን?

እ.ኤ.አ ሰኔ ፪፫ ቀን ፳፩፰ ዓ።ም ፍጹም በሆነ መልኩ ነገሮች ሁሉ ወደ መጥፎነት እንደተቀየሩ ሳስብ በዛር እንደተለከፈ ሰው ያንቀጠቅጠኛል፡፡

እንዲህ ከሚለው ከማርቲን ሉተር ኪንግ ማስጠንቀቂያ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ፊት ለፊት፣ “ዓይን ላጠፋ ዓይን የሚጠፋ ከሆነ ሁሉንም የሀገሪቱን ሕዝቦች ዓይነ ስውር ያደርጋል፡፡“

እ.ኤ.አ ሰኔ ፪፫ ቀን ፳፩፰ ዓ።ም አሸባሪዎች በጥቃታቸው ተሳክቶላቸው ቢሆን ኖሮ በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ የመቶ ሚሊዮን ዓይነ ስውር ሀገር ትሆን ነበር፡፡

ሆኖም ግን እኛ ከላይ አምላክ ምልከታ ስር ነበርን፡፡

ስጦርነት እና የውድመት መጥፎነት ከታሪክ ባልማር ኖሮ መናገር አልችልም ነበር፡፡

የጸረ አፓርታይድ የነጻነት ታጋዩ እና ዋና ስራ አስፈጻሚው እና  የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ የጦር ክንፍ ( ምኮንቶ ሲዝዌ)  የነበሩት የጦር አዛዥ ክርስ ሃኒ በተገደሉ ጊዜ ደቡብ አፍሪካ ምን ያህል ወደ ውስጣዊ ውድቀት ተቃርባ እንደነበር አውቃለሁ፡፡

እጅግ በጣም የተበሳጩ እና የተቆጡ በመቶዎች እና በሺዎች የሚቆጠሩ ጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን በኬፕታውን፣ በደርባን፣ በፖርት ኤልሳቤጥ፣ በፒተርማሪትበርግ እና በሌሎች ከተሞች እንደጎርፍ ፈሰሱ፡፡ “ምንም ዓይነት ሰላም የለም፦ ጦርነት፦ ጦርነት፦ ግደሏቸው፡፡ ለመዋጋት እንፈልጋለን፦” እያሉ በመጮህ በመንገዶች ላይ ይጓዙ ነበር፡፡

በግጭቱ አደጋዎች እየከፉ በሄዱ ጊዜ በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ደቡብ አፍሪካውያን ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ መቱ፡፡ ማንዴላ በስዌቶ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩትን ወጣት ጥቁር አፍሪካውያን ለመግደል ወይም ደግሞ ለመግደል ሙከራ የሚያደርጉትን ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ተነሳሽነታቸውን አሳዩ፡፡

በዚያን ዕለት ማንዴላ ቀደም ሲል የከፈሏቸውን መስዋዕተነቶች ሁሉ ሊያሳጣ የሚችል ሁኔታ እየቀረበባቸው መጣ፡፡ በጠቅላላው የ፪፯ ዓመታት እስረኝነት መስዋዕትነታቸው እንደጉም በኖ ሲጠፋ ታያቸው፡፡

የድምጽ ማጎያውን በመንጠቅ እንዲህ በማለት ተናገሩ፣ “የእናንተን ንዴት እገነዘባለሁ፡፡ የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ መንግስት ለመሆን በመጠባበቅ ላይ ነው፡፡ እናም እንደ መንግስት አባልነት ስርዓት ያለው መንገድ መያዝ እና ክብርን የመጠበቅ ኃላፊነት አለባችሁ፡፡“

እ.ኤ.አ ሚያዝያ ፩፱ ቀን ፩፱፱፫ ዓ።ም በሀኒ የቀብር ስርዓት ላይ የሕይወት ታሪካቸው በሚነበብበት ጊዜ ኔልሰን ማንዴላ ዕበሶስተኛ ወገን ኃይልዕ የሕግ እና ስርዓት ሚኒስትር እና የጦር ኃይሎች ዋና አዛዥ በነበረው ላይ እጃቸውን በመቀሰር ለሀኒ መገደል እና በሀገሪቱ ላይ ለደረሰው ስቃይ ተጠያቂ እንደሆኑ አረጋገጡ፡፡

እ.ኤ.አ ሰኔ ፪፫ ቀን ፳፩፰ ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ላይ በተሞከረው ጥቃት ከጥቃቱ ጀርባ ዕሶስተኛ ወገንዕ ኃይል ነበርን?

ማለት የተፈለገው ማንዴላ እ.ኤ.አ ሚያዝያ ፲ ቀን ፩፱፱፫ ዓ።ም የዋለችዋን ዕለት እልቂት የሚፈጸምባት ዕለት እንዳትሆን ጠብቀዋታል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ አብይ አሕመድ እ.ኤ.አ ሰኔ ፪፫ ቀን ፳፩፰ ዓ።ም የዋለችዋ ዕለት የሁከት እና የእልቂት ዕለት እንዳትሆን ጠብቀዋታል፡፡

ደባ ሸራቢዎቹ ማንም ይሁኑ ማን እ.ኤ.አ ሰኔ ፪፫ ዋናው ዓላማቸው የጎሳ የእርስ በእርስ ጦርነት ክብሪት ለመጫር ነበር፡፡

ሆኖም ግን የፍቅር ኃይል የእነርሱን የጥላቻ ኃይል እንደ ጉም እንዲበን አደረገው፡፡ የአምላክ እውነተኛው የፍቅር ኃይል ሰው ሰራሹን የቦምብ ኃይል አውዳሚነት ድል አደረገው፡፡

ለፍርድ በችኮል መሮጥ የለብንም፣

ከፍንዳታው ጋር በተያያዘ መልኩ በቁጥጥር ስር ስለዋሉት ተጠርጣሪዎች አስር ወይም ከዚያ በላይ ያሉትን የፖሊስ መኮንኖች ጨምሮ ጥቂት ቃላትን ማለት እፈልጋለሁ፡፡

በርካታ ሰዎች ከደባው ጀርባ ወይም ደግሞ ጥቃቱን ያቀነባበሩት “የተለመዱት ተጠርጣሪዎች” እንደሚሆኑ ጥርጣሬ እንዳላቸው አውቃለሁ፡፡ ሌሎች ጥቂቶች ደግሞ በሴራው ውስጥ ሌላ የማይታይ የሶስተኛ ወገን እጅ እንዳለ ሀሳብ ያቀርባሉ፡፡

በዚህ ደረጃ ላይ አሁን በቁጥጥር ስር ያሉት ተጠርጣሪዎች መሆናቸውን በቅንነት ማመን አለብን፡፡ ሌላ ነገር የለም፡፡ ጥርጣሬ ማስረጃ ወይም ማረጋገጫ አይደለም፡፡

ለዚህም ነው ሁሉንም ኢትዮጵያውያን ስለተጠርጣሪዎች ያሏቸውን ጥርጥሪያቸውን ሁሉ በእራሳቸውም ላይ እንዲጠብቁ እየጠየቅሁ ያለሁት፡፡

አሁን አዲስ ቀን ነው፡፡ የሕግ የበላይነት በኢትዮጵያውያን አድማስ ላይ በሚያስደንቅ ሁኔታ በመንገስ ላይ ነው፡፡ ለተወደደችዋ ኢትዮጵያ የመሰረት ድንጋይ የሕግ የበላይነት ነው፡፡ ሁሉም የወንጀል ተጠርጣሪዎች ሁሉ በሚገባ በተደራጀ መሰረት በተቋቋመ ነጻ የሆነ የፍትሕ አካል የጥፋተኝነት ብይን እስካልተሰጠ ድረስ  ከምንም ጥርጣሬ በላይ ንጹሀን መሆናቸው መታወቅ አለበት፡፡

ይህ ጉዳይ ዝም ብሎ የሕግ ፍሬ ከርስኪ አይደለም፡፡ የሰለጠነ የወንጀለኛ መቅጫ ስርዓት አልፋ እና ኦሜጋ ነው፡፡ እንዲሁ ያለበቂ ማስረጃ ወደ ፍርድ ዘለን መግባት የለብንም፡፡ የንዴት ቀለማችንን ወደ ፍርድ ቀለም ለመለወጥ መፍቀድ የለብንም፡፡

ይህንን ጉዳይ እጅግ በጣም ላሰምርበት እፈለጋለሁ ፡፡ በቁጥጥር ስር ያሉት እያንዳንዳቸው እነዚህ ተጠርጣሪዎች በኢትዮጵያ ሕገ መንግስት በተረጋገጡ የሕግ አማካሪ ተቀጥሮላቸው  ፍጥ እስከሚያገኙ ድረስ ጥፋተኞች አይደሉም፡፡

በዚህ መልኩ ሕዝቡን ያስጠነቀቅሁ ቢሆንም የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መንግስት ጥንቃቄ በተመላበት ሁኔታ እና ሕገ መንግስታዊ መብቶቻቸውን ባከበረ መልኩ በዚህ አሰቃቂ አደጋ የተከሰሱ ሰዎችን የሕግ ሂደት እንደሚከታተለው ምንም ዓይነት ጥርጣሬ የለኝም፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የአሜሪካው የፌዴራል ምርመራ ቢሮን (ፍብዒ) ወደ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲገባ እና በሀገር ውስጥ ካለው አቻው ጋር በመገናኘት በቅንጅት በመስራት ደባውን ከስሩ አጣርቶ እውነታው እንዲወጣ በመጋበዛቸው በጣም ደስ ብሎኛል፡፡ የፍብዒ ተሳትፎ መኖር ምርመራው ጠንካራ፣ የሚታሰብበት፣ አጠቃላይ እና ከፍተኛ የሆነ ሞያዊ ብቃት የተንጸባረቀበት ይሆናል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት እንደሚሰፍን በተለያዩ አጋጣሚዎች ቃል ገብተዋል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ በተለያዩ አጋጣሚዎች አንድ ንጹህ ሰው በሽተት ክስ ከሚመሰረትበት ይልቅ መቶ ወንጀለኛ ሰዎች በነጻ ቢሰናበቱ እንደሚሻል ተናግረዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አመራር በቁጥጥር ስር ባሉት ተጠርጣሪዎች ላይ ፍጥን ፍትሀዊ በሆነ መንገድ ሊያረጋግጥ እንደሚችል ሙሉ እምነት አለኝ፡፡

ሰይጣናዊነት በፍጹም አይተኛም፡ ለጨለማው ጎን ኃይሎች ያለኝ ትንበያ፣

ሰይጣናዊነት አይተኛም ይባላል፡፡

የጨለማው ጎን ኃይሎች በሰላማዊ ሰልፍ ላይ ቦምብ በማፈንዳት ላይ አያቆሙም፡፡

በጨለማ ውስጥ ደባ እና አሻጥር መስራትን ይቀጥላሉ፡፡

ሁሉንም ዓይነት ሰይጣናዊ ድርጊቶችን መፈጸማቸውን ይቀጥላሉ፡፡ በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች የሚገኙት ወጣቶች ብጥብጥ፣ ውድመት እና እልቂትን እንዲቀሰቅሱ ገንዘብ ይከፍላሉ፡፡

በሽብር ድርጊቶች ላይ ይሰማራሉ፡፡

በመሪዎቻችን ላይ ሌላ ጥቃት ለመሰንዘር ይሞክራሉ፡፡

በቁልፍ መሰረተ ልማቶች ላይ የኃይል ማመንጫ ተቋማትን እና ቴሌኮሙኒኬሽንን ጨምሮ  አሻጥሮችን ለመስራት ሙከራ ያደርጋሉ፡፡ ግራ መጋባት እና ውድመትን በመፍጠር ወደ ኋላ ወደ እነርሱ የጨለማ ምድር ለመመለስ የሚችሉትን ማንኛውንም ነገር ሁሉ ያደርጋሉ፡፡

ሆኖም ግን ከዚህ በኋላ የጨለማ እና የጥላቻ ምድር ወደነበረችው መመለስ የለም፡፡ አንድ ጊዜ ብርሀን ካየህ በኋላ ወደ ጨለማ መመለስ የሚቻል አይደለም፡፡

የጨለማው ጎን ኃይሎች ከሁሉም በላይ እንዲህ የሚለውን አንድ ሀቅ ሊገነዘቡ ይገባል፣ “በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚሊዮን በላይ አብዮች አሉን፡፡ አብይ አሕመድ በተለያዩ ምክንያቶች መቀጠል ባይችሉ ምልዮኞቹ  ተቀብለው መምራት ይችላሉ፡፡“

ለጨለማው ጎን ኃሎች እንዲህ የሚለውን ሀቅ ልንገራቸው፣ “የእናንተ ቁጥር አንድ መቶ ነው፡፡ እኛ ግን መቶ ሚሊዮን ጠንካሮች ነን፡፡ ኢትዮጵያ ጠንካራ ናት፦“

የፍቅር፣ የይቅርባይነት እና የእርቀ ሰላምን ተዋጊዎች ለማሸነፍ የበረዶ ኳስ ወደ ገሀነም ገብታ ሳትከልጥ መውጣት ይቀላል ፡፡ ቀልድ እየቀለድኩ አይደለም፡፡ ስለሚኖሩበት ገሃነም ከናንተ በላይ የሚያውቅ የለም፡፡

እስቲ በጨለማው ምድር ላይ ስለሚኖሩት ትንበያ ልስጥ

በደንብ አዳምጡ፦

ላለፉት ፩፫ ዓመታት በሰይጣናዊ ድርጊታችሁ የምትቀጥሉ ከሆነ ምን ሊከሰት እንደሚችል በገሃድ አሳዉቄአቸህዋለሁ ነግሪያችኋለሁ፡፡ ወደ ኋላ ተመለሱ እና ሳምንታዊ ትችቴን አንብቡ፡፡

እ.ኤ.አ ከ፳፩፩ ዓ።ም ጀምሮ በየጊዜው እና በተደጋጋሚ እንዲህ የሚለውን የጋንዲን የማይሞት እና ጊዜ የማይሽረውን ትንቢት ስደግምላችሁ ቆይቻለሁ፣ “ተስፋ በማጣበት ጊዜ በታሪክ የእውነት እና የፍቅር መንገድ ሁልጊዜ አሸናፊ እንደሆነ አስታውሳለሁ፡፡ ጨቋኝ ገዥዎች እና ገዳዮች አሉ፡፡ ለጊዜው የማይበገሩ መስለው ይታያሉ፡፡ ሆኖም ግን በመጨረሻ ሁልጊዜ ይወድቃሉ፡፡ ይህንን ሁልጊዜ አስቡ፡፡“

እናንተም የማትበገሩ አይደላችሁም፡፡ ወድቃችኋል እናም አትነሱም፦

እ።ኤ።አ ሰኔ ፳፩፫ ዓ።ም “በቆሻሻ ቅርጫት ውስጥ ትጣላላችሁ” ምክንያቱም ኢትዮጵያ ተነስታለች በማለት ተንብዬ ነበር፡፡

እ.ኤ.አ ግንቦት ፳፩፭ ዓ።ም “በኢትዮጵያ ውስጥ የገነባችሁት የአሸዋ ግንብ በሕዝባዊ ቁጣ ማዕበል በአንድ ጊዜ ይናዳል” በማለት ተንብዬ ነበር፡፡

ላለፉት ፩፫ ዓመታት በየሳምንቱ በመጨረሻ የእውነት፣ የፍቅር እና ሰላም ያሸንፋሉ በማለት ስነግራችሁ ቆይቻለሁ፡፡

እ.ኤ.አ በ፪፻፮ ዓ.ም “በጦር ሜዳ በመገኘት በደም በመነከር እና የሬሳ ክምርን በመቆለል ሳይሆን የመልካም ወገኖችና ዜጎች ልቦች እና አእምሮዎች በመያዝ እናሸንፋችኋለን” በማለት ተንብዬ ነበር፡፡

እ.ኤ.አ ሰኔ ፳፩፰ ዓም አሸንፈናችኋል፡፡ የእውነት፣ የፍቅር እና የሰላም ሕጎች መንገድ የኢትዮጵያውንን ልቦች እና አእምሮዎች እያሸነፈ በገሃድ ይታያል ፡፡

ለእኔ ትንቢታዊ ቃላት ትኩረት ስጡ፡፡ ላለፉት ፩፫ ዓመታት ወደ ኋላ እንደገና ተመለሱ እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ትችቶቸን አንብቡ፡፡ ሁሉም ትንቢቶቼ እውን ሆነዋል፡፡

የመጨረሻውን የማስጠንቀቂያ ትንቢቴን እሰጣችኋለሁ፡፡ አብይ አሕመድ በኢትዮጵያ ታሪክ በአሁኑ ጊዜ ካሏችሁ በአንደኛ ደረጃ ያለ ጓደኛችሁ ናቸው፡፡ ከጨለማው ንጉስ ጠባቂያችሁ ናቸው፡፡ አብይ በእናንተ እና በአራቱ የምጽአት ቀን ፈረሶች መካከል የቆሙ የፍቅር ኃይል ናቸው፡፡

የምትችሉትን ያህል ሞክሩ፡፡ ሆኖም ግን በምንም ዓይነት ሁኔታ በፍጹም አብይ አሕመድን መጉዳት አትችሉም ምክንያቱም በሰላሙ ንጉስ ይጠበቃሉና፡፡

ምንም ዓይነት ሰይጣናዊነት ድርጊት በእርሳቸው ላይ አይፈጸምም፡፡ በሞት ጥላ ስር በእናንተ መካከል ከመንቀሳቀስ አይፈሩም፡፡

እ።ኤ።አ በ፳፩፫ ዓ.ም የሰጠሁትን ትንበያ ትኩረት ስጡት፡፡ በሰይጣናዊ ድርጊታችሁ የምትቀጥሉበት ከሆነ ጉምን ትዘግናላችሁ በማለት እንዲህ የሚል ማስጠንቀቂያ ሰጥቻለሁ፣ “መለስ እና አምላኪዎቹ በኢትዮጵያ ላይ መሰረታዊ የሆነ ችግር እየፈጠሩ ነው፣ በመሆኑም ከዚህ ዕኩይ ምግባራቸው የማይታቀቡ ከሆነ ጉምን ይዘግናሉ፦“

እ.ኤ.አ ሰኔ ፳፩፰ ዓ።ም እንዲህ በማለት እነግራችኋለሁ፣ “አብይ አሕመድ በእናንተ እና ሁሉንም ነገር ጠራርጎ በሚያጠፋው የአውሎ ነፋስ ማዕበል መካከል የቆሙ ብቸኛው የፍቅር ኃይል መሆናቸውን እንድታስተውሉ እማጸናለሁ፡፡“

አብይ አሕመድን ለመጉዳት የምትቀጥሉ ከሆነ ከአውሎ ነፋሱ ጋር ለዘላለም ተጠራርጋችሁ እንደምትጠፉ ጸሐይ ነገ ትወጣለች የሚለውን ያህል ላረጋግጥላቻሁ እወዳለሁ፡፡

እርሳቸውን ለመጉዳት የምታስቡ ከሆነ የእራችሁ ጎራዴዎቻችሁ ልቦቻችሁን ይወጋሉ፡፡

ስለሆነም በሰላም ኑሩ፡፡

ወገኖቼ በሰላም ይኑሩ፡፡

በሰላም እና በፍቅር ኑሩ፡፡

በሰላም እና በፍቅር ወደ ጸሐይ መውጫ ጋልቡ፡፡

ባለፉት ፪፯ ዓመታት በሕገ ወጥ መንገድ በዘረፋችሁት እና ባከማቻችሁት አስገራሚ የሆነ ሀብት እየተደሰታችሁ ለጥቂት ዓመታት ቆዩ፡፡

ከዚያም ምድሪቱን እኛ እንወርሳለን እናም ሰላምን እና ባለጸግነትን እናጣጥማለን፡፡

እንዲህ የሚል አንድ የተሻለ መንገድ አለ…የአብይ አሕመድ የፍቅር፣ የይቅርባይነት፣ የዕርቅ እና የሰላም መንገድ

መንገዱ ጠፍቷቸው በጨለማ ምድር ላይ ለሚዳክሩት ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን መልካም ዜና አለኝ፡፡

መንጠቅ በማለት ውጡ እና ከብርሀን ጎን ኃይሉ ጋር ተቀላቀሉ፡፡ መንጠቅ በማለት ውጡ እና የእኛ የፍቅር ብርህን በእራሳችሁ ላይ እንዲያበራ ፍቀዱ፡፡

ከእኛ ከሁላችንም ጋር በኢትዮጵያ ውስጥ ከጸሐይ በታች የተከበረ ቦታ ይኖራችኋል፡፡ የኢትዮጵያ ምድር ከጨለማው ምድር በእጅጉ የበለጠ ቆንጆ ነው፡፡

ኑ እና ተቀላቀሉን እናም እጅ ለእጅ በመያያዝ ማንዴል ለእኛ በሰየሙልን መልካም ነገር እና ይቅርባይነት በሚባሉት ሁለት መንገዶች አብረን እንጓዝ፡፡

ኑ እና በእኛ የፍቅር ባቡር ተሳፈሩ፡፡ ይህንን የምታደርጉ ከሆነ በሰውነቴ በሚገኝ በማንኛውም ነገር ሁሉ ለእናንተ እዋጋላችኋለሁ፡፡

በፍቅር ብርሀን የተዳሰስን ሰዎች እናስተውል፡፡

በጨለማው ጎን እንዳሉት ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ሁሉ እኛም ጉድለቶች አሉን፡፡ በሁለታችን መካከል ያለው ብቸኛው ልዩነት ክብርና ሞገስ ነው፡፡ እኛ ልቦቻችንን እንድንከፍት እና የፍቅር ብርሀን ወደ ልቦቻችን እንዲገባ እንፈቅዳለን፡፡ ያ ትንሽ የፍቅር ብርሀን ከጨለማው ልብ በጥላቻ በመሞላቱ የእኛ ወንድሞች እና እህቶች ለአደጋ እንዲጋለጡ  ሆነዋል ፡፡

ሆኖም ግን ወደ ውስጥ እራሳችንን በመመርመር በልቦቻችን እና በአእምሯችን ውስጥ ምን ሰይጣናዊ ድርጊት እየተፈጠረ እንዳለ መመርመር ያስፈልጋል፡፡

በደም ስራችን ውስጥ ተዋህደው ያሉትን ጥላቻ፣ በቀል እና ጥልቅ የበቀልተኝነት ጥላቻን በቅንነት እንዴት መንግለን ማስወገድ እንችላለን?

እራሳችንን ከሀጢያት የነጻን አድርገን ማቅረብ የለብንም ምክንያቱም በወንድሞቻችን እና በእህቶቻችን ላይ ስላሉት ሰይጣናዊ ድርጊቶች አመልካች ጣቶቻችን ሲንቀስር  ሌሎቹ ሶስቱ ጣቶቻችን ደግሞ ወደ እኛ እንደሚያመላክቱ መገንዘብ አለብን፡፡

ለጥላቻ የምናባክነው ጊዜ አይኖርም፡፡ ሆኖም ግን ለፍቅር፣ ለይቅርባይነት፣ ለዕርቅ እና ለሰላም ብቻ ነው ጊዜ ያለን፡፡

እንግዲህ ይህንን ነው ወጣት መሪያችን እያስተማሩን ያሉት፡፡ በእርግጥ እነዚህን ነገሮች እራሳቸው አልፈጠሯቸውም፡፡ ከጋንዲ፣ ከማርቲን ሉተር ኪንግ እና ከኔልሰን ማንዴላ የተማሯቸው ናቸው፡፡

አሁን ከእርሳቸው መማር አለብን፡፡

በጨለማው ጎን በወጥመድ ተይዘው ላሉት ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን እጆቻችንን እና ልቦቻችንን ለሰላም እንዘርጋላቸው፡፡

በአንድ ወቅት አንድ ፈላስፋ እንዲህ ብሎ ነበር፣ “በመከራ ውስጥ ለብዙ ጊዜ የምትቆይ ከሆነ መከራው እራሱ ከእንተው ውስጥ በመግባት ይዋሀዳል፡፡“

ከጥላቻ ጋር ለብዙ ጊዜ የምንቆይ ከሆነ ጥላቻ እራሱ በእኛው ህዋሳት ውስጥ ሰርስሮ ይገባል፡፡ እናም በስብዕናችን ላይ ይነግስብናል፡፡

“ጭራቃዊ ሰይጣንን የሚዋጋ ሁሉ እርሱ እራሱ ሰይጣን ያለመሆኑን ማየት እንዳለበት” አንርሳ፡፡

እ.ኤ.አ ሰኔ ፪፬ ቀን ፳፩፰ ዓ።ም ያ ጭራቃዊ ሰይጣን በእኔ ልብ ውስጥ መጥፎ ገጽታውን አሰልጥኖ ነበር፡፡ ሆኖም ግን አብይ አሕመድ ከመቅጽበት አባረሩት፡፡

በዚህ ወሳኝ በሆነው የታሪካችን ምዕራፍ ላይ በልቦቻችን ውስጥ ተደብቆ ለሚገኘው ጭራቃዊ ሰይጣን ላይ የፍቅር ብርሀን እንድናበራበት እፈልጋለሁ፡፡

የየዕለት የፍቅር እና የይቅርባይነት መድሀኒታችንን እስከወሰድን ድረስ ያ በልቦቻችን ውስጥ ቤቱን ሰርቶ የሚገኘው የጥላቻ ጭራቅ አቅመቢስ ሆኖ ይቀራል፡፡

ባለፉት ፪፯ ዓመታት ከጥላቻ እና ከልዩነት ይልቅ ፍቅር እና አንድነት ነግሰው ቢሆን ኖሮ ነገሮች ሁሉ እንዴት መለወጥ እንደሚችሉ ሳስብ ጥልቅ ሀዘን ይሰማኛል፡፡

የጨለማው ጎን ኃይሎች የብርሀን እና የፍቅርን መንገድ ቢመርጡ ኖሮ እንዴት ያሉ ልዩ ልዩ ነገሮች ይከሰቱ ነበር?

እኛን ከመከፋፈል ይልቅ ወደ አንድነት የሚያሰባስቡን ቢሆን ኖሮ፣ ክልል የሚባሉትን የአፓርታይድ አይነት የዘረኝነት ማጎሪያ የጥላቻ በረቶችን ከመገንባት ይልቅ በልቦቻችን እና በአእምሯዎቻችን ውስጥ ፍቅርን ቢያስፋፉ ኖሮ ነገሮች ሁሉ እንዴት ያሉ ልዩዎች ይሆኑ ነበር?

ሆኖም ግን አሁንም ቢሆን ትክክለኛውን ነገር ለማድረግ ጊዜው አልረፈደም፡፡ ትክክለኛውን ነገር ለመስራት በፍጹም የተሳሳተ ጊዜ የለም፡፡

የኃይል ሚዛኑን ለማጠናከር እና ለማስፋት (ጥረቶቻቸውን አጉልቶ ለማውጣት) የአብይ አሕመድን ቡድን (፻ ሚሊዮን አባላት ያሉትን) ተቀላቅያለሁ፡፡

የአብይ አሕመድን ቡድን በተቀላቀልሁ ጊዜ መልዓክት ከሚያደርጉት ጉዞ ጋር እንደተቀላቀልሁ ያህል ተሰማኝ፡፡ በአሜሪካ የጥቁር ዜጎች በበተክስያን የሚዘምሩት ዜማ ነበር ።

ኦ፣ ጌታዬ በዚያ መልዓክት ጉዞ በጀመሩ ጊዜ፨  በነርሱ ቁጥር ውስጥ ለመሆን እፈልጋለሁ/

ጸሐይ ማንጸባረቅ መጀመሯን በምትቃወምበት ጊዜ… ጨረቃ በደም ወደ ቀይነት በምትቀየርበት ጊዜ…/

በዚያ የሀሌ ሉያ ቀን/… በጥሩንባ ጥሪ በሚደረግበት ጊዜ/

ኦ፣ ጌታዬ   በዚያ መልዓክት ጉዞ በጀመሩ ጊዜ/  በነርሱ ቁጥር ውስጥ ለመሆን እፈልጋለሁ/

ጥቂቶች ይህ የመከራ ዓለም፨የምንፈልገው ብቸኛው ነገር ነው ይላሉ/

ሆኖም ግን ለዚያ የንጋት ቀን በገጉት እጠብቃለሁ፨ አዲሲቱ ዓለም በምትገለጽበት ጊዜ/

ገለጻው (አብዮቱ) በሚመጣበት ጊዜ፨ ገለጻው (አብዮቱ) በሚመጣበት ጊዜ/

ኦ፣ ጌታዬ በዚያ መልዓክት ጉዞ በጀመሩ ጊዜ፨  በነርሱ ቁጥር ውስጥ ለመሆን እፈልጋለሁ/

መሪዎቻችን መጮህን ማልቀስን በሚማሩበት ጊዜ/

ኦ፣ ጌታዬ በነርሱ ቁጥር ውስጥ ለመሆን እፈልጋለሁ/

… መልዓክት ጉዞ በጀመሩ ጊዜ/

ኦ፣ ጌታዬ በዚያ መልዓክት ጉዞ በጀመሩ ጊዜ/ በነርሱ ቁጥር ውስጥ ለመሆን እፈልጋለሁ/…

እ.ኤ.አ ሚያዝያ ፪፪ ቀን ፳፩፰ ዓ።ም ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አዘጋጅቸው በነበረው ማስታዋሻ እንዲህ በማለት ጽፊያለሁ፣ “በህወሀት ላይ ያሉኝ የእኔ አመለካከቶች የታወቁ ናቸው፡፡ ሆኖም ግን በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እና በኦቦ ለማ አዎንታዎ አመለካከት እና የከፍታ መልዕክቶች ምክንያት አመለካከቴን በህወሀት ላይ ያለኝንም እንኳ ለውጫለሁ“ ብዬ ነበር፡፡ ሁላችንም መልካም ነገር እና መጥፎውንም ነገር ማድረግ እንደምንችል ማርቲን ሉተር ኪንግ እንዲህ በማለት በትክክል ያስተምሩናል፣ “በመጥፎዎቻችን ውስጥ ጥቂት መልካሞች ይኖራሉ፡፡ በመልካሞቻችን ውስጥ ደግሞ ጥቂት መጥፎዎች ይኖራሉ፡፡ ይህንን በምንገነዘብበት ጊዜ ጠላቶቻችንን የመጥላት እድላችን በመጠኑም ቢሆን ይቀንሳል፡፡“

በቀላሉ ለማለት የፈለግሁት ነገር እንዲህ የሚል ነው፣ “እኔ እራሴ ለበርካታ ጊዚያት ከኃጢያቱ ንጹህ ነኝ ስል የቆየሁት በመለወጥ በፍቅር፣ በይቅርባይነት እና በእርቅ መተቃቀፍ ከቻልኩ ሌላው እያንዳንዱም ማድረግ ይችላል፡፡“

ጋንዲ እንዳስተማሩን ማየት የምንፈልገውን ለውጥን  መሆን አለብን ፡፡

በጨለማው ምድር ላይ የሚኖሩትን ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን በጣም ጠንካራ እና ዓለም አቀፋዊ በሆነው “ፍቅር” በሚሉት መሳሪያ ልናሸንፋቸው እንደምንችል እርግጠኛ ነኝ፡፡

በጨለማው ጎን ኃይሎች ላይ በየዕለቱ የሚገኘው ድል ዋጋ፣

በጨለማው ጎን ኃይሎች ላይ ቋሚ እና ዘለቄታዊ የሆነ ድል የለም፡፡ አንድ ቀን በአንድ ወቅት ጥግ ልናስይዛቸው እንችላለን፡፡ ሆኖም ግን በየዕለቱ የሚገኘውን ድል ዋጋ ልናዳክመው እና ፍጹም ልናጠፋው እንዳንችል በትኩረት መመልከት ያስፈልጋል፡፡

ለዚህም ነው የኢትዮጵያ ሕዝቦች ዓይኖቻቸውን ከፍተው ማየት እና በመንደሮች፣ በከተሞች፣ በጎረቤቶቻችን፣ በገበያዎች፣ በትምህርት ቤቶች፣ በቤተክርስቲያኖች፣ በመስጊዶች እና በሌላውም በእያንዳንዱ ቦታ ላይ ነቅተን መጠበቅ ያለባቸው፡፡ ትክክል መስሎ በማይታያቸው ጊዜ ለሕግ መከበር ሲባል አንድ ነገር ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ እያንዳንዱ ወንድ፣ሴት እና ልጅ ጥንቁቅ ሆኖ መቀመጥ ይኖርበታል፡፡ እንደዚሁም አጠራጣሪ የሆኑ ነገሮችን እና ድርጊቶችን ሲያዩ ወዲያውኑ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡

እ.ኤ.አ ሰኔ ፪፫ ቀን ፳፩፰ ዓ።ም የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕለቱን ጠብቆታል፨አድኖታል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብይ አሕመድ የሚመሩትን የፍቅር፣ የይቅርባይነት እና የዕርቅ አብዮት በግልጽ በመጠበቅ ላይ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝቦች እራሳቸውን፣ ቤተሰቦቻቸውን፣ ዘመዶቻቸውን፣ ጓደኞቻቸውን፣ ማህበረሰቦቻቸውን፣ መሪዎቻቸውን እና ሀገራቸውን ለዘለቄታው በንቃት መጠበቅ አለባቸው ምክንያቱም ጭራቃዊነት በፍጹም አርፎ አይተኛም፡፡

የአሜሪካውያን የሀገር ውስጥ ደህንነት መስሪያ ቤት መፈክር እንዲህ የሚል ነው፣ “አንድ ነገር እይ፣ አንድ ነገር በል“  የአሜሪካ ሕዝብ ንቃቱን በማጎልበት፣ በአጋርነት እና በሌሎች መዳረሻዎች ላይ ተሳትፎ በማድረግ የውስጥ ደህንነቱን ለመጠበቅ ዓላማ ያደረገ መፈክር ነው፡፡

ንቃትን ከፍ ለማድረግ፣ አጋርነትን ለማጠናከር እና ሕዝቡን በማሳተፍ እናት ሀገሩን ኢትዮጵያን ለመጠበቅ ተመሳሳይ ዘመቻ ማድረግ ለምን እንደማንችል ምንም ዓይነት ምክንያት አይታየኝም፡፡

እልም አለ የፍቅር ባቡሩ ኢትዮጵያውያኖችን ይዞ በሙሉ ፦

ኢትዮጵያውያን እ.ኤ.አ ሰኔ ፪፫ ቀን ፳፩፰ ዓ።ም ሀገራዊ የሕይወት ትምህርት ተምረዋል፡፡ ጥልቅ እና መሰረታዊ የሆነ ትምህርት ነው፡፡ ኃይል ኃይልን ይወልዳል፡፡ ፍቅር ፍቅርን ይወልዳል፡፡ ጥላቻ ጥላቻን ይወልዳል፡፡ ሰላም ሰላምን ይወልዳል፡፡ ጦርነት ጦርነትን ይወልዳል፡፡ ይቅርባይነት ይቅርባይነትን ይወልዳል፡፡

ፈገግታ ፈገግታን ይወልዳል፡፡ አብይ አሕመድ ፈገግ ይላሉ እናም መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከእርሳቸው ጋር ፈገግ ይላል፡፡

የፍቅር፣ የይቅርባይነት እና የዕርቅ ዲያሌክቲክስ፨የቁስ አካላዊ ጥናት ባህርይ ይኸው ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በድጋፍ ሰልፉ ላይ በመገኘት በኢትዮጵያ ላይ የሚዘንበው የፍቅር እና የሰላም ዝናብ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

እኔ ደግሞ በኢትዮጵያ ላይ ፍቅር ይዝነብ፣ ፍቅር ያንጸባርቅ እላለሁ፡፡

ማንዴላ ለእኛ መልካም ነገር እና ይቅርባይነት በማለት በሰየሙልን ሁለት የባበሩር መንገዶች ላይ የእኛን ባቡር ከመፈትለክ የሚያግደው ምንም ዓይነት ኃይል የለም፡፡

ስለሆነም በጨለማው ምድር ላይ የምትኖሩት ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ከጨለማው ውጡ፡፡ በኢትዮጵያ የፍቅር ባቡር እየዘለላችሁ ግቡ፡፡ እንቀፋችሁ፡፡ ከወንድሞቻችሁ እና ከእህቶቻችሁ ጋር በአንደኛ ደራጃ ማዕረግ እና በፈጣኑ ባቡር ሳትሳፈሩ ለምንድን ነው ቆማችሁ የምትገኙት?

አሸናፊዎች ሁኑ ምክንያቱም ፍቅር ሁልጊዜ በጥላቻ ላይ ድልን ይቀዳጃል፡፡ ወደ እኛ ኑ እና አብረን ከብርሀኑ ወገን ኃይል ጋር እንጓዝ፡፡

በፍቅር እንድናሸነፍ ዕድል ስጡን፡፡ ከእናንተ ጥላቻ ጋር አንዋጋም፡፡

ከእኛ ጋር ተደመሩ፦ የጨለማውን ኃይል ሳይሆን የፍቅር፣ የይቅርባይነት እና የዕርቅ ደጋፊ እና አጠናካሪ ሁኑ፡፡

በፍቅር ጥላ ስር ከእኛ ጋር ሁኑ፦

የኢትዮጵያ ባቡር መዝሙር፣

በእኔ የልጅነት ዘመን የፍቅር ባቡር መዝሙር በጣም የምወደው መዝሙር ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ ያንን ታላቅ የሆነ የዜማ ቅላጼ ስንቶች ኢትዮጵያውያን ወጣቶች እንደሚያውቁት አላውቅም፡፡ ከአምስት አስርት ዓመታት በኋላ ዛሬ ላይ ሆኘ ስለፍቅር፣ ስለሰላም እና ስለአንድነት ሲያስተላልፏቸው የነበሩትን መልዕክቶች እስከ አሁንም ድረስ በሚገባ አስታውሳለሁ፡፡

የኦጃይን (የአሜሪካ ዘፋኞች)  የፍቅር ባቡር መዝሙር ትክክለኛ የመንፈስ አዳሻችን እና የፍቅር መዝሙራችን እየዘመርን በተራራው ጭፍ ላይ ወደምትገኘው የተወደደችዋ ኢትዮጵያ ለመድረስ ኢንጅኒየር አብይ አሕመድን የኢትዮጵያ የፍቅር ባቡሩ ነጂ በማድረግ የተከበረውን ጉዞ እንጀምር፡፡

የፍቅር ባቡሩ መጓዝ ጀመረ፨ የፍቅር ባቡሩ ጀመረ/

በመላ ኢትዮጵያ የሚገኘው ሕዝብ (በመላ ኢትዮጵያ፣ አሁንም) እጅ ለእጅ በመያያዝ ከአብይ ጋር ተቀላቀሉ፡፡

የፍቅር ባቡሩ መንቀሳቀስ ጀመረ፡፡ እኛ የምናዘጋጀው ቀጣዩ ማቆሚያ በቅርብ ይሆናል፡፡

ይህንን አፈ ታሪክ ለኦሮሚያ፣ ለጎንደር፣ ባሕርዳር፣ መቀሌ፣ ሲዳማ፣ አፋር፣ ደቡብ ሕዝቦች፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ሀራሪ፣ ሶማሊ እና ለጋምቤላ ንገሩ፡፡

የመሳፈሪያ ጊዜው አሁን መሆኑን አታውቁምን?

እናም ይህ የኢትዮጵያ የፍቅር ባቡር መጓዙን ይቀጥል፣ በደህና ይቀጥል፡፡

በመላ ኢትዮጵያ ያላችሁ ሕዝቦች (ገንዘብ አያስፈልግም) ከአብይ ጋር እጅ ለእጅ ተያያዙ (ኑ)

በፍቅር ባቡሩ መጓዝ ቀጥሉ፣ በፍቅር ባቡሩ (ቲኬት አያስፈልግም፣ ኑ)/

በመላ ኢትዮጵያ ያላችሁ ሕዝቦች (ተቀላቀሉን፣ ከአብይ ጋር ይህንን ባቡር ሾፍሩ)

ተቀላቀሉን (ሁላችሁም ይንን ባቡር ሾፍሩ)፨ በፍቅር ባቡሩ መጓዝ ቀጥሉ (ኑ፣ ባቡር)፣ የፍቅር ባቡር

በአሜሪካ፣ በአውሮፓ፨በመላው ዓለም ሁሉ ተሰራጭታችሁ የምትገኙ ሁላችሁም ኢትዮጵያውያን ወንድሞች እና እህቶች

በደቡብ አፍሪካ፣ በሳውዲ አረቢያ እና በእስራልም በስደት ለሚኖሩት ሁሉ የኢትዮጵያን አፈ ታሪክ ንገሯቸው/

ይህ ባቡር ከጣቢያው እንዳያመልጣችሁ፨የሚያመልጣችሁ ከሆነ ሀዘን ይሰማኛል፡፡ ለእናንተ አዝናለሁ፡፡

ደህና፨ በመላ ኢትዮጵያ ያላችሁ ሕዝቦች (እህቶች እና ወንድሞች)

ከአብይ ጋር እጅ ለእጅ ተያያዙ (ተቀላቀሉ፣ ኑ)/ በፍቅር ባቡሩ መጓዝ ቀጥሉ (ይህንን ባቡር ሾፍሩ፣ ሁላችሁም)፣ የፍቅር ባቡር (ኑ)

በመላ ኢትዮጵያ እና በዲያስፖራው ያላችሁ ሕዝቦች (ቲኬት መቁረጥ አያስፈልግም)/ ከአብይ ጋር እጅ ለእጅ ተያዙ (ኑ፣ ሾፍሩ)

በፍቅር ባቡሩ መጓዝ ቀጥሉ፣ የፍቅር ባቡር፨ ሾፍሩ፣ ፍቅር እንዲሾፍር ፍቀዱ

እንዲሾፍር ፍቀዱ/እንዲሾፍር ፍቀዱ

የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ጦርነት የለም/ በመላ ኢትዮጵያ ያሉ ሕዝቦች (በዚህ ባቡር)

አብይን ተቀላቀሉ (ባቡሩን ሾፍሩ)/ በፍቅር ባቡሩ መጓዝ ቀጥሉ፣ የፍቅር ባቡር (ከአብይ ጋር ባቡሩን ሾፍሩ፣ ሁላችሁም)

በመላ ኢትዮጵያ እና በዲያስፖራው ያላችሁ ሕዝቦች (ኑ)፨ ከአብይ ጋር እጅ ለእጅ ተያያዙ (መሾፈር ትችላላችሁ ወይም ደግሞ መቆም፣አዎ)

በፍቅር ባቡሩ መጓዝ ቀጥሉ፣ በፍቅር ባቡር፨ በመላ ኢትዮጵያ የሚገኙ ሕዝቦች ሁሉ (በኢትዮጵያ አካባቢ፣ ሁላችሁም)

ከአብይ ጋር እጅ ለእጅ ተያያዙ (ኑ)፨በፍቅር ባቡሩ መጓዝ ቀጥሉ፣ በፍቅር ባቡር ከአብይ ጋር በኢትዮጵያ፡፡

እልም አለ የፍቅር ባቡሩ ሁላችንም ይዞ በሙሉ ፦

እንደመር፦ አንቀነስ፦ እንባዛ፦ አንከፈል፦

ኢትዮጵያዊነት ዛሬ፡፡ 

ኢትዮጵያዊነት ነገ፡፡ 

ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም፡፡ 

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር፦     

ሰኔ ፪፮ ቀን ፳፲ ዓ።ም

 Original English post:

Memorandum No. 11: All Aboard! Abiy Ahmed’s “Ethiopia Love Train”!