ለ አዲስ አበባ ለሚገኙ ወገኖቼ ስለ እ.ኤ.አ. ሰኔ 23, 2018 ለሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ያለኝ ልዩ መልክት
ለጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ንገሩልኝ – ላሎት የሰላም የእርቅና የፍቅር በጠቅላላ አነጋገር ኢትዮጵአዊነት ለሚያደርጉት ጥረትና ልፋት ከጎኖ አጠገቦ እገኛለሁ ሙሉ በሙሉ ድጋፌን እስጦታለሁ።
ለጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ንገሩልኝ – ላንዴም ለዘላለምም በኢትዮጵያ የዘር የጎሳ የመከፋፈያ ፖለቲካን ከኢትዮጵያ ምድር ለማጥፋት አብሬዎት እቆማለሁ ።
ለጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ንገሩልኝ – ከርሶ ጋር ማንዴላ መልካምነትና እርቅ የሚባል መንገድ የሰየመልንን ይዤ አብረዎት እጉአዛለሁ።
ለጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ንገሩልኝ – ሰውነታችንና አንድነታችን ጥላቻንና ዘርነትን ያሸንፋል የሚለዉን እምነቶን ሙሉ በሙሉ እካፈላለሁ።
ለጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ንገሩልኝ – መልካሙ መፅሐፍ እንደሚለው “ጠላቶቻችን ባንድ መንገድ ይመጡብናል ግን በሰባት መንገድ ከፊታቺን ይበተናሉ።”
ለጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ንገሩልኝ – ከመንደር አንስተን ከትንሽ እስከ ትልቅ ከተማ እስከ ሰፊ አካባቢ የሰላምና የእርቅ ዘመቻ እናካሂዳለን ። በራሳችን ጉልበትና እግዚአብሔር በሚሰጠን ማለቂያ የሌለው ኃይል የሰላምና የእርቅ ዘመቻ እናካሂዳለን ።
ለጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ንገሩልኝ – ይምጡ ይከተሉን ወፊት በአንድነት ኃይል በአንድ ኢትዮጵያዊነት ጠንካራ መንፈስ ስንራመድ ።
ለጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ንገሩልኝ – ያቺ ኢትዮጵያ መሬት ላይ ወድቃ የተጨፈለቀች እውነት ለትንሣኤ ደርሳለች ።
ለጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ንገሩልኝ – የጋናው ፕሬዚደንት ቅዋሜ ንክሩማ ላፍሪካ አንድነት ድርጅት ያሉትን እደግምሎታለሁ “የኢትዮጵያ ትንሣኤ እየደረሰ ነው።”
ለጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ንገሩልኝ – ከርሶ ጋር ሆነን ያቺ ዉድ ኢትዮጵያ የምትባለዋን አገር በኮረብታው ላይ ለመገንባት ዝገጁ ነን ። በሷም መንገዶች ላይ ፍትህ እኩልነት ሰባዊ መብት የሕግ በላይነት እንደጎርፍ ዉሃና እንደ ታላቅ ወንዝ ይፈስባታል ።
አስታውሱ እንዳትረሱ ለጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ንገሩለኝ — እንወዶታለን ፍቅር ሁሉን ያሸነፋል!
እባካችሁ እባካችሁ ወገኖቼ በ እ.ኤ.አ. ሰኔ 23, 2018 መስቀል አደባባይ ወጣችሁ የእኔ ድምፅ ሁኑልኝ።
የናንተው
ዓለማየሁ
ኢትዮጵያዊነት ዛሬ
ኢትዮጵያዊነት ነገ
ኢትዮጵያዊነት ለዘላአም !