“ሲመረው የማይነሳ ህዝብ የለም ባለም፣” አለ አቦይ ስብሐት ነጋ!

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም 

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

የኢትዮጵያውያን የጸደይ አብዮት በ2016 የክረምት ወቅት መጀመሩ ነውን? 

አንድ ህዝብ ታምቆ ፣ ታምቆ ማለት ተጨቁኖ  በዘመንታ አይቆይም ። ዩኒቨርሳል universal  ማለት ነው ።  አንድ ህዝብ እንደ ህዝብ መጠን  በዓለም ታሪክ  አንዳስቀመጡት አንደፈለጉት  የሚቀመጥ አይደለም። ሲመረው ይፈነዳል።  ይሄ ዓለም አቀፋዊ  እውነታ /universal  truth  ነው። ሲመረው የማይነሳ ህዝብ የለም ባለም።  በታሪክም /historically።  አሁንም።  ለወደፊትም ። (አዛውንቱ የእንጨት ሽበት ባለቤቱ አቦይ ስብሀት ነጋ፣ የዘ-ህወሀት ጭንቅላት፣ ንጉስ፣ የክርስትና አባት፣ ተጽእኖ ፈጣሪ እና የአለቆች ሁሉ አለቃ (ካቦ) እ.ኤ.አ በ2015 ከተናገረው የተወሰደ።)  (ለማዳመጥ እዚህ ይጫኑ ።)

በዘ-ህወሀት ላይ የፍርዱ ቀን ደረሰ ማለት ነውን?

Eth Demos2እ.ኤ.አ ታህሳስ 2015 “የኢትዮጵያውያን የጸደይ አብዮት በበጋው ወቅት መጀመሩ ነውን?  በሚል ርዕስ በኢትዮጵያ በመምጣት ላይ ስላለው የጸደይ አብዮት ትችት አቅርቤ ነበር፡፡“

በዚያ ትችቴ ላይ እንዲህ የሚል ምልከታ አድርጌ ነበር፡ “በኢትዮጵያ እንደመዥገር በስልጣን ኮርቻ ላይ ተጣብቆ የሚገኘው የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ (ዘ-ህወሀት) በምን ሰዓት እና መቼ ቀን እንደሚወድቅ በእርግጠኝነት መተንበይ አልችልም፡፡ ሆኖም ግን የመውደቂያው የእጅ ጽሁፍ በግድግዳው ላይ በጉልህ ተጽፎ ይታያል“ ነበር ያልኩት፡፡

ያንን ትችት ካቀረብኩ ከአንድ ወር በኋላ እ.ኤ.አ ጥር 2016 “ለኢትዮጵያውያን ምንም የሚቀር ሀገር የላቸውምን?” በሚል ርዕስ ባቀረብኩት ትችቴ ደግሞ ዘ-ህወሀት የፍርድ ቀኑ በደረቅ ሌሊት እየተሳበ እንደሚደርስ ሌባ ቀስ ብሎ ሳይታሰብ በድንገት ከተፍ ይላል በማለት ተናግሬ ነበር፡፡

በአሁኑ ጊዜ በዘ-ህወሀት ላይ የፍርዱ ቀን ደረሰ ማለት ነውን?

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለፍትህ እና ለፍትሀዊነት መስፈን ሲል ለ25 ዓመታት ያህል ድምጹን ከፍ አድርጎ ሲጮህ ቆይቷል፡፡ ሆኖም ግን እንደበቀቀን የሚለፈልፍበት ሰፊ አፍ እንጅ የሚሰማበት ጆሮ እና ህሊና የሌለው የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ (ዘ-ህወሀት) ሲቀርብለት ለቆየው ህዝባዊ የተማዕጽኖ ጥያቄ ሁሉ አላየሁም አልሰማሁም በማለት ጆሮዳባ ልበስ ሲል ቆይቷል፡፡

ዘ-ህወሀት በተደጋጋሚ ከሕዝብ ሲቀርብለት ለቆየው የተማጽዕኖ ጥያቄ ሁሉ በኤኬ-47 ካላሽንኮቭ እና በሌሎች አውቶማቲክ መሳሪያዎች አማካይነት የእሩምታ ተኩስ በመክፈት የሕዝብ እልቂትን በመፈጸም የአጻፋ ምላሽ ሲሰጥ ቆይቷል፡፡

ሰዎች እንዲህ የሚል አባባልን ይናገራሉ፣ “ፍትህ ልክ አንደምዘገይ ባቡር ነው፣ ምን ቢዘገይ መድረሱ አይቀርም፡፡“   የፍትህ ባቡር በኢትዮጵያ ዘግይቷል፣ ሆኖም ግን የዚያን ባቡር በሐዲዱ የሚተላለፈው መድረሱን የሚገልጥ ድምፅ መስማቴን ሳላቆአርጥ ለበርካታ ዓመታት ተናግሬአለሁ፡፡ የፍትህ ባቡር ቀስ አያሌ አየመጣ ነው! የፍትህ ባቡር አያዘገመ ነው ነው! የፍትህ ባቡር አየገሰገሰ ነው! የፍትህ ባቡር አየደረሰ ነው!  የፍትህ ባቡር ደርሰ አንዴ!?

እ.ኤ.አ በ2016 የኢትዮጵያ የፍትህ የምጽአት ባቡር ጣቢያው ገባ!?

ከባቡር ጣቢያው ሲገባ እየተመለከትኩት ነው፡፡ ሆኖም ግን የባቡሩ ተሳፋሪዎቹ ማን አንደሆኑ በእርግጠኝነት የማውቀው ነገር የለም፡፡

የኢትዮጵያ የፍትህ ባቡር የሰላም ወይም ደግሞ የእርስ በእርስ ጦርነትን የሚያውጁ ተሳፋሪዎች ናቸው ያሉት?

የሰላም ፈጣሪዎች አንዲሆኑ አመኛለሁ እጸልያለሁ።

“ሰላም ፈጣሪዎች የተባረኩ ናቸው” በሚለው መለኮታዊ ትእዛዝ አምናለሁ።

ሆኖም ግን የሰላም ፈጣሪዎችን ጥሪ እየሰማሁ አይደለም፡፡

እንዲህ የሚለውን የጦረኞችን የጦርነት አዋጅ የጥሪ ቀን እየሰማሁ ነው፡ “ማረሻዎቻችሁን ወደ ጎራዴነት ቀይሩ እንደዚሁም ሁሉ የአበባ ማስተካከያ መሳሪያዎቻችሁን ወደ ጦር ቀይሩ፡፡ ደካሞች እንዲህ በሉ፣ ’እኔ ጠንካራ ነኝ!‘“ አንደተባለው ።

ለሩብ ክፍለ ዘመን ያህል በዘ-ህወሀት ጉልበት ስር ወድቆ ደካማ በመሆን ሲያገለግል የቆየው ሕዝብ በአሁኑ ጊዜ በአይበገሬነት፣ በፍርሀትየለሽነት ዓይኑን አፍጥጦ በመቆም እንዲህ እያለ ይዘምራል፡ “እኛ ጠንካሮች ነን! ኢትዮጵያ ትጠንከር! አንዲት ጠንካራ ኢትዮጵያ ለሁላችንም !“

ጋንዲ እንዳስተማሩን ሁሉ ጥንካሬ ከአካላዊ ብቃት፣ ከጦር መሳሪያዎች ወይም ደግሞ ከሚፈነዱ ቦምቦች፣ ሮኬቶች እና ሚሳይሎች አይመጣም የሚለውን እንደማምን ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡

ጥንካሬ የሚመጣው ከማይበገረው የመንፈስ ጽናት ነው፡፡ የጥንካሬ ምንጭ የልብ ወርቅ እና የአረብ ብረት መሆን ነው፡፡

ከሩብ ክፍለ ዘመን የዘ-ህወሀት አምባገነናዊ አገዛዝ በኋላ የኢትዮጵያ ሕዝቦች የማይበገረውን ኃይላቸውን እንዲህ በማለት በማሳየት ላይ ይገኛሉ፡ “ዘ-ህወሀት! በቃ በቃ ነው! ከዚህ በኋላ አብረን መቀጠል አንችልም! ሽንጣችንን ገትረን እንዋጋለን! ከእንግዲህ በኋላ አንተን አንፈራህም! አፈር ድሜ በልተህ ገሀነም ግባ፣ ገሀነም፣ ገሀነም!“ እያሉ ነው፡፡

እ.ኤ.አ በ2010 በቱኒሲያ ሕዝባዊ ለውጥ በመጣ ጊዜ በውድቅት ሌሌት ቀስ እያለ እየተሳበ እንደሚመጣ ሌባ ነበር፡፡

የቱኒሲያ ሕዝባዊ የአመጽ ብልጭታ በመካከለኛው ምስራቅ እና በሰሜን አፍሪካ ባሉ ሀገሮች ሕዝቦች ላይ እሳት ጫረ፡፡ ገሀነም ፈነዳ እናም የህዝብ ቁጣ የአፍሪካን አምባገነኖች አይገቡበት እየገባ ማርበድበድ ጀመረ፡፡ እንደ አይጥ በየቆሻሻ ቱቦው እየተያዙ አፈር ድሜ እየበሉ ወደማይቀረው ዓለም ተሰናበቱ፡፡

ያ በጨለማ በውድቅት ሌሊት ቀስ እያለ ሲሳብ የነበረው ሌባ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ የፍትህ ባቡር ውስጥ ተሳፍሮ እየመጣ ነውን?

እኔ ስለዚህ ጉዳይ የማውቀው ነገር የለም ምክንያቱም ከዚህ በታች ለሚቀርቡት ጥያቄዎች ምላሽ የማውቀው ነገር የለምና፣

ዘ-ህወሀት በ100 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ ነግሶ ከሰብአዊነት አውርዶ እና ባሪያ እድርጎ በአምባገነንነት እና በጭቆና እንደ ብረት ቀጥቅጦ እንደ ሰም አቅልጦ እየገዛ ሊቆይ የሚችለው ለምን ያህል ጊዜ ነው?

ዘ-ህወሀት ሀገሪቱን የባሪያ የእርሻ ቦታ በማድረግ እነርሱ ጌቶች ሆነው እያንዳንዱ የኢትዮጵያ ዜጋ ደግሞ ገባር ሆኖ እየተገዛ እና እየተሰቃየ ሊቆይ የሚችለው ለምን ያህል ጊዜ ነው?

ዘ-ህወሀት አርሶአደሮችን ከመሬት ይዞታቸው በኃይል እያፈናቀለ እርሱ የዜጎችን አንጡራ ሀብት እያጋበሰ ለአስከፊ ድህነት እየዳረጋቸው ሊቆይ የሚችለው ለምን ያህል ጊዜ ነው?

ዘ-ህወሀት የቤት ባለቤቶችን ከመኖሪያ ቤታቸው በኃይል እያፈናቀለ፣ የንግድ ድርጅት ባለቤቶችን ከንግዳቸው እያባረረ እና ቤተክስቲያኖችን እና መስጊዶችን እየደፈረ እና ቅዱስ ቦታዎችን እያረከሰ ያገኘውን ሁሉ እያግበሰበሰ የማይሞላውን ኪሱን በማሳበጥ ሊቆይ የሚችለው ለምን ያህል ጊዜ ነው?

ዘ-ህወሀት የኢትዮጵያ ሕዝቦች ከቀደምቶቻቸው ጀምረው ሲኖሩበት የነበረውን መጠነ ሰፊ የእርሻ መሬቶቻቸውን በኃይል እያፈናቀለ በመቀማት እና በመዝረፍ በርካሽ ዋጋ ለቻይናዎች፣ ለህንዶች፣ ለሳውዲዎች፣ ለቱርኮች እና ለሌሎች በሳንቲም ደረጃ እየቸበቸበ ኪሱን ሲሞላ የሚቆየው ለምን ያህል ጊዜ ነው?

ዘ-ሀወሀት ሕገ መንግስታዊ መብቶቻቸውን በመጠቀም በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞቻቸውን የሚገልጹትን የኢትዮጵያ ወጣቶች እንደ በሬ እያረደ እልቂትን በመፈጸም ሊቆይ የሚችለው ለምን ያህል ጊዜ ነው?

ዘ-ህወሀት የ100 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን ድምጾች እያፈነ ሊቆይ የሚችለው ለምን ያህል ጊዜ ነው?

ዘ-ህወሀት በእግር ጫማው የ100 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን አንገት በመርገጥ ሊቆይ የሚችለው ለምን ያህል ጊዜ ነው?

ንገሩኛ እኮ ለምን ያህል ጊዜ?

እኔ ግን ጊዜው ሩቅ አይሆንም እላለሁ!

ሩቅ አይሆንም! በምንም ዓይነት ሁኔታ ሩቅ አይሆንም!

ነሐሴ ለዘ-ህወሀት የቀውጥ ወር ነው፡፡

አሁን በህይወት የሌለው እና ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ትንሹ አምላክ እንዲሁም ለሁለት አስርት ዓመታት በዘ-ህወሀት ኮርቻ ላይ ተፈናጥጦ የቆየው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ ህይወቱ አለፈ እየተባለ የሚነገርለት በነሀሴ ወር ነው፡፡ አምባገነኑ መለስ ዜናዊ በእርግጠኝነት የሞተበት ቀን ግን በዘ-ህወሀት ሚስጥር ሆኖ ተቀምጧል፡፡

ከአራት ዓመታት በኋላ እ.ኤ.አ ነሀሴ 2016 እንዲህ የሚል ጥያቄ እጠይቃለሁ፣ “የዘ-ህወሀት ኮርቻ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለዘላለሙ ተንኮትኩቶ የሚወድቀው መቼ ነው?“

የኢትዮጵያ ጀግኖች ሕዝቦች ከዘ-ህወሀት የስቃይ እና የመከራ አገዛዝ ነጻ ለመውጣት ረዥሙን የጨለማ ጉዞ በመጋፈጥ ያንን አስቸጋሪ እና አንገብጋቢ የሆነውን ጥያቄ በመመለስ ህልሞቻቸውን ማሳካት የሚችሉት መቼ ነው? (መቀመጫ ኮርቻውን በዛፉ ጫፍ ላይ አስቀምጠው፣ ነፋስ በሚነፍስበት ጊዜ ኮርቻው ወድቆ ይንኮታኮታል፣ ቅርንጫፉ ሲዘነጠል ኮርቻው ይወድቃል እናም ድልዳሉ ኮርቻ እና ሁሉም ኮተቱ አንዴ ወድቆ ይንኮታኮታል፡፡)

በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ ውስጥ ዘ-ህወሀትን ዶግ አመድ የሚያደረግ አደገኛ የሆነ ሕዝባዊ ማዕበል፣ ቁጣ እና የበቀል ጥላቻ የሰደድ እሳት በመቀጣጠል ላይ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ በየቦታው በመነሳት ላይ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ አቦ ሸማኔው (ወጣቱ ትውልድ) አካባቢውን ሁሉ በመውረር ላይ ይገኛል፡፡ በየቦታው የቁጣ ድምጹን ከፍ አድርጎ በማሰማት ላይ ይገኛል፡፡

በዘ-ህወሀት የዛፍ ጫፍ ላይ ተንሰራፍቶ የሚገኘው የወንጀለኝነት እና የሙስና ቅርንጫፍ በህዝባዊ የቁጣ እና የበቀል ማዕበል ተዘንጥሎ አፈር ድሜ ሊበላ የሚችለው መቼ ነው?

ቅርንጫፉ ተሰብሯል ማለት እችላለሁ! በእርግጠኝነት! ብቸኛ ጥያቄ ሆኖ ሊቀርብ የሚችለው የዘ-ህወሀት የወንጀለኝነት፣ የሙስና እና የሰብአዊ መብት ረገጣ ወንጀሎች ኮርቻ ሊወድቅ ይችላል ወይ የሚለው ሳይሆን ይልቁንም ወድቆ ሊንኮታኮት የሚችለው በእርግጠኝነት መቼ ነው የሚለው ነው፡፡

ስለሆነም ነገሩ አሮፓውኖች አንደሚሉት አባባል ብናየው እንዲህ የሚል ነው፡

ዝትቱ እና ግብስብሱ ዘ-ህወሀት በግድግዳ ላይ ተቀምጧል፡፡ 

ዝትቱ እና ግብስብሱ ዘ-ህወሀት ታላቅ ውድቀት ደርሶበታል፡፡ 

ሁሉም የንጉሱ ፈረሶች እና የንጉሱ ሰዎች የተፈረካከሰውን ዝትቱን እና ግብስብሱን ዘ-ህወሀት እንደገና መልሰው አንድ ሊያደርጉት ከቶውንም አይችሉም፡፡ 

ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በለው ወይም ደግሞ ሳሞራ የኑስ፣ ስብሀት ነጋ፣ በለው ወይም ቴዎድሮስ አድሀኖም፣ ስዩም መስፍን፣ አርከበ እቁባይ፣ አባይ ጸሀዬ፣ በለው አባዲ ዘሞ፣ ጸጋይ በርኸ፣ አዜብ መስፍን፣ ሀፍቶም አብርሃ፣ ሬድዋን ሁሴን፣ በለው ወይም ምስኪኑ ናሙና ኃይለማርያም ሰሳለኝ ወይም ደግሞ ሌላ የዘ-ህወሀት ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አባል የዘ-ህወሀትን ዝትት እና ግብስብስ ውዳቂ እንደገና ጠጋግኖ አንድ ሊያደርገው ከቶውንም አይችልም፡፡ አይችልም በምንም አይነት !

ዘ-ህወሀት የፖለቲካ ቀውስን በመምራት ላይ ይገኛል፣

በአሁኑ ጊዜ በዘ-ህወሀት ቁጥጥር ስር ያለችው ኢትዮጵያ የዕለት ከዕለት ስራዋን በመስራት በስርዓት የምትመራ ሀገር መሆኗ በፍጹም ውድቅ ሆኗል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በዘ-ህወሀት የጎሳ ፌዴራሊዝም ሸፍጥ ቁጥጥር ስር እጅ ከወርች ተጠፍንጋ በምትገኘው ኢትዮጵያ ውስጥ አንድም ደስተኛ የሆነ ቡድን የለም፡፡

ዘ-ህወሀት እራሱን በስልጣን ኮርቻ ላይ እንደ መዥገር አጣብቆ ለመቆየት ከሩብ ክፍለ ዘመን በላይ የጎሳ ፌዴራሊዝምን እና ከፋፋይ የጎሳ ፖለቲካ ስልቱን ሲያራምድ ቆይቷል፡፡ ዘ-ህወሀት የአንዱን ጎሳ ቡድን ከሌላው የጎሳ ቡድን ጋር በማጋጨት በከፍተኛ ደረጃ የፍርሀት፣ የጥልቅ ጥላቻ እና የጥላቻ ስልቶችን በህዝቦች ላይ በመጫን ሲተገብር ቆይቷል፡፡ ዘ-ህወሀት የራሳቸው ስብዕና የሌላቸውን አሰስ ገሰስ የፖለቲካ ፓርቲዎች በመሰብሰብ ለማታላያነት እራሱን ኢህአዴግ ብሎ በመጥራት እና እውነተኛ የህዝብ ወካይ ፓርቲዎች አስመስሎ በማቅረብ በሸፍጥ እያጭበረበረ ከሩብ ከፍለ ዘመን በላይ በአምባገነንነት ሲገዛ ቆይቷል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ያፈጠጠው እና ያገጠጠው እውነታ ዘ-ህወሀት (ኢህአዴግ ወይም እራሱን በማንኛውም ስያሜ ቢጠራም) በኢትዮጵያ ውስጥ ባለ በእያንዳንዱ ጎሳ ከፍተኛ በሆነ መልኩ ተቀባይነትን በማጣት እንደ አሮጌ ቁና ተወርውሯል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ዘ-ህወሀት እያራመደው ያለው የጎሳ እና የፓርቲ የድብበቆሽ ጨዋታ ያበቃበት መሆኑን በሚገባ ተገንዝቧል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ዘ-ህወሀት በኃይል ሳይገፈተር፣ ያለውጊያ እና ከኋላው ጥቃት ሳይፈጸምበት በኢትዮጵያ ህዝቦች ላይ የእራሱን ፍላጎት ለመጫን ፍጹም ከማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሶ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝቦች የአንድነት መሰረታቸውን በማጠናከር ቀጥ አድርገው ይዘዋል፡፡ ዘ-ህወሀት እነርሱን እንዲደበድብ እና እንዲያሰቃይ የሚፈቅዱበት ሁኔታ በፍጹም የለም፡፡

ጦርነቱን ወጣቱ ትውልድ በግንባር ቀደምነት በመምራት ላይ ይገኛል፡፡ የሚመራው ግን የኃይል ድርጊትን በመጠቀም ሳይሆን ሰላማዊ በሆነ መልኩ የህዝባዊ እምቢተኝነት ስልቶችን በመተግበር ነው፡፡ ድፍረት የተመላበት ህዝባዊ እምቢተኝነትን በማራመድ ነው፡፡ ጽናትን በተላበሰ የኃይል አልባን ተቃውሞ ተግባራዊ በማድረግ ነው፡፡ ያለምንም ፍርሀት፣ ያለምንም ማቅማማት፣ ያለምንም ጥርጣሬ እንደ አረብ ብረት በጽናት ጠንክሮ የሞት ሽረት ትግል በማድረግ ላይ  ነው፡፡

በዘ-ህወሀት ግድብ ላይ ወጣቶች ታላቅ የቦይ መቀልበሻ ናቸው፡፡

ለበርካታ ጊዚያት ዘ-ህወሀት ወጣቶችን በመደለል በብርቅርቅ ነገሮች ለመግዛት ሙከራ አድርጎ ነበር፡፡ ዘ-ህወሀት ወጣቶችን የማስፈራራት፣ በቁጥጥር ስር የማዋል እና ወደ እስር ቤት ዘብጥያ የመጣል ሙከራ አድርጓል፡፡ ዘ-ህወሀት በአሁኑ ጊዜ በየቦታው ወጣቶችን እንደ ፋሲካ ዶሮ በማረድ እልቂትን በመፈጸም ላይ ይገኛል፡፡ ሆኖም ግን ወጣቶች በየአውራ መንገዶች በመውጣት እንዲህ በማለት ድምጻቸውን ከፍ አድርገው በመጮህ ላይ ይገኛሉ፡ “በአሮሚያ ወንድሞቻችንን መግደሉን አቁሙ፡፡ የአማራን ሕዝብ የጅምላ ግድያ አቁሙ፡፡ የዘ-ህወሀት የበላይነት ይቁም፡፡ የፖለቲካ እስረኞች ያለምን ቅድመ ሁኔታ አሁኑኑ ይፈቱ!“ በማለት ድምጻቸውን በማስተጋባት ላይ ይገኛሉ፡፡

አሁን በህይወት የሌለው የዘ-ህወት ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አድራጊ ፈጣሪ መሪ የነበረው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ አንደተምሳለት የሚከተለው የናዚ መሪ በአንድ ወቅት “ወጣቱን የያዘ አካል የወደፊቱን ድልአድራጊ ይሆናል” ብሎ ነበር፡፡

ዘ-ህወሀት በምንም ዓይነት መንገድ የኢትዮጵያን ወጣቶች ሊሸጥ ሊለዉጥ ሊያሸንፍ አይችልም፡፡ ሆኖም ግን የኢትዮጵያ ወጣቶች ኢትዮጵያን የእራሳቸው ያደርጋሉ፡፡ ዘ-ህወሀትን ያሸነፋሉ ።

ዘ-ህወሀት በህዝባዊ አመጹ የተቀጣጠለውን ቁጣና እና የበቀል እርምጃ ጣቶቹን በመቀሰር እና በሰላማዊ መንገድ በሚያምጹ ተማሪዎች ላይ እልቂትን በመፈጸም ከገደቡ ወጥቶ በማፍሰስ ላይ ያለውን የቦይ መቀልበሻ እንደሚቆጣጠር አድርጎ ያስባል፡፡

ዘ-ህወሀት መገንዘብ የተሳነው ነገር ቢኖር (ወይም ደግሞ ሆን ብሎ ሊገነዘበው የማይፈልገው ነገር) ከተማሪዎች ቁጣ እና የበቀል እርምጃ ከሚቀጣጠልበት ጀርባ መጠነ ሰፊ የሆነ በህዝባዊ ተስፋ መቁረጥ፣ በጥላቻ እና በምሬት የተሞላ ህዝባዊ ባህረ አሳት እንዳለ አለመገንዘቡ ነው፡፡

ዘ-ህወሀት አስተማማኝ ወታደራዊ ብቃት እንዳለው፣ በቅጥፈት የተፈበረከ የኢኮኖሚ ዕድገት እያስመዘገበ ስኬታማ እንደሆነ እና በሀገሪቱ አስተማማኝ የፖለቲካ መረጋጋት፣ ወዘተ እንዳለ አድርጎ ሌት ከቀን እንደ በቀቀን በመለፍለፍ ተግባራት ላይ በመጠመድ እራሱን ህጋዊ እና እውነተኛ እንደሆነ አድርጎ የማቅረብ ቅዠቱን ያሳያል፡፡

ዘ-ህወሀቶች እራሳቸውን ብቻ ጀግናዎች እና ጠንካራዎች፣ እነርሱ ብቻ ብልሆች እና አዋቂዎች፣ እነርሱ ብቻ ምርጦች ሌሎች ህዝቦች ግን ባዶዎች፣ እነርሱ ብቻ ወርቆች፣ ሌሎች ሕዝቦች ግን ጨርቆች እንደሆኑ አድርገው ያቀርባሉ፡፡

የዘ-ህወሀት አፈቀላጤ ከጥቂት ጊዜ በፊት እያንዳንዱ ሰው ፈሪ፣ ቦቅቧቃ እና የአዕምሮ ዘገምተኛ እንደሆነ አድርጎ እየተንተባተበ እና እየተጎላደፈ ተናግሯል፡፡

ዘ-ህወሀት የሚፈልገውን ነገር ማሰብ ይችላል፣ የመረጠውን ማመን ይችላል፡፡

ሆኖም ግን እነዚህ ማናቸውም ነገሮች ቢሆኑ ከዚህ በኋላ ምንም የሚያመጡት ነገር የለም፡፡

የተባበሩ ህዝቦች በፍጹም አይሸነፉም የሚለው አባባል ዓለም አቀፋዊ እውነታ ነው፡፡

ዘ-ህወሀት ጠብመንጃዎችን፣ ታንኮችን እና የጦር አውሮፕላኖችን መጠቀም ይችላል፣ ሆኖም ግን ዘ-ህወሀት ሰላማዊ ኢትዮጵያውያንን በገደለ ቁጥር ሕዝቦች ለነጻነታቸው ሲሉ ችግሮችን ለመፍታት ጠንካራ እና አይበገሬ እየሆኑ ይሄዳሉ፡፡

ምንም የሚመጣ ነገር የለም፡፡

በቅርቡ በተለቀቀ በአንድ የቪዲዮ ምስል አንድ ሰው እንዲህ ሲል ተደምጧል፣ “በዘ-ህወሀት አገዛዝ ሁላችንም ሞተናል፡፡ የቁም ሞት ሞተናል፡፡ ወደፊት አሁን ካለንበት የበለጠ ሞት አይጠብቀንም“። 

በመንገድ በመሄድ ላይ ያለ አንድ ሰው እንደዚህ ያለ ለማመን የሚያስቸግር መግለጫ ሲናገር መስማት ማለት በስርዓቱ ላይ ያለውን አጠቃላይ የሆነ የህብረተሰቡን ጥልቅ የሆነ ስሜት የሚያመላክት መሆኑን ያስገነዝባል፡፡ 

ህዝቦች ከነጻነት ማጣት እና ከባርነት፣ ከሁለተኛ ዜጋነት እና ከሰብአዊነት ከወረደ አያያዝ መካከል መወሰን እንዲችሉ ምርጫ እንዲመርጡ ሲገደዱ ለመዋጋት ይመርጣሉ እንጅ ሾልከው በመሸሽ ለመብረር አይሞክሩም፡፡

ይህ መርህ ዘ-ህወሀት የአእምሮ ዘገምተኛ እና ዝቅተኛ እያለ ለሚዘልፈው ለእያንዳንዱ ሰውም ቢሆን ይሰራል፡፡

ናዚዎች በጀርመን ውስጥ የነበሩት አረያኖች ከሌሎች ሕዝቦች የበለጡ ዜጎች መሆናቸውን እና ሌሎች ሕዝቦች ግን አሰስ ገሰስ እና የማይረቡ መሆናቸውን ለማመላከት ሲሉ እንዲህ በሚል ትንሽ ለየት ባለ ሁኔታ ገልጸው ነበር፡ “ከሰብአዊነት የወረዱ” ነበር ያሉት፡፡ 

የዘ-ህወሀት ኃያሎች ከኢትዮጵያ ብዙሀን ህዝብ ጋር ሲነጻጸሩ፣

ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ዘ-ህወሀትን እንደሚያሸነፍ ምንም ዓይነት ጥያቄ የለውም፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ በእርግጠኝነት ድልን ይቀዳጃል፡፡

በዘ-ህወሀት ላይ የፍርድ ቀን ደርሷል፣

ከልባቸው እና ከህሊናቸው በማውጣት አስከፊው የዘ-ህወሀት አገዛዝ በቃ! አንገሸገሸን! ቋቅ አለን! ከዚህ በላይ ልንቀጥል አንችልም! የሚልን የህዝብ አመጽ ለማቆም የሚያስችል ምድራዊ ኃይል በዚህች ሀገር ላይ ከቶውንም ሊኖር አይችልም፡፡

በዓለም ላይ ያለ የትኛውም ሕዝብ ቢሆን በአምባገነኖች ታፍኖ ለዘላለም መኖር አይችልም። ማንኛውም ሕዝብ ለዓመታት በጭቆና እጅ ከወርች ተጠፍንጎ ሲገዛ መኖር አይችልም ፡፡  ታሪክ ይመሰክ ራል ፡፡

ሰብአዊ ፍጡር የሆነ ሕዝብ  እንደ ቁሳቁስ እንደ ግኡዝ ነገር  ወይም ድጋይ ቁጭ ብሎ  አይቀርም ።  ዘህዋሃት  የኢትዮጵያን  ህዝብ እንደ ቁሳቁስ እንደ  ግኡዝ ነገር   እንደ  ድጋይ  አድርጎ  ነው  የሚ ያየው ።  ሕዝቦች በከፍተኛ ሁኔታ ባመረሩ ጊዜ ያምጻሉ ይዋጋሉ  ለሀገራቸው ለነታፃ ቸው  ይሞታሉ ፡፡

የእኔን ቃላት ለዚህ እውነታ መውሰድ የለባችሁም፡፡

የዘ-ህወሀትን የክርስትና አባት አዛውንቱን እና የእንጨት ሽበት የተላበሰውን ስብሀት ነጋን ጠይቁ፡፡ እንዲህ በማለት እንደወረደ ያለውን ሁኔታ ይነግራችኋል፣ ጥሬውን እንዳለ!

አንድ ህዝብ ታምቆ ፣ ታምቆ ማለት ተጨቁኖ  በዘመንታ አይቆይም ። ዩኒቨርሳል universal  ማለት ነው ።  አንድ ህዝብ እንደ ህዝብ መጠን  በዓለም ታሪክ  አንዳስቀመጡት አንደፈለጉት  የሚቀመጥ አይደለም። ሲመረው ይፈነዳል።  ይሄ ዓለም አቀፋዊ  እውነታ /universal  truth  ነው። ሲመረው የማይነሳ ህዝብ የለም ባለም።  በታሪክም /historically።  አሁንም።  ለወደፊትም ። (አዛውንቱ እና የእንጨት ሽበት ባለቤቱ አቦይ ስብሀት ነጋ፣ የዘ-ህወሀት ጭንቅላት፣ ንጉስ፣ የክርስትና አባት፣ ተጽእኖ ፈጣሪ እና የአለቆች ሁሉ አለቃ (ካቦ) እ.ኤ.አ በ2015 ከተናገረው የተወሰደ።) 

በቆራጥነት ወደፊት! 

ጠንካራ ነን! ኢትዮጵያ ጠንካራ ናት! በአንድነት ለጠንካራ ኢትዮጵያ! 

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!  

ነሐሴ 3 ቀን 2008 ዓ.ም

Similar Posts