ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም፡ በኢትዮጵያ ታሪክ በውርደት ስትታሰብ የምትኖር ዕለት፣
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ግንቦት 20 1983 ኢትዮጵያ መቀመቅ የወረደችበት ዕለት፣
ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በኢትዮጵያ የስልጣን ማማ ላይ የነገሰባት ዕለት ናት፡፡
በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በስልጣን እርካብ ላይ እንደ መዥገር ተጣብቆ የሚገኘው የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ (ዘ-ህዋሃት) አገዛዝ ስሙ በዓለም አቀፍ የሽብርተኝነት የመረጃ ቋት ስም ዝርዝር ውስጥ ተጽፎ የሚገኝ እና በአሸባሪነቱ የተረጋገጠ ወሮበላ የማፊያ ድርጅት ነው፡፡
ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም ህወሀት አዲስ አበባ ደረሰ እና ወሮበላ የዘራፊ መንግስትን ለወሮበላ ዘራፊዎቹ አቋቋመ፡፡
ኢትዮጵያ ላለፉት 25 ዓመታት በአፍሪካ ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ ርህራሄ በሌላቸው ጨካኝ አረመኔዎች፣ በደም በተጠሙ ሰይጣኖች እና በሙስና በበከቱ ወሮበላ ዘራፊዎች ጫማ ስር ወድቃ ትገኛለች፡፡
አሁን በህይወት የሌለው አምባገነኑ የህወሀት አድራጊ ፈጣሪ የነበረው መለስ ዜናዊ እና ዘ-ህወሀት ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም ስልጣን ሲቆጣጠሩ እንዲህ የሚል አንድ እና አንድ ተልዕኮ ነበራቸው፡ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ፍጹም እና አጠቃላይ በሆነ መልኩ ማጥፋት እና ማውደም የሚል ነበር፡፡
ዘ-ህወሀት እና የእነርሱ ወሮባ ዘራፊ አለቆቻቸው ላለፉት 25 ዓመታት ተልዕኳቸውን ለማስፈጸም ሌት እና ቀን ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡
ሆኖም ግን ዘ-ህወሀት እንዳሰበው እና እንደተመኘው ሙሉ በሙሉ እና ፍጹም በሆነ መልኩ ተልዕኮውን ሳያሳካ የወደቀ መሆኑን ስዘግብ ታላቅ ደስታ ይሰማኛል፡፡
ኢትዮጵያን ለማጥፋት ታጥቀው የተነሱ ሁሉ በመጨረሻ እራሳቸው ይጠፋሉ፡፡ ግንቦት 20 ቀን 2008 ዓ.ም 25ኛ ዓመቱን የእዮ በልዩ በዓሉን እያከበረ ላለው ለዘ-ህወት የምመኝለት ይህንን ነገር ነው፡፡
ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የውርደት ዕለት ሆና በኢትዮጵያውያን አዕምሮ ውስጥ ለዘላለም ስትታወስ ትኖራለች፡፡
የዘ-ህወሀትን 25ኛ ዓመት የእዮ በልዩ በዓል ሌላ ማንም ሳይሆን የዘ-ህወሀት አባላት፣ ጓዶች፣ ታዛዥ ሎሌዎች፣ ጋሻ ጃግሪዎች፣ ደጋፊዎች፣ አጋሮች፣ ግብረ አበሮች፣ ጓደኞች እና ተባባሪዎች በማክበር ላይ ይገኛሉ፡፡
ሌላው እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በተሰበረ ልብ እና በተራበ አንጀት ከዳር ቆሞ ይመለከታል፡፡ ሆኖም ግን የኢትዮጵያ ህዝቦች የመጨረሻው የምጸአት ቀን መቼ እንደሚደርስ ጥርሳቸውን እየነከሱ እና የሌባ ጣቶቻቸውን እየቀሰሩ እራሳቸውን በመጠየቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ ሌላ ምንም ዓይነት ነገር ሳልጨምር ያለውን ነባራዊ ሁኔታ እንዳለ እንደወረደ በመናገር ላይ ነው ያለሁት፡፡ ዘ-ህወሀት በሚሊየኖች ለሚቆጠሩት የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ በማለት እና እንዲሁ ምንም ነገር ሳያደርግ በዘፈቀደ ተቀምጦ መጠበቅ ማለት እሳተ ገሞራ ከመፈንዳቱ በፊት እያቃጠለ እንዳለው የቀለጠ የእሳተ ገሞራ ፈሳሽ ዓይነት ሁኔታ ላይ እንደተቀመጠ ያውቃል፡፡
ወይም ደግሞ ምናልባትም እንዲህ እንደሚለው በግድቡ ላይ እንዳለችው ጣት ዓይነት ተረት መሆኑ ነው፡፡ “በግድቡ ስንጥቅ ላይ ጣትን በመለጠፍ ግድቡን ከመደረመስ ማዳን አይቻልም፡፡“ በመጨረሻው ሰዓት ግድቡ በሚደረመስበት ጊዜ ምን ሁኔታ ሊከሰት ይችላል?
ስለዚህ ጉዳይ ምንም ዓይነት ጥርጣሬ የለም፡፡ በድቅድቅ ጨለማ እንደሚመጣ ሌባ ሁሉ የዘ-ህወሀት የፍጻሜ የምጻት ቀንም ባልተበቀ ሁኔታ ከተፍ ይላል፡፡
ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም ለእኔ እና በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩት ኢትዮጵያውያን የውርደት ዕለት መሆኗን ዘ-ህወሀት ሊያውቅ ይገባል፡፡
ግንቦት 20 ቀን 2008 ዓ.ም ሲከበር እ.ኤ.አ በ2005 ተካሄደ የተባለውን የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ እንደማታለያ በመጠቀም በጠራራ ጸሐይ ላይ የተደረገውን የድምጽ ዘረፋ በመቃወም ቅሬታቸውን በሰላማዊ መንገድ ለመግለጽ ወደ አደባባይ በወጡት 193 ንጹሀን ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ላይ ዘ-ህወሀት የፈጸመውን እልቂት በዓለም ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያን እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሁሉ እንደሚያስታውሱት ሊያውቅ ይገባል፡፡
እ.ኤ.አ በ2005 ተካሄደ የተባለውን የይስሙላ የቅርጫ ምርጫን ዘ-ህወሀት እንደ መሳሪያ በመጠቀም በ761 ንጹሀን ወገኖቻችን ላይ የፈጸመውን አረመኒያዊ እና ጭካኔ የተሞላበትን ጥቃት በዓለም ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያን እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሁሉ እንደሚያስታውሱት ሊያውቅ ይገባል፡፡
እ.ኤ.አ በ2005 ተካሄደ የተባለውን የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ ተከትሎ በ10 ሺዎች በሚቆጠሩ ንጹሀን ወገኖቻችን ላይ ዘ-ህወሀት ያደረገውን እስራት በዓለም ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያን እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሁሉ እንደሚያስታውሱት ሊያውቅ ይገባል፡፡
እ.ኤ.አ በ2005 ተካሄደ በተባለው የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ ተከስቶ በነበረው ውዝግብ አሁን በህይወት በሌለው በመለስ ዜናዊ ልዩ ትዕዛዝ በንጹሀን ወገኖቻችን ላይ ምላጭ በመሳብ እልቂት በፈጸሙት እና በስም እና በመልክ በሚታወቁት 237 የውክልና ቅጥር ነብሰ ገዳዮች ላይ ምንም ዓይነት የሕግ ተጠያቂነት ሳይኖር ጉዳዩ እስከ አሁን ድረስ መቆየቱን ዘ-ህወሀት በዓለም ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያን እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሁሉ እንደሚያስታውሱት ሊያውቅ ይገባል፡፡
ከዓለም አቀፍ የድህነት እና ረሀብ አቃጣሪ ወትዋቾች ጋር በመመሳጠር እየተስፋፋ በመጣው ረሀብ ላይ ሸፍጥ በመስራት እና በመደበቅ ዘ-ህወሀት ያቆየውን ዕኩይ ምግባር በዓለም ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያን እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሁሉ እንደሚያስታውሱት ሊያውቅ ይገባል፡፡
የዘ-ህወሀት አለቆች የኢትዮጵያ ሕዝብ በቀን ሶስት ጊዜ መመገብ ከቻለ የእነርሱ መንግስት ስኬቱ የሚለካው በዚህ እንደሆነ የተናገሩትን በዓለም ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያን እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሁሉ እንደሚያስታውሱት ሊያውቅ ይገባል፡፡ በአሁኑ ጊዜ 20 ሚሊዮን የሚሆኑ ወገኖቻቸን የሚላስ የሚቀመስ በማጣት በችግርና ረሃብ አለንጋ በመጠበስ ላይ ናቸው፡፡
በአሁኑ ጊዜ በንጹሀን ወገኖቻችን ላይ ከሕግ አግባብ ውጭ በዘፈቀደ ዘ-ህወሀት እያደረገ ያለውን በቁጥጥር ስር የማዋል እና በድብቅ በተያዙ እና በሚታወቁ የማጎሪያ እስር ቤቶች የሚፈጸመውን እስራት እንዲሁም በሺዎች በሚቆጠሩ ንጹሀን ወገኖቻችን ላይ እተፈጸመ ያለውን እስራት በዓለም ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያን እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሁሉ እንደሚያስታውሱት ሊያውቅ ይገባል፡፡
በኦጋዴን አካባቢ በርካታ በሆኑ ንጹሀን ወገኖቻችን ላይ ዘ-ህወሀት የፈጸመውን ሰብአዊ የዘር ማጥፋት ወንጀል በዓለም ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያን እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሁሉ እንደሚያስታውሱት ሊያውቅ ይገባል፡፡
በጋምቤላ አካባቢ በርካታ የሆኑ ንጹሀን ወገኖቻችን ላይ ዘ-ህወሀት የፈጸመውን ሰብአዊ የዘር ማጥፋት ወንጀል በዓለም ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያን እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሁሉ እንደሚያስታውሱት ሊያውቅ ይገባል፡፡
በጋምቤላ አካባቢ በመንደር ማሳባሰብ ሰበብ በመቶዎች እና በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በዘ-ህወሀት ከመኖሪያ ቦታቸው እየተፈናቀሉ ለአስከፊ ችግር መዳረጋቸውን በዓለም ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያን እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሁሉ እንደሚያስታውሱት ሊያውቅ ይገባል፡፡
ከሕግ አግባብ ውጭ በዘ-ህወሀት እብሪት በማጎሪያው እስር ቤት ታስረው አሳር ፍዳቸውን የሚያዩትን እስክንድር ነጋን፣ በቀለ ገርባን፣ አህመዲን ጀቤልን፣ ውብሸት ታዬን፣ ተመስገን ደሳለኝን፣ አንዷለም አራጌን፣ አንዳርጋቸው ጽጌን፣ እማዋይሽ ዓለሙን፣ ዴልዴሳ ዋቆ ጃርሶን፣ አኬሎ አኮይ ኡቻላን፣ የዞን 9 ጦማሪዎችን፣ የስዊድን ጋዜጠኞች በሆኑት በጆሀን ፔርሰን እና በማርቲን ሽብዬ እንዲሁም በሌሎች በበርካታዎቹ ንጹሀን ዜጎች ላይ ዘ-ህወሀት እየፈጸመ ያለውን ሕገ ወጥ የሰብአዊ መብት ጥሰት በዓለም ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያን እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሁሉ እንደሚያስታውሱት ሊያውቅ ይገባል፡፡
በኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመውን የመሬት ቅርምት በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተው በነበሩት በመቶዎች በሚቆጠሩ የዩኒቨርሲቲ እና የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ላይ ዘ-ህወሀት የፈጸመውን እልቂት በዓለም ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያን እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሁሉ እንደሚያስታውሱት ሊያውቅ ይገባል፡፡
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የኃይማኖት ነጻነት እንዲከበር እና ኃይማኖት እና ፖለቲካ እንዲለያዩ በመጠየቃቸው ብቻ ዘ-ህወሀት ሕገ ወጥ በሆነ መልኩ በእስራት እያማቀቃቸው የሚገኝ መሆኑን በዓለም ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያን እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሁሉ እንደሚያስታውሱት ሊያውቅ ይገባል፡፡
በውርደት እና ኢፍትሀዊነት በተንሰራፋበት ከባቢ አየር ከመኖር ይልቅ በመቶዎች የሚቆጠሩ ጋዜጠኞች፣ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ወጣት ወንዶች እና ሴቶች ስደትን በመምረጥ የጥቃት ሰለባ እንዲሆኑ ዘ-ህወሀት የሚያደርገውን እኩይ ድርጊት በዓለም ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያን እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሁሉ እንደሚያስታውሱት ሊያውቅ ይገባል፡፡
ጭቆናን ለማምለጥ ሲሉ ወደ ሊቢያ በመሰደድ ሌላውን ዘ-ህወሀት በመጋፈጥ አንገታቸውን እየተቀሉ የግፍ ሰለባ እንዲሆኑ ያደረገውን ዘ-ህወሀት በዓለም ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያን እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሁሉ እንደሚያስታውሱት ሊያውቅ ይገባል፡፡
ወጣት ኢትዮጵያውያን በአይኤስአይኤስ/አይኤስአይኤል (ISIS/ISIL) እልቂት ሲፈጸምባቸው እየታየ ዝም ማለት፣ መካድ እና የደንታቢስነት ስሜትን በማሳየት ዘ-ህወሀት ሲፈጽም የነበረውን ዕኩይ ምግባር በዓለም ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያን እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሁሉ እንደሚያስታውሱት ሊያውቅ ይገባል፡፡
የሳውዲ አረቢያ መንግስት በኢትዮጵያውያን የቤት ሰራተኞች ላይ ኢሰብአዊ በሆነ መልኩ ወንጀል ሲፈጽምባቸው በግልጽ እየተመለከተ ዘ-ህወሀት ምንም ዓይነት ጥረት አለማድረጉን በዓለም ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያን እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሁሉ እንደሚያስታውሱት ሊያውቅ ይገባል፡፡
ዘ-ህወሀት የኢትዮጵያ ታሪክ የ100 ዓመት እድሜ ነው እያለ በመቅጠፍ ላይ የሚገኘውን የፍብረካ ታሪክ በዓለም ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያን እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሁሉ እንደሚያስታውሱት ሊያውቅ ይገባል፡፡
የዓለም ባንክ “በኢትዮጵያ ሙስናን መመርመር“ በሚል ርዕስ አዘጋጅቶት የነበረውን ባለ500 ገጽ የሙስና ምርመራ ዘገባ ሰነድ ዘ-ህወሀት በዓለም ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያን እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሁሉ እንደሚያስታውሱት ሊያውቅ ይገባል፡፡
በወያኔ አገዛዝ ኢትዮጵያን የለማኝ ሀገር እንድትሆን ዘ-ህወሀት ትቶት ያለፈውን ትሩፋት በዓለም ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያን እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሁሉ እንደሚያስታውሱት ሊያውቅ ይገባል፡፡
መሬት በኢትዮጵያ ውስጥ ሙሉ በሙሉ እና አጠቃላይ በሆነ መልኩ የመንግስት ይዞታ ሆኖ ዘ-ህወሀት እንደፈለገው የሚያደርግበትን ሁኔታ በዓለም ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያን እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሁሉ እንደሚያስታውሱት ሊያውቅ ይገባል፡፡
በመሬት ቅርምት ምክንያት በዘ-ህወሀት አምባገነናዊ አመራር ከቤት ንብረታቸው እንዲፈናቀሉ የተደረጉትን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አርሶ አደር ወገኖቻችንን ስቃይ እና እንግልት በዓለም ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያን እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሁሉ እንደሚያስታውሱት ሊያውቅ ይገባል፡፡
በአሁኑ ጊዜ በአንድ ወቅት የኩራት ሀገር የነበረችውን የጀግኖች ሀገር ክብር አዋርዶ ዘ-ህወሀት የእራሱ መፈንጫ እና መደሰቻ በማድረግ ለሀገሪቱ ሕዝቦች ሳይሆን የእራሱን የግል በዓል በማክበር ላይ እንደሚገኝ በዓለም ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያን እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሁሉ እንደሚያስታውሱት ሊያውቅ ይገባል፡፡
የእነርሱን 25ኛ ዓመት የእዮ ቤልዩ በዓል ያክብሩ፡፡
የ13 ወራት ሙሉ የጸሐይ ብርሀን በማይለያት ምድር ላይ የእራሳቸውን ቀልድ ይቀልዱ፡፡
በመንገዶች ላይ ይደንሱ፡፡ በድል አድራጊነት መንፈስ ይቦርቁ፣ ይፈንጥዙ፡፡
እኛም እንደዚሁ የውርደት ማቅ የለበስንባትን ዕለት መዝግበን እንይዛለን፡፡
ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ምን በኢትዮጵያ ታሪክ በውርደት ስናስታውሳት እንኖራለን፡፡
ዘ-ህወሀት በ25ኛው የእዮ ቤልዩ በዓሉ ላይ ምን እንደሚሰራ ጉዳያችን አይደለም፣ ምክንያቱም ታላቁ የአፍሪካ ፓን አፍሪካኒስት ክዋሜ ንክሩማህ በአንድ ወቅት እንደተናገሩት ኢትዮጵያ ትነሳለች፡፡
ኢትዮጵያ ከተንከባለለችበት የዘ-ህወሀት ትቢያ በድል አድራጊነት ትነሳለች፡፡
ኢትዮጵያ ከተንከባለለችበት የዘ-ህወሀት ትቢያ በድል አድራጊነት ትነሳለች ምክንያቱም ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች ተብሎ በቅዱስ መጽሐፉ ተጽፏልና፡፡
ኢትዮጵያ ትነሳለች፡፡
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዕንቁ፣
ታሪክ ያላት በደማቁ፣
በልምላሜ የተሸፈነች፣
የሰውን ቀልብ የሳበች፣
በጀግንነት የታወቀች፡፡
የዓባይ ውኃ መፍለቂያ፣
ጥንታዊ ሀገር አቢሲኒያ፣
የብልሆች ሀገር ኢትዮጵያ፣
ለም የትምህርት መፍለቂያ፡፡
የጥንት ታሪክ መገኛ፣
የአፍሪካ ኩራት ሁነኛ፣
የአምባገነኖች መጋኛ፣
የኩራት ሀገር የእኛ፡፡
የአፍሪካ ባህል ቅርሳችን፣
የእኛነታችን የአንድነታችን፣
የማንነት አሻራ የስብዕናችን፡፡
ሀገረ ምድር የፈላስፋ፣
የአፍሪካውያን ተስፋ፣
ትነሳለች በይፋ፣
አቧራዋን አራግፋ፡፡
ከወደቀችበት ትነሳለች፣
ከእኛ ጋር ትታደሳለች፣
በስልጣኔ ትጓዛለች፡፡
የአፍሪካ ተስፋ ቀንዲል፣
ባለታሪክ የአፍሪካ ዕድል፡፡
የጋና ፕሬዚዳንት የነበሩት ክዋሜ ንክሩማህ (እ.ኤ.አ ግንቦት 28/2063 የአፍሪካ አንድነት ድርጅት በተመሰረተበት ዕለት በበዓሉ ላይ በመገኘት ካደረጉት የመዝጊያ ንግግራቸው የተወሰደ)
ኢፍትሀዊነትን የዘራ ሁሉ መከራን ያጭዳል፡፡
ግንቦት 20 ቀን 2008 ዓ.ም የኢትዮጵያ የውርደት ዕለት መታሰቢያ!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!