የዩኤስኤአይዲ/USAID የምግብ እጥረት ጨዋታዎች በኢትዮጵያ፣

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም    

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ 

Famine 7የረሀብ ወይም የድርቅ ጨዋታዎች በኢትዮጵያ?

ዩኤስኤአይዲ/USAID በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የምግብ እጥረት እንጅ ረሀብ አይደለም ይላል፡፡ (ኤል ኒኖ የተባለው የአየር ለውጥ ባስከተለው ችግር ምክንያት ያለው ነገር አስከፊ የአልሚ ምግብ ንጥረ ነገር እጥረት፣ የምግብ ዋስትና እጦት፣ የምግብ እጥረት፣ በቂ ምግብ ያለመኖር፣ የምግብ እጦት፣ አስከፊ የምግብ እጦት፣ አስከፊ የምግብ ንጥረ ነገር እጥረት፣ ጥልቅ የምግብ ንጥረ ነገር እጥረት፣ ወዘተ ብቻ ነው) ይላል ዩኤስኤአይዲ፡፡

እኔ ደግሞ ረሀብ አለ እላለሁ! ረ-ሀ-ብ  አለ !!!

ባለፉት ስምንት ዓመታት ሳቀርባቸው በነበሩት በርካታ ትችቶቼ ረሀብ በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ሲከሰት፣ ተደጋግሞ ሲከሰት እና በድንገተኛ መልኩ ሲንሰራፋ የቆየ መሆኑን ትኩረት በመስጠት ሳሳስብ ቆይቻለሁ፡፡

እ.ኤ.አ ሚያዝያ 2016 በኢትዮጵያ ውስጥ ረሀብ አለ ወይስ የለም?

በኢትዮጵያ ውስጥ ይህንን ጥያቄ መመለስ የሚችሉት የምጽዓት ቀን የሆነውን ባለጥቁር ፈረሱን ረሀብ ፊት ለፊት በተጨባጭ ተጋፍጠው የሚገኙት የኢትዮጵያ ሕዝቦች ብቻ ናቸው፡፡

እነዚህ ሕዝቦች ተናግረዋል፡፡

የትግራይ ሕዝብ ከመቸውም ጊዜ በላይ አስከፊ በሆነ ረሀብ ውስጥ እየተሰቃዩ መሆናቸውን ለዩኤስኤአይዲ/USAID ተናግረዋል፡፡

ከጥቂት ሳምንታት በፊት የትግራይ ሕዝብ ለዩኤስ አሜሪካ የውጭ አደጋ ረዳት የዩኤስኤአይዲ/USAID ጽ/ቤት ዳይሬክተር ለሆኑት ለጀርሚ ኮኒንዲክ በረሀቡ ምክንያት ጠቅላላ ለመጥፋት በቋፍ ላይ እንደሚገኙ  ተናግረዋል፡፡

ኮኒንዲክ የትግራይ ሕዝብ የነገረውን እንዲህ በማለት አጠቃልሎ አቅርቦታል፡

“ይህ ድርቅ መጠነ ሰፊ ነው፡፡ በሀገሪቱ በአብዛኛው አካባቢ ካለፉት 50 ዓመታት ወዲህ ታይቶ የማያውቅ አስከፊ የሆነ ድርቅ ነው…በትላንትናው ዕለት ከትግራይ እየወጣን በነበርንበት ጊዜ ከዚህ ቀደም በህይወታቸው ውስጥ እንደዚህ ያለ አስከፊ ረሀብ አይተው እንደማያውቁ – በበርካታ መንገዶች .ኤአ. 1983 1984 ከተከሰተው ድርቅ እጅግ የከፋ መሆኑን ከበርካታ ማህበሰቦች ጋር ባደረግነው ውይይት ነግረውኛል፡፡ እንደዚህም ሆኖ ይህ በአሁኑ ጊዜ የተከሰተው ድርቅ ውጤቱ እ.ኤ.አ በ1984 ከተከሰተው ድርቅ ውጤት ጋር ተመሳሳይ እንደማይሆን እናውቃለን…” (አጽንኦ ተጨምሯል፡፡)

እ.ኤ.አ በ1984 የተከሰተው ድርቅ ውጤቶች ምን ነበሩ?

ከ32 ዓመታት በፊት እ.ኤ.አ በ1984 በትግራይ ክልል እና በሌሎች የኢትዮጵያ ሰሜናዊ የሀገሪቱ አካባቢዎች ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን አውዳሚ ለሆነ የረሀብ ሰለባነት ተዳርገው ነበር፡፡

በአሁኑ ጊዜ የትግራይ ሕዝብ ከኮኒንዲክ እና ለዩኤስኤአይዲ/USAID በህይወታቸው እንደዚህ ያለ ድርቅ አይተው እንደማያውቁ የተናገሩ ቢሆንም ኮኒንዲክ እራሱም ባለፉት 50 ዓመታት ውስጥ እንደዚህ ያለ አስከፊ ድርቅ ተከስቶ እንደማያውቅ አምኗል፡፡ ኮኒንዲክ እና ዩኤስኤአይዲ/USAID እንደዚህ ያለ አሰቃቂ ሁኔታ መፈጠሩን ለመግለጽ  “ረ”ሀብ  የምትለዋን ቃል በፍጹም ደፍረው አይጠሯትም፡፡ ይፈራታል !

Konyndykኮኒንዲክ በትግራይ ሕዝብ ዘንድ ያለውን አስከፊ ችግር ባለማወቅ በድንቁርና ነው ወይስ ደግሞ ለአስከፊው ቀውስ ምንም ዓይነት ትኩረት ባለመስጠት ጀሮ ዳባ ልበስ ለማለት ነው?

ኮኒንዲክ በዚህ አስከፊ ድርቅ/ረሀብ ክፉኛ የተጠቁትን በርካታዎችን የኦሮሚያ፣ አፋር፣ አማራ እና የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችን ክልሎች ቢጎበኝ ኖሮ ከዚህ ጋር የተያያዘ ታሪክ ይሰማ እንደነበር የሚያጠያይቅ ጉዳይ አይደለም፡፡

እውነት ለመናገር ኮኒንዲክ ወደ ሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች ለምን እንዳልሄደ የማውቀው ነገር የለም፡፡

ምናልባትም ኮኒንዲክ ወደ ሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች እንዳይሄድ ዘ-ህወሀት (ዘራፊ ህወሀት)  ባለመፍቀዱ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ ምናልባት ኮኒንዲክ ወደ ትግራይ ክልል ሄዶ ስለአስከፊ አልሚ ምግብ ንጥረ ነገር እጥረት ጉዳይ የዘ-ህወሀትን ፕሮፓጋንዳ መስመር አይቶ እና ሰምቶ ፎቶግራፎችን በማንሳት በመመለስ በአዲስ አበባ በባለ “5 ኮከብ ሆቴል” ውስጥ በመገኘት መግለጫ እንዲሰጥ ታስቦ ሊሆን ይችላል፡፡

ሆኖም ግን የትግራይ ሕዝብ የሚላስ የሚቀመስ ምንም ዓይነት ነገር ጠፍቶ በከፍተኛ የረሀብ ስቃይ ውስጥ የሚገኝ እንጅ በአስከፊ የአልሚ ምግብ ንጥረ ነገር እጥረት ተዳርገው እንደሚገኙ የማስመሰያ ውሸት አይናገሩም፡፡ ለኮኒንዲክ እውነታውን ፍርጥ አድርገው ነግረውታል፡፡ አውዳሚ በሆነ ረሀብ እየተሰቃዩ መሆናቸውን ነግረውታል!

የዩኤስ አሜሪካ የውጭ አደጋ ረዳት ዋና ሹም የተሟላ ስዕል ሊሰጥ የሚችል መረጃ ለማግኘት እንዲችል በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ቢያንስ ጥቂት አካባቢዎችን ማየት ምንም ዓይነት ትርጉም አልሰጠውም ማለት ነውን?

ምናልባትም ኮኒንዲክ ድርቅ/ረሀብ ያለበትን አንዱን አካባቢ ካየህ ሁሉም ያው ነው ተብሎ ስለሚነገረው ሌሎች የሀገሪቱን አካባቢዎች ለመጎብኘት ደንታ ሳይሰጠው ቀርቶ ሊሆን ይችላል!

ኮኒንዲክ እና ዩኤስኤአይዲ/USAID ስለድርቅ፣ ድርቅ፣ ድርቅ ደግመው ደጋግሞ ያወራል …?

ሆኖም ግን እንዲህ የሚለውን ተገቢ የሆነ ጥያቄ እና ምላሽ ለሕዝብ ይፋ አያደርጉም፡ የድርቅ መንስኤዎች እና ውጤቶች ምንድን ናቸው?

ኮኒንዲክ ሲደረግለት የነበረውን ቃለ መጠይቅ ጥያቄ ግልጽ አድርጓል፡፡ እንዲህ ብሏል፣ “የዚህ የ[2016]  የድርቅ ውጤት እ.ኤ.አ በ1984 ከነበረው የድርቅ ውጤት ጋር አንድ ዓይነት አይሆንም፡፡“

እ.ኤ.አ በ1984 የደረሰሱ የድርቅ ውጤጦች በእርግጠኝነት ምንድን ናቸው?

ኮኒንዲክ ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ባለፉት 50 ዓመታት ውስጥ አጋጥሟት የማያውቅ መጠነሰፊ ለሆነ የድርቅ አደጋ ተዳርጋ ትገኛለች ይላል!

.. 1984-85 ተከስቶ የነበረው መጠነሰፊ ድርቅ መጠነሰፊ የሆነ ረሀብን አስከትሎ ነበር፡፡ ሆኖም ግን ኮኒንዲክ .. 2016 የተከሰተው መጠነሰፊ ድርቅ የሚያስከትለው መጠነሰፊ ድርቅ እንደሆነ ብቻ አድርጎ በማረብ እንድናምን ይፈልጋልን?

“ወይ ጉድ ! ገና ከመጀመሪያው ማታለል ስንጀምር ምን ዓይነት ድር ነው እያደራን ያለነው፡፡”

ዩኤስኤአይዲ/USAID በኢትዮጵያ ውስጥ ተከስቶ ስለነበረው ድርቅ/ረሀብ እውነተኛው ነው ብሎ የተናገረበት ጊዜ ነበር፡፡

ያ ጊዜ ከሶስት አስርት ዓመታት በፊት ነበር፡፡ ጊዜ እና ታላቅ ውሸት ከጊዜ ጋር እንዴት ይበራል እባካችሁ!

ዩኤስኤአይዲ/USAID “የመጨረሻ የአደጋ ዘገባ፡ እ.ኢ.አ የ1985-86 የኢትዮጵያ ድርቅ/ረሀብ“ በሚል ርዕስ (ገጽ iii) ባቀረበው የአደጋ ዘገባው እንዲህ በማለት ተናግሮ ነበር፡

“እ.ኤ.አ በ1984 በጠንካራው የቴሌቪዥን አዲስ ማሰራጫ አማካይነት በኢትዮጵያ ውስጥ ለአሰቃቂ ረሀብ ተዳርገው የነበሩትን ኢትዮጵያውያን ለማወቅ በቅቶ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ በ1984 መጨረሻ በረሀቡ ምክንያት 8 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎች ለሞት አደጋ ተግልጠው እንደነበር እና 1.3 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ምግብ እና ከዚህም በተጨማሪ ሌሎች በሚሊዮኖች ዶላር የሚቆጠር የአስቸኳይ ጊዜ የእርዳታ አቅርቦት እንደሚያስፈልግ ግልጽ ተደርጎ ነበር፡፡ የተሰጡት ምላሾች እጅግ የገዘፉ ነበሩ፡፡“ (አጽንኦ ተጨምሯል፡፡)

እ.ኤ.አ ሚያዝያ 2016 ኮኒንዲክ እንዲህ ይላል፡

“ባለፉት 50 ዓመታት ውስጥ በሀገሪቱ በርካታ አካባቢዎች ተከስቶ የማያውቅ አስከፊ ድርቅ ነው…ቁጥሩ ማለትም የእርዳታ ፈላጊው ብዛት 10 ሚሊዮን ይበልጣል እናም በአሁኑ ጊዜ ያለው ትንበያ የሚያሳየው ይህንን ነው፡፡ ቀጣዩ የክረምት ወቅት ከዚህ የከፋ እንደሚሆን እንገምታለን…“ (አጽንኦ ተጨምሯል፡፡)

ኢትዮጵያ ባለፉት 50 ዓመታት ውስጥ አጋጥሟት ለማያውቅ ድርቅ ተዳርጋ የምትገኝ ቢሆንም ኮኒንዲክ “ረ“ሀብ የምትለዋን ቃል ለመጥራት አፉን ተለጉሞ ይገኛል፡፡

በአንድ ወቅት ቮልቴር እንቆቅልሹን እጅግ ጥልቅ በሆነ መልኩ በማሰብ “አስመሳይነትን ለመግለጽ ምን ያህል አስቸጋሪ ነገር ነው! ማጭበርበር እና ጭካኔ የተመላበት አስመሳይ መሆን ምን አይነት አስፈሪ ነገር ነው?” ብለው ነበር፡፡

የዓለም ህዝብ ሆዳቸው የተነፋውን እና ሰውነታቸው እየሟሸሸ ያለቀውን የኢትዮጵያ ህጻናት በኃይለኛው አዲሱ የቴሌቪዥን ማሰራጫ እንዴት ማየት ይሳነዋል?

መልሱ እንዲህ የሚል ቀላል ነገር ነው፡ “ዘ-ህወሀት በድርቅ ክፉኛ ከተመቱ አካባቢዎች ሁሉንም ዓይነት መረጃዎች ደብቆ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ በመገኘቱ ምክንያት ነው፡፡“

የድርቅ አደጋው ካለባቸው ማናቸውም አካባቢ ቢሆን ማንም ጋዜጠኛ በመሄድ ዘገባ የሚያቀርብ ከሆነ በዘ-ህወሀት በጸረ አሸባሪነት ሕግ የሸፍጥ ክስ ይመሰረትበታል፡፡

ሆኖም ግን በዘ-ህወሀት የሚመረመሩት እና የሚከለከሉት ጋዤጠኞች ብቻ አይደሉም፡፡

ከዚህም በላይ ዘ-ህወሀት “ረ“ሀብ ወይም ደግሞ “ቸነፈር“ የሚሉ ቃላትን እና ሀረጎችን ለምሳሌ ያህልም “ህጻናት በየዕለቱ ይሞታሉ“፣ “ለተፈጠረው ችግር የመንግስት ፖሊሲዎች በከፊል አስተዋጽኦ አላቸው“  የሚሉ መግለጫዎችን የሚያወጡትን መንግስታዊ ያልሆኑ የውጭ ድርጅቶችን ከፍተኛ የሆነ ማስጠንቀቂያ ይሰጣቸዋል፣ የማስፈራራት ድርጊትም ይፈጸምባቸዋል፡፡ ከዚያም ጭራቸውን ወትፈው ወደመጡበት እንዲሄዱ ይገደዳሉ ወይም ደግሞ ምንም ነገር ትንፍሽ ሳይሉ እንዲቀመጡ ይደረጋሉ!

በኃይለኞቹ እና በአዲሶቹ የቴሌቪዥን ማሰራጫዎች በድብቅ ተቀርጾ ምስላቸው የወጣ ሆዳቸው የተነፋ እና ሰውነታቸው የሟሸሸ ጥቂት የኢትዮጵያ ህጻናት ፎቶግራፎችን ማየት የምንጀምረው መቼ ይሆን?

ይኸ ቀላል ነገር ነው፡፡ ዘ-ህወሀት ዓለም አቀፍ የዜና ማሰራጫዎች በድርቅ የተጎዱ አካባቢዎችን በነጻ መመልከት እንዲችሉ ሲፈቅድላቸው ወዲያውኑ ነው፡፡

ኮኒንዲክ ከእርሱ ጋር ዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች የትግራይ ክልልን እና ሌሎችንም በድርቁ/ረሀብ የተመቱ የሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እንዲጎበኙ እና በነጻ ዘገባቸውን እንዲያቀርቡ የሚያደርግ ከሆነ ለአሜሪካ ግብር ከፋይ ሕዝብ ትልቅ አገልግሎት እንደፈጸመ ይቆጠራል፡፡

እንደገና ተወልጃለሁ/ተሀድሶ አድርጊያለሁ በምትል ሀገር ላይ ዩኤስኤአይዲ/USAID ግልጽነት በጎደለው መልኩ እየሰራ ነወይ ብሎ መጠየቅ የሚበዛ ሊሆን ይችልን? 

ኮኒንዲክ በአዲስ አበባ ከተማ በባለ5 ኮከብ ሆቴል ውስጥ ተቀምጦ ጊዜውን እያሳለፈ ከዓለም አቀፍ ብዙሀን መገናኛዎች ለሚቀርቡለት ጥያቄዎች እንዲህ እያለ ምላሽ ይሰጣል፡ “

(እንዴት ያለ የሚያስገርም ሁኔታ ነው! በባለ5 ኮከብ ሆቴል ውስጥ ተቀምጦ ስለተራቡ ሕዝቦች መናገር አስደናቂ ነገር አይደለምን? ምን ዓይነት አስደማሚ ነገር ነው እባካችሁ!!!“)

ፓውል ሸም (ከአሶሺየት ፕሬስ/ዋሺንግተን ፖስት) እንዲህ ብሎ ነበር፡ “በርካታ የእርዳታ ድርጅቶች ከአንድ ወይም ከሁለት ወራት በፊት የምግብ እርዳታ አቅርቦቱ ምንጭ ሊቋረጥ ይችላል…“ በማለት ተናግረው ነበር፡፡

ኮኒንዲክ በበኩሉ እንዲህ ብሎ ነበር፣ “ስለምግብ አቅርቦት ምንጭ ጉዳይ…  ይህንን ነገር ለማስወገድ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ካለው ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ተነጋግረናል…በምግብ አቅርቦት ምንጩ ላይ የመቋረጥ ሁኔታ እንዳይፈጠር አዘጋጅተውት ካለው ዕቅድ ጋር በተያያዘ መልኩ ከእነርሱ ጋር እስማማለሁ…?“

አትለኝም !?

እስክንድር (ከአሜሪካ ድምጽ የአፍሪካ ቀንድ ሬዲዮ አገልግሎት) እንዲህ የሚል ጥያቄ አቅርቦ ነበር፣ “የሰብአዊ ፍላጎቶች ሰነድ በኢትዮጵያ መንግስት እና በአጋሮቹ በመከለስ ላይ እንደሆነ አያለሁ፡፡ ይኸ ማለት አስቸኳይ እርዳታ የሚፈልጉ 10.2 ሚሊዮን እንደሆኑ ተገንዝበናል ማለት ነውን?“

ኮኒንዲክ፡ “ይህንን ቁጥሩን በመጨረሻ የሚወስነው የኢትዮጵያ መንግስት ነው፣ እና በዚያ ሂደት መሰረት መንግስትን እንረዳለን”  አትለኝም !?

ዩኤስኤአይዲ/USAID በሸፍጥ የተሞላውን የ10 በመቶ ዓመታዊ የኢኮኖሚ ዕደገት መጣኔ የአገዛዙን የቅጥፈት ፕሮፓጋንዳ እንደሚደግፍ አይነት መሆኑ ነውን?

አንዷለም ሲሳይ (ከብሔራዊ ሜዲያ ቡድን) እንደህ የሚል ጥያቄ አቅርቦ ነበር፣ “የእኔ ጥያቄ ለእንደዚህ ዓይነቱ አሰቃቂ ሰብአዊ ቀውስ ዘለቄታዊ መፍትሄው ምንድን ነው የሚል ነው፡፡ በየሶስት እና በየአራት ወይም ደግሞ በየአምስት ዓመቱ በእንደዚህ ያለ ሁኔታ ውስጥ እየተገባ ነው፡፡ ስለሆነም ለእንደዚህ ዓይነት ቀውሶች ዘላቂ መፍትሄው ምንድን ነው ብለው ያስባሉ?“

ኮኒንዲክ፡ “ይኸ ታላቅ እና በእርግጠኝነት ጠቃሚ ጥያቄ ነው…ይህ በየአራት ወይም ደግሞ በየአምስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ የሚከሰት ድርቅ አይደለም፡፡ ይኸ በየ50 ዓመታት ጊዜ ውስጥ የሚከሰት ድርቅ ነው…ይኸ ልዩ እና በጣም ኃይለኛ የሆነ ዓለም አቀፋዊ ኤል ኒኖ ነውኢትዮጵያ በዚህ የአየር ለውጥ መነሻነት እስከ አሁን ድረስ ባስከተለው ቀውስ ተጠቅታለች፣ ሆኖም ግን በአሁኑ ጊዜ ደቡባዊ የአፍሪከ ሀገሮች በከፍተኛ ሁኔታ በመጎዳት ላይ ይገኛሉ፡፡“ (አጽንኦ ተጨምሯል፡፡)

አትለኝም !? ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ በኢል ኒኖ የተመረጠች ሀገር ናት?

በነገራችን ላይ ዩኤስኤአይዲ/USAID የመነጋገሪያ ነጥቦችን እንዴት አድርጎ እንደሚያዘጋጅ ያውቃል፡፡ የዩኤስኤአይዲ/USAID አስተዳዳሪ የሆነችው ጋይሌ ስሚዝ በአንድ በቅርብ ጊዜ አድርጋው በነበረ ቃለ መጠይቅ እንዲህ የሚል ተመሳሳይ ምላሽ ሰጥታ ነበር፣ “ይኸ ኤል ኒኖ እየተባለ የሚጠራው የአየር ንብረት ለውጥ በርካታ የዓለም ክፍሎችን በከፍተኛ ሁኔታ አጥቅቷል፣ ሆኖም ግን በኢትዮጵያ ካደረሰው ጉዳት የከፋ በየትም አገር የለም፡፡ (አጽንኦ ተጨምሯል፡፡)

ሁሉም ከአንድ ምንጭ የተቀዳ ንግግርን ነው የሚያነበንቡት!

በርካታዎቹ የዓለም አቀፍ መገናኛዎች በድርቅ/ረሀብ በተጠቁ አካባቢዎች እየተገኙ ለምን እራሳቸው መዘገብ አይችሉም?

ምቾት ባላቸው በባለ5 ኮከብ ሆቴሎች ውስጥ እየተቀመጡ መረጃዎችን በማንኪያ እንዲጎርሱ የሚደረገው ለምንድን ነው?

ኮኒንዲክ በባለ5 ኮከብ ሆቴል በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ተቀምጦ ለእራሱ ድርጅት፣ ለዘ-ህወሀት፣ ለተባበሩት መንግስታት እና ለሌሎች አጋሮች በጥሩ ሁኔታ በተዘጋጀ ስራ ለራስ ጥቅም ብቻ የሚሰጡ ሀሳቦችን እና ተግባሮችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡

ኮኒንዲክ ለዘ-ህወሀት እንዲህ ይላል፣ “ጠቃሚ የሆነ የጉብኝት መስተንግዶ ስለተደረገልን እና ለበርካታ ዓመታታ ሁለታችንም ባለን መሰረተሰፊ አጋርነት እንደዚሁም ከዚህ ድርቅ ጋር በተያያዘ መልኩ ከምንሰጠው ምላሽ ካለን ጠንካራ አጋርነት አኳያ ለኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ የሆነ ምስጋናችንን ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡“

“በርካታ በርካታ ዓመታት እና  ጠንካራ አጋርነት!“ ከዘ-ህወሀት ጋር!

ነገሩ ይገባኛል፡፡

ባራክ ኦባማ እ.ኤ.አ በ2015 ኢትዮጵን ጎበኘ፣ እናም ገዥው ፓርቲ ዘ-ህወሀት (የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እና በአሁኑ ጊዜ ስሙ በዓለም አቀፍ ደረጃ በአሸባሪዎች የመረጃ ቋት ስም ዝርዝር ውስጥ ተመዝግቦ የሚገኘው እንዲሁም እ.ኤ.አ ግንቦት 2015 ተደረገ በተባለው የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ 100 በ100 አሸነፍኩ ብሎ ያወጀው) “ዴሞክራሲያዊ” ነው በማለት አወጀ፡፡

እንግዲህ ጠንካራ አጋርነት የሚሉት እንዲህ ዓይነቱን ጉዳይ አንዳቸው ለአንዳቸው እየሰሩ በእከክልኝ ልከክለህ መርህ እንደሆነ እገምታሁ፡፡ አንዳቸው ለአንዳቸው እስከ ጥርሳቸው ድረስ ይዋሻሉ፡፡

ባራክ ኦባማ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ፊት በመቆም ህወሀትን ዴሞክራት ነው ብሎ ቢጠራው እና ኮኒንዲክ  በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ፊት በመቆም በኢትዮጵያ ውስጥ ረሀብ ተንሰራፍቶ  እያለ ረሀብ የለም ብሎ ቢክድ ማንም የሚደነቅ ሰው አይኖርም ፡፡

አንድ የቆየ እና እንዲህ የሚል የኢትዮጵያውያን አባባል አለ “ዓሳ የሚገማው ከጭንቅላቱ ነው፡፡“

ኮኒንዲክ እንዲህ የሚል እውቅና ይሰጣል፣ “ለተባበሩት መንግስታት እና መንግስታዊ ላልሆኑ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች አጋሮቻችን በእርግጠኝነት ለዚህ ድርቅ ምላሽ በመስጠት ታላቅ እና የጀግንነት ስራን የሰሩ ስለሆነ ምስጋና ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡“

እነዚህ የንግግር ቃላት በዓለም አቀፉ መገናኛ ብዙሀን ቢነገሩ ኖሮ የተሻለ አይሆንም ነበርን?

ዩኤስኤአይዲ/USAID በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚከሰተው ረሀብ (“በጣም አስከፊ የሆነ የምግብ ንጥረ ነገር እጥረት፣” ወዘተ እያለ የሚጠራው) መነሻው ኤል ኒኖ (የውቅያኖሶች የከርሰ ውኃ ገጽታ መሞቅ እና የአየር ግፊት ዝውውር በመፍጠር የዝናብ መጠኑ የመቀነስ ሁኔታ) ነው ይላል፡፡

የዩኤስኤአይዲ/USAID አስተዳዳሪ የሆነችውን ጋይሌ ስሚዝን የሚያምን ከተገኘ የድርቁ መንስኤ ኤል ኒኖ ብቻ ነው ማለት ሳይበቃት እንዲያውም ኤል ኒኖ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ለቅጣት የተላከ ልዩ ታምራዊ ኃይል ይመስላል፡፡

ጋይሌ ስሚዝ ሰጥታው በነበረው ትርጉም የለሽ መግለጫ እጅግ በጣም ተበሳጭቸ ስለነበር ኢትዮጵያ ከዓለም ሀገሮቸ ሁሉ ከፕላኔቷ ተነጥላ ለምን በከፍተኛ ሁኔታ በኤል ኒኖ ተመታች ብላ እንደተናገረች የሚጠይቅ ደብዳቤ ጽፌ ጠይቂያት ነበር፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ዘ-ህወሀት በመልካም አስተዳደር እጦት፣ አቅዶ እና አስተባብሮ መስራት ባለመቻሉ ምክንያት ድርቅ ሊከተል እንደቻለ ከፊል ምክንያት እንደሚሆን ወይም ደግሞ ለክስተቱ መነሻ፣ መስፋፋት እና/ወይም በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ላለው ድርቅ ዘለቄታዊ ሊሆን እንደሚችል ጋይሌ ስሚዝን ጠይቂያት ነበር፡፡

ስሚዝ የላኩላትን ደብዳቤ ከቁብ ባለመቁጠር ለረዳት አስተዳዳሪዋ አሳልፋ ሰጥታዋለች፡፡ ረዳት አስተዳዳሪው በጻፈው ምላሽ እንዲህ በማለት በቢሮክራሲያዊ ፍሬከርስኪ አባባል ለማታለል ሞክሯል፣ “በመጀመሪያ ደረጃ ከድርቁ ጋር በተያያዘ መልኩ የምግብ እጥረት እና የእንስሳት እልቂት ለመኖሩ እውቅና እንሰጣለን፣ እናም እነዚህ ነገሮች ሰዎች ለመኖር በሚያደርጉት ጥረት ላይ ከፍተኛ የሆነ ቀጥተኛ አሉታዊ ተጽዕኖ ይኖራቸዋል“ ብሏል፡፡

ለመኖር ምንም ዓይነት ጥረት ለማድረግ የሚያስችል አቅም ለሌላቸው ሰዎች ይኸ ምን ሊሆን ይችላል፣ ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች ምንም ዓይነት የሚልሱት የሚቀምሱት ምግብ የላቸውምና?

እኔ ግን በኢትዮጵያ ውስጥ የድርቅ መኖር ዋና መንስዔ የ”ኤል ዘ-ህወሀት” ነው እላለሁ፡፡

ኤል ዘ-ህወሀት ባለፉት 25 ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ በስልጣን ኮርቻ ላይ ተፈናጥጦ ይገኛል፡፡ እ.ኤ.አ ግንቦት 2015 ተደረገ በተባለው የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ ኤል ዘ-ህወሀት መቶ በመቶ አሸነፍኩ በማለት  የፓርላማውን መቀመጫ ወንበሮቸ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን አወጀ፡፡

እ.ኤ.አ በ2010 ኤል ዘ-ህወሀት ተደረገ በተባለው የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ 99.6 በመቶውን አሸነፍኩ በማለት የፓርላማ ወንበሮችን ተቆጣጠረ፡፡

ኤል ዘ-ህወሀት የሸፍጥ ምርጫውን በማካሄድ ላለፉት ስድስት ዓመታት ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ ይገኛል፡፡

ዘ-ህወሀት ባለፉት ስድስት ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ በጣም አስከፊ የሆነውን የምግብ ንጥረ ነገር እጥረትን ለመከላከል ምን ያደረገው ጥረት አለ?

ምንም !

ዘ-ህወሀት ባለፉት ስድስት ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ በጣም አስከፊ የሆነው የምግብ ንጥረ ነገር እጥረት ያስከተለውን ጉዳት ለመቀነስ ምን ያደረገው ጥረት አለ?

ምንም !

ዘ-ህወሀት የሰራው ነገር አለ ከተባለ ሰብአዊ እርዳታውን በድበቅ ከሀገሪቱ ወደ ውጭ በማውጣት በእራሱ የባንክ ሂሳብ አካውንት ውስጥ እያጨቀ ይገኛል፡፡

ዘ-ህወሀት የሰራው ነገር አለ ከተባለ ከዓመት ወደ ዓመት ለዓለም አቀፍ ምጽዋት እና ልመና  የመለመኛ ሳህኑን መዘርጋት ነው፡፡

ከአፍሪካ ነባር ለማኝ መንግስት ከዚህ የበለጠ ነገር አይጠበቅም፡፡

ዩኤስኤአይዲ/USAID እና ህወሀት በኢትዮጵያ በክህደት ጎዳና፣

ዩኤስኤአይዲ/USAID በኢትዮጵያ ውስጥ ተከስቶ ያለውን ረሀብ ጸጥ በማለት በክህደት ሸፍጥ ውስጥ ገብተዋል፡፡

እርስ በእርሳቸው እንኳን ደስ አለህ እየተባባሉ እና እራሳቸው ለእራሳቸው በኢትዮጵያ የክህደት ቃለ መጠይቅ በማድረግ የዓለም አቀፉ ማህበሰብ የእነርሱን ውሸት፣ ተራ ቅጥፈት እና አሀዝ አምኖ እንዲቀበል ይጠብቃሉ፡፡

ዘ-ህወሀት (T-TPLF በሚለው ቃል ውስጥ የመጨረሻዎቹ LF የሚሉት ፊደሎች Lie Factory/የውሸት ፋብሪካ የሚለውን ይወክላሉ) ቢያንስ ባለፉት ስምንት ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ ረሀብ መከሰቱን ሲክድ ቆይቷል፡፡

የዘ-ህወሀት መሪዎች በጫካ በነበሩበት ጊዜ ረሀብ በሁለግብ መልኩ በጣም ጠቃሚው ጉዳይ እና የመነጋገሪያ አጀንዳቸው ነበር፡፡ ረሀብን ማጥፋት እና መከላከል የመኖር እና ያለመኖር የህልውና ማጠናቀቂያ እንደሆነ አድርገው ይቆጥሩት ነበር፡፡

እ.ኤ.አ በ1985 በመቶዎች እና በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በረሀብ ምክንያት እያለቁ በነበረበት ጊዜ አሁን በህይወት የሌለው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ እንዲህ ብሎ ነበር፡

“ሕዝቦች በረሀቡ ካለቁ መዋጋቱ ምንም ዓይነት ዋጋ የለውም፡፡ ይህ በህይወቴ በጣም አሳዛኙ ክስተት ነው፡፡ በርካታ ተስፋየለሽ የሆኑ ጊዚያትን አይቻለሁ፣ ሆኖም ግን ሁሉም ቢሆኑ እንደ አሁኑ ያህል ተስፋየለሽ አልነበሩም፡፡ ምክንያቱም እየተዋጋሁላቸው ያሉት ሕዝቦች በምግብ እጥረት ምክንያት በረሀብ እያለቁ ነው፡፡ ጠንካራ ሰራተኞች ናቸው፣ ሆኖም ግን  በድጋፍ እጥረት ምክንያት፣ ሳይንሳዊ የግብርና የአስተራረስ ተሞክሮ እጥረት ምክንያት እነዚህ ህዝቦች እየሞቱ ነው፡፡ በእራሳቸው ላይ ምንም ዓይነት የጥፋት ምክንት ሳይኖርባቸው እያለቁ ነው፡፡ አንድ ታጋይ በህይወቱ ሊጋፈጠው የሚችለው ጠንካራው ነገር ይኸ ነው፡፡“ (አጽንኦ ተጨምሯል፡፡)

አዎ እውነት ነው የእኛ ቅቤ አንጓጭ የሕዝብ አዛኝ ይህንን ቢል አይደንቅም!

እ.ኤ.አ በ1984-86 መለስ እና ግብረ አበሮቹ ለትግራይ ክልል የተመደበውን በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዶላሮች የሰብአዊ እርዳታ እየመነተፉ ወደ ውጭ ሀገር በመውሰድ የጦር መሳሪያ መግዣ እና የግል መበልጸጊያ አድርገው ተጠቅመውበታል፡፡ ይህንን ጉዳይ በማስመልከት “ዘ-ህወሀት ለመስረቅ ፈቃድ ያለው ድርጅት“ በሚል ርዕስ ቀደም ሲል ያቀረብኩትን ትችት ልብ ይሏል፡፡ እንግዲህ ለጠንካራ ታጋይ ምንም ዓይነት ጥረት ሳይደረግ የተገኘ ገንዘብ እያልኩ የምጠራው ይህንን ነው፡፡

አምባገነኑ መለስ መለስዊ በስልጣን ኮርቻ ላይ ከተፈናጠጠ ከ17 ዓመታት በኋላ እ.ኤ.አ ነሐሴ 2008 ለታይምስ መጽሔት በሰጠው ቃለ መጠይቅ እንዲህ የሚል ፍልስፍና ያዘለ የሚመስል ዲስኩር በማሰማት እራሱን ከፍ ከፍ አድርጎ ተናግሯል፣ “ረሀብ በኢትዮጵያ ለብዙ ዘመናት ቆይቷል፣ እንደዚህ ያለ ሁኔታ በሚከሰትበት ጊዜ ጉዳት አያስከትልም ብሎ ማሰብ ደደብነት ነው፡፡ ሆኖም ግን በእኛ እይታ በአሁኑ ጊዜ ምንም ዓይነት ረሀብ የለም፣ ያለው የአስቸኳይ ጊዜ ነው፣ ግን ምንም ዓይነት ረሀብ በፍጹም የለም፡፡“

የአምባገነኑ መለስ ዜናዊ የግብርና እና የገጠር ልማት ሚኒስትር ዴኤታ የነበረው ምትኩ ካሳ አለቃው ያለውን በመከተል እንዲህ በማለት እንደ ገደል ማሚቶ አስተጋብቶ ነበር፣ “በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ረሀብ የለም፣ ቸነፈር የለም…ረሀብ አለ የሚለው መሰረተቢስ አባባል ነው፣ እናም በመሬት ላይ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ በተጻራሪ የቆመ አባባል ነው፡፡ በመረጃ ላይ የተደገፈ አይደለም፡፡ ችግሮችን ለመፍታት መንግስት እርምጃ በመውሰድ ላይ ይገኛል፡፡“

እ.ኤ.አ በ2011 መለስ ዜናዊ እራሱን ከፍ ከፍ እያደረገ እንዲህ በማለት ድንፋታ አሰምቶ ነበር፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ትርፍ አምራች ለመሆን የሚያስችለንን ዘዴ ቀምረናል፣ እናም .. 2015 ምንም ዓይነት የውጭ እርዳታ ሳያስፈልገን እራሳችንን መመገብ እንችላለን፡፡ በሌላ አገላለጽ ረሀብ፣ ቸነፈር፣ ከፍተኛ የሆነ የአልሚ ምግብ ንጥረ ነገር እጥረት፣ ወዘተ ከኢትዮጵያ ለዘላለም ይወገዳሉ“ ነበር ያለው፡፡ ድንቄም መወገድ መጽደቁ ቀረና ባግባብ በኮነነኝ ይላሉ አባቶች ሲተርቱ! እውነት ነው ሞት ቀደመው እንጅ በምግብ እራሳችንን ያስችለን ነበር፡፡ እናም በምግብ እህል እራሳችንን ችለን ምንም ዓይነት የውጭ እርዳታ አያስፈልገንም በማለት በተደሰኮረለት የዲስኩር የዕቅድ ዓመት እ.ኤ.አ በ2015 ሁኔታው ተለውጦ የሚላስ የሚቀመስ የሚታጣበት እና ሰብአዊ እርዳታ እቅራቢ የውጭ ድርጅቶችን እርዱን፣ ምጽዋት አቅርቡልን በማለት የልመና ኮሮጇቸውን ይዘው በመለመን ላይ የሚገኙበት ለመሆን በቅቷል፡፡

እ.ኤ.አ ጥር 2012 ሲኤንኤን ለአምባገነኑ መለስ ዜናዊ እንዲህ የሚል ጥያቄ አቅርቦለት ነበር፣ “ኢትዮጵያ ከፍተኛ ለሆነ ረሀብ ተዳርጋለች፡፡ የእራስዎ ሕዝብ እየተራበ ባለበት ሁኔታ በሌላ ሀገር ጉዳይ ላይ ወታደራዊ ወጭ ለማውጣት የሚችሉት እንዴት ነው?“ ዜናዊ እንዲህ በማለት ምላሽ ሰጠ፣ “የሰብአዊ እርዳታ ለጋሽ ድርጅቶች እንደሚነግሩህ ሳይሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ዓይነት ረሀብ የለም፡፡ አስከፊ የሆነ ድርቅ ነው ያለው፣ ሆኖም ግን ህዝባችንን በመመገብ ላይ እንገኛለን…“

እ.ኤ.አ ሰኔ 2012 ዩኤስኤአይዲ እንዲህ የሚል ዘገባ አቀረበ፡

“በአንዳንድ ክልል አካባቢዎች ድርቁ ባለፉት 60 ዓመታት ውስጥ ታይቶ የማያውቅ እና በአፍሪካ ቀንድ 13.3 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎችን ለአስከፊ ጉዳት ይዳረግ እንደነበር ይታሰባል፡፡ ይፋ መግለጫ ከመስጠቱ ከአንድ ወር በፊት የዩኤስኤአይዲ/USAID የረሀብ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት ኔትወርክ (ረቅማስኔ) /Famine Early Warning Systems Network (FEWS NET) እንዲህ በማለት አስጠንቅቆ ነበር፡ ‘በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ በጣም አስከፊ የሆነ አስቸኳይ የምግብ ዋስትና እጦት ነው፡፡‘“

እ.ኤ.አ ታህሳስ 2015 የዘ-ህወሀት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የሆነው ደመቀ መኮንን አንዲህ አለ፣ “የውጭ መገናኛ ብዙሀን ልዩ ፍላጎት እና ድብቅ ዓላማ ካላቸው አካሎች ጋር በመስራት ላይ እንደሚገኝ ግልጽ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ዓይነት ረሀብ የሚባል ነገር የለም፡፡“

እ.ኤ.አ ሚያዝ 11/2016 ዩኤስኤአይዲ/USAID እንዲህ የሚል ዘገባ አቀረበ፣ “እ.ኤ.አ በ2016 ለኢትዮጵያ ለምግብ እርዳታ የሚያስፈልገው የተረጅ ህዝብ ቁጥር 10.2 ሚሊዮን እንደሚሆን ተተንብዮአል፡፡“

ያ 10.2 ሚሊዮን ተረጅ ህዝብ የሚበላው ምንም ዓይነት ነገር የለውም ማለት ነውን፣ እናም ይህ ከሆነ የእርዳታ አቅርቦቱ በወቅቱ ካልተገኘ ሁሉም በረሀብ ያልቃሉ ማለት ነውን?!

ይህ ነው እንግዲህ የዘ-ህወሀት-ዩኤስኤአይዲ/USAID አጋርነት በኢትዮጵያ ላይ እያካሄዱት ያለው ክህደት፡፡ ምንም ዓይነት ረሀብ የለም! ምንም ዓይነት ቸነፈር የለም! ምንም የሌለ ነገር የለም፡፡ ኤል ኒኖ ብቻ የድርቁ መንስኤ ነው፡፡

አምባገነኑ መለስ ዜናዊ እ.ኤ.አ በ1991 በፍጹማዊ የስልጣን ኮርቻው ላይ ተደላድሎ መቀመጡን ካረጋገጠ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰጠውን የፕሬስ መግለጫ ምንጊዜም ቢሆን አልረሳውም፡፡ አምባገነኑ መለስ እንዲህ ነበር ያለው፣ “ኢትዮጵያውያን በቀን ሶስት ጊዜ መመገብ የሚችሉ ከሆነ የእኔ መንግስት ስኬት የሚለካው በዚያ ነው፡፡“

በአሁኑ ጊዜ ከ10 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን በረሀብ በመሰቃየት ላይ ይገኛሉ፡፡

በአሁኑ  ጊዜ የዘ-ህወሀት አለቆች እና ጋሻጃግሬዎች የተቀማጠለ የድሎት ኑሮ በመኖር ላይ ይገኛሉ፡፡

በአሁኑ ጊዜ የዘ-ህወሀት መሪዎች በመስራቹ እና በባለራዕይው መሪ ታስቦ የነበረው   ስኬታማ ሆነናል ብለው ያስባሉን?

በአሁኑ ጊዜ የዘ-ህወሀት መሪዎች አሁን በህይወት ስለሌለው ባለራዕይው መሪ በቀን ሶስት ጊዜ ኢትዮጵያውያንን ስለመመገብ ወይም ደግሞ በሚሊዮኖች ስለሚቆጠሩት እና በረሀብ ስለሚሞቱት ኢትዮጵያውን ምንም የሚያስቡት ነገር የለም!

ይኸ ተጨባጭ እውነታ ነው!

ሆኖም ግን በአሁኑ ጊዜ ረሀብ በኢትዮጵያ ውስጥ አስከፊ በመሆን ላይ ይገኛል፡፡ ከዓለም ላይ የተደበቁ ሆኖም ግን ቁጥራቸው ያልተነገሩ እና በሞት እየተነጠቁ ያሉ ዜጎች አሉ፡፡

እ.ኤ.አ ሚያዝያ 12/2016 ብሉምበርግ ኒውስ የተባበሩት መንግስታትን ምንጭ ዋቢ አድርጎ በመጥቀስ እንዲህ የሚል ዘገባ አቅርቧል፣ “በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የተለዩ እና በድርቅ የተጎዱ የአስቸኳይ ጊዜ የሰብአዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ወረዳዎች በድርቁ አስከፊ እየሆነ መምጣት ምክንያት በ18 በመቶ በመጨመር ከታህሳስ እስከ መጋቢት ባለው ጊዜ ውስጥ ቁጥራቸው 216 ደርሷል፡፡

በተከታታይ በመከኑት የዝናብ ወቅቶች ምክንያት ባለፈው ዓመት በውቅያኖሶች መሞቅ በተከሰተው ኤል ኒኖ ውጤት መሰረት ከመቶ ሚሊዮን ከሚገመተው የኢትዮጵያ ሕዝብ ውስጥ አንድ አምስተኛው የምግብ እህል እርዳታ ይፈልጋል፡፡ በጠቅላላው 443 ወረዳዎች ቢያንስ የተወሰነ ችግር ያለባቸው ተብለው የተመደቡ ሲሆን ይህም ቁጥር በታህሳስ ወር ከነበረው ከ429 ተነስቶ ከዚህ ለመድረስ መቻሉን የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ እርዳታ ጽ/ቤት ማክሰኞ ባሰራጨው የኢሜል መጽሔቱ ግልጽ አድርጓል፡፡

ከእነዚህ ውስጥ 219 ወረዳዎች ውስጥ በጣም አስከፊ የምግብ ዋስትና እጦት የተከሰተባቸው እና ከፍተኛ የሆነ የሞት መጠንን የሚያካትቱ፣ ከፍተኛ የሆነ እና እየጨመረ የመጣ የአልሚ ምግብ ንጥረ ነገር እጥረት፣ ሊመለስ የማይችል እና የወደመ የኑሮ ዋስትና ቋሚ ሀብቶች ተብለው ተመድበዋል፡፡ በኢትዮጵያ መንግስት ምደባ መሰረት ኢትዮጵያ በጠቅላላው 800 አካባቢዎችን ወይም ወረዳዎችን ትይዛለች፡፡“ አጽንኦ ተጨምሯል፡፡)

በጣም አስከፊ የምግብ ዋስትና እጦት የሚለው እንደምታውቁት ሌላ ምንም ሳይሆን በአጭሩ ለእኔ ረሀብ ማለት ነው፡፡

ከአስከፊ የምግብ ዋስትና እጦት በላይ ሌላ ምን የከፋ ነገር ሊኖር ይችላል?

በጣም፣ በጣም፣ በጣም፣ በጣም… አስከፈፊ የምግብ ዋስትና እጦት?

አስከፊ የሆነ የሆነ የምግብ ዋስትና እጦት መኖር ከፍተኛ ሞትን ሊያስከትል ይችላል፡፡ ረሀብን ለመጥራት ቆንጆው ስያሜ እንግዲህ ይህ ነው (ወይስ ደግሞ ድርቅ ነው?) በርካታ ኢትዮጵያውያንን የሚጨርሰው?

ጆርጅ ኦርዌል በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ነበር፣ “የፖለቲካ ቋንቋ የተፈጠረው ውሸትን በመፈብረክ እውነት ለማስመሰል እና የተከበረውን ነገር ለመግደል እና ንጹህ ጋስ የሆነውን ነፋስ የጠጣርነት ቅርጽ ያለው  አስመስሎ ለማቅረብ ነው፡፡“

ዩኤስኤአይዲ/USAID፣ ዘ-ህወሀት እና የተባበሩት መንግስታት እ.ኤ.አ በ2016 በተከሰተው ረሀብ 10 ሚሊዮን ኢትዮጵያውን ከሰዓት በኋላ ሊቀርብ የሚችለውን መክሰሳቸውን ብቻ እንዳጡ አድርገው የቃላት ትርጉም ስንጠቃ የጅምናስቲክ ጨዋታቸው ላይ ተጠምደው ይገኛሉ፡፡

ለምንድን ነው ዩኤስኤአይዲ/USAID፣ የተባበሩት መንግስታት እና ሌሎችም በኢትዮጵያ ላይ ስለሚከሰተው ረሀብ እስከጥርሳቸው ድረስ የሚዋሹት?

እኮ ለምን?

እ.ኤ.አ ግንቦት 2012 “የአፍሪካ የረሀብ ጨዋታዎች በካምፕ ዴቪድ የሽርሽር ቦታ“ በሚል ርዕስ አንድ ትችት ጽፌ ነበር፡፡ በዚያ ትችቴ ላይ አምባገነኑ መለስ ዜናዊ እና የእርሱ ዓለም አቀፍ ደጋፊዎች እና ዓለም አቀፍ የደህነት ወትዋች አቃጣሪዎች በኢትዮጵያ ሕዝብ ረሀብ እና ቸነፈር ላይ የሕዝብ ግንኙነት ስራ  እና የቃላት ትርጉም ስንጠቃ እየተጫወቱ በመሆናቸው የተሰማኝን ቅሬታ ግልጽ አድርጌ ነበር፡፡

አሁን እውነታውን ወገግ ብሎ አገኘሁት!

ከ10 – 11 በመቶ አማካይ ዓመታዊ የኢኮኖሚ ዕድገት አስመዝግቢያለሁ እያለ ላለፉት አስር ዓመታት በሸፍጥ አባዜ ተወጥሮ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ሲያራግብ የቆየ አገዛዝ በሀገሪቱ ውስጥ አስከፊ ረሀብ መኖሩን ማመኑ እጅግ በጣም አሳፋሪ ነገር ው፡፡

ዩኤስኤአይዲ/USAID እና ዓለም አቀፍ አጋሮቻቸው “F“ amine ረ-ሃ-ብ የምትለዋን ቃል መጠቀም ሲጀምሩ የዩኤስ አሜሪካ ኮንግረስ ስለመነሻው እና ውጤቱ መስማት አለበት፡፡ ይህም ማለት ዩኤስኤአይዲ/USAID ለተጠያቂነት ብቁ ሆነ ማለት ነው፡፡

የዓለም አቀፍ ፕሬስ ተደራሽነት እና ተጠያቂነት እንዲኖር መጠየቅ አለበት፣ እናም ሁሉም የገሀነም አሰራር ይወገዳል፡፡

ማርቲን ፕላውት አሁን በቅርብ ጊዜ በኒውስ ሰቴትስማን በወጣው ጽሑፍ እንዲህ በማለት ተሟግተዋል፣ “እ.ኤ.አ. በ1973 – 74 እና በ1984 – 85 ተከስተው በነበሩት የኢትዮጵያ አውዳሚ ረሀቦች በመቶዎች እና በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወት የተቀጠፈ ሲሆን ምናልባትም እንደየአግባቡ 200 መቶ ሺ እና 400 መቶ ሺ ሰዎች አልቀዋል፡፡ የመጀመሪያው ረሀብ አጼ ኃይለ ስላሤን ከስልጣናቸው እንዲወገዱ ሲያደርግ ሁለተኛው ረሀብ ደግሞ ለመንግስቱ ኃይለማርም ማርክሲስታዊ አገዛዝ ውድቀት የእራሱን ድርሻ አበርክቷል፡፡“

ዘ-ህወሀት በአሁኑ ጊዜ ያለውን ረሀብ ስፋት እና ጥልቀት የኢትዮጵያ ሕዝብ መርምሮ በሚደርስበት ጊዜ ወያኔም እንዳለፉት የኢትዮጵያ መንግስታት እንደደረሰው ዕጣ ፋንታ እንደሚደርሰው ዘ-ህወሀት ሊያውቀው ይገባል፡፡

ለዚህም ነው “F“ amine ረ-ሃ-ብ የሚለው ቃል በሚሰማበት ጊዜ ለመከላከል ሲሉ ዩኤስኤአይዲ/USAID እና ዘ-ህወሀት በደመ ነብስ ምላሽ እየሰጡ ያሉት፡፡ የዓለም አቀፍ ፕሬስ በሀገሪቱ ውስጥ ስላለው የምግብ ሁኔታ እውነተኛ መረጃ ለማግኘት ጥረት በሚያደርግበት ጊዜ የዘ-ህወሀት ሎሌዎች እጅግ በጣም በመቆጣት የዓለም አቀፉን ፕሬስ መግለጫ መሰረተቢስ እና የሀገሪቱን ገጽታ ጥላሸት ለመቀባት የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ናቸው በማለት ዓለም አቀፉን ፕሬስ በማውገዝ ላይ ይገኛሉ፡፡

የዩኤስኤአይዲ/USAID ቸነፈር/ረሀብ/ድርቅ የትርጉም ጨዋታዎች፣

 ዘ-ህወሀትን ከማንኛውም የሕግ፣ የሞራል እና የፖለቲካ ኃላፊነት ተጠያቂነት ለመከላከል እና ለመጠበቅ ሲል በኢትዮጵያ እየተስፋፋ ስለመለጣው ድርቅ/ረሀብ ዘገምተኛ የመሆን እና ምንም ዓይነት አፋጣኝ ምላሽ ያለመስጠት ሁኔታ የዩኤስኤአይድ/USAID መልዕክት እና የመነጋገሪያ ነጥቦች በጥንቃቄ የተሰሉ ናቸው፡፡

ዩኤስኤአይድ/USAID እና ሌሎች ዓለም አቀፍ አጋሮች ስለረሀብ ጉዳይ በግልጽ የመወያየት ጉዳይ ስለሚያስከትለው ውጤት በሚገባ ያውቃሉ፡፡

ሆኖም ግን ዩኤስኤአይድ/USAID ሁለት ቀላል የሆኑ እውነታዎችን ማወቅ ይገባዋል፡፡ እነርሱም፡

1ኛ) እነርሱ እንደሚያስቡት ሁሉ ኢትዮጵያውያን ደደቦች አይደሉም፡፡ ቀጥ ብላችሁ በመቆም በዘ-ህወሀት አምባገነናዊ አገዛዝ ሕወይታችሁ ዴሞክራሲያዊ ነው በማለት ልትነግሯቸው ትችላላችሁ፡፡ ሆኖም ግን እንደ ድንጋይ ዝም በማለታቸው እንደ ድድብና የሚቆጠር ነው ብላችሁ ስህተት አትስሩ፡፡ የማሰብ ደረጃቸውን አትሳደቡ፡፡ ረሀብተኛ እና ደኃ መሆን ከድድብና እና ከድንቁርና ጋር እኩል ነው ብላችሁ አትቁጠሩ፡፡ 

2ኛ) ጽጌረዳ በሌላ በማንኛውም ስም ብትጠራ ያው ጣፋጭ የሆነ ሽታዋን አይለውጥም፡፡ ሆኖም ግን ረሀብ በሌላ በማናቸውም ስያሜ ቢሰየም (በጣም አስከፊ የአልሚ ምግብ ንጥረ ነገር እጥረት ኤል ኒኖ አመጣሽ ድርቅ ወዘተ የጭቆና አገዛዝ መራራ ፍሬ ውጤት ነው፡፡

የዩኤስኤአይድ/USAID የእርሱን ዘ-ህወሀት አጋሮች ለመከላከል፣ ለመሸፈን እና ለእነርሱ ሲሉ ውሸት ለመዋሸት እና ሌላም የፈለጉትን ነገር ሁሉ ለማድረግ ነጻ ነው፡፡ ኤሚሌ ዞላ በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ነበር፣ “እውነትን በቀበርካት ቁጥር እና በጣም አርቀህ ወደ መሬት ውስጥ በቀበርካት ቁጥር ትበቅላለች፡፡“

ህይወትን የሚያቆዩ ዘሮች በኢትዮጵያ ውስጥ አይበቅሉም ሆኖም ግን ስለዘ-ህወሀት እና የዩኤስኤአይድ/USAID እንደ አረሞች የሚበቅሉ የጫካ እውነታዎች አሉ፡፡

የዩኤስኤአይድ/USAID ስለመልም አስተዳደር ውድቀት፣ ድረሀብ/ድርቅን በበቂ ሁኔታ አቅዶ ለማስወገድ ስላልቻለበት ሁኔታ አንድም ነገር (አንድ) መጥቀስ ያለመቻሉ ምን ዓይነት አሳፋሪ ነገር ነው? 

የዩኤስኤአይድ/USAID 50 ዓመታት ድርቅ አንድም ሰው መሞቱን (አንድምም ሰው) መግለጽ ያለመቻሉ እንዴት ያለ አሳፋሪ ነገር ነው!!!

ዩኤስኤአይድ/USAID ባዶ ፕሮፓጋንዳ እየነዛ የህልም እንጀራ በመመገብ የኢትዮጵያን ሕዝብ እንዳታለለ አድርጎ ያስባል፡፡

“ለተባበሩት መንግስታት እና መንግስታዊ ላልሆኑ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች አጋሮቻችን በእርግጠኝነት ለዚህ ድርቅ ምላሽ በመስጠት ታላቅ እና የጀግንነት ስራን የሰሩ ስለሆነ ምስጋና ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡“

ይኸ ድርቅ ያለምንም ጥያቄ አደገኛ ነው፡፡ የግድ ግን አውዳሚ አይደለም፡፡

በአጠቃላይ መልኩ በድርቁ ምክንያት አስከፊ እና አውዳሚ የሆነ ውጤት መከሰቱን ሊያረጋግጥ የሚችል ነገር አላየንም፡፡

ይህንን ድርቅ ለመቋቋም በኢትዮጵያ መንግስት በጣም ግልጽ የሆነ አመራር አይተናል፡፡ አጠቃላይ በሆነ መልኩ ጠንካራ የፖለቲካ ፈቃደኝነት፣ ጠንካራ ቁርጠኝነት ስላለ ይህ ድርቅ አውዳሚ ሊሆን እንደማይችል ማረጋገጫ አይቻለሁ፡፡

በአሁኑ ጊዜ ከ30 ዓመታት በፊት የሌለን አቅም እና ባለሙያነት ስላለን እ.ኤ.አ በ2016 ድርቁን ማሸነፍ እንችላለን፡፡ በአሁኑ ጊዜ ከዚህ ቀደም የሌሉን ቴክኒኮች እና ቴክኖሎጂዎች አሉን፡፡ ልዩ የሆኑ የምግብ ውጤቶች አሉን፡፡

ከመንግስት ጎን በመሰለፍ እንሰራለን፡፡ መንግስት በከፍተኛ እርምጃ ወደፊት ተራምዷል፡፡ ስለሆነም በርካታ የተሰሩ ነገሮቸ አሉ፣ በርካታ ስኬታማ የሆነ ነገሮች አሉ፡፡ ሌሎች በስርዓቱ ውስጥ ያሉ በርካታ ነገሮች አሉ፡፡

የዩኤስኤአይዲ/USAID የውጭ አደጋ ረዳት ጽ/ቤት በኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተው ድርቅ ወደ ሙሉ ሰብአዊ ቀውስ ከመቀየሩ በፊት እርዳታውን በማቀላጠፍ የሚያግዝ ቡድን አሰማርቷል፡፡ (ሙሉ ሰብአዊ ቀውስ “ረሀብ” ነውን?!

ዩኤስኤአይዲ/USAID ረሀብ የምትለዋን ቃል የማይተቀምባት ለምንድን ነው? እ.ኤ.አ. 2016 በኢትዮጵያ  ድርቁ ወደ ሙሉ ሰብአዊ ቀውስ ሊቀየር ይችላል፡፡

ዩኤስኤአይዲ/USAID ከስሸዋለሁ!

በኢትዮጵያ ውስጥ ድርቅን ለመከላክል እና ለመቋቋም ዩኤስኤአይዲ/USAID እያራመደው ያለው አቀራረብ ምጽዋት እና የበለጠ ምጽዋት መስጠትን ነው፡፡

የህንድ የኢኮኖሚክስ የኖቬል ተሸላሚ የሆኑት አማርትያ ሴን ረሀብን ለማጥፋት ዋናው መንገድ ዴሞክራሲን ተቋማዊ ማድረግ እና የሰብአዊ መብቶችን ጥበቃ ማጠናከር ነው፡ በዓለም ታሪክ ውስጥ በመስራት ላይ ባለ የዴሞክራሲ ስርዓት ውስጥ ምንም ዓይነት ረሀብ ተከስቶ አያውቅም፣ ምክንያቱም ዴሞክራሲያዊ መንግስታት ምርጫን አሸንፈው ስለሚይዙ እና የህዝብን ትችትም ስለሚቀበሉ እንዲሁም ረሀብን እና ሌሎች መቅሰፍቶን ለማጥፋት የሚያበረታቱ ጠንካራ እርምጃዎችን ስለሚወስዱ ነው፡፡ ዴሞክራሲያዊ ባልሆኑ ሀገሮች ግን በሚከሰተው ረሀብ ላይ የማስጠንቀቂያ ደወል የሚያሰሙትን የተቃዋሚ መሪዎችን፣ ጋዜጠኞችን እና የሲቪክ ማህበረሰብ ወትዋቾችን በማሰር ረሀብ ድብቅ ሆኖ እንዲቀር ይደረጋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሁኔታ በእርግጠኝነት ይኸ ነው!

ባለፈው ሀምሌ ባራክ ኦባማ በአዲስ አበባ ቆሞ ዘ-ህወሀት ዴሞክራሲያዊ መንግስት ነው ብሎ አወጀ፡፡ ሆኖም ግን በመከላከሉ ደረጃ “የሚሰራ” ዴሞክራሲ ነው አላለም፡፡

የማይሰራ ዴሞክራሲ ወሮበላ የዘራፊነት አገዛዝ ነው፡፡ (እንግዲህ ዴሞክራሲን ወደወሮበላነት ዴሞክራሲ ስትቀይረው ወይም ደግሞ ወሮበሎች ዴሞክራሲን ሲጠልፉ የምታገኘው የማይሰራ የወሮበላ አገዛዝ ዴሞክራንሲን ነው፡፡)

ዘ-ህወሀት ወሮበላ የዘራፊ አገዛዝ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ስላለው ረሀብ እውነታ አንዳንድ ጊዜ ታማኝ በሆኑ ዓለም አቀፍ ለጋሽ እና አበዳሪ ድርጅቶች ይነገራል፡፡

እ.ኤ.አ በ2011 የዓለም ባንክ ዋና ኢኮኖኖሚስት የሆኑት ወልፍጋንግ ፌንግለር እንደ የዓለም ባንክ ባለሙያነት ታማኝነትን ባገናዘበ አጋጣሚ እንዲህ ብለው ነበር፣ “በአፍሪካ ቀንድ ሀገሮች ያለው ረሀብ ከተፈጥሮ እና ከአካባቢያዊ ምክንያቶች የበለጠ በሰው ሰራሽነት እያሻቀበ በመጣው የምግብ ዋጋ ንረት እና በሲቪል ግጭቶች አማካይነት የሚከሰት ነው፡፡ ይህ ቀውስ ሰው ሰራሽ ነው፡፡ ድርቆች ደግመው እና ደጋግመው ይከሰታሉ፣ ሆኖም ግን ወደ ረሀብነት እንዲቀየሩ ዋናው መንስኤ መጥፎ ፖሊሲን አውጥቶ ተግባራዊ የማድረጉ ሁኔታ ነው፡፡“ (አጽንኦ ተጨምሯል፡፡)

በሌላ አባባል በኢትዮጵያ ውስጥ የረሀብ ዋናው መንስኤ መጥፎ እና ደካማ አስተዳደር እንጅ ድርቅ፣ ኤል ኒኖ ወይም ኤል ኒና አይደለም፡፡

የኦክስፋም ዓለም አቀፍ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ፔኒ ላውሬንስ ኢትዮጵያን ከጎበኙ በኋላ የሚከተለውን ምልከታ አስቀምጠዋል፡

“ድርቅ ማለት ረሀብ ወይም ፍጹም የሆነ እጦት ማለት አይደለም፡፡ ማህበረሰቦች ለሰብሎች የመስኖ ውኃ የሚኖራቸው ከሆነ፣ የእህል ማጠራቀሚያ ጎተራ እና የዝናብ ውኃን ለመሰብሰብ የሚያስችል ጉድጓድ የሚኖራቸው ከሆነ በእነርሱ ላይ ምንም ዓይነት አደጋ ወደ እነርሱ ቢወረወርም ያለምንም ችግር መኖር ይችላሉ፡፡“

የቢቢሲ ዓለም አቀፍ ዜና አገልግሎት የአፍሪካ አርታኢ/editor የሆኑት ማርቲን ፕላውት በኢትዮጵያ ውስጥ ላለው ቀውስ ከፊል መንስኤው ገበሬዎችን የመንግስት በሆነው መሬት ላይ አስሮ በማስቀመጥ እና የግላቸው መሬት ኖሯቸው ለመሸጥ ለመለወጥ እንዳይችሉ ቀፍድዶ በያዛቸው ፖሊሲ ምክንያት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ስለሆነም ግልጽ የሆኑት ጥያቄዎች እንዲህ የሚሉ ይሆናሉ፡

1ኛ) ህብረተሰባዊነትን አሽቀንጥሮ የጣለ እና ምናልባትም ለነጻ ገበያ የኢኮኖሚ ስርዓት እራሱን ተገዥ ያደረገ አገዛዝ መሬትን ሙሉ በሙሉ በእራሱ ቁጥጥር ስር የሚያደርገው ለምንድን ነው?

2ኛ) በሀገሪቱ ውስጥ በቂ የሆኑ የምግብ ሰብሎችን ማምረት የሚያስችሉ የመስኖ፣ የእህል ማጠራቀሚያ ጎተራ እና የዝናብ ውኃ መሰብሰቢያ የጉድጓ ስርዓቶች የማይኖሩት ለምንድን ነው?

3ኛ) ስለኢትዮጵያ ዘ-ህወሀት ያለው የምግብ ዋስትና ፖሊሲ ምንድን ነው?

4ኛ) አሁን በህይወት የሌለው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ እ.ኤ.አ በ2015 ኢትዮጵያ የምግብ እርዳታ አትፈልግም ብሎ ነበር፡፡ ይኸ ነገር የዘ-ህወሀት ፖሊሲ ነውን?

እ.ኤ.አ በ1992 ባቀረቡት ጽሁፍ ፕሮፌሰር ኤድሞንድ ጀ.ክለር እንዲህ በማለት ሞግተው ነበር፡

“ እ.ኤ.አ የ1983 – 86 ተከስቶ የነበረው ታላቅ ረሀብ በደርግ ደካማ ፖሊሲዎች የተባባበሰ ነበር፡፡ የአየር ንብረት ለውጦች በከመሰታቸው ምክንያት፣ በዚያን ጊዜ የነበረው ድርቅ ትልቅ ነበር፡፡ ሆኖም ግን በማንኛውም ረገድ ቢሆን የድርቁ ውጤቶች ውጤታማ በሆኑ የፖሊሲ መሳሪያዎች እና በውጭ የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታን በመጠቀም መወገድ ይችሉ ነበር፡፡ ነገር ግን የኢትዮጵያው የደርግ አገዛዝ ለጉዳዩ የበለጠ የፖለቲካ አጀንዳን ለማራመድ ፍላጎት አሳየ፣ ተገቢ ስልቶችን በመንደፍ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ይልቅ አሀዛዊ መረጃዎች እንዳይወጡ መቆጣጠር ጀመረ፡፡“

በአሁኑ ጊዜ ዘ-ህወሀት የበለጠ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ያለው ለፖለቲካ አጀንዳው የመሬት ባለቤትነትን በማረጋገጥ የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ስልትን ከመጠቀም ይልቅ  መሬትን በሙሉ በእራሱ ቁጥጥር ስር አድርጎ የመሬት ቅርምትን በመፈጸም እና አሃዛዊ መረጃዎችን በመቆጣጠር ስራ ላይ ተጠምዶ ይገኛል፡፡

ዩኤስኤአይዲ/USAID በኤል ኒኖ እያሳበበ በኢትዮጵያ ውስጥ ለተከሰተው ድርቅ ኤል ህወሀትን ተጠያቂ ከመሆን በፍጹም ሊያድነው አይችልም፡፡ 

ዩኤስኤአይዲ/USAID ከስሸዋለሁ! 

ዩኤስኤአይዲ/USAID! የኢትዮጵያ ሕዝቦች በረሀብ ሲሰቃዩ በመመልከት የማሰብ ደረጃቸውን አትዘልፍ፡፡

ዩኤስኤአይዲ/USAID ሁሉንም መምሰል አለበት!

አንድ ነፍሳት ዳኪዬ  ከመሰለ አንዴ ዳክየ  ከጮሕ  እንደ ዳክየ  ከተራመደ  ዳክየ መሆን አለበት!

ድርቅ ረሃብን ከመሰለ፣ አንደ ረሃብ ካንገበገ  አንደ  ረሃብ ከገደለ ረሀብ መሆን አለበት!

የዩኤስኤአይዲ/USAID  ይህን እንደ ሃስብ ምግብ ይውሰደው ፡፡

ለዩኤስኤአይዲ/USAID ሊቃወመው የማይችል አንድ የስመምነት ሃሳብ አቀርብለታለሁ ፡

የዩኤስኤአይዲ/USAID በኢትዮጵያ ውስጥ ረሀብ የለም የሚለውን ውሸት መናገሩን የሚያቆም ከሆነ እኔም የዩኤስኤአይዲ/USAIDን ኤል ኒኖ እና አስከፊ የአልሚ ምግብ ንጥረ ነገር እጥረት የሚለውን ቅጥፈቱን በማጋለጥ መናገሬን አቆማለሁ፡፡

እሺ እንስማማለን ዩኤስኤአይዲ/?!

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!  

ሚያዝያ 11 ቀን 2008 .

 

 

 

Similar Posts