Voice of America (Amharic) Interview 3/15/19 (T-TPLF “Apology”)
የሰብ ሰሃራ አፍሪካም ፈላጭ ቆራጮች ሲንሸረተቱና መቀመጫቸውን ሲለቁ ታይተዋል፡፡ኮተ ዲቩዋሩም ሎራንት ባግቦ ከመኮፈሻው የሽቅርቅር ነጭ ኮሊታው ሸሚዙ ተለያይቶ በቤተመንግሥቱ ከተወሸቀበት ጓዳው ተይዞ በፈጸመው የሰብአዊ መብት ጥሰትና ግድያ ለፍርድ ለዓለም የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ተላልፏል፡፡ የኒጀሩ ማማዱ ታንጃ ሕገመንግሥታዊ የስልጣን ገደብን በመጣስ በሥልጣን ላይ ለመቆየት ቢፍጨረጨርም የኒጀር ጦር አሽቀንጥሮ አውርዶታል፡፡የማማዱ ታንጃም ቀንደኛ ተወዳዳ በሕዝባዊ ምርጫ ሥልጣኑን ተረከበ፡፡በቅርቡም፤የሴኔጋሉ መሪ የ85 ዓመቱ አብዱላዬ ዋዴ የሶስተኛ ጊዜ ምርጫ ለማድረግ ለማጭበርበር ሲያቅድ ሕዝባዊ ዐመጽ ተቀጣጥሎበት ምርጫ እንዲካሄድ ሲደረግ አብዱላዬ ዋዴም ለመወዳደር ሞክሮ በቂ ወንበር ሳያገኝ በመቅረቱ በዘዴ ስልጣን ለመያዝ በመንቆራጠጥ ላይ ቢሆንም አሸነፈ ቢባልም ከፍተኛ ሕዝባዊ ተቃውሞ እንዲያጋጥመው አያጠራጥርም፡፡
በምስራቅ ገሰሰ በአሁኑ ጊዜ ይህንን ደብዳቤ እየጻፍኩ ያለሁት ለጡት ካንሰር በሽታ ምርመራ አስፈላጊ የሆኑትን የኤክስ ሬይ/X-Ray እና የአልትራ ሳውንድ/Ultrasound ዓመታዊ ምርመራዬን እንዳጠናቀቅሁ ነው፡፡ ከአምስት ዓመታት በፊት ልክ እ.ኤ.አ መስከረም 25/2010 የጡት ካንሰር ምርመራዬን ካጠናቀቅሁ በኋላ ለኢትዮጵያውያት እህቶቼ ይጠቅማል በሚል እሳቤ ከዚህ ጋር በተያያዘ መልኩ ያለኝን ልምድ እና ተሞክሮ ያካተተ ጽሑፍ አዘጋጅቼ ነበር፡፡ (ያንን ጽሑፍ በእንግሊዘኛ ለማንበብ እባክዎትን…
ፔይን ለአፍሪካ የነበራቸው ያልተቆጠበ ጥረት ታሪካዊና የማይዘነጋ ነው፡፡በ2008 በርካታው መጠን ለአፍሪካ በዓመስት ዓመታት ሂደት በተግባር ላይ የሚወጣውን የ 48 ቢሊዮን ዶላር የድጋፍ ችሮታ(ለኤይድስ መቆጣጠርያ) ኮንግሬስ እንዲፈቅድ በቀረበበት ወቅት ፔይን ከፍተኛ ሚና ተጫውተው እንዲፈቀድ አድርገዋል፡፡በዳርፉር በሰብአዊ መብት ረገጣና ዘር በማጥፋት ላይ የተሰማሩትን ተጠያቂዎች አስመልክቶ በሱዳን ላይ የተጣለው እቀባ እንዲወሰንም ያደረጉት ጥረትና ተሳትፎ ቀላል አልነበረም፡፡ በሱዳን የተደረሰውን የሰላም ስምምነትም እንዲሰምርና በሁለቱም ወገኖችና በዓለም አቀፍ ደረጃም ተቀባይነት እንዲኖረው ከማድረግም ባሻገር ደቡብ ሱዳንም እራሱን መንግሥት ለመሆን የበቃበትን ሂደት በመምራት ውጤታማ ያደረጉ ናቸው፡፡
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ ባለፈው ሳምንት የዓለም አቀፍ ወንዞችን እና ለሶስት አስርት ዓመታት በእነርሱ ላይ ህልውናቸውን መስርተው የሚኖሩ ህዝቦችን መብት ለማስጠበቅ በግንባርቀደምነት በሚታገለው ዓለም አቀፍ ድርጅት ኢንተርናሽናል ሪቨርስ (የዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ) ላይ የኢትዮጵያ ገዥ አካል ለእራሱ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ የማስመሰል ብስጭትና ቁጣን በማሳየት እርምጃዎችን ለመውሰድ የኢትዮጵያ አዋቂ ነን የሚሉ ስማቸው ያልታወቀ ባለሙያዎችን…
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ ባለፈው ሐምሌ ባራክ ኦባማ ኢትዮጵያን ጎበኘ እና የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስበ (ዘ–ህወሀት) አገዛዝ “ዴሞክራሲያዊ መንግስት” ነው በማለት አወጀ፡፡ ዘ-ህወሀት ዓይኑን በጨው ታጥቦ ተካሂዶ የነበረውን የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ መቶ በመቶ ወይም ደግሞ ሁሉንም 547 የፓርላማ መቀመጫዎች ያሸነፈ መሆኑን አይን ባወጣ ዉሸት ባለፈው ግንቦት ገለጸ፡፡ የኒዮርክ ታይምስ መጽሔት ይህንን ጉዳይ በማስመልከት…
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ እ.ኤ.አ በጃንዋሪ 2013 “እ.ኤ.አ 2013 የኢትዮጵያ የአቦሸማኔው ትውልድ ዓመት ይሆናል“ በማለት ትንበያ ሰጥቸ ነበር፡፡ እንዲህ ስልም ቃል ገብቸ ነበር፣ “የኢትዮጵያ ወጣቶች ለፍትህና ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የሚያደርጉትን ትግል ለመደገፍ እና ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ እንዲል የእራሴን ሙሉ አስተዋጽኦ እንደማደርግ እንዲሁም ትግሉ ወደ አዲስ ምዕራፍ እንዲሸጋገር ወጣቱ ትውልድ እንዲነሳሳ ሳደፋፍር ነበር፡፡”…