በኢትዮጵያ “የዘ-ህወሀት ታሪክ ፍጻሜ” መቃረቡ ነውን?

  ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

 ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

End of story T-TPLFየዘራፊ ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ (ዘ-ህወሀት) የሙት ዓመት ታሪክ ቀደም ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር በነበረው እና አሁን በህይወት የሌለው የዘ-ህወሀት አድራጊ ፈጣሪ ጭንቅላት የነበረው ወንጀለኛው መለስ ዜናዊ እና ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) እየተባለ የሚጠራው እና በዘ-ህወሀት የሚዘወረው አስመሳይ ድርጅት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የኢህአዴግ ምክትል ሊቀ መንበር አዲሱ ለገሰ ጓደኛ በሆነው በበረከት ስምኦን ባለፈው ዓመት ተጽፏል፡፡

በአንድ በሚስጥር ተመዝግቦ በተያዘ ውይይት በረከት እና አዲሱ ግልጽ በሆነ መልኩ ለቡድን ደጋፊዎቻቸው በኢትዮጵያ የዘ-ህወሀት ጊዜው እያለቀ መሆኑን፣ የመጨረሻዎቹ ቀናት እየደረሱ እና ቀኑ እያለቀበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አዲሱ እንዲህ በማለት ተናግሯል፡

“አሁን ካለንበት ነባራዊ ሁኔታ አንጻር ስንመለከተው ነገሮች ሁሉ ከእጆቻችን እየወጡ ነው፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ምንም ዓይነት ጥያቄ የሚያስነሳ አይደለም፡፡ ይህንንም የመምህራን ድርጀቶች ምን እየሰሩ እንዳሉ በግልጽ ልንመለከት እንችላለን፡፡ ሁለት ሶስተኛ የሚሆነው የትምህርት ሰው የእኛ ፓርቲ አባል ቢሆንም ከዚህ በተጻረረ መልኩ እኛን በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ላይ የሚገኙ ሲሆን ይህም የታሪኩን ፍጻሜ ያመላክታል፡፡ አረና ፓርቲ ብቻ ነው ብዬ አላስብም፡፡ ግንቦት ሰባትም አብሮ አለ፡፡ በባህርዳ ከተማ ውስጥ ጸረ ህወሀት የሆኑ በራሪ ወረቀቶች ተበትነዋል፡፡ በስብሰባው የነበሩ ተሳታፊዎች በዚህ ጉዳይ ላይ ስምምነት ያላቸው መሆናቸውን በምላሻቸው ግልጽ አድርገዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ወረቀቶች በባህራዳር ውስጥ ተሰራጭተዋል፡፡ ሆኖም ግን ምን ለማለት እንደፈለግሁ የምታውቅ ከሆነ ይህንን ነገር አናውቅም፡፡ በራሪ ጽሁፎች በመበተን ላይ መሆናቸው በተጨባጭ ታይተዋል፡፡ ስለሆነም ይኸ ጉዳይ በየቦታው በሴል ደረጃ እየወረደ በመተግበር ላይ እንዳለ አስባለሁ፡፡ እራሱን በማደራጀት ላይ ያለ አንድ ነገር ያለ ይመስላል፡፡ ስለሆነም ይኸ ነገር ከግንቦት ሰባት የሚመጣ ይመስለኛል፡፡ (አጽንኦ ተሰጥቷል፡፡)“

በረከት የዘ-ህወሀት ቀን እያለቀ መሆኑን አሁን እየተመለከተው ያለው ምልክት ለዚህ ማሳይ ምሳሌ እንደሆነ አምናለሁ በማለት እንዲህ የሚል ምላሽ ሰጥቷል፡

“ስብሰባ ነበር፡፡ በዚያ ስብሰባ ላይ በመገኘት ተገኝቼ ነበር፡፡ ቁርስ በመብላት ላይ ነበርኩ፡፡ ሁለት ሰዎች ከመጡ በኋላ ከእኔ ጋር ማውራት ጀመሩ፡፡ ከእኔ ጋር ሲነጋገሩ በነበሩበት ጊዜ ሀሳቦቻቸውን በእኔ ላይ ለመጫን ጥረት ሲያደርጉ ነበር፡፡ ነገረ ሁኔታቸው ሁሉ አላስደሰተኝም ነበር (ምቾት አልሰጠኝም)፡፡ ይህንን ጉዳይ ስመረምረው እነዚህ ሰዎች ከከተማው የመሬት አቅርቦት የመጀመሪያዎቹ ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡ የመጀመሪያዎቹ! እነዚህ ሰዎች ግራ እና ቀኝ በማለት እያታለሉ ከሚገባው በላይ መሬትን ተቆጣጥረው ይገኛሉ፡፡ ሆኖም ግን የእኛን ጓደኞቹ ለመክሰስ ድፍረቱ ነበራቸው፡፡ ክስ ለመመስረት ዝግጅት እያደረጉ ነበር፡፡ ይህንን አደረጉ፣ ያንን አደረጉ፡፡ ስለሆነም ይህንን ነገር ስትመለከቱት ስለምንድን ጉዳይ ነው በመነጋገር ላይ ያሉት? በትክክል ለመነጋገር እኔ ስለዚያ ጉዳይ በጣም በተሻለ መልኩ ምላሽ ለመስጠት ጥረት እንደማደርግ አስብ ነበር፡፡ ይህንን ነገር ማንም ሊቀበለው የማይችል ክስ ነው፡፡ ሆኖም ግን ሊታመን የሚችለው ነገር ለእኔ ማንም ቢሆን አንድ ነገር ለማለት ድፍረቱ ያለው እንደዚህ ያሉት ግለሰቦች በከተማዋ ውስጥ ታላቅ ቀውስ ሊፈጥሩ እንደሚችሉ መመልከት ይቻላል፡፡ ስለሆነም ፕሮፓጋንዳ በማስፋፋት ላይ የሚገኙት እና እንደዚህ ያለ ነገር የሚሰሩ ሰዎች ተለይተው መውጣት አለባቸው፡፡ እናም ማግለል አለብን፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ከብዙ ጊዜ ጀምረው የእኛ ጓደኞች ሆነው የቆዩት እንዲህ በማለት በሚያስደንቅ ሁኔታ እና በማሾፍ በመናገር ላይ ይገኛሉ፡፡ ኦ! አትጨነቁ፡፡ የምርጫው ወቅት ሲደርስ እንተያያለን እና የመሳሰሉትን በመናገር ላይ ይገኛሉ፡፡ እንደዚህ ያሉ ንግግሮች ደስ አያሰኙህም…(አጽንኦ ተጨምሯል፡፡)“

በረከት፣ አዲሱ እና የዘ-ህወሀት ኩባንያ በእርግጠኝነት ምንድን በማለት ላይ ነው የሚገኙት?

አንደኛ፡ ሁለቱ የዘ-ህወሀት ተልዕኮ አስፈጻሚዎች የዘ-ህወሀት ቀን መጠናቀቂያው እቀረበ መሆኑን በመፍራት ላይ ይገኛሉ፡፡ ግልጽ በሆነ መልኩ እንዲህ ብለዋል፣ “የዘ-ህወሀት የመጨረሻው ጊዜ ነው፡፡“

በረከት፣ አዲሱ እና የዘ-ህወሀት ኩባንያ የታሪኩ መጨረሻ መሆኑን ያውቃሉ፣ ምክንያቱም በስልጣን ርካብ ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው ለመቆየት ያለ የሌላቸውን ማስመሰያ እና ማታለያ መንገዶችን ሁሉ ከመጠቀም ወደ ኋላ አይሉም፡፡

ለ24 ዓመታት ያህል ዘ-ህወሀት የከፋፍለህ ግዛ ጨዋታቸውን በመተግበር የጎሳ እና የኃይማኖት ጽንፈኝነት የጥላቻ ተግባራትን ሲያራምዱ ቆይተዋል፡፡ ጥላቻ ዒላማውን እንደሳተ ሚሳየል ተመልሶ መጥቶ የጥላቻ ፈልፋዩን ጭንቅላት የሚበረቅስ መሳሪያ ነው በማለት አንድ ሰው ተናግሮ ነበር፡፡ ደህና ዘ-ህወሀት ለ24 ዓመታት ያህል ኢትዮጵያን የጥላቻ ሀገር እንድትሆን ዒላማ አድርጎ ሲሰራ የቆየውን እንጠላለን፡፡ የዘ-ህወሀት ጥላቻ የፈጠረው ጥላቻ በአሁኑ ጊዜ የዘ-ህወሀትን ጭንቅላት የሚበረቅስ መዶሻ ፈጥሯል፡፡

ለ24 ዓመታት ዘ-ህወሀት የጎሳ ፌዴራሊዝምን ጨዋታ ሲጫወቱ እና ሁሉም መሬት የመንግስት ነው በማለት አውጀው ሲዘርፉ እና የመሬት ቅርምት ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡

ሆኖም ግን መንግስቱ የማን ነው?

ዘ-ህወሀት እና ዓለም አቀፍ የመሬት ቅርምት ፈጻሚዎች፣ አጭበርባሪዎች እና የድህነት አቃጣሪዎች የህዝቦችን መሬት ይገዛሉ፣ ይሸጣሉ፣ እንደዚሁም ሁሉ ያጫርታሉ፣ ይዘርፋሉ፣ ይቀማሉ፡፡

እ.ኤ.አ ታህሳስ 2015 የዘ-ህወሀት የመሬት ተቀራማቾች እና አጭበርባሪዎች እንዲህ የሚል የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሊሰጣቸው ይገባል፡ “ከዚህ በኋላ የእኛን መሬት እና ሌላውንም ሀብት እንድትሰርቁ አንፈቅድላችሁም፡፡ በቃ በቃ ነው!“

እ.ኤ.አ ታህሳስ 2015 ለዘ-ህወሀት የተላለፈው ጽናት የተመላበት የህዝብ መልዕክት እንዲህ የሚል ነው፡

ለ24 ዓመታት ያህል ክብራችንን ገፍፈኸን ቆየህ፣ እናም በውርደት ተጀቡነን ቆየን፡፡ በአሁኑ ጊዜ ግን “በቃ በቃ ነው!”

ለ24 ዓመታት ያህል ሰብአዊ መብታችንን ደፍጥጠህ ቆየህ፣ እናም የሁለተኛ ዜግነት ደረጃን ተቀብለን አንገታችንን ደፍተን ቆየን በአሁኑ ጊዜ ግን “በቃ በቃ ነው!”

ለ24 ዓመታት ድምጻችንን እና አንደበታችንን ዘግተህ ቆየህ፣ አንገታችንን ደፍተን ቆየን፣ በአሁኑ ጊዜ ግን “በቃ በቃ ነው!”

ለ24 ዓመታት ያህል የልጆቻችንን የወደፊት ብሩህ ተስፋ አጨልመህ በተስፋቢስነት ዝም ብለን አንገታችንን ደፍተን ስንመለከት ቆየን፣ በአሁኑ ጊዜ ግን “በቃ በቃ ነው!”

ለ24 ዓመታት ያህል አንዱ ምርጫ ሲያልፍ ሌላውን እየዘረፍክ እና በአደባባይ የህዝብን ድምጽ እየሰረቅህ ቆየህ፣ በዚህ በሳለፍነው ዓመት ደግሞ በቁስል ላይ እንጨት ስደድበት እንዲሉ የይስሙላ የቅርጫ ምርጫውን መቶ በመቶ አሸነፍኩ ብለህ በእብሪት ተወጥረህ ያለምንም ሀፍረት በድፍረት ተናገርክ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ግን “በቃ በቃ ነው!”

ለ24 ዓመታት ያህል ስብዕናችንን ገዝተህ ቆየህ፣ የደፈጠጥከው ስብዕናችን ወደነበረበት ቦታው እንዲመለስ እንጠይቃለን፡፡ በአሁኑ ጊዜ ግን “በቃ በቃ ነው!”

ለ24 ዓመታት ያህል አባቶችን እና ቅድመ አያቶቻችን ደማቸውን አፍስሰው አጥንታቸውን ከስክሰው ያቆዩትን መሬታችንን እየዘረፍክ ተባባሪ ለሆኑት ዓለም አቀፍ የመሬት ተቀራማቾች እና ለድህነት አቃጣሪዎች በቁርጥራጭ ሳንቲም ለግብር ዓላማህ ስትቸበችበው ዝም ብለን ስንመለከትህ ቆይተናል፡፡ አሁን ግን “በቃ በቃ ነው!”

መሬታችንን ለመጠበቅ ስንል በመሬታችን ላይ እንሆናለን ወይም በመሬታችን ውስጥ እንገባለን፡፡

ኃይልን በመጠቀም ብትገድሉንም፣ ሰላማዊ አመጻችንን ለማፈን የፈለገውን ያህል የኃይል እርምጃ ብትወስዱብንም፣ ብትፈጁንም፣ ብትገፉንም፣ ብታባርሩንም ወይም ደግሞ ብትለያዩንም በምንም ዓይነት መልኩ አናጎበድድም!

በአሁኑ ወቅት እናንተን አንገት እስካላስደፋን ድረስ አናጎነብስም!

ሁለተኛ፡ በረከት እና አዲሱ የዘ-ህወሀት ታሪክ መጠናቀቂያ የመጨረሻው ጊዜ መድረሱን ያውቃሉ ምክንያቱም ድህነት፣ ረሀብ እና ባለፉት አስርት ዓመታት ህዝቡን ስቃይ ፍዳውን እያሳዩት ባለበት ሁኔታ የምጣኔ ሀብቱ በሁለት አሀዝ ዕድገት አስመዝግቧል በማለት የሸፍጥ ፕሮፓጋንዳቸውን በማሰራጨት የቁማር ጨዋታ በመጫወት ላይ ይገኛሉ፡፡ ዘ-ህወሀት በፍርሀት ቆፈን ውስጥ የተጀቦኑ የድህነት አቃጣሪዎችን (ይቅርታ አማካሪዎችን) መላሾ እና ጥቅማ ጥቅም እየሰጠ በሀሰት ምንም ዓይነት የምጣኔ ሀብት በተጨባጭ በመሬት ላይ የሌለውን አለ እያሉ የሀሰት ምስክርነት እዲሰጡ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ የዓለም ባንክ፣ የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት፣ ዩኤስኤይድ እና ሁሉም የዓለም አቀፍ የድህነት አቃጣሪዎች ዘ-ህወሀት ታምራዊ የሆነ የምጣኔ ሀብት አስመዝጋቢ ኃይል እንደሆነ አድርገው ህጋዊ ለማስመሰል የሀሰት የቁጥር ድርደራ በመስጠት የለየለት ቅጥፈታቸውን በመፈጸም ላይ ይገኛሉ፡፡

እኛ የእነርሱን ተራ ውሸት እና እርባና ቢስ ቅጥፈት የማናውቅ ድሁሮች፣ ደደቦች እና ደንቆሮዎች እንደሆንን አድርገው ያስባሉ፡፡

ደህና እነርሱ እንደሚያስቡት ደደቦች እና ደንቆሮዎች እንዳልሆን ግን እየተገነዘቡት ነው፡፡

ባለፉት 24 ዓመታት ዘ-ህወሀት በከተማው ውስጥ ብቸኞቹ ተጫዋቾች እነርሱ እንደሆኑ አድርገው ሰይመዋል፡፡ ኢትዮጵያን የሸፍጣቸው የመጫወቻ ሜዳ አድርገዋታል፡፡ ኢትዮጵያን የመጫወቻ አሻንጉሊት አድርገዋታል፡፡ የስሜታቸው ማርኪያ መዝናኛቸው አድርገዋታል፡፡ ምንጊዜም ለማሸነፍ ብቻ ይጫወታሉ፣ ሆኖም ግን በመጨረሻው እራሳቸውን ከጨዋታው ውጭ አድርገዋል፡፡

አሁን ጨዋታው በዘ-ህወሀት ላይ ነው!

ወይም ደግሞ የአዲሱን የማስታወሻ ቃላት በመጠቀም የዘ-ህወሀት ታሪክ እያለቀ ነው፡፡

ሶስተኛ፡ በረከት እና አዲሱ የዘ-ህወሀት ታሪክ ጊዜ እያለቀ መሆኑን ያውቃሉ ምክንያቱም ዘ-ህወሀት በኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ዓይነት ጓደኛ እንደሌለው ያውቃሉ፡፡

በረከት እና አዲሱ ሎሌዎቻቸው እና ጫማ ላሾቻቸው በእነርሱ ተመልካችነት ሲዘርፉ እና ያለአግባብ በህዝብ ሀብት ሲበለጽጉ ወንጀሎቻቸውን ለበርካታ ጊዚያት እየሸፈኑ የነበሩት ጓዶቻቸው በአሁኑ ጊዜ የእነርሱ ጓደኞች አለመሆናቸውን በአድናቆት በመመልከት ላይ ናቸው፡፡ የሸክስፒርን አባባል በመዋስ የእነርሱ ጓደኞች “በፈገግታ ጥርሶቻቸውን እያሳዩ ሸፍጥ የሚሰሩ“ ጓደኞች ናቸው፡፡

በአሁኑ ጊዜ በረከት፣ አዲሱ እና ዘ-ህወሀት ምንም ዓይነት ጓደኛ እንደሌላቸው እየተገነዘቡ ነው፡፡

በፖለቲካ ዓለም እውነተኛ ወዳጅ እንደሌለ ማወቅ ይኖርባቸው ነበር፡፡ ሻርኮች ብቻ በዙሪያቸው ያለውን ማንኛውም ነገር ዘንጥለው እና በስተው በደም ባህር እንዲጥለቀለቅ አድርገው ወደ ውኃው የውጨኛ አካል ላይ ብቅ ይላሉ፡፡

እንዲሰርቁ እና ህዝቡን እንዲዘርፉ ፈቅደውላቸው የኖሩት የዘ-ህወሀት ጓደኞች በአሁኑ ጊዜ ሻርክ በመሆን አካባቢውን ወርረው በመያዝ ዘንጥለው እና በስተው በውሀው ላይ ደም እንዲታይ በማድረግ በስሜታዊነት ከቁጥጥር ውጭ በመሆን ከሌሎች ጋር በመሆን የዘረፉትን ለመቀራመት ይሞክራሉ፡፡

በረከት፣ አዲሱ እና ዘ-ህወሀት ለማመን አስቸጋሪ የሆነባቸው እውነታ በዘራፊዎች፣ በሌቦች እና በሸፍጠኞች መካከል ምንም ዓይነት ክብር የሌለ መሆኑን መገንዘብ ያለመቻላቸው ጉዳይ ነው፡፡ በዘራፊዎች መካከል በእርግጠኝነት ምንም ዓይነት ክብር የሚባል ነገር የለም፡፡

በረከት፣ አዲሱ እና የእነርሱ ጓደኞች በዘ-ህወሀት ውስጥ ተንከባክበው ያሳደጓቸው የሙስና የቢዝነስ ሰዎች እና የእነርሱ አጉራሽ የሆኑት በዝቅተኛው እርከን ላይ የሚገኙት ጓደኞቻቸው የእነርሱን ክብር ለመጠበቅ ሲባል የዘረፉትን ሀብት እንዲመልሱ እና በእውነት ተናግረው ወደ እስር ቤት እንዲገቡ ይፈልጋሉ፡፡

በድን ሆኖ የደነገጠው በረከት እንዲህ ይላል፣ “ጉዳዩ የዘ-ህወሀትን በሙስና መዘፈቅ እና ከሕግ አግባብ ውጭ ስልጣንን መጠቀምን በሚመለከት ማንም ቢሆን ሊቀበል የመቻሉ ጉዳይ አይደለም፡፡ ሆኖም ግን ሊታመን የማይችለው ጉዳይ ማንም ቢሆን እንደዚህ ያለውን ነገር በድፍረት መናገር የመቻሉ ሁኔታ ነው፡፡“

በረከት እና አዲሱ ያለምንም ክትትል እና ቁጥጥር በሙስና ገበታ ውስጥ እንደፈለጉ ሲዘርፉ እና ስልጣናቸውን ከህግ አግባብ ውጭ ለበርካታ ጊዚያት ሲጠቀሙ እንዲቆዩ ያሰለጠኗቸው ውሾች በአሁኑ ጊዜ ሲመግቧቸው የቆዩትን እጆች ወደ መንከስ ደረጃ የተሸጋገሩ መሆናቸውን ሊያምኑ አልቻሉም፡፡

ሆኖም ግን በረከት የሸክስፒርን አባባል በመዋስ እንዲህ ይላል፣ “ከፍተኛ ተቃውሞ የተነሳ ይመስለኛል፡፡“

ደህና ለምንድን ነው በሙስና የተዘፈቁ በዘ-ህወሀት የተፈጠሩ የቢዝነስ ሰዎች እና ወንጀለኛ የአካባቢ ባለስልጣኖች እንደዚህ ባለ ድፍረትን በተቀላቀለ ሁኔታ፣ ንቀትን በሚያሳይ እና ምንም ዓይነት ፍርሀት በሌለበት መንገድ ከቁንጮ ባለስልጣኖች ጋር መነጋገር የጀመሩት ዘ-ህወሀት ወደፊት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ምንም ዓይነት ዋጋ የሌለው እርባና ቢስ ድርጅት ካልሆነ በስተቀር በሌላ በምን ሊባል ይችላል?

በረከት እና አዲሱ ሊውጡት ያልቻሉት ደረቅ እውነታ ጓደኞቻቸው እና ደጋፊዎቻቸው በወገባቸው ላይ ጎራዴ በመታጠቅ የመጀመሪያ መሆናቸውን እና የተሳፈሩበት ጀልባ የውኃ ስርገት መፍሰስ ሲጀምር ገና በመጀመሪያው ምንም ዓይነት ዕድል ሳይሰጡ እያወጡ ወደ ባህሩ የሚወረውሯቸው መሆኑን ያለመገንዘባቸው ነው፡፡ የተማሩ እና የእኛ የተሻሉ ጓደኞች ያልናቸው የፓርቲ አባሎቻችን እኛን በመቃወም በእኛ ላይ ያምጻሉ… ይኸ የታሪኩ መጨረሻ ነው በማለት አዲሱ የተሰማውን ሀዘን ግልጽ አድርጓል፡፡

በረከት እና አዲሱ የሁኔታውን አሳሳቢነት ዘግይተው የተገነዘቡት ይመስላል፡፡

በመጨረሻም “ኮፍያው ለማን እንደሚስማማ“ በሚል ርዕስ ቦብ ማርለይ ያቀረበውን እና እንዲህ የሚለውን የሙዚቃ ትርጉም ተገንዝበውታል፡

ማን እንደሚታመን በፍጹም አታውቅም፣

ብትሰጥ ብታበላ ከየትም ከየትም፣

ዘርፈህም ቀምተህ ከሀገር ከህዝብም፡፡

 

ደመኛ ጠላትህ፣

ሞት የደገሰልህ፣

በቀጭኑ አንገትህ፣

ሸምቀቅ ያስገባልህ፣

ገልበጥ ይልና፣

ወዳጅ ይሆንና፣

ደግሞም እንደገና፣

መኖር ይጀምራል ይመሳሰል እና፡፡

 

አፍቃሪው ወዳጅህ ጥሩ የሚመስለው፣

በነጋ በጠባ ካንተ እማይለየው፣

ገና ሲያስነጥሰህ መሀረብ አቅራቢው፣

አቤት ወዴት የሚል ገና ሳታዝዘው፣

አብልቶ እሚያበላ ረዥም እጅ ያለው፡፡

 

ወዳጄ ነው ብለህ እንቅልፍ ስተተኛ፣

ደጋፊ ነው ብለህ ጠንካራ ሁነኛ

ባንዴ ተገልብጦ ይሆናል ደመኛ፡፡

 

ጥቂቶች ካንተ ጋር አብረው ይበላሉ፣

መጠጥ በመጠጣት ይመሳሰላሉ፣

ከበስተጀርባ ግን ሀሜት ያስባሉ፣

በስለት ቢላዋ ስጋን ይቆርጣሉ፡፡

 

ጥቂቶች አምርረው ፍጹም ይጠሉሀል፣

አሁን ወዳጅ መስለው ፍጹም ይቀርቡሀል፣

ከበስተጀርባቸው ሞት ይስቡልሀል፣

በምትሄድበት ላይ ፈንጅ ይቀብሩልሀል፣

ዕድሉን ቢያገኙ ሳትሞት ይቀብሩሀል፡፡

 

ዘ-ህወሀት በኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ዓይነት ወዳጅ የለውም፡፡

ዘ-ህወሀት በኢትዮጵያ ውስጥ 100 ሚሊዮን ጠላት አለው፡፡

ዘ-ህወሀትን ወዳጅ ከማድረግ ይልቅ ሲናደፉ መቅን አሳጥቶ ከሚቆጠቁጠው ከተናዳፊ ጊንጦች ጋር ጓደኛ መሆን በእጅጉ የቀለለ ነው፡፡

የዘ-ህወሀት መሪዎች በአሁኑ ጊዜ ምሁራን በማመጽ ክህደት የተፈጸሙባቸው መስሎ ቢሰማቸውም የወታደሮችን፣ የሲቪል ሰርቫንቱን፣ የቢዝነሱን ማህበረሰብ፣ የንግዱን ማህበረሰብ እና የኃይማት መሪዎች ገና ጀርባቸውን እስኪያዞሩባቸው መጠበቅ ይኖርባቸዋል፡፡

የዘ-ህወሀት መሪዎች በአሁኑ ጊዜ ምርጥ የሆኑ ጓደኞቻቸው ነገ ደመኛ ጠላቶቻቸው እንደሚሆኑ ሊገነዘቡ ይገባል፡፡

የዘ-ህወሀት ታዛዥ ሎሌዎች በ100 መቶ ሚሊዮን ሻርኮች ባህር ውስጥ እንደሚዋኙ ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡

የዘ-ህወሀት መሪዎች ያለማንም ደጋፊነት ብቻቸውን መለመላቸውን መቆማቸውን በውል ሊያጤኑት ይገባል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ውስጥ የዘ-ህወሀት መሪዎች፣ ታማኝ ሎሌዎች እና ደጋፊዎች እንዲህ የሚሉትን የማርቲን ሉተር ኪንግን ቃላት ማስታወስ ይኖርባቸዋል፣ “በመጨረሻ የእኛን ጠላቶች ቃላት አይደለም የምናስታውሰው፣ ሆኖም ግን የጓደኞቻችንን ጸጥ ማለት ብቻ ነው የምናስተውለው፡፡“

 የዘ-ህወሀት የመጨረሻ ታሪክ በሚነገርበት በአሁኑ ጊዜ የዘ-ህወሀት ጓደኞች እንደ መቃብር ጸጥ ርጭ ብለው በማስተዋል ላይ ናቸው፡፡

አራተኛ፡ በረከት እና አዲሱ የዘ-ህወሀት ታሪክ የመጨረሻው መሆኑን ያውቃሉ ምክንያቱም በህብረተሰቡ ውስጥ ፍርሀትን ማንገስ እና ጥላቻን መቀስቀስ የማያዋጣቸው ተራ ሸፍጥ እየሆነ መምጣቱን እየተገነዘቡ የሚገኙበት ሁኔታ ላይ ናቸውና፡፡ ተስፋ የቆረጠው በረከት እንዲህ ብሏል፣ “ሆኖም ግን ሊታመን የማይችለው ነገር እኔ አሁን እንደምለው የመናገር ድፍረቱን አግኝቷል፡፡“

ተስፋ የቆረጠው አዲሱ እንዲህ ብሏል፣ “በየቦታው እስከ ሴል ደረጃ ድረስ ሄደዋል፡፡ እራሱን እያደራጀ ያለ አንድ ነገር ያለ ይመስላል፡፡“

የአምባገነኖች ትልቁ መሳሪያቸው እየጨቆኑት ያለው ህዝብ አዕምሮ ነው፡፡

ፍርሀት እና ጥላቻ ብዙሀኑን ህዝብ በፍርሀት ቆፈን ውስጥ በማስገባት አምባገነናዊ አገዛዞች ህዝቡን ለመቆጣጠር የሚያስችላቸው መስሎ ይታያቸዋል፡፡

ሁሉም አምባገነኖች ህዝቡን በፍርሀት ቆፈን ሽብበው፣ በጥላቻ ከፋፍለው እና በድህነት አራቁተው በመግዛት የስልጣን ዘመናቸውን የሚያራዝሙ ይመስላቸዋል፡፡

ፍርሀትን በማንገስ አምባገነኖች እራሳቸውን የማይበገሩ እና የህዝቦች ሁሉ እዳኞች አድርገው ያቀርባሉ፡፡ እነርሱ እስከሌሉ ድረስ በሀገሪቱ ውስጥ ሁከት፣ ብጥብጥ እና ውድመት እንደሚከተል ህዝቡን ለማሳመን ተስፋ ያደርጋሉ፡፡

ጥላቻን በማራገብ ህዝቡን ለመከፋፈል እና ለመግዛት ጥረት ያደርጋሉ፡፡

ነጻነቱን በመግፈፍ በድህነት በዳሸቀው ህዝብ ላይ ባርነትን ይጭናሉ፡፡

ዘ-ህወሀት ህዝቡን 5ለ1 እየተባለ በሚጠራው የቁጥጥር ሰንሰለት ፕሮግራም ጠርንፎ በመያዝ የሌሎችን ኢትዮጵያውያን ህዝብ ማለትም የጓደኞችን፣ የቤተሰብ አባላትን፣ የስራ ባልደረቦችን፣ እና የጎረቤቶችን የቀን ተቀን ውሎ እና እንቅስቃሴ እጅ ከወርች ጨምድዶ በመያዝ በመቆጣጠር ላይ የሚገኝ ቢሆንም ዘ-ህወሀት በታችኛው የእርከን ደረጃ የተደራጅ እና እነርሱን አሽቀንጥሮ የሚጥል ኃይል እንዳለ በፍርሀት ቆፈን ተውጠው በመናገር ላይ ይገኛሉ፡፡ አዲሱ እንዲህ ብሏል፣ “በየቦታው እስከ ሴል ደረጃ ድረስ የወረደ እንቅስቃሴ እንዳለ እገምታሁ፡፡ እራሱን ያደራጀ እና ውስጥ ለውስጥ የሚንቀሳቀስ አንድ ኃይል ያለ ይመስላል፡፡“

በረከት፣ አዲሱ እና ዘ-ህወሀት ላፉት 24 ዓመታት ያህል በኢትዮጵያውያን ልቦች እና አዕምሮዎች ውስጥ መጠነ ሰፊ የሆኑ ጸጥ ያሉ አመጾች እየተካሄዱ መሆናቸውን ሆን ብለው በድንቁርና እየተመለከቷቸው ያሉበት ሁኔታ ያለ ይመስላል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ዘ-ህወሀት እነዚህን ጸጥ ብለው በመንቀሳቀስ ላይ ያሉትን አመጾች በግልጽ እየተንጸባረቁ ያሉበትን ሁኔታ ምስክርነት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ ይኸ ለሁሉም የሚታይ ግልጽ የሆነ እውነታ ነው፡፡

በኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት ተምሳሌት ቀንዲል የሆነችው ጀግኒቷ ርዕዮት ዓለሙ ባለፈው ሳምንት ሰላማዊ ትግን በመተው በትጥቅ ትግል ለመፋለም እና ዘ-ህወሀትን በትጥቅ ትግል ለማስወገድ በጽናት መወሰኗን ባወጀች ጊዜ ይኸ “የታሪኩ መጨረሻ” መሆኑን በግልጽ ያመላክታል!

ርዕዮት ሀሳብን ለመግለጽ ብቻ ሲባል እንደሚደረግ ተራ ሰው አይደለችም፡፡ ርዕዮት እንደ እርሷ ሁሉ በጸረ ዘ-ህወሀት ላይ ለተነሱት ለሌሎች ጀግኒቶች እና ጀግናዎች የቆመች መንፈሰ ጠንካራ ጀግኒት ናት፡፡ በምንም ዓይነት መልኩ አታጎበድድም! በፍጹም!

ርዕዮት ከሌሎች ሴቶች በላይ ልዩ የሆነ ድፍረት፣ ጽናት እና የአዕምሮ ጉብዝና ያላት ጀግኒት ናት፡፡

ርዕዮት ለእርሷ ትውልድ ላለው ህዝብ ድምጽ እና መልዕክተኛ ናት፡፡

ርዕዮት የሰላማዊ ትግል በሀገሪቱ ውስጥ ያበቃለት መሆኑን እና የእርሷ ትውልድ ለትጥቅ ትግል መዘጋጀት እንዳለበት በግልጽ በመናገር ላይ ትገኛለች ምክንያቱም ዘ-ህወሀት ሁሉንም የፖለቲካ አማራጭ ምህዳሩን ዘግቶታል፡፡

ወጣቱ ትውልድ ለትጥቅ ትግል ቆርጦ በሚነሳበት ጊዜ የታሪኩ ፍጻሜ ያን ጊዜ ይሆናል፡፡

ርዕዮት በሰላማዊ  እና በትጥቅ ትግል መካከል ምርጫ አልመረጠችም ሆኖም ግን ዘ-ህወሀት ርዕዮትን የአመጽ እና የትጥቅ ትግልን እንድትመርጥ አስገድዷታል፡፡

ዘ-ህወሀት በቅርቡ በርዕዮት ላይ ስም የማጠልሸት ዘመቻውን ይጀምራል፡፡ እንዲህም ይላሉ፣ ርዕዮት “አሸባሪ” ናት፡፡ አሸባሪውን ቡድን ተቀላቅላለች፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ አስረዋት የነበሩበት ምክንያትም በሽብርተኝነት ተሳታፊ በመሆኗ በሚል ምክንያት ነው፣ ሌላም… ሌላም… ሌላም…

በቅርቡ የርዕዮትን ስም ለማጠልሸት እና ስሟን ለማጥፋት ዘመቻ ይጀምራሉ፡፡ ስለእርሷ ውሸት እና ተራ ቅጥፈት ማሰራጨት ይጀምራሉ፡፡

ዘ-ህወሀት ስለርዕዮት ስለሚያስበው ጉዳይ ማንም ጆሮ እንደማይሰጠው እና ከጉዳይ እንደማይቆጥረው መገንዘብ ይኖርበታል፡፡

ይልቁንም ዘ-ህወሀት በውል ሊገነዘበው የሚገባው ጉዳይ ርዕዮት በተስፋ የተሞላ፣ ራዕይ ያላት እና ከኢትዮጵያ ህዝብ 70 በመቶ የሚይዘው የኢትዮጵያ ወጣት ትውልድ ነጻነቱን ለመጎናጸፍ በጽናት መታገል እንዳለበት የሚያስችል ስብዕናን የተጎናጸፈች ጀግኒት መሆኗን ነው፡፡

ዘ-ህወሀት ማወቅ ያለበት ጉዳይ ቢኖር እንደ ርዕዮት ሁሉ ሌላውም የኢትዮጵያ ወጣት እንደ ኢትዮጵያ ጽጌረዳ እያበበ እና እየፈካ ሀገሩን ከውድቀት በማዳን ለነጻነት ጉዞው እየተገሰገሰ መሆኑን ነው፡፡

እኔ ለወደፊቷ ኢትዮጵያ የማስተውለው ነገር ቢኖር ይህንን ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ከጫፍ አስከታች በፈኩ የጽጌረዳ አበባዎች ተሸፍና እመለከታለሁ፡፡

አምስተኛ፡ የዘ-ህወሀት መሪዎች የታሪካቸው መጨረሻ መሆኑን ማወቅ አለባቸው ምክንያቱም ለማጥፋት የሚፈልጉት እራሳቸው ሰይጣን ሆነው ያሉበትን ነገር ነው፡፡

የትግራይ ማኒፌስቶ በማለት ዘ-ህወሀት ባዘጋጀው ሰነድ (ገጽ 18) ላይ እንዲህ በማለት አውጇል፣ “የትግራይ ህዝብ ግብ እና ዓላማ የጸረ አማራ ጭቆና ትግል መጀመር እና የትግራይ ዴሞክራቲክ ሬፐብሊክን መመስረት ነው፡፡“

ማንም ቢሆን ስለዚህ ጉዳይ ለማወቅ የሚፈልግ ሰው ቀደም ሲል የዘ-ህወሀት ዋና አባል የነበረው እና ዘ-ህወሀት ሁሉንም ኢትዮጵያውያን በተለይም አማራን እንደሚጠላ በማጋለጥ የማጭበርበሪያ እና የጥላቻ ርዕዮት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሚያጋልጠውን የገብረ መድህን አርአያን ንግግር መስማት ብቻ በቂ ነው፡፡ ስለገብረ መድህን አርበኝነት እና በኢትዮጵያ ላይ ስላለው ፍቅር እና እውነት ወዳድነት የላቅ ክብር አለኝ፡፡

ዘ-ህወሀት ከ24 ዓመታት በላይ ለሆነ ጊዜ የአማራን ስም በማጠልሸት፣ በማስፈራራት፣ በማዋረድ የፍርሀት እና የጥላቻ ዘመቻውን ቀጥሎበት ይገኛል፡፡

ዘ-ህወሀት ከ24 ዓመታት በላይ “አማራ ሰይጣን” የሆነ ለምንም የማይጠቅም ህዝብ ነው በማለት ስትራቴጂ ቀይሶ ተንቀሳቅሷል፡፡

ዘ-ህወሀት ከ24 ዓመታት በላይ ሰይጣኑ አማራ ሰዎችን በመግደል፣ ኢትዮጵያዊ ወንድሞቹን እና እህቶቻቸውን በመፍጀት ኖረዋል በማለት ሲሰብክ ቆይቷል፡፡

ዘ-ህወሀት ከ24 ዓመታት በላይ ሰይጣኑ አማራ መሬቱን በመዝረፍ እና ህዝቡን ባሪያ በማድረግ ኢትዮጵያዊ ወንድሞቹን እና እህቶቹን ሲጨቁን ቆይቷል ብሏል፡፡

ዘ-ህወሀት ከ24 ዓመታት በላይ ሰይጣኑ አማራ ስልጣኑን ከህግ አግባብ ውጭ በመጠቀም እና አማራ ያልሆኑ ሰዎችን መብት በመንፈግ ሲገዛ ቆይቷል ብሏል፡፡

ዘ-ህወሀት ከ24 ዓመታት በላይ ሰይጣኑ አማራ በመልክ አስፈሪ ሰይጣን ቀርጾ በህዝቡ ላይ የፍርሀት እና የጥላቻ ዕኩይ ተግባራትን ሲያራምድ ቆይቷል፡፡

ዘ-ህወሀት ላለፉት 24 ዓመታት እኛ ከሌለን “ሰይጣኖቹ አማሮች ተመልሰው በመምጣት በስልጣን ኮርቻው ላይ ይቀመጣሉ“ ሲል ቆይቷል፡፡ ሰይጣኖቹ አማሮች ሌላው ብሄረሰብ በቋንቋው እንዳይጠቀም ይከለክላሉ እያለ ሲያደናግር ቆይቷል፡፡ ህዝቦች የእራሰቸውን ባህል መተግበር በመጀመራቸው አማራ ይቀጣቸዋል ሲል ቆይቷል፡፡ አማራ ሌሎች ህዝቦች እራሳቸውን ማስተዳደር እንዳይችሉ ያደርጓቸዋል ሲል ቆይቷል፡፡

ላለፉት 24 ዓመታት ዘ-ህወሀት ሰይጣኑ አማራ እንደገና ወደ ስልጣን በመመለስ መሬታቸውን እንደሚወስድባቸው ለማመን እንዲችሉ ለማድረግ እኩይ ድርጊቱን ሲሰራ ቆይቷል፡፡

ላለፉት 24 ዓመታት ዘ-ህወሀት የመሬታቸው ባለቤት የሆኑትን ኢትዮጵያውያን መሬት እየነጠቀ ለቻይናዎች፣ ለህንዶች፣ ለሳውዲዎች እና ለቱርኮች ሲቸበችብ ቆይቷል፡፡

ከ24 ዓመታት በኋላ ዘ-ህወሀት ወደ “አዲሱ እና የተሻሻለው ሰይጣን አማራነት” ተሸጋግሯል፡፡

ፍሬድሪክ ኒዤ “ከበጎ እና ከሰይጥንነት በላይ በሚል ርዕስ እንዲህ በማለት ጽፏል፣ ”ከጭራቆች ጋር የሚታገል እርሱ እራሱ ጭራቅ ላለመሆኑ እና እንደማይሆን ማወቅ ይኖርበታል፡፡ እናም ለብዙ ጊዜ በአስቸጋሪው ሁኔታ ላይ አፍጥጠህ ስትመለከት አስቸጋሪው ሁኔታ እራሱ ወደ አንተ ያፈጣል፡፡“

ዘ-ህወሀት ሰይጣኑን አማራ ለመታግል ስትራቴጂ ነድፎ ሲታግል ከቆየ በኋላ በመጨረሻው ታሪኩ እርሱ እራሱ ወደ አዲስ እና የተሻሻለው ሰይጣን አማራነት ተሸጋግሯል፡፡

ስድስተኛ፡ ዘ-ህወሀት የታሪኩ መጨረሻ መሆኑን መገንዘብ አለበት ምክንያቱም ለህልውናቸው አስጊው ሁኔታ የመጣው ከሚቃወማቸው ቡድን ሳይሆን አመራር ከሌለው የወጣት እንቅስቃሴ እና ሊበገር ከማይችል እንቅስቃሴ ነው፡፡

በሚስጥር ተይዞ ተመዝግቦ በተቀመጠው ውይይት ላይ አዲሱ እንዲህ ብሏል፣ “እራሱን ያደራጀ አንድ ኃይል ያለ ይመስላል…በራሪ ጽሁፎች በመሰራጨት ላይ እንደሆኑ ታይተዋል፡፡ ስለሆነም በየቦታው እስከ ሴል ደረጃ ድረስ ወርደው ተደራጅተዋል ብየ አስባለሁ“ ብሏል፡፡

የአዲሱ እና የዘ-ህወሀት ፍርሀት አመራር አልባ፣ ፓርቲ አልባ፣ ድርጅት አልባ እንቅስቃሴ በህዝቡ ውስጥ ተሰራጭቶ እና ዘልቆ ገብቷል የሚል ነው፡፡

እነርሱን ለመቃወም በተደራጀ መልኩ ከተነሱት ተቃዋሚዎች ይልቅ እራሱን ያደራጀ አንድ ነገር አለ በሚለው ላይ እኔም እራሴ እስማማለሁ፡፡ ያ እራሱን ያደራጀ አንድ ነገር ማዕከላዊ አመራር የለውም፣ የእዝ ሰንሰለት ጠገግ የለውም እንደዚሁም ደግሞ የተለየ ርዕዮት ዓለም የለውም፡፡ ያ የተደራጀ አንድ ነገር በየትኛውም ቦታ እስከ ሴል ደረጃ ድረስ ወርዶ ተሰራጭቶ ይገኛል፡፡

ያ የተደራጀ አንድ ነገር  ዘርፈ ብዙ የጎሳ እና ዘርፈ ብዙ የኃይማኖት እንቅስቃሴ እንደሆነ አምናለሁ፡፡

ወጣቱ እስከ ሴል ድረስ ወርዶ በመደራጀት ነጻ በሆነ መልኩ እንደ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ ወይም ደግሞ ጠባብ ፍላጎቶችን በመከላከል የአጻፋ ምላሹን ሊሰጥ ይችላል፡፡

ዘ-ህወሀት ከሁሉም የበለጠ የሚፈራው ነገር በጋራ እምነት እና በሰብአዊ እና በዴሞክራሲ መብቶች መከበር ዙሪያ ላይ ትኩረት በማድረግ የዘ-ህወሀትን ጨቋኝ አገዛዝ ገዝግዞ ለመጣል ጥረት በማድረግ ላይ ያለውን አመራር የለሹን የወጣቱን እንቅስቃሴ ነው፡፡ በሴል ደረጃ ወጣቱ አንድ በአንድ እየቀሰቀሰ በዘ-ህወሀት ላይ በመነሳት ላይ ይገኛል፡፡

አመራር የለሹን እንቅስቃሴ ማጥፋት አይቻልም፡፡

ምንም ዓይነት የሚደመሰስ ነገር ስለሌለ እንደዚህ ያለውን እንቅስቃሴ ማጥፋት አይቻልም፡፡

ቀላሉ እውነታ እንዲህ የሚል ነው፡ የኢትዮጵያ ወጣቶች ተባብረዋል በፍጹም ሊሸነፉ አይችሉም!!!

ለኢትዮጵያውያን ወጣቶች እንዲህ የሚል ምክር አለኝ፡ በዓረቡ ዓለም አመጽ ጊዜ የግብጽ ወጣቶች ሲጠቀሙባቸው የነበሩትን ስትራቴጂዎች ለይቶ በማውጣት እና በማጥናት ተመሳሳይ ስህተት እንዳትፈጽሙ እርግጠኞች በመሆን ታገሉ እላለሁ፡፡

ሰባተኛ፡ የዘ-ህወሀት መሪዎች የታሪካቸውን መጨረሻ ለማራዘም የሚችሉ መስሎ ይታያቸዋል  ምክንያቱም ህዝቡን ሲጨርሱ፣ ሲያሰቃዩ እና የእነርሱን ተቃዋሚዎች ሁሉ ሲፈጁ ዝም ብለው የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ በማለት አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው ተቀምጠዋልና፡፡ ያቀረቧቸው ታሳቢዎችም ምንም ዓይነት መሰረት የሌላቸው ናቸው ለማለት አልችልም፡፡

የዘ-ህወሀት ዋና የገንዘብ ምንጭ የሆኑት አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት እ.ኤ.አ በ2005 አድርጎት የነበረውን የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ ተከትሎ ተፈጥሮ በነበረው ውዝግብ ዘ-ህወሀት ሰላማዊ ህዝቦችን ሲፈጅ፣ ወደ አንድ ሺ የሚሆኑ ዜገችን አካለ ጎደሎ ሲያደርግ ጆሮዳባ ልበስ በማለት ዝም ብለው ተመልክተዋል፡፡

በእርግጥ በሁለት ዓመት እልቂት እና ፍጅት አሜሪካ እ.ኤ.አ በ2005 ወደ 1.8 ቢሊዮን ዶላር የነበረውን እርዳታዋን እ.ኤ.አ በ2008 ወደ 3.5 ቢሊዮን ከፍ አድርጋለች፡፡ እናንተ ለመግደል ያብቃችሁ እንጅ እኔ ለገንዘብ ምጽዋቱ ችግር የለም ማለቷ ነው፡፡

አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት እ.ኤ.አ ታህሰስ 2004 ዘ-ህወሀት በጋምቤላ ክልል በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎችን ሲፈጅ አላየሁም፣ አልሰማሁም ብለው አልፈውታል፡፡

አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት ዘ-ህወሀት በኦጋዴን አካባቢ እ.ኤ.አ ከ2007-08 በሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎችን ሲፈጁ አላየሁም፣ አልሰማሁም በማለት ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው አልፈውታል፡፡

አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት ዘ-ህወሀት እ.ኤ.አ ከ2006-09 ድረስ በሺዎች የሚቆጠሩ ሶማሌያውያንን ድንበር ተሻግሮ ሲፈጅ እና ሲያፈናቅል እንዲያውም በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር በመመጽወት አልሰማንም፣ አላየንም በማለት ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው አልፈውታል፡፡

አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት ዘ-ህወሀት እ.ኤ.አ ታህሳስ 2015 ተቃውሞ ባሰሙ ንጹሀን ዜጎች ላይ እንደገና ሌላ የእልቂት እና የፍጅት ዘመቻ ሲፈጽም እና ይህንንም ዕኩይ ድርጊት እ.ኤ.አ በ2016 በአዲሱ ዓመት አጠናክሮ እንደሚቀጥልበት እያዩ ዝም ብለው አላየሁም፣ አልሰማሁም በማለት ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው መመልከት ይኖርባቸዋልን?

እኔ የማውቀው ነገር የለም፡፡

እኔ የማውቀው ነገር ቢኖር እንዲህ ከሚለው ከሄንሪ ማቱሳላህ ኪሲንገር አባባል ትምህርት የወሰድኩ መሆኔን ነው፣ “አሜሪካ ዘላቂ ጥቅም እንጅ ቋሚ ወዳጆች ወይም ጠላቶች የሏትም“ ብለዋል፡፡

ይህንን አባባል ሰፋ ባለ መልኩ ሳፍታታው ነገሮች ገፍተው በሚመጡበት ጊዜ በእርግጠኝነት አሜሪካ እንደዚሁም የአውሮፓ ህብረት እና ቻይናም እንኳ ቢሆኑ የእነርሱን ፍላጎት የማያሟሉ እስከሆኑ ድረስ እርግፍ አድርገው በመጣል በቅርጫት ወስጥ ተደርጎ እንደሚጣል ቆሻሻ ወደ ጓሮ ይወረውሯቸዋል፡፡

እ.ኤ.አ በ2012 የግብጽ ህዝብ በጨቋኙ አገዛዝ መሪ በሆስኒ ሙባረክ ላይ ሆ ብሎ በተነሳ ጊዜ አሜሪካ ወደ ጎን ነው የጣለችው፡፡ በዚያን ጊዜ ባራክ ኦባማ እንዲህ ብሎ ነበር፡

“የግብጽ ህዝብ ተናገረ፡፡ ድምጻቸው መሰማት አለበት፡፡ እናም ግብጽ እንደቀድሞው መቀጠል የለባትም፡፡ ፕሬዚዳንት ሙባረክ ከስልጣኑ እንዲወርድ ተደርጎ ለለውጥ ለተራበው የግብጽ ህዝብ ተገቢውን ምላሽ ይስጥ፡፡ ሆኖም ግን የግብጽ ሽግግር የመጨረሻው አይደለም፡፡ ገና የመጀመሪያው ነው፡፡ እርግጠኛ ነኝ ወደፊት ፈታኝ የሆኑ ቀናት ይጠብቃሉ እናም በርካታ ያልተመለሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሳያገኙ ቀጥለው ይገኛሉ፡፡ ሆኖም ግን እርግጠኛ ነኝ የግብጽ ህዝብ ሰላማዊ በሆነ መንገድ፣ ገንቢ በሆነ እና በአንድነት መንፈስ እነዚህን ያለፉ ጥቂት ሳምንታትን ከግንዛቤ በማስገባት ምላሽ ለመስጠት ችለዋል፡፡ ለግብጻውያን ቅን የሆነ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ከማራመድ በስተቀር ሌላ ምንም ዓይነት መንገድ እንደሌለ ግልጽ አድርገዋል“ ብሏል፡፡

እ.ኤ.አ መጋቢት 2011 የሊቢያ ህዝብ በሙአማር ጋዳፊ ላይ በተነሳበት ጊዜ የሊቢያ ህዝብ ወደ ታሪክ ቆሻሻ ቅርጫት ውስጥ ከመጣሉ በፊት ኦባማ አስቀድሞ ጥሎታል፡፡ እንዲህ ብሎም ነበር፡

“ጋዳፊ ከተቃዋሚ ኃይሉ የበለጠ ኃይል አለው ብየ አላስብም፡፡ ጋዳፊ በተሳሳተው የታሪክ ጎን ያለ መሆኑን አምናለሁ፡፡ የሊቢያ ህዝቦች ለነጻነት እና ከበርካታ አስርት ዓመታት እስከ አሁን ሲጨቁነው የቆየውን ሰው ለማስወገድ ጉጉት እንዳለው አምናለሁ፡፡ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር በመመካከር ጋዳፊ ከስልጣን መንበሩ እንዲወገድ ከተቃዋሚዎች ጎን መቆም አለብን“ ነበር ያለው፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ በህወሀት ላይ በሚነሳበት ጊዜ ኦባማ በተመሳሳይ መልኩ እንዲህ ይላል ብዬ ከልቤ አስብ ነበር፡

“የኢትዮጵያ ህዝብ ተናገረ፡፡ ድምጻቸው መሰማት አለበት እናም ኢትዮጵያ በቀድሞው ዓይነት ልትራመድ አትችልም፡፡ ዘ-ህወሀት ከስልጣኑ በመውረድ ለኢትዮጵያ ህዝብ የለውጥ ረሀብ ምላሽ መስጠት አለበት፡፡ የመጀመሪያው ነው፡፡ ሆኖም ግን የኢትዮጵያ ሽግግር የመጨረሻው አይደለም፡፡ ገና የመጀመሪያው ነው፡፡ እርግጠኛ ነኝ ወደፊት ፈታኝ የሆኑ ቀናት ይጠብቃሉ እናም በርካታ ያልተለመሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሳያገኙ ቀጥለው ይገኛሉ፡፡ ሆኖም ግን እርግጠኛ ነኝ የኢትዮጵያ ህዝብ ሰላማዊ በሆነ መንገድ፣ ገንቢ በሆነ እና በአንድነት መንፈስ እነዚህን ያለፉ ጥቂት ሳምንታትን ከግንዛቤ በማስገባት ምላሽ ለመስጠት ችለዋል፡፡ ለኢትዮጵያውያን ቅን የሆነ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ከማራመድ በስተቀር ሌላ ዓይነት መንገድ የለም ብየ አምናለሁ፡፡ የኢትዮጵያ ህዝቦች ለነጻነት እና ከበርካታ አስርት ዓመታት እስከ አሁን ሲጨቁነው የቆየውን ሰው ለማስወገድ ጉጉት እንዳለው አምናለሁ፡፡ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር በመመካከር ዘ-ህወሀት ከስልጣን መንበሩ እንዲወገድ ከተቃዋሚዎች ጎን መቆም አለብን“ ይላል ብዬ ነበር የምጠብቀው፡፡

የዘ-ህወሀት የደናቁርት ስብስቦች አሜሪካ፣ አውሮፓ እና ቻይና እስከመጨረሻው ድረስ ከእነርሱ ጋር በጽናት የሚቆሙ ይመስላቸዋል፡፡

የዘ-ህወሀት እርጥባን ሰጭዎች የሆኑትን የቻይናዎችን መርህ ግልጽ አድርጊያለሁን? እንዲህ የሚለውን ጥንታዊ መርህ ይከተላሉ፣ “ምንም ዓይነት ሰይጣናዊ ድርሀጊት አላየሁም፣ ምንም ዓይነተር ሰይጣናዊ ድርጊት አልሰማሁም፣ ምንም ዓይነት ሰይጣናዊ ንግግር አልተደረገም፡፡“

ህዝቡ በዘ-ህወሀት ላይ ሆ ብሎ በሚነሳበት ጊዜ ኦባማ እና አጋሩ የአውሮፓ ህብረት፣ ቻይና እና እንደዚሁም ሌላው ቀሪው ሁሉ በመስመጥ ላይ ባለ መርከብ ውስጥ እንዳለች አይጥ ሁሉ ዘ-ህወሀትን እየተው ውልቅ ውልቅ ይላሉ፡፡

እንዲህ ይሉታል፣ ቻው ዘ-ህወሀት ደህና ሁን! አንተን ማወቃችን ጥሩ ነው! እዚህ ላይ ወራጅ አለ!

ጊዜው በሚደርስበት ጊዜ እና የኢትዮጵያ ህዝብ በሚነሳበት ጊዜ በእርግጠኝነት ሊሆን የሚችለው እንደዚህ ነው፡፡ ይነሳሉ፡፡

እንዲህ የሚሉትን የማያ አንጌሎን የግጥም ስንኞች በመጠቀም መነሳታቸውንም እውን ያደርጋሉ፣

ደግሞ እንደጨረቃ እንደ ጸሐይ ሁሉ፣

ሌት ቀን ለሚያበሩት ፍጥረታቶች ሁሉ፣

እርግጠኛ ሆነን ባመጽ በማዕበሉ፣

ነጻነት ማስፈን ነው በዱር በገደሉ፡፡

 

እንደሚፈነጥቅ የጸሐይ ብርሀን

እንደ ሌት ጨረቃ እሰኪሰጥ ወጋገን፣

ተስፋችን ይፈንጥቅ ለሰው ቤዛ ይሁን፡፡

 

እንደ ጨረቃ እና እንደ ጸሐይ ሁሉ ኢትዮጵያውያን ይነሳሉ፡፡ ሆኖም ግን ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ እንደ ጸሐይ እና እንደጨረቃ በሚነሳበት ጊዜ አሜሪካ ዘ-ህወሀትን ልታድነው እና ልትጠብቀው ከቶ አትችልም፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ ሆ ብሎ በሚነሳበት ጊዜ አሜሪካ ዘ-ህወሀትን እንደተመረዘ ቦታ እርግፍ አድርጋ ትታው ነው የምትሄደው፡፡

አሜሪካ እ.ኤ.አ በ1959 በኩባ ውስጥ ፉልጌንሲዮ ባቲስታንን እንደዚህ ነው ያደረገችው፡፡

እ.ኤ.አ በ1960 ጆን ኬኔዲ ለፕሬዚዳንታዊ የምርጫ ቅስቀሳ በሚያካሂዱበት ጊዜ ገዳዩ እና ሰይጣኑ ባቲስታ በማለት ያወገዙበትን እንዲህ የሚለውን ንግግር አንብቤ አስታውሳለሁ፡፡

“ፉልጀንሲዮ ባቲስታ በሰባት ዓመታት ውስት 20 ሺ ኩባውያንን ገደለ… እናም ፍጹም በሆነ የፖሊስ መንግስት – ሁሉንም የግለሰብን ነጻነት በመግፈፍ ኩባን ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ቀየረ፡፡ ሆኖም ግን የእኛ የኩባ እርዳታ እና የማይሰሩ ፖሊሲዎቻችን ዩናይትድ ስቴትስ ይህንን አሸባሪ የባቲስታ አገዛዝ ከሚረዱት ሀገሮች ስም ዝርዝር ውስጥ እንድትመደብ አድርጓታል” ብለው ነበር፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ በሚነሳበት ጊዜ እና ለዘ-ህወሀት መውጫ በሚያሳይበት ጊዜ በኦባማ ወይም ደግሞ እሱን በሚተካው የሚደረግ እንዲህ የሚል ተመሳሳይ መግለጫ ለማሰብ እችላለሁ፡

“ዘ-ህወሀት ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ጊዜ ውስጥ በመቶዎች እና በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ገድሏል፡፡ ለዘ-ህወሀት የምንሰጠው የእኛ እርዳታ እና የማይሰሩ ፖሊሲዎቻችን ዩናይትድ ስቴትስ ይህንን አሸባሪ የዘ-ህወሀትን አገዛዝ ከሚረዱት ሀገሮች ስም ዝርዝር ውስጥ እንድትመደብ አድርጓታል” ብለው ነበር“ ይላሉ ብየ አስባለሁ፡፡

አሜሪካ እ.ኤ.አ በ1979 የኒኳራጓ አምባ ገነን መሪ የነበረውን አናስታሲዮ ሶሞዛ ግራሲያን በዚህ ዓይነት መንገድ ነበር ያስተናገደችው፡፡

አሜሪካ እ.ኤ.አ በ1979 የኢራኑን አምባገነን መሪ የነበረውን መሀመድ ሬዛ ሻህ ፓህላቪንን በዚህ ዓይነት መንገድ ነበር ያስተናገደችው፡፡

አሜሪካ እ.ኤ.አ በ1981 የፓናማ አምባገነን የነበረውን ኦማር ቶሪጆስን በዚህ ዓይነት መንገድ ነበር ያስተናገደችው፡፡

አሜሪካ እ.ኤ.አ በ2011 የቱኒሲያ አምባነን የነበረውን ኤል አቢደን አሊን እና እ.ኤ.አ በ2012 የየመኑን አምባገነን መሪ አሊ አብደላ ሳለህን በዚህ ዓይነት መንገድ ነበር ያስተናገደቻቸው፡፡

ምንም ዓይነት ክርክር አያስፈልግም፡፡ ምንም ዓይነት ሁከት አያስፈልግም፡፡ አሁን እነርሱን ይይዛሉ፣ ቀጥለው እነርሱኑ ያጣሉ፡፡ ዋሺንግተን ዲሲ ላይ ያለው መገለባበጥ እንግዲህ የሚያሳየው ይህንኑ ነገር ነው፡፡

አሜሪካ ዘላቂ ጥቅም ብቻ እንጅ ቋሚ ወደጃ እና ጠላት የላትም ያለው ሁኔታ ይኸው ነው!

ስምንት፡ የዘ-ህወሀት መሪዎች የታሪካቸው መጨረሻ ይዘገያል ብለው ያምናሉ ምክንያቱም በአሁኑ ጊዜ ያለው አመጽ እንደ ነፋስ አንዴ ሽው ብሎ የሚጠፋ እና ነገሮች ሁሉ ተመልሰው እንደ ቀድሞው እንደተለመደው የሚሆን ይመስላቸዋል፡፡

ከሁሉም በላይ ዘ-ህወሀት በሰላማዊ የሙስሊም አማጺዎች ላይ የኃይል እርምጃ በመውሰድ ጸጥ አድርጊያቸዋለሁ ብሎ ያስባል፡፡ እውን በእርግጥ ጸጥ አድርጓቸዋልን?

በተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ የኃይል እርምጃ ወስደዋል፡፡ ሆኖም ግን ምንም የተሻሻለ ነገር የለም፡፡

በነጻ ፕሬሱ ላይ የአፈና እርምጃ ወስደዋል፡፡ ግን ምንም የተሻሻለ ነገር አልታየም፡፡

በሰላማዊ መንገድ ያመጹ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ገድለዋል፡፡ አሁንም ምንም የተሻሻለ ነገር የለም፡፡

በጋምቤላ፣ በኦጋዴን እና በሶማሊያ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽመዋል፡፡ ሆኖም ግን ምንም የመጣ ነገር የለም፡፡

በአሁኑ ጊዜ 15 ሚሊዮን የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን በረሀብ እንዲቀጡ እያደረጉ ነው፡፡ ሆኖም ግን ምንም የሆነ ነገር የለም፡፡

በአሁኑ ጊዜ ልዩ የሆነው ነገር ታዲያ ምንድን ነው?

የዘ-ህወሀት መሪዎች የህዝቡን ጥያቄ፣ ተስፋ፣ እና ህልም የመምታት የቁማር ጨዋታ በመጫወት መዝለቅ እንደሚችሉ ያምናሉ፡፡ የህዝቡን ጥያቄ ለሌላ ሳምንት፣ ወር እና ዓመት ማዘግዬት ይቻላል የሚል እምነት አላቸው፡፡

የዘ-ህወሀት መሪዎች አንድ ቀን በስልጣን መቆየትም ትልቅ ነገር አድርገው ነው የሚቆጥሩት፡፡ በስልጣን ላይ አንዲትም ቀን ቢሆን እስከቆዩ ድረስ ለዘ-ህወሀት ስበስቦች መልካም ነገር ነው፡፡

የዘ-ህወሀት የደናቁርት ስብስቦች ሆን ብለው በድንቁርና ምንም ዓይነት የተቃውሞ ነፋስ ቢነፍስ በኃይል ለመጨፍለቅ በሚያደርጉት ነገር ላይ የበለጠ ቁጣ፣ ንዴት፣ ጥልቅ ጥላቻ፣ ጥላቻ፣ ምሬት እና ሊመለስ በማይችል መልኩ የበቀል እርምጃ እየገነባ እንደሚሄድ ያለመገንዘባቸው እውነታ ነው፡፡

ምናልባትም በአሁኑ ጊዜ ያለው ተቃውሞ ሊቆም ይችል ይሆናል፣ ግን ይቆማል ብየ አላስብም፡፡

በተከታታይ በዘላቂነት ተቃዋሚዎቻቸውን እና በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን የሚገልጹትን ንጹሀን ዜጎች በመግደል ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆዩ ስትራቴጂ ነድፈው መንቀሳቀሳቸው ሁልጊዜ እነሱ በሚያስቡት መንገድ ብቻ የሚቀጥል ስለሚመስላቸው ዘ-ህወሀት አልፎ በሚሄድ የነፋስ ውሽንፍር እና ድብልቅልቁን በሚያወጣው ታላቅ የነፋስ ሞገድ መካከል ያለውን ልዩነት ማወቅ መቻል ብልህነት ነው፡፡

ዘጠነኛ፡ የዘ-ህወሀት መሪዎች የመጨረሻው ጊዜ እየቀረበ መሆኑን በማወቅ የዘረፉትን ገንዘብ በመያዝ ለመሮጥ በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡

እኔ እናውቃለን ብለው በሚያስቡት ሳይሆን በሚያውቁት መመራት አስፈላጊ እንደሆነ አምናለሁ፡፡ እናም የዘ-ህወሀት መሪዎች መጨረሻቸው መድረሱን ተገንዝበው ከህዝብ ዘርፈው ያስቀመጡት ገንዘብ ወዳለበት ሀገር በመሄድ ለመጨረሻ ጊዜ በሰላም ለመኖር ይሞክራሉ፡፡

ስለደከሙ በመስጠም ላይ ያለውን መርከብ ለማንቀሳቀስ አልቻሉም፡፡ መርከቡ ሰምጦ እያንዳንዳቸው ህይወታቸውን ከማጣታቸው በፊት ተስፋ በቆረጠ ሁኔታ ከመርከቡ ላይ በጥድፊያ በመውረድ ላይ ይገኛሉ፡፡

የዘ-ህወሀት መሪዎች፣ የእነርሱ ግብረ አበሮች እና ደጋፊዎች የመጨረሻ ምርጫቸው መሮጥ እንደሆነ ያውቃሉ፡፡

ከህዝብ የዘረፋችሁትን ገንዘብ ያዙና በሰው ልጆች ላይ ሁሉንም ዓይነት ወንጀል ሰርተው ለሚሄዱባት ሁሉ እጆቿን ዘርግታ እንኳን ደህና መጣችሁ ወደሚባልባት ምድር ወደ አሜሪካ ፈርጥጡ፡፡

በሰው ልጆች ላይ ወንጀልን ለተፈጸመባቸው የግፍ ሰለባዎች ተመልሶ እስከመጣ ድረስ የዘረፋችሁትን ገንዘብ ሁሉ ይዛችሁ ወደ አሜሪካ ፈርጥጡ፡፡

የዘ-ህወሀት የመጨረሻው ታሪክ የመፍረጠጫ ጊዜ ደረሰ፡፡ ለዘ-ህወሀት ተደቁሶ ከመቅረት መሮጥ የተሻለ ነው፡፡

አስረኛ፡ ዘ-ህወሀት የታሪኩ መጨረሻ መድረሱን ያውቃል ሆኖም ግን ታሪካቸው እንዴት መፈጸም እንዳለበት የሚያውቁት ነገር የለም፡፡ ታሪካቸው እጅግ መጥፎ በሆነ ሁኔታ እንደሚደመደም እንደሚገነዘቡ አውቃለሁ፡፡ ሰዎች የዘ-ህወሀት አምባገነናዊ ስርዓት መቼ እና እንዴት እንደሚጠናቀቅ ይጠይቁኛል፡፡

የዘ-ህወሀት የመጨረሻ ታሪክ እንዴት ወይም ደግሞ መች እንደሚጻፍ ምንም ዓይነት ሀሳብ የለኝም፡፡

የዘ-ህወሀት ታሪክ የመጨረሻው ምዕራፍ ከቀናት፣ ሳምንታት፣ ወራት ወይም ዓመታት በኋላ ሊጻፍ ይችላል፡፡ መተንበይ አልችልም፡፡ የነብይነት ኃይል የለኝም፡፡ ሆኖም ግን የማለም ኃይል ነው ያለኝ፡፡

የዘ-ህወሀት የጭቆና አገዛዝ የመጠናቀቂያው ጊዜ መሆኑን ነገ ጸሐይ ትወጣለች የማለትን ያህል እርግጠኛ ሆኘ መናገር እችላለሁ፡፡ ግን ይህንን ከእኔ አትጠብቁ፡፡

ይልቁንም ከበረከት ስምኦን እና ከአዲሱ ለገሰ ጠይቁ እና እወቁ፡፡ የዘ-ህወሀት የመጨረሻ ጊዜው የቀደረሰ መሆኑን አሳምረው ይነግሯችኋል፡፡

ማህተመ ጋንዲ በአንደ ወቅት እንዲህ ብለው ነበር፣ “በታሪክ ውስጥ ምን ጊዜም ቢሆን ለጊዜው ጨቋኞች እና ገዳዮች ይኖራሉ፡፡ ለጊዜው የማይበገሩ ኃይለኞች መስለው ይታያሉ፡፡ ሆኖም ግን በመጨረሻው ሰዓት ተንኮታኩተው ሁልጊዜ ይወድቃሉ ሁልጊዜ፡፡“

በመጨረሻ ጨቋኞች ሁልጊዜ ይወድቃሉ በሚለው እና ለጨቋኞች የታሪካቸው መጨረሻ ነው በሚለው አባባል መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?

ስለሆነም እኔ እስከሚገባኝ ድረስ ጥያቄ ሆኖ መቅረብ ያለበት ጉዳይ የዘ-ህወሀት ታሪክ በኢትዮጵያ የሚጠናቀቀው በጡጫ ወይስ ድግሞ በሹክሹክታ ነው የሚለው ነው፡፡

የዘ-ህወሀት ፍጻሜ እንደማስበው በተፈጸመ ጊዜ “ባዶ ሰዎች“ በሚል ርዕስ የተዘጋጀውን የቲ.ኤስ ኤሊዮትን የግጥም ስንኞች አዳምጣለሁ ብየ አስባለሁ፡፡

የባዶ ሰዎች እና የአዋቂ ሰዎች ዕጣ ፈንታ ዘ-ህወሀት በጡጫ ወይስ በአሾክሿኪዎች ነው የሚወድቀው ከሚለው አባባል ጋር አንድ ናቸውን?

ኤሊዮት ባዶ ሰዎች እና አዋቂ ሰዎች የሚወድቁት በጡጫ ሳይሆን በአሾክሿኪዎች ነው ብለዋል፡፡

በዘ-ህወሀት ላይ ግን ይኸ የሚሆን ለመሆኑ እርገጠኛ አይደለሁም፡፡

እሳት እና በረዶ የሚሉት የግጥም ስንኞች ለእውነታው እንደሚቀርቡ ይሰማኛል፡፡

የባዶ ሰዎች እና የአዋቂ ሰዎች የታሪክ ፍጻሜ እሳት ወይም ደግሞ በረዶ እንዳልሆነ አምናለሁ፡፡ የእነርሱ መጥፊያ ጥላቻ ነው፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ መልኩ እስቲ የፍሮስትን የግጥም ስንኞች እንደሚከተለው እንቃኝ፡

በእሳት ነው እምትጠፋ ዓለምን ይላሉ፣

የለም በበረዶ ሌሎችም ይላሉ፡፡

 

እኔ ግን ፈትሸ እንዳረጋገጥኩት፣

በበረዶ ሳይሆን ትጠፋለች በእሳት፡፡

 

ቢሆንም ግን ዓለም ሁለቴ ከጠፋች፣

በበረዶም ሳይሆን በእሳቶች ፍንካች፣

በጥላቻ ጦር ነው በሰይጣን አመልካች፡፡

 

በዘራፊነት ልዩ ሙያ የተካንኩ የአምባገነንነት ተማሪ ነኝ፡፡

ሁሉንም ዓይነት አምባገነንቶች ሁሉ እጸየፋለሁ፡፡ ከዚህም የበለጠ ደግሞ ዘራፊነትን እጸየፋለሁ፡፡

ስለአምባገነኖች እንዲህ በሚሉት የዊንስተን ቸርችል ገለጻዎች ሙሉ በሙሉ እስማማለሁ፡

“አያችኋቸው እነዚህን አምባገነኖች በወታደሮቻቸው ሳንጃዎች እና በፖሊሶች ቆመጦች ታጅበው ከምቹ ወንበሮቻቸው ላይ ተቀምጠዋል… ሆኖም ግን በልቦቻቸው ውስጥ የማይነገር ፍርሀት ታጅሏል፡፡ ቃላትን እና ሃቦችን ይፈራሉ፣ በውጭ የሚነገሩ ቃላትን እና በቤት ውስጥ የሚቀሰቀሱ ሀሳቦችን ኃይል አላቸው በማለት የሚያስፈሯው በመሆናቸው ምክንያት ይከለክላሉ፡፡ በክፍል ውስጥ ትንሽ ሀሳብ ካለ እና ትልቅ ስልጣን ያለው ቢሆንም አንኳ አይፈቀድለትም፡፡“

 

 የዘራፊ ወሮበላ አምባገነንነት የሚለውን ህልዮት “ዘራፊነት የአፍሪካ አምባገነኖች ከፍተኛው ደረጃ/Thugtatorship, the Highest Stage of African Dicatatorship“ በሚል ርዕስ ለመጀመሪያ ጊዜ ሀሳቡን ያቀረብኩት እኔ እንደሆንኩ አምናለሁ፡፡

ለአብዛኞቹ አምባገነኖች ታሪክ ፍጻሜ የሚሆነው በሌላ አምባገነን በመፈንቅለ መንግስት ሲተኩ ብቻ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ድሀረ አምባገነን አገዛዞች የዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ባህሪ ያላቸው በመምሰል ለቃሉ አዲስ ስያሜ በመፍጠር በአሜሪካ በተለይ እና በምዕራቡ ዓለም በአጠቃላይ በመቀባት ህጋዊነትን በማላበስ አዲስ አገዛዛቸውን ይጀምራሉ፡፡

የአፍሪካ አምባገነኖች በወታደራዊ ኃይል በመደገፍ በሌላ አምባገነን እየተተኩ በአሁጉሩ ከስድስት አስርት ዓመታት በላይ ዘልቀው ይገኛሉ፡፡

እ.ኤ.አ በ1946 እና በ2004 መካከል በአፍሪካ ወደ 400 አካባቢ የሚጠጉ መፈንቅለ መንግስቶች ተካሂደዋል፡፡ በዚህ ጊዜ በጣም ጥቂት የሆኑ እውነተኛ ዴሞክራሲያዊነትን በተላበሰ መልኩ ሰላማዊ ሽግግር ተደርገዋል፡፡

በአፍሪካ አምባገነኖች የሚካሄዱ አብዛኞች ዴሞክራሲያዊ ምርጫዎች እየተባሉ የሚጠሩት ምርጫዎች በሸፍጥ የታጀቡ እና በውስጥ ለውስጥ በኃይል በታጀበ ጡንቻ እየተነጠቁ ለአምባገነኖቹ ስልጣን ጥቅም ሲውሉ ይታያሉ፡፡

ጥቂት የአፍሪካ ምርጫዎች ከፍተኛ የሆነ ሸፍጥ እየተደረገባቸው በአገዛዝ ላይ ያለው ገዥ አካል ስልጣንን በኃይል የሚይዝበት አስደናቂ አጋጣሚ በመሆን ምንም ዓይነት ፋይዳ ሳይፈይድ ሲቀር ይስተዋላል፡፡

እ.ኤ.አ ግንቦት 2015 ተደርጎ በነበረው የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ ዘ-ህወሀት መቶ በመቶ በማሸነፍ የፓርላማውን ወንበሮች ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን አወጀ፡፡

በኢትዮጵያ ህዝብ ቁስል ላይ እንጨት መስደድ እንዲሉ ዘ-ህወት ባራክ ኦባማ የተባለውን አስመሳይ ቀጣፊ በሙስና ወደተጨማለቀው እና የሸፍጥ ጓዳቸው እንዲመጣ በመጋበዝ እርሱም ህሊናውን ሸጦ እውነቱን እያወቀ ሀሰትን በማንገስ መቶ በመቶ በዘ-ህወሀት አሸናፊነት የተጠናቀቀው ምርጫ መቶ በመቶ ዴሞክራሲያዊ ነው በማለት እንደ አቡጀዲ በመቀደድ ወደ ሀገሩ ተመልሷል፡፡

“ኃይልን በመጠቀም መንግስትን ለማስወገድ የሚሞክሩትን ቡድኖች በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠውን የኢትዮጵያን መንግስት ጨምሮ በጥብቅ እንቃወማለን“ በማለት ኦቦማ ጋዜጣዊ መግለጫ ከመስጠቱ በፊት ዘ-ህወሀት ሸፍጡን በማዘጋጀት ኦባማን ያታለለው በመሆኑ አሁንም የሚያስገርመኝ ነገር ነው፡፡

ባራክ ኦባማ በአፍሪካ ምህረት የለሽ ወሮበላ የዘራፊ አምባገነኖቹ መካከል ቆሞ “የኢትዮጵያ መንግስት ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ የተመረጠ መንግስት ነው“ ብሎ ከተናገረባት ቀን የበለጠ በኦባማ ላይ ያፈርኩበት ቀን እስከ አሁን ድረስ በፍጹም የለም፡፡

አንድ ወሳኝ ክስተት በመጣ ጊዜ ከስተቱን እራሱን እኔው እወስነዋለሁ ወይም ደግሞ ክስተቱ እራሱ እኔን ይወስነኛል የሚለውን ነገር ቀደም ሲል ትምህርት አግኝቸበታለሁ፡፡

እ.ኤ.አ በ2009 ኦባማ በጋና አክራ ላይ በመገኘት ለአፍሪካ ህዝቦች እንዲህ የሚል መልዕክት አስተላልፎ ነበር፣ “አፍሪካ ጠንካራ ሰዎችን አትፈልግም፣ ይልቁንም አፍሪካ የምትፈልገው ጠንካራ ተቋማትን ነው፡፡“ በዚያው ቀን ባራክ ኦባማ ክስተቱን ወስኗል፡፡

እ.ኤ.አ ሀምሌ 2015 ባራክ ኦባማ በአዲስ አበባ ከተማ በመገኘት ከወሮበላ ዘራፊዎች ጋር ትከሻ ለትከሻ ተቃቅፎ በመቆም መቶ በመቶ የምርጫ ውጤት እየተባለ ለሚጠራው የሸፍጥ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ ነው በማለት ቅጥፈት ተናግሯል፡፡ በዚያው ዕለት ባራክ ኦባማ ክስተቱ እራሱ ኦባማን ወስኖታል፡፡ እንግዲህ ኦባማ በዚህ ዓይነት ሁኔታ ነው ከክብር ወርዶ በቅሌት ምንጣፍ ላይ በመንከባለል ላይ ያለው!

ለአምባገነናዊነት መጨረሻ ማስረጃው ትንሽ ነው ሆኖም ግን ዘራፊ ወሮበላነት በተለየ መልኩ ከተለምዶው ተራ አምባገነንነት ሊጠናቀቅ እንደሚችል አምናለሁ፡፡

ለወሮበላ ዘራፊ አምባገነንነት ታሪክ መጨረሻ በህብረተሰቡ ላይ ከፍተኛ ዋጋ ሊያስከፍል የሚያስችልን ኪሳራ በመያዝ ማቀጣጠል እና ለፍጻሜ ማብቃት ይቻላል የሚል እምነት አለኝ፡፡

የዘ-ህወሀት የፍጻሜ ታሪክ እንዴት እና መቸ እንደሚነገር የማውቀው ነገር የለም፡፡

በድረ ገጼ በኩራት በጽናት እንደማቀርበው ሁሉ በስልጣን ላይ ላሉት እውነት ተናገሩ/Speak truth to power የሚለው ይገልጻል፡፡ ይህም ማለት ስልጣናቸውን ከሕግ አግባብ ውጭ የሚጠቀሙትን እና ኃይል አምላኪዎችን ሁሉ ያጠቃልላል፡፡

እውነት እናገራለሁ፡፡ ትረካዎችን አላወራም፡፡

በአሁኑ ጊዜ የዘ-ህወሀትን ታሪክ ፍጻሜ መናገር የለብኝም፡፡

በአሁኑ ጊዜ ለ-ዘህወሀት እውነታውን መናገር የለብኝም፡፡

በአሁኑ ጊዜ ለዘ-ህወሀት እውነተኛውን ነገር መናገር አለብኝ፡፡

በአሁኑ ጊዜ ሁለት የዘ-ህወሀት ሁለት እውነት ተናጋሪዎች እንደተናገሩት ሁሉ እኔም ለዘ-ህወሀት እውነት እናገራለሁ፡፡

በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ህዝቦች እንዲህ ከሚለው እውነታውን ከፈረሱ አፍ (ከጅቡ አፍ አላልኩም) መስማት እንዲችሉ እወዳለሁ፡

“አሁን ካለንበት ነባራዊ ሁኔታ አንጻር ስንመለከተው ነገሮች ሁሉ ከእጆቻችን እየወጡ ነው፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ምንም ዓይነት ጥያቄ የሚያስነሳ አይደለም፡፡ ይህንንም የመምህራን ድርጀቶች ምን እየሰሩ እንዳሉ በግልጽ ልንመለከት እንችላለን፡፡ ሁለት ሶስተኛ የሚሆነው የትምህርት ሰው የእኛ ፓርቲ አባል ቢሆንም ከዚህ በተጻረረ መልኩ እኛን በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ላይ የሚገኙ ሲሆን ይህም የታሪኩን ፍጻሜ ያመላክታል፡፡”

አሜን!

እኔ በግሌ በኢትዮጵያ ውስጥ የዘ-ህወሀት ፍጻሜ የመጨረሻው ነው ብየ አላስብም፡፡

ይልቁንም በኢትዮጵያ ውስጥ የዘ-ህወሀት ፍጻሜ የመጀመሪያው ነው ብየ አላስብም፡፡

ሆኖም ግን በኢትዮጵያ ውስጥ የዘ-ህወሀት ፍጻሜ የመጀመሪያው መጨረሻ ነው ብየ አስባለሁ፡፡

የታሪኩ ፍጻሜ ይቀጥላል…

 

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

ታህሳስ 19 ቀን 2008 ዓ.ም

 

Similar Posts