ኢትዮጵያ፡ በሰላማዊ መንገድ ለውጥ እንዲመጣ ያልፈቀደ በኃይል ለውጥን እንዲቀበል ይገዳዳል!

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም   

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ 

Mourners of T-TPLF Massacre Victims 12 2015
Mourners of T-TPLF Massacre Victims 12 2015

.. ታህሳስ 2015 በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ አእምሮ ውስጥ ታላቅ ስፍራን በመያዝ እየተብላላ ያለ አንድ ጥያቄ ብቻ አለ፡፡ 

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ (ህወሀት) የኢትዮጵያን ህዝቦች በዘፈቀደ በመግደል፣ እልቂትን በመፈጸም፣ በማረድ፣ ሰላማዊ ህዝቦችን በጅምላ በመፍጀት እና እልቂትን እና አካለ ጎደሎ የማድረግ ዘመቻውን አጠናክሮ በመቀጠል ላይ ያለው በስልጣን ኮርቻ ላይ ዘላለም እንደ መዥገር ተጣብቆ ለመኖር ስለሚፈልግ ነውን? 

አሳዛኝ በሆነ መልኩ የዚህ ጥያቄ ምልሽ አዎንታዊ ነው፡፡ አዎ እንደ መዥገር በስልጣን እርካብ ላይ ተጣብቆ ህዝቦችን እያተራመሰ ሲገዛ ለመኖር ነው! 

ላለፉት 24 ዓመታት ህወሀት በሀገሪቱ ውስጥ ሰላማዊ ሽግግር ለማድረግ መልካም አጋጣሚን አግኝቶ ነበር፡፡ 

ህወሀት በእያንዳንዷ የሰላም እና እርቀሰላም የድርድር መድረክ፣ በእያንዳንዷ የፖለቲካ ተሳትፎ እና መስተጋብር፣ በእያንዳንዷ የዴሞክራሲያዊ ሂደቱን የማጠማዘዝ እና ምርጫውን በሸፍጥ በታጀበ ድል አድራጊነት አሸነፍኩ እያለ በማወጅ በህዝብ ላይ ሸፍቶ እልቂትን እየደገሰ ህዝቦችን በመግደል መኖርን በመምረጡ ምክንያት እንጅ ሰላማዊ የሽግግር ለውጥ ለማምጣት የሚያስችሉትን መልካም አጋጣሚዎች ሁሉ ያጣበት አጋጣሚ አልነበረም፡፡ 

ላለፉት 24 ዓመታት ህወሀት በኢትዮጵያ ውስጥ ሰላማዊ የሽግግር ለውጥ እንዳይመጣ አሻፈረኝ በማለት ህዝቦችን እንደ ቄራ በሬ እያረደ ሞገደኛነቱን አጠናክሮ ቀጥሎበት ይገኛል፡፡ 

በአሁኑ ጊዜ ህወሀት ህዝባዊ እምቢተኝነትን በኃይል ለመቀበል የሚገደድበት እና የቱንም ያህል ሰላማዊ ህዝቦችን ቢገድል፣ ቢፈጅ እና እንደ አበደ ውሻ ከወዲያ ወዲህ ቢቅበዘበዝ ከለውጡ አይቀሬነት እና ከህዝቡ የትግል መንፈስ አይበገሬነት ሊያመልጥ እንደማይችል በዓይኑ በብረቱ እየተመለከተ ነው፡፡ ህዝባዊ ማዕበል ዓይኑን አፍጥጦ እየመጣበት ነው! እራሱ ሰላማዊ ዜጎችን በህዝብ ገንዘብ በተገዛ ጥይት በግንባራቸው እና በደረታቸው ላይ እያነጣጠረ እየገደለ እና እልቂትን እየፈጸመ ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሀል እንዲሉ በዚሁ በተለመደው አደንቋሪ ቅጥፈቱ ለህዝቦች ህልፈት ምክንያት የሆኑት ጸረ ሰላም እና ጸረ ልማት ኃይሎች ስለሆኑ ህዝቡ እነርሱን አሳልፎ እንዲሰጥ በማለት ህዝቡን እያስገደደ በካድሬዎቹ እና በእበላ ባይ ምሁራን ተብየዎች እንዲሁም በኢኮኖሚያዊ ጥቅም በተገዙ እበላባይ የደናቁርት ስብስብ አንደበት አማካይነት እንደበቀቀን እያስጮኸ የስብሰባ መድረኮችን በየከተማው እና በየቀበሌው እያዘጋጀ በህዝብ ግብር የሚተዳደሩትን የመገናኛ ብዙሀን አጨናንቆ ይገኛል፡፡ የሞኝ ዘፈን ሁልጊዜ አበባዬ እና የቂል ለቅሶ መልሶ መላልሶ እንደሚባለው ህወሀት የህዝቡን ነባራዊ የትግል ወኔ እና አይበገሬነት ወደ ጎን አሽቀንጥሮ በመጣል አሁንም ደግሞ እና ደጋግሞ ድብቅ አጀንዳ ያላቸው ጸረ ሰላም እና ጸረ ልማት ኃይሎች የቆቀሰቆሱት አመጽ ነው በማለት ህዝቡን ለማደናገር እና ከተቀጣጠለው የአመጽ ማዕበል ለማዘናጋት የቅጥፍና ድርጊቱን በማራመድ ላይ ይገኛል፡፡ 

.. ታህሳስ 2015 የኢትዮጵያ ህዝቦች በሰላማዊ የለውጥ ሽግግር እና በአመጽ ኃይል መካከል ያለውን መስመር ተራምደውት አልፈዋል፡፡ 

.. ታህሳስ 2015 የኢትዮጵያ ህዝብ የለውጥ ማዕበሉ ሊቀለበስ የማይችልበትን መስመር ተሻግሮ ለወሳኙ ድል በመገስገስ ላይ ይገኛል፡፡ 

በአሁኑ ጊዜ የለውጥ ሂደቱ ሊቀለበስ የማይችልበትን መስመር ተሻግሮ የመሄዱን እውነታ በግልጽ የሚያመላክተው ህዝቡ ማንንም ሳይሆን የእራሱን በሙስና የተዘፈቁ ነቀዞች እና ገዳይ መሪዎቹን፣ የጥፋት ግብረ አበሮቹን እና ታዛዥ ሎሌዎቹን ብቻ በሚወክለው ህወሀት በሚባለው ወንጀለኛ ድርጅት ላይ ያለውን ጥላቻ በግልጽ እና በአደባባይ በማሳየት ላይ የመገኘቱ ሁኔታ ነው፡፡ 

በአሁኑ ጊዜ የለውጥ ሂደቱ ሊቀለበስ የማይችልበትን መስመር ተሻግሮ የመሄዱን እውነታ በግልጽ የሚያመላክተው የኢትዮጵያ ህዝብ ህወሀትን የሚፈራበት ሁኔታ ጭራሽ የማይታይ የመሆኑ ሁኔታ ነው፡፡ 

ህወሀት የሚባለው ቅጥር የነፍሰ ገዳይ ወሮበላ ስብስብ በዓለም አቀፍ ለጋሽ እና አበዳሪ ድርጅቶች ጉያ ውስጥ ተወሽቆ ያለ እና እስከ አፍንጫው በኢትዮጵያ ህዝብ አንጡራ ሀብት የተገዛ የጦር መሳሪያ ታጥቆ የሚገኝ እና በአንበሳዎቹ መካከል እያሽካኩ እንደሚገኙ የጅብ መንጋዎች ዓይነት መሆኑን የአንበሳ ልብን የተጎናጸፈው የኢትዮጵያ ህዝብ አሳምሮ ያውቃል፡፡ 

በአሁኑ ጊዜ ህዝቡ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ደፍሮ በአደባባይ በመውጣት በዘህወሀት ላይ ያለውን እምቢተኝነት በግልጽ እና በማያሻማ መልኩ በማሳየት ላይ ይገኛል፡፡ 

ህዝቡ በሀገሪቱ ውስጥ በግልጽ ፍጹም የሆነ መዋቅራዊ ለውጥ እንዲደረግ በመጠየቅ ላይ ይገኛል፡፡ 

በአሁኑ ጊዜ ህዝቡ ህወሀት የሚባለው በህዝቦች ደም የተጨማለቀ ቅጥር ነፍሰ ገዳይ ወሮበላ የወንጀለኛ ድርጅት በህዝቦች ጫንቃ ላይ እንደ መዥገር ተጣብቆ ከሚገኝበት ስልጣኑ በአስቸኳይ እንዲወገድ በመቀስቀስ እና ከፍተኛ የሆነ እንቅስቃሴ በማድረግ በግልጽ በመጠየቅ ላይ ይገኛል፡፡ 

በአሁኑ ጊዜ የለውጡ ሂደት ሊቀለበስ ከማይችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን የሚያመላክተው እውነታ ህዝቡ ህወሀት የተባለው ወንጀለኛ ድርጅት በማንኛውም መንገድ በየትኛውም የትግል አማራጭ ከሚያመልከው ስልጣኑ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ ላይ መወገድ አለበት ብሎ የተነሳ መሆኑን በግልጽ መመልከት በመቻሉ ነው፡፡ 

ህወሀት የተቀመጠበት በሰዓት የተሞላ ፈንጅ ባሩድ/ደማሚት በርሜል ላይ ፊዩዝ (ምላጭ) አሳት አየተቀጣጠለ መፈንዳት ብርሀን በማሳየት ላይ ይገኛል፡፡ በጣም አጭር የሆነች የማፈንጃ ፊዩዝ ናት፡፡ ጥያቄ ሆኖ የሚነሳው ይህች የመተኮሻ ፊዩዝ በባሩድ የተሞላውን የፈንጅ ሳጥን እሳት የምትለኩስበት ሰዓት መቸ ነው የሚለው ብቻ ነው፡፡ 

ህወሀት 25 ዓመታት ያህል በኢትዮጵያ ህዝቦች ልብ ውስጥ የሚነድ እሳትን ሲለኩስ እና ሲያቀጣጥል ቆይቷል፡፡ 

በአሁኑ ጊዜ ህወሀት በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን የሚያሰሙትን ህጻናትን እና ወጣቶችን እንዲሁም ሴቶችን እና አዛውንቶችን በመጨፍጨፍ፣ በመግደል እና በማሰቃየት እንደ ቋያ እሳት በመቀጣጠል ላይ ያለውን አመጽ ለመጨፍለቅ የሚችል መስሎ ይታየዋል፡፡ 

ህወሀት በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ ውስጥ እንደ ቋያ እሳት ከዳር እስከ ዳር የተቀጣጠለውን የአመጽ እንቅስቃሴ በፍጥነት እና አሁኑኑ በማጥፋት፣ ነገ፣ በሚቀጥለው ሳምንት እና በቀጣዩ ዓመት የሚነሳውን ህዝባዊ አመጽ በሙሉ የሚያጠፋው መስሎ ይሰማዋል፡፡ 

ባለፈው ሳምንት ሂዩማን ራይትስ ዎች የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት እንዲህ የሚል ዘገባ አውጥቷል፡ 

ፖሊስ እና ወታደራዊ ኃይሎች በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ ጥይቶችን በመተኮስ ቢያንስ 75 ሰላማዊ ሰልፈኞችን የገደሉ ሲሆን ሌሎች በርካታዎችን ደግሞ ቁስለኛ እንዲሆኑ አድርገዋልኦሮሞዎች ባደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ የመንግስት ምላሽ በዜጎች ላይ በመተኮስ እልቂትን መፈጸም ሆኗል፡፡ መንግስት ሰላማዊ የሆነውን ሰልፍአሸባሪዎችየጠነሰሱት የሚል ፍረጃ በመስጠት ከፍተኛ የሆነ ወታደራዊ ኃይል በማሰማራት እያጸመው ያለው ግድያ እና የኃይል እንቅስቃሴ ይህንን በቋፍ ላይ ያለን ሁኔታ ወዳልተጠበቀ እና ከፍተኛ ወደሆነ አደገኛ ሁኔታ ሊወስደው ይችላል፡፡

እንደዚሁም ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ መልኩ እንዲህ የሚል ዘገባ አውጥቷል፡ 

40 ሰዎች እልቂት ምክንያት ለሆነው እና ሰላማዊ አመጸኞችን በመጨቆን መሬትን በኃይል ለመያዝ መንግስት እያደረገ ያለውን ድርጊት በመቃወም ወደ አደባባይ የወጡ ሰላማዊ ሰልፈኞች በኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣኖች አሸባሪዎች ተብለው ተፈርጀዋል፡፡

በሀገር ውስጥ እየታተመ የሚወጣው አዲስ ፎርቹን እየተባለ የሚጠራው ሳምንታዊ ጋዜጣ በበኩሉ እንዲህ የሚል ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል፡

በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን በሚያሰሙ የዩኒቨርስቲ ወይም ደግሞ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ጠብመንጃ ተኩሶ መግደል መፍትሄ ሊሆን አይችልም፡፡ በአሁኑ ጊዜ በቋፍ ላይ ያለውን ሁኔታ የበለጠ ያባብሰዋል፣ እናም በሀገሪቱ ውስጥ ባለው የጸጥታ ሁኔታ ላይ አሉታዊ እንደምታ ሊያሳርፍ ይችላል፡፡ ህይወታቸውን ላጡት ሰላማዊ ዜጎች ከህዝቡ ጋር በመቀራረብ ለመነጋገር እና ሁኔታውን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ጥረት የማይደግ ከሆነ የአሁኑ ብቻ ሳይሆን ከዓመት በፊት በተመሳሳይ መልኩ ወገኖቻቸው የተገደሉባቸውን ዜጎች ስሜት እንደገና በመቀስቀስ ሌላ መዘዝ ሊያስከትል ይችላል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የመንግስት መምሪያ ከፍተኛ ተጽእኖ ያለውን እና እንዲህ የሚለውን መግለጫ አውጥቷል፡ 

ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ በኦሮሚያ ክልል ዜጎች በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን ባሰሙበት ጊዜ ለበርካታ ዜጎች ህይወት መጥፋት ምክንያት የሆነው ጉዳይ እጅግ ያሳስባታል፡፡ በተደረገው ግድያ እጅግ በጣም እናዝናለን፡፡ እንዲሁም በዚህ ድርጊት ህይወታቸውን ላጡት ዜጎች ቤተሰቦች የተሰማንን ሀዘን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ሰላማዊ ተቃውሞን እንዲፈቅድ እና ሕጋዊ ጥያቄውን በመቀበል ተቀራርቦ በመወያየት ቅሬታዎችን እንዲፈታ እንጠይቃለን 

የቀድሞው የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ዋና ጸሀፊ የነበሩት እና .. 1991 በለንደን ተደርጎ በነበረው የድርድር ኮንፈረንስ ላይ ህወሀት አዲስ አበባ በመግባት ስርዓት እንዲያስከብር በማለት አሁን የሙጥኝ ብሎት ለሚገኘው ስልጣን ያበቁት ኸርማን ኮሆን በአሁኑ ጊዜ ህወሀት የጦር መሳሪያ ባልታጠቁ ኢትዮጵያውን ዜጎች ላይ እያደረሰ ያለው እልቂት እንቆቅልሽ እንደሆነባቸው እንዲህ በማለት ግልጽ አድርገዋል፡ 

የኢትዮጵያ መንግስት የፖለቲካ አመራሮች በእነርሱ ላይ ተቃውሞ ለማሰማት ወደ አደባባይ መንገዶች በሚወጡ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ግድያ የመፈጸም ፖሊሲን ያራምዳሉ፡፡ ሌሎች መግለጫ በመስጠት ተቃውሞ የሚያሰሙትን እና ሆኖም ግን ሰላማዊ ሰልፍ የማያደርጉትን ዜጎች ደግሞ ለብዙ ጊዚያት ለሚቆይ እስራት ወደ ዘብጥያ ይወረውሯቸዋል፡፡ በኢትዮጵያ ላይ ያለው አገዛዝ በእራሱ ዜጎች ላይ እጅግ በጣም ጥብቅ የሆነ ቁጥጥር ማደርግን እና በየጊዜው እንደዚህ ያለ ግድያ ለምን እንደሚፈጽም ሊገባኝ አልቻለም፡፡ መንግስት በመሰረተ ልማት እና በግብርናው ዘርፍ ላይ እያደረገ ባለው የመውዕለ ንዋይ ፍሰት የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በአዎንታዊነት መልኩ ይመለከተዋል፡፡ እያደረገ ያለውን ከፍተኛ የሆነ ቁጥጥር ዘና ቢያደርገው እና እንዲላላ የሚያደርግ ቢሆን ኖሮ በህዝቦች ዘንድ ታዋቂነትን ያተርፍ ነበር፡፡ ከምንም ጥርጣሬ በላይ በቀረቡት እውነታዎች ላይ ፊት ለፊት እንጋፈጥ!

በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን ለመግለጽ ወደ አደባባይ በወጡ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ምላጭን በመሳብ እልቂት እና ግድያን መፈጸም የዘህወሀት የሁልጊዜ መገለጫው ነው፡፡ 

ህወሀት .. 2005 ተደርጎ ነበረበረው የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ ወደ 1000 የሚጠጉ ወገኖቻችንን በአደባባይ ገድሏል አቅሱሏል ፡፡

ህወሀት .. 2004 በጋምቤላ ክልል የሚገኙ የአኙዋክ ብሄረሰብ አባላት የሆኑትን 400 ወገኖቻችንን በጥይት እየቆላ በጊሬደር በተቆፈረ በአንድ ጉድጓድ ውስጥ እንዲቀበሩ አድርጓል፡፡ 

ህወሀት .. 2007/08 በሶማሊ ክልል በኦጋዴን አካባቢ በአስርት የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን በጥይት እየረፈረፈ እልቂት ፈጽሞባቸዋል፡፡ 

ህወሀት .. 2006-2009 ድረስ ባሉት ዓመታት ውስጥ የሰውን ሀገር ሉዓላዊ ድንበር ጥሶ በመግባት 10 ሺዎች የሚቆጠሩ ሶማሌያውያን ዜጎች ላይ ግድያ ፈጽሟል፡፡ ይህ የእብሪት ወረራ እና ግድያ ለመጭው የኢትዮጵያ ትውልድ የማይድን ጥቁር አሻራ ጥሎ ከማለፉም በላይ የአረቡ ዓለም በኢትዮጵያ ላይ ቂም በመቋጠር በየዘመኑ ጥቃቱን ሲሰነዝር እንዲኖር የሚያደርግ ዕኩይ የሰይጣን ድርጊት መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ 

ህወሀት .. 1991 ስልጣንን ከተቆጣጠረ ጀምሮ በኢትዮጵያ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ውስጥ በሚኖሩ 10 ሺህ በላይ በሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ላይ የግድያ እልቂትን ፈጽሟል፡፡ 

ውልደቱ እና ተፈጥሯዊ ባህሪው ስለሆነ የዘህወሀት የግድያ አባዜ ለማንም ሰው ቢሆን የሚያስገርም ነገር አይሆንም፡፡ 

በአሁኑጊዜ የዘህወሀት መሪዎች ወታደራዊ ዩኒፎርሞቻቸውን በመልበስ ሌሎችንም የማስመሰያ ድርጊቶችን ሁሉ በማድረግ በሰለጠነው የኢትዮጵያ ህዝብ መካከል ተሰግስገው ይገኛሉ፡፡ ወገኖች እባካችሁ ይህንን ማስመሰያቸውን እና የኒፎርሞቻቸውን በሙሉ አስወልቋቸው! ሸክስፒር በግልጽ እንዳስቀመጡት እነዚህ የዕኩይ ምግባር ባለቤቶች እዚህ ቆመው ያሉት የህዝቦችን ጉሮሮ ለማነቅ ነው፡፡ 

ህወሀት በህዝቦች ደም ጨቅይቶ የተጸነሰ ደም መጣጭ አጋንንት ድርጅት ነው፡፡ 

ህወሀት በእልቂት የተፈጠረ ቀንዳም የሆነ ሰይጣናዊ ደም አፍሻሽ ድርጅት ነው፡፡ 

ህወሀት የህዝብ እልቂትን ደም በማፍሰስ በመፈጸም የሚኖር እና የሚጥር ዕኩይ ድርጅት ነው፡፡ 

ብቸኛ ሆኖ ሊቀርብ የሚችለው ጥያቄ ግን ህወሀት እርሱም እራሱ በደም እልቂት ይጠፋል ወይስ አይጠፋም የሚለው ነው፡፡ 

የዘህወሀት መሪዎች፣ ግብረ አበሮች እና ከስር ያሉ መጋቢ ሞተ ለሆዱ ሙሰኛ አለቅላቂ ምሁራን ተብዬዎች በአሁኑ ጊዜ እየተደረገ ባለው ህዝባዊ አመጽ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ውስጥ ፈርተው እና ተሸማቅቀው ወኔ ከድቷቸው ይገኛሉ፡፡ እነዚህ የህዝብ ጠላቶች ለመጨረሻ ጊዜ በአስከፊ የፍርሀት ቆፈን ውስጥ ተወሽቀው የተገኙበት ጊዜ ቢኖር የአለቆች ሁሉ አለቃ የነበረው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ .. 2012 እንደ ጧት ጤዛ ከጎናቸው ብን ብሎ የጠፋ ጊዜ ነበር፡፡ 

በአሁኑ ጊዜ እየተካሄደ ላለው ህዝባዊ አመጽ ዋና መነሻ ሆኖ የቀረበው ከሀገሪቱ መናገሻ ከተማ ዳርቻ በሁሉም አቅጣጫዎች የሚገኘውን የኦሮሚያ መሬት በመውረር እና በመቀራመት በሚሊዮኖች ብር እየቸበቸቡ ለማይሞው ኪሳቸው ለመዝረፍ በማሰብ የተዘጋጀው የዘህወሀት እርባና ቢስ የአዲስ አበባ የተቀናጀ ማስተር ፕላን የተባለው ስልት ነው፡፡ (በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን እና የአዲስ አበባ የተቀናጀ ማስተር ፕላን እየተባለ የሚጠራውን የሸፍጥ ሰነድ እዚህ በመጫን ማንበብ ይችላሉ፡፡) 

የመወሰን አቅም የለሹ የዘህወሀት የይስሙላው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ለዚህ ተቃውሞ ዋና አንቀሳቃሹ ድብቅ አጀንዳ ያላቸው የውጭ ኃይሎች ናቸው በማለት እንዲህ የሚል አደንቋሪ ዋይታውን አሰምቷል፡ 

ይህንን አመጽ ከፊት እና ከኋላ በመሆን በማደራጀት በርካታ የሆነ የመንግስት እና የሕዝብ ሀብት እንዲቃጠል ያደረጉት ከውጭ የሚገኙት ጸረ ልማት ኃይሎች ናቸው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የመንግስት ታጣቂ ኃይሎች እንደተገደሉ እና በጸጥታ ኃይሎች እና በህዝቡ ላይ ጉዳት እንደደረሰባቸው አይተናል፡፡ እንደዚህ ያለው ሁኔታ በምንም ዓይነት መልኩ ሊቀጥል አይችልም፡፡ እኛ ከህዝቡ ጋር በመተባበር በአካባቢዎች ላይ መረጋጋት እንዳይፈጠር በሚንቀሳቀሱት ጸረ ሰላም ኃይሎች ላይ ምንም ዓይነት ምህረት የማይደረግለት ሕጋዊ እርምጃ እንደምንወስድ መልዕክት ማስተላለፍ እፈልጋለሁ በማለት ዝቷል፡፡ 

ድንቄምምህረት የማይደረግለት ሕጋዊ እርምጃ!” 

መቸም ወያኔ እና ሎሌዎቹ የሚነግሩን ሁሉ የተገላቢጦሽ ነውና ይልቁንም ኃይለማርያምምህረት የማይደረግለት ግድያእንፈጽማለን ማለቱ ነውን? ለመሆኑ ይህን ያህል ሰላማዊ ዜጋ (የትምህርት ቤት እምቦቀቅላዎች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች እና አዛውንቶች) በጥይት እየተቆሉ በመገደል ላይ ያሉት በየትኛው የሕገ መንግስት ሰነድ እና የሕግ አንቀጽ እንደሆነ የዘህወሀት የይስሙላው ጠቅላይ ሚኒስትር ያውቀው እና ይጠቅስልን ይሆን? 

ለስሙ የፕሮቴስታንት ኃይማኖት እምነት ተከታዩ ኃይለማርያም ቅዱሱ መጽሐፍ ሰው አትግደል፣ ጠላትህን እንደራስህ አድርገህ ውደድ የሚለውን አምላካዊ ቃል ወደ አራት ኪሎ ቤተመንግስት ስትገባ በካራቴ መትተህ ስለጣልከው ነው ይህንን የእብሪት ቃል የምትናገረው፡፡ የዘህወሀት የይስሙላው ጠቅላይ ሚስትር ኃይለማርያም የኃይማኖቱን ጉዳይስ ተወው አንዴ ስልጣንን ስትወድ እና የዘህወሀት ታማኝ አገልጋይ ሎሌ ሆነህ ስትሰየም ቀንዳሙ ሰይጣን ተፈናጥጦብሀልና፡፡ 

እንዲያው ለመሆኑ የይስሙላ ሕጋችሁን እንኳ ለይስሙላ እንኳ ለመናገር ድፍረቱ ቢኖርህ በሰላማዊ መንገድ ቅሬታቸውን ወደ አደባባይ በመውጣት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና ለኢትዮጵያውያን ወገኖቻቸው ለማሰማት ሰላማዊ ሰልፍ የወጡትን ዜጎች በጠራራ ጸሐይ ከግንባራቸው እና ከደረታቸው ላይ በማነጣጠር እልቂትን በፈጸሙ ቅጥር ነፍሰ ገዳዮች ላይ ነው ሕጋዊ እርምጃ መወሰድ ያለበት ወይስ ደግሞ መብቴ ይከበር፣ ይህንን ድርጊት እቃወማለሁ ባለ ዜጋ ላይ ነው? የኃማኖቱን ነገር ተወው እና በዓለማዊው ሕግም ቢሆን እንኳን መብቴ ይከበር ብሎ የጠየቅን ሰላማዊ ህዝብ ይቅርና ህዝብ በስሜት ተነሳስቶ ግድያ ቢፈጽምም እንኳ ለሕግ ይቀርባል እንጅ ግደል የሚል ሕግ የለም፡፡ ግን በሕገ መንግስት ሰነዱ ላይ እንጅ በዘህወት ላይ ይኸ ነገር አይሰራም እንደምትለን ጥርጥር የለውም፡፡ 

ኃይለማርያም እና የእርሱ ህወሀት ጌቶቹ ፍጹም በሆነ መልኩ ምህረት የለሽ እርምጃ የመውሰድ ብቃቱ አላቸው፡፡ ሆኖም ግን በምንም ዓይነት ሁኔታ ሕጋዊ እርምጃ የመውሰድ ብቃቱ የላቸውም፣ ምክንያቱምከሕግ የበላይነትጋር በፍጹም አይተዋወቁምና ነው፡፡ 

ኃይለማርያም እና የዘህወሀት ጌቶቹበህግ የበላይነትእናበወሮበሎች የሕግ የበላይነትመካከል ያለው ልዩነት ተምታቶባቸዋል! 

ኃይለማርያም በዘህወሀት ጌቶቹ እንዲህ የሚለውን ነገር እንዲናገር ተነግሮታል፡ህወሀት በስልጣኑ ላይ ለመቆየት የትኛውንም ዓይነት እርምጃ በመውሰድ ተቃዋሚዎቹን እና ሰላማዊ ሰልፍ አድራጊዎቹን ያለምንም ምህረት ይገድላል፡፡ 

ህወሀት በተቃዋሚዎቻቸው ላይ ምህረት የለሽ ዲያብሎሳዊ እርምጃ እንደሚወስዱ የሚያጠያይቅ ጉዳይ አይደለም፡፡ የሸክስፒርን አባባል በመዋስገሀነም ባዶውን ቀርቷል ምክንያቱም ሁሉም ሰይጣኖች ከዘህወሀት ጋር ተቀላቅለዋልና!” 

ሌላው የዘህወሀት ተቀጣሪ አወናባጅ የሆነው እና ለንደን የሚኖረው በስም አብይ ብርሀኔ በሚል የሚጠራው እንደ ኃይለማርያም ሁሉ ተመሳሳይ የገደል ማሚቶውን እንዲህ በማለት አሰምቷል፣በኦሮሚያ ክልል በአንዳንድ አካባቢዎች የተቀሰቀሰው አመጽ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ሕገ መንግስታዊ ስርዓት በኃይል ለመናድ መሰረታቸውን በውጭ ያደረጉ ተቃዋሚ ቡድኖች ያደረጉት እንቅስቃሴ ነው፡፡ 

ሌላው በሞራል ስብዕና የዘቀጠው እና የዘህወሀት የአሻሻጭነት ሰራተኛ ስብዕናን ተላብሶ እንደ በቀቀን እና ዛር እንደያዘው በሽተኛ እየተንተባተበ የሚለፈልፈው በስም ጌታቸው ረዳ የተባለው ሎሌ ካድሬ እንዲህ የሚል ዲስኩር አሰምቷል፣የችግሮቹ ዋና ምክንያት በከተማዋ መስፋፋት ጉዳይ ላይ ከህዝብ ጋር ምክክር ለማድረግ ጥረት እያደረገ ያለውን ህወሀትን በመቃወም ላይ ያሉ የታጠቁ ወሮበላ ኃይሎች ናቸው፡፡ የወሮበላ ቡድኑን ዓላማ ለማምከን እና በክልሉ ውስጥ ባሉ አካባቢዎች የሚኖሩ ህዝቦችን በማስፈራራት ላይ ያለውን ቡድን የጸጥታ ኃይሎች ኃላፊነት የተመላበት እና ተጨባጭነት ያላቸውን እርምጃዎች ይወስዳሉ፡፡በእርሱ ትርጉም እና አረዳድ ኃላፊነት በተመላበት መልኩ ማለት መግደል ማለት ነው፡፡ 

እስከ አፍንጫው የታጠቀ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን አገዛዝ ምንም ዓይነት የጦር መሳሪያ ያልታጠቁ ተማሪዎችን እና ወጣት ተቃዋሚዎችን የጦር መሳሪያ የታጠቁ ወሮበሎች በማለት የሚጠራው እንዴት ዓይነት ስብዕና እና አመክንዮ ቢኖረው ነው? 

የዘህወሀት መሪዎች፣ አስመሳዮች እና ከታች ያሉት ጫማ ላሽ መጋቢዎች የተቃዋሚዎችን ስም በማጥፋት፣ በመወንጀል፣ በማዋረድ፣ ስሚታዊነትን በማሳየት፣ ትችት በማቅረብ እና የኃይል እርምጃዎችን በመውሰድ ጊዚያቸውን አያጠፉም፡፡  

ህወሀት የማይቀረውን ህዝባዊ አመጽ እንዴት እንደሚያፋጥነው፣ 

ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ የነጻ ፕሬስ ቀንዲል የሆነችው ርዕዮት ዓለሙ በዘህወሀት ላይ የትጥቅ ትግል ከሚያካሂደው ግንቦት 7 ለተባለው የፖለቲካ ድርጅት አባል ሆና መቀላቀሏን ይፋ አድርጋለች፡፡ 

.. 2012 ህወሀት ሸፍጥን በተላበሰ መልኩ ርዕዮትን በአሸባሪነት በመክሰስ 14 ዓመታት እስራትን በይኖባት ነበር፡፡ ባለፈው ሀምሌ ወር ከእስር ከተፈታች በኋላ ካለፉት ጥቂት ሳምንታት በፊት ከዚህ ከዩናይትድ ስቴትስ ገብታለች፡፡ 

ርዕዮት ህወሀትን በትጥቅ ትግል ከስልጣኑ ለማባረር እንቅስቃሴ እያደረገ ካለው ድርጅት ጋር ለምን እንደተቀላቀለች እንዲህ በማለት ግልጽ አድርጋለች፡ 

በሀገር ውስጥ ምን ማድረግ እንደምችል ሳስብ ቆይቻለሁ፡፡ የምጽፍ ከሆነ እታሰራለሁ፡፡ ወደ እስር ቤት ዘብጥያ እወርዳለሁ፡፡ የመጨረሻው የሚሆነው ይህ ነው፡፡ ይህንን አገዛዝ ለመቃወም እና ስርዓቱን ለመለወጥ አንድ ነገር ማድረግ እንዳለብኝ አውቃለሁ፡፡ ይህንን ለማድረግ ደግሞ ልዩ የሆነ የእራሴን ድርሻ ማበርከት አለብኝ፡፡ የእኔ መስዋዕትነት ሰይጣናዊ ድርጊቱን ከማስወገድ አንጻር ሊመጥኑ የሚችሉ መሆን መቻል አለባቸው፡፡ አንድ ነገር በመጻፌ ብቻ ታስሬ ከምንም እንቅስቃሴ ተገድቤ መቀመጡን አልፈቅድም፡፡ ይኸ ለምከፍለው መስዋዕትነት ተመጣጣኙ አይደለም የሚል ሀሳብ አለኝ፡፡ በሀገሬ ላይ ለውጥ ለማምጣት አንድ ነገር ለማድረግ በማስብበት ጊዜ የተሻለ ነገር ለማድረግ እንደምችል አስቤበታለሁ፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎችን እነሱ በሚፈልጉበት ጊዜ ሊዘጓቸው ይችላሉ፣ በማንኛውም በሚፈልጉበት ጊዜ የጋዜጦችን ህትመት ማገድ ይችላሉ፡፡ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አባላትን ወይም ደግሞ መሪዎችን ማሰር መቻላቸው ቢያንስ የተሻለ ነገር ነው፣ ምክንያቱም ፓርቲው ከእንቅስቃሴው ሳይታቀብ መጓዝ ይችላልና፡፡ ፓርቲዎችን እና ጋዜጦችን በመዝጋት ጋዜጠኞችን ማሰር ለእነርሱ ቀላል ነገር ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ትንሹ ነገር ለምሳሌ ያህልም በፌስ ቡክ ሀሳብን መግለጽ ሊያሳስር የሚችል ነገር ነው፡፡ እንዲያውም አስቂኝ ተውኔቶችን የሚሰሩ ኮማኪዎች በአገዛዙ ላይ ቀልድ መስራት አይችሉም፡፡ ስለሆነም ምን ማድረግ አለብኝ? ብዙም አይደል፡፡ በእስር ቤት ሆኘ ምንም ነገር መስራት እንደማልችል ግንዛቤ በመውሰድ ከድምዳሜ ላይ ደረስኩ፡፡ ከእስር ቤት ከተፈታሁ በኋላ በኢትዮሜዲያ የሚወጣ ጽሁፍ በመጻፍ እና ቃለ መጠይቅም በመስጠት አቋሜ ምን እንደሆነ ግልጽ አደረግሁ፡፡ የፍርሀት ድባባችንን በማስወገድ በተጨባጭ ሊታዩ እና ሊዳሰሱ የሚችሉ ተግባራትን በማከናወን ገንቢ የሆኑ እርምጃዎችን መውሰድ እንዳለብን አምናለሁ፡፡ ተጨባጭንት ያለው ድርጊት ዝም ብሎ መልካም ነገርን በማሰብ ብቻ የሚመጣ ነገር አይደለም፡፡ ይህንን ሁሉ እናገራለሁ ምክንያቱም ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ዕቅዱ የለኝምና፡፡ ከዚህ በኋላ ወደ ሀገር ቤት ብመለስ ቃሊት እየተባለ በሚጠራው [የመለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት] እንደምገባ አሳምሬ አውቃለሁ፡፡ ስለዚህ ከውጭ ሆኘ ለትግሉ መጎምራት የትግል ድርሻዬን በማበርከት አስተዋጽኦ ባደርግ የተሻለ ነገር ነው፡፡ ገና በእስር ቤት ሳለሁ የግንቦት 7 ንቅናቄን መቀላቀል እንዳለብኝ ወስኛለሁ፡፡ ለሰላማዊ ትግል ምንም ዓይነት ዕድል የለም፡፡ እንዲያውም ትንሽም ቢሆን አለ ከተባለ እኔ በእስር ቤት ታስሬ በነበርኩበት ጊዜ የነበረው ዕድል በአሁኑ ጊዜ ጭራሹን የለም፡፡ ምንም ዓይነት የቀረ ምርጫ የለም፡፡ ምንም የቀረ ነገር የለም፣ የቀረው ምርጫ ቢኖር የትጥቅ ትግል ማካሄድ ብቻ ነው፡፡ ለዚህም ነው ግንቦት 7 የተቀላቀልኩት፡፡ 

በኢትዮጵያ ውስጥ የቀረየሰላማዊ ትግል ዕድልየለምን? 

ርዕዮት በኢትዮጵያ ውስጥ የቀረ ምንም ዓይነት የሰላማዊ ትግል ዕድል የለም በማለት የሰጠችው መግለጫ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዘንድ ትልቅ ጠቀሜታ ያለው ጥያቄ ሆኖ ቀርቧል፡፡ የዚህ ጥያቄ ምላሽ የወደፊቷን ኢትዮጵያ መጻዒ ዕድል ሊመልስ በማይችል መልኩ ሊወሰን የሚችል ጉዳይ ነው፡፡ (የዘህወሀት የወደፊት ዕጣ ፈንታ አስቀድሞ ተወስኗል፡፡ ምንም ዓይነት አዎንታዊ የሆነ የወደፊት ዕጣ ፈንታ በፍጹም የለውም!) 

እኔ 10 ዓመታት ያህል በዘህወሀት ወንጀለኞች ላይ ያለምንም ማቋረጥ ጣቴን በመቀሰር ትችት ሳቀርብ ከቆየሁት የትግል መንፈስ እና አሳቤ ጋር ሳነጻጽረው የርዕዮት መግለጫዎች ጥልቅ መሰረት ያላቸውን ጥያቄዎች የሚያስነሳ ጉዳይ ነው፡፡ 

በመጀመሪያ ደረጃ ለርዕዮት ከፍተኛ የሆነ ክብር አለኝ፡፡ ለከፈለችው እና አሁንም ውድ ሀገሯን በመተው በሰው ሀገር ላይ ሆና እየከፈለችው ላለው መስዋዕትነት ከፍተኛ የሆነ ምስጋና ላቀርብ እፈልጋለሁ፡፡ ለዘህወሀት አይበገሬ እምቢተኛነቷን ያሳየች ጀግኒት በመሆኗ ከፍ ያለ አድናቆት አለኝ፡፡ 

ርዕዮት ይቅርታ በመጠየቅ ምህረት እንዲደረግላት እና ከማጎሪያው እስር ቤት እንድትለቀቅ በዘህወሀት ትንንሽ አምላኮች ፊት በመቅረብ ለመስገድ የቀረበላትን ጥሪ በጽኑ ተቃውማለች፣ ሞቴን እመርጣለሁ እንጅ ይህ በፍጹም አይደረግም በማለት አይበገሬነቷን በተግባር አሳይታለች፡፡ 

ከመሰረታዊ ዓላማዋ ንቅንቅ ሳትል በእስር ቤት ውስጥ ሆና በዘህወሀት ሲደርስባት ከነበረው ማስፈራራት፣ ማዋረድ እና ስብዕናን የማጥፋት ዕኩይ ምግባር ሳትንበረከክ በድል አድራጊነት የወጣች አይበገሬዋ ጀግኒት ናት፡፡ 

ርዕዮትበኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ዓይነት ሰላማዊ የሽግግር ለውጥ ዕድል የለምስትል በመብረቅ የተመታሁ ያህል ክው ብዬ ነው የቀረሁት፡፡ 

ርዕዮት የእራሷን አመለካከት ግልጽ አደረገች ብዬ የማምን ቢሆንም እንኳ የእርሷን መግለጫዎች የግል የእምነቷ መገለጫዎች ናቸው የሚል እምነት ይኖረኝ ነበር፡፡ 

ሆኖም ግን ርዕዮት እኔ ለማውቀው ለምንም ሳይሆን 70 በመቶ ለሚሆነው ለወጣት ኢትዮጵያውያን ትውልዷ ወክላ  ነው እየተናገረች ያለችው፡፡ 

ርዕዮት ጨለምተኝነት፣ ተስፋቢስነት፣ ፍጹም የሆነ ፍርሀት፣ ከፍተኛ ስቃይ እና ለእርሷ ትውልድ መጻዒ ዕድል ስትል ድምጿን ከፍ በማድረግ በመጮህ እንደገደል ማሚቶ በማስተጋባት ላይ ትገኛለች፡፡ 

ርዕዮት በኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ዓይነት የቀረ የሰላማዊ ትግል ዕድል የለም የሚል መልዕክት ስታስተላልፍ ለእኔ እርሷ የጨዋታው ሕግ አጧዥ ኃይል ሆና መቅረቧን በውል እንድገነዘብ ያደርገኛል፡፡ 

የርዕዮትን መግለጫዎች በውል በማጤንበት ጊዜ ለሰላማዊ ትግል ሌላ አማራጭ ምን መሆን እንዳለበት እራሴን እጠይቃለሁ፡፡ የትጥቅ ትግል ሊሆን ይችላልን? 

ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በአንድ ላይ ተሰባስቦ ምንም ዓይነት የጦር መሳሪያ ባልታጠቁ ሰላማዊ ሰልፈኞች እና በተቃዋሚው ስብስብ ላይ የእሩምታ ተኩስ በመክፈት፣ በአምልኮት ቦታዎች በምዕመናን መካከል የእጅ ቦምቦችን በማፈንዳት፣ ተቃዋሚዎችን በማሰር እና በማሰቃየት፣ የህዝቡን የምርጫ ድምጽ በመዝረፍ መቶ በመቶ አሸንፊያለሁ ብሎ በማወጅ እና በአደባባይ ምህረት የለሽ እርምጃ እወስዳለሁ በማለት ማወጅ እና መዛት ምርጫው በሰላማዊ እና በትጠቅ ትግል መካከል ያለመሆኑን በግልጽ ያመላክታል፡፡ 

አይደለም! አይደለም! ምርጫው በሰላማዊ እና በትጥቅ ትግል መካከል ያለመሆኑን፣ ይልቁንም ምርጫው በቦቅቧቃ ፈሪዎች እና በደፋር ኃይለኞች መካከል መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያመላክታል፡፡ 

ርዕዮት ጋንዲየጎራዴው መርህበሚል ርዕስ ካዘጋጁት እንዲህ ከሚለው መንፈሳዊ ድምጽ የመጨረሻ ጠርዝ ላይ ደርሳለች ብዬ አምናለሁ፡ 

በፍርሀት እና በድፍረት/ኃይል መካከል ምርጫ ሲቀርብ ኃይልን መምረጥ የተሻለ እንደሆነ ምክር መምከር እንዳለብኝ አምናለሁህንድ በፍርሀት አዘቅት ውስጥ ሰጥማ እረዳትየለሽ ሆና ለእራሷ ውርደት ምስክር ሆና ከምትዳክር ይልቅ የእራሷን ክብር ለመጠበቅ ስትል መሳሪያ አንስታ ብትዋጋ የምመርጥ ይሆናል፡፡ 

እንደዚሁም ሁሉ ርዕዮት ኢትዮጵያውያን በዘህወሀት ተዋርደው እና ክብራቸውን እና ሀገራቸውን አጥተው ለዘላለም በውርደት አንገታቸውን በመድፋት እየተገደሉ እና እየተሰቃዩ መኖር ወይም ደግሞ በአንድነት በህብረት በአንድነት በመነሳት የዘህወሀትን አፋኝ ስርዓት በትጠቅ ትግል ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ከኢትዮጵያ ህዝቦች ጫንቃ ላይ ማስወገድ የሚያስፈልግበት ደረጃ ላይ የደረሰች መሆኗን አምናለሁ፡፡

እስከ አፍንጫው ድረስ በዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን ኃይለኛ ወታደራዊ ኃይል፣ እንዲሁም የገንዘብ አቅም ውስንነት ባለበት እና ህወሀት ሁሉንም ነገር ሙሉ በሙሉ ጨምድዶ በእራሱ ቁጥጥር ስር ይዞ በሚገኝበት ሁኔታ የተጨቆነው እና የተገፋው ህዝብ እንዴት አድርጎ ለድል ይበቃል ለሚለው ጥያቄ ርዕዮት እንዲህ የሚለውን የጋንዲን አዋጅ ደግማ አውጃለች፣ኃይል ከአካላዊ እና ከቁሳዊ ብቃት የሚመጣ አይደለም፡፡ ኃይል የሚመጣው ከማይበገረው የዓላማ ጽናት ነውብላለች፡፡ 

ርዕዮት ከሰላማዊው የትግል መንገድ እንድትወጣ ያስቻላት የእምነቷ ድፍረት እና ሌላ ምንም ነገር ሳይሆን እምቢኝ አሻፈረኝ ለጨቋኙ እና ለበከተው ስርዓት ለዘህወሀት አልገዛም ብላ ፍርሀትን በመቃወሟ እና በቀጣይነትም የዘህወሀትን ውርደት በመሸከም እና ክብርን በማጣት እንደ እንስሳ ሆኘ አልኖርም ከሚል የማይበገረው የዓላማ ጽናቷ በመነሳት ነው፡፡ 

ርዕዮትበቃ በቃ ነው!“ ከሚለው ጠርዝ ላይ ደርሳለች፡፡ 

እንደዚሁም ሁሉ ሁሉም ኢትዮጵያውያንበቃ በቃ ነው!“ ከሚለው ጠርዝ ላይ ደርሰዋል ብዬ አምናለሁ፡፡ 

እኔ 10 ዓመታት በላይ ሰላማዊውን የትግል መንገድ በመከተል ለድል መብቃት ይቻላል የሚል እምነት በመያዝ የግል አመለካከቴን በማራመድ በዘህወሀት እና በዓለም አቀፍ ደጋፊዎቹ ላይ ጣቴን ስቀስር በቆየሁበት ጉዳይ ላይ ጥያቄ እንዳነሳ በማድረግ ሰላማዊ የትግል ጥያቄ ያበቃለት እና የተቀበረ መሆኑን በማስረገጥ የሰላማዊ የትግል መንገዱን እርግፍ አድርጎ መተው እና በፍርሀት እና በድፍረት መካከል ያለውን ምርጫ በውል አጢኖ ፍርሀትን ከላያችን ላይ ጠራርጎ በመጣል አምባገነኑን አገዛዝ በኃይል እና በሁለገብ የትግል ስልት አሽቀንጥሮ ለመጣል በጽናት የተያዘው የርዕዮት ውሳኔ ለሌሎቹ በእርሷ የትውልድ ዘመን የሚገኙትን የበርካታዎቹን ወጣቶች አመለካከት፣ ስሜት እና ፍላጎት የሚያንጸባርቅ እንደሆነ አምናለሁ፡፡ 

ረዣዥሞቹን ትችቶቼን ለበርካታ ጊዘያት ስታነቡ ለቆያችሁ አንባቢዎቼ .. 2005 ተካሄደ የተባለውን የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ ተከትሎ ተፈጥሮ በነበረው ውዝግብ አሁን በህይወት የሌለው አምባገነኑ የዘህወሀት መሪ በእብሪተኝነት እና በማን አለብኝነት የግፍ ስሜት ተነሳስቶ ለአፋኝ እና ለቅጥር ነፍሰ ገዳይ ሎሌዎቹ የእልቂት ትዕዛዝ በማስተላለፍ በጠራራ ጸሐይ በአደባባይ የተዘረፈውን የኢትዮጵያን ህዝብ ድምጽ ለመቃወም እና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና ለኢትዮጵያ ህዝብ ለማሳወቅ ወደ አደባባይ በወጡ ሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈጸመውን እልቂት ከተመለከትኩ በኋላ በቁጭት በወገኖቼ ላይ የተፈጸመውን ግፍ እና ወንጀል ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና ለሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በማሳወቅ የስርዓቱ አዛዥ ቁንጮዎች እና ቅጥር ነፍሰ ገዳዮች ለፍትህ አካል ለፍርድ እንዲቀርቡ በማሰብ ወደ ትግሎ ዘው ብዬ እንደገባሁ የምታስታውሱት ጉዳይ ነው፡፡ 

በኢትዮጵያ ውስጥ የሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ ትግል በጀመርኩበት ጊዜ በሚከተሉት ሶስት ነገርች ላይ ሙሉ እምነት ነበረኝ፡፡ እነርሱም፡ 

1) በኢትዮጵያ ሰላማዊ የለውጥ ሽግግር ለማድረግ መቻሉ ብቻ ሳይሆን የማይቀር ግዴታም ነው የሚል ሙሉ እምነት ነበረኝ፡፡ 

2) አምባገነኑ መለስ ዜናዊ እና ህወሀት በኢትዮጵያ ላይ እሳት ለኩሰዋል፡፡ እንደ እኔ ያሉት እሳት አጥፊዎች ደግሞ የጎሳ ጥላቻ፣ የዘር እና የብሄር ክፍፍል፣ የበላይነት እና ተጻራሪነት እንዲሁም የእኩልነት እጦት እና የኢፍትሀዊነት እሳት እንዲጠፋ እንድንታገል አስፈላጊዎች ነን የሚል እምነት ነበረኝ፡፡ 

3) የኃይል አመጽ (የጭካኔ ሕግ) ማህበራዊ ለውጥን እንደሚያስገኝ መሳሪያ አድርጎ መውሰድ ኢሞራላዊ፣ ያልሰለጠነ ኋላቀር እና ኢሰብአዊነት ነው የሚል እምነት ነበረኝ ፡፡ 

ጋንዲሰላማዊነት የሰው ዘር ሕግ ነው፡፡ አላግባብ ኃይለኛነት ግን የጨካኞች ሕግ ነውበማለት አስተምረውናል፡፡ በጨካኞች ላይ የመፍጀት የሕግ መንፈስ ነው ያለው፡፡ የሰው ልጅ ክብር የመንፈስ ከፍተኛ ጥንካሬ ለሆነው ሰላማዊ  መንፈስ ታዛዥ መሆን ይጠይቃል፡፡ 

የሰው ልጆች ዘር ሕግ ሰላማዊ እንደሆነ አድርጌ አምን ነበር፣ አሁንም አምናለሁ፡፡ ሆኖም ግን ከዚህም በተጨማሪ በሰው ልጆች ዘር ላይ ምህረት የለሽ እርምጃ የሚወሰድ ከሆነ ሌላው ወገን ደግሞ ባጻፋው ምህረት የለሽ ምላሽ እንደሚሰጥ እገነዘባለሁ፡፡ 

.. ነሐሴ 2006 HR 5680 ጋር በተያያዘ መልኩኢትዮጵያ ነጻነት፣ ዴሞክራሲ እና የሰብአዊ መብቶች መጠናከር 2006 ድንጋጌ/Ethiopia Freedom, Democracy and Human Rights Advancement Act 2006“ በሚል ርዕስ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ለውጥ አስፈላጊነቱን በእራሴ ፍልስፍና በማወጅ ትችት አቅርቤ ነበር፡፡ የህዝቡን ልብ እና አዕምሮ በማሸነፍ በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ ማምጣት እንችላለን በማለት እንዲህ ብዬ ነበር፡ 

የእኛን ትክክለኛነት የምናረጋግጠው በጦር ሜዳ ውስጥ በመግባት በደም በመዘፈቅ እና የሬሳ ክምርን በመከመር አይደለም፣ ሆኖም ግን የእኛን ትክክለኛነት የምናረጋግጠው ለመልካም እና ለጥሩ ነገር በወንዶች እና በሴቶች አእምሮ እና ልብ ውስጥ በምናስቀምጠው ደግ ነገር እንደሆነ አምናለሁየአእምሮ እና የልብ ውስጣዊ ትግል በማድረግ እራሳችንን ከጎሳ ጥላቻ መርዝ ማጽዳት አለብን ብየ አምናለሁ፡፡ 

.. 2016 የአዲስ ዓመት ደወል ከመደወሉ ጥቂት ቀናት ቀደም ሲል ህወሀት 24 ዓመታት ከሕግ አግባብ በላይ ስልጣኑን በመጠቀም የኢትዮያን ህዝብ ልብ ሊጠገን በማይችል መልኩ እንዲሰበር አድርጓል፣ 24 ዓመታት በዘለቀው ኢፍትሀዊ አገዛዙ የኢትዮጵያን ህዝብ ልብ አቃጥሏል፣ 24 ዓመታት ክብር በማሳጣት እና በማዋረድ የህዝቡን ልብ አጥቁሯል፣ 24 ዓመታት በመበዝበዝ የህዝቡን ልብ እንዲያመር አድርጓል፣ 24 ዓመታት በሙስና ባህር ውስጥ በመዘፈቅ የህዝቡን ልብ እንዲታመም አድርጓል፣ እንደዚሁም ሁሉ 24 ዓመታት በዘለቀው አምባገነናዊ የጭቆና እና የጭካኔ አገዛዙ የህዝቡን ልብ እንዲደነድን አድርጓል፡፡ 

በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ህዝቦች የልብ ትርታ በግድ ወደ መሳሪያ የትጥቅ ትግል ወደማድረግ እና  የጦርነት ከበሮ ወደ መምታት ተሸጋግሯል፡፡ 

ባለፉት አስር ዓመታት ጊዜ ውስጥ ስልጣንን ከሕግ አግባብ ውጭ መጠቀምን፣ ስለአምባገነንነት እና ጨቋኝነት፣ ስለሰብአዊ መብት ድፍጠጣ እና ስለዴሞክራሲ፣ በኢትዮጵያ ስለፍትህ እና ስለሰብአዊ መብት ጥበቃ ያደረግሁትን እልህ አስጨራሽ ትግል ወደ ኋላ መለስ ብየ ስመለከተው ለሰላማዊ ለውጥ ሳደርጋቸው የቆየኋቸው እነዚያ ሁሉ ጥረቶች የመከኑ ባዶ እንደሆኑ ያህል ሆኖ ይሰማኛል፡፡ ምንም ነገር ያልተደረገ እርባና ቢስ አድርጌ ግን አልቆጥረውም፡፡ 

አቅጣጫቸውን እንዲቀይሩ እና ትክክለኛውን አካሄድ እንዲከተሉ ለዘህወሀት እና ለመሪዎቹ የሰጠኋቸው ምክሮች እና ማስጠንቀቂያዎች ሁሉ ተደማጭነትን እና ትኩረትን ሳያገኙ ቀርተዋል፡፡ 

ጭቆናውን እንዲያቆም፣ የበለጠ ሰብአዊነት እንዲሰማው እና ትክክለኛውን መንገድ እንዲከተል እንደዚሁም ደግሞ ህዝቦቸን ማዳመጥ እንዲችል ያቀረብኳቸው ልመናዎች ሁሉ ምንም ሰሚ ሳያገኙ ህወሀት ጆሮ ዳባ ልበስ ብሏቸው ቀርቷል፡፡ 

በኢትዮጵያ ተለኩሶ የነበረው እና ለማጥፋት ጥረት ሳደርግ የቆየሁት እሳት በአሁኑ ጊዜ በመላ የሀገሪቱ ክፍሎች ውስጥ ተቀጣጥሎ ይገኛል፡፡ 

.. 2007 “ትንሿ ወፍ እና የጫካው እሳትበሚል ርዕስ አቅርቤው የነበረውን ተመሳስሎ በርካታዎቹ የረዥም ጊዜ አንባቢዎቼ ታስታውሱታላችሁ፡፡ 

በዚያ ባቀረብኩት ትችት ላይ ራቅ ካለ ወንዝ በመመላለስ በኩምቢዋ ውኃ እያመጣች እሳቱን ለማጥፋት ጥረት ስታደርግ በነበረችዋ ትንሿ እሳት አጥፊ ወፍ እራሴን በመመሰል አቅርቤ ነበር፡፡ 

አመናችሁም አላመናችሁም ሀገራችን በእሳት ተቀጣጥላ ትገኛለች፡፡ በእሳት ለማቃጠል ምንም ኃላፊነት የማይሰማው አውዳሚ ኃይል ከጎን ተቀምጧልሆኖም ግን ጢሱ እንዲህ የሚል መልዕክት ያስተላልፋል፡በሺዎች የሚቆጠሩ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን በእሳቱ ውስጥ በመቃጠል ላይ ናቸው፣ በአስር ሺዎች እና ከዚያም በላይ የሚሆኑት ወገኖቻችን ደግሞ በአሁኑ ጊዜ በመቃጠል ላይ ይገኛሉ፣ እንደዚሁም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩት ዜጎች በጥይት እየተደበደቡ በመሞት ላይ ይገኛሉ፣ 77 ሚሊዮን የሚሆኑት ዜጎች በጥይት የተኩስ መስመር ጠርዝ ላይ ተሰልፈው ይገኛሉ! 

ቤትህ በእሳት ተቀጣጥሎ ሳለ በአካባቢው ዝም ብለህ ቆመህ መልካም ንግግር እየተናገርክ አትመለከትም፡፡ የተቀጣጠለውን እሳት ለማጥፋት እንደ ትንሿ እሳት አጥፊ ወፍ ሁሉ ከወንዝ እየተመላለስክ የውኃ ጠብታዎችን እያመጣህ እሳቱን ለማጥፋት ጥረት ማድረግ ይኖርብሀል፡፡ 

ሆኖም ግን በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ወጣት ወገኖቻችን በየዕለቱ በእሳት ነበልባል መስመር ላይ ተጥደው ይገኛሉ፡፡ በሰላማዊ መንገድ ለመቃወም እንቅስቃሴ ካሳዩ እንደ አበደ ውሻ በጥይት ይገደላሉ፡፡ አእምሯቸው የሚያምንበትን ነገር አውጥተው ከተናገሩ አሸባሪ በመባል ተፈርጀው ወደ ሞጎሪያው እስር ቤት ዘብጥያ ይወርዳሉ፡፡ ለአገዛዙ ታማኝ አይደሉም የሚል ጥርጣሬ ካለ የማስፈራራት ድርጊት ይፈጸምባቸዋል፡፡ ግፈኛውን አገዛዝ በኃይል ያስወግዳሉ ተብለው የሚጠረጠሩ ከሆነ ታፍነው የደረሱበት ደብዛው እንዲጠፋ ይደረጋሉ፡፡  

እነዚህ የዲያስፖራ እሳት አጥፊዎች እሳትን በእሳት አይዋጉም፣ በፍጹም፣ እሳትን የሚዋጉት በውኃ ነው፡፡ ውኃ በእሳት ላይ እንደሚያደርገው ድርጊት ሁሉ እነዚህ እሳት አጥፊ ተዋጊዎች ጨለምተኝነትን በተላበሰው እና ምንም ዓይነት የተስፋ ጭላንጭል እና ብሩህ ነገር በማይታያቸው ላይ ላሉት ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን የተስፋ እና የብሩህ ልምላሜ ስሜትን  በመፈንጠቅ፣ የጭቆናን እና የጭካኔ አምባገነናዊ ቆሻሻን በዴሞክራሲ እና በሰብአዊ መብት መጥረጊያ ጠርጎ እና ጠራርጎ ወደ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ቅርጫት በመጣል፣ በፖለቲካ ሸፍጠኝነት፣ በሙስና፣ በኋላቀር ድርጊት እና በሕግ አልበኝነት ምድረበዳ በሆነው መሬታችን ላይ የነጻነት እና የፍትህ ዘርን በመዝራት ወደ ልምላሜ ይመልሳሉ፡፡ 

እነዚህ እሳት አጥፊዎች እንዲህ የሚል አንድ ብቸኛ ተልዕኮ አላቸው፡በብሄራዊ ራዕይ የሚመራ የኢትዮጵያን ህዝብ በማይከፋፍል አንድነት ላይ መሰረት ያደረገ በኢትዮጵያ ውስጥ እርስ በእርሳቸው የሚወዳደሩ እና በጥልቅ ቅራኔ፣ በቋንቋ፣ እና በአካባቢያዊ የልዩነት አዘቅት ውስጥ ተዘፍቀው ያሉ ተዛማጅነት የሌላቸው ስብስቦች ናቸው የሚለውን የመከነ ሀሳብ አሽቀንጥሮ በመጣል በፍቅር የተሳሰረ አዲስ የህብረተሰብ እንዲገነባ ማገዝ ነው፡፡ 

እንግዲህ እንዲህ በማለት ደመደምኩት፡ 

ወጣቶቻችን ተቀጣጥሎ የሚገኘውን እሳት ሰላማዊ በሆነ መንገድ ሆኖም ግን በማይበገር ወኔ እና ጽናት ለማጥፋት እንዲችሉ እናስተምራቸው፣ እናሰልጥናቸው፣ እናበረታታቸው፣ እንደግፋቸው፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩትን የእሳት ሰለባዎች እና የወደፊት ዕጣፈንታቸውን ለማዳን ሲባል በእሳት ነበልባል ተቀጣጥለው በተስፋየለሽነት የሚገኙትን ወገኖቻችንን እንቀፋቸው፡፡ በመጨረሻም በማቅለጫ ምድጃው/ፈርነሱ ውስጥ ቀልጦ እንደሚወጣው የአረብ ብረት የሚያንጸባርቁ እና ምድረበዳ ለሆነው እና ለጠፋው ደን ፈውስ የሆነችውን ብርቅየዋን ጸሐን እንደሚያመጡ እርግጠኛ እናድርጋቸው፡፡ 

የእኛ ወጣት እሳት አጥፊዎች ለዘመናት በፖለቲካ ጭቆና እና በሰብአዊ መብት ድፍጠጣ የደቀቀ ማህበረሰብ እንዳላቸው የሚገነዘቡ ቢሆንም እንኳ በአንድ ወቅት በተራራው ጫፍ ባለች ከተማ ላይ ፍትህ የሰፈነባት፣ ሰብአዊነት የሚከበርባት እና ክብርን እና ሞገስን የተላበሰ ህዝብ የሚኖርባት፣ ማንም ወንድ መንግስትን የማይፈራበት ወይም ማንም ሴት መንግስትን የማትፈራበት፣ መንግስት የእራሱን ዜጎች የሰብአዊ መብት እና ነጻነት የማክበር ግዴታ ያለበት፣ ማንም ሰው ያለምንም ፍርሀት እና መሸማቀቅ ቀጥ ብሎ የመሄድ፣ አዕምሮው የፈቀደውን ነገር በነጻ የመግለጽ፣ ማንም ወንድ፣ ሴት ወይም ልጅ ህይወቱን የማያጣበት፣ ከሕግ አግባብ ውጭ ማንም ሰው ንብረቱ የማይወረስበትን ማህበረሰብ ለመፍጠር እንደሚችሉ ምንም ዓይነት ጥርጥር የለውም፡፡ 

በኢትዮጵያ አሁንም ሰላማዊ የሽግግር ለውጥ ማምጣት ይቻላልን? 

ከዚህ በኋላ በኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ የሽግግር ለውጥ ማምጣት ይቻላል በሚለው ጉዳይ ላይ በእርግጠኝነት የማውቀው ነገር የለኝም፡፡ 

በአሁኑ ጊዜ በእርግጠኝነት የማውቀው ነገር ቢኖር በተራራ ጫፍ ላይ የኢትዮጵያን ከተማ ለመገንባት ሳስበው የነበረው ህልሜ ከመቅጽበት እንደጉም በኖ ጠፍቷል፡፡ 

በአሁኑ ጊዜ በእርግጠኝነት የማውቀው ነገር ቢኖር በኢትዮጵያ ውስጥ በሰላማዊ መንገድ ለውጥ ለማምጣት ወጣቶቻችንን ለማስተማር እና ለማሰልጠን ሳደርገው የነበረው ጥረት ሁሉ መክኖ እና ወደሌላ መንገድ ተሻግሮ በማይበገር መልኩ የጎሳ ክፍፍል እሳትን፣ የሰብአዊ መብት ረገጣ እሳትን እና ስልጣንን ከሕግ አግባብ ውጭ በመጠቀም አየተካሄደ ያለውን አምባገነናዊ የጭቆና አገዛዝ እሳት በአንዴ እና ከመቅጽበት ተለውጦ እሳትን በእሳት ወደማጥፋት የአካሄድ መንገድ ተቀይሯል፡፡ 

በአሁኑ ጊዜ በእርግጠኝነት የማውቀው ነገር ቢኖር የኢትዮጵያ ህዝብ በፈረጠመ ህዝባዊ ጡንቻው ህወሀትን እንደ መዥገር ተጣብቆ ካለበት ስልጣኑ ላይ በኃይል ለማስወገድ በጽኑ የወሰነ መሆኑን ነው፡፡ ምክንያቱም ህወሀት ለምክንያታዊነት ተገቢውን ምላሽ የማይሰጥ ግትር ወንጀለኛ ነው፣ የውይይት መድረክ ለመክፈት ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ የተቀመጠ እብሪተኛ እና ሞገደኛ ድርጅት ነው፣ በውይይት እና በክርክር የማያምን እና ሀገሪቱን በእርስ በእርስ የጦርነት እሳት ውስጥ ለመማገድ ሌት ቀን አበርትቶ እየሰራ ያለ ኃላፊነት የማይሰማው ወንጀለኛ የዘራፊ ወሮበላ ስብስብ ነው፡፡ 

ስለሆነም በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ ውስጥ እየተፈጸሙ ያሉ እንደዚህ ያሉ ክስተቶች ቢኖሩም በሰላማዊ መንገድ ለውጥ ማምጣት የሚለው ህልሜ አሁንም ድረስ እኔን ብቸኛ አድርጎኛል፣ ኃይልን በመጠቀም በመሳሪያ ኃይል በአመጽ ለውጥን ከማምጣት በሰላማዊ መንገድ ለውጥ የማምጣት ተስፋ ላይ የመቸከል እምነት የእኔ ብቻ ተስፋ እንዲሆን አድርጎኛል፣ እንደዚሁም ሁሉ ለባዶ ለማይሆን ነገር ሰላማዊ መንገድን ብቻ መከተል የሚለው የእኔ ሰበካ የእኔ ብቻ አመለካከት እንዲሆን አድርጎኛል፡፡ 

ኢትዮጵያ ሰላሟን አስጠብቃ እራሷ ሰላም ሆነ ከጎረቤቶቿም ጋር በሰላም እንዲትኖር አሁንም ብቸኛው ህልም አላሚ ሆኘ የቀጠልኩ ይመስለኛል፡፡ 

.. ሀምሌ 2012 አሁን በህይወት የሌለው አምባገነኑ የዘህወሀት መሪ ከዚህ ዓለም በሞት በተለየበት ጊዜበሰላም የምትኖር ኢትዮጵያ ህልም/Dreams of an Ethiopia in Peace” በሚል ርዕስ ትችት አቅርቤ ነበር፡፡ 

በዚያ ትችቴ ላይ በስልጣን ላይ ባሉ አዳራሾች ብቻ ሳይሆን፣ በቢሮክራሲው እና በወታደራዊ ኃይሉ የመሰብሰቢያ አዳራሾች ላይ ብቻ ሳይሆን፣ በጣም ሩቅ በሆኑ መንደሮች፣ ቤተክርስቲያኞች፣ መስጊዶች የመሰብሰቢያ አዳራሾች እንዲሁም በትምህርት ቤቶች፣ በኮሌጆች፣ በጎረቤታም ማህበራት እና በምግብ ቤት አዳራሾች፣ በመንገዶች እና በገበያዎች እንዲሁም በሌሎች ሁለት ወይም ከሁለት በላይ ሰው ሊሰበሰብባቸው በሚችሉ በየትኞችም ቦታዎች  ላይ ጭምር  ውይይት በማድረግ ብሄራዊ እርቅ የማውረድ ጥረት እንዲጀመር ሀገራዊ ጥራ አቅርቤ ነበር፡፡ ምንም ዓይነት አማራጭ የለንም ሆኖም ግን በመልካም ፈቃደኝነት እና እምነት ላይ በተመሰረተ መልኩ እርስ በእርሳችን መነጋገር ብቻ ነው ብየ ነበር፡፡ 

ሰላሟ የተጠበቀ ኢትዮጵያን እመኛለሁ ምክንያቱም ጥቂት ሰዎች ነገሮችን ከብዙ አቅጣጫ በመመልከትለምን’?  ይላሉ፡፡ 

ሆኖም ግን ከዚህ ቀደም ሆነው የማያውቁትን ነገሮችለምን መሆን አይችሉም’? የሚል ምኞት በማቅረብ እናገራለሁ፡፡ 

ሁላችንም ኔልሰን ማንዴላ በተጓዙበት መንገድ መጓዝ እንችላለን በማለት በድፍረት በመናገር ያለኝን እምነት አገልጻለሁ፡፡ 

ትምኔታዊዋን ኢትዮጵያ ለማየት በድፍረት አልማለሁ! ለምን አይሆንም? እላለሁ፡፡ 

በህልም ትችቴ ላይ ለመውደድ ጊዜ አለው፣ ለመጥላትም ጊዜ አለው፣ ለጦርነትም ጊዜ አለው እናም ለሰላምም ጊዜ አለው በማለት የክርክር ጭብጥ በማቅረብ የመንፈሳዊ ጥቅስ አቅርቤ ነበር፡፡ 

ከሁለት አስርት ዓመታት የዘህወሀት የጭቆና አገዛዝ በኋላአሁን በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር መሰረት ስንት ሰዓት ነው?” የሚል ጥያቄ አቀረብኩ፡፡ 

አሁን ጊዜው የሰላም ነውስለ ሰላም የምናልምበት ከፍተኛ ጊዜ፡፡ መራራውን የጥላቻ መንፈስ በእርቀ ሰላም የምንተካበት፣ ህብረተሰቡን የሚያቆስለውን ጥላቻን በፍቅር የምንተካበት፣ በቀልን በይቅርታ የምንለውጥበት፣ ተስፋቢስነትን በተስፋ የምንተካበት፣ ቁስልን በፈውስ የምንሽርበት፣ ፍርሀትን በድፍረት የምንቀይርበት፣ ክፍፍልን በአንድነት የምንተካበት፣ ጥርጣሬን በመተማመን መንፈስ የምንቀይርበት፣ ውርደትን በክብር የምንተካበት፣ ማጭበርበርን በቀጥተኛነት እና በታማኝነት የምንተካበት፣ ግንፍልተኝነትን በአምክንዮአዊ አቀራረብ የምንተካበት፣ ጭካኔን በሩህሩህነት የምንቀይርበት፣ ጥላቻን በጓዳዊነት የፍቅር ስሜት የምንተካበት፣ አታላይ ነገር ሰሪነትን በግልጸኝነት የምንቀይርበት፣ ቃልን በተግባራዊ ድርጊት የምንተካበት፣ ልዩነትን በፍቅር የምንገልጽበት፣ ያልሰለጠነ ኋላቀር አስተሳሰብን በጨዋና በሰለጠነ አስተሳሰብ የምንተካበት፣ ጥርጣሬን በመተማመን የምንቀይርበት፣ ስግብግብነትን በለጋስነት የምንተካበት፣ ታማኝየለሽነትን በታማኝነት የምንቀይርበት፣ ምቾትን እና ድሎትን በክብር እና ሞገስ የምንተካበት፣ ተራ የማጭበርበር ኢሞራላዊ ስብዕናን በሞራላዊ ስብዕና መቀየርን፣ ድንቁርናን በእውቀት መተካትን፣ ጠባብ አስተሳሰብን በአርቆ አሳቢነት መተካትን፣ ብልግናን በሰለጠነ አካሄድ መቀየርን፣ ምኞትን በስኬት መተካትን፣ የጭቃ ጅራፍን እና ስህተት ፈላጊነትን ብሄራዊ ውይይት በማድረግ መተካትን ጊዜው መቼም ሳይሆን አሁኑኑ ነው፡፡ 

ለመነጋገር እና ለማድረግ ጊዜው አሁን ነው ብያለሁ! ለሰላማዊ ለውጥ እውንነት ጊዜው አሁን ነው! 

ሆኖም ግን የዘረዘርኳቸው ቃሎቼ ምንም ሰሚ ጆሮ ሳያገኙ እንዲያው በአየር ላይ ተበትነው የቀሩ ይመስላሉ፡፡ 

.. 2015 እየተጠናቀቀ ባለበት በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ህዝብ የታላቁን የአሜሪካ አብዮተኛ የፓትሪክ ሄንሪን ቃላት በመጠቀም ድምጻቸውን ከፍ አድርገው እና የበለጠ ግልጽነትን በተላበሰ መልኩ ከእኔ ቃላት በበለጠ ሁኔታ እንዲህ እያሉ ለሰላማዊ ሽግግር ተቃውሟቸውን በማሰማት ላይ ይገኛሉ፡ 

ለሰው ልጅ በተስፋ ውስጥ መኖር ተፈጥሯዊ ነው፡፡ ለሚያም እውነታ ዓይኖቻችንን ድርግም አድርገን እንዘጋለን፣ እናም የዚያ ሙዚቃ አባዜ ወደ አውሬነት እስከሚቀይረን ድረስ ዝም ብለን በትዕግስት እናዳምጠዋለን፡፡ ይህ ድርጊት ለነጻነት ሲባል በታላቅ እና በአስቸጋሪ ትግል ውስጥ የሚገኝ ብልህ ሰው ሊፈጸመው የሚችል አካል ነውን? እኛ ሁላችንም ዓይኖች እያሉን የማናይ፣ ጆሮዎች እያሉን መስማት የማንችል ዝም ብለን ምንም ዓይነት ስሜት ሳይሰማን፣ ለምንም የማንፈይድ ዜጎችን ከአደጋ ለመጠበቅ የማንችል ፍጡራን ሆነን ቀጥለናልን? በእኔ በኩል የፈለገውን ያህል ጭራቃዊ መንፈስን የተላበሰ ድርጊት ይሁን ሁሉንም እውነታ ለማወቅ፣ እንዲሁም መጥፎውን ነገር በመጥፎነቱ አሳምሬ ለማወቅ እና ለዚህም መፍትሄ ለመስጠታ ጥንቃቄ በማድረግ እሰራለሁ፡፡

ሰዎች ሰላም፣ ሰላም በማለት ይጮሃሉ ሆኖም ግን ምንም ዓይነት ሰላም የለም፡፡ ጦርነቱ በእርግጠኝነት ተጀምሯል፡፡ በቀጣይነት ከስተሰሜን አቅጣጫ የሚነፍሰው ሞገድ ግልጽ የሆነ የመሳሪያ ግጭን ለጆሯችን የሚያደርስ ነው! ወንድሞቻችን በአሁኑ ጊዜ ቀጥታ በጦር ሜዳ ውስጥ ናቸው! እኛ እዚህ ስራፈት ሆነን የተቀመጥነው ከቶ ለምንድን ነው? ህይወት እንደዚህ ውድ ነው ነገር ነው ወይስ ደግሞ ሰላም በሎሌነት እና በአሽከርነት ዋጋ የሚገዛ እንደዚህ ያለ ጣፋጭ ነገር ነው? 

ኃያሉ አምላክ እባክህ ቸርነትህ አይለየኝ! ሌሎች ምን መንገድ መከተል እንዳለባቸው የማውቀው ነገር የለኝም፡፡ ለእኔ ግን ነጻነቴን ወይም ደግሞ ሞቴን ስጠኝ! 

አመናችሁም አላመናችሁም አሁንም ቢሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ሰላማዊ የሽግግር ለውጥ ይመጣል ብዬ አምናለሁ፡፡ 

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ሰላማዊ የሽግግር ለውጥ ይመጣል ብዬ የማምነው በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ ውስጥ ያሉት ነባራዊ እውነታዎች ይደግፋሉ በሚል ምክንያት አይደለም፣ ወይም ደግሞ የእኔ እምነቶች በኢትዮጵያ ህዝቦች ሀሳቦችም የተደገፉ ናቸው በሚል ምክንያትም አይደለም፣ እንደዚሁም ደግሞ ህወሀት 11ኛው ሰዓት ላይ ከውድቀቱ ትምህርት በመውሰድ ለውጡን ያፋጥነዋል የሚል እምነት ይኖረኛል በሚል ምክንያትም አይደለም፣ ወይም ደግሞ ህወሀት የሚፈጥረው ግጭት እና የሚከተለው የህዝቦች እልቂት እና የደም ጎርፍ አሳስቦት በምሁርነት ደረጃ እና በሰለጠነ አስተሳሰብ ተገቢውን እርምጃ በመውሰድ ህዝብን ከእልቂት ይታደጋል ከሚል ምክንያትም አይደለም፣ ኃያልና ሀገራት በጉዳዩ ላይ ጣልቃ በመግባት በዘህወሀት ላይ ጫና በማሳደር ወደ ህሊናው እንዲመለስ ያስገድዱታል በሚል ምክንያትም አይደለም፣ እንደዚሁም ደግሞበመሆኑ ምክንያት አይደለም 

በኢትዮጵያ ውስጥ አሁንም ቢሆን ሰላማዊ የሽግግር ለውጥ ሊደረግ ይችላል የሚል እምነት አለኝ ምክንያቱም ሀሳባዊ ተቆርቋሪ ኢትዮጵዊ ነኝና፡፡ 

ይቀጥላል 

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!        

ታህሳስ 12 ቀን 2008 .

 

 

Similar Posts