ዘ-ህወሀት በኢትዮጵያ የተከሰተውን ረሀብ ማቆም ይችላልን?
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ በአውዳሚ ረሀብ መካከል ተሰንጋ መያዟ ታላቅ ዓለም አቀፍ ሚስጥር ሆኖ ይገኛል፡፡
እ.ኤ.አ ከ1984-85 ወዲህ ለሁለተኛ ጊዜ የተከሰተ ታላቅ ረሀብ!
ባለፈው ሳምንት ግሎባል ፖስት/Global Post የተባለው የዜና ወኪል በርዕሰ አንቀጹ የመጀመሪያ ርዕስ በማድረግ እንዲህ የሚል ጥያቄ አቅርቧል፡
“ኢትዮጵያ ባለፉት 30 ዓመታት ጊዜ ውስጥ በአስከፊነቱ የመጀመሪያ የሆነውን ድርቅ ተጋፍጣ ትገኛለች፡፡ መንግስት በአሁኑ ጊዜ የተከሰተውን ረሀብ ማስቆም ይችላልን?”
ግሎባል ፖስት መንግስት ረሀቡን ማስቆም ይችላል ወይ የሚል ጥያቄ ያቀረበለት እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) እያለ ለሚጠራው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ (ዘ-ህወሀት) ነው፡፡
እ.ኤ.አ ወደ 1984-85 መለስ በማለት የነበረውን የወያኔ ታሪክ ስንመለከት ህወሀት በኢትዮጵያ ውስጥ አሸባሪ ቡድን ነበር፡፡
በአሁኑም ጊዜ ህወሀት በዓለም አቀፍ የአሸባሪዎች የመረጃ ቋት/Global Terrorism Database ስም ዝርዝር ውስጥ ስሙ ሰፍሮ አሸባሪ ቡድን ተብሎ ተፈርጆ ይገኛል፡፡
ከዚህ አንጻር በአሁኑ ጊዜ ሊቀርብ የሚችለው ዋና ጥያቄ፡ ዘ-ህወሀት በኢትዮጵያ የተከሰተውን ረሀብ ማስቆም ይችላልን? የሚለው ነው፡፡ (“ዘ” የምትለዋ ፊደል ዘራፊ የሚለውን ቃል ትገልጻለች፡፡ የዘራፊ መንግስት ማለት ደግሞ ለዘራፊዎች በዘራፊዎች የተቋቋመ የዘራፊ ወሮበላ መንግስት ማለት ነው፡፡)
ከዚህ በላይ ለቀረበው ጥያቄ መልስ ሊሆን የሚችለው፡ ዘ-ህወሀት የልመና አኮፋዳውን በመያዝ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ላይ የምግብ ልመናን፣ ተመጽዋች መሆንን ሊያቆም ይችላልን? የሚል ይሆናል፡፡
ላለፉት 24 ዓመታት ዘ-ህወሀት በኢትዮጵያ ሲከሰት የቆየውን የረሀብ ችግር ለመቋቋም ሲል በእያንዳንዱ ዓመት ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የምግብ እርዳታ የልመና ጥያቄ ሲያቀርብ እና ምጽዋዕት መጽውቱኝ እያለ ሲማጸን ቆይቷል፡፡
በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ዓለም አቀፍ የምግብ እርዳታ ልመና፣ የተመጽዋችነት ሱሰኞች እና በአሜሪካ ከተማ ማዕከል በሚገኘው ጠባብ መንገድ እየተዘዋወረ የዜጎችን አዕምሮ በሚያደነዝዘው አደንዛዥ የሀሺሽ ዕጽ አዘዋዋሪዎች መካከል ያለው ልዩነት በጣም ትንሽ ነው፡፡
ሁለቱም አንድ ዓይነት ባህሪ አላቸው፡፡
ያላቸው ብቸኛው ልዩነት የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የልመና ሱሰኞች በደንብ ያልተሰፋ ሱፍ ልብስ ለብሰው መዞራቸው ብቻ ነው።
አንድን ሰው ልመናን እንደ ሙያ ባህል በመያዝ እንደ ህይወት መርሆው አድርጎ እየተጠቀመበት የሚሄድ ከሆነ እንዴት አድርጎ ነው ውርደትን በማስወገድ የእራሱን ክብር ሊይዝ የሚችለው?
አንድ ሰው በምን ዓይነት መስፈርት እና መለኪያ ነው ከልመና ወጥቶ ባለፋብሪካ ሊሆን የሚችለው?
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አጠቃላይ ሁኔታ በሸክስፒር ስለኪንግ ጆን የተቋጠሩትን እና እንዲህ የሚሉትን ለአሁኑ ሁኔታ ተስማሚ የሆኑ የግጥም ስንኞች አስታወሰኝ፡
ለማኝ በሆንኩ ጊዜ በርትቼ እዞራለሁ፣
ጸሐይ ቁር ውርጅብኝ ማለትን ትቻለሁ፣
በመዞር፣ በመንጎድ ምጽዋት አግኝቻለሁ፡፡
ምንም ሀጢያት የለም ሀብታም መሆን እንጅ፣
ምጽዋትን ማግበስበስ ከዘመድ ወዳጅ፣
ክብር እና ሞገስን በመጣል ከደጅ፣
ልመናን ማጦፍ ነው ከነጭ ከፈረንጅ፣
እናም ብልሀቱ የማግኘት ዘዴው፣
ሌት ከቀን ልመናን ባህል ማድረግ ነው፣
ክብር እና ህሊናን ገደል መጣል ነው፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች ልመናን ክብር እና ሞገስ አድርገውታል፡፡
ለእነርሱ ከሚገኘው እርዳታ በሙስና እያግበሰበሱ ለግል ጥቅማቸው በማዋል ርካሽ ሀብታምነትን መጎናጸፍ እንጅ በልመና ጊዜ ምንም ዓይነት የሞራል ስብዕና ኪሳራ ጉዳይ የሚባል ነገር አይነካቸውም፡፡
ባለፉት ስምንት ዓመታት የታየው መረጃ በትክክል እንደሚያረጋግጠው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የለማኝ አገዛዝ መሆኑን በውል ያመላክታል፡፡
እ.ኤ.አ የካቲት 2014 እንዲህ የሚል ዘገባ ቀርቦ ነበር፣ “ኢትዮጵያ 2.7 ሚሊዮን የሚሆኑ ረሀብተኛ ዜጎቿን ለመመገብ የለጋሽ ድርጅቶችን እርዳታ አጥብቃ ትሻለች፡፡“ እ.ኤ.አ በ2014 መጀመሪያ አካባቢ የዩኤስ አሜሪካ ግብር ከፋይ ሕዝብ ለዚያ ረሀብ ግዙፍ የሆነ 218 ሚሊዮን ዶላር ችሮታ ሰጥቶ ነበር፡፡
እ.ኤ.አ በ2013 ኢትዮጵያ ከ4 ሚሊዮን በላይ የሚሆን ህዝብ ለመመገብ ወደ 700 ሚሊዮን ዶላር አካባቢ የሚሆን ገንዘብ ለሰብአዊ እርዳታ ተቀብላለች፡፡ የዩኤስ አሜሪካ ግብር ከፋይ ሕዝብ 236 ሚሊዮን ዶላር ችሮታ ሰጥቶ ነበር፡፡
እ.ኤ.አ መስከረም 2012 “የኢትዮጵያ መንግስት በዚህ ዓመት በነሐሴ እና በታህሳስ መካከል 3.7 ሚሊዮን እና በጥር ወር ደግሞ 3.2 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎቹ ሰብአዊ እርዳታ እንደሚያስፈልገው ይፋ አድርጓል፡፡“ የዩኤስ አሜሪካ ግብር ከፋይ ሕዝብ 307 ሚሊዮን ዶላር ችሮታ ሰጥቶ ነበር፡፡
እ.ኤ.አ በ2011 ለኢትዮጵያ የተሰጠው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ እርዳታ 500 ሚሊዮን ደርሷል፡፡ የዩኤስ አሜሪካ ግብር ከፋይ ሕዝብ 313 ሚሊዮን ዶላር ችሮታ ሰጥቶ ነበር፡፡
እ.ኤ.አ ነሐሴ 2010 የተባበሩት መንግስታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት/Food and Agricultural Organization (FAO) እንዲህ የሚል ዘገባ አውጥቶ ነበር፣ “ወደ 5.2 ሚሊዮን አካባቢ የሚገመት የኢትዮጵያ ህዝብ እስከ አሁን ድረስ የአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ጥገኛ ሆኖ የሚገኝ ሲሆን የተለያዩ ድርጅቶች በረዥም ጊዜ ዕቅድ በሀገሪቱ ውስጥ አስከፊ የሆነ ረሀብ ሊከሰት እንደሚችል ከስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡“
ሂዩማን ራይትስ ዎች የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት እ.ኤ.አ በ2010 ባወጣው ዘገባ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ከዓለም አቀፉ እርዳታ ሰጭ ድርጅት የተገኘውን እርዳታ ለማዳበሪያ፣ ለዘር እና ለስራ አገልግሎት እንዲውል በመመደብ የአከባቢ ባለስልጣኖች፣ ሚሊሻዎች እና ሰላዮች ያሉበት ሰፊ መሰረትን በመዘርጋት ማን ምን ማግኘት እንዳለበት፣ መቸ እና እንዴትስ ማግኘት እንዳለበት ይጫወቱ የነበረውን ተደጋጋሚ እና ገዳይ የሆነ ጨዋታ ግልጽ በሆነ መልኩ መዝግቦት ይገኛል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ 588 ሚሊዮን ዶላር የሚሆነውን ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የተገኘውን እርዳታ ከተራበው የህዝብ ጉሮሮ በመንጠቅ ለግሉ በማድረግ እንክት አድርጎ በልቶታል፡፡
እ.ኤ.አ በ2010 የዩናይትድ ስቴትስ የመንግስት መምሪያ ዋና ተቆጣጣሪ የሆነው ቢሮ የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት/United States Agency for International Development (USAID) የተባለው ድርጅት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ተብሎ ከአሜሪካ ግብር ከፋይ ሕዝብ የተገኘውን በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠረውን ዶላር ለምን ለምን ተግባር ሊያውለው እንደሚገባ ሊገልጽ የሚችል ትክክለኛ መንገድ እንደሌለ እንዲህ በማለት በግልጽ አስቀምጧል፡
ዩኤስኤይድ/ኢትዮጵያ (USAID/Ethiopia) ለገበያ መር ኢኮኖሚ እድገት ስኬታማነት የእራሱን ሚና እየተጫወተ እና ገበሬዎች፣ አርብቶ አደሮች እና ሌሎች በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ተጠቃሚዎች ሁሉ ከተፈጥሮ አደጋ ሊቋቋሙባቸው የሚችሉባቸውን መንገዶች ያመላከተ ነው ቢባልም ድርጅቱ ተጫውቶታል ተብሎ የተነገረለትን ሁኔታ እና ያበረከተውን ድርሻ በእርግጠኝነት መለካት አልተቻለም፡፡ ይህም የሆነበት ዋናው ምክያት የድርጅቱ የአፈጻጸም አስተዳደር እና ዘገባ የማቅረብ ስርዓቱ ደካማ ከመሆኑ አንጻር ነው፡፡
እ.ኤ.አ በ2009 የተባበሩት መንግስታት እንዲህ የሚል ዘገባ አውጥቷል፣ “ወደ 4.8 ሚሊዮን ገደማ የሚሆን ህዝብ የአስቸኳይ ጊዜ ለምግብ እና ለተመሳሳይ ጉዳዮች የሚውል እ.ኤ.አ በ2010 የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት 270 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ያስፈልጋል“ ብሎ ነበር፡፡ ከዚህ አኳያ የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ግብር ከፋይ ሕዝብ 346 ሚሊዮን ዶላር ችሮታ ሰጥቶ ነበር፡፡
እ.ኤ.አ ነሐሴ 2009 ዘኢንዲፔንደንት/The Independent የተባለው የእንግሊዝ ብሄራዊ መጽሔት እንዲህ የሚል ዘገባ አውጥቶ ነበር፣ “በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ደኃ ኢትዮጵያውያን የአልሚ ምግብ ንጥረ ነገር እጥረት እና ምናልባትም ለአስርት ዓመታት ሊዘልቅ የሚችል አስከፊ የሆነ የረሀብ አደጋ በዚህ የበጋ ወቅት ተጋርጦባቸዋል፡፡ እናም በዚህ ዓመት የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ የሚፈልጉት ተረጅዎች ቁጥር ተከታታይነት ባለው መልኩ እየጨመረ በመምጣት በጥር ወር ከነበረበት ከ5.3 ሚሊዮን ከፍ በማለት በግንቦት ወር 6.2 ሚሊዮን ሊደርስ ችሏል፡፡“
እ.ኤ.አ በ2008 የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በኢትዮጵያ ተረጅ ህዝብ ስም ከአሜሪካ ግብር ከፋይ ሕዝብ የተገኘውን 479 ሚሊዮን ዶላር የሰብአዊ እርዳታ ገንዘብ በመቀበል ወደ ኪሱ አጭቆታል፡፡
ባለፈው ሳምንት የኒዮርክ ታይምስ ጋዜጣ እንዲህ የሚል ዘገባ አውጥቷል፣ “የኢትዮጵያ መንግስት ቀደም ሲል በነሐሴ ወር የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ የሚያስፈልገው የተረጂ ህዝብ ቁጥር 4.55 ሚሊዮን የሚገመት የነበረ ሲሆን ይህ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመር አሁን (ሁለት ወር ሳያልፍ) ወደ 8.2 ሚሊዮን አካባቢ ደርሷል“ ብሎ ነበር፡፡
ኢትዮጵያ እንደገና የተራቡ ህጻናትን ስዕሎች በማውጣት የሰብአዊ እርዳታ መለመኛ አድርጋ በመገኘቷ ዘገባውን ያስደነቀበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ኢትዮጵያን የረሀብ መቅሰፍት የሆነው የባለጥቁር የምጻት ፈረሱ (ረሀብ) የማስተዋወቂያ መሬት እንድትሆን አድርጓታል፡፡
በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በረሀብ የተጠቁ ኢትዮጵያውያንን ቁጥር ከ4.5 ሚሊዮን በሁለት እጥፍ በማሳደግ ወደ 8.5 ሚሊዮን አድርሶታል፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እንዲህ ዓይነት ድድብና የተሞላበትን የቁጥር ጨዋታ ነው በመጫወት ላይ የሚገኘው፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሁሉንም ነገር በማካተት በአንድ ጊዜ እውነታውን አይናገርም፡፡ ረሃቡን ቀላል ለማስመሰል ትንሽ በትንሽ እና ቀስ በቀስ ነው የሚገልጸው፡፡
የአሁኑን የረሀብ ሁኔታ ከግንዛቤ በማስገባት በዚህ ዓመት መጨረሻ (እ.ኤ.አ) የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በረሀብ የተጠቃውን ህዝብ ቁጥር ወደ 12 ሚሊዮን በማድረስ ሊያውጅ ይችላል የሚል ጥያቄ ሊያስነሳ የሚችል ሊሆን አይችልምን?
እ.ኤ.አ በ2016 የክረምት ወቅት አቶ “ኤል ኒኖ” በሀገሪቱ ላይ ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ጥላውን ካጠላ በኋላ ወደ 25 ሚሊዮን ገደማ የሚደርስ የኢትዮጵያ ሕዝብ የረሀብ ሰለባ ከባለጥቁሩ ፈረስ መዳፍ ስር ሆነው በመሰቃየት የሚገኙ ሊሆኑ አይችሉምን?
የ2015-16 የምጽአት ቀን!
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ቅን ልቦና አስመሳይነት፣
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እራሳቸውን እያንዳንዱን ሰው የሚበልጡ እና የሚያደናግሩ አታላዮች አድርገው ይቆጥራሉ፡፡ እነርሱ ማንንም ሳይሆን እራሳቸውን ብቻ ነው በማሞኘት ላይ የሚገኙት፡፡
እውነታው ፍርጥ ፍርጥርጥ ብሎ ሲታይ ግን ባለፉት 24 ዓመታት ጊዜ ውስጥ በእያንዳንዷ ዓመት የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ሲለምን እና በመቶ ሚሊዮኖች ዶላር የሚቆጠርን ገንዘብ ከዩኤስ አሜሪካ እና ከሌሎች ምዕራባዊ ለጋሽ ድርጅቶች እያጋበሰ ወደ ኪሱ ሲጨምር ነው የቆዬው፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ይህንን የልመና ባህል ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻሻለው እና እያዳበረው ስለመጣ ቃሉን በትክክለኛው መንገድ ለመግለጽ “የለማኝ መንግስት” በማለት ሰይሜዋሁ፡፡
እ.ኤ.አ ጥቅምት 2014 በዋናነት ዓለም አቀፍ ቀፍ እርዳታዎችን (እርዳታ + ብድር) እና ለሕገወጥ ድርጅቶቻቸው ሕጋዊ ሽፋን በመስጠት በብድር እና በእርዳታ በሕዝብ ስም የሚመጣውን የእርዳታ ገንዘብ በተለያዩ ዓይነት የሙስና መገለጫዎች እና ተሞክሮዎች አማካይነት ለእራሳቸው ጥቅም እና ትርፍ ማጋበሻ የሚያደርጉትን አገዛዞች እና መንግስታትን ለማጥናት እንዲያስችል በመቀመር “የለማኝ መንግስት” በማለት የቃሉን ጽንሰ ሀሳብ ለማስተዋወቅ ሞክሪያለሁ፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ለማኝ መንግስት የናይጀሪያ ብሔራዊ ደራሲ እና ቃል አቀባይ የሆኑት አለቃ ኦባፌሚ አዎሎዎ አፍሪካውያንን ለማስጠንቀቅ እንደሞከሩት ሁሉ አንድ ዓይነት የለማኘ መንግስት ነው፡፡
እ.ኤ.አ በ1967 ተካሂዶ በነበረው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት 4ኛ ጉባኤ ላይ አለቃ አዎሎዎ ጥንቃቄ በተሞላበት እና ነብይነትን ባካተተ መልኩ እንዲህ በማለት ትንበያ በመስጠት አስጠንቅቀው ነበር፡
በአሁኑ ጊዜ አፍሪካ እርስ በእርሳቸው የሚወዳደሩ የአፍሪካ ሀገሮች የለማኞች አህጉር ናት፡፡ ከቀድሞዎቹ ቅኝ ገዥዎች አለቆቻችን መዳፍ ስር ወድቀን የተሻለ ነገር ለማግኘት አንዳችን በአንዳችን በመመቃቀን ላይ እንገኛለን፡፡ ይህንንም በማድረግ ሆን ብለን የእጅ አዙር ቅኝ ገዥዎች በተለያዩ የአህጉሪቱ ግዛቶች በመግባት የምጣኔ ሀብት ዕድሎቻችንን እንዲወስኑ እና እንዲቆጣጠሩ በማድረግ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ላይ እንገኛለን…
…ስለሆነም ያለንን ስልጣን በመጠቀም እና የትኛው ሉዓላዊነት ተጽዕኖ እንደሚፈጥር ከግንዛቤ በማስገባት እንደዚሁም ሁሉ ምን ዓይነት ዘዴዎችን እና ሸፍጦችን እንደምንተገብር እና የትኛውን ዓይነት ዓለም አቀፍ ዴፕሎማሲ በመጠቀም ከእርዳታ ሰጭ ድርጅቶች የበለጠ ምጽዋዕት ለመቀበል ይህንን ድርጊታችንን ልንቀጥልበት እንድምንችል እና በእርግጥም በትክክለኛው መስመር ላይ እንዳለን በመቁጠር በድርጊቱ ልንቀጥልበት እንችላለን፡፡ ሆኖም ግን ከጊዜ ወደጊዜ ችግር በመፍጠር ላይ የሚገኘው ዋናው ሰይጣን ሌላ ከማንም ጋር ሳይሆን ከእኛ ጋር ተጣብቆ ይገኛል፡፡ ለማኝ እንዲወገድ ካልተደረገ እና ሊመለስ በማይችል መንገድ እጁን ከልመና ወደ ልማት አቅጣጫ እስካላዞረ ድረስ የእርሱን የልመና ባህል በማጠናከር ለዘላለሙ ለማኝ እንደሆነ ይኖራል፡፡ ይህ ዓይነት አገዛዝ ብዙ በለመነ ቁጥር ተነሳሽነት የጎደለው፣ ድፍረት የሌለው እና በእራስ የመተማመን ባህልን በማስወገድ ልመናን ባህል እያደረገ የሚጓዝ ይሆናል፡፡ (አጽንኦ ተጨምሯል፡፡)
የአለቃ አዎሎዎ ማስጠንቀቂያ ከተሰጠ ከግማሽ ምዕተ ዓመት ገደማ በኋላ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የልጆች የረሀብ ማስታወቂያ ፖስተሮች ለአፍሪካ ለማኞች አንጸባራቂ ምሳሌ ሆነው ቀርበዋል፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በአሁኑ ጊዜ 9 ሚሊዮን የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን የረሀብ ሰለባዎች መመግብ ይችላልን?
የሚችል ከሆነስ በምን ዓይነት ሁኔታ እና እንዴት?
ከዓለም ሕዝብ ምግብ በመለመን?
ልመና፣ ልመና፣ ልመና፣ ልመና…
በታሪክ በየትኛውም ሀገር ቢሆን በምጽዋዕት እና በልመና ረሀብን ማስወገድ የተቻለበት ክስተት የለም፡፡
ታዲያ እውነታው ይህ ከሆነ የማይሞከረውን እና ከቶም ሊፈጸም የማይችለውን ነገር ኢትዮጵያ እንዴት ተግባራዊ ማድረግ ተችላለች?
ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ከፍተኛ የሆነውን የውጭ እርዳታ ስትቀበል የቆየች እና አሁንም በመቀበል ላይ የምትገኝ ሀገር ናት፡፡
የውጭ እርዳታ ከፍተኛ በሆነ መልኩ ለልመና የሚያመች አማላይ ቃል ነው፡፡ ይህ ቃል በሀገሮቻቸው ሕዝቦች ስም ለሚለምኑ ለማኝ ለሆኑ አገዛዞች የተሰጠ ስያሜ ነው፡፡
እንደ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ እርዳታ/Global Humanitarian Assistance ከሆነ እ.ኤ.አ በ2012 ኢትዮጵያ 484 ሚሊዮን ዶላር ዓለም አቀፍ እርዳታ በመቀበል ከዓለም በእርዳታ ተቀባይነት በ7ኛ ደረጃ ላይ እንድትገኝ አድርጓታል፡፡
እ.ኤ.አ በ2013 በመጀመሪያ የተገመተው እርዳታ 550 ሚሊዮን ዳላር ነበር፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ባለፉት አስር ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያ የሰብአዊ እርዳታ ከሚቀበሉ 10 የመጀመሪያዎቹ ሀገራት ስም ዝርዝር ውስጥ ስሟ ሰፍሮ እንደሚገኝ ድርጅቱ ዘገባውን አቅርቧል፡፡ እ.ኤ.አ በ2008 በኢትዮጵያ የሰብአዊ እርዳታ በከፍተኛ ደረጀ በማደግ 987 ሚሊዮን ዶላር በመድረስ ከዓለም ሁለተኛዋ ታላቅ እርዳታ ተቀባይ ሀገር በመሆን ተመዝግባለች፡፡
በሌላ አገላለጽ ኢትዮጵያ በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አገዛዝ ዘመናት አስር ዓመታት ውስጥ ከአፍሪካ ከሁሉም ሀገሮች መካከል በመጀመሪያው ረድፍ ላይ የምትገኘ ሲሆን ከዓለም ሀገራት ደግሞ ሰብአዊ እርዳታን ከሚቀበሉ ሀገሮች 10 የመጀመሪያ ሀገሮች መካከል አንዷ ሆናለች፡፡
እንደ የልማት እርዳታ ቡድን በኢትዮጵያ የተባለው እና በኢትዮጵያ የሚገኘው የለጋሽ ድርጅቶች ስብስብ ዘገባ ከሆነ እ.ኤ.አ በ2008 ለኢትዮጵያ ለልማት ተብሎ የተሰጠው እርዳታ 3.819 ቢሊዮን ዶላር፣ እ.ኤ.አ በ2010 ደግሞ 3.525 ቢሊዮን ዶላር እና እንደዚሁም በ2011 3.563 ቢሊዮን ዶላር ነበር፡፡
እ.ኤ.አ በ2011 እንግሊዝ በሚቀጥሉት አራት ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ከፍተኛውን ደረጃ የልማት እርዳታ ተቀባይ ሀገር አድርጋ መርጣታለች፡፡
ዩኤስ አሜሪካ ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አገዛዝ የምትሰጠውን የልማት እርዳታ እ.ኤ.አ በ2005 ከነበረበት 1.8 ቢሊዮን አካባቢ በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ እ.ኤ.አ በ2008 ወደ 3.5 ቢሊዮን ዶላር ከፍ እንዲል አድርጋለች፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በሶስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ከአሜሪካ ግብር ከፋይ ሕዝብ የሚያገኘውን የእርዳታ ምጽዋዕት ግማሽ በግማሽ ያህል ከፍ እንዲል ከፍተኛ ጥረት አድርጓል፡፡
የዩኤስ አሜሪካ መንግስት ከኢትዮጵያ በተለይም ማህበረ ረድኤት ትግራይ (ማረት)/Relief Society of Tigray (REST) እየተባለ ከሚጠራው ድርጅት ጋር የምግብ እርዳታን በጋራ በማስተዳደር ላይ ይገኛል፡፡
ባለፈው ዓመት ዩኤስኤአይዲ/USAID እንዲህ የሚል መግለጫ አውጥቶ ነበር፣ “ማረት/REST በዩኤስኤአይዲ/USAID ድጋፍ ከድርጅቱ ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ የምግብ ለስራ ፕሮግራምን/Productive Safety Net Program (PSNP)ን ከሚተገብሩ አራት መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች መካከል አንዱ ነው፡፡ ሌሎቹ ደግሞ የካቶሊክ እርዳታ አገልግሎት/Catholic Relief Servicesን፣ ምግብ ለተራቡ/Food for Hungry እና የህጻናት አድን ድርጅት/Save the Childrenንን ያካትታል፡፡“
በአሁኑ ጊዜ ከዩኤስ አሜሪካ እርዳታ የአንበሳውን ድርሻ (ይቅርታ የጅቡን ድርሻ) የሚወስደው ማን ሊሆን ይችላል ብላችሁ ታስባላችሁ?
ማረት/REST ምንድን ነው?
ማረት/REST እ.ኤ.አ በ1984-85 በወቅቱ በረሀብ ሰለባ ለወደቀው ለትግራይ ሕዝብ ተብሎ ከዓለም አቀፍ እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች ቀርቦ የነበረውን እርዳታ ከታለመለት ውጭ በመቀልበስ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች ለድርጅቱ ወታደራዊ እና ለመሪዎቹ ያከፋፈለ በእርዳታ ሰጭነት ስም የተቋቋመ አጭበርባሪ ድርጅት ነው፡፡
“ለመስረቅ ፈቃድ ያለው ድርጅት” በሚል ርዕስ እ.ኤ.አ በ2010 አቅርቤው በነበረው እና በሁፊንግተን ፖስት/Huffington Post ድረ ገጽ በተለቀቀው ትችቴ ላይ የማረት/RESTን አጭበርባሪነት እና መሰሪነት ግልጽ አድርጌ ነበር፡፡
ማረት/REST ከሶስት አስርት ዓመታት በፊት ለረሀብ ተብሎ ለሕዝብ እንዲቀርብ ከእርዳታ ሰጭ ድርጅቶች የተላከውን እርዳታ እያጭበረበረ ከታለመለት ዓላማ ውጭ ለእራሱ የግል ጥቅም ሲያውል የነበረበት የሽፍጥ አካሄድ ድርጅቱ ቅንነት የሌለለው ሰይጣናዊ ድርጅት መሆኑን በግልጽ የሚያመላክት ነው፡፡
እ.ኤ.አ በ1984-85 መጀመሪያ አካባቢ ማረት/REST ያደረገው የምግብ እርዳታ የማጭበርበር ሸፍጥ ሶስት ደረጃ ሂደቶችን የያዘ ነበር፡፡
በደረጃ ሂደት አንድ ላይ አንድ የህወሀት/ማረት ባለስልጣኖች ቡድን ሕጋዊ የእህል ነጋዴ መስሎ በማጭበርበር በመቅረብ በርካታ የሆኑ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የምግብ እርዳታ አከፋፋይ መስሎ በመቅረብ ለረሀብ ሰለባ ለሆኑት ተጠቂዎች በአፋጣኝ እና በአስቸኳይ እህል በማቅረብ መሸጥ እና ማከፋፈል እንደሚችል የአጭበርባሪነት አንደበቱን ተጠቅሞ ተግባራዊ እንዲሆን አድርጎ ነበር፡፡
ከዚህ ጎን ለጎን ህወሀት ከተለያዩ ምንጮች ማለትም መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ጨምሮ ለእርሱ ተዋጊዎች አገልግሎት የሚውሉ በድብቅ በርካታ የሆነ የምግብል እህል በማግኘት በመጋዝኑ ውስጥ እንዲታጨቅ አደረገ፡፡ ይኸ በድብቅ እና በሚስጥር በመጋዝን ውስጥ የታጨቀው የምግብ እህል ክምችት በእርግጥ መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ለሽያጭ የቀረበ ነበር፡፡ የህወሀት/ማረት እህል አዳዮች የሽያጭ ስራውን በማከናወን ካጠናቀቁ በኋላ የእህል ሽያጭ ክፍያቸውን ከመንግስታዊ እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች በመቀበል ወደሚደበቁበት ቦታቸው ተመለሱ፡፡
በደረጃ ሂደት ሁለት ላይ ሌላ የህወሀት/ማረት ቡድን በትግራይ ውስጥ የምግብ እርዳታ እህሉን የማከፋፈል ኃላፊነቱን ተረከበ፡፡ መንግስታዊ ባልሆኑ እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች ዘንድ ታማኝነትን ለማትረፍ ሲሉ የህወሀት/ማረት ባለስልጣኖች በድብቅ ባለው የክምችት መጋዝናቸው እና በማከፋፈያ ጣቢያዎች የፍተሻ ስራዎችን በመስራት የማስመሰል ዕኩይ ምግባራቸውን ማድረግ ቀጠሉ፡፡ ሆኖም ግን በመጋዝኑ ውስጥ ታላቅ የማጭበርበር ድርጊትን ፈጽመዋል፡፡ ያንን ሸፍጥ የተሞላበትን ማጭበርበር እንደተመለከተው አንድ የህወሀት አባል የዓይን ምስክርነት “እዚያ ሄዳችሁ ብትመለከቱ ግማሽ ያህሉ የመጋዝኑ ቦታ አሸዋ በተሞሉ ጆንያዎች የተሞላ ነበር“ በማለት ሸፍጡን ይፋ አድርጓል፡፡ መንግስታዊ ያልሆኑ የእርዳታ ሰጭ ድርጅቶች ተወካዮች የእህል ክምችት ያለባቸውን ቦታዎች በመገኘት በዓይን በማየት ፍተሻ እና ምርመራ በማድረግ አስተያየታቸው እንዲጸድቅ በማድረግ እንደገና ተጨማሪ የእህል ግዥ ለመፈጸም ወደ ሱዳን ይመለሱ ነበር፡፡
በደረጃ ሂደት ሶስት ላይ አንድ ዓይነት ወይም ሌላ የህወሀት/ማረት ባለስልጣን ቡድን ወደ መንግስታዊ ያልሆኑ እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች በመሄድ በሌሎች የተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ሊሰራጭ የሚችል እህል ሽያጭ ክንውን እንዲፈጸም እና እንዲታደል ሀሳብ ያቀርባል፡፡ በዚህ መልኩ የተገኘው አዲስ እህል ወይም ደግሞ ንጹህ የሆነ እህል ለረሀብ ሰለባዎቹ አይታደልም ነበር፡፡ ከዚያ ይልቅ በትግራይ በተለያዩ አካባቢዎች ድብቅ የእህል መጋዝን ውስጥ የነበረው እየተጫነ መንግስታዊ ላልሆኑት እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች የለገሷቸው አዲስ እና ንጹህ የሆነው እህል ለረሀብ ሰለባው ሕዝብ እየተሰራጨ የሚደርስ በማስመሰል የለየለት የማጭበርበር የሸፍጥ እኩይ ምግባራቸውን ፈጸሙ፡፡ የእርዳታ ሰጭ ሰራተኞች ነጻ በሆነ መልኩ አዲሱ እህል ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ በመወሰድ የሚሰራጭ እና የሚታደል መሆኑን የሚያረጋግጡበት ዘዴ ስለሌላቸው በጣም ፈጣን እና ጥልቀት የሌለው ዓይነት ፍተሻ በማድረግ ክፍያዎችን ይፈጽሙ ነበር፡፡
በዚያ ዓይነት ሁኔታ ህወሀት/ማረት ቀደም ሲል አንድ ጊዜ የተገኘውን እህል ብዙ እና ለበርካታ ጊዚያት በመደጋገም እየሸጡ በርካታ ሚሊዮን ዶላር ሽያጭ ለማግኘት ቻሉ፡፡ ህወሀት/ማረት እ.ኤ.አ በ1985 መንግስታዊ ካልሆኑ እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች ጋር ያላቸውን ሸፍጥ የተሞላበት የማጭበርበር የንግድ እንቅስቃሴ ተግባራዊ ለማድረግ እና በእርዳታ ሰጭ ሀገሮች የተላከውን የመርከብ እህል እየሸጡ ለእራሳቸው ጥቅም አዋሉት፡፡
እ.ኤ.አ በ2009 የዩኤስ አሜሪካ የመንግስት መምሪያ ለምግብ እና ለጸረ ድህነት እንቅስቃሴዎች እርዳታ እንዲውል ተልኮ የነበረውን 850 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ በወቅቱ በነበረው የፓርቲው ጠቅላይ ሚኒስትር ትዕዛዝ የፖለቲካ ወገንተኝነትን በያዘ መልኩ የታደለ ለመሆኑ ምርመራ እንዲደረግበት ቃል ገብቶ ነበር፡፡
ሆኖም ግን እስከ አሁን ድረስ ምንም ዓይነት የምርመራ ዘገባ አልቀረበም፡፡ (የአሜሪካ ግብር ከፋይ ሕዝብ ዶላር ለፖለቲካ ወገንተኝነት ወይም ደግሞ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አላማጭ ተምቾች በውድ ሆቴሎች እየተዘዋወሩ ኮኛክ ሲገለብጡበት፣ የተለያዩ ውድ ምግቦችን ሲያማርጡበት እና ሌሎችን ሕገወጥ ድርጊቶች በመፈጸም በብክነት ላይ ውሏል በማለት ዩኤስኤአይዲን ለበርካታ ጊዚያት አስጨንቄ በመያዝ ጥያቄ እያቀረብኩለት ነበር፡፡)
በአሁኑ ጊዜ የዩኤስ አሜሪካ መንግስት ቀደም ሲል እንደዚያ ያለ የማጭበርበር ስራ ሲሰራ የነበረውን ማረት የተባለውን ያንኑ ሸፍጠኛ ድርጅት በኢትዮጵያ የረሀብ ሰለባ ለሆኑ ወገኖች የእርዳታ እህል ማከፋፈል እንዲችል በድጋሜ መርጦታል፡፡
እንግዲህ እስኪ አስቡት የዩኤስ መንግስት የረዥም ጊዜ ግንኙነት (ሽሪካ) (የዩኤስኤአይዲን አባባል በመዋስ ከማረት ጋር ባለው የትብብር ግንኙነት) የማፍያው ኮሚሽን ወይም ደግሞ በአሜሪካ በከተሞች አካባቢ ለሚገኙት ድሆች የእርዳታ እና የማህበራዊ አገልግሎቶችን ለማከፋፈል የተዘጋጀ የማቃጠያ እቶን/ፈርናስ ነው የሚሆነው፡፡
የአሜሪካ ግብር ከፋይ ሕዝብ በእንደዚህ ያለው የመንግስታቸው ወራዳ የቅሌት ተግባራት ቢያውቁ ከባድ ትያቄ ያቀርቡ ነበር።
ሆኖም ግን በአሜሪካ ግብር ከፋይ ሕዝብ ሊታወቅ በማይችል መልኩ በድብቅ በኢትዮጵያ በስልጣን እንደመዥገር ተጣብቆ ከሚገኘው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ጋር ሽርክና በመፍጠር በአሜሪካ ግብር ከፋይ ሕዝብ ላይ ተመሳሳይ ሸፍጥን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
በአሁኑ ጊዜ በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እና የምዕራብ ለጋሽ እና አበዳሪ ድርጅቶች የጋራ ጥምረት የተፈበረኩ አዳዲስ የማታለያ ጨዋታዎችን በመፈልፈል ለዓይናችን እይታ እንዲቀርቡ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ላለው ረሀብ መነሻው አንድ “ኤል ኒኖ” እየተባለ በሚጠራ ሰው የተከሰተ ነው በማለት የባጥ የቆጡን በመቀባጠር ላይ ይገኛሉ፡፡
የብሉምበርግ የዜና ወኪል ቃል አቀባይን ጠቅሶ እንደገለጸው ባለፈው ሳምንት አንድ አብርኃም ተከስተ እየተባለ የሚጠራ እና የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ልምድ የሌለው ሚኒስትር ደኤታ “በኢትዮጵያ ለተከሰተው ረሀብ መንስዔ ኤል ኒኖ ሲሆን አሁንም ቢሆን የኢኮኖሚ ዕድገታችን ለቀጣዮቹ 12 ወራት እስከ ሀምሌ 7 ድረስ 10 በመቶ እድገት በማሰመዝገብ አሁንም ቢሆን ግቡ የሚደረስበት ነው“ በማለት በድፍረት የገለጸ መሆኑን ይፋ አድርጓል፡፡
ምን ዓይነት ቅጥፈት ነው እባካችሁ***!
የብሉምበርግ ዘጋቢ በአሁኑ ጊዜ በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አገዛዝ “የ10 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት ይመዘገባል” የሚለው በምንም ታምር ሊሳካ የማይችል ሸፍጥ እና በአሁኑ ጊዜ ኤል ኒኖ የተባለው የአየር ለውጥ በረሀቡ ላይ ያለው ተጽዕኖም በጣም ትንሽ እንደሆነ በመግለጽ ውሸት የሚያመርተውን ተከስተ የተባለ ሚኒስትር ዴኤታ በጥያቄ አላፋጠጠዉም፡፡
ጠንካራ ትችትን የማይወዱት የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች፣ መሰረታቸውን በኢትዮጵያ ያደረጉ ጥቂት የውጭ ሀገር ዘጋቢዎች እና ሌሎች በኢትዮጵያ ያለው ኢኮኖሚ በሁለት አሀዝ ዕድገት በማስመዝገብ በዘላቂነት ይቀጥላል በማለት ያለምንም ሀፍረት ታላቅ ውሸት በማራመድ ላይ ይገኛሉ፡፡
ባለሁለት አሀዝ የኢኮኖሚ ዕድገት የሚለውን ቅጥፈት ከዓመታት በፊት ፍጹም በሆነ እና ሙሉ በሙሉ ዉሸት መሆኑን ደጋግሜ አሳይቻለሁ። ሆኖም ግን የውጭ ዘጋቢዎች ያለምንም ማሰብ በዘፈቀደ ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ጋዜጣዊ ፍትህን ለመስጠት በሚል የለዬለትን ውሸት ደግመው እና ደጋግመው መዋሸታቸውን ቀጥለዋል፡፡
ባለሁለት አሀዝ የኢኮኖሚ ዕድገት በሚለው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሸፍጥ ሙሉ በሙሉ ሸፍጥ መሆኑን ከዚህ ቀደም ባለኝ አስተማማኝ መረጃ ላይ በመመስረት ሀሰት እና ቅጥፈት መሆኑን ከማንም የውጭ ዘጋቢ ጋር ለመሞገት እችላለሁ፡፡
“የዓለም ባንክ እና የኢትዮጵያ ዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን” በሚል ርዕስ ባቀረብኩት ትችቴ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ስለ ባለሁለት አሀዝ የኢኮኖሚ ዕድገት እያቀረበ ያለውን ተራ ቅጥፈት በሬ ወለደ ከሚለው የባሰ ነው።
ግሎባል ፖስት እንዲህ የሚል ዘገባ አቅርቦ ነበር፣ “እነርሱ [ኢትዮጵያውያን] ከፍተኛ የሆነ የማህበራዊ ፕሮግራምን በሚተገብር እና በ20 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ድህነትን በግማሽ እቀንሳለሁ በሚል መንግስት እየታገዙ በአሁኑ ጊዜ በፈጣን ዕድገት ላይ ከሚራመደው ኢኮኖሚ ጋር አብረው ይኖራሉ፡፡“
በኬንያ የሚገኘው እና ደይሊ ኔሽን እየተባለ የሚጠራው ታዋቂ ዕለታዊ ጋዜጣ በቅርቡ እንዲህ የሚል ዘገባ አውጥቶ ነበር፣ “ወደ ሁለት አሀዝ ገደማ የተቃረበው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዕድገት እና ግዙፍ የሆነ የመሰረተ ልማት የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት ሀገሪቱን ከአፍሪካ ቀዳሚ የኢኮኖሚ ስኬታማ እና የውጭ መዋዕለ ንዋይ አፍሳሾችን የመሳብ ኃይል ያላት ሀገር እንድትሆን እድርጓታል“ ብሏል፡፡ ይህ አባባል ተራ የሆነ ውሸት፣ ውሸት አሁንም እንደገና ውሸት ነው!!!
ምን ዓይነት ተራ ቅጥፈት ነው***!
እውነታው ፍርጥ ፍርጥርጥ ብሎ ሲታይ ግን በዓለም ባንክ የቢዝነስ ስራ የ2015 ዘገባ መሰረት በዓለም ላይ ከሚገኙ ከ189 ኢኮኖሚዎች መካከል ኢትዮጵያ በ132ኛ ደረጃ ላይ ሆና ትገኛለች፡፡ እ.ኤ.አ በ2014 ኢትዮጵያ ትንሽ “ትሻል” ነበር ከ2015፡፡
ቢዝነስን መጀመር ከሚለው ክፍፍል ጋር ሲታይ እ.ኤ.አ በ2015 ኢትዮጵያ ከ189 ሀገሮች መካከል በ168 ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡
እ.ኤ.አ አቆጣጠር በ2014 ኢትዮጵያ ከ189 ሀገሮች ኢኮኖሚ መካከል በተመሳሳይ ክፍፍል በ165ኛ ደረጃ ላይ ትገኝ ነበር (እ.ኤ.አ በ2015 ከነበረው በመጠኑ ብልጫ በማሳዬት)፡፡
እነዚህ እውነታዎች ቢሆኑም ቅሉ እነዚህ የአዋቂ ማይም የውጭ ደንቆሮ ጋዜጠኞች በስንፍና እና አዕምሯቸውን በመሸፈን በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እና በዓለም አቀፍ የድህነት ወትዋች አቃጣሪዎች የሚቀርብላቸውን የውሸት እና የሸፍጥ መረጃ መሰረት በማድረግ ስለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዕድገት እና ኢንቨስትምነት እድገት ውሸትን እንደ በቀቀን በመድገም እና በመደጋገም ላይ ይገኛሉ፡፡
እነዚህ የውጭ ጋዜጠኞች ተራ አጭብርባሪዎች ናቸው፣ ሌላው ቀርቶ በዓለም ላይ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገበች ነው የምትባለው ሀገር ለምን ህዝቦቿን መመገብ አልቻለችም እና 10 በመቶ የሚሆነው ህዝቧ ለምን የረሀብ ሰለባ ሆነ የሚል ጥያቄ እንኳ አያቀርቡም፡፡
ወደ ኋላ መለስ ብለን ስንመለከት ስለኢትዮጵያ ዘገባ የሚያቀርቡት የውጭ ጋዜጠኞች “ብጫ ጋዜጠኞች” ወይም ተራ ወሬ ለቃሚዎች ናቸው ።
በአሁኑ ጊዜ ለማመን የሚያስቸግረው እና ትልቁ እውነታ ግን በማንኛውም በሚቻለው ነገር ሁሉ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ምድር ላይ ተንሰራፍቶ ለሚገኝው አስከፊ ረሀብ ዋናው መሰረቱ ኤል ኒኖ የተባለው የአየር ሁኔታ ነው የሚሉት ጉዳይ ነው፡፡
ጋዜጠኞች እየተባሉ የሚጠሩት ባለፉት 15 ዓመታት ቢያንስ ሶስት ኤል ኒኖዎች የነበሩ መሆናቸውን ያለማወቃቸው እውነታ አውቀው ማይም መሆንን የመረጡ መሆናቸውን ያሳያል፡፡ ሆኖም ግን እስከ አሁን ድረስ ረሀብ በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ እየታየ ባለው ሁኔታ ረሀብን ለማስወገድ እና የረሀብ ሰለባ የሆኑትን 9 ሚሊዮን የሚሆኑ ወገኖቻችንን በምን ዓይነት ሁኔታ ለማስተናገድ እንደተዘጋጁ ያለማወቃቸው ጉዳይ ነው፡፡
በእርግጥ እ.ኤ.አ በ1997-98 ተከስቶ የነበረው ኤል ኒኖ እ.ኤ.አ ከ1950 ጀምሮ ተከስቶ ከነበረው ሁሉ በጣም ትልቅ በመሆን በሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ ነበር፡፡ ሆኖም ግን በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ እየታዬ እንዳለው አውዳሚ ረሀብ በአስከፊ ሁኔታ የተከሰተ አልነበረም፡፡
እንደተባበሩት መንግስታት ዘገባ ከሆነ በኢትዮጵያ ያሉ የረሀብ ሰለባዎች በአሁኑ ጊዜ በእርስ በእርስ ጦርነት እየተበጣጠቀች ካለችው ሶርያ በከፋ መልኩ በሚቀጥለው ዓመት ወደ 15 ሚሊዮን የሚሆን ህዝብ በረሀብ በመጠቃት የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋል (አጽንኦ ተጨምሯል፡፡)
ዘገባው እንዲህ በማለት ተጨማሪ አስተያየቱን ግልጽ አድርጓል፣ “በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጠንካራ የእርዳታ ምላሽ እስካልተሰጠ ድረስ ከፍተኛ የሆነ የምግብ ዋስትና እጦት እና የምግብ ቀውስ ሊፈጠር የሚችልበት አጋጣሚ ሊከሰት ይችላል፡፡“
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እና ምዕራባውያን ለጋሽ እና አበዳሪ ድርጅቶች የኢትዮጵያ ህዝቦች በረሀብ ሲያልቁ ደስታ እና ፈንጠዝያ እያደረጉ ነው በማለት የዓለምን ሕዝብ በማታለል ለማሳመን በመውተርተር ላይ ይገኛሉ፡፡
ከጥቂት ሳምንታት በፊት የመንግስት ኮሙኒክሽን ጉዳዮች ሚኒስትር የሆነው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ቀልደኛ ሬድዋን ሁሴን የተባለው በሀገሪቱ ውስጥ አስከፊ የሆነ የምግብ ቀውስ እንዳለ ዕውቅና የሰጠ ሲሆን የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እርዳታ ማድረግ እንደማያስፈልግ እና በመንግስት አቅም ሁሉም ነገር መሸፈን እንደሚችል ዓይኑን በጨው ታጥቦ በድፍረት ውሸት ተናግሮ ነበር (ሀሳቤን በተሻለ ሁኔታ ይገልጽልኝ እንደሆን መናገር ሳይሆን መቀደድ ልበለው ይሆን?)
ሬድዋን እንዲህ ይላል “ኢትዮጵያ የውጭ የምግብ እርዳታ አትፈልግም፡፡“ ሆኖም ግን የኢትዮጵያ መንግስት ከሬድዋን መግለጫ ጋር በተጻረረ መልኩ 8.2 ሚሊዮን የሚሆነውን የረሀብ ሰለባ የሆነ ሕዝብ ለመመገብ የውጭ እርዳታ ያስፈልጋል ይላል፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ደናቁርት ታሪካቸውን እንኳ ቀጥተኛ በሆነ መልኩ ሊያቀርቡት አይችሉም፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ሬድዋን እንዲህ ብሎ ነበር፣ “እራሳችንን መመገብ እንችላለን፣ እናም በዝናብ እጥረት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎች ጨምሮ የረሀቡ ችግር በአብዛኛው ህዝብ ዘንድ ምንም ዓይነት ጉዳት ሊያስከትል ስለማይችል እራሳችንን መመገብ እንችላለን“ (አጽንኦ ተጨምሯል፡፡)
ስለሆነም 8.2 ሚሊዮን የሚሆኑት ህዝቦች በአሁኑ ጊዜ በምግብ መትረፍረፍ ምክንያት በደስታ እና በፈንጠዝያ ላይ ነው ያሉትን?
ይኸ ሬድዋን የሚባል ሰው ክህደት እየፈጸመ ነው ወይስ ደግሞ በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ህይወት ላይ እርባናየለሽ ቀልድ እያደረገ ነው?
ምናልባትም ከጆንያ ሙሉ ድንጋይ የደነዘ እና ትንሽም ቢሆን የእውቀት ጭላንጭል የሌለው ውሸታም እና አስመሳይ ፍጡር ነው?
እንደ ሬድዋን አባባል ከሆነ የረሀብ ሰለባ የሆኑት ኢትዮጵያውያን በረሀብ መጠቃታቸውን አያውቁትም ማለተ ነው፡፡
ስለሆነም እውነተኛው ጥያቄ መሆን ያለበት፡ ሬድዋን እና (ምናልባትምምናልባትም ሬድዋን የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ሊቅ ተብሎ ሊታይ ይቻላል) 8.2 ሚሊዮን የሚሆኑትን የረሀብ ሰለባ የሆኑትን ኢትዮጵያውያን ከረሀብ ለመታደግ ይችላሉን?
እ.ኤ.አ መስከረም 2010 አሁን በህይወት የሌለው የሬድዋን አለቃ መለስ ዜናዊ (የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አዕምሮ) እራሱን ከፍ ከፍ እያደረገ ምጸትን በተላበሰ መልኩ እንዲህ በማለት አውጆ ነበር፣ “የተትረፈረፈ ምርት ለማምረት የሚያስችለንን ዘዴ ቀይሰናል፣ እናም እ.ኤ.አ በ2015 ምንም ዓይነት የውጭ እርዳታ ሳያስፈልገን እራሳችንን መመገብ እንችላለን፡፡“
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በእነርሱ የድድብና አገላለጽ ባለሁለት አሀዝ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ ኢንቨስትመንትን መሳብ፣ እና ሌላም ሌላም በማለት ሁሉንም ህዝብ ማታለል እንደሚችሉ አድርገው እራሳቸውን አሳምነዋል፡፡
ማንም ቢሆን መረጃዎችን በመጠቀም እውነታውን ነቅሶ በማውጣት ውሸት መሆኑን ያረጋግጥብናል ብለው አያስቡም፡፡
(ፍትሀዊ ለመሆን ስንት ኢትዮጵያውያን ምሁራን፣ ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ ተንታኞች፣ ወዘተ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እምነተ ቢስ ከሀዲ እና በቅጥፈት የተሞላ መሆኑን አረጋግጠዋል?)
ደህና እውነቱ መነገር አለበት፡፡ ለሴቷ ዳክዬ ጥሩ የሆነው ነገር ሁሉ ለወንዱ ዳክየም ጥሩ ነው፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስቦች ውሸታሞች ሆነው እንደተፈጠሩ ሁሉ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችም የምሁርነት አንደበታቸው ሽባ ሆኗል፡፡
የበለጠ አስከከፊው ሁኔታ ገና ወደፊት ይመጣል፣
እ.ኤ.አ በ2011 የዩኤስ የሕዝብ ቆጠራ ቢሮ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር እ.ኤ.አ በ2050 አሁን ካለበት ከሶስት ጊዜ በላይ እጥፍ በማደግ 278 ሚሊዮን እንደሚሆን ትንበያ ሰጥቷል፡፡
እ.ኤ.አ በ2025 ማለትም ከዛሬ 10 ዓመታት በኋላ የዩኤስ አሜሪካ የሕዝብ ቆጠራ ቢሮ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር 131 ሚሊዮን እንደሚሆን ትንበያ ሰጥቷል፡፡
በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ 99 ሚሊዮን ሕዝቦቿን መመገብ አትችልም፡፡
እ.ኤ.አ በ2010 87 ሚሊዮን የነበረውን ሕዝብ መመገብ አልቻለችም ነበር፡፡
እንደዚሁም ሁሉ እ.ኤ.አ በ2006 78 ሚሊዮን የነበረውን ሕዝብ መመገብ አልቻለችም ነበር፡፡
አንግዲህ ያሉት ተጨባጭ መረጃዎች ሁሉ ይህንን የመሰለ እውነታ የሚያመላክቱ ከሆነ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2025 131 ሚሊዮን የሚሆነውን ሕዝብ ለመመገብ ከፍተኛ የሆነ ችግር ሊሆንባት አይችልምን?
ኢትዮጵያ በተዛነፈው እና በተሳሳተው የማልተስ የእልቂት መንገድ፣ (በሽታ፣ ረሀብ፣ ጦርነት፣ ወዘተ ተመጣጣኝ የምግብ አቅርቦት ደረጃ ላይ እስከሚደረስ ድረስ የሕዝቡን ቁጥር ወደፊት ሊቀንሱት ይችላሉ ወደሚለው አስተሳሰብ) በፍጥነት በመጓዝ ላይ ናት፡፡
በኢትዮጵያ ረሀብ በኤል ኒኖ፣ በኤል ኒና ወይም ደግሞ በኤል ቻፖ አልተፈጠረም፡፡
እንደዚሁም ደግሞ ረሀብ በድርቅ አልተፈጠረም፡፡
ረሀብ በኢትዮጵያ የተፈጠረው በብልሹ አስተዳደራዊ ስርዓት ምክንያት ነው!
ረሀብ በኢትዮጵያ የተፈጠረው በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በኤል ፓትሮንስ ማለትም የረሀብ ቋሚ ደንበኞች አማካይነት ነው፡፡
የዓለም ባንክ ዋና ኢኮኖሚስት የሆኑት ወልፍ ጋንግ ፌንግለር ይህንን በማስመልከት እ.ኤ.አ በ2011 አንዲህ ብለው ነበር፡
በአፍሪካ ቀንድ ያለው ረሀብ ዋና ምክንያት በተፈጥሮ እና በአካባቢያዊ ምክንያቶች ከመሆን ይልቅ በዘፈቀደ በሚጨመረው የምግብ ዋጋ እና በህብረተሰቡ መካከል በሚደረገው ግጭት ምክንያት ነው፡፡ ቀውሱ ሰው ሰራሽ ነው፡፡ ድርቆች በተደጋጋሚ ይከሰታሉ፣ ሆኖም ግን ያንን ረሀብ እንዲከሰት የሚያደርገው መጥፎ የፖሊሲ አነዳደፍ ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ በኢትዮጵያ ለረሀብ ችግር ድርቅ ወይም ደግሞ ሌላ አካባቢያዊ ሁኔታ ሳይሆን ዋናው መንስኤ መጥፎ እና ደካማ አስተዳደር ነው፡፡ (አጽንኦ ተጨምሯል፡፡)
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ “ኤል ፓትሮንስ” (የዝርፍያ አባቶች) በኢትዮጵያ ረሀብን ሊያጠፉ አይችሉም፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ኤል ፓትሮንስ ወደ ስልጣን የመጡት እ.ኤ.አ በ1984-85 በጥቁር የምፃት (ረሃብ) ፈረስ እየጋለቡ ነው፡፡
ረሀብ ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ለኤል ፓትሮንስ የእናት ጡት ማለት ነው፡፡
ረሀብ በኢትዮጵያ ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ኤል ፓትርንስ ትልቅ የቢዝነስ ስራ ነው፡፡
ረሀብ እ.ኤ.አ በ1984-85 ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ኤል ፓትሮንስ ታላቅ የቢዝነስ ስራ ሆኖላቸው ነበር፡፡
እ.ኤ.አ በ2015 ረሀብ በኢትዮጵያ ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ኤል ፓትሮንስ ትርፋማ የሆነ የቢዝነስ ስራ ሆኗል፡፡
እ.ኤ.አ በ2016 ትልቅ ረሀብ ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ኤል ፓትሮንስ ትልቅ የወተት ላም ማለት ነው፡፡
ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ፓትሮንስ በየዲፕሎማሲ ጽ/ቤቶች እና በየኤምባሲዎች በመሄድ እንደበግ በመጮህ መነጋጋቸውን ያፋጫሉ፣ የልመና አኩፋዳቸውን ይዘረጋሉ፡፡ ለተራቡት ወገኖች የሚሆን እባካችሁ ምጽዋዕት ለግሱን በማለት ይለምናሉ!
እ.ኤ.አ በ2016 የረሀብ ቢዝነስ መልካም የሚሆነው ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ኤል ፓትሮንስ ብቻ ነው፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ኤል ፓትሮንስ በረሀብ በዓላቸው ጊዜ እንዲህ በማለት የመዝናናት ቸበርቻቻ ድርጊቶችን ይፈጽማሉ፡
ምንድን እፈልጋለን? ረሀብ! ረሀብን የምንፈልገው መቼ ነው? አሁኑኑ!
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ረሀብን ከኢትዮጵያ እንዲያጠፋ መጠየቅ ማለት ከማፊያ ቡድን በከፍተኛ የወለድ ምጣኔ ብድር መበደርን፣ ማጭበርበርን፣ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ማካሄድን እና የፖለቲካ ሙስናን ማስወገድ እንዲችል ከመጠየቅ ጋር አንድ ዓይነት ነው፡፡
“በአሁኑ ጊዜ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በኢትዮጵያ ያለውን ረሀብ ማስቆም ይችላልን?” ለሚለው ጥያቄ እንዲህ የሚል ሌላ ጥያቄ ማቅረብ ይቻላል፡፡
“በአሁኑ ጊዜ የማፊያ ቡድን ወንጀል መስራትን ማቆም ይችላልን?“
“የወንጀል አረም መራራ ፍሬን ትሰጣለች፡፡ ወንጀል አዎንታዊ ውጤት የለውም“ ያለው ማን ነበር?
ደህና!!! እንደዚሁም ሁሉ የረሀብ አረም መራራ ፍሬን ትሰጣለች፡፡ ሆኖም ግን ረሀብ ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ኤል ፓትሮንስ የተንፈላሰሰ የምቾት የኑሮ ዘይቤን ያመቻቻል!
ይቀጥላል…
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
ጥቅምት 16 ቀን 2008 ዓ.ም