አሜሪካ በቀዩ ምንጣፍ ላይ እንደገና እንድትከበር ትፈልጋለችን?  

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም  

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

Obama Receptionየዶናልድ ትሩምፕ (ያሜሪካ ፕሬዚደንት ዕቹ ለመሆን ተወዳዳሪያነጋገር ዘይቤ እንዲህ የሚል ነው፡አሜሪካ ንደገና ለመከበር ትፈልጋለች፣ ምክንያቱም ቀሪው የዓለም ክፍል አሜሪካንን ማክበሩን ትቷልና ፡፡

ስለዶናልድ እኔ ጉዳዬ አይደለም፡

ሆኖም ግን ኢትዮጵያን ሲጎበኝ የመጀመሪያ የሆነው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ባለፈው ወር ኢትዮጵያን በጎበኘበት ወቅት በቀይ ምንጣፉ ላይ የተደረገለትን ክብር የጎደለው አቀባበል አስመልክቶ ዶናልድ ትሩምፔት የተናገረው የአነጋገር ዘይቤ በአምሮዬ ውስጥ አቃጨለ፡፡

የክብር መገለጫ የሆነው የቀይ ምንጣፍ ተውኔት እና እርባናቢስነት ከነገሮች እይታ አንጻር ትልቅ ጉዳይ አይደለም፡፡ ሆኖም ግን ለአንድ ሉዓላዊ ለሆነ ሀገር ቁጥር አንድ የመንግስት ኃላፊ የሀገሩን/ሯን ክብር የሚገልጽ ጉዳይ ስለሆነ ነገሩ እንዲህ በቀላሉ የሚታይ እና የሚታለፍ አይደለም፡፡

ቀደም ሲል እንዳልኩት ሁሉ እኔ ከፍተኛ ለሆነ የአቀባበል ዝግጅት በዓል እና ለአጋጣሚዎች ቸበርቻቻ ለሆነ የአቀባብል ስነስርዓት ብዙም ትኩረት አልሰጥም፡፡ ሆኖም ግን እኔ የማስተምርበት ዩኒቨርሲቲ የምረቃ በዓል በሚያዘጋጅበት ጊዜ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ ባለስልጣን እጅግ በጣም የተዋበ እና ያጌጠ የፕሮፌሰር የመጎናጸፊያ ልብስ በመልበስ እንዲሁም በጭንቅላት ላይ የሚደፋውን የዩኒቨርሲቲውን መለዮ እያደረጉ ክብረ በዓላትን ሲያከናውኑ ተሳትፈአለሁ፡፡  

መደበኛ የሆኑ የክበር ዝግጅቶች መደረ ጠቀሜታ ይገባኛል፣ ሆኖም ግን ሲደረጉ እጅግ በጣም ባማረ እና በተዋበ የዝግጅት ሁኔታ መሆን አለባቸው፡፡

.. ባለፈው ሀምሌ ወር ሁለተኛው አጋማሽ ላይ እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) እያለ የሚጠራው ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ለፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ያደረገው የአቀባብል ስነስርዓት እጅግ በጣም የወረደ እና የዩናይትድ ስቴትን የፕሬዚዳንቱን ቢሮ እና መላውን የአሜሪካንን ህዝብ የዘለፈ እና ያዋረደ አሳፋሪ ድርጊት እንደነበር እምነት አለኝ፡፡

ለዓለም ህዝብ ባራክ ኦባማ የዩናይትድ ስቴት አሜሪካ ተጠሪ እና በጣም ጠቃሚ እና ተጽእኖ ፈጣሪ የሆነ የዩናይትድ ስቴት አሜሪካ ህዝብ ተወካይ ነው፡፡ ስለሆነም መንግስቱን ወክሎ ጉብኝት በሚያደርግበት ጊዜ ከፍተኛ የሆነ ክብር ሊደረግለት ይገባል፡፡ 

ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) ለፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ሊመጥን የማይችል እንዲያውም ብልህነት የጎደለው እና የመድረክ ላይ አስቂኝ አቀባበል የተውኔት ጨዋታ አካሂዷል!

ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) ለአባማ እንደዚያ ያለ ክብርን ያጎደፈ አቀባበል ለምን እንዳደረገ ሲታሰብ ህሊናን የሚበጠብጥ ጉዳይ ነው፡፡

ኦባማ ከአሜሪካ ግብር ከፋይ ህዝብ እየሰበሰበ ለህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) ከፍተኛውን የገንዘብ እርዳታ የሚሰጥ ሰው ነው፡፡

ኦባማ በየዓመቱ በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ ከአሜሪካ ግብር ከፋይ ህዝብ እያፈሰ ለህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) በማጀል በሙስና የነቀዘውን እና የበከተውን እንዲሁም በወንጀል የተዘፈቁ ድርጆቶቹን በገንዘብ ይደግፋል፡፡

ኦባማ ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) በሰው ልጆች ላይ እየፈጸማቸው ያሉትን ኢሰብዓዊ ወንጀሎች አይቶ እንዳላዬ፣ ሰምቶ እንዳልሰማ፣ መናገር እየቻለ መናገር እንደማይችል ዱዳ በመሆን ዝም ብሎ የተቀመጠ መሪ ነው፡፡

ኦባማ ለህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) እውቅና ለመስጠት እና ሕጋዊነትን ለማላበስ ሲል እስከ ጥርሱ ያገጠጠ ውሽት እና ቅጥፈትን በማራመድ ላይ ያለ መሪ ነው፡፡ ከዚህም አልፎ ኦባማ የእብሪተኝነት ድፍረትን በተላበሰ መልኩ አሁን ባለፈው ግንቦት ወር በተካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫ ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) መቶ በመቶ በማሸነፍ ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ ድልን ተቀዳጅቷል በማለት የሸፍጥ የምስክርነት ቃሉን ሰጥቷል፡፡ የወፍ ምስክሯ ድንቢጥ እንዲሉ፡፡

የኦባማ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ የሆነችው ቅብጥብቷ ሱሳን ራይስ ለአባባሉ ከፍተኛ ግነት በመስጠት ፕሬዚዳንቱ ህወሀትፍጹም በሆነ መልኩ መቶ በመቶ ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ ድልን ተቀዳጅቷልብለዋል የሚል ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥታለች፡፡ ከዚያም በኋላ ራይስ ስሜቷን ልትቆጣጠረው በማትችለው መልኩ በሳቅ ፈንድታለች! ኦባማ ይህን የመሰለ ውለታ እና ወገንተኝነትን ለህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) ያደረገው ምን ትርፍ ለማግኘት ነው? ሌላ ምንም ነገር ሳይሆን ክብርን የማጣት ውርደት!

በምላሹ አሜሪካ ምን አገኘች? ክብርን የማጣት ውርደት!

በላስ ቬጋስ ከተማ ብዙም እርባና ለሌላቸው ቁማርተኞች ፕሬዚዳንት ኦባማ በአዲስ አበባ ላይ ከተደረገለት የአቀባበል መስተንግዶ የበለጠ ክብር ይሰጣቸዋል፡፡

የቀይ ምንጣፍ አቀባበልማለት የእራሱ የሆነ ልዩ መገለጫ ትርጉም እና ምልክት አለው፡፡ ለዚህም ነው ጠቃሚ የሆኑ የመንግስታት እና ሌሎች ይፋ የሆኑ ጉዳዮች ጉብኝቶች በሚደረጉበት ጊዜ ብዙውን ጊዜ ቀይ ምንጣፍ በማንጠፍ የአቀባበል ስነስርዓት የማድረግ እና የክብር ዘብ በማቆም አቀባበል የሚደረገው፡፡ ልዩ የሆነ የአለባበስ እና የበዓል ዝግጅት በማድረግ ለክብር ተብሎ በተነጠፈው ቀይ ምንጣፍ ላይ በችኮላ እና በጥድፊያ ሳይሆን ርጋታን የተላበሰ አረማመድ በማድረግ ዓለም ክብር እና ፍቅር ለመስጠት ላሰበችው ህዝብ ሀገር ተወካይ ትሰጣለች፡፡ የሚደረገው ለጉብኝት እንግዳውን ለላከው ህዝብ ክብር ሲባል ነው፡፡

ቀይ ምንጣፍ አንጥፎ ታላቁን እንግዳ የመቀበል ስነስርኣት ባህል እና ትርጉም ከጥንት ታሪክ ጀምሮ የነበረ ነው፡፡

ከክርስቶስ ልደት በፊት 458 ዓመተ ዓለም አጋመምነን የተባለው ጦረኛ ከትሮጅን ጦርነት በሚመለስበት ጊዜ ዝሙተኛና በባሏ ላይ የሚባልግ ሚስቱ ክሊተምነስትራ የክብር አቀባበል ለማስመሰል ቀይ ምንጣፍ አንድዘረጋለጥ አዛ ነበር፡፡  

ሆኖም ግን አጋመምነን ደማቅ ቀይ ቀለም ያለው ምንጣፍ የሚነጠፈው ለአማልዕክት እንጅ ለእኔ አይደለም በማለት በምንጣፉ ላይ በመራመዱ ሁኔታ ላይ አመነታ፡፡

የእኛዎቹ ዘመነኞቹ መላዕክትፕሬዚዳንቶች፣ ጠቅላይ ሚኒስትሮች፣ የመንግስታት ተወካዮችማንኛውንም የአቀባበል ክብረ በዓል ዝግጅት ለማድረግ ያንን የጥንቱን ባህል በማሰብ በቀይ ምንጣፍ ላይ በመራመድ እነርሱም መላዕክት መሆናቸውን እና እነርሱን ሞት የማይነካቸው ፍጡሮች እንደሆኑ አድርገው በመቁጠር እንድንገነዘብላቸው እና የእኛ ተግባር እነርሱን ማክበር፣ ወይም ደግሞ ከልባችን እንድናመልካቸው ይፈልጋሉ፡፡

ኦባማ በምድር ላይ ያለ አንድአምላክ” ቢያንስ በግሪክ የግንጋይ አማልዕከት ደረጃ ሊታይ የሚቺል ሰው ነው። ስለዚህም ትክክለኛ የሆነው የቀይ ምንጣፍ የአነጣጠፍ ስነስርዓት ሊከናወንለት እንደሚገባ አምናለሁ፡፡

የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ኦባማን እጅ ለእጅ በመያያዝ ልጆች እየዘመሩ በሚሄዱበት የህጻናት ጨዋታ ዓይነት ቀይ ምንጣፍ ነገር ላይ እንዲሸከረከር ሄድ በመደረጉ ክስተት ላይ በጣም ደንግጨ ነበር፡፡

ኦባማን በባለ አራት ማዕዘን በተሰራ መረማመጃ ላይ እንደ ፐርሻ ምንጣፍ ተመሳሳይ ሆኖ በተዘጋጀው ምንጣፍ ላይ ዋና መረማመጃ በማድረግ ለክብሩ ሲባል እንዲራመድበት አድርገዋል፡፡

ኦባማ ከቆመበት ወደ ግራ አቅጣጫ 8 እርምጃዎችን እንዲራመድ ተደርጓል፡፡ ከዚያም ወደ ቀኝ በመታጠፍ 12 እርምጃዎችን ተራምዷል፣ እንደገናም ወደ ቀኝ ሌሎች 15 እርምጃዎችን ተራምዷል፣ በመቀጠልም 11 እርምጃዎችን ወደ ቀኝ የተራመደ ሲሆን በመጨረሻም 7 እርምጃዎችን ወደ ቀኝ በመራመድ ቀደም ሲል ቆሞበት ወደነበረበት የመጀመሪያ ቦታው ደረሰ፡፡

በአጠቃላይ የቀይ ምንጣፍ የጥበቃ አጃቢ ዘብ አባላት የአቀባበል ስነስርዓት 59 ሰከንዶችን ወስዷል! የቪዲዮውን ምስል እዚህ ጫን በማድረግ ይመልከቱ፡፡ የቀረው ነገር ቢኖር አሸሸ ገዳሜ እያሉ መጨፈር ብቻ ነው፡፡ በእውነት ሁላችንም ወድቀናል፡፡ 

(ሁላቸውም ለመውደቃቸው እና ይህ ጉዳይ እንዴት እውነት እንደሆነ አስረግጦ በድፍረት መናገር ይቻላል!)

Ob 2Pixህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) ለፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ እና ለአሜሪክ ግብር ከፋይ ህዝብ የሚኪ ማውስ የካርቱን ገጸ ባህሪ የያዘውን ተዋናይ ተውኔት የያዘ ዓይነት የቀይ ምንጣፍ በማዘጋጀት ለጉብኝቱ ክብር የሌለው አቀባበል እንዳደረገለት አምናለሁ፡፡ ከዚያ የተሻለ አቀባበል ሊደረግለት ይገባው ነበር፡፡

የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስበ ለፕሬዚዳንት ኦባማ መንግስታዊ ይፋ ጉብኝት 59 ሰከንዶችን የያዘ የቀይ ምንጣፍ የአቀባበል ስነስርዓት ለምን እንዳደረገ የማውቀው ጉዳይ የለም፡፡

ምናልባትም በዘራፊ ወሮበሎች፣ ሌቦች እና ምስጋና የለሽ ለማኞች መካከል ምን ክብር እና ሞገስ አያስፈለግም ተብሎ ታስቦ ይሆን?

ወይም ደግሞ ኃይለማርያም እና የእርሱ የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) አሻንጉሊት አለቆቹ እንደዚያ ያለው የሚኪ ማውስ የካርቱን ገጸ ባህሪ የያዘውን ተዋናይ ተውኔት የያዘ ዓይነት የቀይ ምንጣፍ የጥበቃ አቀባበል ስነስርዓት ለዩናይትድ ስቴት አሜሪካ ፕሬዚዳንት ይመጥነዋል፣ እናም ይገባዋል በማለት በእርግጠኝነት ያሰቡት የሸፍጥ ስራ ሊሆን ይችላልን?

Desalegn Red carpetአሻንጉሊቱ ኃይለማርያም እና የእርሱ  አለቆቹ ከዚህ ቀደም በቂ እና በርካታ የሆኑ እውነተኛ የቀይ ምንጣፍ የእንግዳ አቀባበል ስነስርዓት ሂደቶች ምን መምሰል እንዳለባቸው ከሚገባው በላይ እንደሚያውቁ ጥርጣሬ የለኝም፡፡

ኃይለማርያም እና ደመወዝ ከፋይ አለቆቹ የተለየ ክብር የማይሰጠው የአገር ውስጥ ዜጋ እና ብዙ ትምህርት የሌለው የአገር ውስጥ ሰው ወይም ደግሞ በሀገሪቱ ውስጥ እንዳለ በአንድ ከተማ ውስጥ እንደሚኖር ተራ ዜጋ ዓይነት ባህሪ በመውሰድ እንደዚያ ዓይነት አሳፋሪ እና አስደንጋጭ የሆነ የአቀባበል ስነስርዓት ከማድረግ ይልቅ ከሌሎች ሀገሮች በመመልከት ተሞክሮ እና ልምድ መውሰድ አይችሉምን?

ይህንን ስል የተንዛዛ እና ጥልቀት ያለው ትምህርት ማለቴ አይደለም፡፡ ይልቁንም ይህንን ማለት የፈለግሁት ቀላል የሆነ ትምህርት ጦጣ ሌላውን አይታ እንደምታደርገው ሁሉ ማድረግ ይችሉ ነበር ማለቴ ነው፡፡

እነዚህን ሰዎች ሊያስተምር የሚችል ሰው በአካባቢያቸው የለምን? እባካችሁ እንደዚህ ተማሩ የሚል ሰዉም የላቸው፡

አዳምጡ! የቀይ ምንጣፍ አነጣጠፍ ስነስርዓት ይህንን ይመስላል፡፡ አስተውሉ! ምንጣፉ ቀይ ነው፡፡ ሌላ ምንም ዓይነት ቀለም ያልተጨመረበት ነው፡፡ ይህም ማለት ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ በርካታ ቀለሞች ያልተቀላቀሉበት ቀለም ነው፡፡ ልዩ ትኩረት ስጡ! ቀይ ምንጣፍ ማለት በቻይና አገር እየተመረተ የሚሸጠው አርቲፊሻል ባለብዙ ረዣዥም ክር የፐርሻ ምንጣፍ ሌላ ማስመሰያ ምንጣፍ ማለት አይደለም፡፡ ይህንን በሚገባ አረጋግጡ! ይህም ማለት ባለ 50 ሜትር ቀይ ምንጣፍ እንዴት እንደሚነጠፍ ያመላክታል፡፡ እዚህ ተመልከቱ! ትምህርቱ ወደ መጠናቀቁ ተቃርቧል፡፡ 8 ጫማ የመሮጫ ቡትቶዎችን [ባለረዣዥም ክር ርካሽ የቻይና ቡትቶዎችን] በአንድ ላይ በማያያዝ ወይም ደግሞ በመደረት የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካንን ፕሬዚዳንት የመቀበል ስነስርዓት ማድረግ ተገቢ አይደለም፡፡ ለጉዳዩ ትኩረት ስጡ! ፍጹም በሆነ እና ቀና አስተሳሰብን በተላበሰ መልኩ ከሳልቫጅ መደብር ለሚገዙት ዉራጅ ምንጣፍ የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ፕሬዚዳንት የአቀባበል ክብር ሲባል 99 ሳንቲም የእንኳን ደህና መጡ ቡትቶ ጨርቅ በማንቸዉም አይነት አትጠቀሙ !!!!!

Obama in Addis Ababa

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

አረ ጉድ በሉእነዚህ እምነተቢስ ፍጡሮች አንድ ትክክለኛ የሆነ ቀይ ምንጣፍ በማንጠፍ የታላቋን ሀገር መሪ መቀበል ካልቻሉ እንዴት በማድረግ እና ምንስ ታምር በመስራት ነው 100 ሚሊዮን ለሚሆን ህዝብ የምጣኔ ሀብት ዕቅድ በማውጣት ሀገርን ማሳደግ፣ ማበልጸግ እና ማስተዳደር የሚችሉት!? እዲያው ዕለት በዕለት የጉራ ችርቸራ ባዶ ፕሮፓጋንዳቸው ለመልቀቅ ካልሆነ በስተቀር፡፡

ከዚህ የበለጠ አስከፊ የሆነው ነገር ደግሞ የማስመሰያውን የፐርሻን ረዣዥም ክር የያዘውን የቡትቶ ምንጣፍ አያይዞ እና አነባብሮ የማንጠፉ ጉዳይ ኦባማን አደናቅፎት በፊቱ በግንባሩ እንዲደፋ ሊያደርገው የሚችል አደገኛ ሁኔታ ነበር፡፡ አምላክ በኪነ ጥበቡ ጠበቀው እንጅ፡፡ (የሚስጥር የደህንነት አገልግሎቱ የፕሬዚዳንቱን ደህንነት በመመልከት አዳልጦት ከመውደቅ እና ከምንጣፉ ችግሮች መጠበቅ ጋር በተያያዘ መልኩ በአንክሮ መመልከት አልነበረባቸውምን? በርካታ ተራ የሆኑ ሰዎች ይህንን አደጋ ተመልክተውታል፡፡)

ለዚህ ጉዳይ ብቸኛው አመክንዮያዊ ማብራሪያ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አለቆች ባራክ ኦባማን ለማሸማቀቅ በመፈለጋቸው ምክንያት ነው፡፡ ለባራክ ኦባማ ይህ ለአንተ አይመጥንም ብለው በተዘዋዋሪ ለመንገር ፈልገዋል በሚለው አስተሳሰብ ላይ እምነት አድሮብኛል—…!

በእውነቱ ይህ ድርጊት እኔ ለኦባማ መሪነት ደጋፊ ባልሆንም እንደዚሁም ለእርሱ ያለኝ ክብር የወረደ ቢሆንም እና እርሱ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን ለመከላከል ሲል እውነትን በአፍጢሟ በመድፋት እንደ አቡጀ ሲቀደድ የሰማሁት ቢሆንም ይህ ድርጊት ግን እጅግ በጣም እንድበሳጭ አድርጎኛል፡፡

የእኔ ግላዊ አስተሳሰብ ቢሆንም ቅሉ ባራክ ኦባማ የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ፕሬዚዳንት ከመሆኑ አንጻር መንግስቱን ወክሎ ኢትዮጵያን ለመጎብኘት በመምጣቱ ሌላውን ነገር ሁሉ ወደ ጎን በመተው አሁንም ቢሆን ከፍተኛ የሆነ ክብር ሊሰጠው ይገባል የሚል እምነት አለኝ፡፡

ማለት የምፈልገው ነገር ቢኖር ዘራፊ ወሮበሎችን ከጫካው ውስጥ ማስወጣት ትችላለህ፣ ሆኖም ግን ጫካውን ከወሮበላ ዘራፊዎች ልታወጣው አትችልም!

እንደዚሁም ሁሉገንዘብ ቢከመር የሰው ልጅ ክብሩን ሊገዛ የማይችል መሆኑ ሀቅ ነው!”

ባራክ ኦባማ የአሜሪካንን መንግስት በመወከል በኢትዮጵያ ላደረገው ይፋ ጉብኝት የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ባደረገው የማስመሰል የአቀባበል አስቂኝ የመድረክ ላይ ትወና እጅግ በጣም አዝኛለሁ!

የቻይና ፐርሻን ርካሽ የቡትቶ ቀይ ምንጣፎችን ለኃይለማርያም ደሳለኝ አንጥፉለት (.. ነሐሴ 212015 ላደረገው የሩዋንዳ ግብኝት) ሆኖም ግን ለኦባማ ጉብኝት ግን የቻይናን የሑዋነግፑን ቀይ ምንጣፍ አንጥፉለት!)

ይህ ነገር እውነት ሊሆን አይችልምን!?

በሁለገብ የፕላስቲክ ክር ምንጣፍ የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካንን ፕሬዚዳንት እንኳን ደህና መጣህ ማለት ጥሩ አይሆንምን?!?

(ለእግዚአብሔር ምስጋና ይግባውና ፕሬዚዳንቱ የተነጠፈው ቡትቶ ምንጣፉ ሳያዳልጠው እና በግንባሩ ሳይደፋ ቀረ፡፡ በእርግጥ ፕሬዚዳንቱ የሊመውሲን ተሸከርካሪዋን የኋላ መስታወት አጥብቆ በመያዙ ምክንያት ምንጣፉን በሚረግጥበት ጊዜ አዳልጦት ሳይወድቅ ቀርቷል፡፡ ያንን ጉዳይ የደህንነት ሰዎች ይሆኑ ያዘጋጁት?!)

ሆኖም ግን ነገሩ እውነት ነው!

በእርግጠኝነት ትክክለኛው የእንኳን ደህን መጡን ምንጣፍ በገፍ ለመግዛት የሚከተለውን የግንኙነት መስመር በመጠቀም ማዘዝ ይቻላል፡

http://www.customized-door-mats.com/sale-329177-red-blue-outside-entrance-polypropyylene-door-mats-with-charming-welcome-printing.html

ዶናልድ ትሩምፕ እንዲህ ብሎ ነበር፣አሜሪካ እንደገና ለመከበር ትፈልጋለች፣ ምክንያቱም ቀሪው የዓለም ክፍል አሜሪካንን ማክበሩን ትቷል፡፡

ዶናልድ ትሩምፕ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ቢሆን ኖሮ እና ኢትዮጵያን ሲጎበኝ እንደዚህ ያለ ክብርን ዝቅ ያደረገ የሚኪ ማውስ አስቂኝ የመድረክ ላይ ትወና ካርቱን ዓይነት የምንጣፍ አነጣጠፍ ስነስርዓት ቢያጋጥመው ኖሮ ምን ያደርግ ነበር?

ለቻይናውያን ከሚነግራቸው ትንሽ ለየት ባለ መልኩ ለህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እንዲህ በማለት ይነግራቸው ነበር፣አዳምጡ– 25 በመቶ ግብር እንቆርጥባችኋለን!“

እናንተ ህወሀቶች አዳምጡ! እየተሰጣችሁ ያለውን የምትንደላቀቁበትን የመሞላቀቂያ የደህንነት የገንዘብ ቸክ 25 በመቶ እንቆርጥባችኋለን፡፡ይል ነበር ትሩምፕ።

አንደዚህ ነበር  ለአሜሪካ ትሩምፕ የምያስመለሰው 

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

ነሐሴ 25 ቀን 2007 .

 

Similar Posts