ባራክ ኦባማ! ምነው እውነቱን ብትናገር ስለ ኢትዮጵያ !

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም  

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ 

ማስጠንቀቂያ!

አቁም!

ስለ ባራክ ኦባማ እውነት ማወቅ ካልፈለግህ ይህን ጦማር ማንበብ አቁም። “እውነትን ለሚጠሉ ሁሉ እውነት ጥላቻ ይመስላቸዋል፡፡” 

“ም ላሴን  ብቆነጥት አምሮየን ያመዋል!”

ባራክ ኦባማ መላስህን ቆንጥጥ !

ባለፈው ሳምንት ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ኢትዮጵያን በጎበኘበትጊዜ የሚከተለውን መግለጫ በመስጠት በርካታ ህዝቦችን አስደንግጧል፡

“ወደእነዚህ ጉዳዮች በሚመጣበት ጊዜ እጅግም  ምላሴን አልቆነትጥም ፡፡ በዴሞክራሲያዊ ምርጫ የተመረጠውን የኢትዮጵያን መንግስት ጨምሮ ኃይልን በመጠቀም ከስልጣን ለማስወገድ ጥረት የሚያደርግን ማንኛውንም ቡድን አጥብቀን እንቃወማለን፡፡ ይህች ሀገር ያለፈችባቸውን ፈተናዎች ሁሉ ከግንዛቤ በማስገባት የኢትዮጵያን ታሪክ በጥንቃቄ እንከታተላለን፡፡ ሕገ መንግስት ተረቅቆ እና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ምርጫ እየተካሄደ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ስልጣን የያዘበት ጊዜ ኢትዮጵያ ዉስጥ ቅርብ መሆኑም አናውቃለን ፡፡”

እውን በኢትዮጵያ ያለው መንግስት በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ ነውን!?!

ባራክ ኦባማ ምን ለማለት እንደፈለገ  ሀሳቡን ግልጽ ቢያደርግ !!!

እ.ኤ.አ ግንቦት 24/2015 በኢትዮጵያ ከህዝብ ፈቃድ ውጭ በጠብመንጃ ኃይል በስልጣን ኮርቻ ላይ ተንጠልጥሎ የሚገኘው ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ አካሂዶ ነበር፣ እናም የቅርጫ ምርጫውን መቶ በመቶ አሸነፍኩ ብሎ አይን አውጥቶ አውጇል፡፡

አምባገነኑ የሰሜን ኮሪያው ኪም ጆንገን እንኳ እ.ኤ.አ መጋቢት 2014 ተካሄደ በተባለው ፓርላሜንታዊ ምርጫ መቶ በመቶ በማሸነፍ የምርጫ ድልን ተቀዳጅቻለሁ ለማለት አልደፈረም ነበር፡፡

ቢያንስ በወረቀት ላይ የኪም ጆንገን “የሰሜን ኮሪያው የሰራተኞች ፓርቲ” 88.3 በመቶ (ከ687 መቀመጫዎች ውስጥ 607 መቀመጫዎችን በመያዝ) ብቻ ማሸነፉን ገልጾ ነበር፡፡

“የኮሪያ ሶሻሊስት ዴሞክራቲክ ፓርቲ” 50 መቀመጫዎችን አሸንፎ ነበር፡፡ እንደዚሁም ደግሞ “የቾንዶይስት ቾንጉ ፓርቲ” 22 መቀመጫዎችን አሸንፎ ነበር፡፡ በጃፓን የሚኖሩ ጠቅላላ ኮሪያውያን ማህበር/General Association of Korean Residents in Japan ደግሞ 5 መቀመጫዎችን አሸንፎ ነበር፡፡ በሌላ በኩልም የኃይማኖት ማህበር/Religious Associations የተባለው ፓርቲ 3 መቀመጫዎችን አሸንፎ ነበር፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ “በምርጫ በንቃት የሚሳተፉ” 79 የተመዘገቡ እና ሕጋዊ ህልውና ያላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች አሉ አየተባለ ይለፈፋል፡፡

እ.ኤ.አ ግንቦት 2015 የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ)/Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF) እየተባለ የሚጠራው ግን የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ/Tigrean People’s Liberation Front  እያለ አራሱን የሚጠራው  ፈላጭ ቆራጭ ድርጅት መደበቂያ  ግንባር  የሚመራው የይስሙላ ስብስብ ድርጅት ለይስሙላ  የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  ከ547 መቀመጫዎች ውስጥ 547ቱንም ጠቅልሎ በመውሰድ ማለትም መቶ በመቶ አሸነፍኩ በማለት አወጀ፡፡

ከ78ቱ ተቃዋሚ እና ተለጣፊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ አንዳቸውም ቢሆኑ ለማሸነፍ የተቀራረበ አንድም ድምጽ ሳያገኙ ቀርተዋል!

ባራክ ኦባማ እ.ኤ.አ ሀምሌ 26/2015 አዲስ አበባ ላይ በመገኘት እንዲህ በማለት አወጀ ፣ “የኢትዮጵያ መንግስት ዴሞክራሲያዊ በሆነ ምርጫ የተመረጠ መንግስት ነው፡፡”

ኦባማ  የሐዋሃት የውሸት ኢትዮጵያ ወይስ 13 ወራት ሙሉ የጸሐይ ብርሀን በማይለያት ኢትዮጵያ ምድር ውስጥ ሆኖ ነው አንደዚህ የሚዋሸው?

የባራክ ኦባማ 13 ወራት ሙሉ የጸሐይ ብርሀን በማይለያት ኢትዮጵያ ያደረገው ጉብኝት ሳንዲ እየተባለች በምትጠራው እና በውሸት እና በቅጥፈት ምድር ውስጥ የምትኖረውን አንድ ትንሽ ተንቀሳቃሽ ሲንማ  ሆና የምትሰራውን ልጃገረድ ታምራዊ ጉብኝት አስታወሰኝ፡፡

ውሸት እና ቅጥፈት በሚነገርባት ምድር ፑፍ የተባለው ድራጎን (ዘንዶ) ሳንዲ ለተባለችዋ ተንቀሳቃሽ ካርቱን ልጃገረድ ፕኖክዮ የተባለዉንና በሬ ወለደ እያለ ለሚናገረው ቀጣፊዎች እንዲህ በማለት አስተዋወቀ፡

ሳንዲ፡ ፑፍ ተመልከት!

ፑፍ፡ ማንም አይቷት የማያውቅ ቀይ እና ሰማያዊ ላም ያቻትና፡፡

ሳንዲ፡ ቀይ እና ነጭ ዝሆንም ያው ይታያል፡፡

ፑፍ፡ ጥቂቶች ሁልጊዜ ያዩታል፡፡ እኔ ድራጎኑ ለምሳዬ የቤት ስራዬን እንደምበላ ስታስቢ የሚገርም እና ያልተለመደ ነገር መሆኑን አታውቂምን? በእርግጥ ሆኖ የማያውቅ ነገር ስለሆነ ያልተለመደ ነገር ነው፡፡ ይኸ ነገር ውሸት ነበር፣ ተራ ማታለል እና ተራ ቅጥፈት ነበር፡፡ ኦ፣ ለምንድን ነው እንደዚህ ቁጥቋጦውን የሚደበድቡት፡፡ ይህ ጉዳይ ሳንዲ በተባለች ትንሽ ልጃገረድ የተፈበረከ ተራ ውሸት ነበር፡፡

ሳንዲ፡ ኦ፣ እነዚያ እርባናየለሽ ውሸቶች ናቸው፡፡

ፑፍ፡ አይደለም፣ እነዚያ ምዕናባዊ ውሸቶች ናቸው፣ እናም ጎጅ ያልሆኑ ምዕናባዊ ሀሳቦች ናቸው እሺ፡፡ እናም ቀልድ እና ፌዝም ናቸው፡፡

አንድ የፖለቲካ ፓርቲ መቶ በመቶ ያሸነፈበት ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ከተገኘ እስከ አሁን ድረስ ማንም አይቷቸው የማያውቅ በእርግጥም አስደናቂ የሆነች ቀይ እና ሰማያዊ ላምም ሆነ ጥቂቶች ሁልጊዜ የሚያዩት ቀይ እና ነጭ ዝሆንም አሉ ማለት ነው፡፡

ሆኖም ግን አንድ ነጠላ የፖለቲካ ፓርቲ አንድን ምርጫ መቶ በመቶ አሸነፈ ማለት ተራ ቅጥፈት እና ውሸት፣ ማጭበርበር እና እውነትን መካድ ነው፡፡

ኦ፣ ለምንድን ነው ቁጥቋጦውን የሚደበድቡት፡፡ ይህ ውሸት እና ተራ ማታለል የኃያሏ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት እየተባሉ በሚጠሩት በባራክ ኦባማ የተነገረ ተራ ቅጥፈት ነው፡፡

እነዚህ እርባና የለሽ ውሸቶች፣ ምዕናባዊ ቅጥፈቶች እና ተቃውሞ የማይቀርብባቸው ማታለሎች ባራክ ኦባማ የፕኖክዮ ኃይለማርያም ደሳለኝ እና በሬ ወለደ ለሚለው ለቴዎድሮስ አድኃኖም  ጋር ሆነው የተተነሰሱ ማጭበርበሮች ናቸው፡፡

ባራክ ኦባማ አንድ መቶ ሚሊዮን የሚሆን ህዝብ በሚኖርባት ሀገር የህዝብ የእርስ በእርስ ጥላቻ እንዲዘራ እና ሀገሪቱን ለውድመት የሚዳርግ አደገኛ የሆነ ውሸት ተናግሮ ሸመጠጠ!

ባራካ ኦባማ ከበቂ በላይ ምሁራዊ ክህሎት ያለው ሰው ነው፡፡

ሆኖም ግን 13 ወራት የጸሐይ ብርሀን የማይለያትን ምድር በኦባማ አማካይነት ውሸት እና ቅጥፈት ወደሚነገርባት ምድር አሸጋግረዋታል፡፡

ኦባማ በቴሌቪዥን ቀርቦ  እስከ ጥርሱ ድረስ ዋሽቷል፡፡ ሆኖም ግን ይህ ብቻ አልነበረም፡፡

የእርሱ  ቅጥፈት ለመደበቅ እና ለማስመሰል እንዲሁም የህዝቡን ቀልብ ከእውነተኛ ጉዳዮች እንዲርቅ አድርጎ ለማስቀየስ በሚል ዕኩይ እሳቤ በሀገሪቱ ውስጥ ከሚንቀሳቀሱት 79 የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ አንዱ ብልሀተኛ ሳይሆን ጉልበተኛ እና አጭበርባሪ የፖለቲካ ፓርቲ መቶ በመቶ በማሸነፍ ሁሉንም የፓርላማ መቀመጫዎችን መውሰዱን ከምንም በላይ አሳምሮ  እያወቀ ህሊናውን በመሸጥ ስለዚህ ጉዳይ አንዲትም ቃል ትንፍሽ ሳይል  በዴሞክራሲያዊ ምርጫ የተመረጠን መንግስት በኃይል ከስልጣን ማስወገድን እንቃወማለን የሚል እርባናየለሽ ንግግር አሰምቶ ሄደ፡፡

ኃይልን በመጠቀም ማንኛውንም ነገር ማስወገድ የሚለውን ነገር ያነሳ ሰዉም አልነበረም ፡፡

ከህዝቦች ፈቃድ ውጭ በጠብመንጃ ኃይል በስልጣን እርካብ ላይ ተንጠልጥሎ ስለሚገኘው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ገዥ አካል የዘረፋ ምርጫ እና የምርጫ ሂደት ውንብድና ኦባማ አንዲትም ቃል ትንፍሽ ሳይሉ ኃይልን በመጠቀም ከስልጣን ስለማስወገድ እንቶ ፈንቶ ነገር ያወራ ነበር ኦባማ ፡፡ ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ እንደማለት!

በእርግጥ ኦባማ የጫካ ወንበዴዎች የሚሉትን በመከተል በአሸባሪዎች እና በአማጺዎች በመሳሪያ ኃይል ከስልጣን መንበራቸው ለማባረር የሚደረግ ዓላማን ያዘለ ነው እያሉ የነገሯቸውን ትረካ ለማጉላት ሲጮኹ እና ህጋዊነትን እንዲላበሱ ለማድረግ በድሁር ስብዕናቸው ሲውተረተሩ ተስተውለዋል፡፡

የኦባማ ዋና እና ግልጽ የሆነው ዓላማ ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ዓለም አቀፋዊ ፍቅር እና ድጋፍ እንዲደረግለት መቀስቀስ እና ቀስ ብለውም ወያኔን የሚቃወሙ ኃይሎች ኃይልን በመጠቀም ከስልጣን የሚያስወግዱ ኃይል አምላኪዎች እና አሸባሪዎች እንደሆኑ አድርገው የስም ማጥፋት ዘመቻ ማካሄድ ነው፡፡

የኦባማ ድብቅ መልዕክት ደግሞ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን የሚቃወም ማንኛውም ኃይል ቢሆን ከህግ አግባብ ውጭ በኃይል ለማስወገድ ጥረት የሚያደርግ እና አሸባሪ ነው የሚል ሆኖ ይገኛል፡፡

ስለሆነም ገዥው አካል ይህንን እንደ መተማመኛ በመቁጠር በአሜሪካ ሙሉ ድጋፍ እና ፈቃድ ከተለጣፊዎቹ በስተቀር ሁሉንም የተቃዋሚ ኃይሎችን ለመደምሰስ ግብዓት ሆኖታል፡፡

ለባራክ ኦባማ አንድ ቀላል የሆነች እንዲህ የምትል ጥያቄ አለችኝ፣ አሁን በስልጣን ላይ ያለውን ገዥ አካል ለክርክር ያህል እንዲያው ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ያልተመረጠ እና መቶ በመቶ የህዝብ ድምጽም አላገኘም ውሸት ነው ብለን ብናስብ እንኳ ይህንን በዴሞክራሲያዊ መንገድ ያልተመረጠን አምባገነን ስብስብ እና ስልጣን ወይም ሞት ብሎ የተቀመጠን አምባገነን ከህዝቦች ጫንቃ ላይ በኃይል ማስወገድ መልካም ሊሆን አይችልምን? ይህንን ጥያቄ ከመመለስህ በፊት ኦባማ እስቲ የኢራቅን ጉዳይ መለስ በማለት አስተዉል !

የኢትዮጵያ መንግስት ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ የተመረጠ ነው የሚለው የኦባማ መግለጫ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ተግባራዊ እየተደረገ ያለ ጭካኔ የተሞላበት ጨዋታ ሊሆን አይችልምን?

ኦባማ እንደዚህ ያለ የተዛባ መግለጫ በሰጡበ ት ወቅት እነዚያን በእብነ በረድ ላይ የተጻፉትን ቃሎች እረስቶታል ማለት ነውን?

ኦባማ ያንን የመሰለ ነገር የተናገረው ለበርካታ ሰዓታት በአውሮፕላን በመጓዙ ምክንያት ከድካም ስሜት በመነጨ ሁኔታ እና ግራ በመጋባት ነውን?

እ.ኤ.አ ሀምሌ 26/2015 የታየው እውነታ ግን ባራክ ኦባማ በአዲስ አበባ ከተማ በመገኘት ፊቱን ቀጥ በማድረግ ለዓለም ህዝብ እንዲህ በማለት አወጁ፣ “የኢትዮጵያ መንግስት ዴሞክራሲያዊ በሆነ ምርጫ የተመረጠ መንግስት ነው፡፡“

ውድ አንባቢዎቼ! ግራ በተጋባ ሁኔታ ላይ ነኝ፡፡ እባካችሁን እገዛ አድርጉልኝ!

ከፕሬዚዳንት ኦባማ ጋር በመከባበር ላይ በተመሰረተ መልኩ አለመስማማቴን ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ የተመረጠ መንግስት ነው ብሎ ኦባማ ሲናገር  አንዴት አድርጌ ነው በመከባበር የምናገረው ፡፡ ግን ሌላ ምን አማራጭ አለኝ?

ማንም ቢሆን “የኢትዮጵያ መንግስት እ.ኤ.አ ግንቦት 2015 በተደረገው የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ ሁሉንም ድምጽ በማግኘት መቶ በመቶ በማሸነፍ ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ የተመረጠ መንግስት ነው” ብሎ የሚያምን ማንም ሰው ቢሆን የዩናትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ለመሆን ብቃት የለዉም፡፡

ለማንኛውም  አንደዚህ ብሎ የሚያምን ሰው የመገድ ዉሻ ያዥ  ሆኖ አንክዋን ሊሰየም አይቺልም።

.. 2009 የደቡብ ካሮሊና የምክር ቤት አባል የሆኑት ዊልሰን ኦባማ ንገግር ላይ እንዲህ በማለት ጮሆ ነበር፣ አንት ዉሸታም!

ያ አባባል ለፕሬዚዳንት ኦባማ ያላቸውን ክብር የለሽነት የሚያረጋግጥ ነው ብዬ ከጆ ውልሶን ጋር ተፋልሜ ነበር ፡፡ (ወይ ሞኙ እኔ !)

ከስድስት ዓመታት በኋላ ጆ ያለው በደንብ ገባኝ ፡፡ (ይቅርታ ጆ!)

ኦባማን የማግኘት ዕድል ቢያጋጥመኝ ኖሮ በፊቱ  ላይ አመልካች ጣቴን በመቀሰር እንዲህ በማለት ልክ ልኩን  እስከ አፍንጫው ድረስ እነግረው ነበር፣ “ባራክ ኦቦማ! ለምን እንደ ቡትቶ ጨርቅ ትተ ረተራለህ ፡፡“

ለካስ ባራክ ኦባማ እንደዚህ ያለ ከቁጥጥር ውጭ የሆነ እና ምክንያታዊ ያልሆነ ውሸትን የሚያራምድ ቀጣፊ  ነው ?

ባራክ ኦባማ በስሜት የሚነዳ  ውሸታም እና ቀጣፊ ሊሆን ቻለ? ይህም ማለት ከልምድ በመነሳት እና በተደጋጋሚነት የሚዋሽ  ስለሆነ አአምሮው በውሽውት ታጥሯል፡፡

ኦባማ የክር እጽዋቱን (Pinocchio) ዓይነት በሺታ ይዞት ይሆን?

ኦባማ የኢትዮጵያ መንግስት ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ የተመረጠ መንግስት ነው ብለው መግለጫ የመስጠታቸው ሁኔታ ተራ ቅጠፈት እና ውሸትን በመያዝ እንደ አቡጀዲ ከመተርተር በላይ አስከፊ የሆነ እና የሚያናድድ ቅጥፈት በምድር ላይም ሆነ በሰማይ ገሀነም ሊኖር እንደማይችል ግንዛቤ ሊኖራቸው ይገባል!

ሆኖም ግን ምንም ዓይነት ተግዳሮት እንደሚገጥማቸው ባለመገንዘብ እና የዓይናቸውን ሽፋፍት እንኳ ሳያራግቡ እንደ ሀቀኛ ሰው ወይም ደግሞ ምንም ዓይነት ሀፍረት ሳይሰማቸው በድፍረት እና ዓይን ባወጣ መልኩ ተናግረውታል፡፡ በውሸት ልምድ የተካኑት ቀጣፊ መግለጫ ነው፡፡

ኦባማ ዓለም ላይ እጅግ በጣም ተመራጭ ከሆነ የሕግ ትምህርት ቤት ሰልጥነው የወጡ የሕግ ባለሙያ መሆናቸውን ማንም ያውቃል፡፡

እውነትን በመናገር እና ውሸትን በመናገር መካከል ያለውን ልዩነት ያጡታል ብሎ ጥርጣሬ ውስጥ የሚገባ የለም፡፡

ድምጽን ከፍ አድርጎ እንደገደል ማሚቶ በመጮህ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ናቸው! እውነትን በመናገር እና ውሸትን በመናገር መካከል ያለውን ልዩነት በግልጽ መናገር እንዳለባቸው ግን ማወቅ ይኖርባቸዋል!!!

የኢትዮጵያ መንግስት ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ የተመረጠ መንግስት ነው የሚለው የኦባማ መግለጫ አንድ ሰው 10  ሜትር  ይርረዝማል ከሚለው ተራ ቅጥፈት ጋር መሳ ለመሳ ነው፡፡

በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ እስከ አሁን ድረስ የተመዘገበ 10 ሜትር ርዝመት ያለው ሰው በምንም ዓይነት ሁኔታ በፍጹም አልታዬም፡፡

አንድ ነጠላ የሆነ የፖለቲካ ፓርቲ በትክክለኛነት እና በቅንነት ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ምርጫ አካሂዶ የህዝቡን ድምጽ በማግኘት መቶ በመቶ ያሸነፈበት በሰው ልጅ ታሪክ የተመዘገበ ውጤት እስከ አሁን ድረስ በዓለም ላይ በፍጹም አልታዬም፡፡

ኦባማ ቀጥ ብሎ  አይኑ በማይዘጋ የቪዲዮ ካማራ እየተመለከተ እስከ ጥርሱ ድረስ ያገጠጠውን ውሸት እና ቅጥፈት ሲናገር  ማየቴ ለእኔ የተረፈኝ እና ላደርገው የሚገባኝ ነገር ቢኖር በድን ሆኖ ከመቅረት እና በድንጋጤ እና በሀፍረት መሸማቀቅ ደርቆ ከመቅረት በላይ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል?

የኦባማ ምላስ ሲቀጥፍ እና የውሸት ድርን ሲያደራ የአካል ገጽታቸው ግን ሌላ ታሪክን የሚናገር ነበር፡፡ የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ በሚሰጥበት ጊዜ በምስል የሚታዬው ቪዲዮ በድምጽ ከሚሰማው በተጻረረ መልኩ ሌላ ታሪክን ይናገር ነበር፡፡

በምስል ማሳያ ቪዲዮው የኦባማ የአካል እንቅስቃሴ ከሚናገሯቸው ቃላት የበለጠ ይናገር ነበር፣ እናም ስለሚናገሯቸው ነገሮች እየዋሹ እና እየቀጠፉ መሆናቸውን በግልጽ ያሳብቅባቸው ነበር፡፡

“የኢትዮጵያ መንግስት ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ የተመረጠ መንግስት ነው” ብለው መግለጫ ሲናገር የኦባማ የሰውነት እንቅስቃሴ ምስል ወዲያውኑ ተለወጠ፡፡

ዓይኖች  ወደ መሬት አፍጥጠው ቀሩ፡፡

ጭንቅላቱ  ውን ወደ ላይ ከፍ በማድረግ ለኤግዚቪዥን ዕይታ እንደቀረቡ ዓቃዎች በዶ ሆነው ይታዩ ነበር፡፡

ሰውዬው እስከ ጥርሱ  ድረስ በሚዋሽ በት ጊዜ የዲስኩር ማንበቢያ ወረቀት ከሚያስቀምጥ በት ድጋፍ ጎን በመሆን አካሉን  የዘፈቀደ አቋቋምን ያመላክት ነበር፡፡

ኦባማ ባዶ ዲስኩሩን  በሚያሰማ በት በዚያን ወቅት በሚቀጥፈው ምላሱና  በእውነተኛው ህሊናው (ያን ጊዜ በምርጫው ወቅት ሁላችንም ድምጻችንን ለሰጠንለት እና በማይክሮስኮብ ብቻ በሚታየው የቀረ ህሊናው) መካከል ያለውን ውስጣዊ መረበሽ ለመደበቅ ሲል ከፍተኛ የሆነ ሙከራ ሲያደርጉ ይስተዋል  ነበር፡፡

ኦባማ ውሸቶቹን  ለማስዋብ እና ለማሳመር ሲል  ፍጹም እርባናየለሽ የሆነ እና የሚያደናግር የሕግ የቃላት እና የሀረግ አጠቃቀሞችን በመጨመር ዲስኩሩን  ቀጥሎ  በነበረበት ጊዜ የሚዋሸዉን የንግግር እና የስነ ልቦና ጉዳዮችን ለመደበቅ ጥረት ሲያደርግ ይታይ ነበር፡፡

ስለወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የቅርጫ ምርጫ የማጭበርበር ድር ሲያደሩ የጥፋተኝነት ስሜታዊ ምልክት አይታይበትም ነበር፡፡ በንግግሩ  ይዞ ት ወይም አቀራረብ ላይ ሊታዩ የሚችሉ መረበሾችን ለመገደብ ጥረት ሲያደርግ  ይስተዋል  ነበር፡፡ ሆኖም ግን ባዶ ዓይኑ  አይቀጥፉም ነበር፡፡ ዝም ብሎ በማተኮር ወለሉን ብቻ ይመለከት  ነበር፡፡

ኦባማ አካሉን ሊቆጣጠር  በማይችልበት  መልኩ እያንቀሳቀሰ  እና እጁን ከፍ ዝቅ፣ ወደ ግራ ወደ ቀኝ በማለት እያወራጩ ምላሱ  የሚናገረውን አንድ ነገር እና የአካል እንቅስቃሲያቸው የሚናገረውን ሌላ ነገር ለመደበቅ ሲል  ከፍተኛ ጥረት በማረግ ላይ ነበረ ፡፡ “ያ እውነት አልነበርም፡፡ የለየለት ቅጥፈት ነበር፡፡”

የኦባማ አካላዊ ሰውነት እንደ አንጨት  ደርቆ ነበር፡፡ ለጥቂት ሰከንዶች ፍጹም ህይወት አልባ በድን መስሎ ነበር፡፡

ሁላችሁም አንደምታውቁ በኦባማ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ በሆነቸው “ንግስት ቅብጥብጤ”  (ሱዛን ርይስ ተጽፎ የተሰጣቸውን የዲስኩር ነጥቦች ሲሸመድድና  እና ሲመለከት ይታይ ነበር፡፡

ኦባማ ቅጥፈት  ማሰማቱን በቀጠሉበት ወቅት ቆም በማለት ይናገር  ነበር፡፡ ለቅጥፈቶቹ  ማሳመሪያ የሚሆኑ ትክክለኛ የሆኑ ቃላትን በመምረጥ ለሚያቀርበው የውሸት ዲስኩር ማስመሰያ እንዲሆን ከፍተኛ የሆነ የቃላት ምርጫ ጥንቃቄ ሲፈልግ  ይታይ ነበር፡፡

ኦባማ ስልታዊ በሆነ መልኩ ወደ ኋላ የመመለስ እና አሰልች የሆነ የንግግር ድምጽ (ቀልድ ለመቀለድ ዓላማ የለም) በማሰማት ታላላቅ እና ታናናሽ ለሆኑ ሀገሮች አንድ ዓይነት የሰብአዊ መብት ጥበቃ መስፈርት እንደሚጠቀሙ ለማስመሰል ሞክሮ ነበር።

ሆኖም ግን ስለቻይና የሰብአዊ መብት ጥበቃ አያያዝ ከኦባማ በስተቀር ማንም የተናገረ ሰው የለም፡፡

ኦባማ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጠበት ጊዜ የአሮጌ መኪና ሻጭ አጭ በርባሪ ነጋዴ ይመስል ነበር።

እውነተኛው እና በጣም አስቂኙ ነገር ግን ከኢትዮጵያ ህዝቦች ፍላጎት ውጭ በጠመንጃ ኃይል በስልጣን ኮርቻ ላይ እንደ መዥገር ተጣብቆ የሚገኘው አገዛዝ መቶ በመቶ ያሸነፈው የምርጫ ድል በዴሞክደራሲያዊ ምርጫ ስለመሆኑ ሱሳን ራይስ ጥያቄ በቀረበላት  ጊዜ ባለፉት አስርት ዓመታት ማንም የአሜሪካ ባለስልጣን እንደተመለከተው ሁሉ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ መሆኑን በመግለጽ ሆዳቸው ለመፈንዳት እስኪቃረብ እና ከንፈሮቻቸው ተለጥጠው ከጆሯቸው እስከሚደርሱ ድረስ በሳቅ ሲትፈነድቅ ይታይ ነበር፡፡ አማካሪ ወይዘሮዋ ሳቃቸውን በቀላሉ ለመቆጣጠር አልቻሉም ነበር! ሮም በምትቃጠልበት ጊዜ ንጉስ ኔሮ ይስቁ ነበር ይባላል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ በኢትዮጵያ ምርጫዎች የሚያስቁ ነገሮች ስለመሆናቸው ሱሳን ራይስ የምታስብ ከሆነ የሚያስደንቀኝ ይሆናል፡፡

ሆኖም ግን ባራክ ኦባማ ምንም ሳያቅማማ  ቀጥተኛ በሆነ መልኩ እንዲህ የሚል ቂትፈት ትናግሯል “የኢትዮጵያ መንግስት ዴሞክራሲዊ በሆነ መንገድ ተመርጧል፡፡“ ሁለት ጊዜ!

ለኦባማ ፍትሀዊ ለመሆን እፈለጋለሁ!

በእርሱ  የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ በሆኑቺው  “በሰይጣኗ የነገር አጧዥ” በሱሳን ራይስ የተጻፈውን እና ኦባማ እንዲያነበው  የተሰጠ ዉን ባዶ ገለባ ዲስኩር በእርግጠኝነት በመረጃ ላይ በተመሰረተ የፖሊሲ ትንተና ላይ ተመስርቶ እና በሚገባ እውነት መሆኑ ተፈትሾ እና ተረጋግጦ የተዘጋጀ ሰነድ ይዞ ነበር ንግግር ያረገው?

እ.ኤ.አ ግንቦት 24/2015 የተካሄደው የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ ከመካሄዱ ከአንድ ወር በፊት እ.ኤ.አ በሚያዝያ ወር ሱሳን ራይስ የዩናይትድ ሰቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ረዳት ጸሐፊ የሆኑትን ዌንዲ ሸርማንን አንድ ዓይነት የንግግር ነጥቦችን በማዘጋጀት እና በማስያዝ ዲስኩር እንድታሰማ ወደ አዲስ አበባ ልካት ነበር፡፡

ሸርማን በተሰጣት ተልዕኮ መሰረት እ.ኤ.አ ሚያዝያ 16/2015 በአዲስ አበባ በመገኘት ኦባማ እ.ኤ.አ ሀምሌ 2015 በተመሳሳይ መልኩ በአዲስ አበባ በመገኘት እንደቀጠፉት ተመሳሳይ ቅጥፈት ሁሉ እርሳቸውም ተመሳሳዩን ውሸት እና ቅጥፈት አሰምታ ተመልሳለች ፡፡ ሸርማን እንዲህ የሚል መግለጫ አውጃ ነበር፣ “ኢትዮጵያ በማደግ ላይ ያለ ዴሞክራሲን እያራመደች ያለች ሀገር ናት፡፡ አሁን በቅርቡ ወደፊት የሚደረገው ምርጫም ነጻ፣ ፍትሀዊ፣ በህዝብ ዘንድ ታማዕኒነት ያለው፣ ግልጽ እና ሁሉን አቀፍ እንደሚሆን እና ኢትዮጵያ ሁልጊዜ እንደምታደርገው ሁሉ የዴሞክራሲያዊ ስርዓቱን እንደምታጠናክር እና በየጊዜው ምርጫ እንደሚደረግ እንጠብቃለን፡፡ ዴሞክራሲያዊ ስርዓቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ የመጣበት ሁኔታ ነው የሚታው፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ በህጋዊ መንገድ የተመረጠን መንግስት በኃይል ለማስወገድ ወይም ደግሞ በዴሞክራሲያዊ ምርጫ ስልጣን የያዘን መንግስት ከስልጣን ለማስወገድ ቅስቀሳ ማድረግ ግንቦት 7ትን ጨምሮ ሌላም ማንኛውም ቡድን ቢሆን መኖር እንደሌለበት በጽኑ ታምናለች፡፡“

ባራክ ኦባማ እ.ኤ.አ ሀምሌ 26/2015 አዲስ አበባ በደረሰ  ጊዜ ሸርማን እ.ኤ.አ ሚያዝያ 16/2015 አዲስ አበባ ላይ በመገኘት የተናገረችዉን  እንዳለ ቃል በቃል የሆነ አንድ ዓይነት ንግግር ነው ያደረገው !!!

ይኸ እንዴት ነው ሊሆን የሚችለው? እኛ ሁላችንም ምንም ነገር የማናውቅ ደደቦች ነን ብለው ማሰብ አለባቸው፡፡

የሸርማን መግለጫ የእሳት ነበልባልን አቀጣጥሏል፡፡ ውሸት እና ቅጥፈትን በህዝብ ላይ በማራመዷ በጥያቄ አፋጥጨ ይዣት ነበር፡፡

ዋሽንግተን ፖስት ሸርማንን በትችት ሸንቁጧጣል ፣ እናም ያቀረበቸው ነጥቦች ባዶ በመሆናቸው እና የተጠቀሙባቸውን የማሰብ ችሎታን የሚፈታተኑ ያልተገሩ ቃላት ስህተቶቻቸውን ተቀብለው በመዋጥ “አቀራረባቸውን መቀየር እንዳለባቸው” በግልጽ ነግሯቸዋል፡፡ ሸርማን ከዚያ የትችት የአርትኦት ስራ በኋላ ብዙም ሳይቆዩ ከያዙት ስልጣን በእራሳቸው ፈቃድ ለቀዋል፡፡

ሆኖም ግን ለሸርማን ላስተላልፍላቸው የምፈልገው መልዕክት አለ፡፡ ሸርማን እ.ኤ.አ ግንቦት 24/2015 ተካሂዶ ስለነበረው የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ ሰጥተውት የነበረው ትንበያ ትክክል ነበር፡፡ አዎ አርግጥ ነው የዴሞክራሲያዊው ምርጫ መሻሻል አሳይቷል፡፡ እ.ኤ.አ ግንቦት 2010 ተካሂዶ በነበረው የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ በስልጣን ኮርቻ ላይ ተፈናጥጦ የሚገኘው ገዥ አካል 99.6 በመቶ የህዝብ ድምጽ በማግኘት አሸንፊያለሁ ብሎ አውጆ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ ግንቦት 24/2015 ደግሞ በእርግጥም ይህንን ሪከርድ በሰፊ ልዩነታ በማሻሻል አንዲትም ቅንጥብጣቢ ነጥብ ሳያስቀር የይስሙላ የቅርጫ ምርጫውን ሙሉ በሙሉ እና መቶ በመቶ አሸንፊያለሁ በማለት ደረቱን ነፍቶ አወጀ፡፡ ትንቢት ተናጋሪዋ ማዳም ሸርማን እንዳሉት ከዚህ በላይ መሻሻል ምን ነገር ሊኖር ይችላል ወገኖቼ!

ዘውዱን  የሚያነቃንቀው የሱሳን ራይስ ስውር እጅ፣

ኦባማ በምን ዓይነት የዴሞክራሲ ህልዮት መለኪያ እና መስፈርት ተመርተው ነው የኢትዮጵያ መንግስት ያካሄደውን የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ “ዴሞክራሲዊ ምርጫ ነው” በማለት ማረጋገጫ ለመስጠት የበቃው ?

እ.ኤ.አ ሰኔ 2009 ባራክ ኦቦማ በካይሮ ከተማ በመገኘት እንዲህ የሚል የዴሞክራሲን ትርጉም ምንነት ሰጥቶ  ነበር፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ዴሞክራሲን ከማጎልበት አንጻር አወዛጋቢ ነገር እንዳለ አውቃለሁ…

ጥቂቶች የስልጣን እርካብን ባልተቆናጠጡበት ወቅት ብቻ ስለዴሞክራሲ ደህና አድርገው ይሰብካሉ፣ ሆኖም ግን የስልጣን ማማዋ ላይ በሚወጡበት ወቅት የሌሎችን ህዝቦች ሰብአዊ መብቶች በመርገጡ እና በመደፍጠጡ ረገድ ተወዳዳሪ የሌላቸው አረመኔዎች እና ጨካኞች ይሆናሉ፡፡ የትም ሆነ የት በህዝብ ይሁንታ ስልጣን ሲያዝ አንድ ዓይነት የስልጣን ገደብን በስምምነት መያዝ አስፈላጊ ነገር ነው፣ ጭቆናን ማካሄድ ተገቢ አይደለም፡፡ የአናሳዎቹን የህብረተሰብ ክፍሎች መብት ማክበር አለበት፡፡ እንዲሁም በመቻቻል እና በመግባባት ተሳትፎ ማድረግ እና የህዝቦችን ፍላጎት ማሟላት እና ስልጣንን ከተቆጣጠረው የፖለቲካ ፓርቲ ፍላጎት በላይ የፖለቲካውን ሂደት ህጋዊነት መጠበቅ አለባችሁ፡፡ ከእነዚህ ውጭ ምንም ይደረግ ምን ምርጫዎች ትክክለኛ ዴሞክራሲያዊ ምርጫዎች በፍጹም ሊሆኑ አይችሉም፡፡ (አጽንኦ ተጨምሯል፡፡)

ኦባማ የኢትዮጵያ መንግስት ዴሞክራሲያዊ በሆነ ምርጫ የተመረጠ መንግስት ነው በሚሉበት ጊዜ ምርጫዎች ብቻ ከሌሎች ነገሮች መሟላት ውጭ ትክክለኛ ዴሞክራሲን በግልጽ ያመጣሉ ማለቱ  ነው፡፡

በኦባማ በእራሱ  የዴሞክራሲ ትርጉም መሰረት ሌሎች ለምርጫው ዴሞክራሲያዊነት አስፈላጊ የሆኑት ነገሮች በሌሉበት ሁኔታ የኢትዮጵያ መንግስት ምርጫውን መቶ በመቶ ማሸነፉ ሌሎች የኦባማ የዴሞክራሲያዊ ምርጫ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች በባለሙያ የተዘጋጁ እና የተቀቀሉ በመሆናቸው ነውን?

እ.ኤ.አ ሀምሌ 28/2015 ባራክ ኦባማ በአፍሪካ ህብረት የኔልሰን ማንዴላ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በመገኘት እንዲህ የሚል ዲስኩር አሰምቶ  ነበር፡ የአፍሪካ መሻሻል በዴሞክራሲው መጠናከር ላይ የተመሰረተ ነው ምክንያቱም አፍሪካውያን እንደማንኛውም በዓለም ላይ እንደሚገኝ ሰው ሁሉ የእራሳቸውን ህይወት እራሳቸው የመቆጣጠር መብትን ሊጎናጸፉ ይገባል፡፡ የትክክለኛ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ መገለጫዎች  አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ምን ምን እንደሆኑ ሁላችንም ጠንቅቀን እናውቃለን፡፡ ነጻ እና ፍትሀዊ ምርጫዎችን ያካትታል፣ ከዚህም በተጨማሪ የመናገር፣ የፕሬስ፣ የመሰብሰብ፣ ነጻነቶች መከበር አለባቸው…ሆኖም እስከ አሁኗ ቅጽበት ደረስ  እነዚህ ነጻነቶች በአፍሪካውያን ህዝቦች ዘንድ ተገድበው እና ተነፍገው ይገኛሉ፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ዴሞክራሲ እንዲሁ ለታዕይታ ሲባል ብቻ በየጊዜው ምርጫ የሚካሄድበት ጉዳይ አይደለም፡፡ ጋዜጠኞች ስራቸውን በመስራታቸው ብቻ ወደ እስር ቤት እየተጋዙ የሚታሰሩ ከሆነ ወይም ደግሞ የሰብአዊ መብት ወትዋቾች መንግስት በሲቪል ማህበረሰቡ ላይ ከመጠን ያለፈ እርምጃ በሚወስድበት ጊዜ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው በመናገራቸው ብቻ ማስፈራሪያ የሚደርስባቸው ከሆነ ይኸ ሌላ ሳይሆን የይስሙላ ዴሞክራሲ አለ ማለት ነው፣ ሆኖም ግን በተግባር ምንም ዓይነት ዴሞክራሲ የለም ማለት ነው፡፡

እ.ኤ.አ ሀምሌ 26/2015 ባራክ ኦባማ የፕሬስ ነጻነትን በመደምሰስ በጋዜጠኞች ተከላካይ ኮሚቴ ከሚከሰሰው እና ከዓለም በአስከፊ የፕሬስ ድፍጠጣው በአራተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው እና ከአፍሪካ አፋኝ የሆነ የፕሬስ ጠላት በመሆን በሁለተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው የወሮበላ ዘራፊ ቡድን ስብስብ ጎን ቆሞ  እንዲህ በማለት በድፍረት አውጆ ነበር ፣ “የኢትዮጵያ መንግስት ዴሞክራሲያዊ በሆነ ምርጫ የተመረጠ መንግስት ነው” አይን ያወጣ ዉሸት!!!

ባራክ ኦባማ በአፍሪካ ህብረት የኔልሰን ማንዴላ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በመገኘት ያደረጉት ንግግር  አድላይ ኢ. ስቴቨንሰን ከኤይሰንሆወር ጋር ለፕሬዚዳንታዊ ምርጫ) በአንድ ወቅት እንዲህ ያሉትን ንግግር አስታወሰኝ፡ “ታላቅ ቀይ ዛፍን ቆርጦ የሚጥል አንድ ዓይነት የፖለቲከኛ የአካሄድ ዘዴ ነው፣ ከዚያም ከተቆረጠው ዛፍ ቀሪ ጉማጅ አናት ላይ ቀጥ ብሎ በመቆም ስለደኖች ክብካቤ ማውራት ነው፡፡“

በተመሳሳይ መልኩ ባራክ ኦባማ እ.ኤ.አ ሀምሌ 26/2015 በኢትዮጵያ በመገኘት የዴሞክራሲን የግራር ዛፍ ቆርጠው በመገንደስ እንዲህ የሚል ባዶ ዲስኩራቸውን አሰምተዋል፣ የኢትዮጵያ መንግስት ዴሞክራሲያዊ በሆነ ምርጫ የተመረጠ መንግስት ነው

እ.ኤ.አ ሀምሌ 28/2015 በአፍሪካ ህብረት የኔልሰን ማንዴላ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የንግግር ማድረጊያ ሰገነት መድረክ ላይ ቀጥ ብለው በመቆም በአፍሪካ ዴሞክራሲን ለመመለስ፣ እንዲያገግም እና ለመንከባከብ ሲማጸኑ ተስተውለዋል፡፡

እንግዲህ እንደዚህ ዓይነቱ አቀራረብ የኦባማን የአፍሪካን ዴሞክራሲ የዛፍ ቆራጭነት እና የአመላላሽነትን የአስመሳይነት ባህሪ በግልጽ የሚያመላክት ጉልህ ማስረጃ ነው፡፡ 

ለመሆኑ ባራክ ኦባማ በእውነተኛው ትክክለኛ ዴሞክራሲ እና በይስሙላው ዴሞክራሲ መካከል ያለውን ልዩነት በውል ይገነዘቡታልን

ኦባማ በካይሮ ከተማ በመገኘት ባደረጉት ንግግራቸው የሰብአዊ መብት ጥበቃ የዴሞክራሲ መሰረት ነው የሚለውን እምነታቸውን እንዲህ በማለት አራምደዋል፡

ሁሉም ህዝቦች እንዲህ ለሚሉ ለተወሰኑ ነገሮች ከፍተኛ ነገሮች ፍላጎት እንዳላቸው ጽኑ እምነት አለኝ፡ አዕምሮ የፈቀደውን ነገር በነጻነት የመናገር ችሎታ፣ እንዴት እንደሚተዳደር ሊለው የሚገባ ነገር የመኖር፣ በሕግ የበላይነት ላይ እምነት የመኖር፣ ፍትህን ለሁሉም ዜጋ በእኩልነት ደረጃ የማስተዳደር፣ ግልጽ የሆነ መንግስት እና ከህዝቡ ሀብትን የማይሰርቅ፣ በመረጡት አካባቢ የመኖር ነጻነት የሚሉት ናቸው፡፡

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ነገሮቸ ሁሉ የአሜሪካ ሀሳቦች አይደሉም፣ ይልቁንም የሰብአዊ መብቶች ናቸው፡፡ ለዚህም ነው በየትኛውም አካባቢ ድጋፍ የምናደርግላቸው፡፡

ኦባማ መቶ በመቶ የመራጮችን ድምጽ በማግኘት የኢትዮጵያ መንግስት ዴሞክራሲያዊ በሆነ ምርጫ የተመረጠ መንግስት ነው በማለት ሲናገር  በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ህዝብ አዕምሯቸው የፈቀደውን በነጻነት የመናገር ችሎታ አላቸው ማለቱ  ነውን?

ኦባማ ኢህአዴግ (ትክክለኛው ስሙ ህወሀት) ምርጫውን መቶ በመቶ አሸንፏል ብለው ሲናገር  የኢትዮጵያ ህዝቦች እንዴት እንደሚተዳደሩ የሚሏቸው ነገሮች አሏቸው ማለቱ ነውን?

ኦባማ አንድ ነጠላ የፖለቲካ ፓርቲ ፖለቲካውን፣ ኢኮኖሚውን እና ማህበራዊ ተቋማትን መቶ በመቶ በብቸኝነት ሲቆጣጠር እና ምርጫውን መቶ በመቶ ሲያሸንፍ በኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት ተከብሯል ማለቱ ነውን?

በኢትዮጵያ ያለው ገዥ የፖቲካ ፓርቲ የተቃዋሚ የፖለቲካ መሪዎችን እያሰረ፣ እያስፈራራ እና እያሸማቀቀ ባለበት ሁኔታ የኢትዮጵያ ምርጫ በምን ዓይነት መለኪያ እና መስፈርት ነው ዴሞክራሲያዊ ነው ሊባል የሚችለው?

ነጻው ፕሬስ እየታፈነ እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ጋዜጠኞች በእስር ቤት እየማቀቁ ባሉበት ሁኔታ የኢትዮጵያ የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ በምን ዓይነት መለኪያ እና መስፈርት ነው ዴሞክራሲያዊ ነው ሊባል የሚችለው?

የምርጫ ኮሚሽኑ የገዥው የህወሀት የኋላ ኪስ ሆኖ እያገለገለ ባለበት ሁኔታ የኢትዮጵያ የቅርጫ ምርጫ በምን ዓይነት መለኪያ እና መስፈርት ነው ዴሞክራሲያዊ ነው ሊባል የሚችለው?

የብዙህን መገናኛ ዘዴዎች በገዥው የፖለቲካ ፓርቲ እጅ ብቸኛ ቁጥጥር ስር ባሉበት ሁኔታ የኢትዮጵያ የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ በምን ዓይነት መለኪያ እና መስፈርት ነው ዴሞክራሲያዊ ነው ሊባል የሚችለው?

በኦባማ በእራሱ  የዴሞክራሲ መለኪያ እና መስፈርት መሰረት የሳዳም ሁሴን “የ11 ሚሊዮን ለዜሮ” የመራጭ ህዝብ ድምጽ በማግኘት መቶ በመቶ ማሸነፍም ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ነው ሊባል ይችላል ማለት ነው፡፡

ዩኤስ አሜሪካ መቶ በመቶ የህዝብ ድምጽ በማምጣት በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ እጅግ በጣም ፍጹም የሆነ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ባካሄደች ሀገር ላይ ጦርነት ማወጅ ነበረባትን?

ከወገኖቸቼ ጋር ታጋሽ በመሆን በጸጥታ እየተመለከትኩ ነው፡፡

የኦባማን “የኢትዮጵያ መንግስት ዴሞክራሲያዊ በሆነ ምርጫ የተመረጠ መንግስት ነው የሚለውን የቅጥፈት እና የውሸት መግለጫን ሊተካው የሚችል ሌላ የመግለጫ ማብራሪያ ምንድን ሊሆን ይችላል?

ኦባማ እያወቁ ደንቆሮ ሆኗል  የሚል ይሆን?

ኦባማ ሊታመን በማይችል መልኩ እንዲያገኝ እና እንዲያውቁት ያልተፈለገ እና የተሳሳተ መረጃ ደርሶታልን ?

ኦባማ እውነታውን ከውሸት መለየት ተስኖታል ?

ኦባማ ለህዝብ የሚያቀርበው መግለጫ እውነትም ይሁን ቅጥፈት የተሞላበት ደንታ የለዉም?

ኦባማ እውነትን በሀሰት የመለወጥ መጥፎ ልማድ ተጠናውቶታል?

ኦባማ ምንም ዓይነት መሰረታዊ የሆነ የግንዛቤ ክህሎት የሌለው ሰው ነው?

ኦባማ ምንም ዓይነት ሀፍረት የሌለው  ዓይን አውጣ ቀጣፊ ነው ?

ባራክ ኦባማ እንደዚህ ባለ ሁኔታ በቀላሉ እና ቀስ ብለው የሚለነበጡ እና እንዲያውም ከእባብ ሆድ በታች የሚወርድ ወራዳ ይሆናል ብዬ በፍጹም እምነት አልነበረኝም፡፡

በዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ ምስራቅ የምትገኘው የቴኔሴ ግዛት ተውኔት ጸሐፊ የነበሩት ዊሊያምስ እንዲህ በማለት ጽፈው ነበር፣ “ከውሸት ሁሉ የበለጠ አስከፊ የሚሆነው የአስመሳይነት ውሸትን የተላበሰ ቀጣፊ ነው!“

ዊሊያምስ የባራክ ኦባማ አስቀድሞ መድረስ ቁልጭ ብሎ ታይቷቸው ኖሯል፡፡

ባራክ ኦባማ ውሸታም፣ ቀጣፊ እና የአስመሳይነት ስብዕና የተጠናወጠው ሰው ነው !

ጓደኛዬ ባራክ ኦባማ ወደ ኢትዮጵያ ባደረገው ጉዞ ላይ ድምፁን  ከፍ አድርጎ ለመጮህ ያጋጠመው ችግር ምንድን ነው!?                                                                    

ባራክ ኦባማ ባለፉት ስድስት ዓመታት ስላከናወነው ስኬታማ ነገሮች እናገራለሁ

አምስት የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ፕሬዚዳንቶች ለአንድ ምዓተ ዓመት ያህል ለመስራት  ያልቻሉትን የጤና ማሻሻያ ፕሮግራም ውሳኔ በሴኔቱ እንዲጸድቅ እና እንዲያልፍ አድርግዋል ፡፡ (የጤና አጠባበቅ ሰብአዊ መብት እንደሆነ አምናለሁ፡፡)

በኢራቅ ላይ ሲካሄድ የቆየውን ጦርነት እንዲጠናቀቅ አድርገዋል፡፡ (በኢራቅ ላይ ተከፍቶ የነበረውን ጦርነት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሬ ስቃወም ነበር፡፡)

ኦሳማ ቢንላደንን በተቀናጀ የማጥቃት ወታደራዊ እርምጃ እንዲደመሰስ አድርገዋል፡፡ (ኦባማ እ.ኤ.አ ግንቦት 2011 ምሽት ላይ ዩናይትድ ስቴትስ በወሰደችው ፈጣን የማጥቃት እርምጃ በሺዎች ለሚቆጠሩ ንጹሀን ወንዶች፣ ሴቶች እና ልጆች ግድያ ተጠያቂ የሆነው እና የአልቃይዳ መሪ እና አሸባሪ የሆነውን የኦሳማ ቢላንደንን መገደል ዘገባ ለአሜሪካ ህዝብ እና ለመላው የዓለም ህዝብ ማቅረብ እችላለሁ የምትለዋን ጣፋጭ ሙዚቃ በጆሮዬ በሰማሁበት ጊዜ ደስ ነበር ያለኝ፡፡)

ኢራን የኒኩሊየር መሳሪያዎች ፍላጎቷን እንድታቆም አድርገዋል፡፡ (የኒኩሊዬር ጦር መሳሪያን ትጥቅ ሙሉ በሙሉ በማስፈታት ላይ እምነት አለኝ፡፡)

የስፓኒሽ ዝርያ ያላቸውን የመጀመሪያዋን ሴት የከፍተኛው ፍርድ ቤት 3ኛ ዳኛ አድርገው መሾማቸውን እና የቡሽን የማሰቃየት ፖሊሲ ማጠፋቸው ትልቅ ነገር ነው፡፡ (እንደ ሕግ ባለሙያ ለእኔ ይኸ ትልቅ ጉዳይ ነው፡፡)

በሚሊዮኖች የሚቆጠር ሄክታርን ደን በማልበስ እንዲስፋፋ እና መፋሰሻ ስነምህዳሮች እንዲጠበቁ አድርገዋል፡፡ (አዎ እኔ ዛፍ የማፈቅር እና በዚህም የምኮራ ሰው ነኝ፡፡)

እጅግ በጣም በተጣራው እና በፓውደር መልክ በተዘጋጀው ኮኬይን መካከል ባለው ልዩነት የተነሳ በህገወጥ መልኩ ይዞ ይገኝ በነበረ ሰው ላይ ይሰጥ የነበረውን ከ100 ወደ ከ1 እስከ 18 እና እስከ 1 እንዲወርድ በማድረግ ፍትሀዊ የሆነ ብይን እንዲሰጥ ፈርመዋል፡፡ በፌዴራሉ ሕግ መሰረት 28 ግራም የሚመዝን ኮኬን በፓውደር መልክ ለሽያጭ ማቅረብ እስከ 5 ዓመት በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል ነው፡፡ አንድ ግራም የአንድ ኪሎ ግራም 1/1000ኛ ናት፡፡ (እንደ ወንጀል መከላከል የሕግ ባለሙያነቴ በርካታ የሆኑ ወጣት ጥቁር ወንዶች ለበርካታ ዓመታት በእስር ቤት ሲማቅቁ የማየት ምስክርነት ስላለኝ ይህ ጉዳይ ትልቅ ነገር ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡)

ከታላቁ የምጣኔ ሀብት ቀውስ ወዲህ በዓይነቱ ሁለተኛ የሆነውን የአሜሪካንን የምጣኔ ሀብት ቀውስ ከመጥፎ አደጋ መታደግ ማዳኑን አደንቃለሁ።

በእርግጥ ኦባማ እኔ ፍጹም የማልስማማባቸውን እና እዚህ ተዘርዝረው የማያልቁትን በርካታ ነገሮችን አከናውኖአል፡፡

ሆኖም ግን ኦባማ “የኢትዮጵያ መንግስት ዴሞክራሲያዊ በሆነ ምርጫ የተመረጠ መንግስት ነው በማለት እስከ አገጫቸው ድረስ ከዋሿቸው ውሸቶች ሁሉ የበለጠ የዋሹት ነገር ስለመኖሩ በፍጹም፣ በፍጹም እስከ አሁን ድረስ ሰምቼ አላውቅም፡፡ 

ጓደኛዬ ባራክ ኦባማ ወደ ኢትዮጵያ ባደረገው ጉዞ ላይ ድምፁን  ከፍ አድርጎ  ለመጮህ ያጋጠመው ችግር ምንድን ነው!?

.. መስከረም 2014 ላይ በፕሬዚዳንት ኦቦማ ላይ ኩራት በማሳደሬ ሀፍረት ተሰምቶኛል በሚል ርዕስ ባዘጋጀሁት ትችት ላይ እጅግ በጣም ታማኝ እና ይቅርታ ጠያቂ ነበርኩ፡፡

ሀፍረተቢስ ከሆኑ እና ከተጠሉ ፖለቲከኞች መካከል እንደ ባራክ ኦባማ ልዩ የሆነ ማንም የለም የሚል የክርክር ጭብጥ አቀርባለሁ፡፡

ኦባማን እወደውዋለሁ ምክንያቱም ወጣት ነበረ ፣ እንደማግኔት የሚስብ ኃይል ያላው  አንደበተ ርትዑ እና እንዲሁም ሀሳብ አፍላቂ ሰው ይመሰል ነበር፡፡

እንደማንኛውም ሰው ሁሉ ላስመዘገበው ስኬቶች እና ለሚያምንቤት እሴቶች ኦባማን እወደዋለሁ፡፡

በኦባማ እኮራበት ነበር ፣ ሆኖም ግን የመጀመሪያው ጥቁር ፕሬዚዳንት መሆን ከመቻላቸው እውነታ ጋር በተያያዘ መልኩ ያለኝ ኩራት በጣም አናሳ ነበር ፡፡ ኦባማን የገመገምኩት  በቆዳው ቀለም አይደለም ካለው የይዘት ባህሪ አንጻር ነው፡፡ ባላው የዓላማ ጽናት፣ የሞራል ስብዕና፣ ቅንነት እና ታማኝነት ልዩ ጸጋን የተላበሰ ነበር፡፡

እ.ኤ.አ በ2007 ተደርጎ በነበረው ዕጩ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በኩራት ስደግፋቸው እና የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ፕሬዚዳንት እንዲሆኑ የኢትዮ-አሜሪካንን ዜጎች በማሰባሰብ የድምጽ ድጋፋቸውን እንዲሰጡ ሳደርግ ወደ ላይ በመውጣት ላይ ያሉ ምርጥ የፖለቲከኛነት ባህሪን የተላበሱ እንጅ እንደዚህ ያሉ አጭበርባሪ እና በጣም አደገኛ የሆኑ አስቸጋሪ እና መሰሪ ፖለቲከኛ ይሆናሉ የሚል እምነቱ አልነበረኝም፡፡

.. ሀምሌ 2015 ባራክ ኦባማ በመጨረሻ በእርግጠኝነት የተናቀ ቆሻሻ ባህሪ ያለው፣ እንደ ግሪስ አሙለጭላጭ የሆነ  እና የፖሊስተር ዩኒፎርም እንደለበሰ የአሮጌ መኪና ሻጭ ዓይነት የዘቀጠ የሞራል ስብዕና ያለው ሰው ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡

የጫካ ወሮባላ የሽፍቶች ስብስብ ተሰባስበው የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ ካካሄዱ በኋላ እና ለዓለም ህዝብ መቶ በመቶ ምርጫውን አሸንፈናል ብለው ማወጃቸውን ተከትሎ ባራክ ኦባማ ለእነዚህ መንታፊ ሌቦች እንኳን ደስ ያላችሁ በማለት የምርጫውን ዴሞክራሲያዊ መሆንን በማስመልከት “የኢትዮጵያ መንግስት ዴሞክራሲያዊ የሆነ ምርጫ አካሂዷል” በማለት የምርጫውን ውጤት በመቀደስ ቡራኬ ሰጥጧል፡፡

“የ” ስጠኝ፣ “መ” ስጠኝ፣ “ዴ” ስጠኝ፣ “በ ” ስጠኝ… በማለት “ኢትዮጵያ ንግስት ሞክራሲያዊ ሆነ ምርጫ ተመርጧል/The Government of Ethiopia has been democratically elected የሚል እወጃ አውጇል እንደ አቡጀዲ የሚተረተሩት ቀጣፊው የዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚዳንት፡፡ ይደልዎ! ይደልዎ!

ባራክ ኦባማ ከአፍሪካ አምባገነኖች እና ዘራፊ ወሮበሎች ጋር ሳእሆን በስተቀር  አብዛኛውን ግዜዉን በየትኛው ፕላኔት እንደሚያሳልፉ ሊነግረኝ የሚችል ሰው ሊኖር ይችላልን?

በዓለም ላይ ከሽርሙጥና ቀጥሎ ሁለተኛው ጥንታዊ ሙያ ፖለቲካ ነው ይላሉ፡፡ አልፎ አልፎ እነዚህ ሁለት ሙያዎች በአንድ ሰው ላይ አንድ ሊሆኑ የሚችሉበት አጋጣሚ ሊኖር ይችላልን?

በራክ ኦባማ ምን በሽታ ነካው!?

የይስሙላ የቅርጫ ምርጫን በማካሄድ መቶ በመቶ የህዝብ ድምጽ በማግኘት ያሸነፈ መንግስት “በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ ነውን”!?

ኦባማ የተሰጠውን መግለጫ እንደ ግል ሰብአዊ ፍጡር ዘለፋ እቆጥረዋለሁ፡፡

የኦባማን “ዴሞክራሲያዊ መንግስት” ሁልጊዜ ሰኞ በየሳምንቱ ሰኞ ጠንካራ እና ሸንቋጭ የሆኑ ትችቶችን በማዘጋጀት ለዘጠኝ ተኩል ዓመታት ያህል ባለማቋረጥ በአምባገነኑ መንግስት በሰው ልጆች ላይ የሚደርሱ የሰብአዊ መብት ድፍጠጣዎችን፣ ኃይለኝነትን እና እብሪተኝነትን፣ የዘር ማጥፋት ወንጀልን እና ከህግ አግባብ ውጭ በዘፈቀደ የሚፈጸሙ ግድያዎችን በማጋለጥ የተጠናከረ ትግል ሳደርግ ቆይቻለሁ፡፡ በኢትዮጵያ ላይ ሳከናውን በቆየሁት የሰብአዊ መብት ጥበቃ ውትወታ ላይ ባስመዘገብኩት ስኬት ታላቅ ኩራት ይሰማኛል፡፡

ሆኖም ግን ባራክ ኦባማ የኢትዮጵያ መንግስት በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ ነው በማለት ሲናገር  100 ሚሊዮን የሆነውን የኢትዮጵያ ህዝብ መናቃቸውን፣ መዘለፋቸውን እና ማዋረዳቸውን የሚገነዘቡት ከሆነ የሚገርመኝ ሊሆን አይችልምን?

ለምንድን ነው የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ፕሬዚዳንት በ100 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝቦች ፊት በመቆም የውሸት ቅጥፈቱን የሚለቀው?

እኒህ በቅጥፈት የተሞላ  ፕሬዚዳንት ኢትዮጵያውያን ምንም የማያውቁ ደደቦች ናቸው ብለው ሊያስብ  ይችላልን?

ኢትዮጵያውያን በእውነተኛ ምርጫ እና በይስሙላ የቅርጫ ምርጫ መካከል ያለውን ልዩነት መለየት የማይችሉ ዱዳዎች እና ደደቦች ናቸው ብሎ ማመን ይኖርበታል እንዴ?

ኢትዮጵያውያን በዴሞክራሲ እና በእብደት ዴሞክራሲ መካከል ያለውን ልዩነት መለየት የማይችሉ ዱዳዎች እና ደደቦች ብሎ ማመን አለበት!

የኦባማ ዓይን ያወጣ ቅጥፈት በኢትዮጵያውያን ላይ ያለዉን ንቀት በግልጽ ያመላክታል፡፡

ለኢትዮጵያ ህዝቦች ክብር ቢሰጥ  ኖሮ እ.ኤ.አ በግንቦት 2015 የተካሄደው የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ  ዲፕሎማሲያዊ በሆነ መንገድ ማስተናገድ ይችል ነበር፡፡

ሆኖም ግን ኦባማ ኢትዮጵያውያን ምን እንዳሰቡ ከቁብ የቆሩት ጉዳዩ አልነበረም!

እ.ኤ.አ መስከረም 2/2012 የኦባማ ብሔራዊ የደህንነት አማካሪ የሆነቸው ሱሳን ራይስ አሁን በህይወት በሌለው በመለስ ዜናዊ የቀብር ስነ ስርዓት ላይ በመገኘት በጥባጭ የሆነ ስሜታዊ ንግግር አድርጋ ነበር፡፡

ራይስ እንደህ ብላ  ነበር፣ “መለስ ጠንካራ ሰው ነበር፣ ስሜታዊ ያልሆነ እና አንዳንድ ጊዜ የማይበገር ጽኑ አቋም የነበረው ሰው ነበር፡፡ በእርግጥም እርሱ ለመጥራት ይወደው እንደነበረው ለሞኞች እና ለደደቦች ትዕግስቱ አልነበረውም፡፡“

በኢትዮጵያውያን ዓይን እይታ ባራክ ኦባማ የመለስ ዜናዊ ተለዋጭ የእብሪት ቀልቀሎ ሆነዋል፡፡

ሆኖም ግን በምንም ዓይነት መለኪያ እና መስፈርት ኢትዮጵያውያን ሞኞችም ደደቦችም አይደሉም፣ በፍጹም ሊሆኑም አይችሉም፡፡

እውነት ለመናገር ሞኝ እና ደደቡስ በዓለም አቀፍ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ላይ ቆሞ ስለእብደት ዴሞክራሲ ትረካ የሚተርክ እና ባዶ ዲስኩር እና ለምንም የማይፈይድ እርባናየለሽ ከንቱ ንግግር በማድረግ ያለውን ሰዓቱን በከንቱ የሚያባክን አስመሳይ ቀጣፊ ነው፡፡

ኦባማ “በዴሞክራሲያዊ ምርጫ የተመረጠውን መንግስት” (የወሮበላ ስብስብ) ለመከላክል ጥረት በሚያደርጉበት ወቅት ጥርሴን አልነከስኩም ብሏል፡፡

ደህና፣ ባራክ ኦባማ ይህንን ያግኙ፣

100 ሚሊዮን የሚሆኑት ኢትዮጵያውን ሁሉ ምላሳቸውን በርሱ  ላይ በማውጣት የመካለል ጣቶቻቸዉን ያሳዩታል!

ዊሊያም ሸክስፒር በህይወት ቢኖሩ ኖሮ “የኢትዮጵያ መንግስት ዴሞክራሲያዊ በሆነ ምርጫ የተመረጠ ነው” የሚለውን የባራክ ኦባማ ባዶ እና ተራ ቅጥፈት “አሰልቺ የሞኝ ንግግር እና አስፈሪ ቀጣፊ ” በማለት ይጠሩት ነበር፡፡

መንፈሳዊ ቅብዓቱ ቢኖረኝ ኖሮ ባራክ ኦባማን ከአጠገቤ አስቀምጨ ገሀነም በማስገባት በማርቆስ ወንጌል 8፡18 የተጠቀሰውን እና እንዲህ የሚለውን ወንጌል አስተምረው ነበር፣ “ዓይን ሳላችሁ አታዩምን? ጆሮስ ሳላችሁ አትሰሙምን? ትዝ አይላችምን? እንደ ዕብራውያን ቃል 5፡21 ይህንን አሁን ስማ እንደሚለው ሞኙ ኦባማ/ምንም ዓይነት ግንዛቤ ሳይኖረህ /ዓይን እያለህ ማየት የተሳነህ /ጆሮ እያለህ ማዳመጥ የተሳነህ ይህንን አሁኑኑ ስማ!“

ባራክ ኦባማ “የኢትዮጵያ መንግስት ዴሞክራሲያዊ በሆነ ምርጫ ተመርጧል” ብሎ ሲናገር  በዳውር መዝሙር  መልዕክት በምዕራፍ 140 እንደተመለከተው “ባራክ ኦባማ ምላስዎ እንደ እባብ ትናደፋላች፣ ከከንፈርህ የመርዛማ እባብ መርዝ ይንጠባጠባል፡፡“

ፈላስፋ ብሆን ኖሮ ለባራክ ኦባማ የፕላቶን “በህይወት ላይ መዋሸት” የሚለውን ትምህርት አስተምረው ነበር፡፡ ባራክ ኦባማ በህይወት በጣም ጠቃሚ ስለሆኑ ነገሮች አቷሽ!

ፈላስፋ ብሆን ኖሮ በሰው ልጆች ላይ ፍጹም በሆነ እና ምንም ዓይነት የዕቅድ ሁኔታ ሳይቀመጥ መፈጸም ያለበትን በተለይም የሀገር መሪዎች እውነት መናገር እንዳለባቸው የሚያስገድደውን  የካንትን “የሞራል ሕግ” ለባራክ ኦባማ አስተምረው  ነበር፡፡ በመሪዎች ላይ ምንም ዓይነት እውነት ተናጋሪነት ከሌለ የተረጋጋ፣ ስምምነት ያለው እና ለሕግ የማይገዛ ማህበረሰብ መገንባት አይቻልም፡፡

የኦባማ ተመራጭ ፈላስፋ ሬይንሆልድ ኔይቡር ሊሆኑ እንደሚችሉ አውቃለሁ፡፡ ኦባማ “የኢትዮጵያ መንግስት ዴሞክራሲያዊ በሆነ ምርጫ የተመረጠ መንግስት ነው” ብሏል፡፡

ፈላስፋ ብሆን ኖሮ ኔይቡር “የሰው ልጅ ስለፍትህ መስፈን ያለው ችሎታ ዴሞክራሲ እውን እንዲሆን ያስችላል፣ ሆኖም ግን የሰው ልጅ ስለኢፍትሀዊነት ዝንባሌ ባሳዬ ጊዜ የዴሞክራሲን አስፈላጊነት ያመላክታል፡፡“ ብለው ሲናገሩ ምን ለማለት እንደፈለጉ ዲስኩር ለባራክ ኦባማ ሰጠው ነበር፡፡

ጋዜጠኛ ብሆን ኖሮ ባራክ ኦባማ እ.ኤ.አ በ2009 በካይሮ ከተማ በመገኘት “ስልጣን በሌላቸው ጊዜ ስለዴሞክራሲ የሚወተውቱ ጥቂቶች አሉ፣ ሆኖም ግን አንድ ጊዜ በስልጣን ወንበር ላይ ከተቀመጡ አረመኔ ጨካኞች በመሆን የሌሎችን ሰዎች መብቶች በመደፍጠጥ ጭቆናን ያራምዳሉ፡፡“ የሚለውን እንዲያብራራልኝ ባራክ ኦባማን እጠይቀው  ነበር፡፡ በሚያቀርበው ማብራሪያ እና ገለጻም መሰረት በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ተቆናጥጦ የሚገኘው ገዥ አካል መቶ በመቶ ምርጫን በማሸነፍ እንዴት “በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ ዴሞክራሲያዊ መንግስት እንደሆነ እንዲያብራሩልኝ ባራክ ኦባማን እጠይቀው ነበር፡፡

የቀጣፊነት/ውሸታምነት  መሳሪያ መርማሪ አዋቂ ብሆን ኖሮ ባራክ ኦባማን እንዲህ የምትል አንዲት ጥያቄ አቀርብለት ነበር፣ “የኢትዮጵያ መንግስት ዴሞክራሲያዊ በሆነ ምርጫ የተመረጠ መንግስት“ ነውን?

ምርመራዉን ኦባማ በጣጥሶ ያልፍ ነበር።

ባራክ ኦባማ በደም ግፊት፣ በልብ ምት፣ በመተንፈስ ወይም ደግሞ በቆዳ ንክኪ (የዉሸት ምልክቶች) ምንም ዓይነት ለውጥ አያሳይም ነበር፡፡

እኔ ግን ከላይ ከተጠቀሱት ከአንዳቸውም አይደለሁም፡፡

እኔ በእርግጥ መካከለኛ የሆነ የኮሌጅ ፕሮፌሰር እና የወንጀል መከላከል የሕግ ባለሙያ ነኝ፡፡

ስለሆነም በመንገዴ ላይ ምን እንደሚሰማኝ ለባራክ ኦባማ እነግራቸዋለሁ፡፡

ባራክ ኦባማ! የእርስዎ “የኢትዮጵያ መንግስት ዴሞክራሲያዊ በሆነ ምርጫ የተመረጠ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ነው” የሚለው መግለጫ የበሬ ወለደ አይነት ዉሸት ከሆነ ትረካ ጋር አንድ ዓይነት ነው፡፡

ባራክ ኦባማ በእርግጠኝነት ባራክ ኦባማ ነዉን?

ባራክ ኦባማ እ.ኤ.አ ሀምሌ 2009 “እንዳትሳሳቱ፡ ታሪክ ከእነዚህ ከአፍሪካ ጀግኖች ጎን እንጅ በስልጣን ኮርቻ ላይ ለመቆየት መፈንቅለ መንግስት ከሚያካሂዱ እና ሕገ መንግስቱን ከሚያሻሽሉ ሰዎች ጎን አይደለም፡፡ አፍሪካ ጠንካራ ተቋማትን እንጅ ጠንካራ ሰዎችን አትፈልግም፡፡“ ሲል የነበረው ባራክ ኦባማ ባሁኑ ጊዜ ምንድን ሆነ?

እንዲህ በማለት የተናገረው ባራክ ኦባማ ወዴት አለ ?

“ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ለምሳሌ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር ለሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ዘብ በምትቆምበት ጊዜ እራሳችንን በዓለም ላይ ከሚገኙ ሃሳባቸውን በነጻነት መግለጽ ከሚፈልጉ፣ መሪዎቻቸውን እራሳቸው ከሚመርጡ እና በክብር እና በመከባበር መኖር ከሚፈልጉ ወንዶች እና ሴቶች ጋር በማዋሀድ ጥረቷን ትቀጥላለች፡፡ የሰብአዊ መብቶች መደፍጠጥ በአሁኑ ጊዜ እየተጋፈጥነው ያለውን ወታደራዊ ግጭት እና ሰብአዊ ቀውስ እንዲሁም የሙስና መንሰራፋት እና ጥላቻን የሚያስፋፋ እና ኃይልን የሚጠቀም ርዕዮት ዓለም መከተል ዓለም አቀፋዊ የሆነ አደጋን ያስከትላል፡፡”

አንዲህ የሚሉትን የቀድሞውን ጓደኛዬን ባራክ ኦባማን ያዬ ይኖራልን፣ “የሕግ የበላይነት ለሕገ አራዊትነት ቦታውን በሰጠበት እና ሙስና በተንሰራፋበት ማህበረሰብ ውስጥ ለመኖር የሚፈልግ ማንም ሰው የለም፡፡ እንደዚህ ያለው ሁኔታ ዴሞክራሲ አይደለም፣ አንዳንድ ጊዜ አልፎ አልፎ ምርጫ የሚካሄድ ቢሆንም እንኳ አምባገናነዊነት እና ጨቋኝነት ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ እንደዚያ ያለው ጊዜ የመጠናቀቂያው ወቅት ነው፡፡“

ለባራክ ኦባማ እና የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ፕሬዚዳንት ለሆነው ለባራክ ኦባማ ያለኝን ክብር ሙሉ በመሉ አንስቻለሁ፡፡

እውነትን ለመናገር አጅግ በጣም ቦቅቧቃ በመሆኑ ምክንያት እስከ ጥርሱ ድረስ ውሸት እንደ ጫጩት የሚቀፈቅፍን ሰው እንዴት ማክበር እችላለሁ?

ለባራክ ኦባማ ፍትሀዊ መሆን እፈልጋለሁ፡፡

የአሜሪካ ፕሬዚዳንቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ ውሸት ሲዋሹ ይያዛሉ፡፡

ጆን ኤፍ.ኬኔዲ በኩባ ላይ ወረራ ለማካሄድ ዕቅድ ከነደፉ በኋላ ዩኤስ አሜሪካ በኩባ ላይ ወረራ ለመፈጸም ምንም ዓይነት ዕቅድ የላትም ብለው ነበር፡፡ ነጭ ውሸትን ዋሽተዋል፡፡

ታላቁ ጆርጅ ቡሽ “አዲስ ግብሮች አይኖሩም” በማለት ለህዝብ ተናግረው ነበር፡፡ ሙልጭ አድርገው ዋሽተዋል፡፡

ቢል ኪሊንተን ካናቢስ የተባለውን አደንዛዥ ዕጽ ያጤሱ ነበር፣ ሆኖም ግን ጭሱን አልዋጥኩም ይሉ ነበር፡፡ እንደዚሁም ደግሞ ከዚያች ሴት (ከሞኒካ ሌዊንስኪ) ጋር ምንም ዓይነት ግብረ ስጋ አላረግኩም ብለው ነበር፡፡ ዓይን ያፈጠጠ ውሸት ዋሽተዋል፡፡

ሪቻርድ ኒክሰን አጭበርባሪ ሰው አደለሁም ብለው ነበር ፡፡ ተራ ውሸት ዋሽተዋል፡፡

ሮናልድ ሬጋን ምርኮኛ ለነበረችው “ለኢራን ምንም ዓይነት እድግመዋለሁ ምንም ዓይነት የመሳሪያ ወይም የሌላ ነገር ንግድ አልፈጸምኩም፡፡” በማለት ተናግረው ነበር፡፡ ያገጠጠ ውሸትን ዋሽተዋል፡፡

(በነገራችን ላይ ሱሳን ራይስ እ.ኤ.አ በ1994 በሩዋንዳ ስለደረሰው የዘር ማጥፋት እልቂት ምንም ዓይነት አውቀት የለኝም በማለት ነጭ ውሸትን ዋሽታለች ፡፡ ሴትዮዋ በዚያን ወቅት የተናገረችው እንዲህ የሚሉ ቃላት ነበሩ፣ “የዘር ማጥፋት የሚለውን ቃል ከተጠቀምን እና ምንም ነገር ሳናደርግ እጃችንን አጣጥፈን የምንታይ ከሆነ በጥቅምት ወር በሚካሄደው የኮንግረስ ምርጫ ላይ የሚኖረው እንደምታ ምን ሊሆን ይችላል?“)

ሆኖም ግን ማንም የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ቢሆን የኢትዮጵያ መንግስት ዴሞክራሲያዊ በሆነ ምርጫ የተመረጠ መንግስት ነው፡፡ በማለት የዋሹትን እና የቀጠፉትን የዓሳ ነባሪ ያህል የገዘፈውን ውሸት የዋሸ እና እስከ አሁንም ድረስ የታዬ ፕሬዚዳንት በአሜሪካ ምድር አንዴ ባራክ ኦባማ በፍጹም አልታየም፡፡

እ.ኤ.አ ሰኔ 2013 ሮበርት ሙጋቤ በዚምባብዌ በተካሄደው ምርጫ 61 በመቶ የመራጮችን ድምጽ በማግኘት አሸንፊያለሁ ብለው ሲያውጁ አስመሳዩ ኦባማ እንዲህ በማለት በንዴት ሰክሮ ነበር፡

የነጻነት ቃል ኪዳን በስልጣን ሙስና ሲተካ እና የሀገሪቱ የምጣኔ ሀብት ተንኮታኩቶ ሲወድቅ እስቲ ጎረቤታችሁን ዚምባብዌን ተመልከቱ፡፡ አሁን በደቡብ አፍሪካ የሚመራው የአህጉሩ የመሪዎች ስብሰባ ከተጠናቀቀ በኋላ ለረዥም ጊዜ ተንሰራፍቶ የቆየው የዚምባብዌ ቀውስ ያከትም እና የዚምባብዌ ህዝቦች አዲስ ሕገ መንግስትን በማጣጣም የምጣኔ ሀብቱም ማገገሙን የሚቀጥል ይሆናል፡፡ ስለሆነም ወደፊት ለመራመድ ጥሩ ዕድል ሊፈጠር ይችላል፣ ሆኖም ግን ነጻ፣ ፍትሀዊ እና ሰላማዊ ምርጫ በተግባር ላይ የሚውል ከሆነ ብቻ የዚምባብዌ ህዝቦች ያለምንም ማስፈራራት እና የበቀል እርምጃ ፍርሀት ሳይንበረከኩ የወደፊት ዕጣፈንታቸውን እራሳቸው የሚወስኑ ይሆናሉ፡፡ እናም ከምርጫዎች በኋላ ዴሞክራሲ የሚወሰንበት ዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ መብት መጠበቅ አለበት፡፡

እ.ኤ.አ ሀምሌ 2015 በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል ምንም ዓይነት ፍርሀት፣ ማስፈራራት እና የበቀል እርምጃ ሳይኖር ነፃ እና ፍትሀዊ በሆነ ምርጫ አሸንፏል ብሏል፡፡

ሆኖም ግን ባራክ ኦባማ በስልጣን ላይ እንደ መዥገር ተጣብቆ ለሚገኘው ገዥ አካል “ምርጫ  ከተካሄድ በኋላ ለዴሞክራሲ መሰረት የሆኑት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መጠበቅ አለባቸው” በማለት አልተናገረም፡፡

ስለሰብአዊ መብት ትንሽ ነገር አውረተናል አለ ኦባማ (ከአየር ንብረቱ ሁኔታ ጋር እና ከኢትዮጵያ የቡና ጣዕም ጋር በተያያዘ ቸዋታ ላይ)፡፡

ከህዝቦች ፈቃድ ውጭ በጠብመንጃ ኃይል በስልጣን እርካብ ላይ እንደ መዥገር ተጣብቆ የሚገኘው በኢትዮጵያ የሚገኘው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እ.ኤ.አ ግንቦት 2010 99.6 በመቶ የህዝብ ድምጽ በማግኘት አሸንፊያለሁ በማለት ሲያውጅ ኋይት ሀውስ የሚከተለውን መግለጫ አውጥቶ ነበር፡

ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ምርጫው የዓለም አቀፍ የምርጫ መስፈርቶችን አያሟላም በማለት ባወጡት መግለጫ መሰረት ያለንን ስጋት እንገልጻለን፡፡ የዩናይትድ ሰቴትስ ኤምባሲ ባለስልጣኖች በድምጽ መስጫ የምርጫው ዕለት ከመናገሻ ከተማዋ በመውጣት መታዘብ እና በመመልከት ምስክርነታቸውን እንዳይሰጡ በመከልከላቸው አዝነናል፡፡ ነጻ የሆነ የምርጫ መታዘብ ሁኔታ እና ነጻ የመገናኛ ተወካዮች ምርጫውን እየተመለከቱ እንዳይዘግቡ በመከልከላቸው በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡

እ.ኤ.አ ግንቦት 2015 ያው መንግስት መቶ በመቶ ምርጫውን አሸንፊያለሁ በማለት ሲያውጅ ባራክ ኦባማ ወይም ደግሞ የእርሳቸው አስተዳደር ምንም ዓይነት ስጋትን አልገለጠ ም፡፡ ሁሉም እየመጡ ምርጫው ዴሞክራሲያዊ ነው በማለት ቡራኬ ሰጥተዋል፡፡ (ምርጫው ዴሞክራሲያዊ ነው በሚለው ሀሳብ ላይ በሳቅ ከፈነዳችው ከሱሳን ራይስ በስተቀር)፡፡

.. ሀምሌ 21/2015 በቡሩንዲ ፔሬ ንኩሩንዚዛ ለሶስተኛ ዙር አሸናፊ መሆኑን ሲያውጅ የተባበሩት መንግስታት ሁሉን አሳታፊ፣ ነጻ፣ ፍትሀዊ እና በህዝብ ዘንድ ታማዕኒነት ያለው የምርጫ ሂደት አይደለም ብሏል፡፡

ንኩሩንዚዛ 69.41 በመቶ የመራጮችን ድምጽ በማግኘት አሸነፈ፤

እ.ኤ.አ ሀምሌ 28/2015 ባራክ ኦባማ በአፍሪካ ህብረት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በመገኘት በስልጣን ላይ ለመቆየት ሲባል አንድ መሪ በጨዋታ መካከል ላይ የጨዋታውን ህግ ለመቀየር ሲሞክር በቡሩንዲ እንዳየነው አለመረጋጋትን እና የእርስ በእርስ ጥላቻን ያስከትላል፡፡ ይህም ሁኔታ ብዙውን ጊዜ ወደ አስቸጋሪው መንገድ ለመግባት የመጀመሪያው እርምጃ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ መሪዎች ይህችን ሀገር አንድነቷን በመጠበቅ ይዠ ላቆያት የምችለው እኔ ብቻ ነኝ ሲሉ ይሰማሉ፡፡ ይህ ትክክል ከሆነ መሪው በእርግጠኝነት ሀገሩን በመገንባቱ ረገድ ፈተናውን ወድቋል፡፡

እ.ኤ.አ ሀምሌ 26/2015 በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል እና ምርጫውን መቶ በመቶ በማሸነፍ ባራክ ኦባማ የኢትዮጵያ መንግስት ዴሞክራሲያዊ በሆነ ምርጫ የተመረጠ መንግስት ነው ብለው ካወጀ ለት የይስሙላ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆነው ከኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር ቆመው ታይቷል፡፡

ባራክ ኦባማ የእራሳቸውን አመክንዮ መፋለስ ይመለከታሉን

አንድ ነጠላ የፖለቲካ ፓርቲ አንድን ምርጫ መቶ በመቶ አሸናፊ በሚሆንበት ጊዜ ፓርቲ የዚችን ሀገር አንድነት በመጠበቅ መያዝ የምንችለው ብቸኛ ተቋም እኛ ብቻ ነን ማለት አይሆንምን?

ባራክ ኦባማ የአስመሳዮች ሁሉ አስመሳይ!!!

ለእግዚአብሔር ሲባል ምን ዓይነት ገሀነም ነው በባራክ ኦባማ ላይ ያለው?!?

ኦባማ ለአፍሪካ አምባገነኖች እና ወሮበላ ዘራፊዎች ምን ዓይነት መልዕክት ነው እያስተላለፈ ያለው?

ባራክ ኦባማ የኢትዮጵያ አገዛዝ (ምርጫውን መቶ በመቶ ያሸነፈው) ዴሞክራሲያዊ በሆነ ምርጫ የተመረጠ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ነው ሲሉ ለቀሪዎቹ አምባገነን የአፍሪካ መሪዎች ምን ዓይነት መልዕክት እያስተላለፈ ነው ያለው ?

የሱዳኑ ኦማር አልባሽር በዚህ ባለፈው ሚያዝያ ወር የፕሬዚዳንትነት ቦታውን 94.1 በመቶ የህዝብ ድምጽ በማግኘት በሚቀጥለው ምርጫ ደግሞ መቶ በመቶ ለማድረግ በርትቶ እንዲሰራ ባራክ ኦባማ እየነገረ ያለው?

ኦባማ ለኬንያው ኡሁሩ ኬንያታ እ.ኤ.አ በ2013 በ50.51 በመቶ አሸናፊ በመሆን በሰሜን ካሉ ጎረቤቶቹ መቶ በመቶ ማሸነፋቸውን በማየት ለቀጣዩ ጊዜ አበርትቶ እንዲሰራ እየነገርረ ያለው?

ኦባማ እ.ኤ.አ በ2010 በ93.08 በመቶ ላሸነፈው እና አሁን በቅርቡ ደግሞ ሕገ መንግስቱን በማጣመም ለእድሜ ልክ ፕሬዚዳንት ለመሆን አውጆ ላለው ለሩዋንዳው ፖል ጋሜ ምን መልዕክት እያስተላለፉ ነው? ወንድም ፖል ከህወሀት ይማራል፡፡ እ.ኤ.አ በ2017 ያገኘውን ትምህርት ተግባራዊ በማድረግ መቶ በመቶ አሸናፊ ነኝ ብሎ ያውጃል፡፡ እየሰማህ ነው ኦባማ?!

አባማ እ.ኤ.አ በ2011 በተደረገው ምርጫ 68.38 በመቶ የህዝብ ምጽ በማግኘት አሸናፊ የሆነውን የኡጋንዳውን ዮሪ ሙሴቬኒ ምን ምክር ሊመክረው ነው?

ስማ! ስማ! ስማ! 68 በመቶ ውጤት ምን ሊያደርግልህ ነው ሙሴቬኒ—ሌሎችን ወንድሞችህን በሙሉ ስታይ የአንተ ውጤት መጥፎ ነው፡፡ ወንድም ይህንን ውጤትህን እ.ኤ.አ በ2016 ከፍ አድርገው፡፡ አግዝፈው! መቶ በመቶ አድርገው፡፡ ማን ይነካህና በጉልበት አሳድገው!

ባራክ ኦባማ ለዚምባብዌው ለሮበርት “መቱሳላ ” ሙጋቤ (በሚቀጥለው ዓመት አንድ ሺ ዓመት የሚሆነው) የያዘውን ጨዋታ 61 በመቶ ያገኘውን የመራጮች ድምጽ መቶ በመቶ እንዲያደርገው ይነግረዋል?

(የሙጋቤ ጉዳይ ከሌሎች የተለየ ነው፡፡ ሌሎቹ የምርጫ ሌቦች የእራስ ናቸው፡፡ የእኛ ወዳጆች ናቸው፡፡ ሙጋቤ የእኛ ልጅ አይደለም፡፡ እንደፈለገው በእራሱ ይሂድ፡፡)

ኦባማ በአፍሪካ ለዴሞክራሲ መስፈን በመታገል ላይ ላሉት ሁሉም የአፍሪካ ወትዋቾች ምንድን ነው የሚነግረው?

ባራክ ኦባማ ምርጫዎች በእራሳቸው እውነተኛውን ዴሞክራሲ ያመጣሉ በማለት ለአፍሪካ ወጣቶች ይነግራል?

ኦባማ ዩኤስ አሜሪካ የአፍሪካን ህዝቦች ህይወት የሚያጠፉትን ዋናዎቹን አምባገነኖች አቅፋ እና ተንከባክባ ትይዛለች በማለት ለአፍሪካ ወጣቶች ይናገራል?

.. 1995 የአባቴ ህልሞች በሚል ርዕስ ባራክ ኦባማ እንዲህ የሚል ጽሁፍ አስፍረው ነበር፡

ኃይል የሌላቸውን እና ተስፋ የቆረጡትን ተስፋ ቢሶች አይቻለሁ፡ በጃካርታ መንገዶች ላይ የበርካታ ልጆችን ህይወት የሚያጣምሙ ወይም በናይሮቢ በተመሳሳይ መልኩ በችጋጎ ደቡባዊ ክፍል መንገዱ ለልጆች ውርደት ምን ያህል ጠባብ እንደሆነ እና ያልተቋረጠ ንዴት እንደሚታይ እና እንዴት ለኃይል እና ለተስፋየለሽነት እንደሚዳረጉ የሚያመላክት ነገር ነው፡፡ የነገሮችን አስቸጋሪነት እገነዛባለሁ፡፡ የአክራሪነትን መታቀፍ፣ የጎሳ እና ሌሎችም ሁሉ ሁላችንንም የሚያሰጉን ጉዳዮች ናቸው፡፡

በእርግጠኝነት ኦባማ ኃይል የሌላቸውን ተስፋቢስ የሆኑትን የጃካርታ ወይም የናይሮቢን ወጣቶች እና ልጆች ለመመልከቱ ጥርጣሬው አለኝ፡፡

በአዲስ አበባ ያሉትን ተስፋየለሽ እና ኃይል የሌላቸውን ወጣቶች እንዳላዩ በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁ፡፡

ምናልባትም ኦባማ ለአፍሪካ ወጣቶች የሚያስተላልፉት መልዕክት ወጣቶቹ ጸጥ ብለው እንዲቀመጡ እና በእራሳቸው መንገድ እንዲህ እንዲሆኑላቸው ይፈልጋሉ፡

ስለአዕምሮም ሆነ ስለቁስ አካል ያለው ሁኔታ ይኸው ነው፡፡ ስለተስፋ መቁረጥ እና ስርዓተ አልበኝነት ለእርራሱ  ጉዳዩ  አይደለም፡፡

የአፍሪካ ህይወቶች ለኦባማ ጉዳዩ አይደለም፡፡

የጥቁር ህዝቦች ህይወት ለኦባማ ጉዳዩ ነውን? እውነታውን መያዝ ይቻላልን?

ኦባማ እ.ኤ.አ ሀምሌ 26 ወይም ሀምሌ 28 ባሰማው ዲስኩሩ  እራሱ  ዴሞክራቶች እና የአሸባሪነት ተከላካዮች እያሉ በሚያሞካሿቸው የጫካ ወሮበሎች አሳር ፍዳቸውን እያዩ እና ህይወታቸው እየተጣመመ ስለሚገኙት ወጣት ጋዜጠኞች ማለትም እስክንድር ነጋ፣ ውብሸት ታዬ፣ ተመስገን ዳሰለኝ፣ የዞን 9 ጦማሪያን፣ ወጣት የእስልምና ኃይማኖት መብት ወትዋቾች እና ስለሌሎች የፖለቲካ እስረኞች ጉዳይ አንዲትም ቃል ትንፍሽ ሳይሉ ቀርቷ፡፡

ባራክ ኦባማ “የኢትዮጵያ መንግስት ዴሞክራሲያዊ በሆነ ምርጫ የተመረጠ መንግስት” ነው እያሉ በሚያወድሱት ወሮበላ አገዛዝ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩት ተስፋየለሾች ምንም ዓይነት ሀሳብ የላውም፡፡

ባራክ ኦባማ ኢትዮጵያውያን በየዕለቱ ስለሚደርስባቸው ውርደት እና ለመገደብ አስቸጋሪ እየሆነ የመጣው ቁጣ ለመፈንዳት ከጫፍ ላይ እየደረሰ ስለመሆኑ እና ህዝቦች አዕምሯቸው እና ልቦቻቸው ሁሉ ሳይቀሩ በወሮበላው የዘራፊ ቡድን ስብስብ አስመሳይ መንግስትነት ቁጥጥር ስር የወደቁ ስለመሆናቸው ትንሽም ሀሳብ ቢሆን ሊሰጥ  የሚችለው ነገር አለው?

ባራክ ኦባማ የእነርሱን የጫካ ወሮበላ ዘራፊዎች እየረዳ  ምክንያቱም ያንን ቆሻሻ ስራቸውን በሶማሌ እና በደቡብ ሱዳን እየሰሩለት ስላሉ ብቻ ዝም በማለት በዚሁ ሁኔታ እገዛቸውን የሚቀጥል  ከሆነ እና ወደፊት በኢትዮጵያ ሊከሰት ስለሚችለው ሁኔታ ትንሽም ሀሳብ ቢሆን ሊኖረው  ይችላልን?

እ.ኤ.አ ታህሳስ 2013 የኔልሰን ማንዴል የቀብር ስነስርዓት በሚፈጸምበት ጊዜ ባራክ ኦባማ ማንዴላ “ታሪክን በእጆቻቸው አስገብተው የያዙ እና ዓለም አቀፍ የሞራል ስብዕና ጎራዴን ወደ ፍትህ እንዲዞር ያደረጉ“ በማለት አወድሶ ነበር፡፡

ታሪክ ባራክ ኦባማን “ታሪክን በሁለት እጆቻቸው የያዙ እና ዓለም አቀፍ የሞራል ስብዕና ጎራዴን ወደ ፍትህ እንዲዞር ያደረገ ” ወይስ ደግሞ ባራክ ኦባማ “የአፍሪካ ደም መጣጮች፣ ጓደኛ እና አጋሮች” ሊለው ይችላልን?

በእውነት ስለባራክ ኦባማ ከልብ አዝናለሁ፡፡

ባራክ ኦባማ ለታላቅነት ታድሎ ነበር፡፡

ሆኖም ግን ነገሩ ሁሉ ግልብ እና በምክንያታዊነት ላይ የተመሰረተ ሳይሆን ኢአመክንዮያዊ ሆኖ አረፈው፡፡

አፍሪካውያን በባራክ ኦቦማ ላይ ከፍተኛ የሆኑ ተስፋዎች ነበሯቸው፡፡ ባራክ ኦባማ የምረጡኝ ዘመቻ ቅስቀሳቸውን እያካሄደ በነበረበት ወቅት ሁሉም አፍሪካውያን ይደለዎ ብሎት ነበር፡፡ ከዚህም በላይ በአንድ ጎን በኩል የዘራቸው ሀረግ የሚመዘዘው ከአፍሪካ በመሆኑ በተደረገላቸው ከፍተኛ ድጋፍ አሸንፎ ድልን ለመቀዳጀት በቃ፡፡

ባራክ ኦባማ በምርጫው አሸናፊ ከሆነ በኋላ ስሜትን በሚማርከው አንደበተ ርትዑ ንግግሩን የአፍሪካውያንን ልብ እና አዕምሮ መቆጣጠር ችሎ ነበር፡፡

ዛሬ ግን በአፍሪካ የኦባማ ክብር ወድቆ ተንኮታኩቷል፡፡

ባራክ ኦባማ የአፍሪካን ህዝቦች ማፍቀሩንና እና ማክበሩን  እርግፍ አድርገው በመተው በዚያ ፋንታ የአፍሪካን ህዝቦች መብቶች ከሚያዋርዱ እና ከሚደፈጥጡ እንዲሁም የስቃይ ኑሮን እንዲገፉ ከሚያደርጉት አምባገነኖች ጋር ወደመሞዳሞድ እና መተቃቀፉ ተመልሰው ባተሌ ሆኖ  ይታያል፡፡

ባራክ ኦባማ አምባገነኑ አገዛዝ መቶ በመቶ አሸንፊያለሁ ብሎ ያወጀውን የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ “ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ነው” በማለት የኢትዮጵያን ህዝቦች የማሰብ ክህሎት ዘልፏል፡፡

ባራክ ኦባማ በፈጸመው  መጥፎ ተግባር የኢትዮጵያን ህዝብ እንዲሁም ሌላውን የአፍሪካን ህዝብ አስቆጥቷል፡፡

በቁስል ላይ እንጨት እንዲሉ ባራክ ኦባማ በአፍሪካ ህብረት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በመገኘት ስለመልካም አስተዳደር እና ስለግልጽነት ሲሰብክ  ተስተውሏል፡፡

እንዲህ በማለትም ድምፁን  ከፍ በማድረግ ጩኸቱን  አም ቷ ል፣ “አፍሪካውያን በሰው ልጆች ክብር ላይ የተቃጣውን አደጋ በሚያህል መልኩ በድህነት ውስጥ ተዘፍቀው ይኖራሉ፡፡ ዩናይትድ ሰቴትስ ከእናንተ ጋር በመሆን በጋራ ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመዋጋት፣ መልካም አስተዳደርን ለማጎልበት፣ ግልጽነትን እና የሕግ የበላይነትን ለማስፈን ከጎናችሁ ተሰልፋ ለመስራት ትፈልጋለች፡፡“

ባራክ ኦባማ ንግግራቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ከእነዚያው ወሮበላ ዘራፊ አምባገነኖች ጎን  በመቀመጥ ቸበርቻቻ ግብዣውን አቅልጠውታል፡፡

ባራክ አቦማ ስለመልካም አስተዳደር፣ ግልጽነት እና የሕግ የበላይነት ለአፍሪካ ህብረት ይሰብካሉ፣ እናም በአህጉሪቱ ውስጥ በእስከፊ ሁኔታ የሰብአዊ መብትን ከሚደፈጥጡ ወሮበላ ዘራፊ አምባገነኖች ጋር ውሸትን ይቀጥፋሉ፡፡

ባራክ ኦባማ ይቅርታ ይተይቀን?

በመጀመሪያ ደረጃ ባራክ ኦባማ ይቅርታ እንዲያደርግልኝ እጠይቃለሁ!!

ኢትዮጵያን እንዲጎበኝ  በመጋበዜ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች፣ የመገናኛ ብዙሀን ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጉብኝት እንዲሰርዝ  በተደጋጋሚ እያሳወቁ ባሉበት ጊዜ እኔ ግን ይቀጥሉ፣ ሂድ ጎብኝ   በማለት ሽንጤን ገትሬ ብጽናት ስታገል ነበር፡፡

ኦባማ ወደ ኢትዮጵያ በመሄድ እውነታውን መናገር እንደማይችል  እና ክፍት አፍ መሆኑን አስቀድሜ ባውቅ ኖሮ እኔም ሌሎችን ቡድኖች በመቀላቀል ወደ ኢትዮጵያ እንዳይሄድ ለማድረግ እታገል ነበር!

እንደዚሁም ሁሉ የዘራፊ ወሮበላው መንግስት የጥበቃ አባላት ኦባማ አዲስ አበባ በገባበት ወቅት ላደረጉት አቀባባል ይቅርታ ጠይቃልወሁ አቀርባለሁ፡፡

ወያኔዎች ለዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ፕሬዚዳንት ለባራክ አቦማ ክብር ሲሉ የቀበሌ ጥበቃ አባሎችን ወስደዋቸው ነበር፡፡ ምን ዓይነት አሳፋሪ ነገር ነው!!!

ከዚህ ቀደም እንደተናገርኩት ሁሉ ዘራፊ ወሮበላውን ከጫካ ልታወጣው ትችላለህ፣ ሆኖም ግን ጫካውን ከዘራፊው ውስጥ ልታወጣው ከቶውንም አትችልም!

ከዚህ ጋ ጫን በማድረግ ለኦባማ በህንድ ጥበቃ አባላት ለክብራቸው ሲባል የተደረገውን እና በተመሳሳይ መልኩ በአዲስ አበባ የተደረገውን በማነጻጸር የእራስን ግንዛቤ መውሰድ ይቻላል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ባራክ ኦባማ ለኢትዮጵያ ህዝብ ይቅርታ የማቅረብ ዕዳ አለበትን?

ባራክ ኦባማ ጨዋ እና ለህሊናው የሚገዛ  እውነተኛ ሰው ቢሆን ኖሮ የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ እንዲጠይቅ አሳስበው ነበር።

እኔንም በግል ይቅርታ እንዲጠይቀኝ እጠይቀው ነበር።

ከሁሉም በላይ ደግሞ ሁለት ጊዜ ተመራጩ ዕጩ ፕሬዚዳንት በነበረበት ጊዜ ለእርሱ  ድጋፍ ለማሰባሰብ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዓቶችን አባክኛለሁ!

ባራክ ኦባማ የመልካም ስብዕና ትንሽ ቁራጭ አለው ብዬ ባምን አረገው ነበር።

ሆኖም ለመጠየቅ የሚያስጨንቀኝ ምንም ዓይነት ጉዳይ የለኝም፡፡

ኦባማ ይቅርታ የሚጠይቅ  ቢሆንም እንኳ የእርሱው ይቅርታ የውሸት እንደሚሆን አውቃለሁ፡፡

በባራክ ኦባማ ላይ በጣም አዝኛለሁ፡፡

ያሉኝን ቅሬታዎች ለመግለጽ ቃላት ያጥሩኛል፡፡

ሆኖም ግን የግል ቅሬታዎቼን ራሴ አቸለዋለሁ።

ሆኖም ግን ኦባማ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩትን ደኃ አፍሪካውያን ህዝቦችን መክዳቱ ሊረሳ የማይችል አሳፋሪ ታሪክ ነው፡፡

ተስፋን ለማለምለም እና ለማጎልበት ሲባል በርካታ አፍሪካውያንን በሚመስጡ ንግግሮቻቸው ሰዎችን ይስብ ነበር ሆኖም ግን በወሳኙ ጊዜ እና ተጨባጭነት ያለውን ጥቅም ማግኘት በሚኖርባቸው ወቅት ተስፋቸውንም ለመንጠቅ እና ተስፋቸውን ለማደብዘዝ ብቻ ጊዘዉን ሲያባክን ታየ።

ፍጹም ካሁን በህዋላ ከዚህ ዕለት ጀምሮ ባራክ ኦባማ የሚለው ስም ለእኔ በሁለት ቢላዋ የሚቆርጥ፣ መንታ ምላስ፣ የተዛባ እና እርባና ቢስ ከሚል ሀረግ የዘለለ ሌላ ትርጉም የለውም፡፡

እውነታውን አቀርባለሁ

ማንም ፖለቲከኛ እኔን ፊት ለፊት ሊያሞኘኝ እና ሊያታልለኝ ቢሞክር እንዲህ በማለት እነግረዋለሁ/እነግራታለሁ፣ አንዴ ባራክ ኦባማ አትሸርድደኝ “ በማለት እነግረዋለሁ/እነግራታለሁ፡፡

“ባራክ” የሚለው ቃል የተባረከ የሚል አፍሪካዊ ስምን ይዞ የሚገኝ ቃል ነው፡፡

ሆኖም ግን ባራክ ኦባማ የሚለው ስም በኢትዮጵያ ታሪክ ክብሩ ተንዘቃዝቆ በመውረድ “ባራክ ከይሲ” በሚለው ተተክቷል፡፡

የሸክስፒር እንዲህ ብሏል። “በጣም ታዋቂ የሆነ ቦቅቧቃ ፈሪ፣ ምንም ማብቂያ እና ማቋረጫ የሌለው ውሸት እና በየሰዓቱ የሚደረግ ቃል ኪዳንን የሚያፈርስ ፣ ጥሩ ለሆነ ነገር ምንም ባለቤት የማይሆን” በሚል ግልጽ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ደህና፣ ባራክ ኦባማ ለእኔ ጓደኛ ወይም ደግሞ አጋር ሊሆኑ አይችሉም!

በባራክ ኦባማ የኢትዮጵያ  ጉብኝት ሁሉም ነገሮች ደህና በሚባል መልኩ ያልተጠናቀቁ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ሁሉም ነገሮች ለባራክ ኦባማ  መጥፎ ሆነው በጣም መጥፎ ሆነው ተጠናቅቀዋል!

ባራክ ኦባማ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የማይታይ በጣም የደበዘዘ የታርቅ የግርጌ ማስታወሻ ማውጫ ሆኖ ይቀጥላል፡፡

ባራክ ኦባማ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የቀልድ መሳለቂያ ሆኖ ይኖራል፡፡

የኦባማ ስም የበሬ ኮርማ ጥጃ ወለደ ከሚለው አባባል ጋር በእኩል ደረጃ በመፈረጅ አንድ ገዥ አካል መቶ በመቶ የመራጮችን ድምጽ በማግኘት ዴሞክራሲያዊ ምርጫ አካሄደ ከሚለው ጋር መሳ ለመሳ ይሆናል፡፡

ኦባማ ከፕሬዚዳንትነት ስልጣኑ ከሚለቅበት ከሁለት ዓመታት በኋላ ለኢትዮጵያውያን የምያስታዉሰዉም አይኖር።

ከዛሬ ጀምሮ ከሁለት ዓመት በኋላ የኦባማን እርባናየለሽ እና የቅጥፈት ቃላት ይረሷቸዋል፡፡ የእርሱን አናሳ ለእራስ ታላቅ ግምት የመስጠት እና የጉብኝቱን  አጋጣሚ ሁሉ ይረሳሉ፡፡

ጥቂት ኢትዮጵያውያን እራሴን ጨምሮ ኦባማ ስለተናገራቸው ጉዳዮች ሁሉንም ነገር በመርሳት ይቅርታ እናደርግላቸዋለን፡፡

ለኦባማ ይቅርታ አደርጋለሁ ምክንያቱም ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ በማስተማር ስብከታቸው “ጠላቶችህን እንደ እራስህ ውደድ” በማለት ይቅርታ ማድረግ እንዳለብኝ አስተምረውኛል፡፡

ሆኖም ግን ኦባማ የእኔ ጠላት አይደለም፡፡ በፍጹም ጠላቴ አይደለም! እርሱ በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ በሚያራምዳቸው ፖሊሲዎቻቸው ላይ አልስማማም፡፡

ዶ/ር ማርቲን ኪንግ እንዲህ ብለው ነበር፣ “ይቅርታ ለማድረግ እራሳችንን ማዘጋጀት እና አቅማችንን ማጎልበት ይጠበቅብናል፡፡“

እውነት ለመናገር በቃላት ልገልጸው ከምችለው ባላይ በባራክ ኦባማ ላይ ተበሳጭቻለሁ በጣምም አዝኛለሁ፡፡ ለእርሱ ይቅርታ ለማድረግ አልፈልግም!

ሆኖም ግን ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ በስብከት ትምህርታቸው ላይ በግልጽ ባስቀመጡት ምክንያት እና ባራክ ኦባማም ስለኢትዮጵያ ድሆች የተናገረዉን ነገሮች ምን ጊዜም እንደማይረሷቸው ጽኑ እምነት አለኝ፡፡

ባራክ ኦባማ በኢትዮጵያ ህዝቦች ቤቶቻቸው፣ በእራሳቸው ከተማ እና በሀገራቸው በመምጣት በህዝቦች ላይ ገዥ ሆነው የተቀመጡት አምባገነኖች ያደረጉት ምርጫ በዴሞክራሲየዊ መንገድ የተካሄደ እና ዴሞክራሲያዊ ነው በማለት ሲናገር  የህዝቡን ሞኝነት፣ ድድብና እና እርባናቢስ አድርጎ  ከማየት ጋር የተቆራኘ በመሆኑ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩት የኢትዮጵያ ህዝቦች ምንጊዜም ቢሆን በፍጹም፣ በፍጹም፣ በፍጹም ሊረሱት እንደማይችሉ ሊታወቅ ይገባል፡፡

ተስፋ የማደርገው ግን እነዚህ ህዝቦች ይቅርታ ማድረግ እና ነገሩን ሁሉ መርሳት ይኖርባቸዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ እንዲህ የሚሉትን መርሆዎች መተግበሬን አልረሳውም፡፡ “ትክክለኛ ነገርን ለመስራት ጊዜ ሁልጊዜ ትክክለኛ ሆኖ ይጠብቀናል፡፡“ “እውነት ነው፣ ትክክለኛ ነገርን ለመስራት በፍጹም ትክክለኛ ያልሆነ ጊዜ የለም፡፡“

ባራክ ኦባማ በኢትዮጵያ ህዝቦች አማካይነት ደህና ስራ ለመስራት ይችላል ከፈለገ፡፡

ጨለምተኝነት በተንሰራፋበት፣ የአዕምሮ ጭንቀት በወጠረበት፣ ምንም ዓይነት የተስፋ ጭላንጭል በማይታይበት፣ድፍረት በጠፋበት፣ አሳዛኝ ክስተት በተንሰራፋበት ስሜት ይህንን ትችት እየጻፍኩ ባለሁበት ጊዜ በተስፋ መለምለም በመገፋፋት ለህዝብ አገልግሎት ሲባል ባራክ ኦባማ ወደዚች ሀገር መጥተዋል የሚል አስተሳሰብ አለኝ፡፡

የሕግ ባለሙያው ባራክ ኦባማ ሀብታም የሆኑ የሕግ ድርጅቶችን ሳይሆን ለህዝብ ቅን የሆነ አገልግሎት ለመስጠት ዕጣ ፋንታ መርጦ ነብወር።

እ.ኤ.አ በ2008 ባደረጉት መሳጭ ንግግሩ  ከትክክለኛው የታሪክ ሕግ መቆም እንደሚኖርብኝ ከፍተኛ መነሳሳት ፈጥሮብኝ እንዳልነበረ ሁሉ አሁን አ.ኤ.አ በ2015 ደግሞ ሁሉም ነገር ሙጥጥ ጥርግ ብሎ ጠፍቶ የህዝቦችን ተስፋ መና የሚያደርግ የከሀዲነት ንግግር ሲያሰማ ከማየት በላይ የከበደ ነገር የለም፡፡

በጥልቁ ተስፋ መቁረጥ ላይ ጥልቅ የሆነ ተስፋ መቁረጥ ተጨምሮ እንዲህ የሚሉትን የዕውቁን የኒኩሊዬር ሳይንቲስት የጀ. ሮበርት ኦፐንሄይመርን የእሳት እና አቧራ (የኑክሌር ፈንጂ ማለት) አይተው ሲናገሩ፡

ዓለም አንድ እንደማትሆን እናውቃለን፡፡ ጥቂት ሰዎች ይስቃሉ፣ ጥቂቶቹ ደግሞ ያለቅሳሉ፣ አብዛኞቹ ህዝቦች ግን ጸጥ ብለዋል፡፡ ከህንዱ ስነጽሁፍ ባጋቫድ ጊታ ከሚለው አንድ መስመር አስታውሳለሁ፡፡ የቪሽኑ [የሂንዱ የመልካም ስርዓት፣ ትክክለኛነት እና እውነት] ልዕልቷን [ስልጣንን ለመያዝ በሚደረግ ሽኩቻ እና ትግል] ለማሳመን ጥረት በማድረግ የእራሱን ስራ እየተወጣ ባለበት ሁኔታ እና የእርሱን ዘርፈ ብዙ ወታደራዊ አደራጃጀት በመመልከት እንዲህ ይል ነበር፣ ‘እኔ አሁን ሞት ሆኛለሁ፣ ዓለምን የሚደመስስ’ ስለሆነም እኛ ሁላችንም በአንድ ወይም በሌላ መልኩ እናስባለን፡፡

በምድር ላይ በጣም ታላቁ ኃያሉ ሰው ባራክ ኦባማ የእራሱን  የጸረ ሽብርተኝት ጦርነትን አጋር ለማስደሰት እና ለመሳብ በማሰብ በኢትዮጵያ ላይ ውሸት በመናገር ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ ስለመስራቱ  ላይገባው ይችላል።

ባራክ ኦባማ በግልጽ ሊታዩ የማይችሉ ኃይሎችን ስለመቀስቀሳቸው፣ ስላነሳሱት ቁጣ እና “የኢትዮጵያ መንግስት በዴሞክራሲያዊ ምርጫ የተመረጠ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ነው” ብሎ  በአንድ ዓረፍተ ነገር ሲናገር  በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ህይወት ሊጎዳ የሚችል እና ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ስሜታዊነትን ሊቀሰቅስ እንደሚችል ምንም ዓይነት ሀሳብ የለዉም፡፡

የባራክ ኦባማ 7ቱ አታላይ ቃላት ስለሚያስከትሉት ጉዳት ምንም ዓይነት ሀሳብ ሳይኖር በኢትዮጵያውን ላይ የጥላቻ እና የበቀል ዘሮችን በመዝራት ከፍተኛ የሆነ ዋጋ ሊያስከፍል የሚችል አደጋን ይጋብዛል፡፡

ባራክ ኦባማ በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ኢትዮጵያውን ልብ እና አዕምሮ ውስጥ የጥላቻ፣ የፍቅር እጦት፣ የጠላትነት እና የደስታ እጦትን በመፈልፈል አንድ ቀን የእሳት እና የአቧራ እንጉዳዮችን ሊፈለፍሉ እንደሚችሉ እንዲያውም ከዚህም ባለፈ መልኩ የተራሮችን መሰረት ለመናድ እሳት ለኩሰው እንደሚሄዱ ልብ ሊለው ይገባል፡፡

ይህ ድርጊት ዓይን ላላቸው እና ማየት ለሚችሉ ህዝቦች ሁሉ በግልጽ ሊታይ የሚችል ራዕይ ነው፡፡

ባራክ ኦባማ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ታጥቆ  የተነሳ ሞት ሆኗል!  

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

ሀምሌ 28 ቀን 2007 .

 

 

Similar Posts