ኤጭ! ወያኔ እንደገና አሸነፈ!
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በዘረፋ ለሚያሸንፈው የይስሙላ ምርጫ የምስራች የሚሉት አሽቃባጮች በዝግጅት ላይ ናቸው!
“ፖለቲከኞች እንደ ዳይፐር/የህጻናት መጸዳጃ ጨርቅ ናቸው፣ ለአንድ ዓይነት ምክንያትም በየጊዜው መለወጥ አለባቸው”
ሆኖም ግን በወያኔ ኢትዮጵያ ይህ ጉዳይ የሚሰራ አይደለም!
ምስኪኗ ኢትዮጵያ የወያኔን ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የጠነባ ዳይፐር እንደገና ለ5 ዓመታት በጠቅላላው ለ25 ዓመታት እንድትለብስ ተፈርዶባታል፡፡ ይህም ማለት ለሩብ ምዕተ ዓመታት ያህል ማለት ነው፡፡ እንደው ምን ክፉ ጥሎሽ ነው ኢትዮጵያን የጣላት!
ደህና!!! መጀመሪያ ነገሮች ይቅደሙ፡፡ እኔ እራሴን እንደ ጨዋ ሰው፣ ምሁር እና እንደ ፍርድ ቤት መኮንን አድርጌ አሰባለሁ፡፡ የሸፍጥ እና የተጭበረበረ የይስሙላ ምርጫ አሸናፊ ባለድሎችን አንክዋን ደስ አላቸሁ ማለት ላፍም ያህል ቢሆን መባል አለበት፡፡
በጨዋ ሰው ባህል አንክዋን ደስ አላችሁ ይባላ። የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አንክዋን ደስ አላችሁ፡፡ (በእርግጥ ወያኔ ዛሬ ለሚያሸንፈው የይስሙላ ምርጫ ከዓመት በፊት እንኳን ደስ ያላችሁ ብዬ ነበር፡፡ ይህንን ሳበስር ባለፉት ጥቂት ወራት ሁሉ ደግሜ እና ደጋግሜ ስለው ቆይቻለሁ፡፡)
ወያኔዎች በሸፍጥ ለተሞላው እና ለተጭበረበረው የይስሙላ ምርጫ እንኳን ደስ አላችሁ፡፡ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ሁለተኛ አስርት ዓመታት ውስጥ በዓለም እጅግ በጣም ምርጥ የሆነ የዘረፋ ምርጫ ስላካሄዳችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ!
ለወያኔ ማሸነፍ ዕውቅና ሰጥተናል፡፡ አሸንፋችኋል፣ የዘረፋ ምርጫችሁን ማለቴ ነው፡፡! በግልጽ ለመነጋገር ወያኔ ያሸነፈው የኢትዮጵያን ህዝብ ልብ እና አዕምሮ አይደለም፡፡ በዚህ ዓይነት መንገድ ቢሆን ኖሮ ምንጊዜም ቢሆን አሸናፊ ልትሆኑ አትችሉም ነበር፡፡ ክብራቸውን፣ አድናቆታቸውን እና ምስጋናቸውን በምንም ዓይነት መንገድ ልታገኙ አትችሉም፡፡ በሺዎች ዓመታትም እንኳ አታገኙትም፡፡ ይሄ የማይጠረጠር ነገር ነው።
ወያኔ እንደ እንደዚህ ያለውን ቅጥ አንባሩ የጠፋ የሸፍጥ ምርጫ እንዴት አድርጎ ነው ማሸነፍ ቻለ? ይኸ ነገር በእርግጠኝነት የጥንታዊቷ ቻይና ድብቅ ሚስጥር አይደለም፡፡
ምናልባትም ይህንን ጉዳይ ወደኋላ መለስ በማለት ለማየት እሞክራለሁ፡፡ እርግጠኛ ነኝ ቻይናዎች ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አንድ ወይም ከዚያ በላይ የሆነ የጠለፋ (የምርጫ ዘረፋ ጠለፋ፣ ይህም ደግሞ ሌላው የእንግሊዝኛ አዲስ ቃል) ትምህርት አስተምረዋል ብዬ አምናለሁ፡፡
እ.ኤ.ኤ 2007-08 በተካሄደው ብሔራዊ የህዝቦች የምርጫ ኮንግረስ/National People’s Congress Election የኮሙኒስት ፓርቲው 2987 መቀመጫዎችን በሙሉ ጠቅልሎ ወስዷል (አሸንፏል ለማለት የማያስሄድ ስለሆነ ነው፡፡)
እ.ኤ.አ በ2010 በኢትዮጵያ በተካሄደው ሀገር ምርጫ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሁለት መቀመጫዎችን በመተው 547 የሆኑትን መቀመጫዎች በሙሉ በመውሰድ 100 በመቶ ለመያዝ ምንም የቀረው ነገር አለ ለማለት የሚያስደፍር አይደለም፡፡ ይህም ማለት ወያኔው 99.6 በመቶ በመያዝ የአንድ ፐርሰንት አራት አስረኛ ብቻ ነበር የቀረችው፡፡
እ.ኤ.አ በ2010 የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ምን አደረገ? በ2015ስ ምን ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል?
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የዘረፋ ምርጫ የማሸነፊያ ሚስጥርን እነሆ፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ድምጽን በገንዘብ በመግዛት ያሸንፋል፡፡ ይኸ ምንም የሚያሻማ ነገር የሌለው ግልጽ ነገር ነው!
ወያኔ ለገበሬው ምርጥ ዘር፣ ማዳበሪያ እና ምቾትን የሚያስገኙ ሌሎች ክፍያዎችን በመስጠት የሸፍጥ ድምጽ ለማግኘት ሲል የወሮበላ ንግድ ስራን ይሰራል፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የዘረፋ ምርጫን ለማሸነፍ ሲል የዩኤስ አሜሪካንን እርዳታ (ከአሜሪካ ህዝብ ኪስ የተሰበሰበውን ዶላር) ከታለመለት ዓላማ ውጭ ለተጭበረበረ ድምጽ ማስገኛ እንዲውል ያደርጋል፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የመሰረታዊ አገልግሎቶች ጥበቃ/Protection of Basic Services (የደህንነት ክፍያ) እየተባለ የሚጠራውን ገንዘብ ድምጽን ለመሸመት ሲል ከታለመለት ዓላማ ውጭ ህሊናቸውን ለገንዘብ ለሸጡ ጥቅመኞች እና ድሆች በማደል የተጭበረበረ ድምጽ ለማግኘት ይውተረተራል፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የተራበውን ህዝብ እንደ ደካማ ጎን በመውሰድ የእርዳታን እህል እንደ ድምጽ ማካበቻ ስልት ይጠቀምበታል፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በድብቅ እና ህገወጥ በሆነ መልኩ ድምጽን በመግዛት ለእኩይ ዓላማው ማስፈጸሚያ ለማድረግ ጥረት ያደርጋል፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ጉቦ በመስጠት፣ በማሸማቀቅ እና በማስፈራራት ድምጽን ለማግኘት የሞት ሽረት ትግል ያደርጋል፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የተጭበረበረ ድምጽ ለማግኘት ሲል ማንኛውንም ዓይነት ድርድር እና ስምምነት ያደርጋል፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ያለምንም ይሉኝታ እና ሀፍረት ድምጽን በጠራራ ጸሐይ ይሰርቃል፣ ይዘርፋል፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሁሉንም ድምጽ ያገኘ ለማስመሰል የድምጽ መስጫ ካርዶችን በድምጽ መስጫ ኮሮጆዎች ውስጥ በድብቅ እየወሰደ ያጅላል፣ ያጭቃል፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ምርጫውን አጭበርብሮ ለማሸነፍ ያለ የሌለ ኃይሉን ሁሉ ይጠቀማል፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ምርጫውን እና የምርጫውን ሂደት የሚከታተለውን የምርጫ ኮሚሽን ተብዬውን በባለቤትነት በመያዝ እንደፈለገው የሚያዝዘው እና ምርጫውን ለማጭበርበር እና ለመዝረፍ የሚጠቀምበት ዋናው መሳሪያው ነው፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ወደ ምርጫ ጣቢያው የሚሄደው ሰው ሁሉ እርሱን መምረጥ እንዲችል በየምርጫ ጣቢያው ወሮበላ ዘራፊዎችን አሰማርቶ እንዲያስተባብሩ ያደርጋል።
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እርሱን በፖለቲካ አመለካከት የሚቃወሙትን ሁሉ ሰብስቦ በማሰር በይስሙላው ፍርድ ቤት በህግ ሰበብ በተንዛዛ ቀጠሮ በማመላስ ከውድድር ውጭ በማድረግ ዘርፈ ብዙ ጭቆናውን ያካሂዳል፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አሸባሪ ወሮበሎች አንዱን ጎሳ በሌላው፣ አንድን የኃይማኖት ቡድን በሌላው ላይ በማነሳሳት ድምጽን ለመዝረፍ እንዲመቸው የተቻለውን ሁሉ ነገር ያደርጋል፡፡ ይህን እኩይ ምግባሩን ተግባራዊ ለማድረግ ሲል ወያኔን ካልመረጣችሁ አማራ ተመልሶ ይመጣባችኋል፡፡ ወያኔን ካልመረጣችሁ አሮሞዎች ከኦሮሞ ክልል ሙልጫ አድርገው በማስወጣት ያባርሯችኋል፡፡ ወያኔን ካልመረጣችሁ የክርስትና እምነት ተከታዮች በእስልምና እምነት ተከታዮች…የእስልምና እምነት ተከታይ ቡድኖች ደግሞ በክርስትና እምነት ተከታዮች ላይ ይነሳሉ…. ወያኔን ካልመረጣችሁ ሰማይ እና ምድር ይገለባበጣል፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የድምጽ ቆጠራ ስራውን በማዛባት ይቆጥራል፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ድምጽ ለመስጠት ከተመዘገቡት መራጮች የበለጠ የተሰጠ ድምጽ ይቆጥራል (የሞቱትን ሳይጨምር ለመምረጥ የተመዘገቡትን ብቻ በመውሰድ)፡፡
ከሁሉም በላይ ደግሞ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ድምጾችን ይቆጥራል፣ እናም የሁሉም ድምጽ ሰጭዎች እኩል የመቆጠር መብት ያላቸው መሆኑ ቢታወቅም ጥቂት ድምጾች ግን ከሌሎች ድምጾች የበለጠ ድምጽ እንዳላቸው አድርጎ ይቆጥራል! አንድ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ድምጽ የሌሎችን የሺዎችን ያህል ድምጽ እንዳለው አድርጎ ይቆጥራል፡፡
እንግዲህ ይኸ ነው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ነጻ፣ ፍትሀዊ እና በህዝብ ዘንድ ታማዕኒነት ያለው እየተባለ ህዝብ ግብር እየከፈለ በሚያስተዳድረው የህዝብ መገናኛ ብዙሀን ሌት ቀን እንደበቀቀን እየደጋገመ በመለፍለፍ እና የዘረፋ ምርጫ በማካሄድ በሸፍጥ ለማሸነፍ አበርትቶ እየሰራ ያለው፡፡
ወሮበሎች አሁንም ኢትዮጵያን መግዛት ይቀጥላሉ!
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እ.ኤ.አ ከ1991 ጀምሮ ኢትዮጵያን በመግዛት ላይ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የዘረፋ ምርጫውን በድል አድራጊነት አሸንፈናል በማለት በየመንገዶች ጭፈራ እና ዳንሳቸውን በማቅለጥ ላይ ይገኛሉ፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በአሁኑ ጊዜ በየደረሱበት በመደሰት እና በመጮህ ላይ ይገኛሉ!
ህም! ይህ ድርጊት ጆርጅ ዋላስን አስታወሰኝ፡፡ እ.ኤ.አ በ1960ዎቹ አካባቢ የአልባማ የለየለት ዘረኛ ገዥ ነበር፡፡ እንዲህ የሚለውን ሰይጣናዊ አባባል ያወጀውም እርሱ እራሱ ነበር፣ “አሁኑኑ መከፋፈል! ነገም መከፋፈል! ለዘላለምም መከፋፈል!“ በእርግጥም ለዚህ ሰይጣናዊ አባባል ትኩረት በመስጠት የምናስብ ከሆነ የተጋነነ እና ለማሳመን የማያስችል አይደለም፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ክልላዊ አስተሳሰብ የአፓርታይድ ባንቱስታንስ ከመሆን የዘለለ ሌላ ምንም ነገር ሊሆን አይችልም፡፡ በሁለቱ መካከል ያለው ብቸኛው ልዩነት በአፓርታይድ በኩል ስለዘር መከፋፈል ጉዳይ ላይ ብቻ ያተኮረ ከመሆኑ ላይ ነው፡፡ በክልላዊ አስተሳሰብ ደግሞ ስለጎሳ ክፍፍል የሚያጠነጥን ከመሆኑ ላይ ነው፡፡ አፓርታይድ ያገለገለው የደቡብ አፍሪካን ህዝብ በዘር በመከፋፈል ጥቂት የነጭ የበላይ መንግስት በማቋቋም ዘረኝነትን ማራመድ ነበር፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ክልላዊነትን የሚጠቀመው ኢትዮጵያ የምትባለውን ሀገር በዘር እና በቋንቋ ከፍሎ እና ከፋፍሎ ለመግዛት ነው፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ጎሳን ጥላሸት የመቀባት እና በሰፊው የዘር ማጥፋት እኩይ ምግባሮችን በተለይም በአማራ እና በጋምቤላ ህዝቦች ላይ ተግባራዊ አድርጎታል፡፡
የቀድሞው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የመከላከያ ሚኒስትር የነበረው መለስ ዜናዊ ከጥቂት ዓመታት በፊት እንዲህ ብሎ ነበር፣ “የቃሊቲ እስር ቤት ኦሮምኛ ይናገራል፣ እናም በቃሊቲ የማጎሪያ እስር ቤት ግቢ ውስጥ የሚገኙት በመቶዎች ከሚቆጠሩት እስረኞች መካከል 90 በመቶ የሚሆኑት ኦሮሞዎች ናቸው፡፡ አብዛኞቹ እስረኞች በምን ምክንያት እንደታሰሩ የሚያውቁት ነገር የለም፣ ሆኖም ግን የኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባር ተጠርጣሪዎች ናቸው በማለት በእስር ቤት በመማቀቅ በርካታ ዓመታትን አስቆጥረዋል፡፡“ ከዚህም በላይ ደግሞ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በእስር ቤትም ሳይቀር የመከፋፈል እኩይ እና ሰይጣናዊ ምግባሩን በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡
እውነት ለመናገር የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ክልላዊ አስተሳሰብ በጥንታዊቷ ደቡብ አሜሪካ ጥቁሮችን ከማግለል ልምድ ጋር እኩል የሆነ የህይወት ተሞክሮ ነው፡፡ ሕግን መሰረት በማድረግ ሁሉንም ነገር በዘር ከፋፍለውት ነበር፡፡ ሌላው ቀርቶ የውኃ መጠጫ ምንጮችን ሳይቀር በዘር ከፋፈሏቸው፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ኢትዮጵያውያንን/ትን በጎሳ እና በቋንቋ ከፋፈለ፡፡ ይኸ በወያኔ አመለካከት የማይሻር ህግ ነው፡፡ ይህንንም ህግ “የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች” በማለት ይጠሩታል፡፡ ይህም ህዝቡን እንዳይገናኝ፣ እንዲደናገር እና ከብሄራዊ ማንነት ውጭ ሆኖ እንደ ከብት መንጋ አድርጎ በመፈረጅ ለመከፋፈል የሚጠቀሙበት ሁነኛ የሸፍጥ መሳሪያቸው ነው፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ክልላዊነት የሚለውን የመከፋፈያ መሳሪያ በመጠቀም የይስሙላ ምርጫዎችን በማካሄድ ለዘላለም በስልጣን ወንበር ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው ለመኖር ነው ዕቅዳቸው፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ክልላዊነትን ለማደስ በሚል ስሌት በየአምስት ዓመቱ የይስሙላ ምርጫቸውን ያካሂዳሉ፡፡ ከክልላዊነት ውጭ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ህልውና የለም፡፡ ከወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ውጭ ክልላዊነት ሊኖር አይችልም፡፡ ሁለቱም በገለፈጭ ውስጥ ያሉ አተሮች ናቸው፡፡ ይህ ሁኔታ እንደ ገዳዩ እና ተስፋፊው ካንሰር በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሰውነት ላይ በመዛመት የሚገኝ ነው፡፡
ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የይስሙላው ምርጫ በስልጣናቸው ላይ ለአንድም ቀን ቢሆን፣ ለአንድ ተጨማሪ ሳምንት፣ ለአንድ ተጨማሪ ወር እና ለአንድ ተጨማሪ ዓመት በስልጣን ወንበራቸው ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው ለመቆየት እና ጊዜ ለመሸመት የሚጠቀሙበት ተስማሚ እኩይ መሳሪያቸው ነው፡፡
ወፍራም በሆኑ ለጋሽ እና አበዳሪ ድመቶች ድጋፍ አማካይነት የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የምርጫ ማጭበርበር እና የቁማር ጨዋታ እንዲጫወት ያደርጋሉ፡፡
ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ምርጫዎች ብዙሀኑን ህዝብ አጭበርብሮ ለማሸነፍ ዋነኛ መሳሪያው ናቸው፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ምርጫዎች የፖለቲካ ውድመትን ለማምጣት ዋነኛ መሳሪያዎች ናቸው፡፡ ነጻውን ፕሬስ ለመግደል፣ ተቃዋሚዎችን፣ ሰላማዊ አመጸኞችን፣ የሲቪል ማህበረሰቡን እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን ለማፈን ምርጫዎችን ይጠቀማሉ፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ምርጫ ህዝቡን ለማታለል እና ለማደናገር ሲባል በመድረክ ላይ የሚተወን የቅጥፈት እና የይስሙላ ምርጫ ነው፡፡ አበዳሪ እና ለጋሽ ድርጅቶች ተባባሪ እጆች ናቸው፡፡ ከመጋረጃ ጀርባ ሆነው ሁሉንም ገመድ እና ሽብልቅ የሚስቡ ናቸው፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ምርጫዎች የፋሲካ ዕለት ጠዋት በምዕናብ የምትታይ ጥንቸል በቅርጫት ውስጥ እንቁላሎችን በማስቀመጥ በቀለም የተዥጎረጎረውን እንቁላል በመደበቅ ፈልጉ ከምትለው እና ከገና አባት ጋር አንድ እና መሳ ለመሳ ናቸው፣
በአሁኑ ጊዜ በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የምርጫ ድል ላይ እምነት የሚያድርበት ሰው የፋሲካ ዕለት ጠዋት በቅርጫት ካሉ እንቁላሎች መካከል አንዱን እና በቀለም የተዥጎረጎረውን እንቁላል ፈልጉ በምትለው ጥንቸል እና በገና ዋዜማ የገና ስጦታ በሚሰጠው እና በሰማይ ላይ ክንፍ አውጥቶ በሚበረው የገና አባት ላይ እንደማመን ያህል ነው፡፡
በአሁኑ ጊዜ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ነጻ እና ፍትሀዊ በሆነ መልኩ ምርጫውን አሸንፏል በማለት የሚያምን ምክንያታዊ ሰው ሊኖር ይችላልን? የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን የደናቁርት ስብስብ የዝርፊያ ምርጫው ድል ትክክል ነው ብሎ የሚያምን ሰው ሊኖር ይችላልን? እኔ እርግጠኛ ነኝ ከወያኔ ቱልቱላ በስተቀር ሌላ ህሊና ያለው ሰው እምነት ይኖረዋል ብዬ አልገምትም፡፡
በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ህዝብ ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ወያኔ እንደገና ሌላ ዙር አምስት ዓመታት እንዲገዛው ድምጹን ይሰጣል ብሎ ማሰብ የበግ ጠቦቶች ለሚያስካኩ ጅቦች ወይም ደግሞ ለተክለፈለፉ ተኩላዎች ከአደጋ ሁሉ ጠብቁን ብለው ሀሳባቸውን እንደመጣል ያህል ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ምርጫ ከቤት ውጭ ተዘጋጅቶ ለተራበ ህዝብ እንደሚቀርብ ምግብ ነው፡፡ በግብዣው ላይ በሚደርሱበት ጊዜ በውሀ የተሞሉ የምግብ ሳህኖችን ፎቶ ነው የሚያዩት፡፡ ፎቶዎችን ብቻ እንዲመለከቱ፣ የፈለጉትን ሁሉ እንዲያዩ እና ምራቃቸውን እንዲያንጠባጥቡ ብቻ ነው የሚፈቀድላቸው፣ ሆኖም ግን በጥሩ መዓዛ የሚያውደውን ምግብ መቅመስ በፍጹም አይችሉም፡፡
በአሁኑ ወቅት እ.ኤ.አ ግንቦት 24/2015 የኢትዮጵያ ህዝቦች ዲሞክራሲን ተርበው ለመምረጥ ወደ ምርጭ ጣቢያዎች ይሄዳሉ፡፡ ሆኖም ግን በድምጽ ኮረጆው ውስጥ ሁሉም ያገኙት ሊታኘክ የማይችል ጅማት ነው፡፡ በባዶ ሆዳቸው ወደቤታቸው ተመልሰዋል፡፡
ታላቁ የሙዚቃ አቀንቃኝ ቦብ ማርሌይ በባዶ ሆዳቸው ወደ ቤቶቻቸው ስለተመሰሉት ወንዶች እና ሴቶች እንዲህ የሚል ትምህርት አስተምሮናል፣ “የእነርሱ ሆዳቸው ሞልቷል እኛ ግን ተርበናል፡፡ የተራበ አመጽ የተቆጣ አመጽ ነው…የኑሮ ውድነት ሰማይ ጠቀስ ሆኗል፣ ሀብታም እና ደኃ በአንድነት ማልቀስ ይጀምራሉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ደካማው ኃይለኛ ይሆናል…/ በአሁኑ ጊዜ ደካማው ኃይለኛ ይሆናል፡፡“
መራብን በማስመልከት አሁን በህይወት የሌለው መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት የእርሱ መንግስት ስኬት የሚለካው የእርሱ አገዛዝ ማንም ኢትዮጵያዊ በቀን ሶስት ጊዜ መመገብ ከቻለ እንደሆነ በድፍረት እና በአደባባይ በህዝብ መገናኛ ዘዴዎች ተናግሮ ነበር፡፡ ሆኖም ግን በአሁኑ ግዜ በቀን ሶስት ጊዜ መመገብ የሚችሉት የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አባላት እና ደጋፊዎቻቸው ብቻ ናቸው፡፡ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ባዶ ሆዱን ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ትልቁ የወያኔ መፈክር ከሁሉም የአፍሪካ ሀገሮች ታላቅ የሆነውን የገደበውን ግድብ መገደብ ነው፡፡
ህዝብ በረሀብ አለንጋ እየተጠበሰ ሲሆን የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ግን ግድቦችን አየገደበ ነው፡፡ ቅጣንባሩ የጠፋበት ጊዜ ነው!
በአሁኑ ወቅት እ.ኤ.አ ግንቦት 24/2015 በጣም የተበሳጩሁበት ዕለት ነው ምክንያቱም ድምጾቻቸው በጠራራ ጸሐይ በአደባባይ ተዘርፈዋል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ለዴሞክራሲ እንደተራቡ ናቸው፡፡ በአሁኑ ጊዜ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የተቆጡ እና የተራቡ ኢትዮጵያውያን/ት በመቆጣት ጊዜያቸውን በማሳለፍ ላይ ይገኛሉ፡፡
ስለሆነም ለእነርሱ ከዚህ በኋላ የምናለቅሰው ነገር የለም፡፡ ለውዲቷ ሀገራችን ከእንግዲህ ወዲያ አናለቅስም፡፡ ኢትዮጵያውያን/ት በመከፋፈላቸው ምክንያት ተዳክመዋል፡፡ እናም ትርምሱ ወደ አንድነት መምጣት አለበት፡ ስለሆነም በየዕለቱ ጠንካራ እና ጠንካራ መሆን አለብን ምክንያቱም የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በየዕለቱ ደካማ እና ደካማ እየሆነ በመሄድ ላይ ነው፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብሰብ ድል አድራጊነቱን እንዴት እንደሚመለከተው፣
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የኢትዮጵያ ህዝብ ከወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እና አባላት እንዲሁም ደጋፊዎች በስተቀር ሁሉም ቢሆን ደንቆሮ እና የማይናገር ቦቅቧቃ ፈሪ እንደሆነ አድርገው ያምናሉ፡፡ ይህ ትክክለኛ ሀቅ ነገር ነው፡፡ የእነርሱ ሰዎች ናቸው ይህንን የነገሩኝ፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ዋና ፍልስፍናው እንዲህ የሚል ሆኖ ይገኛል፣ “ከእኛ ጋር ያልሆኑ ሁሉ የእኛ ጠላቶች ናቸው፡፡“ እንዲህ ለሚለው መልካም አባባል ክብር የላቸውም፣ “ከእኛ በተጻራሪው ያልቆሙት ሁሉ ከእኛ ጋር ናቸው፡፡“
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የገደል ማሚቶ ድምጻቸው እንዲህ የሚለውን እምነቶቻቸውን እና ፍልስፍናቸውን ይተገብራሉ፣ “ህዝቡ ይወደናል፡፡ እኛን ያደንቃል፡፡ እኛን ብቻ እንጅ ሌላ ማንንም አይፈልግም፡፡“
እ.ኤ.አ በ2010 አሁን በህይወት የሌለው እና የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ትንሹ አምላክ ተደርጎ የሚወሰደው መለስ ዜናዊ በዚያን ወቅት ተካሂዶ በነበረው ሀገር አቀፍ የይስሙላ ምርጫ 99.6 በመቶ በማምጣት የፓርላማውን ወንበር ሙሉ በሙሉ በተቆጣጠሩበት ጊዜ ባደረገው የመመጻደቅ ንግግር ህዝቡ ምን ያህል እንደሚወዳቸው እና እንደሚደግፋቸው እንዲሁም የእርሱ ጋሻጃግሬዎች ደስተኞች እንደሆኑ እንዲህ በማለት ተናግሮ ነበር፡
የመጀመሪያዎቹ ውጤቶች እንደሚያመላክቱት አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ በነጻነት እና በሰላም ሀገሪቱን በቀጣዮቹ ዓመታት ማን መምራት እንዳለበት ህዝባችን በሚገባ ተገንዝቦ ከስምምነት ላይ ደርሷል…ከከፍተኛ ማክበር ጋር ለመረጠን ህዝብ እና ድጋፋቸውን ለሰጡን እና በነጻ እና በዴሞክራሲያዊ መንገድ ለመረጡን ደጋፊዎቻችን ሁሉ ያለንን ምስጋና እና አድናቆት ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡
ከዚህም በተጨማሪ የድርጅታችን የጀርባ አጥንት ለሆኑት ለኢትዮጵያ ሴቶች… እና ለኢትዮጵያ ወጣቶች ለማይታጠፈው ድጋፋቸው እና አድናቆት ከልብ ላመሰግናቸው እወዳለሁ! እንደዚሁም ደግሞ የከተማችን ኗሪ ለሆኑት ለበርካታዎቹ ዜጎች እና እራሳቸው ከወያኔ አንድ ዓይነት ንግድ ከሚሰራው ከኢህአዴግ ጋር የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች የሆኑትን የሀገራችንን አርሶ አደሮች ከልብ አመሰግናለሁ…
እ.ኤ.አ በ2015 ለሚካሄደው ምርጫ መለስ እያንዳንዷን የመጨረሻ ድምጽ ለራሱ ገዥ ፓርቲ ድምጽ ያልሰጡትን ሰዎች ድምጽ ለመውሰድ እንዲህ የሚል ከፍተኛ የሆነ ፍላጎት ነበረው፡
ለእኛ ድምጻቸውን ያልሰጡን ዜጎች እንዳሉ እናውቃለን፡፡ ድምጻቸውን ለእኛ ያልሰጡንን ዜጎች ውሳኔ በጽኑ አከብራለሁ…ለእኛ ድምጽ ያልሰጣችሁንን እኛን ያልመረጣችሁበትን ምክንያት ከእናንተ ትምህርት በመውሰድ እና በእኛ በኩል ያሉብንን ድክመቶች በቀጣይነት በማስተካከል ንቁ ሆነን ለመቅረብ እንደምንችል ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ፡፡ በቀጣዩ ምርጫ የእናንተን ድጋፍ ለማግኘት ሌት እና ቀን እንሰራለን፡፡
ትልቅ ብዙሀን እና ሰፊ ብዙሀን 99.6 በመቶ ድምጽ በመዝረፍ ሁሉንም መቀመጫዎች ጠቅልሎ መውሰድ እንደሆነ ጥቂቶች ያውቃሉ፡፡ በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የገደል ማሚቶ ጩኸት 99.6 በመቶ ድምጽ በመዝረፍ ድልን መቀዳጀት ትርጉም ይሰጣል ምክንያቱም ህዝቡ እነርሱን ይወዳቸዋልና ነው፡፡ ሙአማር ጋዳፊ እንደዚሁ እንዲህ በማለት ተመሳሳይ ነገር ነበር የተናገረው፡፡ “ይወዱኛል፣ ሁሉም ህዝቦች ከእኔ ጋር ናቸው፣ እናም ይወዱኛል፡፡ ለእኔ ለመከላከል ሲሉ ይሞቱልኛል፣ የእኔ ህዝቦች፡፡“ ከጥቂት ቀናት በኋላ እርሱን እንዴት እንደሚወዱት በሚገባ አሳይተውታል፡፡ መልካም እይታ አልነበረም፡፡
በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ 99.6 በመቶ ድምጽ በማግኘት ድል ተቀዳጀሁ ሲል እንዴት በህዝብ ዘንድ እታመናለሁ ብሎ ይገምታል? ለዚህ ጥያቄ ሁለት መልሶች ብቻ አሏቸው፡፡ እነርሱም፡
1ኛ) የኢትዮጵያ ህዝቦች በእርሱ አስተሳሰብ ምንም የማያውቁ ድንጋዮች ናቸው ብሎ ስለሚያስብ ነው፡፡
2ኛ) የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ 99.6 በመቶ ድምጽ አግኝቻለሁ በማለት የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያምንለት ማሰቡ እርሱ እራሱ ከድንጋይ ያልተሻለ ፈጣጣ መሆኑን የሚያመላክት ነው፡፡
በነገራችን ላይ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አዲሱ ጠባቂ፣ ዘበኛ እና ሻምፒዮን የሆኑት ኢቨሊን ሸርማን ኢትዮጵውያን ከወያኔ የበለጠ ደደቦች ናቸው የሚል ሀሳብ አራምደዋል፡፡ ኢትዮጵያ አዲስ ዴሞክራሲያዊ ሀገር በመሆን ነጻ፣ ፍትሀዊ እና ታማዕኒነት ያለው ምርጫ አካሂዳለሁ የሚል ቡድን እንዴት ደደብ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለድድብና እና ደደብነት መነጋገር ለኢቨሊን ሸርማን እና ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ደጋፊዎች የኢትዮጵያ ህዝብ እነርሱ እንደሚሉት ደደብ ያለመሆኑን ሊገነዘቡ ይገባል፡፡
ሸርማን እንዴት እንደሚያስቡ ወይም እንደማያስቡ አስቂኝ ነገር ነው፡፡ እንዲህ ይላሉ፣ “ኢትዮጵያ አዲስ የዴሞክራሲ ስርዓት የምታካሂድ ሀገር ናት፡፡“ አዲስ ዴሞክራሲ በአሮጌ እና በበሰበሰ አምባገነን የሚመራ? የጅብ መንጋዎች የበግ ጠቦቶችን ሊጠብቁ ይችላሉን? ከእባብ እንቁላል እርግብ ሊፈለፍል ይችላልን? አሮጌውን ወይን በአዲስ ጠርሙስ በመገልበጥ አዲስ ወይን ማድረግ ይቻላልን? ጥቂት ሰዎች እንዴት እንደሚያስቡ ወይም እንደማያስቡ እኔ ልገነዘብ አልችልም፡፡
በእርግጥ ሸርማን የአሜሪካ ከፍተኛ የፖሊሲ አውጭ ሆና እኛን ለመስደብ እና ክብራችንን ለማዋረድ ሲደፈወሩ እርሳቸው የመጀመሪያዋ እና ብቸኛዋ ሴት አይደሉም፡፡
የኦባማ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ የሆኑት ሱሳን ራይስ እ.ኤ.አ በ2012 በመለስ የቀብር ስነስርዓት ለመገኘት መጥተው በነበረበት ጊዜ ተመሳሳይ ዘለፋ አካሂደዋል፡፡ እንዲህ ብለው ነበር፣ “በእርግጥ መለስ ለሞኞች ወይም ደግሞ ለደደቦች ምንም ዓይነት ትዕግስት ያልነበረው ሰው ነበር፡፡“ መለስ ስለሞኞች እና ደደቦች ስለነበረው አመለካከት መናገር በመቻላቸው ኩራት ተሰምቷቸዋል፡፡ እነርሱ እነማን እንደሆኑ ሴትዮዋ ምንም አልተናገሩም፡፡ እነርሱ እነማን እንደሆኑ ለማወቅ አስቸጋሪ ነገር አይደለም፡፡ መለስ በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የቀድሞ አመራሮች ላይ ንቀትን ያሳይ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብንም ይንቅ ነበር፡፡
መለስ በአንድ ወቅት የእርሱ የወያኔ ድል ከአርብቶ አደሩ ውጭ በሁሉም ቦታ የተረጋገጠ ነው በማለት ተመጻድቆ ነበር፡፡ “በገጠሪቱ ኢትዮጵያ እኔ የማውቀው ለእኛ ድምጹን ያልሰጠ አንድም መንደር የለም፡፡ በአርብቶ አደሩ አካባቢ ካልሆነ በስተቀር፡፡ በእነዚህ አካባቢዎች እድል የለንም፡፡ እንደዚሁም ደግሞ እዚያ ሄደን ምርጫዎችን አንቃወምም፡፡ በዚያ አካባቢ ያለ ህዝብ ፍጹም ደንቆሮ እና ምንም ዓይነት ፍላጎት የማያሳይ ነው፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ደንቆሮዎች ናቸው ሁሉም ነገር በእኛ ብቻ ነው የሚፈጸመው…“
እንግዲህ አስቲ አስቡ! ከፍተኛው የቄስ ደናቁርት አርብቶ አደሮችን እና የተቃዋሚ ቡድኖችን ደንቆሮ ይላቸዋል፡፡ እሺ ድንቁርና ደንቆሮ እንደሚመራው ነው፡፡ መዝሙሮቹ ያስተማረው ትምህርት ቀላል እና ግልጽ ነው፡ ትምህርቱም እንዲህ የሚል ሆኖ ይገኛል፣ “እ.ኤ.አ በ2010 በተደረገው ሀገር አቀፍ ምርጫ እኛን ያልመረጡንን ሰዎች ድጋፍ ለማግኘት ሌት እና ቀን መስራት አለባችሁ፡፡“
መለስ ስለምንም ነገር አይጨነቅም ነበር፡፡ እ.ኤ.አ ግንቦት 2015 የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ማድረግ ያለበት ቀላል ነገር ቢኖር ምርጫውን አጭበርብሮ 100 በመቶ ድል በማድረግ አሸነፍኩ ማለት ነው፡፡
እ.ኤ.አ በ2010 የአንድ ፐርሰንት 4 አስረኛ (4/10) ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ድምጽ አልሰጡም ነበር፡፡ እነርሱ ሰላማዊውን ህዝብ ያባርሩ ነበር፣ በህዝቡ ላይ ችግር እና ሁከት ይፈጥሩ ነበር፣ የህዝቡን እጅ ጠፍንገው ይይዙ ነበር፣ ከዚያም የህዝብን ድምጽ በመስረቅ እና በመዝረፍ 99.6 በመቶ በማምጣት አሸነፍን አሉ፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እ.ኤ.አ በ2015 በሚካሄደው ሀገር አቀፍ የይስሙላ ምርጫ የአንድ ፐርሰንት 4 አስረኛዋን በማሟላት ምርጫውን አሸነፍኩ ለማለት ምን ዓይነት አስቸጋሪ ነገር ሊሆንበት ይችላል? ከህጻን ላይ ከረሜላ ነጥቆ የመውሰድ ያህል ከባድ ነገር ሊሆን ይችላልን?
ድህረ ምርጫ ትንተና
ላለፉት በርካታ ዓመታት (በእርግጥም ላለፉት 5 ዓመታት) የ2015 የኢትዮጵያ ምርጫ አሳፋሪ ይሆናል የሚል ትንበያ ሰጥቸ ነበር፡፡ ምርጫው በዴሞክራሲ ላይ የሚደረግ ደባ እንዲሁም በዴሞክራሲያዊ ምርጫዎች ላይ የሚደረግ ተራ ማጭበርበር እና ሸፍጥ ነው፡፡ ስለዚህ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ዳንስ እና አሻሻ ገዳሜ ስለምንድን ጉዳይ ነው?
እውነታ ቁጥር 1፡ እ.ኤ.አ ግንቦት 24/2015 የሚካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫ ስለዴሞክራሲ ወይም ስለመልካም አስተዳደር ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈይደው ነገር የለም፡፡
ስለኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ እና ፍላጎቱ ያላቸው ኢትዮጵያውያን እና ሌሎች እ.ኤ.አ ግንቦት 24/2015 ይካሄዳል የተባለው የይስሙላ ምርጫ ስለመልካም አስተዳደር ወይም ደግሞ ስለደህንነት ጉዳይ ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈይደው አንዳችም ነገር እንደሌለ ግንዛቤ ሊወስዱ ይገባል፡፡ ምርጫው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን እና እርሱን በገንዘብ የሚያንበሸብሹትን ማለትም የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካንን፣ የአውሮፓ ህብረትን፣ የዓለም ባንክን እና የዓለም አቀፉን የገንዘብ ድርጅት ፍላጎት እና ጥያቄ ከማሟላት ባለፈ ለኢትዮጵያ ህዝብ አንዳችም የሚፈይደው ነገር የለም፡፡
እ.ኤ.አ በ2015 የሚካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫ በኃይለኛዎቹ ለጋሽ እና አበዳሪ ድርጅቶች ትዕዛዝ መሰረት እንዲካሄድ የተወሰነ ነው! ማንም ቢሆን ይህንን እውነታ ማወቅ እና መቀበል ይኖርበታል፡፡ ለጋሽ እና አበዳሪ ድርጅቶች ከብዙ ጊዜ በፊት የምርጫ ህጉን ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ጽፈው ለወሮበላው ድርጅት ቀያሽ መሀንዲስ ለነበረው እና አሁን በህይወት ለሌለው ለመለስ አስረክበውት ነበር፡፡ በዓለም አቀፍ ለጋሽ እና አበዳሪ ድርጅቶች የምክር አገልግሎት እና ስምምነት አማካይነት የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሀገሪቱ ባልተረጋጋ እና መደናገርን ባካተተ መልኩ አንድም ጥያቄ በአግባቡ መመለስ የማትችል ተራ እና ቀላል ሀገር እንድትሆን የሚያስችላትን ስርዓት እንዲተከል አድርገዋል፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን የድንቁርና አካሄድ ካዩ በኋላ ስለምርጫው ጨዋታ ሙሉ በሙሉ በመርሳት ወያኔው ያለምንም ተጠያቂነት በምርጫ ዝርፊያ እና ኃይልን በመጠቀም ከስልጣን ማማ ላይ እንደገና ጉብ በማለት የስልጣን ጊዚያቸውን ያድሳሉ፡፡
ግን ለምንድን ነው ለጋሽ እና አበዳሪ ድርጅቶች ምርጫ እንዲካሄድ ትዕዛዝ የሚሰጡት? ይህንን የሚያደርጉበት በርካታ ምክንያቶች አሏቸው፡፡
1ኛ) በዘፈቀደ የእራሱን ዜጎች በእስር ቤት እያጎረ ለሚያማቅቅ፣ የእራሱን ዜጎች ለሚያሰቃይ እና ለሚገድል ወሮበላ አገዛዝ በሚያደርጉት እርዳታ መሰረት ኃላፊነት ላለመውሰድ እና የሞራል ስብዕና ተጠያቂ ላለመሆን የነገሩን አሳሳቢነት አደብዝዞ የእራሳቸውን ጥቅም እና ፍላጎት እያሟሉ የመቀጠል ዓላማ ስላላቸው ነው፡፡ የኦባማ አስተዳደር ያለምርጫ የይስሙላ ቸበርቻቻ ሂደት ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እርዳታ ለመስጠት አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ይወድቃሉ፡፡ ባለፈው ወር የዩኤስ አሜሪካ መንግስት ረዳት ጸሐፊ የሆኑት ኢቨሊን ሸርማን በአዲስ አበባ በመገኘት የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የይስሙላውን ምርጫ እንዴት ማካሄድ እንዳለበት የመጨረሻውን ትዕዛዝ የሰጡ ይመስላል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ መልዕክቱን በሚገባ አግኝቷል፡፡ ለዚህም ነው ሸርማን እንዲህ በማለት ያወጁት፣ “ኢትዮጵያ በዴሞክራሲ እየተራመደች ያለች ሀገር እና ወደፊት የሚካሄደው ምርጫ ነጻ፣ ፍትሀዊ፣ በህዝብ ዘንድ ታማዕኒነት ያለው፣ ግልጽ እና የዴሞክራሲ ስርዓት ሂደቱ እያጠናከረ በየጊዜው ምርጫ መደረግ እንደሚኖርበት እንጠብቃለን፡፡ ሀገሪቱ በየጊዜው እየተሻሻለች የመጣችበት ሁኔታ ነው የሚታው፡፡“ ድንቄም መሻሻል! ከድጡ ወደማጡ እየተወረወረች ባለች ሀገር እንዴት ነው ስለመሻሻል አፍን ሞልቶ መናገር የሚቻለው?
2ኛ) ለጋሽ እና አበዳሪ ድርጅቶች በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እያደሉ ገንዘቡ ሲገባ እንጅ በህዝቡ ስም የመጣው ገንዘብ ለምን ለምን ጉዳይ እንደዋለ በማይታወቅበት ሁኔታ በየተወሰነ ጊዜ የይስሙላ ምርጫ መካሄዱ ለእነርሱ ከሞራል ስብዕና ተጠያቂነት ሊያድነን ይችላል የሚል ከንቱ አመለካከት ስላላቸው ነው፡፡ በእርግጥ ለጋሽ እና አበዳሪ ድርጅቶች በልካቸው መለያ ልብስ የተሰፋላቸውን አምባገነን ዘራፊዎች እየደገፉ መሆናቸውን ሊያውቁት ይገባል፡፡ ዌንዲ ሸርማን ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ከልክ ያለፈ ሙገሳ በማድረጋቸው ምክንያት አንዳንድ የወያኔ አመራሮች ሴትዮዋ ከተሳፈሩበት መርከብ ውጭ ሆነው ውኃውን ለመቅዘፍ ይሞክራሉ በማለት የሽሙጥ ንግግር አድርገዋል፡፡ ዋሽንግተን ፖስት በሁኔታው ቅር በመሰኘት እንዲህ የሚል ዘገባ አስነብቦ ነበር፡ “ምርጫው በነጻ የምርጫ ታዛቢዎች አማካይነት የማይካሄድ ከሆነ እና ማዳም ሸርማን እንዳሉት የማይፈጸም ከሆነ የኦባማ አስተዳደር የሴትዮዋን ቃል መጠበቅ ይኖርበታል – እናም በአካሄዱ ላይ ለውጥ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡“
3ኛ) በየጊዜው የሚደረግ የይስሙላ ምርጫ በዓለም አቀፍ ለጋሽ እና አበዳሪ ድርጅቶች ላይ በሰብአዊ መብት ተሟጋቾች የሚሰጠውን ትችት በማደብዘዝ የመደበቂያ ጋሻ ሆኖ እንዲያገለግላቸው ያደርጋል፡፡ እ.ኤ.አ ሚያዝያ 17/2015 ማዳም ሸርማን “ኢትዮጵያ በዴሞክራሲ ጉዞ ላይ ነች” የሚለውን መግለጫ ከአፋቸው ካወጡ ጥቂት ቀናት በኋላ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ዩኤስኤ/Amnesty International USA፣ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ፕሮጀክት/Ethiopia Human Rights Project፣ የፍሪደም ሀውስ/Freedom House፣ የፍሪደም ናው/Freedom Now፣ ሂዩማን ራይትስ ዎች/Human Rights Watch እና የዓለም አቀፍ ወንዞች/International Rivers የተባሉት ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ለጆን ኬሪ ደብዳቤ በመጻፍ ማዳም ሸርማን የእነዚህን ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ቁጣ ለመጋፈጥ ተገድደዋል፡፡ እነዚህ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችም እንደዚህ የሚል ተማጽዕኖ አቅርበዋል፣ “የአፍሪካ ህብረት ያወጣውን የዴሞክራሲያዊ ምርጫ ዓለም አቀፍ መስፈርት ላለማሟላት በሚል እኩይ አስተሳሰብ የኢትዮጵያ መንግስት ስለሚፈጽማቸው ስልታዊ የምርጫ ግድፈቶች የዩናይትድ ስቴትስ የመንግስት መምሪያ ቀደም ብሎ መግለጫ ማውጣት ይኖርበታል፡፡“ ሆኖም ግን የሚያስደንቀው ነገር ኬሪም ሆኑ ሸርማን አንድም ቃል ትንፍሽ ሳይሉ እንደዋዛ አልፈውታል፡፡
እውነታ ቁጥር 2፡ ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ምርጫ የህዝብ ጨዋታ በዓል ማለት ነው፣
የይስሙላ የምርጫ በዓል በማዘጋጀት የኢትዮጵያን ህዝብ ከበርካታ ዓመታት ጀምሮ ወደ ኋላ መጎተት አስፈላጊ ነገር ነውን?
እውነታው ፍርጥርጥ ብሎ ሲታይ ግን እ.ኤ.አ ግንቦት 24/2015 የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የሰርከስ ቡድን ትዕይንት እና ተውኔት የሚታይበት ነው፡፡ በዚያን ዕለት የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አስቂኝ ቀልዶች፣ የጅምናስቲክ ባለሙያዎች፣ የገመድ ላይ ጉዞ አድራጊዎች፣ ዘላዮች፣ የሰለጠኑ እንስሶች፣ የተለያዩ የዝላይ ድርጊቶች እና የድሁር አለቆች የሰርከስ ትዕይንቶች ሁሉ በሙሉ አቅም እየተተወኑ የሚታዩበት ዕለት ነው፡፡ የሰርከስ ትርኢት አስተዋዋቂው ከህዝብ ስብስቡ መንጠቅ ብሎ ይወጣ እና “ኢትዮጵያ በእንዴት ያለ የተሻሻለ የዴሞክራሲ መንገድ ላይ እየተጓዘች” እንደሆነ እንዲሁም የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በዚህ ከባድ በሆነ የምርጫ ውድድር ላይ እንዴት አድርጎ በአሸናፊነት እንደሚወጣ በማስተዋወቅ ቡራኬ ይሰጣል፡፡ የምርጫውን ውጤት በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ የሚያደርገውን ወይም ደግሞ ተቃውሞ የሚያሰማውን ለማስፈራራት እና ለማፈን እሳት አጥፊዎች ከስብስቡ መንጋ ተንጋግተው ይወጣሉ፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ዘላዮች ምርጫው እንዴት ያለ ሰላማዊ፣ ነጻ፣ ፍትሀዊ እና በህዝብ ዘንድ ታማዕኒነት ያለው እንደነበር በመስበክ ዝላያቸውን ይቀጥላሉ፡፡ ቅርጽ አጣማሚዎቹ እውነታውን ማጣመሙን ይቀጥላሉ፡፡ በእርግጥ ዋናው ትልቁ ቀልደኛ (ወይም ደግሞ በእራሱ የማይተማመነው አሻንጉሊቱ) በመድረኩ ላይ ተጀንኖ ብቅ በማለት እንዲህ በማለት ያውጃል፣ “ወያኔ አሸንፏል፡፡“
ወደ ሰርከስ ማሳያው ቦታ መሄዱ ቀልድ ነው፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ታላቅ የሆነ የሰርከስ ተውኔት ከባቢ አየር በማዘጋጀት ስኬታማ ሆኗል፡፡ እኔ እራሴ በቴሌቪዥን መስኮት ከሚተላለፉት ተውኔቶች መካከል አንዱን ተውኔት የመመልከት አጋጣሚውን አግኝቸ ነበር፡፡ ይህንን ተውኔት የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የምርጫ ክርክር ብሎ ይጠራዋል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ለወባ ትንኝ ተመራማሪው እና በብርሀን ፍጥነት ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ለተተኮሰው ለቴዎድሮስ አድኃኖምን በክርከሩ ላይ ቁርስ፣ ምሳ እና እራት አድርጎት ነበር ፡፡ ስለተዘጋው የፖለቲካ ምህዳር ምንድን ነው የሚባለው? ስለጋዜጠኞች፣ ስለፖለቲካ እና ስለሰብአዊ መብት ጥበቃ ወትዋቾች ምንድን ነው ሊባል የሚችለው? ወደ እስር ቤት ስለተጋዙት ወይም ደግሞ እትብታቸው ከተቀበሩባት ሀገራቸው እንዲወጡ ስለተገደዱት የሲቪል ማህበረሰብ አመራሮች ምን ሊባል ይችላል? መንግስት እና ፓርቲ ገጥመው አንድ ስለመሆናቸውስ ምን ማለት ይቻላል?
ቴዎድሮስ ቀልቡን ሁሉ በሳተ መልኩ ተቀምጦ ነበር፡፡ ምንም እርባና ያለው ንግግር ሲያደርግ አይታይም ነበር፡፡ እንዲህ ሲል ተደምጧል፣ “ተቃዋሚዎች ዕቅድ ይዘው ይመጣሉ ብለን እንጠብቅ ነበር…ወዘተ…ወዘተ…ወዘተ፡፡“ በእርግጥ እንደ እርሱ ያለ ግራ የተጋባ የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዓይነት ይዘው እንዲመጡ ይጠበቅ ነበርን?
አድኃኖም በኩሬ ላይ እንደነበረው አውራ ዶሮ ይቁነጠነጥ ነበር ፡፡ ስለኩሬ ስናነሳ እውነት ለመናገር አድኃኖም ወደ ኩሬ ተመልሶ ወባ ትንኝ ብያሳድድ ይሻለው ነበር። በፖለቲካ ላይ ምንም ዓይነት ቦታ የለውም፡፡ ይቅርታ! ለካ ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ነው አድሃኖም።
እውነታ ቁጥር 3፡ እ.ኤ.አ ግንቦት 24/2015 የሚካሄደው ምርጫ፣ ምርጫ አይደለም፣
ለወንዱ ዳክዬ ጥሩ የሆነው ነገር ሁሉ ለሴቷ ዳክዬም ጥሩ ነው፡፡ ልክ ነውን?
ለኦባማ አስተዳደር ማስታወሻ፡ ምርጫ እውነተኛ ለመሆኑ እና ላለመሆኑ የምርጫ ሂደቱን ማን እንደሚመራው የሚወሰን ቢሆንም ምርጫው ትክክለኛ ሊሆን ይችላል ወይም ደግሞ የምርጫ ሸፍጥ የሚሰራ እና ማጭበርበር እና ዝርፊያ በሚኖርበት ጊዜ ምርጫው ትክክለኛ ምርጫ ላይሆን ይችላል፡፡ ምርጫውን የዘረፈው እና ያጭበረበረው ዘራፊ የአቦማ አስተዳደር ሁነኛ ጓደኛ ካልሆነ ምርጫው የተጭበረበረ ነው ይባላል፡፡ ሆኖም ግን ምርጫውን የዘረፈው እና ያጭበረበረው የኦባማ አስተዳደር ሁነኛ ጓደኛ ከሆነ የተዘረፈው እና የተጭበረበረው ምርጫ የተዘረፈ እና የተጭበረበረ ምርጫ አይደለም፡፡ እንደዚህ ዓይነቱ ምርጫ ዓለም አቀፍ መስፈርቱን ያላሟላ ነው ይባላል፡፡ እንግዲህ እንደዚህ ባለ የምርጫ ስርዓት ነው የኦባማ የአፍሪካ ምርጫ የመድረክ ላይ ትውና እየተተገበረ ያለው፡፡
እ.ኤ.አ ነሀሴ 2013 ሮበርት ሙጋቤ 61 በመቶ በሆነ ውጤት የእርሱ ተቀናቃኝ የሆነውን ዕጩ ፕሬዚዳንት ባሸነፈ ጊዜ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ የሙጋቤን ድል አድራጊነት በማውገዝ እንዲህ የሚል መልዕክት አስተላልፈው ነበር፣ “እንዳትሳሳቱ፡ በሀገር ውስጥ እና በአህጉር አቀፍ ታዛቢዎች በተደረገው ምልክታ መሰረት በርካታ የሆኑ የምርጫ ግድፈቶች ተፈጽመዋል፡፡ በዚህም መሰረት ዩናይትድ ስቴትስ ዛሬ ይፋ የተደረገው የምርጫ ውጤት ታማዕኒነት ያለው እና የዚምባብዌን ህዝብ ፍላጎት ያንጸባረቀ ነው የሚል እምነት የላትም…“
ከሁለት ሳምንታት በፊት ኦማር ሀሰን አልባሽር በሱዳን 94.01 በመቶ የምርጫ ውጤት በማምጣት የእርሱ ፓርቲ የሆነው ብሄራዊ ኮንግረስ ፓርቲ/National Congress Party ከ426 መቀመጫዎች 323ቱን በመያዝ ምርጫውን አሸንፏል ብሎ ሲያውጅ የትሮይካ ፈረሶች (ዩኤስ አሜሪካ፣ እንግሊዝ እና ኖርዌ) ምርጫው የሸፍጥ እና ተቀባይነት የሌለው ነው በማለት አውግዘው ነበር፡፡ እነዚህ የትሮይካ ፈረሶች የሱዳን መንግስት ነጻ፣ ፍትሀዊ እና ምቹ የምርጫ ምህዳር አልፈጠረም በማለት ተቃውሟቸውን አሰምተው ነበር፡፡ በፖለቲካ መብቶች እና ነጻነቶች ላይ እቀባ በመጣል በሱዳን ህገመንግስት ላይ በግልጽ የተደነገገውን መብት በመደፍጠጥ በህዝብ ዘንድ ታማዕኒነት ያለው የምርጫ ክርክር ሳይካሄድ የተደረገ ምርጫ ስለሆነ ይህ የምርጫ ውጤት የሱዳንን ህዝብ ፍላጎት ያላንጸባረቀ ነው በማለት ውድቅ እንዲደረግ ጥረት አድርገው ነበር፡፡
በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ዩኤስ አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ኖርዌ እና ሌሎቹ የምዕራብ ሀገራት ለጋሽ እና አበዳሪ ድርጅቶች በኢትዮጵያ የሚካሄደውን የይስሙላ ምርጫ በመባረክ የኢትዮጵያ ታላቁ ምርጫ በማለት እውቅና መስጠታቸው አይቀርም፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ቢያንስ ከ94.01 በመቶ ባነሰ ድምጽ አሸነፍኩ የሚል ከሆነ በጣም የሚደንቀኝ ይሆናል፡፡ እነዚህ ስብስቦች ከአልባሽር ባነሰ ውጤት ማሸነፍን ሊቀበሉ አይችሉም፡፡ በእርግጠኝነት ለመናገር በ90 በመቶ ወይም ደግሞ ባነሰ ቢያሸንፉ ምን እንደማደርግ የማውቀው ነገር የለም፡፡ ያ ከሆነ እንግዲህ በጣም ትንሹ የማሸነፊያ ጣራ ነው የሚል አድርጌ እወስደዋለሁ፡፡ ያ ከሆነ መለስን ከመቃብር እንዳይገላበጥ የሚያደርገው ነው፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ግልጽ የሆነ የማሸነፊያ ወሰን አስቀምጠዋል፡፡ እኔ እንደምገምተው ከሆነ ከ99.7 በመቶ በታች በሆነ ውጤት እንደማያሸንፉ እና ከዚያ ካነሰም እንደማይዘግቡ እምነት አለኝ፡፡ የማሸነፊያ ነጥቡን ሙሉ በሙሉ እንደሚያደርጉት ጥርጥር የለውም፡፡
ማዳም ኢቨሊን ሸርማን የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን የማመስገን ጩኸታቸውን እና ኢትዮጵያ በዴሞክራሲ ጉዞ እየተጠናከረች መምጣቷን ለመስማት የምችልበት ትዕግስቱ የለኝም፡፡ የእርሳቸውን እጅ እና እግር የሌለውን እንዲህ የሚለውን የተዘበራረቀ ንግግር ማስታወስ እችላለሁ፣ “የኢትዮጵያ በመጎልበት ላይ ያለው ዴሞክራሲ አሸናፊ ነው!“ ምናልባትም በጣም ደስተኛ ናቸው፣ እናም እንዲህ በማለት ይዘምራሉ፣ “አሀሀ እንደምን ነሽ! አሸሸ ገዳሜ!) ኦ! የግንቦቱ ምርጫ ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እንዴት ያለ አስደናቂ ምርጫ ነው!“
ስለይስሙላው ምርጫ ውጤት ከቀጣፊዎቹ ከዩኤስ አሜሪካ አስመሳይ ዲፕሎማቶች ለመስማት መዘጋጀት አለብን (የአሜሪካ እና የምዕራብ ዴፕሎማቶችን እና የድህነት ወትዋቾችን ለመግለጽ የገባ ቃል)
የተጭበርበረ እና ሸፍጥ የታከለበትን ምርጫ ለማክበር የሚያደርጉትን ቸበርቻቻ ዝም ለማየት እንፍቀድላቸው፡፡ ከሁሉም በላይ የተዘጋጀ ገንዘብ ይከፍሉ ነበር፡፡ ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሲያንበሸብሹት የነበሩት በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የሚያስቅ ነገር ነው፡፡ ፍትሀዊ ብቻ ነው፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ፊኛዎች ከፈነዱ እና የተከፈተው ሻምፓኝ ጠርሙሶች ካለቁ በኋላ ምንድን ነው የሚሆነው?
የማርች 25 የንግድ እንቅስቃሴ እንደተለመደው ነው፡፡ ይህም ማለት የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ከማንኛውም ተቃዋሚ ጋር ድርድር አያደርግም ማለት አይደለም፡፡ ሊያምጽ የሚፈልገውን ኃይል ሊመታ የሚችል የተደራጀ የጦር ኃይል አላቸው፡፡ የሚያደርጉት ነገር ቢኖር በሰላማዊ ተቃዋሚ ህዝብ ላይ ጦርነት ማወጅ ነው፡፡ እ.ኤ.አ 2005ን እናስታውስ፡፡የመለስን እልቂት እናስታውስ! በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ከኋይት ሀውስ እና ከብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት በሚከተሉት መስመሮች ላይ የተጻፈ መግለጫ እንደምናነብ እንጠብቅ፡
እ.ኤ.አ ግንቦት 24/2015 በኢትዮጵያ ለተካሄደው የፓርላማ ምርጫ ውጤት እውቅና እንሰጣለን፡፡ የኢትዮጵያ የሲቪክ ማህበረሰብ በምርጫው ሂደት ወቅት ላደረገው ተሳትፎ እና ምርጫው በሰላማዊ መንገድ በመጠናቀቁ ያለንን አድናቆት እንገልጻለን፡፡
ጥቂት ዓለም አቀፍ የምርጫ ታዛቢዎች ምርጫው ዓለም አቀፍ መስፈርትን አያሟላም በማለታቸው የምርጫው ሂደት አሳስቦናል፡፡ በአዲስ አበባ የሚገኘው የኤምባሲያችን ባለስልጣኖች በምርጫው ዕለት ከአዲስ አበባ ውጭ በመንቀሳቀስ ምርጫውን ለመታዘብ ሲጠይቁ በመንግስት በኩል ፈቃድ በመከልከላቸው ሁኔታው አሳስቦናል፡፡ በነጻ ታዛቢዎች ላይ የሚደረገው እቀባ እና በነጻው ሜዲያ ተወካዮች ላይ የሚደረገው ማስፈራራት የሚያሳስብ ጉዳይ ነው፡፡
ከምርጫው ዕለት በፊት እንኳ ነጻ እና ፍትሀዊ የምርጫ መጫወቻ ምህዳር አልነበረም፡፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የኢትዮጵያ መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማጥበብ የማስፈራራት፣ የማሸማቀቅ፣ በሲቪል ማህበረሰቡ ላይ የሚያደርገውን ቁጥጥር በማጥበቅ እና ነጻውን ፕሬስ በመዝጋት አሳሳቢ የሆኑ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ይገኛል፡፡ እንደዚህ ያሉ እርምጃዎች ሀሳብን በነጻ የመግለጽ እና የመደራጀት መብቶችን የሚገድቡ እና ከኢትዮጵያ መንግስት የሰብአዊ መብቶች ግዴታዎች ጋር የሚጻረሩ ስለሆነ ያሳስበናል፡፡
የድምጽ መስጠት ስርዓት ሂደቱ እንደተጠናቀቀ እና ውጤቱም ይፋ እንደሆነ ሁሉም ወገኖች የኃይል እርምጃ ከመውሰድ እንዲታቀቡ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ የምርጫውን ጠቅላላ ሂደት እና የመጨረሻውን የድምጽ ቆጠራ ውጤት ግምገማ ከነጻ ታዛቢዎች ለመስማት እና መንግስት በተረጋጋ ሁኔታ ከወገንተኝነት በጸዳ መልኩ የሚከሰቱ ችግሮችን እና ውዝግቦችን መፍታት እንዲችል ተማዕጽኖዎቻችንን እናቀርባለን፡፡
ኢትዮጵያ እና ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ዘርፈ ብዙ ግንኙነቶች አሏቸው፣ እናም በርካታ የሆኑ ፍላጎቶችን ይጋራሉ፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ዜጎቹ መሰረታዊ የሆኑ መብቶቻቸውን መጠቀም እንዲችሉ እንዲፈቅድ እንማጸናለን፡፡ የተጠናከሩ የዴሞክራሲያዊ ተቋማት እንዲኖሩ እና ግልጽ የፖለቲካ የውይይት መድረክ ለኢትዮጵያ ህዝቦች በተግባር እንዲገለጽ የኢትዮጵያን መንግስት እንማጸናለን፡፡
ከዩኤስ አሜሪካ የመንግስት መምሪያ የሚሰጡ መግለጫዎችን በሚከተሉት መስመሮች ላይ መመልከት እንችላለን፡
በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ የተደረጉ የመጀመሪያ የምርጫ ውጤቶች ገዥው ፓርቲ በአብዛኞቹ በሀገሪቱ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ድል የተቀዳጅ መሆኑን የሚያመላክቱ ናቸው፡፡ በአጠቃላይ በምርጫ ሂደቱ ላይ የመራጮች የመምረጥ ነጻነት በኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣኖች፣ በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ፣ በገዥው የፖለቲካ ፓርቲ እና በካድሬዎቹ በሚደረጉ ህገወጥ ድርጊቶች እና ማድረግ የሚገባቸውን ነገር ሳያደርጉ በመቅረታቸው የተፈጠሩ ችግሮችን በሄድንባቸው እና ግምገማ ባካሄድንባቸው አካባቢዎች ሁሉ ተመልክተናል፡፡ ቀደም ሲል እ.ኤ.አ በ2005 ከተካሄደው ምርጫ ለገዥው ፓርቲ በአጠቃላይ በምርጫ ሂደቱ ግልጽ እና ወሳኝ ጥቅም ሊያስገኙ የሚችሉ በርካታ የሆኑ ህጎች፣ ደንቦች እና የአሰራር ሂደቶች እንዲወጡ ተደርገው ተግባራዊ ሆነዋል፡፡
ከኢትዮጵያ ጋር ሰፊ እና አጠቃላይ የሆነ በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ግንኙነት አለን፣ ሆኖም ግን በዴሞክራሲ እና በመልካም አስተዳደር የሚስተዋሉ ችግሮች ላይ ያለንን ስጋት በቀጥታ ለመንግስት ግልጽ አድርገናል፡፡ ይህንን ምርጫ ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት የሚወስዳቸው እርምጃዎች በቀጣይነት የዩኤስ–ኢትዮጵያ ግንኙነቶች ላይ ተጽዕኖ ሊያሳርፉ ይችላሉ፡፡ ኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ተቋማትን ለማጠናከር እና ምርጫዎች በሚካሄዱበት ጊዜ ማንም ቢሆን ሳይሸማቀቅ እና ሳይፈራ እንዲሁም ለአንደኛው ወገን ወገንተኛነቱን ሳያሳይ በነጻ መሳተፍ እንዲችል ለሁሉም እኩል የሆነ የምርጫ መጫወቻ ሜዳ ማዘጋጀት ያለባት መሆኑ አስፈላጊ ነገር ነው፡፡
ካርል ማርክስ እንዲህ ብለው ነበር፣ “ታሪክ እራሱን ይደግማል፣ በመጀመሪያ እንደ አሰቃቂነት ቀጥሎም እንደ አስቂኝ ቀልድ፡፡“ ከዚህ ሌላ መንገድ ይኖር ይሆን? እንደገና አንድ ጊዜ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን አስቂኝ የምርጫ ቀልድ እንመለከታለን፡፡ እ.ኤ.አ በ2015 ምን ዓይነት አሰቃቂ ነገር ይደገም ይሆን?
2005ን እናስታውስ፡፡ የመለስን የህዳር እልቂት እናስታውስ!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
ግንቦት 23 ቀን 2007 ዓ.ም