ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ…

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

ገጣሚዋ የኪነ ጥበብ ባለሙያ “ከማይበገረው የመንፈስ ጽናቷ ጋር”

እጅግ በጣም የተለዬ ችሎታ ያላት ወጣት ኢትዮጵያዊት የኪነ ጥበብ ባለሙያ የሆነችው ሜሮን ጌትነት ባለፈው ሳምንት “ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ጠንካራ የሆነ የአማርኛ ግጥም በዩቱቢ ድረ ገጽ በመልቀቅ እንዲነበብ አድርጋለች፡፡ ሜሮንን ለመጨረሻ ጊዜ “ያየኋት” በዚህ አሁን በያዝነው ዓመት መስከረም ወር በአንዲት ኢትዮጵያዊት ልጃገረድ ላይ በተደረገው የጠለፋ ጋብቻ ወንጀል ላይ ተመስርቶ የተሰራውን ተውኔት (ፊልም) በማስታወቂያነት እንዲያገለግል በቪዲዮ ተቀርጾ  የቀረበውን ምስል ባየሁበት ጊዜ ነበር፡፡ በሀገሪቱ በስልጣን ላይ እንደ መዥገር ተጣብቆ የሚገኘው ገዥ አካል ለዚህ ጉዳይ ጆሮ ዳባ ልበስ ስላለ ያ አስቀያሚ የጠለፋ ጋብቻ ወንጀል ድርጊት አሁንም ቢሆን እንደቀጠለ ይገኛል፡፡ ድፍረት በሚለው ተውኔት ላይ ሜሮን የማትበገር የህግ ባለሙያ ገጸ ባህሪን በመላበስ ወሳኝ ሚናን በመጫወት የጥቃቱ ሰለባ ለሆነችው ልጃገረድ ነጻነት ብቻ ሳይሆን እርሷ እንደሴትነቷ የራሷን እና የሌሎችን ሴቶች ክብር ለማስጠበቅ ስኬታማ የሆነ ተውኔት ሰርታለች፡፡Meron Getnet, the extraordinary young Ethiopian actress, put out on Youtube a powerful Amharic poem

ታላቅ ዕውቅናን ያገኘው እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የአሸናፊነት ቦታን የያዘው “ድፍረት” የተሰኘው ተውኔት ባለፈው መስከረም ወር በአዲስ አበባ በአንድ ትያትር ቤት ውስጥ ለህዝብ ዕይታ ለመቅረብ የሰከንዶች ያህል ጊዜ ሲቀረው የተያዘው ዕቅድ እንዲሰረዝ በማድረግ ተውኔቱም እንዳይታይ እገዳ ተጥሎበታል፡፡ በዚያ አስደንጋጭ ድርጊት ላይ የተውኔቱ ዳይሬክተር የሆነው ዘረሰናይ ብርሀኔ ከመድረኩ ላይ በመውጣት ታላቅ ይቅርታን በመጠየቅ ለተመልካቾች እንዲህ የሚል አስደንጋጭ ማሳሰቢያ ሰጠ፣ “ይህንን ተውኔት ለተመልካች ማሳየት እንደማንችል በፖሊስ ተነግሮናል፡፡ የፍርድ ቤት ማገጃ ታዟል ተብለናል… በእውነቱ ይህ በእኛ ላይ የተሰነዘረ ግልጽ ጥቃት ነው…“

በሰንዳንስ እና በበርሊን ዓለም አቀፍ የፊልም በዓል ውድድር ላይ ቀርቦ የ2014ን የዓለም አቀፍ “የተመልካቾች ሽልማት” አሸናፊ በሆነው ተውኔት ላይ ለተሳተፉት ሁሉ ግልጽ የሆነ የውርደት ጊዜ ነበር፡፡ በተለይም ደግሞ የእርሷን የተከበረ ሙያ እና ኪናዊ ውበት ለህዝብ ለማሳየት ጠንካራ ፍላጎትን ሰንቃ በቀረበችበት ጊዜ እና በሀገሯ ክብር እና በስራዋ እንዲሁም በጓደኞቿ ላይ የደረሰውን ውርደት በማየት ሜሮን ጌትነት የተለዬ ሀዘን ደርሶባታል፡፡ እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ወያኔ) እያለ የሚጠራው በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል እንዲህ ያለውን ቆንጆ አጋጣሚ በመጠቀም ተመልካችን ከሚያስደስቱት ወጣት ከያኒያን ነጥቀው ለምን ለእራሳቸው ለማድረግ ግዴለሽነትን ለማሳየት እና ጨለምተኛ ለመሆን እንደፈለጉ ገርሞኛል (ለረዥም ጊዜ ባይሆንም እንኳ)፡፡ ወያኔን  “በሰዎች ስቃይ እና መከራ የሚረካ ገዥ አካል” ማለትም የገዥው አካል አመራሮች በሰዎች ስቃይ፣ መከራ እና ሌሎች ሰዎች መጥፎ ዕድል ሲያጋጥማቸው የሚረኩ እና የሚደሰቱ አርኩሳን ፍጡሮች የሚል ስያሜ ሰጥቻቸዋለሁ፡፡

በመስከረሙ የቪዲዮ ምስል ላይ ሜሮንን በተመለከትሁ ጊዜ ለእርሷ ሀዘን እና ለህዝቡ መዋረድ ጥልቅ የሆነ ስሜት ተሰማኝ፡፡ ያ ታዋቂ እና አሸናፊነትን የተቀዳጀው ምርጥ ተውኔት ለተመልካች ዕይታ ቢቀርብ ኖሮ ለሀገሯ፣ ለህዝቧ እና ለእራሷም ክብር ምርጥ የሆነ አጋጣሚ ሊሆን ይችል የነበረውን በመጨረሻዎቹ ሰከንዶች እንዲታገድ መደረጉን ከገለጸችበት ጊዜ በኋላ ተውኔቱን የማየት ጽናቴ ሟሾ ከሰመ፡፡ በዚያ የቪዲዮ የማስተዋወቂያ ምስል ላይ የነበራትን ውጫዊ ባህሪ እንደዚህ ነበር የገለጽኩት፡

…ቆንጆዋ ወጣት የፊልም ተዋንያን ሜሮን ጌትነት ምንም ነገር ትንፍሽ ሳትል በድን ሆና ተቀምጣለች፡፡ በግልጽ እንደምትታየው በጣም የማዘን እና ግራ የመጋባት ሁኔታ ይነበብባት ነበር፡፡ ከመድረኩ የሰማችው ነገር እውነት ሊሆን አይችልም በሚል የተደበላለቀ ስሜት እና እምነት ስለዚሁ ጉዳይ የተሰማትን ስሜት እና እውነት መሆኑን ለማረጋገጥ ሀሳቧን ለማካፈል የምትፈልገው ሰው ለማግኘት በዓይኖቿ በአካባቢው ላይ በማማተር ላይ ነበረች፡፡ ማንንም አላገኘችም እናም ከመጥፎ የሌሊት ቅዠቷ ጋር እንዳለች ያህል ቆጠረችው፡፡ ሜሮን ከተቀመጠችበት ቦታ ሆና በልማዳዊው የጸሎት አቀራረብ ዓይነት የማይሳነው አምላክ በዚህ አስደንጋጭ እና በሀገር ላይም ታላቅ ውርደትን ሊያስከትል በሚችል ሰይጣናዊ ድርጊት ላይ እጁን እንዲያስገባ እና ፍትህን በመስጠት ህዝቡን ከብስጭት ሀገሪቱን ከውርደት እንዲታደግ በሚማጸን መልኩ የእጅ መዳፎቿን ጠበቅ አድርጋ በመያዝ ወደ ላይ አንጋጠጠች፡፡ አንድ ማንንቱ በውል ያልታወቀ ሰው በዚህ አስደንጋጭ ሁኔታ ላይ ምን እንደሚሰማት ጥያቄ አቀረበላት፡፡ (አንድ ሰው ልቡ ከዓለም እይታ ላይ ተነቅሎ እንዲወገድ ከተደረገ በኋላ እንዴት ያለ ስሜት ሊሰማው ይችላል?) ሜሮን በግልጽ በሚታይ መልኩ በተሰበረ ልብ ውስጥ ናት፡፡ ሆኖም ግን ጸጥታን የተጎናጸፈ እና ጀግንነትን የሚያንጸባርቅ ዓይነት ገጽታዋን ታሳያለች፡፡ ንዴቷን እና ድንጋጤዋን ለመደበቅ ትግል ስታደርግ በግልጽ ትታያለች፡፡ ከእንባዎቿ ጋር እፈሳለሁ አትፈሱም ትንቅንቅ ገጥመዋል፡፡ ሆኖም ግን በተሰበረ ልብ ውስጥ ያለች ብትመስልም እርሷ ግን በፍጹም የተሰበረ መንፈስ እና ልብ ውስጥ አይደለችም…

ክብር ማጣት፣ ክብርን ማግኘት፣

ባለፈው መስከረም ወር ድፍረት በተባለው የማስታዋቂያ ፊልም ላይ የሀዘን እና የውርደት ስሜት ያጠላባትን ሜሮንን ከተመለከትሁ በኋላ ወንጀለኛው የህወሀት ገዥ አካል የሜሮንን ኪናዊ ውበት የተላበሰውን ተውኔት ለእይታ እንዳይቀርብ በማገድ እና እርሷንም በስነልቦና እንድትጎዳ የተቻለውን ሁሉ በማድረግ ተሳክቶለታል የሚለውን እውነታ በግርድፉ ተቀብየው ነበር ፡፡ ሆኖም ግን በቅርቡ “ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ” በሚል ርዕስ ያወጣችውን ግጥም ካዳመጥኩ በኋላ መንፈሷ አንድቺም አንዳልተነካ ተገነዘብኩ፡፡ ሜሮን የደረሰባትን ስቃይና መከራ ለማስታገስ ስትል በግጥሞቿ እራሷን ለመከላከል እና ለማጽናነት እንዲሁም ለመሞገት ጥረት አድርጋለች፡፡ የእርሷን ኪናዊ ውበት ለመጨፍለቅ ጥረት ያደረጉትን ኃይሎች ጽናትን እና ድፍረትን በተላበሰ መልኩ እስከ አፍንጫቸው ድረስ ነግራቸዋለች፡፡ ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ በሚለው ግጥሟ የሜሮንን እራስ በእብሪተኞች ተመትቶ አየሁት; ሆኖም ግን ጭንቅላቷ በምንም ዓይነት መልኩ አላጎነበሰም፣ ዘንበልም አላለም፡፡ የመንፈስ ጽናቷ ተጎድቶ አየሁት ሆኖም ግን አይበገሬነት እና የአሸናፊነት ጽናቷ በጉልህ ታየኝ ፡፡ በፊቷ ላይ የአምባገነኖችን አደጋ አነበብኩ ሆኖም ግን የማትፈራ እና የማትበገር እንደምትሆን ሆና አገኘኋት፡፡ ዕውቅ ገጣሚ የሆኑትን የዊሊያም ኢርነስት ሄንለይ  ሀረጎች በመዋስ በሀገሬ፣ ህዝቤ እና ክብሬ ሜሮን የማትበገር! (ሜሮን ፍጹም የማትሸነፍ! የማትበገር ) ሆና አገኘኋት፡፡  ሜሮን አትበገሬ !!!

ቃላት የሰውን ባህሪያት የሚገልጹ ከሆኑ “ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ” የሜሮን ግጥም የስብዕና መገለጫ ከሆኑት ልዩ የመሳብ ኃይል፣ ብሩህ ህሊና እና ክብር እና ሞገስ የካርቦን ክሮች ጋር በጽኑ የተሰሩ እና ከአረብ ብረት 10 ጊዜ እጥፍ የጠነከሩ ባህሪያት ሜሮን አንዳላት ያሳያሉ፡፡ ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ የሚሉት የእርሷ ግጥም ቃላት እንደ ቁጡው የሳሙራይ ጎራዴ የሚከትፉ፣ እንደ አለት መፈርከሻ ደማሚት በኃይል የሚመቱ ናቸው፡፡ እያንዳንዱ ቃል የህወሀትን የፖለቲካ የማታለያ ሸፍጥ ነቅሶ የሚያወጣ ነው፡፡ እያንዳንዱ ሀረግ የህወሀትን የአስመሳይነት ባህሪ አፍረጥርጦ የሚያጋልጥ ነው፡፡ እያንዳንዱ የግጥም ስንኝ የህወሀትን አሳፋሪ ከሀዲነት ፈልፍሎ የሚያወጣ ነው፡፡ ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ የህወሀትን ቀጣፊነት፣ የህወሀትን በሙስና ባህር ውስጥ እየዋኘ ያለ የበከተ ድርጅት መሆኑን እና ህወሀት የሰብአዊ መብቶችን እንደ ገና/ታህሳስ በርበሬ እየደቆሰ ያለ የወንጀለኛ ወሮበላ ቡድን ስብስብ መሆኑን በግልጽ ያመላክታል፡፡

ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ የተሰኘው ግጥም እንደ ድህረ ጸረ-አፓርታይድ/የጸረ-ዘረኝነት የተቃውሞትግል

የግጥም ዋና እና ልዩ የውበት መገለጫው ለአንባቢው እና ለአድማጩ የሚቀርቡት ቃላት እና ሀረጎች ጥልቀት ላለው ትርጉም እና ለአጠቃላይ ግንዛቤ በመጋበዝ ብዙ ምርምር እንዲደግ የመፍቀድ ችሎታቸው ነው፡፡ ግጥሙ አንድ ጊዜ በገጣሚው ከተወለደ እና ለተጠቃሚው ከደረሰ በኋላ ወዲያውኑ ህይወት ከሰጠው አካል በመለየት ነጻ በመሆን የእራሱን ህይወት ይጀምራል፡፡ ግጥም በእያንዳንዱ/ዷ አንባቢ እና አድማጭ አዕምሮ ውስጥ የእራሱን መኖሪያ ያዘጋጃል፡፡ ግጥሙ የእራሱን ድብቅ መልዕከት ለመግለጽ እና ሚስጥራዊነቱ እንዲታወቅ እንዲሁም እንቆቅልሹን ለመፍታት እንዲቻል በግጥም አፍቃሪው የቀዶ ጥገና ማካሄጃ ጠረጴዛ አዕምሮ ላይ ይዘረጋል፡፡ ድብቁን ትርጉም ፈልጎ ማግኘት፣ ከሸፍጡ እና ለትርጉም ክፍት ከሆኑ ቃላት ሀረጎች መካከል ለይቶ በማውጣት ግጥሙ ለማስተላለፍ የፈለገውን ዓላማ እና የግጥሙን እውነተኛ ትርጉም ሚስጥር ማጋለጥ፣ መፍታት እና ግልጽ ማድረግ የአንባቢው እና የአድማጩ ተግባር ነው፡፡    

በተለያዩ የስነጽሁፍ የጥበብ ስራዎች እና በአሜሪካ የባህላዊ ይዘት ያላቸው ትምህርቶች እና ጽሁፎች እራሱን እንዳስተማረ ሰው የትርጉም ገላጭነት እና ትንታኔን የመስጠት ባህሪ ባላቸው የስነጽሁፍ መስኮች ላይ ጥቅም ሊያስገኙ የሚያስችሉ ጥቂት የማይባሉ እውቀቶችን ሸምቻለሁ፡፡ ለእኔ ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ግጥም ግላዊ ትንታኔ በዋናነት የድህረየጸረ-አፓርታይድ/የጸረ-ዘረኝነትየተቃውሞትግልግጥምነው፡፡

ዘረኝነት በደቡብ አፍሪካ የጥቂት አፍሪካውያን/ት የነጭ ዘሮች የፖለቲካ የበላይነቱን በመቆጣጠር በአብዛኞቹ በጥቁር አፍሪካውያን/ት ዘንድ ፍጹም የሆነ የፖለቲካ ጫናን በማሳደር ሲገዙ የነበረበት፣ እንዲሁም የምጣኔ ሀብቱን ሙሉ በሙሉ በእነዚህ ጥቂት ዘረኛ ነጮች የበላይነት ተይዞ የሚመራበት ስርዓት ነበር፡፡ የደቡብ አፍሪካ የዘርኝነት ስርዓት የተመሰረተው ባንቱስታንስ (በትክክል ትርጉሙ የትውልድ ”ክልል”) ተብሎ ተለይቶ የተቀመጠ አስተዳደር በሚጠራ እና ፍጹም የሆነ የዘረኝነት አድልኦ የሚፈጽመው የጥቂት የነጮች የበላይነት በሚል የህዝቦች አመዳደብ ሁኔታ ነበር፡፡ ጥቂቶቹ አፍሪካውያን/ት የነጮች የበላይነት በዘረኝነት ዕኩይ ምግባር በመታበይ የበላይነት ስሜት ይሰማቸዋል ምክንያቱም በወታደራዊ ኃይል አሸንፈው የመጡ ስለሆነ ምንም ዓይነት የጊዜ ገደብ ሳይኖር እንደፈለጉ ህዝቡን እንደብረት ቀጥቅጠው እንደ ሰም አቅልጠው የመግዛት እና በስልጣን ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው ለመኖር እንዲሁም እነርሱን የሚቃወም ማናቸውም ዓይነት ኃይል ቢመጣ ርህራሄ የሌለው የሰብአዊ መብት ረገጣ ከማካሄድ የማይታገሱ አምባገነኖች ነበሩ፡፡ በአፍሪካ የጥቂት ነጮች የዘረኝነት አገዛዝ ጊዜ አምስት ዓይነት የዜጎች ምድቦች ነበሩ፡፡ የመጀመሪያው መደብ የሀገሪቱን የፓርቲ አመራሮች፣ የእነርሱ ደጋፊ ሀብታሞችን እና የእነርሱን ግብረ አበሮች ያካትታል፡፡ ሁለተኛው የዜጎች መደብ አፍሪካን የሚባል ቋንቋ የሚናገሩ እና በ17ኛው ክፍለ ዘመን ከሆላንድ አገር መጥተው የሰፈሩ እና የሆላንድ ዝርያ ያላቸው ተራ አፍሪካውያንን/ትን ያጠቃልላል፡፡ የነጭ እና የጥቁር ድብልቅ ዝርያ ያላቸው ዜጎች ደግሞ በሶስተኛ ደረጃ ምድብ ይካተታሉ፡፡ የህንድ እና የኤስያ ዝርያ ያላቸው ዜጎች ደግሞ በአራተኛ ደረጃ መደብ ይጠቃለላሉ፡፡ አብዛኞቹ የአፍሪካ ዜጎች በጥቂት የነጮች የበላይነት የሚመራው ገዥ አካል ለምንም የማይጠቅሙ እና ዋጋ ቢስ ዜጎች ብሎ የፈረጃቸው ደግሞ በአምስተኛ ምድብ ላይ ተካተዋል፡፡

እንደ ደቡብ አፍሪካው የጥቂት የነጮች የዘረኛ የፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ሁሉ በኢትዮጵያ የፖለቲካ አመራሩ፣ መንግስታዊ ቢሮክራሲው፣ የፖሊስ ኃይሉ፣ የደህንነት እና የወታደራዊ ተቋማት በሙሉ በህወሀት የገዥ አካል በብቸኝነት ተይዘዋል፡፡

እንደ ደቡብ አፍሪካው የጥቂት የነጮች የዘረኛ የፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ሁሉ ደም መጣጩ የህወሀት ገዥ አካል እና ደጋፊዎቹ ሁሉንም የኢኮኖሚ ዘርፎች ማለትም የባንክ ኢንዱስትሪውን፣ የግንባታ እና የስሚንቶ ምርቶችን፣ የማዕድን ስራውን፣ የትራንስፖርት ዘርፉን፣ የኢንሹራንስ እና የአስመጭ እና ላኪ ዘርፉን በብቸኝነት አጠቃልሎ ይዟል፡፡

እንደ ደቡብ አፍሪካው የጥቂት የነጮች የዘረኛ የፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ሁሉ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃ ዜጋ መደቦች የህወሀት ገዥዎች ናቸው፡፡ የሁለተኛ ዜጋ ቡድን ደግሞ የህዝብን ሀብት እየዘረፉ እና ከህግ አግባብ ውጭ በሆነ መልኩ የሀገሪቱን ጥሪት በብቸኝነት እየተቀራመቱ የሚገኙት ያለአግባብ በሀብት የደለቡት የህወሀት አሽከሮች እና ደጋፊዎቻቸው ናቸው፡፡ ዛሬ በአዲስ አበባ እና በሌሎች የክፍለ ሀገር ከተሞች እየተገነቡ ያሉት ትላልቅ ሰማይ ጠቀስ ፎቆች በባለቤቶቹ የድካም እና የላብ ውጤት የተገነቡ ሳይሆኑ በአንጡራ የአትዮጵያ ህዝብ ገንዘብ እና ንብረት የተሰሩ መሆናቸው አገር ያወቀው እና ጸሐይ የሞቀው ቢሆንም ጊዜው ሲደርስ የሚጠየቁበት እና ለባለቤቱ ህዝብ የሚመለሱ መሆናቸውን በውል ሊያጠኑት ይገባል፡፡ ገዥው የወያኔ ቡድን አባላትም አይን ባወጣ መልኩ በሌሎች ዘመዶቻቸው እና በአቃጣሪ ሎሌዎቻቸው ስም በማስመሰያነት ይዘዋቸው ያሉት ህንጻዎች እንዲሁም በውጭ አገሮች በተለያዩ ዓለም አቀፍ ባንኮች የባንክ ደብተር እየከፈቱ የሚያጭቁት የዶላር ሀብት በተራ ዘራፋ ከኢትዮጵያ ደኃ ህዝብ በጠመንጃ አፈሙዝ እያስፈራሩ የነጠቁት እንጅ የላባቸው ዋጋ ስላልሆነ በህግ አግባብ ለባለንብረቱ የሚመለስ እንደሆነ እና ያ ሀብት ለዘራፊው የወሮበላ ቡድን ላም አለኝ በሰማይ ወተቷን የማላይ እንደሆነ እንዲገነዘቡት ያስፈልጋል፡፡

በሶስተኛ ዜግነት መደብ  የሚመደቡት ዜጎች ደግሞ ለግል ጥቅማቸው እና ሌሎች ገዥው አካል የውጭ ኢንቨስተሮች እያለ የሚጠራቸው ከከርሳቸው ውጭ ሌላ ስለምንም ጉዳይ የማያስቡት “ሆዳሞች” እየተባሉ የሚጠሩት ሆድ አደሮች ይካተታሉ፡፡ እነዚህ ሆድ አደሮች መዋዕለ ነዋይን በሀገር ውስጥ ማፍሰስ በሚል ስልት ከገዥው አካል ጋር በመሞዳሞድ እና ሌላ የፖለቲካ ሸፍጥን ለመስራት እንዲችል በማስመሰያነት የሚጠቀምባቸው ስመ ዲያስፖራ ኢትዮያውያን/ት በጭንቅላታቸው ሳይሆን በቦርጫቸው የሚያስቡ እኩይ ምግባር ያላቸው በኢትዮጵያ ህዝብ መከራ እና ስቃይ ላይ ቁማር የሚጫወቱ የገዥው አካል ሎሌዎች እና ሆድ አደሮች ናቸው፡፡

አራተኛው የዜግነት መደብ እራሱን ኢህአዴግ እያለ የሚጠራው እና በኢትዮጵያ ውስጥ እውነተኛ የብዙሀን ፓርቲ ስርዓት እንዳለ ለማስመሰል በሎሌነት እና አሽከርነት እንዲሁም በተራ ጥቅም እየተደለሉ በውስጥ ግን እውነተኛውን ፈላጭ ቆራጭ ገዥ አካል ህወሀትን ለማስመሰያነት የሚደብቁ ሆዳሞችን ያካትታል፡፡ እነዚህ ሆዳሞች ከየብሄረሰቡ ለይስሙላ ስልጣን እየተወከሉ ለህወሀት እኩይ ተልዕኮ በአስፈጻሚነት የቆሙ በእራሳቸው ስብዕና መመራት የማይችሉ በአዕምሯቸው ሳይሆን በቦርጫቸው የሚያስቡ ሆድ አደሮች ናቸው፡፡ እነዚህ ፍጡሮች በህገወጥ መልክ የዜጎችን መሬት እየተቀራመቱ በመሸጥ ኪሳቸውን እስካደለቡ ድረስ፣ በሙስና እና በምልጃ የተዘረጠጠውን ቦርጫቸውን እና ቀፈታቸውን እስከሞሉ ድረስ ነጻ ሆነው በእራሳቸው አስበው ሊሰሩበት በማይችሉት የስልጣን ወንበር ላይ እንደ አሻንጉሊት ፊጥ ብለው ርካሽ የከርስ ጥቅሞቻቸውን ከማግበስበስ ውጭ ለኢትዮጵያ ህዝብ ፋይዳ ያለው ስራ የማይሰሩ ሆድ አምላኩ ናቸው፡፡

በመጨረሻ እና በአምስተኛ ደረጃ የዜግነት መደብ ላይ የተቀመጡት ደግሞ ምንም ነገር የሌላቸው ሆኖም ግን በስርዓቱ ጎስቋላ አመራር እየተደቆሱ፣ እንደ በግ እየታሰሩ፣ እንደ እባብ እየተቀጠቀጡ የሚገደሉ፣ እንደ ፈረስ የሚጋለቡ፣ ሲያስፈልግም ከገዛ ሀገራቸው በማን አለብኝነት ውጡ እየተባሉ ለስደት የሚዳረጉ፣ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እናንተ የሌላ ብሄረሰብ አባል ናችሁ ውጡ እየተባሉ የሚባረሩ፣ በዘመናት ያፈሯቸውን ንብረቶቻቸውን የሚቀሙ፣  የሚገደሉ እና ሁሉም ዓይነት በምድር ላይ ያለ የጭቆና ዓይነት የሚተገበርባቸው ንጹህኢትዮጵያውያን/ት ናቸው፡፡

እንደ ደቡብ አፍሪካው የጥቂት የነጮች የፈላጭ ቆራጭነት አገዛዝ የአፍሪካ ብሄራዊ ፓርቲ ሁሉ የወያኔ አመራሮች እና አባላትም ለዘላለም ኢትዮጵያን ለመግዛት የትውልድ መብት ያላቸው እና እራሳቸውን የተቀቡ የዘር ቅብአቶች አድርገው ይቆጥራሉ፣ ምክንያቱም አሁን እየዘረፉ ያሉበትን ከንቱ ስልጣን ያገኙት በወታደራዊ ኃይል አሸንፈው እና የማቋርጥ ኃይልን በመጠቀም በስልጣን ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው ለመኖር ፍላጎት ስላላቸው ነው፡፡ በደቡብ አፍሪካ እንዳለው የዘረኛው ጥቂት ነጮች የፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ሁሉ ኢትዮጵያም ክልል (በመሰረታዊ ፍልስፍናው እና በፖሊሲ ደረጃም ከአፓርታይድ የዘረኛ መንግስት ጋር አንድ ዓይነት የሆነ) እየተባሉ በሚጠሩ ለከብቶች እንደሚከለሉ የግጦሽ መሬቶች ሁሉ በዘር የአንድ አካባቢ ህዝቦችን በዚያው ተወስነው ስለሌላው የሀገሪቱ ክፍሎች የማይመለከታቸው እና ተዘዋውረው የመስራት መብታቸውን ገደቦ በካድሬዎቹ አማካይነት የጠብ አጫሪነት ድርጊቶችን እየፈጸሙ ብሄር ከብሄረሰቦች እያጋጩ ዜጎቻችንን በማስጨረስ ላይ ይገኛሉ፡፡ እንደ ደቡብ አፍሪካው የጥቂት የነጮች የዘረኛ የፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ እና አብዛኛው የደቡብ አፍሪካ ህዝቦች መሬት አልባ እንደተደረጉት ሁሉ በአሁኑ ጊዜ ሁሉም ኢትዮያውያን/ት መሬት አልባ እንዲሆኑ ተደርገዋል (መሬቶቻቸውም በርካሽ ቁርጥራጭ ገንዘብ በጨረታ ለወያኔ እና ለዓለም አቀፍ የመሬት ተቀራማቾች ተቸብችበዋል፣ በመቸብቸብም ላይ ይገኛሉ)፣ ምክንያቱም መንግስት አጠቃሎ በእራሱ ቁጥጥር ስር አውሏል፡፡ የነጻ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ከምዕራባውያን አበዳሪ እና እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች ማታለያነት ያለፈ ፋይዳ የሌለው ጉዳይ በመሆኑ፡፡ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ያለው መንግስት ማን ነው? ወያኔ/ህወሀት!

የደቡብ ጥቁር አፍሪካውያን/ት ከሁለት አስርት ዓመታት በፊት እና በአሁኑ ጊዜ ደግሞ አብዛኛው  የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ የሆነ አንድ ዓይነት ነገር አላቸው፡ አጠቃላይ የሆነ አገር አልባነት፣ ዜግነት አልባነት እና ከሀዲነት፡፡ ስለሆነም ሜሮን ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ በማለት የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲሰማው ድምጿን ከፍ አድርጋ ትጮሀለች፡፡

የፖለቲካ ተቃዋሚ ግጥም እንደመሆኑ መጠን ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ እንደዚህ ያለውን ዜጎችን በስነጽሁፋዊ ይዘት መመደብን ይቃወማል፡፡ ልዩ በሆነ መልኩ የተለያዩ የግጥም ዓይነቶችን በውስጡ ሊያቅፍ ይችላል፡፡ የምልክትነት ስብስቦች ሊኖሩት ይችላል፣ ሆኖም ግን ሊያጠራጥር በማይችል መልኩ እውነተኛ እና ተገቢ የሆነውን መልዕክት ሊያስተላልፍ የሚችል መሆን አለበት፡፡

ግጥሙ ስሜትን የሚኮረኩሩ እና ለየት ያለ ትርጉም ያለው ይመስላል፣ ቢሆንም ግን በስልጣን ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው ለሚገኙት ስልጣናቸውን ከህግ አግባብ ውጭ ለሚጠቀሙት እውነታውን እስከ አፍንጫቸው ድረስ ይነግራቸዋል፡፡ ይህ ግጥም የነገሮች ተመሳስሎን፣ የተዘዋዋሪ ገላጭነትን፣ ተመሳሳይነት ያላቸውን አናባቢዎች የመጠቀም ስልትን፣ የቃላት ጨዋታ አጠቃቀምን፣ አንድን ነገር በሌላ አስመስሎ መግለጽን እና ትክክለኛ ምሳሌ መስጠትን ይጠቀማል፡፡ ሆኖም ግን ተራኪ እና ኪናዊ ውበትን የተላበሰ የማያቋርጥ፣ መሳጭ እና ቀልብን የሚማርክ  የግጥም ዓይነት ነው፡፡ ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ የሚለው ግጥም በቴክኒካዊ አቀራረቡ የሚማርክ እና መሳጭ መሆኑ እንዳለ ሆኖ በእያንዳንዱ ቃላት እና ሀረጎች ላይ የተካተቱት የፖለቲካ ተቃውሞዎች ከምንም በላይ ስሜቴን ነክተውታል፡፡

(ማስታዋሻ፡ በዚህ ጽሁፍ የቀረቡት ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ የሚሉት ስንኞች የእንግሊዝኛ ትርጉሞች የእራሴ ናቸው ሆኖም ግን ሌሎችም ጠቃሚ የሆኑ ነገሮችን የሚያበረክቱ መሆኑ እንዳለ ሆኖ፡ የተመሳስሎ፣ የስነጽሁፍ ውበት እና የባህል ውስብስብነት ያላቸውን የአማርኛ ግጥሞችን መተርጎም እጅግ በጣም አስቸጋሪ ነገር ነው፡፡ ከዚህ በታች በእንግሊዝኛ ተርጉሜ ያቀረብኩት የሜሮንን ግጥሞች ውስጣዊ ይዘት ሙሉ ትርጉም ይወክላል ብዬ እገምታለሁ፡፡)

ገና ከመጀመሪያ በዩቱቤ ኦዲዪዮ ሲደመጥ ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ ወያኔን እና የወያኔ የክርስትና አባት የሆነውን አሁን በህይወት የሌለውን መለስ ዜናዊን ለመክስስ ተዘጋጅቶ የቀረበ የወንጀለኞች የክስ መጥሪያ እንደሆነ አድርጌ ነው ያሰብኩት፡፡ በሀገሪቱ ላይ ደባ እና ሸፍጥ በመስራት ላይ የሚገኙት የወሮበላ እና የወንጀለኛ ቡድኖች ሁሉንም የሀገሪቱን ሀብት በመዝረፍ፣ ሁሉንም ህዝብ ዜግነት አልባ በማድረግ እና የሁሉንም ህዝብ ክብር በማዋረድ በሚል አቃቤ ህጉ የክስ ጭብጡን ሲያነብ የሚጠቀምባቸው ቃላት እንደ ገደል ማሚቶ በእራሳቸው ያስተጋባሉ፡፡ በእርግጥ ግጥሙ በስም ህወሀት/ወያኔ እነማን እንደሆኑ አይገልጽም፣ ሆኖም ግን በተዘዋዋሪ መንገድ በጣም ከፍተኛ ወንጀሎችን የፈጸሙ እና መለስተኛ ወንጀሎችን የፈጸሙ በሚል የቀረበው አገላለጽ የወንጀለኞችን ማንነት በተጨባጭ የሚያመላክት ነው፡፡

ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ የሚለው የግጥም መድብል የተመሰረተው እና የሚያጠነጥነው የዜግነት መብቶች እጦት፣ የሰብአዊ መብት ረገጣ፣  ሰብአዊ ክብርን ማጣት እና መዋረድ፣ ስልጣንን ከህግ አግባብ ውጭ መጠቀም፣ ሙስና፣ የተምኔታዊ የሀሰት የምጣኔ ሀብት ልማት፣ እና በኢትዮጵያ የገቢ ኢፍትኃዊነት በሚሉ ርዕሶች ስር ነው፡፡ የግጥም መድበሉ አገራዊ የሆኑ በርካታ ጉዳዮችን የዳሰሰ፣ በጣም ጠልቆ በመግባት ስሜትን የሚቀሰቅስ እና የዚህ ግጥም አድማጮች የወያኔን ገዥ አካል የጭቆና አገዛዝ እና የኢትዮጵያውያንን/ትን ከሰብአዊነት በወረደ መልኩ ግፍ እየተፈጸመባቸው ያሉ መሆኑን ስዕላዊ የሆነ መግለጫ በመስጠት ኃይላቸውን አስተባብረው ይህንን ያገጠጠ እና ያፈጠጠ የዕውር ድንብር ስርዓት በመራራው ትግላቸው አሽቀንጥረው በመጣል የእራሳቸውን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መመስረት እንዲችሉ የሚያነሳሳ ጠንካራ የግጥም መድብል ነው፡፡

በእኔ የትንታኔ አተረጓጎም ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ ጸጥ ያለውን የኢትዮጵያውያንን/ትን ድምጽ እንደ ገደል ማሚቶ እንዲያስተጋባ የሚያደርግ እና በሚሊየኖች የሚቆጠሩትን በእራሳቸው ሀገር የተገፉትን እና ባይተዋር የሆኑትን እንዲሁም እነርሱ እንዳይታዩ እና ተረስተው እንዲቀመጡ የተደረጉትን ብቻ ሳይሆን እንደ ሰው ያልተቆጠሩትን፣ ከምንም ያልተቆጠሩትን ኢትዮጵያውያን/ት የተስፋ መቁረጥ ጸጥታ የሚመልስ እና ለአዲስ የትግል ምዕራፍ በአዲስ ወኔ ባማነሳሳት እውነተኛ የሀገሩ ባለቤት እና አድራጊ ፈጣሪ በመሆን የወያኔን የጅብ መንጋ ስብስብ ከምድረ ገጽ ኢትዮጵያ በማስወገድ ሰላም፣ ዴሞክራሲ፣ ሰብአዊ መብት እና የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት አዲሲቱን ኢትዮጵያ በአምባገነኖች ከርሰ መቃብር ላይ ይገነባል የሚል ትርጉምን ይሰጠኛል፡፡ በፍቅር የተሞላው እና ለተገፉት ምንም ለሌላቸው ኢትዮጵያውያን/ት የሚጮኸው የሜሮን ግጥም እንዲህ የሚለውን የኢዱአርዶ ጋሊያኖን የግጥም ስንኞች አስታወሰኝ፣ “ምንም የሌላቸው ያጡ የነጡ”፡…/ ምንም የሌላቸው ያጡ የነጡ፣ የማንም ያልሆኑ ልጆች፣ ንብረት አልባ የሆኑ/ ምንም የሌላቸው ያጡ የነጡ፡ ማንም ያልሆኑ፣ ማንም ያልነበሩ፣ እንደ ጥንቸል የሚሮጡ/በህይወት የሚሞቱ፣ በየመንገዱ የሚጠመዘዙ…ምንም የሌላቸው ያጡ የነጡ፣ የተገደሉበትን ጥይት ያህል ዋጋ የማያወጡ/…/ “

በእኔ የትንታኔ አተረጓጎም ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ለሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ መደቦች የተለያዩ ትርጉሞችን ይዞ ይገኛል፡፡ የወያኔ አባላት ለሆኑት ለመጀመሪያዎች የዜግነት መደቦች የውግዝ መልዕክትን ያስተላልፋል፡፡ የህወሀት ሀብታም ሎሌዎች እና ደጋፊዎች ከወያኔ ጋር ቁርኝት በመፍጠር ያልተገባ ጥቅም በማግበስበስ ላይ ለሚገኙት ለሁለተኛ ደረጃ የዜግነት መደብ ለተሰጣቸው ደግሞ እንዲጠነቀቁ የማስጠንቀቂያ መልዕክት ያስተላልፋል፡፡ በአጠቃላይ መልኩ ለግል ጥቅማቸው ብቻ እንጅ ለምንም ነገር ለማያስቡ እንዲሁም የወያኔ አቃጣሪ በመሆን በስመ ኢቨስተርነት ወደ ሀገር ቤት በመምጣት የሚሞዳሞዱ እና ከሆዳቸው እና ከከርሳቸው በስተቀር ለህዝባቸው እና ለሀገራቸው ምንም ነገር ትዝ የማይላቸው ሆዳም/ከርሳም እየተባሉ ለሚጠሩት በሶስተኛ ደረጃ የዜግነት ምድብ ላይ ለሚገኙት ደግሞ ግጥሙ የቅሌት ዘለፋ ያቀርብላቸዋል፡፡ እንደዚሁም ኢህአዴግ በሚል የማተለያ ሽፋን ስር እራሳቸውን ወሽቀው ህወሀት የሚያሽከረክራቸው በስም ሰው መሳይ በተግባር ግን የሚፐወዙ ሮቦቶች ለሆኑት እና በብዙህን መድብለ ፓርቲ ስም የተፈጠሩባትን የእናት አገራቸውን ጡት አስቆራጭ ከንቱዎች እና ለአራተኛ የዜግነት ምድብ ላላቸው የባዶ አዕምሮ እና የተነፋ ቦርጭ ባለቤቶች ያልተቀደሰውን የሸፍጥ የፓርቲ መሳይ ዱለታ ያጋልጣል፡፡ ኢህአዴግ የሚባለው የከንቱዎች እና የሴረኞች ስብስብ ቡድን ባለራዕይው መሪያቸው በጫት እና በሀሽሽ ምርቃና ሲፈላሰፍ እንደተነበየው ሁሉ ሲፋቅ ህወሀት ሆኖ ይገኛልና፡፡ ምንም የሌላቸው ቀሪዎቹ ኢትዮጵያውየን/ት የሚመደቡበት አምስተኛው እና የመጨረሻው የዜግነት ምድብ ደግሞ ከእንቅልፋችሁ ንቁ፣ በአንድነት እና በጽናት ቁሙ እና ለመብታችሁና ለምንም ለማንም ድርድር ለማይቀርበው ነጻነታችሁ አሁኑኑ ተነሱ በማለት የጥሩንባ ድምጹን በጉልህ ያሰማል፡፡

ሜሮን በተውኔቱ ላይ በግልጽ ቀደም ሲል የሀገሯ ልጅ ሀገሩን ህዝቡን ጥሎ ወደ ውጭ እንዳይሰደድ በማለት የተማጽኖ ጥያቄ በማቅረብ እንደተረከችው የእርሷ ጥልቅ የሆነ ጸጸትን በማቅረብ ይጀምራል፡፡ ክብር እና ሙሉ የዜግነት መብት እዚሁ ለሚቆዩ እና ሀገራቸውን ለሚገነቡ አይደለም የሚሰጠው ሆኖም ግን ሀገራቸውን ጥለው ሄደው ለነበሩ እና አሁን ሀብታም ሆነው ለሚመጡት ሆድ አደሮች የሚሰጥ መሆኑን ሜሮን በጣም ዘግይታ ነው የተረዳችው፡፡ አንድ ሰው ወደ ውጭ ሀገር ሄዶ  ለበርካታ ዓመታት እዚያው በመቆየት ገንዘብ ይዞ ወደ ሀገሩ በመመለስ ዜግነቱ እውቅና እንዲሰጠው እና ክብሩ እንዲከበርለት ያደርጋል፡፡ እዚሁ ሀገራቸውን ለመገንባት በሀገራቸው ውስጥ ያሉ ዜጎች ግን ከዜግነት ውጭ እየተደረጉ ይረሳሉ ይወገዛሉ፡፡ በግጥሟ የመጀመሪያው መስመር ላይ ሀዘኔታ በተቀላቀለበት መልኩ የተጸጸተች መሆኗን እንዲህ በማለት ገልጻለች፣ “እንዳትሄዱ! እንዳትሄዱ!፡፡ ብዕሬን መዝዠ በእናንተ ላይ ጩኸት አሰምቸ ነበር/ከሀገራችሁ እና ከህዝባችሁ ፍቅር ውጭ ጥላችሁ እንዳትሄዱ/ከእኛ ላብ ውጭ የሀገራችን ህልውና ሊረጋገጥ አይችልም/…/ሀገራችሁን ጥላችሁ እንዳትሄዱ ለማስቆም የምችለውን ሁሉ አድርጊያለሁ/…/ሙሉ በሙሉ በእሾህ በታጠሩ መንገዶች ላይ እየተጓዝን ቢሆንም/ ’እንዲሆን እፈቅዳለሁ፣ እኔ እለቅቃለሁ‘ በፍጹም እንዳትሉ/አብረን ሆነን እናጽዳው፡፡/ በመቆጣት ዓይነት እዚሁ አገር ውስጥ እንድትቆዩ ብየ ስህተት እንድተሰሩ ሳደርግ ስሀተት ሰርቸ ነበር…/እነዚያን ቃላት የጻፍኩበት ብዕር አሁን እኔን ይመለከተኛል/እኔን በሀፍረት ይይዘኛል/…/

የሜሮን የሀገሯ ልጅ ለእራሱም ሳይሆን እራሱንም ሳይሆን  ይኸው እስከ አሁን ድረስ በሀገሩ ውስጥ አለ፡፡ የእርሱን መጥፎ ዕድል እንዲህ በማለት ትገልጸዋለች፣ “…በሀገርህ አፈር ለመኖር ትግል ስታደርግ/የአንተን መከራ እና ስቃይ የሚያይልህ የለም…/የአንተ እርባናየለሽ ላብ በዶላር ይተካል/… ለሀገርህ በምትጭህበት ጊዜ የአንተን ታማኝነት በምን ያህል ማትረፍ እንደቻልክ ይገመግሙሀል…/ህዝቡ የውጭ እሴቶችን አምላኪ ሆኗል/ ልቦቻቸው ተንበርክከዋል/…

የሜሮን የሀገር ልጅ ሀገርም የለውም፣ ክብር እና መብትም የለውም፡፡ እዚሁ መቆየት ይችላል ወይስ መሄድ፣ መሄድ ሲባል ክብሩን ሊያስመልስ ወደሚችል በጣም ሩቅ ሀገር፣ ዜግነት ሊያገኝበት ወደሚችል ሀገር እና መብቱን ሊያስከብር ወደሚችልበት ሀገር እናም ተመልሶ ሲመጣ ተመሳሳይ ሁኔታ የሚገኝባትን ሀገሩን በመናፈቅ፡፡

ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ አጠቃላይ የሆነ የዜግነት አልባነት ስሜት፣ ለበርካታ አስርት ዓመታት በውጭ ሀገር የሚኖሩ ዓለም አቀፋዊ ባለሙያዎች እንደ አጋጣሚ በጣም ባልተጠበቀ መልኩ የሚሰማቸው ዓይነት ስሜት ያለው መልዕክት ያስተላልፋል፡፡

ግጥሙ አድማጮቹን በኢትዮጵያ ሀገርየለሽ፣ ንብረትየለሽ፣ አቅመቢስ ኃይልየለሽ፣ እረዳትየለሽ እና ተከላካይየለሽ ምን ማለት እንደሆኑ በውል እንዲሰማቸው ያስገድዳቸዋል፡፡ በእኔ የትርጉም ትንታኔ ግጥሙ በአጠቃላይ መልኩ ስለንብረት አልባነት፣ ጭቆና እና በቅኝ ግዛት አገዛዝ ስር እንደመበዝበዝ ያህል ነው፡፡ በሀገር ውስጥ ወያኔ እየተባለ በሚጠራው የጠባብ ጎሳዊ ቡድን አማካይነት ኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት እየተገዛች እንዳለች ሊገልጽ የሚችል ግጥም ነውን?

ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ በእብሪት የተወጠሩ አጉል ጀብደኛ መሪዎችን እና በውርደት፣ ክብራቸው ዝቅ ተደርጎ እና ዜግነታቸውን ተነፍገው እየተጭበረበሩ ስለሚኖሩ ተገዥዎች ይናገራል፡፡ ግጥሙ የሀገር ባለቤትነታቸውን ለተነጠቁት፣ ቤታቸውን እና መሬታቸውን ላጡት እንዲሁም ክብራቸውን እና ሙገሳቸውን ለተቀሙት ዜጎች የሀዘን ጩኸቱን ያሰማል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ግጥሙ ሀገራቸው ለተዘረፈችባቸው እና ለተሰረቀችባቸው ዜጎች ይጮሀል፡፡ ግጥሙ እንዲህ የሚለውን የነብዩኤርምያስን ትንቢት ያስታውሰኛል፣ “የእኛ ውርሶች ለእንግዶችተሰጡ፣ ቤቶቻችን ለውጭ ባዕዳንተሰጡ፡፡ እኛ አባቶች የሌሉን ወላጅ አልባዎች ነን፣ እናቶቻችንጋለሞታዎች ናቸው፡፡ ለገንዘብ ስንልውኃዎቻችንን በአልኮል በከልናቸው፣ እንጨቶቻችን ለእራሳችንተሸጡ፣ አንገቶቻችን በታላቅ ስቃይውስጥ ናቸው፡ እንሰራለን፣ እናም እረፍት የለንም…“

ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ ላጡ ለነጡ፣ ከጭቃ ጎጆዎቻቸው ተነቅለው በግፍ መሬቶቻቸውን ተነጥቀው ለተባረሩት በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን/ት እና በርካታ ፎቆች ያሏቸው ህንጻዎችን ለሚገነቡ የገዥው አካል አቃጣሪዎች እና አደግዳጊዎች ለሚሰጡት በሀዘን እጮሀለሁ፡፡ ግጥሙ የከተማ ተሀድሶ እና ልማት በሚል ሰበብ ከቀያቸው እየተነቀሉ ለሚባረሩ ወገኖች ይናገራል፡፡

ግጥሙ ስለወያኔ ጉልበተኞች እና የእነርሱ የውጭ አገር ግብረ አበሮች የድሆችን መሬቶች በገፍ እየተጠቀሙ ህዝቡን ቤትየለሽ፣ የረኃብ ሰለባ እና ድህነት እንዲበላቸው ስለማድረጉ ይናገርላቸዋል፡፡ የከተማ እና የገጠር መሬት በጣም አስደንጋጭ በሆነ ፍጥነት እየተበላ መሆኑን እና ለድሆች ወደፊት ምንም ዓይነት ኪስ የሆነ ትንሽ መሬት እና ከዚያም አልፎ ለንብረት የለሾች እና ለድሆች ለቀብር የሚሆን ቦታ እንኳ ማግኘት እንደማይቻል ግጥሙ ይናገራል፡፡

በቤት እጦት ችግር ምክንያት ለረዥም ጊዜ ሲሰቃዩ እና የመንግስት አፓርትመንቶችን (ኮንዶምንዩም) ለማግኘት ቃል ተገብቶላቸው ከቆዩ በኋላ በአቋራጭ ከመጠባበቂያ የስም ዝርዝሩ እያወጣ ወፍራም ጉቦ ለሚሰጡት ሙሰኞች እንዲሰጡ ይደረጋል፡፡ “ደስታ፣ ደስታ፣ ደስታ ለሁሉም እዚህ ለሚኖሩ ድሆች/ ሀገራቸውን ከነውድቀቷ ለሚወዱ ወገኖች/ ለድሆች እና ለተጨቆኑ/ባለብዙ ፎቅ ህንጻዎች ለእናንተ ይገነባሉ/ቤት ለማግኘት የሎተሪ ቲኬቱን በመያዝ ጸሎት ማድረግ ይገባል/ቆይ እና ቆይ፣ እና ለዓመታት ቆይ/ ከዚያም የእራስን ቤት ለማግኘት ዝግጁ ስትሆን/ጉቦውን ለመክፈል ሳትችል ትቀራለህ/እንደገና ደግሞ ሌላ ለውጥ እስኪመጣ ድረስ እና ጎረቤትን እስኪያስወጣልህ/…ለሁሉም ነገር ማመስገን ጥሩ ነገር ነው/ማቃሰት ዋጋ የለውም/በሀገሪቱ ውስጥ ለመቀበሪያ የሚሆን መሬት እንኳ አይኖርም/…/   “

ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ በኢትዮጵያ መሰረታዊ የሰዎችን ክብር እና የሰብአዊ መብቶችን ጥበቃ በመከልከሉ እረገድ እንዲህ የሚሉ የተወሰኑ ጥያቄዎችን ያነሳል፡፡ ዜጋ የመሆን ዋጋው ምንድን ነው?/ብዙ መሬት ተትረፍርፎ ይገኛል/ግን መሬቱን በነጻ ለማግኘት የምትችለው በውጭ አገር ያገኘኸውን ገንዘብ ይዘህ ስትመጣ ነው/ያንተ ዋጋ የዚህን ያህል ነው/…/እንዴት ያለ ተጻራሪ ነገር ነው፣ ሀብታቸውን ከውጭ አገር ያገኙ ሰዎች፣ የሀገሪቱ ዜጋ ያልሆኑ በህገወጥ መልክ በድህነት ከደቀቁ ኢትዮጵያውያን/ት ያገኙትን ገንዘብ ሁሉንም ነገር ማግኘት ይችላሉ፣ ሆኖም ግን ድሆቹ ዜጎች መከራቸውን የሚያዩት እና ሀገራቸውን ለመገንባት ስቃይ እያዩ ያሉት ከምንም ሳይቆጠሩ ይተዋሉ፣ ይረሳሉ እናም ከዜግነት ውጭ ይደረጋሉ!

ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ መናገር እና መስማት ለተሳነው ህዝብ ነው፡፡ በኢፍትሀዊነት ላይ ተቃውመው ለቆሙ እና ስለኢፍትሀዊነት፣ ስልጣናቸውን አለአግባብ ለሚጠቀሙ እና ሙስና ለሚፈጽሙ ማህበረሰቡ ምንም ደንታ በሌለው መልኩ በጸጥታ ይለመከታል፡፡ ማንም የሚሰማ የለም፡፡ ሁሉም ተኝቷል፡፡ በኢትዮጵያ ስላለው ኢፍትሀዊነት የሚደረገው ጩኸት ጀሮ ዳባ ልበስ ተብሏል፡፡ ሆኖም ግን በውጭ አገር የሚገኙት ዲያስፖራዎች ለውጥ መደረግ አለበት በማለት ሲንሾካሾኩ ይደመጣሉ፡፡ “በሀገሪቱ መሀከል ላይ ቆመሀል/በሀገሪቱ መሀከል ላይ ቆመሀል/እናም ለሀገርህ ለሀገርህ ጩህ/እዚያ የሚሰማ ምንም የለም/በውጭ አገር ስትሆን ብቻ ነው የአንተ ሽክሽክታ ነገሮችን ሊለውጥ የሚችለው/…/

ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ ስለትምህርት ጥራት መዝቀጥ እና ዋጋየለሽ መሆን እና ባልተማሩ ደናቁርት እየተመራ መሆኑን (የገዥው አካል በሆኑ ሰዎች እና ዝቅተኛ የትምህርት ደረጃ ባላቸው እና እንዲሁም ዲግሪን ከኢንተርኔት የዲፕሎማ መፈልፈያ ወፍጮዎች እየተገዛ ያለበት ሁኔታ) መቃወም አስፋላጊ ነገር ነው፡፡ “እድሜ ልክህን ለትምህርት በማዋል ከፍተኛ ዲግሪ ማግኘት ትችላለህ/የማስተር ወይም የፒኤች ዲግሪ ዲግሪ ማግኘት ትችላለህ/እውነታውን ልንገርህ/በእኔ ሀገር የትምህርት የእውቀት ደረጃውን የሚያመዛዝነው የሶስት ወራት (የካድሬ) ስልጠና ሰርቲፊኬት ነው/…/

ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ ስለባለስልጣኖች የአቅም ማነስ ድሁርነት እና ሀላፊነትን በአግባቡ መወጣት አለመቻል ቅሬታ ያቀርባል፡፡ የዕለት ከዕለት ስራዎችን የሚያከናውነው የቀበሌ ባለስልጣን (የአካባቢ አስተዳዳሪ) በቢሮው ውስጥ በፍጹም አይገኝም፡፡ የእራሱ ስራ ህዝቡን ማገልገል አይደለም ሆኖም ግን ጊዜውን በከንቱ ማጥፋት እና በየዕለቱ ስብሰባ እና ዲስኩር ሲያሰማ የሚውል አለቃውን በድብቅ ሲከታተል ይውላል፡፡ “ከቀበሌ አገልግሎት ለማግኘት ተገኝታችሁ ነበርን?/ በቢሮ ውስጥ ምንም ዓይነት ሰው አይገኝም፣ ባዶ ወንበር ብቻ/ለሻይ ወጥቷል ተብሎ ይነገራችኋል/ከሻይ እስከሚመለስ ድረስ ለሁለት ወይም ለሶስት ሰዓታት ያህል ጠብቁ ትባላላችሁ/ዝም በሉ፣ ተቀመጡ እና ጠብቁ/ነገ ከቢሮ አይኖርም ምክንያቱም ይድከመዋል/ለእረፍት ይወጣል/አንድ ቀን ይታመማል/ሌላውን ይረሳዋል/በማስፈረሚያ ወረቀቱ ላይ ሳይፈርም ወጥቶ ሄዷል/በስብሰባ ላይ ነው/ስራ ላይ ነው/በእርግጠኝነት ምንድን ነው የሚሰራው?…/ዛሬ በስብሰባ ላይ ነው/ነገ ከአለቆቹ ጋር ነው/…/

የሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ ግጥም አንድ ሰው በገዛ ሀገሩ ከመኖር ይልቅ ከሀገሩ ተሰዶ በሰው ሀገር እንግዳ ሆኖ መኖሩ የተሻለ ስለመሆኑ ይናገራል፡፡ አንድ ሰው በገዛ ሀገሩ አምስተኛ ደረጃ ዜጋ ሆኖ እንዲኖር የሚገደድ ከሆነ ለምንድን ነው በትውልድ ሀገራቸው ለመቆየት የሚፈልጉት? “እንደፈለጉ ይሁኑ/ልንገርህ/ብትለቅ የተሻለ ነው (ሀገርህን)/የአንተን መኖር የሚያውቅልህ ምንም ዓይነት ሰው ከሌለ/ሀገርህን የማትለቀው ለምንድን ነው?/…/“

ግጥሙ ሀገራቸው የተሰረቀችባቸው ዜጎች ወደ ውጭ ሀገር እንዲሄዱ እና ጥቂት ዓመታትን እዚያ ከቆዩ በኋላ በአዲስ ዓይነት የጸጉር አቆራረጥ እና ገንዘብ ይዞ ወደ ሀገር እንዲመለሱ ይመክራል፡፡ ከዚያም ገንዘብ ይዘው የሚመጡ ዲያስፖራዎች በመንግስት ስራ የበዛበት ሚኒስትር እጆቻቸውን ዘርግተው እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ይቀበሏቸዋል፡፡ ሀገራቸውን ለመገንባት እዚሁ ሀገራቸው ውስጥ የሚቆዩ እታች ያሉትን የቀበሌ መሪዎችን እንኳ ማየት አይችሉም፡፡ “እተወሰኑ ጥቂት ሀገሮች ለሶስት ዓመታት ብትሄዱ/እና በአዲስ የጸጉር አቆራረጥ/ምንም ዓይነት ችግር አይገጥምህም/ምንም ዓይነት ጭራቃዊ ዓይን አያይህም/…/በምትመለስበት ጊዜ የአንተን ችግሮች የሚሰማው የተከበረ ሚኒስትር ይሆናል…/በአደባባይ ለአንተ ምን ዓይነት ሀውልት ሊነባልህ እንደሚገባ ይነግርሀል/ስለዚህም መጭው ትውልድ የአንተን ፈለግ ተከትሎ ይሄዳል/ለአንተ ያላቸው ዘመቻ የዚያ ዓይነት ነው…/

ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ ጋብቻ መፈጸም የግል የጋብቻ ስርዓት ተቋም ውጤት መሆኑን ይናገራል፡፡ ወጣቷ ልጃገረድ ባለፈው ጊዜ በባህላዊ ሽማግሌዎች አማካይነት እጇ ለሌላ ሳይሰጥ አምልጣ ከቆየች በአሁኑ ጊዜ በደኃዋ እናቷ ገንዘብ ላለው ለሀብታም ትሰጣለች፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው መልካም አጋጣሚዎች ያለመኖር እና አስደንጋጭ የሆነ የድህነት መንሰራፋት ምክንያት የተከበሩ ወላጆች ልጃገረዶቻቸውን ወደ ውጭ አገር ለመሄድ አቅሙ ላላቸው ለመኖር ለሚችሉ ሰዎች እንዲሰጡ ይገደዳሉ፡፡ “ቆንጆዋን ልጃገረድ ሽማግሌዎችን በመላክ ልታገኛት አትችልም/በልጆች እና በአዋቂዎች ተፈቃሪ የሆነች ታገኛለህ/አሁን ከእናቷ እቅፍ መንጭቀህ ልትወስድ ትችላለህ/ውጭ ሀገር በመሄድህ እና ሀብታም በመሆንህ አይደለምን?/

ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ ነገሮችን እንዳሉ ባለመገንዘብ ምክንያት እና በዘፈቀደ አንድን ሀገር እና ህዝብ በማፍቀሬ ምክንያት ይቅርታ ባለማድረጌ እና ግለሂስ ባለመውሰዴ ይናገራል፡፡ ግጥሙ የገዥው አካል ዋናው የፖሊሲ ማጠንጠኛ ዜጎችን ከሀገራቸው እንዲሰደዱ በማድረግ ተቃዋሚ ይሆናሉ ተብለው የሚጠረጠሩትን ዜጎች መቀነስ ይቻላል፣ እንደዚሁም ሁሉ ከውጨ ሀገር ወደ ሀገር ውስጥ በሚልኩት ገንዘብ የረሚታንስ ገቢን ማግኘት ይችላል፡፡ ገንዘብ ያላቸው እና ገንዘባቸውን ወደ ሀገር ወስጥ በመምጣት መዋዕለ ንዋያቸውን የሚያፈስሱ የዲያስፖራ ሰዎች ይከበራሉ፣ እናም አንበሳ ሆነው ይቆጠራሉ፣ ሆኖም ግን እዚህ በሀገር ውስጥ ትንሽ ገንዘብ ይዘው ያሉ ዜጎች ግን ፍጹም ይተዋሉ፡፡ “ እራሴን ተመልክቻለሁ/በእራሴ አፍሪያለሁ/እንዲህ ያለውን ርካሽ የሆነ ሀሳብ/…/ምስጋና የሌላት ሀገር መኖር ለአንተ ምን ጥሩ ነገር አለው/የለቀቁ ሰዎች እንዲቆዩ ይፈቀድላቸዋል/እዚህ የቆዩት ግን እንዲጠፉ ይደረጋል/ምስጋና የሌላት ሀገር ለአንተ ምን ጥሩ ነገር ይኖረዋል?/…

ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ ስለብልህ እና የተማሩ ሰዎች መጥፋት ጉዳይ ነው፡፡ ግጥሙ አንድን ትልቅ የቴምር ዛፍ በሰው በመመሰል የሞራል መሪዎች እና የህብረተሰቡ ምሰሶ የሆኑት፣ የህዝቡ የሀሳብ አመራሮች እና የህብረተሰቡን ንቃተ ህሊና የሚያጎብቱ እንደቴምር ዛፉ ቀስ በቀስ እየደከመ እንደመጣ ይገልጻል፡፡ እነዚህ መሪዎች ለጥላነት የሚያገለግሉትን ቅጠሎቹን እንደሚያረግፍ  የቴምር ዛፍ ሁሉ ተቆርጠው ይወድቃሉ፡፡ በማህበረሰቡ ዘንድ የቴምር ዛፎች ስማቸውን በትክክል መጻፍ የማይችሉ የደናቁርት የደንደኑ ቅርንጫፎች ናቸው፡፡ “ብልህ ሰዎች በማይኖሩህ ጊዜ/ሀገር ናት እየተሰቃየች ያለች/ህዝቡ ነው በመሰቃየት ላይ ያለው/ባንዲራዋ ናት እየደበዘዘች ያለችው/መዝሙሩ ነው ትክክለኛ ትርጉሙን እያጣ ያለው/እንድትመለስ ነግሬህ የነበረው እንግዲህ ያ ነው/ስለሆነም ሀገርህን አትለቅም/ምንም የቀረ ሀገር የለም/ምንም የቀረ መንፈስ የለም/የብልህ እጥረት አለ/ትልቁ ዛፍ (ዋርካ) ምንም ዓይነት ጥላነት አይሰጥም/ማዕረግ ክብሩን አጥቷል/ምን ዓይነት ትልቅ ዛፍ?/ጥሩ መጥረቢያ በዛፉ ቅርንጫፍ ላይ መጠቀም የተመረጠ ነገር ነው/መሬቱን እና እንጨቱን ቤቶቻቸውን ለሚሰሩት ባለሀገሮች ስጣቸው/ለለውጥ መጓዝ/ልበስ እና ወደ ከተማ ሂድ/እወቀት ምን ያህል ጥሩ ነገር ነው በስልጣን ላይ ያሉ ባለስልጣኖች የማሰብ ችሎታ ዜሮ ሲሆን?/በአሀኑ ጊዜ ያለው ፋሽን ድንጋይን በድንጋይ ላይ መቆለል እና ባለብዙ ፎቅ ህን  ጻዎችን መገንባት/ስለሆነም መልሸ እወስደዋለሁ/ስላለመልቀቅ ቀደም ብየ እንደነገርሁህ መልሸ ወስጀዋለሁ/ሰርዠዋለሁ/ደውልልኝ ስለሆነም ከአንተ ጋር እለቅቃለሁ/ሀኖም ግን አልጠራጠርም/የኢትዮጵያን ውኃ የጠጣሁ ስለሆነ ተመልሸ እመጣለሁ/ስሜን ከለወጥኩ በኋላ ተመልሸ እመጣለሁ/ከዚያ በኋላ ህዝቦቸ እኔን ይቀበሉኛል እናም በፍቅር እንድሞላ ያደርጋሉ/ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ/

በሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ የግጥም ኃይል አማካይነት ተስፋየለሽነትን እና ተስፋ ማጣትን ባዶ ስለማድረግ ጉዳይ ነው፡፡ በግጥም ተስፋቢስነትን፣ ውሸትን በመታሪ እና በከታፊ ቃላት የመዋጋት ጉዳይ ነው፡፡ ግጥም ብቻ ነው አዳማጮቹን በእራሳቸው ቅዠት ውስጥ ተዘፍቀው ከሚደናበሩ፣ እራሳቸውን ከሚጠራጠሩ እና እራሳቸውን ከሚያታልሉ አምባገነኖች ነጻ የሚያወጣው፡፡

“ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ አገር አልባነት፣ ንብረትየለሽነት፣ ኃይልየለሽነት፣ እረዳትየለሽነት እና ተከላካይነት ስሜት ስለሚሰማቸው ኢትዮጵያውያን/ት ጉዳይ ነው፡፡ ግጥም ነው ስለእውነታው ጩኸቱን የሚያሰማው፣ “ከዚህ በኋላ የትም ድረስ ልሸከመው አልችልም! ከዚህ በኋላ በድሀረ አፓርታይድ የዘረኞች አገዛዝ ስርዓት ውስጥ ለመኖር አልችልም!”

ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ ግጥም ለድርጊት የሚያነሳሳ ጥሩንባ ለመጨረሻ ጊዜ እየነፋ ነው፡፡ ይህ ጥሪ ዜግነት አልባ ድፍረትን በመላበስ ሀገሩን መልሶ የሀገሩ ባለቤት ለሆነው ህዝብ የቀረበ ጥሪ ነው፡፡ ለእኔ ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ የተባለው ግጥም ማለት የፈለገው ከሀገር ውጭ ምንም ዓይነት ክብር እንደሌለ፣ ከህዝብ ውጭ ሀገር እንደሌለ፣ ከሀገር እና ከህዝብ ውጭ ክብር እንደሌለ በግልጽ ያስተምራል፡፡ ግጥሙ ለሰው ልጅ ትዕግስት የእራሱ ወሰን ያለው ሲሆን ከዚያ ካለፈ በኋላ ግን ተቀባይነት እንደማይኖረው ወይም ደግሞ ትዕግስት እንደማይኖር ያስገነዝባል፡፡ “ቀስ በቀስ የሚንጠባጠብ ውኃ ጠንካራውን አለት ይፈረካክሳል/ሁላችንም ህዝቡ ከተኛበት እስኪነቃ ድረስ በህብረት አብረን እንጩህ/ሀገሪቱ እስከምትነሳ ድረስ/ከዚያ በኋላ እንደነገርኩህ ተመለስ/ምን ያህል ትንሽ ነገር ነው የማውቀው/ወርቁን እርግፍ አድርገው በመተው መዳቡን ለማግኘት ይስገበገባሉ/

ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ ኃያሉን አምላክ ስለማመስገን ነው፣ የእራሱ ቁጣ እና የበቀል እርምጃ እስከሚነሳ ድረስ ጭራቃዊነትን ድርጊትን ሲፈጽሙ ያለምንም ማስጠንቀቂያ በትዕግስት ስለሚመለከተው አምላክ ጉዳይ ነው፡፡

ህይወትን የሚያመሳስል ኪነ ጥበብ፣

ሜሮን ጌትነት ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ በሚሉት ቃላት ሁላችንንም በሚገባ ደስሳናለች፡፡ ስለሜሮን ግጥም ለቁጥር የሚያዳግቱ የአድናቆት አስተያየቶችን ተቀብያለሁ፡፡ ግጥሙን የሰሙ ሰዎች ሜሮን ከሀገር፣ ከህዝብ እና ከክብር ውጭ የሚኖረውን ስሜት ምን እንደሚመስል የነገራቻቸው መሆናቸውን፣ በአምስተኛ የዜግነት ምድብ ደራጃ መኖር ምን ማለት እንደሆነ፣ የእብሪተኛ ደናቁርት ሰለባ መሆን፣ በጭቆና እና ከህግ አግባብ ውጭ መኖር እንዲሁም ምንም የለሽነት፣ ኃይልየለሽነት፣ እረዳትየለሽነት፣ እና ተከላካይየለሽነት በወሮበላ ዘራፊ አምባገነን የአዙሪት አገዛዝ መዳፍ ስር መኖር ምን ማለት እንደሆነ እና ከዚህ ጭራቃዊ ስርዓት እንዴት መውጣት እንደሚቻል የሚያመላክት ነው፡፡ እኔም የዚህ ዓይነት ስሜት ተሰምቶኛል፡፡

የ19ኛው ክፍለ ዘመን የአየርላንድ ደራሲ እና ገጣሚ የነበሩት ኦስካር ዊልዴ በጽሁፋቸው እንዲህ ብለው ነበር፣ “ህይወት ኪነጥበብን የመመሰሉ ሁኔታ ኪነጥበብ ህይወትን ከሚመስለው የበለጠ ይመስላል፡፡ ይህ ህይወት በዘፈቀደ ከሚመስለው ውጤት የሚመነጭ አይደለም ሆኖም ግን የህይወትን የእራስ ንቃት ህሊና ዓላማ ለመግለጽ እና ያ ኪነጥበብ የተወሰኑ ቆንጆ ዓይነት ሁኔታዎችን ህይሉን ወደተግባር ለመተግበር የሚያስችለው ነው፡፡“

ድፍረት በተባለው ተውኔት ላይ በነበራት ሚና እና ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ በሚለው ግጥሟ  የሜሮንን ስራ በጥንቃቄ ስመለከት ባለሁበት ሁኔታ የእርሷ ህይወት እንዴት ወደ ኪነጥበብነት ማመሳሰል እንደቻለ ተደንቂያለሁ፡፡ ድፍረት በሚለው ተውኔት ላይ ሜሮን የማትበገር የኢትዮጵያዊነት የህግ ባለሙያ ገጸ ባህሪን በመያዝ ለአንዲት የጠለፋ ጋብቻ እና የአስገድዶ መደፈር በአንድ በኋላ ቀር እና ጎጅ ባህል የተጠመደ ሰው ሰለባ ለሆነች ልጃገረድ ተከላካይ ጠበቃ ሆና ስትሰራ ተመልክቻለሁ፡፡

ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ በሚለው ግጥሟ ኢትዮጵያ የምትባል ሌላ ሴት ምህረት በሌላቸው የወሮበላ እና የዘረፋ ስብስቦች ለሁለት አስርት ዓመታት ያህል ተጠልፋ እና የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተፈጽሞባት እውነተኛ ተከላካይ ጠበቃ ሆና ደግማዋለች፡፡ ድፍረት በሚለው ተውኔት ሜሮን የጠለፋ ጋብቻ እና የአስገድዶ መደፈር ሰለባ የሆነችውን የአንዲት ወጣት ልጃገረድ ክብር እና ሞገስ አስጠብቃለች፡፡ ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ በሚለው ግጥሟ ደግሞ የሐገሯን ክብር፣ የህዝቦቿን እና የእራሷን ክብር ታስከብራለች፡፡ ሜሮን በተውኔቱ ላይ ባላት ትክክለኛ የስራ ድርሻ እና በምትጫወተው ሚና መሰረት በአሁኑ ጊዜ ደግሞ ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ በሚል ርዕስ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ባቀረበችው ግጥሟ ልዩ የሆነ ድፍረትን አሳይታለች፡፡

ሜሬሮን በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን/ት በተለይለም በዝምታ በተቀመጡ ሁልጊዜ ለሚወገዘው እና በተስፋ መቁረጥ ህይወትን ይገፋል ለሚባለው ለእርሷ ትውልድ እና በእራሳቸው ላይ ዘግናኝ የሆኑ ወንጀሎች እየተፈጸሙባቸው ዓይኖቻቸውን ሰፋ አድርገው ከፍተው እንቅልፍ ለወሰዳቸው ወገኖች ሜሮን ከልብ ተናግራላቸዋለች፡፡ የእርሷ ድፍረት በግጥሞቿ ላይ በመናገር እና በመጮህ ኢትዮጵያውያንን/ትን ሁሉ በተለይም ወጣቱን ትውልድ በአዲስ መንፈስ ነጻነቱን ለማስከበር እና በጽናት ለመታገል እንዲነሳሳ ትርጉም ያለው መልዕክት አስተላልፋለች፡፡ ሜሮን ትክክል ናት፣ በጣም ትክክል ናት፡ “ሁላችንም ህዝቦች ከእንቅልፋቸው እስኪነቁ ድረስ እስቲ ሁላችንም በአንድነት እንጩህ/ሀገሪቷ ለነጻነቷ እስከምታምጽ/…

ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ ለእኔ የተለዬ ግጥም ነው፡፡ በስልጣን ወንበር ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው ለመኖር ህልማቸው አድርገው የተነሱት የደናቁርት ወሮበላ ገዥዎች የኢትዮጵያን ወጣት መስዋዕት አድርገው እነርሱ በደስታ እና በፈንጠዝያ ዓለማቸውን ሲቀጩ ሳይ የእራሴ ንዴት እንደ ገደል ማሚቶ እያቃጨለ እንቅልፍ ይነሳለኛል፡፡ ሆኖም ግን ሁልጊዜም ቢሆን ከኢትዮጵያ ወጣቶች ጋር በጽናት እቆማለሁ፡፡

የሜሮን ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ በሚለው ግጥሟ ላይ ያሉት እነዚህ ቃላት በአዕምሮዬ ላይ ያቃጭላሉ፡፡ “በሀገሪቱ እምብርት ላይ ቆመሻል/በሀገሪቱ እምብርት ላይ ቆመሻል/እናም ለሀገርሽ እሪ ብለሽ ጩሂ/እዚያ አንድም የሚሰማ የለም/ውጭ ሀገር ስትሆን ብቻ ነው የአንተ ሽክሹክታ ነገሮችን ሊለውጥ የሚችለው/…/

ሜሮን ድምጿን ከፍ አድርጋ እና በግልጽ መጮኋን የሰማን መሆናችንን ልትገነዘብ ይገባል፡፡ አንችን  ለመስማት እዚህ ነን፡፡ አንንሾካሾክም፣ እንጮሀለን፣ እናለቅሳለን እናም ከእርሷ ጋር እሪ እንላለን፡፡

ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ” “ኢትዮጵያ የሚለውን ግጥም” አስታወሰኝ፡፡ ታላቁ የሙዚቃ ንጉስ ጥላሁን ገሰሰ ሀገሬ፣ ህዝቤ፣ ክብሬ የሚለውን ትርጉም ለእኔ ትውልድ ያስተማረ የመጀመሪያው የኪነ ጥበብ ሰው ነበር፡፡ ሁልጊዜ “ኢትዮጵያ! ኢትዮጵያ!” እያልኩ እዘምራለሁ…

ኢትዮጵያ! ኢትዮጵያ!

ኢትዮጵያ! የእኛ መመኪያ (ጋሻ)

የእኛ እናት ሀገር፣ ኢትዮጵያ

የእኛ እናት ሀገር፣ ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ! የእኛ መመኪያ (ጋሻ)

የእኛ እናት ሀገር፣ ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ ምድረ ገነት ሀገር…

ኢትዮጵያ ከተዘፈቀችበት የሲኦል ማጥ ውስጥ ትነሳለች፣ እናም እንደገና ምድረ ገነት ትሆናለች! 

(ይቀጥላል ….) 

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

 ህዳር 9 ቀን 2007 ዓ.ም

Similar Posts

Leave a Reply