በኢትዮጵያ የቅንጦት ግድቦችን መገደብ ለምን አስፈለገ?

ከፕሮፌሰር  አለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

ባለፈው ሳምንት የዓለም አቀፍ ወንዞችን እና  ለሶስት አስርት ዓመታት በእነርሱ ላይ ህልውናቸውን መስርተው የሚኖሩ ህዝቦችን መብት ለማስጠበቅ በግንባርቀደምነት በሚታገለው ዓለም አቀፍ ድርጅት ኢንተርናሽናል ሪቨርስ (የዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ) ላይ የኢትዮጵያ ገዥ አካል ለእራሱ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ የማስመሰል ብስጭትና ቁጣን በማሳየት እርምጃዎችን ለመውሰድ የኢትዮጵያ አዋቂ ነን የሚሉ ስማቸው ያልታወቀ ባለሙያዎችን በማሰማራት በድሕረገጽዎች ላይ ጦርነት አንዲከፍቱ አድረጎ ነበር፡፡ ኢንተርናሽናል ሪቨርስ ዋና ጽ/ቤቱን በሰሜን  ካሊፎርኒያ ግዛት በበርክሌይ ከተማ በማድረግ ህዝቦች ሁሉ ያለምንም የክልከላ ገደብ ውኃዎችን እና ወንዞችን ዘላቂነት ባለው መልኩ መጠቀም እንዲችሉ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ዓለም አቀፍ ድርጅቱ “በህዝብ ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ የግድቦች ግንባታዎች እንዳይካሄዱ፣ ውጤታማ የሆኑ የጎርፍ አያያዝ ተሞክሮዎችን በማስፋፈት፣ በዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅቶች ፖሊሲዎች እና ተሞክሮዎች ላይ ማሻሻያ እንዲደረግባቸው በማድረግ እና ለሰብአዊ መብቶች መጠበቅ እና ለአካባቢዊ ስነምህዳር ዘለቄታዊ ጥቅም በሆኑት የውኃ እና የኤሌትሪክ ኃይል አጣቃቀም መፍትሄዎች ላይ ትኩረት በማድረግ በአፍሪካ፣ በኤስያ እና በላቲን አሜሪካ አመርቂ የሆኑ አበይት ተግባራትን አከናውኗል፡፡“

የገዥው አካል ስም፣ እውቅና እና ህሊና የሌላቸው “ባለሙያዎች”  “በሙያው ደረጃ በእውቀት የተካኑ እና ከታላቁ የህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ሁኔታ እራሳቸውን ሁሉን አዋቂ ኢትዮጵያውያን አማካሪ ባለሙያዎች በሚያስመስል” መልኩ በቅርቡ ያረፉትን በጥላቻ ተሞልተው ይናገሩ የነበሩትን የጌታቸውን የአቶ መለስ ዜናዊ ስም እየጠሩ የእርሳቸውን የጥላቻ አካሄድ መንገድ እንዳለ የሚደግም በሚመስል መልኩ በዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ ድርጅት ላይ በስሜታዊነት የተሞሉ የጥላቻ ትችቶችን፣ እንደ ኮሶ የሚመሩ አግባብነት የሌላቸውን መሰረተቢስ እና እውነታን ያልተላበሱ ኢፍትሀዊ የሆኑ ትችቶችን እንደ በቀቀን ሲደጋግሙ እና ሲያዥጎደጉዱ ተስተውለዋል፡፡ “በኢትዮጵያ ላይ እየተካሄደ ያለ የውክልና ዘመቻ” በሚል ርዕስ አጨቃጫቂ እርካሽ ተግባር ላይ በመዘፈቅ “የታላቁ ህዳሴ ግድብ ብሄራዊ የባለሙያዎች ቡድን” የተባሉት እነዚህ ሆድ አደር ምሁራን ተብየዎችም በተመሳሳይ መልኩ እንደ ምሁር ያለውን እውነታ ግራ እና ቀኝ በማየት ለአገሪቱ የሚጠቅማትን እና የሚጎዳትን ነገር በመለየት ትክክለኛውን ሙያዊ አስተያየት ከመስጠት ይልቅ የተራቡ የውሻ መንጋዎች በባለ እረዥም ጭራ አይጥ መሳይ የዱር አውሬ ላይ እመር ብለው በላዩ ላይ እንደሚሰፍሩበት ዓይነት ሁሉ እነርሱም በተመሳሳይ መልኩ በዓለም አቀፍ ወንዞች ተንከባካቢ ድርጅት ቁንጮ ላይ ተስፈንጥረው በመውጣት የአቅማቸውን ሲዳክሩ ታይተዋል፡፡

የገዥው አካል “የታላቁ ህዳሴ ግድብ ብሄራዊ የባለሙያዎች ቡድን” የክስ ዉንጀላቸዉን በኢንተርናሽናል ሪቨርስ ላይ ሲከፍቱ አንዳሉት: ኢንተርናሽናል ሪቨርስ “በዓለም ላይ ለሚገኙት ወንዞች በሙሉ ‘ጠባቂ’ ነን በሚል እራሳቸውን ሰይመው የሚገኙት እነዚህ ቡድኖች ኢትዮጵያ የውኃ ሀብቶቿን በአግባቡ ተጠቅማ ህዝቧን ከድህነት አራንቋ ለማውጣት የምታደርገውን ጥረት ለማደናቀፍ ሌት ተቀን የሚታትሩ የልማታችን አደናቃፊዎች ናቸው፡፡“ ኢንተርናሽናል ሪቨርስን የዉሃ አምላክ አድረገዉት ቁጭ አሉ!

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ብሄራዊ የባለሙያዎች ቡድን ደስ በመሰኘት ነው ወደ መድረኩ የወጡት፡፡ ምንም ዓይነት የወሰዱት ጥንቃቄ የለም፡፡ ምንም የሚገጣጠም ተያያዥነት ያለው ጉዳይ አላቀረቡም፡፡ ብሄራዊ የባለሙያዎች ቡድን (ብባቡ) የዓለም አቀፍ ወንዞች ጥባቃ መረብ የዓለም አቀፍ ወንዞቸን ደህንነት ለመጠበቅ እና ጉዳት የሚያስከትሉ ግድቦች እንዲቆሙ በፖለቲካ ፍልስፍና አመለካከት ወይም ደግሞ በሌላ ጥልቅ ስሜት በተሞላበት የሀሰት ነብይነት ዓይነት አቀራረብ እያካሄደ የቆየውን ጸረ ኢትዮጵያዊ ጉትጎታ እስከ አሁን ባለው ጊዜ ውስጥ ከመደነቅ ባለፈ መልኩ  ወደ ጎን ጥሎት መቆየቱን መርጧል፡፡ እንደ “የታላቁ ህዳሴ ግድብ ብሄራዊ የባለሙያዎች ቡድን” አመለካከት ኢንተርናሽናል ሪቨርስ የዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ መረብ በአንድ ላይ በመጠቃለል እራሱን ከሳሽ፣ ፖሊስ፣ ዳኛ እና የተሰባሰቡ ውሰኔ ሰጭ ዳኞች ዓይነት ተቋም ነው፡፡ እንደ ቡድኑ አባባል የዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ መረብ ለአገሮች በተለይም በማደግ ላይ ላሉ እና እንደ ኢትዮጵያ ደኃ ለሆኑ አገሮች የውኃ ልማት ፕሮግራሞቻቸውን እና ፕሮጀክቶቻቸውን በትክክለኛው መንገድ እንዴት መስራት እንዳለባቸው ሊወስኑላቸው ይፈልጋሉ፡፡ ኢንተርናሽናል ሪቨርስ  “የዓለም አቀፍ የወንዞች ሁሉ የጥበቃ ፖሊስ” ሊሆን ይችላል ብሎ የሚጠረጥረው ማን ነው?”

“የታላቁ ህዳሴ ግድብ የባሉሙያዎች ቡድን” እንዲህ በማለት በይፋ ተናግሯል፣ “ኢንተርናሽናል ሪቨርስ“ ለአካባቢያዊ ጥበቃ ውጤታማነት እና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ለአካባቢው ማህበረሰብ፣ ለብሄራዊው እና ለአህጉራዊው ህዝብ ጥቅም በጣም አስፈላጊው ነገር ምንድን ነው የሚለውን የውኃ እና የየብስ አካባቢያዊ ስነምህዳር ከኃያሉ አምላክ ጋር እየተናኘ የሚወስን ታላቅ ቄስ ብቻ ሳይሆን በሰዎች ህልውናም ላይ ተጽዕኖ መፍጠር የሚችል ድርጀት እንጅ፡፡ ምን ዓይነት ዕብሪት!!… ሁሉን የውኃ ሀብት ልማት አዋቂ የሆነው አምላክ “ኢንተርናሽናል ሪቨርስ ኢትዮጵያ የጥሩ ውኃ ሀብ ልማት ዕቅድን በአግባቡ አልተገበረችም በሚለው ትዕዛዝ ላይ ተበሳጭቷል!…”

“የታላቁ ህዳሴ ግድብ የባሉሙያዎች ቡድን” በኢንተርናሽናል ሪቨርስ ላይ “የውኃ ጦርነት” እንዲህ በማለት አውጀዋል፣ “በኢትዮጵያ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ምክር የመስጠት እና በመሰል ጉዳዮች ላይ ሁሉን አቀፍ የእውቀት ባለቤት ኢትዮጵያዊ ባለሙያነታችን መጠን ኢንተርናሽናል ሪቨርስ የሌሎች ሀሳብ በእነርሱ እንዲዋጥ እና ወገንተኝነት የሆነ ሀሳብን እያራመደ በግልጽ ከግብጽ ጎን በመቆም በህዳሴው ግድብ እና በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የተዛባ፣ እርባናቢስ እና የጥላቻ ከሀዲነት በተሞላበት ፕሮፓጋንዳ ላይ ተጠምዶ እያየን ዝም ብሎ መመልከቱ ህሊናቢስነት ነው… ኢንተርናሽናል ሪቨርስ ድምጹን ከፍ አድርጎ አጋንኖ በማሰማት በማስመሰል፣ የሞራል ልዕልና የተላበሰ በመምሰል፣ ገለልተኛ መስሎ በመቅረብ እና በኢትዮጵያ ላይ ምንም ዓይነት ፍላጎት የሌለው በማስመሰል እንዲሁም ከግድቡ ግንባታ ጋር በተያያዘ መልኩ የኢትዮጵያን ፍላጎት እና ተስፋ የለሽነት አጉልቶ በማሳየት ዓላማው በግዳጅ ተፈጻሚነት እንዲኖረው ይፈልጋል፡፡ በነገራችን ላይ ሱዳን የታችኛው ተፋሰስ አገር አይደለችምን? ለምንድን ነው ኢንተርናሽናል ሪቨርስ ሱዳን በህዳሴው ግድብ ላይ ያላትን ግልጽ አቋም እና ታላቁን የህዳሴ ግድብ ደግፋ እና ከዚያም አልፎ ለስኬታማነቱ እየረዳች ያለችበትን ሁኔታ ለዓለም አቀፉ ህብረተሰብ ግልጽ ለማድረግ ጆሮ ዳባ ልበስ ያለው?!!!!!!! ኢንተርናሽናል ሪቨርስ ለምንድን ነው በግልጽ ወገንተኝነትን በማራመድ የግብጽን ጥቅም ሙሉ ለሙሉ ደግፎ ጥረት በማድረግ ላይ ያለው?“ የዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ መረብ ከግብጽ ጋር ያለውን ግንኙነት “ከኃያሉ አምላክ ጋር እየተናኘ የሚወስን ታላቅ ቄስ” በማለት በእራስ መተማመን የሌለው ለግብጽ ከሎሌነት እና አሻንጉሊትነት ያልዘለለ ተግባር የሚፈጽም ተደርጎ ሲቀርብ እንዴት የሚያስገርም ነገር ሊሆን አይችልም? ኃያሉ እና ኢንተርናሽናል ሪቨርስ እየተባለ የሚጠራው የግብጽ ሎሌ በአንድ ላይ ሆኖ ሰይጣን፣ ፖሊስ፣ ዳኛ እና ውሳኔ የሚሰጡ የችሎት የዳኞች ስብስብ ሆኖ የቀረበው እርሱ ማን እና ምንድንስ ነው?

የሁሉ ነገር አዋቂ የውኃ እና የየብስ አካባቢያዊ ስነምህዳርን ጉዳይ ከኃያሉ አምላክ ጋር እየተናኘ የሚወስን ታላቅ ቄስየተባለው ኢንተርናሽናል ሪቨርስ በኢትዮጵያ ባለው ገዥ አካል ላይ ለምንድን ነው የሚበሳጫው? ኢንተርናሽናል ሪቨርስ እንዲሁምሁሉንም የውኃ ጉዳይ የሚያውቅ አምላክበመባል ባሽሙር  የሚጠራው በኢትዮጵያ ባለው ገዥ አካል ላይ ያለውጥላቻእንዴት ነው ሊታይ የሚችለው?”

“የታላቁ ህዳሴ ግድብ የባሉሙያዎች ቡድን” እንዲህ ይላሉ፣ “ኢንተርናሽናል ሪቨርስ“ በእነርሱ ላይ ይበሳጫል ምክንያቱም “በኢትዮጵያ ላይ የሚገነባውን የግድብ ሀሳብ ስለማያበረታቱ ነው::” ኢትዮጵያ የግድብ ስራውን እንድታቆም የሚለውን የዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ መረብ መልዕክት ገዥው አካል ሆን ብሎ ለማበሳጨት የሚያደርገውን መወራጨት ለማቆም ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ “ኢንተርናሽናል ሪቨርስ ይበሳጫል ምክንያቱም ኢትዮጵያ የፕሮጅክቱን ግንባታ ለማካሄድ የቀረቡትን መስፈርቶች አልለዉጥም ስላለች ነው፡፡ አልለዉጥም ስላለች ይበሳጫል ምክንያቱም “ክፍያ ለምትፈጽምለት ግብጽ እንደ ዓለም አቀፍ ጎትጓችነቱ እያካሄደ ያለው ዓላማ ስለከሸፈበት ነው::” “የሁሉ ነገር አዋቂ የውኃ እና የየብስ አካባቢያዊ ስነምህዳርን ጉዳይ ከኃያሉ አምላክ ጋር እየተናኘ የሚወስን ታላቅ ቄስ (ኢንተርናሽናል ሪቨርስ)” ይበሳጫል ምክንያቱም ዋናው ትኩረቱ “የግብጽ የውኃ ደህንነት” እንጅ የኢትዮጵያ ድህነት፣ የውኃ፣ የኃይል እና የምግብ ዋስታ አይደለምና!፡፡

“የታላቁ ህዳሴ ግድብ የባለሙያዎች ቡድን”ሲፎክሩ በኢትዮጵያ ገዥ የሚሰራውን የግድብ ስልት ለማሰናከል ኢንተርናሽናል ሪቨርስ እያደረገ ያለውን ሰይጣናዊ ስራና ዘዴዎች አጋልጠናል፡- ደረጃ 1 የተያዘው የግድብ ስራ ፕሮጀክት ወደ ተግባር እንዳይሸጋገር ማሳመን! በመጀመሪያ ደረጃ የዓለምአቀፍ ወንዞች ጥበቃ መድረክ የጸረ ግድብ ግንባታ ስራውን አቁሞ ቀደም ሲል ይዞት የነበረውን ዓላማ መተው አለበት… የዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ መረብ ለግብጻውያን ገንዘብ ከፋዮቹ የመጎትተጎት ዕጣ ፈንታውን በፍጹም አያቆምም፡፡ ደረጃ 2 ጥላሸት የመቀባት ዘመቻ፡ ግድቡ እንዳይሰራ የሚሉትን እንደገና በማሳመን ቀደም ይዘውት የነበረው ዓላማ ሲጨናገፍ እና የታላቁ ህዳሴ ግድብ ተግባራዊ ሲደረግ ኢንተርናሽናል ሪቨርስ ጥላሸት በመቀባት ተግባራት ላይ ይጠመዳል… ሁሉን አዋቂ የውኃ ልማት አምላክ የሆነው ኢንተርናሽናል ሪቨርስ ኢትዮጵያ ጥሩ የሆነ የውኃ ልማት ትዕዛዞችን አላከበረችም በማለት ይበሳጫል… ደረጃ 3 የማንቂያ ደወል መፍጠር፡ ገና በመጀመሪያ እና ፕሮጀክቱ በዕቅድ ነደፋው ወቅት የነበረውን የግድብ ስራ እንቅስቃሴ “ኢንተርናሽናል ሪቨርስ“ እንደገና እንዲያምን እና የግድብ ስራው ይቁም የሚለውን ሀሳብ እንዲተው እና ግድቡ እንዲቆም ሲያካሂድ የቆየው ጥላሸት የመቀባት ዘመቻ አልሳካለት ሲለው በተስፋ መቁረጥ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና ለታችኛው ተፋሰስ አገሮች የማንቂያ ደዎል በመደወል በተለይም ግብጽ በንቃት እና ለጥቅሟ ስትል እንድትከታተለው ያደርጋል፡፡ ደረጃ 4 የይቁም ዘመቻ ማካሄድ፡ የዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ መረብ ከላይ የተጠቀሱት ሶስት ስልቶች ምንም ዓይነት ውጤት የማያስገኙለት ከሆነ በግልጽ ወደ አደባባይ በመውጣት ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ እንዲቆም ድፍረት የተሞላበት ዘመቻ ውስጥ በመግባት የግንባታ ስራው እንዲቆም ለማድረግ አሉታዊ ቅስቀሳውን ይጀምራል…”

ሰለሚመጣው ውድመት ድምጻችንን ከፍ አድርገን እንጩህ! የውኃ ጦርነት አምጭ ውሾችን እናስወግድ፣

ከጥቂት ሳምንታት በፊት በኦሞ ወንዝ ሸለቆ ለዘመናት ህይወታቸውን መስርተው በሚኖሩት ቋሚ ህዝቦች ላይ የደረሰውን ከቀያቸው የማፈናቀል እና ሌሎች ሰብአዊ መብቶችን በማስመልከት ድምጽ ለሌላቸው ህዝቦች ድምጽ በመሆን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጥሪ ላስተላለፉት ለዓለም አቀፍ  ወንዞች መረብ እና ለሌሎች የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ያለኝን ታላቅ አክብሮት (የእራሴን ሀፍረትም በመቀበል ጭምር) መግለጼ የሚታወስ ነው፡፡ እኔ እና በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ሌሎች እትዮጵያውያን/ት ገዥው በኦሞ ወንዝ ሸለቆ ኗሪ  ላይ እየፈጸመ ያለውን ወንጀል እና ስቃይ አይተን እንዳላየ ጆሮ ዳባ ስንል የዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ መረብ ከሌሎች የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ጋር ሆኖ በግንባር ቀደምትነት ለመብቶቻቸው የቆመው እና ስለእነርሱ ድምጹን ጎላ አድርጎ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ያሳወቀው እና ከጨቋኙ ገዥ አካል የሚወረወሩባቸውን የወንጭፍ ድንጋዮች እና የሚስፈነጠሩባቸውን የደጋን ቀስቶች ተቀዋቁመው ትክክለኛውን ስራ እየሰሩ ያሉት፡፡ “በግድቡ ሕይወታቸው የተገደበ ኢትዮጵያውያንን/ትን ለማትረፍ የሚደረገው እርብርብ” በሚለው ትችቴ በይፋ አምኘ ለህዝብ አሳውቂያለሁ፡፡ እንዲህ የሚል ነበር፤

ያንን ትችት ጽፌ ካቀረብኩ ከሁለት ዓመታት በኋላም ቢሆን እስከ አሁን ድረስ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መበቶች እና የአካባቢ ስነምህዳር ጥበቃ ድርጅቶች ለእኛ ብለው ያንን ሁሉ እልህ አስጨራሽ ትግል እና ጥረት እንዲሁም የእኛን ወገኖች ህልውና ለመታደግ እርብርብ እያደረጉ ባሉበት ወቅት እኛ ከዳር ቆመን እየተመለከትን የመገኘታችንን ሁኔታ ሳስበው ለመቀበል በጣም ይቆጠቁጠኛል (በግልጽ ለመናገር ሀፍረት ይሰማኛል፡፡) እነዚህ ከዚህ ቀጥሎ የቀረቡት ተመሳሳይ ጥያቄዎች ምንም ምላሽ ባይኖራቸውም ደግሜ ደጋግሜ እንዳነሳቸው እገደዳለሁ፡ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች እና የአካባቢ ስነምህዳር ጥበቃ ድርጅቶች በኦሞ ወንዝ ሸለቆ ላይ እየተካሄደ ላለው የከፋ አደጋ የሚያመጣ መርሀግበር መቀልበስ ለእኛ ሲሉ ሁሉንም እልህ አስጨራሽ ስራዎች እንዲሰሩ መጠበቅ በእውነቱ ፍትሀዊ ነውን? እነዚህ ዓለም አቀፋዊ ድርጅቶች ለወጎኖቻችን እና ለሀገራችን ሲሉ ይህንን የመሰለ ጥንቃቄ እና ክብካቤ ሲያሳዩ እኛ የጉዳዩ ባለቤቶች ምንም ዓይነት ትኩረት ያልሰጠነው ለምን ይሆን? ለወገኖቻችን ህልውና ሲሉ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ከሚያሰሙት ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር የማንቀላቀል እና ድጋፍ የማናደርግላቸውስ ለምን ይሆን? ጨቋኙ ገዥ አካል የጭቃ ጅራፉን እያጮኸ በእነዚህ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ላይ ቅጥፈት የተሞላበት እና አሳፋሪ መግለጫ እየሰጠ መልካም ስራቸውን እና ስማቸውን ሲያጠለሽ ለምንድን ነው ወደ እነዚህ ድርጅቶች በመጠጋት የማናግዛቸው እና የማንከላከልላቸው? በምን ዓይነት ሁኔታ ነው እረፍት በሌላቸው ዓለም አቀፍ ድርጅቶች [እንደ ዓለም አቀፍ ወንዞች] ከፍተኛ ተጋድሎ አማካይነት በኦሞ ወንዝ ሸለቆ ግራ እና ቀኝ ለሚኖረው ህዝብ የተገኘ የአካባቢ ክብካቤ እና ጥበቃ ቅርስ ነው እናም ኑ ተረከቡን ብለን የወደፊቱን ትውልዶች ለማሳምን የምንሞክረው? ውድ አንባቢዎች በእነዚህ ጥያቄዎች ላይ በአንክሮ እንድታስቡ እጠይቃለሁ፡፡

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል በዓለም አቀፍ ወንዞች ላይ እንደ ጅብ አንጃቧል፡፡ የዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ መረብም በማስፈራሪያ ጋጋታ የሚታቀብ ድርጅት አይደለም፡፡ “ለታላቁ ህዳሴ ግድብ የባለሙያዎች ቡድን” እንዲህ የሚል አፍ የሚያስይዝ መልስ ሰጥተዋል፣ “የፕሮጀክት ሰነዶችን በመገመገም ዘገባ እንዲያቀርቡ ኃላፊነት በተሰጣቸው የዓለም አቀፍ የባለሙያዎች ቡድን አማካይነት በታላቁ የህዳሴ ግደብ ላይ ሚስጥርን ያካተተ ዘገባ አትመን ካወጣን በኋላ የኢትዮጵያ መንግስት ትልቁን የምስል ማሳያ ሰሌዳ አቅጣጫ ወደ ሌላ ማዞር ጀመረ፡፡ ነጻ በሆኑት የእኛ ባለሙያዎች የቀረቡት የእነርሱ ሰነዶች የማጠቃለያ ዘገባዎች ብዙ ጉዳዮችን ማለትም የሚያስከትለው የኃይድሮሎጂካል ጥናት ከበቂ በታች እና ደካማ መሆኑ (ግድቡ ህብረተሰቡን እንዴት እና በታችኛው የተፋሰሱ ክፍል ያለውን ስነምህዳር እንዴት ሊጎዳ እንደሚችል የሚያሳይ በጣም ወሳኝ የሆነው ሰነድ) የሚዳሰሱ ናቸው፡፡“ምላሻቸውን በመቀጠል እንዲህ ብለዋል፣ “የዓለም አቀፍ ወንዞች የኢትዮጵያ መንግስት በሰጠው “ያልሰለጠነ ውንጀላ” ሀዘን ተሰምቶታል:: ዓለም አቀፍ ወንዞች ከማንኛውም መንግስታዊ የሆነ ድርጅት ላይ ግብጽን ጨምሮ ገንዘብ አይቀበልም፡፡ ምንም ዓይነት ወገናዊነት አናሳይም- በዓለም ዙሪያ በጣም ወሳኝ የሆኑ አውዳሚ የወንዞች ፕሮጀክቶች ጉዳይ እና ደካማ የወንዞች አያያዝ ሁኔታ በሚያጋጥመን ጊዜ ገበለልተኝነት በጥንቃቄ ስራችንን እንሰራለን…“

ዓለም አቀፍ ወንዞች ለገዥው አካል አሮጌ ማታለሎች እና ህገወጥ እና መሰረተቢስ ክሶች ተዳርገዋል፡፡ የገዥው አካል አመራሮች ገና ጫካ በነበሩበት ጊዜ ሲያደርጉት የነበረውን ጥላሸት የመቀባት ጦርነት፣ በሀሰት መፈረጅ እና ውሸትን እንደ ቁም ነገር ማነብነብ በመሳሰሉት ብስለት የጎደላቸው የህጻናት ጨዋታ ልምምዶች ላይ የተካኑ ናቸው፡፡ የእነርሱ የሸፍጥ የጨዋታ ጥበብ ነጻ ሰዎችን ሊያጠቁባቸው የሚችሉ እርባናየለሽ፣ መሰረተቢስ እና አስደንጋጭ የሆኑ ነገሮችን መፈብረክ እና የሚያጠቋቸውን ሰዎች ከውጭ ሆነው ለመከላከል ሲዋከቡ መመልከት ነው፡፡ ለማጥቃት ያሰቧቸውን ሰዎች መፈረጅ፣ የተቀናቃኞቻቸውን እና ትችት የሚያቀርቡባቸውን ድርጅቶች ድምጾች ጸጥ ለማድረግ በሚያሳፍሩ ክሶች እና ውሸቶች የተቀነባበረ ድራማ በመስራት ስም ማጥፋት፣ ጥላሸት መቀባት እና በቆዳ ላይ የማይለቅ ምልክት ማስቀመጥ ነው፡፡ እንደሚጠበቀው ዓለም አቀፍ ወንዞች ከገዥው አካል ጋር እንካ ሰላንቲያ እና የጥላቻ አዙሪት ውስጥ ለመግባት ሀሳቡም የለውም፡፡ ዓለም አቀፍ ወንዞች እራሱን ዝቅ አድርጎ ከማይመጥነው ምግባር ጋር ውዝግብ ውስጥ አይገባም፡፡ “በጭቃ ውስጥ ከአሳማ ጋር ትግል አትግጠም፣ አንተ ትቆሽሻለህ አሳማው ግን ይደሰትበታል” የሚለውን የጥንት አባባል አበክረው ይገነዘባሉና፡፡

ለመሆኑ የኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ባለሙያዎች እነማን ናቸው? ባለሙያ ያሰኛቸውስ ምንድን ነው? 

“በኢትዮጵያ ላይ የውክልና ዘመቻ” በማለት ለኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ የባለሙያዎች ቡድን የባለሙያነት ማረጋገጫ መስፈርት ከሆነ ከምንም ጥርጣሬ በላይ የስድብ፣ ፍትሀዊ ላልሆነ ውንጀላ፣ ሰውን የመዘርጠጥ ባህሪ፣ ጥላቻ እና ስምን ማጠልሸት፣ ሰውን መናቅ እና የንቀት ሳቅን በሚያሳዩ ዕኩይ ተግባራት ላይ ተሰማርተው የሚገኙ የስድብ ባለሙያዎች ናቸው፡፡ በመስኩ የጠለቀ እውቀት ወይም ደግሞ በዘርፉ ሁለገብ እውቀት ያላቸው ለመሆናቸው በእርግጠኝነት አልተረጋገጠም፡፡ እራሳቸውን “የኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ የባለሙያዎች ቡድን” ብለው የሰየሙ ብቻ አይደሉም ሆኖም ግን ባለሙያ ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንኳ በትክክል የማያውቁ ናቸው! ባለሙያ ማለት “የአንድ የቴክኒክ ብቃት እውቀት ወይም ክህሎት ምንጭ ሆኖ በህብረተሰቡ ዘንድ በስፋት የሚታወቅ፣ ነገሮችን የመዳኘት፣ በትክክል እና በእርግጠኝነት የመወሰን፣ እና በብልሀቱ ወይም ባለው ዕውቀት በጓደኞቹ ወይም ደግሞ በህዝቡ ዘንድ በአንድ በተወሰነ የእውቀት ዘርፍ ስልጣን ወይም ማዕረግ የተሰጠው“ ማለት ነው በአጭሩ ሲተረጎም፡፡ እነዚህ ስምየለሽ፣ እውቅና የሌላቸው ሆኖም ግን ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እና ተመሳሳይ ጉዳዮች እንዲያማክሩ የተቀመጡ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች እነማን ናቸው? እነዚህ ሰዎች በስማቸው፣ በትምህርት መስካቸው እና በተቋማዊ ዝንባሊያቸው እራሳቸውን ያላስተዋወቁት ወይም እንዲተዋወቁ ያልተደረጉት ለምንድን ነው? የአካዳሚያዊ እና ሙያዊ ብቃታቸው ምን ያህል ነው? ስልጠናቸው፣ ትምህርታቸው፣ ያሳተሟቸው ጽሑፎች ወይም ደግሞ የስራ ልምዳቸው ባለሙያ ለመሰኘት ያበቃቸው ምኑ ነው?

ባለሙያዎች በፊቶቻቸው ላይ መጋረጃ አይሸፍኑም፣ ባለሙያዎች በጨለማ ወስጥ ተደብቀው የሚተኩሱ እና ባለሙያነታቸውን እና ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች መሆናቸውን ለዓለም ህዝብ በመገናኛ ብዙሀን የሚያስተላልፉ አይደሉም፡፡ እውነተኛ ባለሙያዎች ተቃራኒዎቻቸውን ጥላቻ በተሞላ መልኩ አይገዳደሩም፡፡ እውነተኛ ባለሙያዎች በይፋ በአደባባይ በመውጣት በህዘብ መድረኮች ላይ በመገኘት በነገሮች ላይ በሰከነ መልኩ ክርክር ያደርጋሉ፡፡ እውነተኛ ባለሙያዎች የትምህርት ብቃታቸውን ለምርመራ እና ለመፈታተን ለማቅረብ ችግር የለባቸውም፡፡ እውነተኛ ባለሙያዎች በእውነት፣ በመረጃ እና በአመክንዮ ላይ መሰረት ያደረጉ እንጅ በስሜት፣ በምዕናባዊ አስተሳሰብ የሚነዱ እና በስም ማጥፋት ዘመቻ ላይ የሚሰማሩ አይደሉም፡፡ እውነተኛ ባለሙያዎች ተቀናቃኞቻቸውን በጥንቃቄ በተዘጋጀ የምርምር ትንተና ውጤቶች ላይ ተመስርተው የሚሰጡ የሙያዊ ብቃት ውጤቶች እንጅ ከመሬት ተነስቶ በሌላው ላይ የሚለጠፍ ጭቃ ወይም ነገሮች ትክክል ላለመሆናቸው በይሆናል ምልክት በመናገር በአደባባይ የሚፈተፈትበት ጉዳይ አይደለም፡፡

አንድ እራሱን አክባሪ “የባሉሙያዎች ቡድን”  ስለአንድ በዓለም ላይ በስፋት ታዋቂነትን ያተረፈ በዓለም አቀፍ ወንዞች ዙሪያ የሚሰራ ድርጅት ባለሙያዎችን ምን ዓይነት የህዝብ መግለጫ መስጠት እንዳለበት እና ምንስ መናገር እንዳለበት ከሚከተሉት ለማየት እንሞክር፡

የዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ መረብ ከኃያሉ አምላክ ጋር መገናኘት የሚችል ታላቅ ቄስ እና ስለአካባቢ ተስማሚነት መወሰን የሚችል ድርጅት ነው…

ስለውኃ ሀብት ልማት ሁሉን ነገር አዋቂ አምላክ የሆነው የዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ መረብ ኢትዮጵያ የጥሩ ውኃ ሀብት ልማት ዕቅድ ትዕዛዝን ባለመፈጸሟ ምክንያት ለብስጭት ተዳርጓል…

የዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ መረብ ትልቁ ትኩረቱ ስለግብጽ የውኃ ደህንነት እንጅ ስለኢትዮጵያ ድህነት፣ ስለውኃ፣ ስለ ኃይል እና የምግብ ዋስትና አይደለም! ኦ፣ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ተጠንቀቁ! ገንዘባችሁን እዚያ አያስቀምጡ፡፡ ከዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ መረብ ጋር አጋርነት መመስረት ምን ዓይነት አሳፋሪ ነገር ነው፡፡ በድብቅ እና በህገወጥ መልክ ለዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ መረብ ገንዘብ ብንሰጥ ልንከሰስ እንችላለን?

በተስፋ መቁረጥ ምክንያት የዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ መረብ በግልጽ ወደ አደባባይ በመውጣት ትክክለኛ ገጽታውን አሳይቷል፡፡ ለወንዞች ጤንነት እንደሚዋጋ ዓለም አቀፍ ተቋም ማስመሰያነት በድብቅ የግብጽ ወኪል ሆኖ ተገኝቷል!!

የዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ መረብ ድምጹን ከፍ አድርጎ አጋንኖ በማሰማት በማስመሰል፣ የሞራ ልዕልና የተላበሰ በመምሰል፣ ገለልተኛ መስሎ በመቅረብ እና በኢትዮጵያ  ላይ ምንም ዓይነት ፍላጎት የሌለው በማስመሰል እንዲሁም ከግድቡ ግንባታ ጋር በተያያዘ መልኩ የኢትዮጵያን ፍላጎት እና ተስፋ የለሽነት አጉልቶ በማሳየት ዓላማው በግዳጅ ተፈጻሚነት እንዲኖረው ይፈልጋል፡፡ በነገራችን ላይ ሱዳን የታችኛው ተፋሰስ አገር አይደለችምን? ለምንድን ነው የዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ መረብ ሱዳን በህዳሴው ግድብ ላይ ያላትን ግልጽ አቋም እና ታላቁን የህዳሴ ግድብ ደግፋ እና ከዚያም አልፎ ለስኬታማነቱ እየረዳች ያለችበትን ሁኔታ ለዓለም አቀፉ ህብረተሰብ ግልጽ ለማድረግ ጆሮ ዳባ ልበስ ያለው?!!!!!!!

ለምንድን ነው የዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ መረብ በብቸኝነት ለግብጽ ፍላጎት የሚዋጋው? በእውነታው እና በሚታሰበው መካከል የተፈበረኩ ፍርሃቶች ለምንድን ነው ሆን ተብሎ የሚራመዱት ታላቁ የአስዋን ግድብ ሲሰራ አንድም ቃል ሳይነገር የተጠናቀቀው…

የዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ መረብ የኢትዮጵያን ታላቁን የህዳሴ ግድብ አንድም መልካም ነገር እንዲያነሳ አይገደድም፡፡ ያንን ማንሳት የተወገዘ ግኡዝ ነው!

የዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ መረብ የሀፍረት ወሰን የለውም፡፡ ሌሎች የአካባቢ ጥበቃ አባላት ዝም በማለታቸው ክስ መስርቷል! በመሬት ላይ ያለ ማንም ማገናዘብ የሚችል ሰው ወደ የዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ መረብ ግላዊ የሙስና እንቅስቃሴ ውስጥ መግባት ይችላልን?

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት መግለጫዎች ከጫካ ካድሬዎች የመጣ የማደናገሪያ ድምጽ እንጅ እራሳቸውን ከሚያከብሩ ባለሙያዎች አንደበት ሰምተን አናውቅም፡፡ ባለሙያዎች በማቃሰት እና በመጨነቅ፣ በሆድ ቁርጠት፣ ነገሮችን በውል በማጤን፣ በማጉተምተም እና ምክንያታዊ ባልሆነ መንገድ በማጉተምተም ጉዳዮቻቸውን ማረጋገጥ አይችሉም፡፡ ባለሙያዎች ጥርስ በመፍጨት፣ በማጠልሸት እና ጣት በመቀሰር ተግባራት ላይ አይጠመዱም፡፡ የኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግደብ ባለሙያዎች በትክክለኛነት ባለሙያዎች ሳይሆኑ የዕለት እንጀራቸውን ከጌቶቻቸው ለማግኘት ምንም ነገር የማይናገሩ እና የማያደርጉ ህሊናየለሽ ታማኝ ሎሌዎች እና ካድሬዎች ናቸው ለማለት ይቻላልን?

ገዥው አካል ከእውነታ ጋር በሚፋጠጥበት ጊዜ ተፈጥሯዊ እና የሚጠበቀው ምላሽ በስሜታዊነት መሞላት፣ ባልተረጋጋ መልኩ ተጨንቆ መዞር፣ በጭንቀት ተውጦ መንፈራገጥ፣ እና ድምጽን ከፍ አድርጎ መጮህ ነው፡፡ ይህንን ነው አንግዲህ በስልጣን ላይ ያለው አካል እያደረገ ያለው፡፡ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ባለሙያዎች “የግመሏን ጀርባ የሰበረች ገለባ“ በሚል ርዕስ እ.ኤ.አ በማርች 31/2014 በዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ መረብ ድረ ገጽ ላይ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዘገባ፡ “ታላላቅ የቀሩ ጥያቄዎች” በሚል ርዕስ የወጣው ጽሑፍ ለአሁኑ የመወያያ ርዕስ ሆኗል፡፡ በግልጽ ለመናገር ገዥው አካል በዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ መረብ ትንታኔ መሰረት የድብቅ ሪፖርት ባለሙያዎች እየተባሉ በሚጠሩት አባላት በቀረበው ዘገባ ላይ እራሱ የሚመታበት ይሆናል፡፡ ለዚህም ነው እንደተወጋ አሳማ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው የሚጮሁት፡፡ እራሳቸው በምዕናብ ከፈጠሩት ቦክሰኛ ተቀናቃኝ ጋር የቦክስ ግጥሚያ እያደረጉ ከወዲያ ወዲህ እየተወዛወዙ ነው (በጨለማ ውስጥ)፡፡ ሆኖም ግን አንዳቸውም ቢሆን እውነተኛውን ግጥሚያ አያደርጉም፡፡ ይቅርታ፣ ማስተካከያ፡ አቶ መለስ ብቻ ናቸው ከአውነት ጋር ጦርነት ማረግ የሚችሉት፡፡ የአውሮፓ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን እ.ኤ.አ በሜይ 2010 አቶ መለስ ዜናዊን እጆቻቸውን በድምጽ መስጫ ሳጥኑ ውስጥ አስገብተው እጅ ከፍንጅ በያዛቸው ጊዜ አቶ መለስ በቡድኑ ላይ በቀጥታ በሚያዋርድ መልኩ ከወር በላይ የቆዩበት “የምርጫ ዘገባው  እርባየለሽ የለሽ ስለሆነ ወደ ቆሻሻ ቅርጫት መጣል ያለበት ነው” በማለት  ውርጅብኝ ሸኝተዋችዋል፡፡ እ.ኤ.አ በኦገስት 2005 በተደረገው አገር አቀፍ ምርጫ እርሳቸው የሚመሩት ፓርቲ በተቃዋሚዎች ህብረት ሽንፈት በገጠመው ጊዜ አቶ መለስ የአውሮፓ ህብረት ፓርላሜንት አባል በሆኑት በአና ጎሜዝ እና በምርጫ ታዛቢ ቡድኑ አባላት ላይ ያላቸውን ጥላቻ ገልጸዋል፡፡ እንዲህም ብለዋል፣ “በሚቀጥሉት ቀናት እና ሳምንታት ይህንን ነጭ ውሸት እና ትክክል ያልሆነ ነገር ለማጋለጥ የምናደርገውን ታያላችሁ፡፡“

የኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ባለሙያዎች ከአቶ መለስ ዜናዊ “የማስፈራራት እና ጥላሸት የመቀባት” መጽሐፍ ውስጥ የሚጋሩት ገጽ አለ፡፡ ይኸውም የዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ መረብን ማስፈራራት እና ስም ማጠልሸት ነው፡፡ “የጠነከረው ሲላላ የላላውን ወጥር“ የሚለው አባባል በኢትዮጵያ ላለው ገዥ አካል አይሆንም፡፡ “የላላው ሲወጠር ገዥው አካል መጮህ፣ ሰዎችን ማዋረድ እና ጥላሸት የመቀባት የጭቃ ጅራፉን ይጀምራል፡፡”

“የኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ባለሙያዎች” እንደ መንፈስ አባታቸው እንደ አቶ መለስ ሁሉ “ባለሙያዎች” ናቸው፡፡ አቶ መለስ በሁሉም ነገር ባለሙያ እንደነበሩ ማንም ያውቃል፡፡ እርሳቸው በኢኮኖሚው፣ በፖለቲካው፣ በማህበረሰብ፣ በፌዴራሊዝም፣ በወታደራዊ ስልት፣ በዓለም አቀፍ ግንኙነቶች እና በማናቸውም ቢሆን የበቁ ባለሙያ ነበሩ፡፡ ብቁው ባለሙያ አቶ መለስ እንግሊዝ አገር ከሚገኘው ኦፕን ዩኒቨርስቲ እየተባለ ከሚጠራው ተቋም የርቀት ትምህርት ያላቸው ሲሆን ለቅድመ ምረቃ እና ለድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች የሚሰጡ አንዳንድ ኮርሶችን ለተለመዱት የቅበላ መስፈርቶችን ወደ ጎን በማለት የመዝለል ባህሪ ይታይበታል፡፡ የኢትዮጵያ “የታላቁ ህዳሴ ግድብ ባለሙያዎች” የትምህርት ሁኔታ ምን ይመስላል? ከተደበቁበት የጨለማ ጓዳ ውስጥ ወጥተው በአደባባይ በህዝባዊ መድረኮች በይፋ የምናያቸው እና ከእነርሱም የልሂቃንነት ትሩፋት ለመቋደስ ዕድሉን እናገኝ ይሆን? ስለሆነም ለኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ባለሙያዎች ትልቁ ፈተና ሆነው የሚቀርቡት፡ ወደፊት መምጣት፣ ፊታችሁን ፊት ለፊት እንድታሳዩ፣ የትምህርት ውጤቶቻችሁን በጠረጴዛ ላይ እንድታስቀምጡ እና የሙገታ አደባባዩን በይፋ እንድትቀላቀሉ፣ ወይም ይህ ካልሆነ የአንደበታችሁን ጥርቅም አድርጋችሁ ዝጉት፡፡

በገዥው አካል የታላቁ ህዳሴ ግድብ ባለሙያዎች አንደበት “ የመርዶ ነጋሪ ደወል አሰሚዎች”፣በግብጽ ጌቶቻቸው ተከፋዮች”፣አደገኛ የስም አጥፊዎች”፣ጸረ ኢትዮጵያ ጎትጓቾች”፣በኢትዮጵያ የታላቁ የህዳሴ ግድብ እና በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የከሀዲነት ፕሮፓጋንዳ የሚሰሩ”፣ሀፍረተቢስ ወገንተኞች”፣ ወዘተ በማለት የዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ መረብን መፈረጅ በእንቁራሪት አፍ አስቀያሚ መልከ ጥፉ  አንደመባል ነው ፡፡

ገዥው አካል በመጽሐፍ ውስጥ ያለውን ስድቦች ማንኛውንም ዓይነት ስም ለዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ መረብ ላይ አነደነጎድግዋድ ጥሎበታል፡፡ የዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ መረብ ድብቁን ዘገባ ፈልፍሎ በማውጣት የሰጠው ሙያዊ ትንታኔ ገዥውን አካል ጎጆው ከተነካበት ተናዳፊ ተርብ የበለጠ አበሳጭቶታል፡፡ የዓለም አቀፍ ወንዞች ጠበቃ መረብን በአስፈራሪነት፣ “ከግብጽ ጌቶቻቸው ተከፋዮች፣ አደገኛ ስም አጥፊዎች፣ጸረ ኢትዮጵያ ጎትጓቾች፣ የኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ እና የኢትዮያ ህዝብ ጸር፣ ሀፍረተቢስ ወገንተኞች፣በዓለም አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋችነት ቡድን ለወንዞች ጤንነት ጥበቃ ስም የግብጽ ወኪሎች፣” ወዘተ በማለት በዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ መረብ ላይ ክስ አቅርበዋል፡፡ በስም የለሾች፣ ታዋቂነት በሌላቸው ሰዎች እና በህሊና የለሽ የኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ባለሙያዎች መፈረጅ የዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ መረብን መፈረጅ በእንቁራሪት አፍ አስቀያሚ መልከ ጥፉ  አንደመባል ነው ፡፡ ዓለም አቀፍ የወንዞች ጥበቃ መረብ በሁሉም ዓይነት ስሞች እና ዘለፋዎች መፈረጁ የሚያስገርም አይሆንም፡፡ የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ባለሙያዎች ከፋይ ጌቶቻቸው በዘለፋ እና በመፈረጅ ረገድ ከታየ የበለጠ ባለሙያዎች ናቸው፡፡ ከእነርሱ ጋር የማይወግኑትን እና የማይሞዳሞዱትን በእራስ የሚተማመኑ ወገኖቻችንን “አክራሪ ዲያስፖራ” በማለት ይፈርጇቸዋል፡፡ “ነጻነትን ከሚደፈጥጡ ኃይሎች ለመከላከል የሚደረግ ተጋድሎ የሞራል ውድቀት አይደለም” ብለዋል ባሪ ጎልድዋተር፡፡

ሀፍረተቢስ ወገንተኛነት? “የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ባለሙያዎች” በዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ መረብ ላይ እጅግ በጣም አዝነዋል፡፡ ይህ “የዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ ምን ዓይነት ሀፍረተቢስ የሆነ ተቋም ነው፣ በድብቅ ክፍያ ሙስና ተሰጦት ይሆን ብለው ይጠ ይቃሉ::  ከጥቂት ሳምንታት በፊት የአምራች ኢንዱስትሪዎች ግልጽነት ተነሳሽነት ሊቀመንበር ለሆኑት ለማዳም ክላሬ ተመሳሳይ ነገር ሳስብ ነበር፡፡ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ማዳም ሾርት በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል እርሳቸው ለሚመሩት ክለብ አባልነት እንዲፈቀድለት እና እንዲገባ ከፍተኛ የሆነ የሞት ሽረት ትግል አድርገው ነበር፡፡ በገዥው አካል ወገን ሆነው ሲያደርጉት የነበረው የማግባባት ጉትጎታ በጣም አስደንጋጭ እና በድርጅታቸው ውስጥ ቅራኔ እና በድርጅቱ ውስጥ ከፍተኛ የጥላቻ ስሜትን ጥሎ አልፏል፡፡ እውነት ለመናገር ተመሳሳይ ጥርጣሬ ነበር የነበረኝ፡፡ ማዳም ክላሬ ለገዥው አካል ከድርጅታቸው መርህና ደንብ ውጭ ሽንጣቸውን ገትረው ለገዥው አካል ሲከራከሩ የነበሩት በሚስጥር ለእርሳቸው የተፈጸመ ክፍያ ይኖር ይሆን እንዴ? የሚል ጥያቄ አንስቸ ነበር፡፡ አሁንም እየጠየቅሁ ነው፡፡

ጥላሸት የመቀባት ዘመቻዎች? የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ባለሙያዎች ዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ መረብን በአደገኛ ጥላሸት መቀባት ከስሶታል፡፡ ሁለት አስፈሪ እና ስም አጥፊ የሙስሊም ወገኖቻችንን ያዋረደ ግብር በሚከፈልበት የህዝብ መገናኛ ብዙሀን በይፋ እንዲታይ ያደረገ ማን ነበር?  አኬልዳማ ወገን የማይለይ አሰቃቂ እልቂት ወደፊት የምጻት ቀን ሊመጣ እንደሚችል አውጃውን በማስረገጥ ጀምሮ እንዲህ የሚል መልዕክት አስተላልፏ፡ “ሽብርተኝነት ዓለምን እያጠፋ ነው፡፡ ሽብርተኝነት በዕለት ከዕለት ህይወታችን አደጋ ደቅኗል፣ ችግር አይደለም፡፡ ይልቁንምእየተናገርሁያለሁትአገራችንኢትዮጵያንአኬልዳለማድረግወይምየደምመሬትለማድረግእየተሸረበስላለውዕቅድነው:: ለእኛ ለኢትዮጵያውያን/ት ሽብርተኝነት መራራ ችግር ሆኖ ቀርቧል…“ በማለት ተናግረዋል፡፡

ጭራቃዊ አድርጎ ማቅረብ እና የዘለፋ የትችት ዘመቻዎችን ማካድ? የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ባለሙያዎች የዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ መረብ ዓለም አቀፍ ወንዞችን መጠበቅ በሚል ሽፋን በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል ላይ “የጽንፈኛ የሀሰት መሲህነት” ተልዕኮን በማራመድ የዘለፋ ትችት አራምዷል በማለት ክስሶታል፡፡ በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ ንጉስ የነበሩት የዳግማዊ ዓጼ ምኒልክ መቶኛ የሙት ዓመት እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በዚህ በያዝነው ዓመት በሚከበርበት ጊዜ ገዥው አካል ጽንፈኛ እና ዲያብሎሳዊ ድርጊትን በመላበስ ጭራቃዊ አድርጎ በማቅረብ እና በሀሰት ፕሮፓጋንዳ ስብዕናቸውን ለማራከስ የዘለፋ ዘመቻ ሲያካሂድ የነበረው ዕኩይ ጥረት እና የተወነው ትወናስ ምርቃት እና ምስጋና ሊባል ይሆን? ዳግማዊ ዓጼ ምኒልክን ጭራቃዊ አድርጎ በማቅረብ እና ስማቸውን ጥላሸት በመቀባት ገዥው አካል ትክክለኛውን ታሪክ ደምስሶ እንደገና የውሸት ለመጻፍ፣ አዛብቶ ለመጻፍ፣ ገልብጦ ለመጻፍ፣ አወዛጋቢ አድርጎ ለመጻፍ፣ በመቀባባት የሚያምር አስመስሎ ለማቅረብ እና እውነተኛውን የዳጋማዊ ዓጼ ምኒልክ ታሪክ በማስወገድ እራሳቸው የመልዓክ ተምሳሌት አድርገው በሚቆጥሯቸው በአቶ መለስ ዜናዊ ታሪክ ለመተካት የታለመ ዕኩይ ምግባር ነው፡፡

የከሀዲነት ፕሮፓጋንዳ?  የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ባለሙያዎች በታላቁ የህዳሴ ግድብ እና በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያልተረጋገጠ እና በጥላቻ የተሞላ የከሀዲነት ፕሮፓጋንዳ በመፈልፈል በሚል የዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ መረብን ከስሷል፡፡ እ.ኤ.አ በ1990 ስለኢትዮጵያ አንድነት ጥያቄ በቀረበለት ወቅት የትኛው ከሀዲ የፕሮፓጋንዳ ተጫዋች ነበር የሚከተሉትን መግለጫዎች የሰጠው?: “በመጀመሪያ ደረጅ ይህንን ጉዳይ የምንመለከተው ከትግራይ ህዝብ ፍላጎት አንጻር ነው ከዚያ በጠቅላላ ከኢትዮጵያ አንጻር የምናየው ይሆናል፡፡ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር መልካም ግንኙነት መስርታ ማየት እንፈልጋለን፡፡ ትግራይ የባህር በር እንደሚያስፈልጋት እናውቃለን፣ እናም ይህ ጉዳይ ተግባራዊ የሚሆነው በኤርትራ በኩል በማለፍ ብቻ ነው፡፡ ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል ሆነች ወይም እራሷን ችላ ነጻ ሆነች ይህንን የባህር በር ጉዳይ የምንፈልገው ነው፣ እናም በሁለታችን መካከል የጠበቀ ግንኙነት ሊኖረን ይገባል፡፡ በኤርትራ በርካታ ትግራውያን አሉ፡፡ የሚያሳስባቸው ጉዳይ አለ፡፡ እዚያ እንደ ውጭ ዜጋ መስተናገድን አይፈልገጉም…“ የትኛው ከሀዲ ነው የኢትዮጵያን የባህር በር አሳልፎ ለሌላ የሰጠው (ለመቀበልም ፈቃደኛ ባለመሆን በጽናት የታገለው)? የባህር መውጫ በር ሳይኖር የአቶ መለስ ዜናዊ የአእምሮ ልጅ እየተባለ ሌት ከቀን የሚደሰኮርለት “የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ“ በአሁኑ ጊዜ በመጀመሪያው ማርሽ ላይ ተቀርቅሮ ጎማው በሙስና እና በመልካም አስተዳደር እጦት ማጥ ውስጥ ሰምጦ በመሽከርከር ላይ ይገኛል፡፡

የግብጾች ውክልናነት፣ የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ባለሙያዎች “ለዓለም ወንዞች ጤንነት እና ለዓለም አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ቡድን የሚታገል የዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ ድርጅት በመምሰል በደብቅ የግብጽ የውክልና ጥቅም አራማጅ ሆኖ ተገኝቷል!!” በማለት በዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ መረብ ላይ ክስ አቅርበውበታል፡፡ ለመሆኑ እ.ኤ.አ በ2006 በሶማሌ የውክልና ጦርነት አካሂዶ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ሶማሌያውያንን ለሞት የዳረገ እና በመቶ ሺዎች በሚቆጠሩት ላይ ደግሞ ጫና በመፍጠር እንዲፈናቀሉ ያደረገ ማን ነው? እ.ኤ.አ በሜይ 2007 አቶ መለስ ከአልጀዚራ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዲህ ብለው ነበር፣ “በሶማሌ ለዩናይትድ ስቴትስ ብለን የውክልና ጦርነት አላካሄድንም፡፡ ቢሆንም ግን ዩናይትድ ስቴትስ በእኛ ጣልቃገብነት በጣም ጥርጣሬ ነበራት፡፡ በእርግጥ ጣልቃመግባታችን ከተረጋገጥ በኋላ ዩናይትድ ስቴትስ እና አብዛኛው የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ደጋፊ ሆኖ ነበር…“ ሆኖም ግን እ.ኤ.አ በጁን 2006 በዊኪሊክስ የተለቀቀው መረጃ ከዚህ መግለጫ ተጻራሪ ነበር፡፡

ውድ የሆኑ የቅንጦት ወጨዎች በኢትዮጵያ!

በግድቡ ክርክር ዙሪያ ያለው ትልቁ ችግር እውቅና በሌላቸው፣ በስምየለሽ እና በህሊና የለሽ “ባለሙያዎች” እርባናየለሽ ንግግር፣ እና በፍጥነት እየተነጋገሩ የመንተባተብ ጉዳይ አይደለም፡፡ ጉዳዩ የጅብ ዓይነት ስብዕና ያላቸው እና የእባብ ዓይነት የአመራር ጥራት ዘይቤ ያላቸው መሰሪ መሪዎች እንኳ አይደለም፡፡ በኢትዮጵያ ያለው ትልቁ ችግር በጣም ውድ የሆኑ የቅንጦት ወጭዎችን ምን ማድረግ እንዳለብን ከማወቁ ላይ ነው፡፡ “የቅንጦት ወጭዎች” ለሚለው ሀረግ ተመሳሳይ ትርጉም ብክነት ያለባቸው ፕሮጀክቶች ናቸው፡፡ “እነዚህ ፕጀክቶች ጠቃሚዎች ሲሆኑ ባለቤቶቻቸው ግን የማይቆጣጠሯቸው እና ወጪያቸው (በተለይም የአስተዳደር ወጭዎች) ከሚያስገኙት ጠቀሜታ ወይም ዋጋ በላይ ነው፡፡“

በአፍሪካ የግድብ ፕሮጀክቶች በእርግጠኝነት “ውድ የሆኑ ወጨዎች” የሚፈስሱባቸው ናቸው፡፡ የአፍሪካ “ትልልቅ መሪዎች” ታላላቅ ፕሮጅክቶችን መገንባት ይወዳሉ፡፡ ክዋሜ ንክሩማህ በወቅቱ በጋና የኢኮኖሚ ልማት ዕቅድ ላይ ትልቁ ብቸኛ ኢንቨስትመንት ተብሎ በቮልታ ወንዝ ላይ የአኮሶንቦን ግድብ ገንብተዋል፡፡ ግድቡ ላለፉት በርካታ አስርት ዓመታት በአካባቢው ስነምህዳር ላይ ያስከተለው አሉታዊ ተጽዕኖ ተመዝግቧል፡፡ ሞቡቱ ሴሴኮ ከንክሩማህ የተሻለ በአፍሪካ በዴሞክራቲክ ሬፐብሊክ ኮንጎ (ዛየር) በዓለም ላይ ታላቁ በሆነው በኢንጋ ፏፏቴ ላይ ታላቅ ግድብ ገንብተዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ2011 የዴሞክራቲክ ኮንጎ ብሄራዊ የኤሌክትሪክ ኩባንያ ጠቅላላ ቦርድ በተከታታይ እና በተደጋጋሚ የኃይል እጥረት መቋረጥ ምክንያት ከስራ ተባረዋል፡፡ ባለፈው ወር ለኢንጋ የኃይድሮ ኤሌክትሪክ ግድብ ፕሮጀክት ማስፋፊያ የዓለም ባንክ 73 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለዲሞክራቲክ ኮንጎ እርዳታ ሰጥቷል፡፡

በአይቬሪ ኮስት ፌይሌክስ ቦኒ በዓለም ላይ ታላቁን ቤተክርስቲያን በ300 ሚለዮን የአሜሪካ ዶላር በባሲሊካ ያማሳውክሮ የሰላም ወይዘሮ ገንብተዋል፡፡ ህንጻው በአሁኑ ጊዜ ባዶውን ተገትሯል፡፡ እራሳቸውን በስልጣን መንበር ላይ ቁጢጥ ያደረጉት የማዕከላዊ አፍሪካ ሬፐብሊክ ንጉስ የነበሩት ጂን በደል ቦካሳ በሚሊዮን የሚቆጠሩት ዜጎቻቸው በርኃብ እየረገፉ ባለበት አሳሳቢ ሁኔታ ባለ 500 ክፍል ዓለም አቀፋዊ ሆቴል በመቶ ሚሊዮን ዶላሮች ገንብተዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ልክ የሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ወንጀል ከተፈጸመ ከ20 ዓመታት በኋላ የመካከለኛው አፍሪካ ሬፐብሊክ “የጎሳ-ኃይማኖት ማጽዳት” እየተባለ በሚገለጸው በተለያዩ የማህበረሰብ እና የኃይማኖት ቡድኖች መካከል አካላዊ ማሰቃየትና ግድያ እየተፈጸመ ነው ያለው፡፡ ሞአማር ጋዳፊ በዓለም ላይ ታላቅ የመስኖ ፕሮጀክት እየተባለ በሚጠራው እና “በዓለም ላይ ከአስደናቂ ነገሮች በስምንተኛ ደረጃ” ላይ የሚገኘውን በሊቢያ ታላቁን ሰው ሸራሽ ወንዝ ጀምረው ተግባራዊ አድርገዋል፡፡ የኡጋንዳው አምባገነን መሪ ዮሪሙሴቬኒ እ.ኤ.አ በ2012 የግንባታ ስራው የተጠናቀቀውን የቡጃጋሊን ግድብ ገንብተዋል፡፡ የዚህ ግድብ ውኃ ከግድቡ ወደ ኋላ በመፍሰሱ ምክንያት በጣም ትልቅ የሆነ የሚታረስ መሬት በግዳጅ ወደዚህ ቦታ መጥተው የሰፈሩ ብዙ ሰፋሪ ሰዎችን ቦታ በሙሉ እንዲሰምጥ አድርጎታል፡፡

የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ (ቅንጦት) ግድብ (ወይም የአቶ መለስ ዜናዊ መታሰቢያ  ግድብ) ከንቱነት  

የኢትዮጵያ “ታላቁ የህዳሴ ግድብ” የኢትዮጵያ የቅንጦት ወጨዎች የሞፈጸሙበት ነውን? አለትርጥር ነው! “ኢትዮጵያ፡ በናይል የውኃ ጦርነቶች ጉምጉምታ?” በሚለው ትችቴ የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ/የአቶ መለስ ዜናዊ መታሰቢያ ግድብ ማንም በግልጽ እና በትክክል ለመናገር የማይፈልገው የቅንጦት ወጭ ነው በማለት ሞግቸ ነበር፡፡ አቶ መለስ እንዳለፉት ቀደምት የአፍሪካ አምባገነኖች ትልቅ የመሆን ምናብ ውስጥ ገብተው ይሰቃዩ ነበር፡፡ እንደሌሎች ወንድም የአፍሪካ አምባገነኖች አቶ መለስ ታላቁን ፕሮጀክት በመተግበር የአፍሪካ “ታላቁ መሪ” የሚል የማይሞት ዘላለማዊ ስም መያዝ ይፈልጉ ነበር፡፡ ውድ የሆኑ ወጨዎችን የሚያስከትሉ ፕሮጀክቶችን በመገንባት አቶ መለስ ታላቅነትን እና ዕድልን መቀዳጀት እንዲሁም ሞተውም ቢሆን ዘላለማዊ ስም ይፈልጉ ነበር፡፡ ሆኖም ግን በትክክል የተገበሩት ነገር ቢኖር በህይወት በነበሩበት ጊዙ ብዙሀንን ማዋረድ እና በህይወት ከተለዩ በኋላ ያው መሆኑ ነው፡፡ በእርግጠኝነት በአፍሪካ በትልቅነቱ የሚታወቀው እና 1870 ሜጋ ዋት በማመንጨት በአፍርካ ታላቁ የኃይድሮኤሌክትሪክ ግድብ እየተባለ የሚጠራው የግልገል ጊቤ ሶስት ግድብ ግንባታን ለኮንትራክተሮች በሚሰጡበት ጊዜ የማይሞት ስም ለመትከል በማሰብ አጠቃላይ የስራ ሂደቱን ይከልሱ ነበር፡፡

እንደሌሎች የአፍሪካ የቅንጦት ወጭዎች ሁሉ የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ እየተባለ የሚጠራው እዩልኝ-እመኑልኝ ፕሮጀክት ዋና ዓላማው ከሞቱ በኋላም አቶ መለስን አግዝፎ ለማሳየት እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ክብር እንዲሰጣቸው ለማድረግ እንዲሁም በህይወት በነበሩበት ጊዜ የእራሳቸውን አገዛዝ እየመደመደ ከበላው ስር የሰደደ ሙስና የህዝቡን ቀልብ ለማስቀየስ የነበረ ለመሆኑ “በአትዮጵያ ሙስናን መመርመር” በሚል ርዕስ የዓለም ባንክ በባለ 448 ገጽ ባወጣው ዘገባ ይፋ አድርጓል፡፡ አቶ መለስ በደም የጨቀዩ እጆቻቸውን እና ጨካኝ አምባገነንነታቸውን ታላላቅ ፐሮጀክቶችን በመገንባት በአገሪቱ እድገት እና ልማት እንዳለ አድርጎ ለማቅረብ ይፈልጋሉ፡፡ አቶ መለስ  በናፖሊዮን ግራ አጋቢ አካሄድ ትንሹ የአፍሪካ “ታላቅ መሪ” ነበሩ፡፡ አቶ መለስ ግራ መጋባቱን ኢኮኖሚው ከ11-15 በመቶ ዓመታዊ እድገት አስመዘገበ በማለት እና የታላቁ ግድብ የመሰረተ ልማት ፋሲሊቲዎች እንደተሟሉ በማስመሰል  አስፈሪ የውሸት ሸፍጥ በመደርደር ማታለልን ይፈልጋሉ፡፡

በኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብባለሙያዎችየጭቃ ጅራፍ መደነቅ፣

የገዥው አካል ታማኝ አእምሮ ከጨለማ ሆኖ ባልሰለጠነ መልኩ እየተወዛወዘ መታየቱ የሚያስደንቅ እና ቀልድ ነገር ነው፡፡ በሙሉ ታማኝነት በተላበሰ መልኩ የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ “ባለሙያዎች የከፋይ አለቆቻቸውን ለመከላከል የመውጣታቸውን እውነታ አደንቃለሁ፡፡ ለዚያ ሙሉ መብት አላቸው፡፡ ውሻ የሚመግበውን ሰው እጅ በፍጹም አይነክስም፡፡ ከገዥው አካል ጋር ስምምነት የሌላቸው ደግሞ ለመተቸት ሙሉ መብት አላቸው፡፡ ከገዥው አካል እና ከተወካዮቹ ጋር ግልጽ፣ የሰለጠነ እና በውል የተዘጋጀ የክርክር መድረክ ተዘጋጅቶ በሁሉም ጉዳዮች ላይ መወያየት ትልቅ ነገር ነው፡፡ ሆኖም ግን ገዥው አካል የክርክር መድረኩን ከእውነት አይደግፈውም፡፡ ተቀናቃኞቹን እና ትችት የሚያቀርቡበትን ቡድኖች በተራ ጥላቻ እና በጭቃ ላይ ትግል የማድረግ ጨዋታ እንዲጠመዱ ይፈልጋል፡፡ እራሳችንን በወረዱ ተግባራት ላይ አናሰማራም፡፡ እራሳቸውን ከፍ አድርገው ወደ አደባባይ በመውጣት ከህዝብ ፊት ቅበው ፊት ለፊት ለመወያየት ይቃወማሉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ያለው ማንም አሸናፊ የማይሆንበት ሁኔታ ይኸው ነው!

የህዝቡን ፍላጎት ለማርካት የኢትዮጵያን የውኃ ሀብት በአግባቡ በስራ ላይ መዋል አለበት የሚለውን ሀሳብ የሚቃወም ምክንያታዊ ኢትዮጵያዊ/ያት አይኖርም/አትኖርም፡፡ ሆኖም ግን የኢትዮጵያን ዕጣ ፈንታ ለመወሰን ወይም ደግሞ ያሏትን ሀብቶች በአግባቡ ለመጠቀም ገዥው አካል እርሱ እና የእርሱ አጋር ብቻ መሆን እንደሌለባቸው በውል ሊያጤነው ይገባል፡፡ ገዥው አካል የዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ መረብን “ከኃያሉ አምላክ ጋር መገናኘት የሚችለው ታላቁ ቄስ እና ለአካባቢ ስነምህዳር ደህንነት አስፈላጊ ነገሮች ሁሉ የሚወስነው“ በማለት ኢንተርናሽናል ሪቨርስ (የዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ) አንደከሰሰው ሁሉ  “ገዥው አካል እራሱ “ከኃያሉ አምላክ ጋር መገናኘት ከሚችለው ታላቁ ቄስ” ስር ነን በሚል እምነት ተጠምቆ በኢትዮጵያ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና የባህል እድገት ላይ እራሱን ፈላጭ ቆራጭ አድርጎ አሰቀምጧል፡፡ ሁልጊዜ የምለውን ትንሽ አሻሽየ ለማቅረብ “የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ፣ የፖለቲካ፣ እና የባህል እድገትን የብዙሀንነት ስርዓትን በማስፈን ለመወሰን በኢትዮጵያ ላለው “ከኃያሉ አምላክ ጋር መገናኘት ለሚችለው ታላቁ ቄስ“ ገዥ አካል መስበክ ለማያዩ፣ ለማይሰሙ እና  መናገር ለማይችል ዱዳዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ እየጠቀሱ እንደ መስበክ ይቆጠራል፡፡

ጆርጅ በርናንድ ሻው እንዲህ አሉ፣ “ከአሳማ ጋር በፍጹም ጭቃ ዉስጥ ትግል አትግጠም፡፡ ሁለታችሁም ቆሻሻ ትሆናላችሁ፡፡ አሳማው ግን ይንን ድርጊት ይወደዋል፡፡“ ገዥው አካል የዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃን ስቦ ወደ ጭቃ ማብክዋት ጨዋታ  ውስጥ ለማስገባት በሚያደርገው ጥረት የምደነቅ ብሆንም የዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ ግብዣውን ንቆ ለጭቃ ልፊያ የገዥውን የጭቃ ማጥ አልቀበልም በማለቱ በጣም ተደስቻለሁ፡፡ የዓለም አቀፉ ወንዞች ጥበቃ ላለፉት ሶስት አስርት ዓመታት ላስመዘገባቸው ዓለም አቀፍ ስኬቶች ሊኮራ ይገባል፡፡ እስከ አሁን ሲያከናውኗቸው የነበሩትን ተግባራት፡ ለቋሚ በአንድ አካባቢ ለበርካታ ዓመታት በቋሚነት ለኖሩ ህዝቦች መብት መጠብቅ፣ ዓለም አቀፍ ወንዞችን በመንከባከብ፣ እና የተራውን ህዝብ እና የፖሊሲ አውጭዎችን እንዲሁም  ዓለምን ህዝብ ልብ እና አእምሮ በመቆጣጠር በተጠናከረ መልኩ ሊቀጥሉባቸው ይገባል፡፡

የዓለም አቀፉ ወንዞች ጥበቃ “ከኃያሉ አምላክ ጋር መገናኘት የሚችል ታላቁ ቄስ እና ለአካባቢ ስነምህዳር ደህንነት አስፈላጊ ነገሮች ሁሉ ለዓለም የሚወስን“ ድርጅት አይደለም፡፡ ሆኖም ግን ለአምላክ ምስጋና ይግባው እና ለአካባቢ ስነምህዳር ፍትሀዊ አጠቃቀም በሰው እና በአምላክ ፊት የሚናገር እና የሚጮህ የዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ ድርጅት ኖረ፡፡ ገዥው አካል እና ውሾቹ ስለግድብ የውሀ ጦርነት በተከታታይ በማንሳት የዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃን ወደ ሌላ ዙር የጭቃ ትግል ጨዋታ ለመጋበዝ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ሌላ ድጋሚ ክብሪት እንደሚጭሩ ምንም የሚያጠራጥር ጉዳይ አይደለም፡፡ ለዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ የምሰጠው ብቸኛ ምክሬ፡ “ወንዞቹን መጠበቅ ጠበቅ አድርጉ፣ እራስን የሚያዋርድ ተራ ነገረን ለባለሙያዎቹ ተውት!”

የዓለም አቀፍ ወንዞች ጥበቃ በኦሞ ወንዝ ሸለቆ ለኢትዮያውያን/ት መብት መከበር በመናገራችሁ እና በጽናት በመቆማችለሁ አመሰግናለሁ!

ይቀጥላል

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

ሚያዝያ 14 ቀን 2006 .

Similar Posts

Leave a Reply