ኢትዮጵያ፣ የመንቀሳቀስ ነጻነት የተገደበባት አገር

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም ከነጻነት ለሀገሬ

ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያው ገዥ አስተዳደር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስራ ፍለጋ ወደ ውጭ አገር በሚሰደዱት ኢትዮጵያውያን/ት ላይ እገዳ በመጣል የሚከተለውን አውጇል፤

“ስራ ፍለጋ በሚል አገር ጥለው በሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮያውያት ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ የመጣውን የጉልበት ብዝበዛና የውርደት ማዕበል ለማስቆም ሲባል ለስራ በሚል ሰበብ ወደ ውጭ አገር በኢትዮጵያውያን/ት በሚደረግ ጉዞ ላይ ላልተወሰነ ጊዜ እገዳ ተደርጓል፡፡ ጊዚያዊ እገዳው የተጣለው ስራ ፍለጋ በሚል ወደ ውጭ አገር በሚሄዱ  ዜጎች ላይ የሚደረገውን ውርደት ከዚህም አልፎ  ብዙ ኢትዮጵያውያን/ት ላይ የሚፈጸመውን አሰቃቂ ግድያ ለማስቆም ሲባል ነው፡፡ ጊዚያዊ እገዳው ውጭ አገር ሄዶ ስራ ለመቀጠር የሚያሰችሉት ተቋማዊ፣ አስተዳደራዊ እና ህጋዊ ክፍተቶች ምላሽ እስኪያገኙ ድረስ ተፈጻሚነት ይኖረዋል፡፡ እነዚህ እርምጃዎች አስፈላጊ ሆነው ተገኝተዋል፣ ምክንያቱም የዜጎቹን ውጭ አገር ሄዶ የመስራት መብት ለማስከበር ሲል የኢትዮጵያ መንግስት ከዚህ ቀደም ሲያደርግ የቆየው ጥረት ስኬታማ ሳይሆን በመቅረቱ ነው፡፡ ለዜጎቹ ምቹ የስራ ሁኔታን ማረጋገጥ የመንግስት አንዱ ዋና ተግባሩ ሆኖ ይቀጥላል፡፡ ጊዚያዊ እገዳው ለስራ ወደ ውጭ አገር የሚደረገውን ጉዞና በአገር ውስጥ ባሉ የውጭ የስራ አስቀጣሪ ኤጄንሲዎች ላይ ስራቸውን እንዳይቀጥሉ የተጣለው እቀባ ወደፊት ወደ ውጭ አገር ሄደው ለመስራት የሚያስቡ ኢትዮጵያውያንን/ትን የስራ ሁኔታ በማሻሻል ቀልጣፋ ያደርገዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡”

“በውጭ አገር ለስራ ፍለጋ በሚደረግ ጉዞ ላይ እገዳ/እቀባ ማድረግ ህገመንግስታዊ” ነውን? ገዥው አስተዳደር የኢትዮጵያውያንን/ትን የጉልበት ብዝበዛና ብዙዎችንም ከአሰቃቂ ሞት ለማዳን በሚል ምክንያት “የመንቀሳቀስ መብትን ለማገድ“ ህገመንግስታዊ ስልጣን አለውን? ለሁለቱም ጥያቄዎች መልሱ በማያሻማ መልኩ በፍጹም አይችልም! የሚል ነው፡፡

“የመንቀሳቀስ መብት“ ለኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች በሁለት ምክንያቶች ህገመንግስታዊ መብት በመሆኑ ይህንን የአሁኑን ትችት እንዳዘጋጅ ተገድጃለሁ፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ቀደም ሲል በነበረኝ ስጋትና ገዥው አስተዳደር ያራምድ በነበረው የግዳጅ ማፈናቀልና ከሚኖሩበት አካባቢ ማባረር የተሳሳተ ፖሊሲ መሰረት (ይህም ማለት የኢትዮጵያ ዜጎችን ለመኖሪያነትና ሰርቶ ለመኖር ከመረጡት አካባቢ ገዥው አስተዳደር “ክልል“ (“ራሳቸውን የቻሉ አካባቢያዊ መንግስታት“] እያለ ወደሚጠራቸውው “ወደተወለዱባቸው አካባቢዎች“ ተመልሰው እንዲሄዱ በግዳጅ በማፈናቀሉ ወይም በማባረሩ ምክንያት) ጠንካራ ትችት በተከታታይ ሳቀርብ ነበር፡፡ በዚህ ዓመት ባለፈው ሚያዝያ ወር ታዋቂው የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራርና የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የሩዋንዳን የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ባቃቤ ህገነት የመሩት ፕሮፌሰር ያዕቆብ ኃ/ማርያም ይህንን ጉዳይ በማስመልከት “የአማራ ጎሳ ተወላጅ የሆኑትን ዜጎች ከቤንሻንጉል ጉሙዝ (በኢትዮጵያ ከሚገኙ ዘጠኝ ክልሎች አንዱ) በኃይል ማባረር የዘር ማጽዳት ዘመቻ ነው“ በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ “አንድ ዓይነት ቋንቋ በመናገራቸው ምክንያት ህዝቦችን ከሚኖሩበት አካባቢ በኃይል ማፈናቀል/ማባረር አካባቢያዊ አለመረጋጋትን ከመፍጠሩም በላይ በተጨባጭ ማስረጃ ተደግፎ ለተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት በቀረቡት ወንጀሎች ላይ ምርመራ እንዲያደርግ የዓለም አቀፉን የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ሊያዝዝ ይችላል፡፡” በማለት አስተያየታቸውን አጠቃለዋል፡፡

በብዙ ክልሎች ማለትም በጋምቤላ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ኦሮሚያ፣ ሶማሊ/ኦጋዴን እና በደቡብ ክልል በቤንች ማጂ ዞን በጉዳ ፈርዳ ወረዳ የተከናወኑት ማፈናቀሎች/የማባረር ድርጊቶች በበቂና በታመኑ የዓይን ምስክሮች እንዲሁም በጉዳቱ ሰለባዎች የተሰጡ የምስክርነት ቃሎች የገዥውን አስተዳደር አረመኒያዊ የማፈናቀል/የማባረር ፖሊሲ ባህሪ ከብዙ በጥቂቱ በገሀድ ያመላክታሉ፡፡ በቅርቡ በህይወት በተለዩት በገዥው አስተዳደር መሪ አስፈጻሚነት “የምስራቅ ጎጃም አማራ ሰፋሪዎች” በመባል የሚጠሩትን ከደቡብ ክልል ቤንች ማጂ ዞን ከጉራ ፈርዳ ወረዳ በኃይል መባረር በማስመልከት ህዝብ እንዲያውቀው ማድረጌ የሚታወስ ነው፡፡ የአገዛዙን ወንጀለኛነት በማስመልከት በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የሮማ ስምምነት አንቀጽ 7(1)(d) መሰረት “ህዝቦችን ማባረር ወይም በኃይል ማፈናቀል” የሚለውን በመውሰድ በእራሴ አባባል “የአማራ ሰፋሪዎችን ከሚኖሩበት በኃይል ማፈናቀል/ማባረር የፌደራል ስርዓቱ ሆን ብሎና በተቀነባበረ የዘር ፌዴራል ፖሊሲ የአንዱን የሲቪል ጎሳ ዘር በማስወገድ ሌላውን በደቡብ ኢትዮጵያ ያለውን ጎሳ ገዥነት በማረጋገጥ ሌሎችን ጎሳዎች ለአደጋ በማጋለጥ የዘር ማጽዳት የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ያነጣጠረ ይመስላል“ ብየዋለሁ፡፡

ሁለተኛ ገዥው አካል ሆን ብሎ አውቆ እንዳላወቀ ወይም ሳያውቅ በድንቁርና የህገመንግስቱን ድክመት በመጠቀም በቅርቡ ለስራ ፍለጋ ወደ ውጭ አገር በሚደረግ ጉዞ ላይ የጣለው እገዳ በጣም እንቆቅልሽ ሆኖብኛል፡፡ በቦታ ውሱንነት ምክንያት (አዎ፣ በሹክሹክታ ሰምቸዋለሁ የእኔ ትችቶች በጣም ረዣዥሞች ናቸው፣ ቢሆንም ግን “አጭር አነጋገር  የብልህነት ህይወት ነው“ ሸክስፒር እንዳለው፣ ግን ደግሞ ለአጭርነት ሲባል የነገሩን ዳህራ መስዕዋት ማድረግ ለእኔ ጉብዝና አይደለም)፣ አሁን ሁለተኛውን ጉዳይ ለማብራራት እሞክራለሁ፣ ሆኖም ግን አስገድዶ ማባረር/ማፈናቀል እና የዘር ማጽዳት የሚለውን ጉዳይ ለሌላ ጊዜ አስተላልፊያለሁ፡፡

ከቦታ ቦታ የመዘዋወርና የጉዞ ነጻነት የኢትዮጵያውያን ህገመንግስታዊ መብት፣

አንቀጽ 32 (“ከቦታ ቦታ የመዘዋወር ነጻነት”) ለኢትዮጵያውያን ዜጎች ያልተገደበ ነጻነትን ያጎናጽፋል፡፡ “(1) ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወይም የውጭ ዜጋ በሀገሪቱ የወሰን ክልል ውስጥ በመረጠው ቦታ የመኖርና ከቦታ ቦታ የመዘዋወር ነጻነት አለው፣ እንዲሁም በፈለገው ጊዜ ከሀገር የመውጣት መብት አለው” በሚል ተደንግጓል፡፡ ይህ “የመዘዋወር ነጻነት“ ኢትዮጵያ ወድዳ በፈረመቻቸው ሁለት አስገዳጅ/ቀያጅ ዓለም አቀፍ ስምምምነቶች የበለጠ ጠብቋል፣ ተጠናክሯልም፡፡ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌ (UDHR) በኢትዮጵያ ህገመንግስት አንቀጽ (13)(2) ስር በግልጽ እንደተቀመጠው፣ “በዚህ ምዕራፍ በግልጽ የተቀመጡት መሰረታዊ መብቶችና ነጻነቶች፣ በተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌ መርሆዎች እና በተባበሩት መንግስታት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ስምምነቶችና ዓለም አቀፍ መሳሪያዎች/instruments በኢትዮጵያ መንግስት እንዳለ ተወስደው ከእነዚህ ድንጋጌዎች አንጻር በተጣጣመ መልኩ የተተረጎሙ ናቸው” በተመሳሳይ መልኩ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌ አንቀጽ 13 አንዲህ ይላል፣ “(1) እያንዳንዱ ዜጋ በሀገሩ ግዛት የወሰን ክልል ውስጥ በመረጠው ቦታ የመዘዋወርና የመኖር ነጻነት አለው፣ (2) እያንዳንዱ ዜጋ ወደየትኛውም አገር የእራሱን ጨምሮ የመሄድና ወደአገሩም የመመለስ መብት አለው”፣ የዓለም አቀፉ የሲቪልና የፖለቲለካ መብቶች ስምምነት በአንቀጽ 12 በግልጽ እንዳስቀመጠው  በንኡስ አንቀጽ 3 ስር ለአገር ደህንነትና ለህዝብ አስተዳደር ሲባል ከተቀመጡት በስተቀር በሌላው መልኩ ከተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌ ጋር በአንድ ዓይነት ቋንቋ የተካተቱ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ህገመንግስት በአንቀጽ 9 (“የህገመንግስቱ የበላይነት“)፣ “(1) ህገመንግስቱ የአገሪቱ የበላይ ህግ ነው፣ ማንኛውም ህግ፣ ልማዳዊ አሰራር ወይም የአንድ መንግስታዊ አካል  ወይም የህዝብ ባለስልጣን ውሳኔ ሕገመንግስቱን የሚጻረር ከሆነ ተፈታሚነት አይኖረውም፡፡” በማለት በግልጽ አስቀምጦታል፡፡

ገዥው አስተዳደር በኢትዮጵያ ህገመንግስትና በሌሎች ዓለም አቀፍ ሰምምነቶች በግልጽ የተቀመጠውን አንቀጽ 32 በድፍረት ሳይደፈጥጥ በውጭ አገር የቅጥር ጉዞ ላይ እገዳ/ማዕቀብ መጣል ይችላልን?

የአንቀጽ 32 ቋንቋ ግልጽና የማያደናገር ነው፡፡ የቃሎቹን ትክክለኛ ትርጉም ለመረዳት ልዩ የአተረጓጎም እገዛ ወይም የትንታኔ ስልት አያስፈልግም፡፡ አንቀጽ 32 ፍጹም የመንቀሳቀስ ነጻነትን ለማረጋገጥ ጥቅልና ዝርዝር ጉዳዮችን አካትቶ ይዟል፡፡ “ማንኛውም ኢትዮጵያዊ/ት በመረጠው ቦታ የመኖርና የመንቀሳቀስ ነጻነት እንዲሁም በፈለገው ጊዜ ከሀገር የመውጣት መብት አለው“፡፡ ማንኛውም ዜጋ ለመኖር “ከሚመርጠው ቦታ”፣ በሀገር ውስጥ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ለመዘዋወር፣ ወይም ከሀገር ለመውጣት ከመወሰን በፊት ምንም ዓይነት ቅድመ ሁኔታ ማሟላት አይኖርበትም፡፡” ብቸኛ ቅድመ ሁኔታ አለ ቢባል አንኳ ዜጎች ለጉዞም ሆነ ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀስ ያላቸውን ፍላጎት  መግለጽ መቻላቸው ብቻ ነው፡፡

አንቀጽ 32 ዓላማውን ለመተገበር ሲባል ሌላ ተጨማሪ “በህግ እስካልተፈቀደ ድረስ“ የሚል የህግ ድንጋጌ ገላጭ ሀረጎች አያስፈልጉትም፡፡ አንቀጽ 32 ያለምንም ተቀጽላ በእራሱ ተፈታሚነት ያለው አንቀጽ ነው፣ ይህም ማለት በህገመንግስታዊ ድንጋጌ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ሙሉ በሙሉ በእራሱ መተግበር የሚችል አንቀጽ ነው፡፡ በሌላ መተካት፣ መለወጥ፣ ማስተካከል ወይም በዘፈቀደ የህግ ወይም የባለስልጣን ትዕዛዝ ሊታገድ አይችልም፡፡

የገዥው አስተዳደር “በጉዞ ላይ የጣለው እገዳ/ማዕቀብ” በአስገዳጁ አንቀጽ 9 (“የህገመንግስቱ የበላይነት“)፣ “(1) ህገመንግስቱ የአገሪቱ የበላይ ህግ ነው፣ ማንኛውም ህግ፣ ልማዳዊ አሰራር ወይም የአንድ መንግስታዊ አካል  ወይም የህዝብ ባለስልጣን ውሳኔ ሕገመንግስቱን የሚጻረር ከሆነ ተፈታሚነት አይኖረውም፡፡” በሚል አንቀጽ 32ን በድፍረት ለመጨፍለቅ የሚደረግ ጥረት የዜጎች መብት ሊሰረዝ፣ ወይም ጊዚያዊ እገዳ ሊደረግበት ወይም ደግሞ ኢሞራላዊ የሆነ ነገር ሊፈጸምበት አይገባም፡፡ የገዥው አስተዳደር የጉዞ እገዳ በጥልቅ ሊወገዝ እና ህገወጥ ተብሎ በህግ ውድቅ ሊደረግ ይገባል፣ (በዚህ ጉዳይ ላይ ለምን ተገቢው ህገመንግስታዊ ውሳኔ አይሰጠውም ብዬ በይስሙላው ፍርድ ቤት ወይም ደግሞ በተምኔታዊው “የህግ አርቃቂ ኮሚሽን” በአንቀጽ 82 በተቀመጠው መሰረት ቀርቤ በመጻፍ ብዕሬንም አላበለሽ፣ ጊዜዬንም አላጠፋ)፡፡

አስቸጋሪው የኢትዮጵያውያት የቤት ሰራተኞች ዕጣ ፈንታ በባዕዳን አገራት፣ 

ባለፉት ጥቂት ዓመታት በርካታ አትዮጵያውያት የቤት ሰራተኞች በተለያዩ የመካከለኛው ምስራቅ አገሮች በእራሳቸው ፈቃድም ሆነ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር አስፈጻሚ ደላሎች አማካይነት በመሄድ በጣም ዘግናኝ የሆነ ስቃይ እና ኢሰብአዊ ድርጊት የተፈጸመባቸው መሆኑ፣ አሁንም በመሰቃየት ላይ መሆናቸው አጠያያቂ አይደለም፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ እየተደረገ ያለውን ሰብአዊነት የጎደለው የሰራተኛ አያያዝ ከ3 ዓመታት ገደማ በፊት “ከዓለም አቀፋዊ የባሪያ ንግድ ወደ ዓለም አቀፋዊ የቤት ሰራተኝነት ንግድ“ በሚል ርዕስ ትችት ማቅረቤ ይታወሳል፡፡ በአሁኑ ጊዜም ቢሆን በርካታ የቤት ሰራተኛ ሴቶች በመካከለኛው ምስራቅ አገሮች በአሰሪዎቻቸው አስገዳጅ እስራት፣ የጾታ ትንኮሳ፣ የሰሩበትን ምንዳ መቀማትና ኢኮኖሚያዊ ብዝበዛ እንዲሁም በሚኖሩባቸው አገሮች እንደ ህገወጥ መቆጠር እና ሌሎች ለመናገር የሚዘገንኑ ድርጊቶች  ይፈጸሙባቸዋል፡፡ አሁን ያሉበት ሁኔታ “ልብን የሚያደማ ብቻ ሳይሆን ልብን የሚሰብርም” ሆኗል፡፡

ሆኖም ግን የማይገደበውን የአትዮጵያውያት ዜጎችን የመንቀሳቀስ ነጻነት መገደብ በመካከለኛው ምስራቅ አገሮች ያሉትን ኢትዮጵያውያት የቤት ሰራተኞችን ስቃይ መፍታትም ሆነ ብዝበዛውንና ውርደቱንም ሊያቆመው አይችልም፡፡ “ቀደም ሲል በመንግስት ሲደረግ የነበረው ጥረት በውጭ አገር ተቀጥረው የሚሰሩትን ኢትዮጵያውያን/ት መብት አላስከበረም“ በሚለው የፖሊሲ እንደምታ ምክንያታዊነት ሰበብ “ወደ ውጭ አገር ሄዶ ለመስራት በሚደረግ ጉዞ ላይ የተጣለው ጊዚያዊ እገዳ የኢትዮጵያውያን የስራ ሁኔታ መሻሻል ያፋጥናል“ የሚለው አባባል ትርጉም የለሽ እና ከቀረበው ማሳመኛ ጋር የማይገናኝ ተራ ማስመሰያ ነው፡፡ ክርክሩን በመቀጠል “ወደ ውጭ አገር ሄዶ ለመስራት በሚደረግ ጉዞ ላይ የተጣለው ጊዚያዊ እገዳ የኢትዮጵያውያን የስራ ሁኔታ መሻሻል ያፋጥናል“ የሚለው ማሳመኛ “የረጋ ኩሬ ጎርፍን በመፍጠር አካባቢውን ያጥለቀልቃል“ እንደማለት ይቆጠራል፡፡ “የተበዘበዙትና የተዋረዱት ኢትዮጵያውያን/ት“ አሁንም ቢሆን በተለያዩ ሀገሮች እየተበዘበዙና እየተዋረዱ ስላሉ በዚህ ረገድ የተያዘው የፖሊሲ ማሳመኛ ውኃ የሚቋጥር አይደለም፡፡

እውነታው የሚያመላክተው ገዥው አስተዳደር እነዚህ ሰራተኞች ለበርካታ ዓመታት ሲሰቃዩ ምንም ዓይነት እገዛ ለዜጎቹ ሳያደርግ በመቀጠሉ ለተደጋጋሚ ሸንቋጭ ትችቶች ተጋልጦ መቆየቱን ነው፡፡ ስቃይና መከራው በሚደረግባቸው ሀገሮች አካባቢ ያሉት የገዥው አስተዳደር ኤምባሲዎች የእነርሱን እርዳታና ድጋፍ የሚፈልጉትን ኢትዮጵያውያን/ት እያወቁ ጆሯቸውን ደፍነዋል፣ አይናቸውን ሸፍነዋል፣ አፋቸውን ለጉመዋል፡፡

“ጊዚያዊ እገዳው” በአሰቃቂ ሁኔታ ላይ የሚገኙትን በአሁኑ ጊዜ እየተዋረዱና እየተበዘበዙ ያሉትን ኢትዮጵያውያት የቤት ሰራተኞች የማቴሪያል ቁሳቁስ ፍላጎት ያሻሽለው ይሆን? አያሻሽለውም! የእነዚህን በዝባዥ ቀጣሪዎች የፍርድ ሂደት ያፋጥነው ይሆን? አያፋጥነውም! ጊዚያዊ እገዳው በኢትዮጵያና በቀጣሪ አገሮች ወንጀለኞችና እና በእነሱ ጠባቂዎች  የሚፈጸሙትን ህገወጥ የስራ ዝውውሮች እና የግዳጅ ጉልበትን ያስቀር ይሆን? አያስቀርም! ጊዚያዊ እገዳው ለቀጣሪው አገር እንደዚህ ያለውን የጉልበት ብዝበዛ እንዲቀጥልና ለሰራተኞች የሚደረገውን ዝቅተኛ የህግ ጥበቃ እንዳያደርግ የደርድር ስምምነት ያሰገኝለት ይሆን? አያስገኝለትም! ማለት የሚቻለው ጊዚያዊ እገዳው ገዥው አስተዳደር ለበርካታ ዓመታት በዜጎቹ ላይ ሲፈጸም የቆየውን ግፍ በዝምታ ሲመለከተው ስለነበር ለዚያ ማባበያ የዲፐሎማሲ ስራ መሆኑ ነው፡፡ ይህ የአሁኑ የገዥው አስተዳደር ሽር ጉድ ማለት ተልዕኮው ለስራ በመካከለኛው ምስራቅ ያሉ ሰራተኛ ዜጎቹ እራሳቸውን በመግደል፣ በሌላ ሰው ሲገደሉ እና ብዝበዛ ሲካሄድባቸው ምንም ሳያደርግ ስለቆየ ለዚህ በተዘየደ በልሀት የህዝብን የትኩረት  አቅጣጫ ለማስቀየር ነው፡፡

በውጭ ላሉ ኢትዮጵያውያት የቤት ሰራተኞች የሚደረግ ጥበቃ አስፈላጊነት፣

በሰደት ባሉ የቤት ሰራተኞች ላይ የሚደረገው ማዋረድና ብዝብዛ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ከሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች አንዱ መሆኑን አምናለሁ፡፡ በመካከለኛው ምስራቅና በሌሎች አገሮች ተሰራጭተው የሚገኙት ወደ 150 ሺ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያት የቤት ሰራተኞች በዓለም ላይ ከሚገኙት የሰብአዊ መብት ረገጣ እና ብዝበዛ ከሚፈጸምባቸው በሚሊዮን የሚቆጠሩ የቤት ሰራተኞች መካከል የሚደመሩ ናቸው፡፡ ሆኖም ግን ዝምታን እና ከድርጊት ከተቆጠበው የኢትዮጵያ ገዥ በተቃራኒ ሌሎች በህጋዊ ምርጫ የተመረጡ መንግስታት እንደዚህ ያለ ተመሳሳይ ሁኔታ በዜጎቻቸው ላይ ሲፈጸም ለችግሩ መፍትሄ በመስጥት አዎንታዊ እርምጃ ይወስዳሉ፡፡

በአትዮጵያ ያለው ገዥ አስተዳደር በኢትዮጵያ ስደተኛ ዜጎቹ ላይ እየጨመረ የመጣውን የብዝበዛ ማዕበልና ውርደት ለማስቆም ትኩረት አሰጣለሁ ካለ የማስመሰል ድርጊቱን ትቶ ከዚህ አልፎ በመሄድ በትክክለኛው መንገድ ለድርጊቱ ተመጣጣኝ የሆኑ እርምጃዎችን በሙሉ እምነት ሊወስድ ግድ ይላል፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ገዥው አስተዳደር በዓለም አቀፍ የሰራተኛ ድርጅት (ILO) ለሰራ ፍለጋ ስደት የሚለውን ስምምነት (የተሸሻለውን)፣ 1949 (ቁጥር 97) መፈረም ይገባዋል፡፡ያ ስምምነት ስለህጉ ዝርዝር አፈጻጸም ስዕል ይሰጣል፣ እንዲሁም ለእንደነዚህ ያሉ ሰራተኞች ጠንካራ ጥበቃ በማድረግ በቀጣሪዎችና በሰራተኞች መካከል ለስራ የተደረጉ ስምምኖተችን ይገመግማል፡፡ ሁለተኛ ገዥው አስተዳደር የተባበሩት መንግስታት ስምምነትን የስደተኛ ሰራተኞችና ቤተሰቦቻቸውን መብት የሚያስጠብቀውን ሰነድ መፈረም አለበት፡፡ ያ ስምምነት ከሁሉም በላይ ይህን መብት ያጎናጽፋል፣ “ማንም ስደተኛ ወይም የቤተሰብ አባል ምንም አይነት ስቃይ ወይም ጭካኔ ወይም ኢሰብአዊ ወይም የሚያዋርድ አያያዝ ወይም ቅጣት አይፈጸምበትም” የዚህ ስምምነት ዝርዝሮች እየተቆጠሩ በገዥው አስተዳደር በቀጣሪው አገር በስደተኞች ፕሮግራም ስምምነት መገባት አለበት፡፡

ሶስተኛ ገዥው አስተዳደደር ብዙ ዜጎቻቸውን ለስራ ወደ ውጭ አገር ከሚያሰማሩ አገራት ልምዶች፣ ፖሊሲዎች እና ህጎች ምቹ አጋጣሚዎችን በመጠቀም መማር ይኖርበታል፡፡ እዚህ ላይ “መማር” የሚለውን ቃል ለምክር ተጠቅሜበታሁ፡፡ እዚህ ላይ መማር ሲባል የሌሎችን አገሮች ህጎችና ፖሊሲዎች ያምንም ማገናዘብ በድፍረት እንዳለ መቁረጥና መለጠፍ ማለቴ አይደለም፡፡ በዚህ ወቅት በቅርቡ በህይወት የተለዩት መሪ እ.ኤ.አ በፌብሯሪ በ2012 የጸረ ሽብር ህጉን አስመልክተው የሌሎችን አገሮች ሰነድ እንዳለ በመኮረጅ ዘርፈው እና አዋህደው ለፓራላማው ያቀረቡት ዲስኩር አስደንጋጭና አሳፋሪ ነበር፡፡ ሙሉ ቃሉም እንዲህ ይነበባል፣ “ የጸረ-ሽብር ህጉን ለማርቀቅ በዓለም ላይ ያሉ  ተሞክሮዎችን ቃል በቃል ገልብጠናል፣ ከአሜሪካ፣ ከእንግሊዝ እና ከአውሮፓ የጸረ-ሽብር ህጎችን ሞዴል አድርገን ወስደናል… ምክንያቱም ልምዱ አላቸው፣ ከእነዚህ አገሮች ልምድ ብንወስድ ምንም ክፋት የለውም፣ ከጥሩ መምህር መማር ጠቃሚ እንጅ ጎጂ አይደለም፣ ለዚህ የሚያሳፍር ነገር የለውም፣ የጸረ ሽብር ህጋችን ምንም ዓይነት ችግር የለበትም፣ በዓለም ላይ ካሉ ምርጥ ከተባሉ የጸረ-ሽብር ህጎች የተሻለ ነው፣ ነግር ግን ከማናቸውም ቢሆን ያነሰ አይደለም…”  በእርግጥ ምንም ዓይነት የጸረ-ሽብር ህግ ረቂቅ ህግ አልነበረም፣ እንዳለ ቃል በቃል ከሌሎች አገሮች ያጸረ-ሽብር ኅጎች የተገለበጠ (የተዘረፈ)  እንጂ፡፡ አይን ባወጣ መልኩ የተቆረጠና የተለጠፈ ተግባር ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በዚህ አሳፋ ህግ እና ህግና ፖሊሲ የቃላት ድርደራና የዓረፍተ ነገር መሰካካት እንዲሁም በአንቀጾች መለያየት በሚመስላቸው ደንቆሮዎች ለእስር ተዳርገው በመማቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡

ቀላሉ የእኔ አስተያየት ገዥው አስተዳደር ሌሎች አገሮች የስደተኛ ዜጎቻቸውን መብት ለማስከበር ሲሉ ያዘጋጇቸውን ፖሊሲዎች ማጥናት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የስደተኛ ዜጎቻቸውን ሰብአዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶቻቸውን ለማስከበር ሲል የፊሊፒንስ መንገስት ካዘጋጃቸው ህጎችና ፖሊዎች ብዙ ትምህርት ሊቀሰምባቸው የሚቸሉ ጉዳዮች እንዳሉ አምናለሁ፡፡ እ.ኤ.አ በ1982 የፊሊፒንስ መንግስት የውጭ ስራ አስተዳደር የሚል ተቋም መሰረተ፡፡ የተቋሙ መሰረታዊ ዓላማ በውጭ አገር የሚሰሩ የፊሊፒንስን ሰራተኞች የስራ ሁኔታ ከፍ ለማድረግና ለመከታተል፡፡ እ.ኤ.አ በ1995 የፊሊፒንስ ሰራተኞችና ቤተሰቦቻቸው ላይ የታየውን ቸግር ለመቅረፍ ድርጅቱ ወደ ከፍተኛ ደረጃ ከፍ ያለ የኑሮ ሁኔታን ለማምጣትና መብቶቻቸውን ለማስተበቅ በርትቶ ሰርቶል፡፡ ይህ ህግ በ2009 ተሻሻለ በሪፑበሊክ አክት 10022 የፈሊፒንስን ሀሳብ በማጠናከር የፊሊፒንስ ስደተኛ ዜጎች መብት በሚከበርባቸው አገሮች ብቻ ለስራ መሄድ እንዳለባቸው ተደነገገ፡፡ የእነዚህ ሰራተኞች መብቶች መከበራቸውን ለማረጋገጥ የፊሊፒንስ መንግስት ቀጣሪ አገሮች የሰረታኛ ዜጎቻቸውን የጉልበትና ማህበራዊ ህጎችን መብት እንዲያከብሩ እንዲያጸድቁት ወይም ብዙ ስምምነቶችን፣ አዋጆችን ወይም ወሳኔዎችን ለመፈጸም ነበር፡፡ በ2011 በሪፑበሊክ አክት ቁጥር 10022 መንግስት የፊሊፒንስ ዜጎች ለስራ የማይሄዱባቸውን አገሮች ዝርዝር አወጣ፡፡ ይህም ቀጣሪ አገሮች በተለያየ መልኩ የዜጎችን መብት ለማስከበር የተዘጋጁትን ህጎች ባለማተታቸው ነበር፡፡ የፊሊፒንስ ሰራተና ዜጎች እንዳይሄዱባቸው በዝዝር ከተያዙት አገሮች ውስጥ ሳውዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ ካታር፣ ኩዌት እና ባህሬን ይገኙበታል፡፡

ሪፑበሊክ አክት ቁጥር10022 ስለ ህገወጥ የሰዎች ዘውውር፣ ሰልህገወጥ የሰራተኛ መልማዮች፣ ስለ ፍትህ ሂደቱ፣ ስለምርመራ፣ ዝርዝር ጉዳዮችን በማካተት ቀርቧል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ህጉ ዜጎች ተቀጥረው ሲሰሩባቸው ከነበሩ አገሮች ወደ ፊሊፒንስ በሚለሱበት ጊዜ የተሟሉ አገልግሎቶችን ማለትም የህግ አግልግሎት፣ የሰራተኞች የውል ስምምነቶች በስምምነቱ መሰረት እንዲፈጸሙ የመከታተል፣ የሰራተኛ ኢንሹራንስናና የመሳሰሉትን ያካተተ ነበር፡፡

የነጻነት እንቅስቃሴ ጠቀሜታ፣

ለልቤ ቅርብና ውድ ስለሆነው የነጻነት እንቅስቃሴ ሰለሚለው ርዕሰ ጉዳይ ሰፋ ባለ መልኩ ልመለስበት፡፡ የስደት ህግን በመለማመድና ጥገኝነትን እና መባረርን ከአሜሪካ በመረዳት በእራሳቸው እግር የሚወስኑትንና ከጭካኝ እና ከመጥፎ መንግስታት በሚየማልጡት ላይ አተኩራለሁ፡፡ የእንቅስቀሴ ነጻነት ለእኔ ልዩ ጠቀሜታን ትርጉም አለው፡፡ የሰው ነጻነትን ከማክበር ጋር እኩል የሚታይ ጉዳይ ነው፡፡ ነጻ ወንድንና ሴትን ነጻ ካልሆኑ ወንድና ሴት ለመለየት ያህል ተመሳሳይ ነው፣ እስረኞች (የፖለቲካ እስረኞችን ጨምሮ) የመንቀሳቀስ ነጻነት የላቸውም፣ በእስር ቤቱ ህንጻ ወሰን የተከለሉ ናቸው፣ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የፖሊቲካ እስረኞች ለብቻቸው ተለይተው ለብዙ ጊዚያት ይታሰራሉ፤ በመጨራሻም የእንቅስቀሴ ነጻነት መነፈግ ነጻነትን መነፈግ ማለት ነው፡፡ የወንጀል ደመወዝ የመንቀሳቀስ ነጻነትን መከልከል ነው፡፡ ሆኖም ግን የመንቀሳቀስ ነጻነት ከጠባቡ የግድግዳ ወሰን የዘለለ ነው፡፡ ነጻ የሆነ ዜጋ በከተሞች ለመዞር ነጻ ነው፤ በገጠሩ አገሩ/ሯ ኑሮ መመስረት ይችላል፤ ስራ ፈልጎ የመቀጠር ወይም ያለምንም መሸማቀቅ ከባለስልጣኖች ጥቃት፣ መፈናቀል፣ መባርር ነጻ ሆኖ መኖር ይችላል፡፡ ነጻ የሆነ ዜጋ መርጦ ከሚኖርበት ቦታ፣ ወይም ከሚሰራበት ቦታ ከህግ አግባብ ውጭ በኃይል እንዲለቅ አይገደድም፡፡

በአሁኑ ጊዜ የነጻነት እንቅስቃሴ በነጻነት ታሪክ ውስጥ በአደጉ አገሮች ትልቅ ቦታ ይዞ ይገኛል፡፡ ከ2000 ዓመታት በፊት አፍላጦን  የአቴናውያንን የመንቀሳቀስ ነጻነት ታሪክ ጽፏል፣ “እደሜው አየገፋ ሲሄድ አንድ ወጣት እኛን አይመስልም፣እና የከተማውን ሁኔታም ተመለክቷል፣እና በመጠኑም ቢሆን የት እንደሚሄድ አውቋል፣ እና ንብረቶቹን ከእራሱ ጋር ወሰዶ መሄድ ይችላል ፣የእኛ ህጎች በእርሱ ጣልቃ አይገቡም ወይም የእኛ ህጎች እርሱን አይከለክሉም”:: ታላላቆቹ ምሁራንና የዓለም አቀፍ ህግ ተጽእኖ ፈጣሪዎች ሁጎ ግሮቲዎስ እና ኢመሪቺ ዲቫቴል የእያንዳንዱን ዜጋ የመንቀሳቀስ ነጻነት ተከላክለዋል፡፡ ቫቴል እንዲህ ሲል ተከራክሯል፣ “ማንኘውም ሰው ነጻ ሆኖ ተፈጥሯል፣ እና የከታማ ልጅ፣ በአመታት በእራሱ እውቅና ሲሄድ ለእርሱ ጥሩ መሆን አለመሆኑን ይመረምራል፣ እርሱ ሲወለድ ከነበረበት ህብረተሰብ ጋር ለመቀላቀል፣ እዚያ ለመቅረት ጠቃሚ ሆኖ ካላገኘው እርሱ በነጻነት ያቋርጥል…“ ዊሊያም ብላክ ስቶን የታወቀው የእንግሊዞች የሕግ ተቺ ሲናገር ማናቸዉም ሰው ሕግ ካልገታው በስተቀር  አንደልቡ መዘዋወር ይችላል ብሎ አስረደቶል::

አሜሪካ ታላቋ የስደተኞች አገር የእንቅስቃሴ ነጻነት ሀሳብ የተመሰረተባት ናት፡፡ ቶማስ ጅፍረሶን እንዲህ ሲል ጽፏል፣ “አሜሪካ ከመሰደዳቸው በፊት የእኛ አያቶች በአውሮፓ በእንግሊዝ ግዛት በነጻ የሚኖሩ ሀዋሪዎች ነበሩ፣ እንም ለሰው ሁሉ የተሰጠ የተፈጥሮ መብት ነበራቸው፣ ከሀገር  የመልቀቅ ነጻነት፣ አዲስ መኖሪያ ለመጠየቅ መሄድ፣ እና እዚያ አዲስ ህዝቦችን ለመፍጠር፣ በእንደዚህ ያሉ ህጎችና ደንቦች የህዝብን የደስታ ትኩረት ከመሳብ ይመስላል”:: ዛሬ ያንን አሜሪካውያንን የሚመስል ግጥም በነሀስ የነጻነት ተጽፎ ይገኛል:: በደቡብ አፍሪካ ትልቁ የመቆጣጠሪያ እን መጨቆኛ ጥቁር አፍሪካዎች እንዳይንቃሰቃሱ የሚከለከልው ነበር፡፡ ከዚያም አፓርታይድ (የጥቁሮችና ነጮች የተለያዩ ልማቶች) የሚለው ጥቁር አፍሪካውያኖች በቤታቸውና በከተማቸው ብቻ እንዲወሰኑ፣ ለአስርት አመታት ጥቁር አፍሪካውያን በእራሳቸው ከተማ እስረኞች ነበሩ፡፡ ገዥው አፓረታይድ በተለያዩ መንገዶች የጥቁሮችን የመንቀሳቀስ ሀይል በመገደብ አቅማቸውን አዳክሟል፣ እንደ ከብት በባነቱስታ በረት ታጉረዋል፣ በአገራቸው ውስጥ ለስራ ከአንዱ ቦታ ወደ ሌላ ሲቀሳቀሱ ቪዛ እንዲይዙ ይደረጉ ነበር፡፡ በተገኙበት ማስቆምና ሰዓት አላፊ ገደብ ይጣልባቸው ነበር፣ ባልተፈቀደ ቦታና ጊዜ ገተገኙ በቁጥጥር ስር ውለው የታሰሩ ነበር፣ የአፓርታይድ አገዛዝ የብሄራዊ አፍሪካ ኮንግረስን እን ሌሎች ድርጅቶችን የሰዎች እገዳ በሚል አቅማቸውን ያዳክሙ ነበር፡፡

ጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን ከደቡብ አፍሪካ ውጭ እንዲንቀሳቀሱ አይፈቀድም ነበር፣ በአፓርታይደ አገዛዝ ፓስፖርትም አያገኙም፡፡ ፓስፖርተ ማግኘት ከፈለጉ እን ጉዞ ለማድረግ ካሰቡ በመጀመሪያ ደረጃ ዜጎች መሆን አለባቸው፣ እ.ኤ.አ በ1962 ነልሶን ማንዴላ  ስምምነት ከተደረገ በኋላ የኢትዮጵያ ፓስ ፖረት ዳቪድ ሞትሳማይ በሚል ተሰጥቷል፡፡ ማንዴላ በኋላ ኢትየጵያን መውደዱን በማስታወስ “ኢትዮጵያ በእኔ አስተሳሰብ በልቤ ወስሰጥ ሁነኛ ቦታን ትይዛለች፡፡ እናም ፈረንሳይን ከመጎብኘት ይልቅ ኢትዮጵያን መጎብኘት ሳበኝ፣አሜሪካና እንግሊዝ ተገናኝተወላ፡፡ የእራሴን ዘር መጎብኘት አስባለሁ፣ ንጉሱን በራሱ ማግኘት የታሪክን እጅ መጨበጥ ነው::” በአሁኑ ጊዜ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አትዮጵያውያን ጥገኝነትን በፈረነሳይ፣ በእንግሊዝ፣ በአሜሪካ በመካከለኛው ምስራቅ“ ይጠይቃሉ፡፡ የታሪክ አሰገራሚነትም ይህ ነው፡፡

ነጻነት ለመግባትና ለመውጣት፣ ተስፋ ዘላለማዊ ይሆናል፣

ብዙውን ጊዜ በኢትዮጵያ ያለውን ገዥ አስተዳደር አውቆ በሚያደርገው ህገመንግስቱን ያለማከበር ሁኔታ ትችት አቀርባለሁ፡፡ በአገሪቱ የህግ የበላይነት እንዳይከበር ንቀትን ማሳየትና በዓለም አቀፍ ህግ ያለመገዛትና ግዴታን ያለመወጣት፣ ገዥው አሰተዳደር የዜጎችን ወደ ከመካከለኛው ምስራቅ የሚደረገውን የዜጎቹን ስደት አስመልከቶ ችገሩን ለመፍታት የፖሊቲካል ፈቃደኝነት፣ የቴክኒካልና አስተዳደራዊ ብቃት የለውም፡፡ እንዲህ በማለት ሀሳቤን  በመጥቀስ “የህግ የበላይነትን ለመጥፎዎችና ለከሀዲዎች መስብክ ለተሰባሰቡ አረማውያን መጽሀፍ ቅዱስ ጥቅስ እንደመጠቀስ ነው፣ ወይም በተጠረበ የባልጩት ድንጋይ ላይ ውህ እንደማፍሰስ ነው”:: ምንም ከንቱና ተስፋ የሌለው ቢሆንም የማስተማር ጥረቴን እቀጣላለሁ፣ ተስፋ በሰው ልጅ ጡት ላይ ይከሰታል፣ ሰው ምንም አይደለም ግን የተቀደሰ ነው:: የቻይናዎችን ጥቅስ በመዋስ “የሚንጠባጠብ ውህ ድንጋዩን ስርስሮ ይገባል::”

ተምኔታዊ ኢትዮጵያዊ ያለመሆን ያስደንቃልን?

 

 

 

 

 

Leave a Reply