ለአፍሪካ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች ፍትሕ አይቀሬ ናት
ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ
ማስታወሻ ለአንባቢው፡፡ ባለፈው ሳምንት ሐተታዬ ‹‹የዘር አደን›› በሚል አሉባልታዊ ክስ የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በተሰነዘረበት ክስ ደግፌው ተሟግቼለታለሁ፡፡ በዚህም ሳምንት ድጋፌን በመቀጠል እነዚህ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች የፈጠሙትን ግፍና በደል ጭቆና በመዘርዘር ራሳቸውን ነጻ በማድረግ የአይ ሲ ሲን (የኣለም ወንጀለኛ ፍርድ ቤት) ስም በማብጠልጠልና የቆመለትን ዓላማ የሳተ በማስመሰል ገዢዎችና አስፈጻሚዎ ቡችሎቻቸው ያነሱዋቸውን ማስረጃ ቢስ ውንጀላዎች በተጨባጭ ማስረጃ ድርጊቶታቸውንና ሸፍጣቸውን ይፋ ለማድረግ ወስኛለሁ፡፡ የኦክቶበር 11-12, 2013 የአፍሪካ አንድነት ‹‹መሪዎች›› የጨረባ ስብሰባ የተጠራውም ቴአትራዊ የልብ ወለድ ሴራ ለማካሄድና ነጻ ለመምሰል የሚያስችላቸውን ቅጥፈት ለማናፈስ ነው፡፡
በኔ እምነት አይ ሲ ሲ የዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ሕግጋት ትክክለኛውና ጠንካራው ምልክት ነው፡፡ አይ ሲ ሲ ላለፉት ጥቂት ዓመታት ስራውን በማከናወን ላይ ነው፡፡እስካሁን ያስመዘገባቸው ውጤቶች ጥቂት ቢሆኑም ለወደፊቱ ግን ያሻቸውን በደልና ግፍ ፈጥመው ግድያና አስገድዶ መድፈርን ሰብአዊ መብት በደልን አዘው በማስፈጸም በሥልጣናቸውም አላግባብ ባልገውና ተጠቅመው፤ ሃገርን አራዉተው፤ ሕዝብን በበደልና ግፍ ጫና አጉብጠውና አንበርክከው፤ በነጻ ሲቀመጡና ሲንደላቀቁ የነበሩትን እያጋለጠ ለፍርድ ለማቅረብ የሚችል ጠንካራ ተቋም እንደሚሆን እምነቴ ነው፡፡ የአፍሪካ ጨቋኝና የግፍ በደል ባለቤት የሆኑት ገዢዎች በሕዝቡ ላይ ሊኩራሩና ሊደነፉ፤ የሕግ የበላይነትን በመጨፍለቅ ሊቀጥሉ ይጥሩ ይሆናል፤ አሁን ግን አይ ሲ ሲ ስለመጣባቸውና ለሕዝቡ ወግኖ ስለቆመ ስሙ በተጠራ ጊዜ እየተርበደበዱና መግቢያ እያጡ በመሄዳቸው የአይ ሲ ሲን ስም በማጉደፍ ነጻ ለመሆን ቢጥሩ መንገድ ሁሉ፤ በደላቸው ሁሉ፤ ግፋቸው ሁሉ አይ ሲ ሲን እየቀሰቀሰባቸው በመሆኑ ኦክቶበር 13 2013 የቁም ተዝካራቸው ማውጫ አድርገው ሊሰባሰቡ ነው፡፡
በኦክቶበር 11-12, 2013 አድመኞቹ የአፍሪካ ‹‹መሪዎች›› አስተጋቢው የእንግዳ መቀበያ የአፍሪካ አዳራሽ በመሰባሰብ አብዛኛዎቹ በሮም ከጸደቀው ደንብ (አለም ኣቀፍ ዉል) በመውጣት በደስታ ተሞልተው የዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤትን የሞት ውሳኔ ያስተላልፋሉ፡፡ ቀብሩንም ለማስፈጸም የኢትዮጵያ የይስሙላ ጠቅላይ ሚኒስትርና የአፍሪካ አንድነት ተዘዋዋሪ የ2013ቱ ሊቀመንበር ሃይለማርያም ደሳለኝ ነው፡፡ ስብሰባውንም ሲከፍት ‹‹ዛሬ በዚህ የምጽዋት አዳራሻችን የተሰባሰብነው አይ ሲ ሲን ለማወደስ ሳይሀሆን ልንቀብረው ነው….›› በማለት ይሆናል፡፡ የዚህ የቀብር ጥድፍም ሰበቡ የኬንያው ፕሬዜዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በኬንያ በተካሄደው የ2007 ምርጫ ወቅት በፈጸመው የሰብአዊ መብት ግፍ ለመጠየቅ ኖቬምበር 12 2013 ለፍርድ ሊቀርብ በመሆኑ ነው፡፡ በተመሳሳይ ወንጀልም ምክትሉ ዊሊያም ሩቶ ፍርዱ በሄይግ የዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ መታየት ከጀመረ ሁለተኛ ወሩ ነው፡፡ የአፍሪካ አንድነት በኬንያታ እና በሩቶ ላይ የተመሰረተውን ክስ ዘዴ ፈልጎ ካላነሳ በስተቀር ‹‹የኑክሊየር ፈንጂ መቃወሚያውን›› በመጠቀም ከአይ ሲ ሲ አባልነት ለመውጣት እንደሚችልም በማስፈራራት ላይ ነው፡፡
ላለፉት ጥቂት ወራት ሃይለማርያም በአይ ሲ ሲ ላይ የቃል ጦርነት ሲያካሂድ ነበር፡፡ ባለፈው ግንቦት የጃጀዉና በቅዠት ዓለም ያለው ሮበርት ሙጋቤን በመደገፍ በአይ ሲ ሲ ላይ ውንጀላ አካሂዷል፡፡ ግልጽና ማስረጃው ከመጠን ያለፈውን ግፍ ለፈጸመ የአፍሪካ ገዢ ጥብቅና መቆምና ሕዝብን ለባሰ ግፍ ማብቃት የሃይለማርያም የአፍሪካ ወቅታዊ ሊቀመንበርነት ተግባር ሆኗል፡፡ ሃይለማርያም ቃላትን በማሰባሰብና ከጀርባ ባሉት ሽነቋጭ አለቆቹ በመመራት ግራ የገባውን አባባል በመጠቀም አይ ሲ ሲ ‹‹99 በመቶ›› የሆኑት በደለኛ ተከሳሾች አፍሪካውያን በመሆናቸው የዘር አደን ላይ ነው የሚል መሰረተ ቢስ ወሬ እየነዛ ነው፡፡
ባለፈው ሳምንት በተካሄደው 68ኛው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ስብሰባ ላይ ባሰማው ወሬው፤ አይ ሲ ሲ የኬንያታንና የሩቶን ክስ በማንሳት ጉዳዩ በኬንያ ባለስልጣናት እንዲታይ ማድረግ አለበት በማለት የማይገባ የድፍረት ጥያቄ አንስቷል፡፡ ሆኖም ኬንያታ ከተሰነዘረበት ወንጀል ነጻ ሳያደርገው፤ ማድረግ ያሰበው ግን ኬንያታ ራሱ በሚያዘውና መመርያ በሚሰጠው ችሎት ይዳኝ ለማለት ነው፡፡ አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ ይይላሉ ሲተርቱ፡፡ ባለፈው ሳምንት ኢትዮጵያና ናይጄርያ ለአይ ሲ ሲ ይጋባኝ ሰሚ የኬንያው ክስ እንዲነሳ ያቀረቡትን የጽሁፍ ጥያቄ ውድቅ አድርጎታል፡፡
ሃይለማርያም የዚህ ተቀባይነት የሌለው አሳፋሪ ጉዳይ አፈጉባኤ ሆኖ የመገኘቱ ምጸታዊ መነሾ አስገራሚ ነው፡፡ 34 የአፍሪካ ሃገራት የሮምን ደንብ/ዉል የፈረሙበት ሲሆን (አይ ሲ ሲ ሰን በማቋቋም ወንጀሎችን በመመርመር ሰብአዊ መብት ጥሰትን የዘር ጭፍጨፋን ግፍ በማጥራት ለፍርድ እንዲያቀርብ ውክልናና ስልጣን ሰጥቶታል):: እስከሁንም ኢትዮጵያ የዚህ ሕግ አባል ለመሆን ፊርማዋን ነፍጋ ቆይታለች፡፡ የሃይለማርያም የሥላጣን አባት ይህን ሕገ ደምብ ላለመፈረም ወስኖ ያቆየው ምናልባትስ አይ ሲ ሲ እንደማይለቀውና ወንጀሉን አጥርቶ እንደሚፋረደው ተገንዝቦ ይሆን? ለፊርማውም ችግር የሆነበት ሰበብ ሕጉን ፈርሞ ከተቀበለው የፊርማው ቀለም ሳይደረቅ በሰራቸው ሕገ ወጥ ተግባራት በፈጃቸውና ባስፈጃቸው ንጹኃን ዜጎች ሳቢያ አይ ሲ ሲ በሩን እንደሚያንኳኳና ለሕግ እንደሚያቀርበው ጠንቅቆ በመረዳቱ ነው? እነዚያስ 34 ሃገራት ሕጉን አጽድቀው አይ ሲ ሲን ሲያቋቁሙ አይ ሲ ሲ የአፍሪካ ጋሻ መከታ ሆኖ ወንጀለኞችን አላንዳች አድልዎ እያደነ ለፍርድ እንደሚያቀርባቸው አልተገነዘቡትም ነበር?
አይ ሲ ሲን በአፍሪካ አለሳልሶ የመግደል ጥበብ የሃይለማርያም ተንኳሽና የሚያስቆጣው ክሱ የሚያሳየው፤ አይ ሲ ሲን ከአፍሪካ በድል በማስወጣት እራሱን ‹‹ጭራቅ ገዳዩ ጀግና›› ላመሰኘት የተነሳሳ መስላል፡፡ (የሱ ቀደምት የሥልጣን አባቱም ‹‹የአዲሱ ትውልድ አፍሪካዊ መሪ›› በሚል መጠርያ ለራሱ የፈረስ ስም ሰጥቶ፤ ታላቅ በመሆን በሽታ ተለክፎ ለማይለቅና ለማይድን እጀሰብ ተዳርጎ ነበር::) የነገሩ እውነታ መሰርት ግን በዚህ አካሄድ የሃይለማርያምና የጸረመስቀል ተዋጊዎቹ አካሄድ በኬንያዊያን ባለስልጣናት ላይ የተመሰረተውን ክስ ለማስነሳት፤ በብዛት ከአይሲ ሲ አባልነት መውጣትን እንደማስፈራሪያና ማገቻ በማድረግ ወንድሞቹን ኬንያታንና ሩቶን ከአይ ሲ ሲ ማነቆ በማላቀቅ፤ ወደፊት በእነሱ ላይ ሊደርስ የማይችለውን አይቀሬውን ህጋዊ የክስ እርምጃ አስቀድሞ ለመዝጋት የሚያደርገው የአልሞት ባይ ተጋዳይ የሕልም ሩጫ ነው፡፡ አፍሪካን በሚገባት ከፍተኛ የአመራር ስልጣን ላይ ላመስቀመጥ የሚጥረውን አይ ሲ ሲን ለማጥፋት ከንቱ ጥረት ከማድረግ ይልቅ ሃይለማርያምና መሰል ግፈኛ ገዢዎች ራሳቸውን ከግፍ ባህሪና ልምዳቸው በመመለስ እንደሰው በማሰብ ለሰብአዊ ፍጡራን ተገቢውን አገልግሎት ለማከናወን ቢተጉ ይበጃቸዋል፡፡
በኦክቶበር 11-12 2013 በአፈሪካ አንድነት ስለ አይ ሲ ሲ ቀብር ስለሚደረገው ንግግር ቅድመ ትርኢት
የአፍሪካ ‹‹ገዢዎች›› በኦክቶበር 11-12 2013 በአፍሪካ አንድነት በሚሰባሰቡበት ጊዜ ስለሚያካሂዱት እብደት ቀረሽ ጸረ አይ ሲ ሲ ዘመቻ በቂ ግንዛቤ አለን፡፡ የንግግራቸው መነሾና አካሄድየ አይ ሲ ሲን ወኔ ለመገድልና ተግባሩን ለማገድ አስቀድሞ ንድፉ በአምባሳደር ቋሚ ተወካይ ማቻሪያ ካማው፤ በኬንያ በተባበሩት መንግስታታ ቋሚ ሚሲዮን በኩል ለአምባሳደር ሜናንካዶ (የሴኪውሪቲ ካውንስል የሜይ ወር 2013 ሊቀመንበር) በተዘጋጀው ባለ 13 ገጽ ሚስጥራዊ ሰነድ ተዘርዝሯል፡፡
መላ የሌለውና ቅጥ ያጣ እርማት የተካሄደበት የካማው ሚስጥራዊ ሰነድ፤
ኬንያታን ሩቶ ከአይ ሲ ሲ ማነቆ ሊላቀቁ ይገባል ምክንያቱም እነሱን ለክስ ማቅረብ የኬንያን ልኡላዊነት ነጻነት የሚጥስ ነው፡፡ እንደ ካማው አባባል ‹‹የኬንያታና የሩቶ ክስ ራሱን ለሚያስተዳድረው መንግስታችን በውስጥ ጉዳያችንና በሃገራችን ኬንያና በልኡላዊነታችን ላይ የተቃጣ ውርደት ነው በማለት ይከራከራል፡፡ የኬንያ ልኡላዊነት ከኬንያ ውስጥና ውጭ የተለያዩ ተዋንያንን በመጠቀም ለወቀሳ እየተዳረግን ነው፡፡እንዳለፈውና እንደተለመደው የሲቪሉን ማህበረሰብ በማነሳሳት የራሱን ፖሊሲ እንዲቃወም በመደረግ የሮምን ስምምነት ሰበብ በማድረግ አይሲሲን በአስፈጻሚነት እየተጠቀሙበት ነው፡፡›› ነጻነት ለአፍሪካውያን ጨካኝና አረመኔ ገዢዎች የመጀመርያው ስደተኛ ነው፡፡ አሁን የአፍሪካን ነጻነት ለማስከበር በማለት የሚንደፋደፉት አስመሳይ የአፍሪካ ጨቋኞች በኖቬምበር 2010 ምርጫ ወቅት ፈረንሳይ በቀጥታ በአይቮሪኮስት ግጭት ጣልቃ በገባችበት ወቅት፤ ገዳም እንደገባች አይጥ ተሸጉጠው ትንፍሽ ሳይሉ ፈረንሳይ የቀድሞ ቅኝ ግዛቷን መልሳ ስተወር አንዲት ቃል አልተነፈሱም፡፡ የአፍሪካ አንድነትም ቢሆን በዝምታ ተቀምጦ ጠበይ ተመልካች በመሆን ከጎን ሆኖ ከመመልከት አላለፈም፡፡ በጃንዋሪ 2013 ፈረንሳይ የሰሜን ማሊን ከሽብርተኞች ወረራ ነጻ ለማውጣት ጣልቃ ሲገባ የአፍሪካ መሪዎች የፈረንሳይን ጦር ለማስወጣት የነጻነትንና የልእልና ማስከበርን ጉዳይ አላነሱም፡፡ አሁንም እንደገና የአፍሪካ አንድነት ከተመልካችነት አላለፈም፡፡
በወንጀል ፤ በሰብአዊ መብት ጥሰት፤በጦር ወንጀለኛነት፤በዘር ማጥፋት ለሚሰነዘር ክስ ሉአላዊነት ሕጋዊ መከላከያ አለያም የፖለቲካ ውይይት ሁኖ አይቆምም፡፡ አሁን በአፍሪካ ፈላጭ ቆርጫ ገዢዎች የሚነሳው የሉአላዊነት ጥያቄ አይ ሲ ሲ የተጣለበትን አደራ ላማዘናገት ሆን ተብሎ የተነሳና ቀድሞ ከነበሩት የንጉሳዊ ገዢዎች በምድራዊ ዳኝነት እንጠየቅም ሥዩመ እግዚአብሔር ነን እንደሚሉት ለመሆን የታቀደ ዘዴ ነው፡፡ ሕገ ወጥ የሆነውን የአፍሪቃ ፈላጭ ቆራጭ ገዢ ሊዳኘው የሚገባውና የሚችለው ሌላው ሕገወጥ አፍሪካዊ ገዢ መሆን አለበት ነው የሚሉት፡፡
ኬንያታና ሩቶ ከክስ ነጻ የመሆን መብት አላቸው ምክንያቱም በማርች 2013ቱ ምርጫ ‹‹ንጹህ›› ናቸው ስለተባሉ፤ካማው ኬንያታና ሩቶን በተመለከተ ሁለቱ ሰዎች ንጹሃን ብቻ ሳይሆኑ በክፍተኛው የመንግስት ስልጣን ላይ ስለተቀመጡ ሃለፊነትም አለባቸውና ክሱ ሊሰረዝላቸው ይገባል በማለት ይሞግታል፡፡ አይ ሲ ሲ የከፈተው የክስ መዝገብ የሚዘጋበት ምክንያት ኬንታና ሩቶ የፈጸሙት የሰብአዊ መብት ድፍረትና ጥሰት በፍትህ አደባባይ ቆሞ ስለሚመሰክርባቸውና ለፍርድ ሊያቀርባቸው ስለሚችል የንጹሃን ግፍና በደል በነሱ የስልጣን ወንበር መያዝ ተቻችሎ ነጻ ሊሆኑ ይገባል ነው፡፡ እነዚህ ሁለት ዋናና ምክትል ገዢዎች የኬንያውያን ሁሉ መተሳሰርያ በመሆናቸውና ሕዝቡም በፍቅር ስለመረጣቸው፤ 86 በመቶ ድምጹን ሰጥቶ መንበራቸው ላይ ስላስቀመጣቸው ክሱ ሊሰረዝላቸው ግድ ነው፡፡ ካሙ ክርክሩን በመቀጠል፤ የሮሙ ስምምነት ኬንያታንና ሩቶ ሊያካትት አይገባም፤ምክንያቱም በአሁኑ ጊዜ ከፍተኛውን የሃገሪቱን አመራር በዋናነትና በምክትልነት የያዙ በመሆናቸውና የኬንያ ሪፑብሊክ የመከላከያ አዘዦች በመሆናቸው፤ነው ይለናል፡፡ ካሙንን ግራ ያጋበው ነገር ኬንያታና ሩቶ ንፁህነታቸውን ለማረጋገጥ መመረጥ አያስፈልጋቸውም፡፡ ማንም ሰው ቢሆን በፍርድ ሸንጎ ወንጀለኛ እስካልተባለ ድረስ ንጹህ ነውና፡፡ ስለዚህም በተጠረጠሩበት ወንጀል ኣይ ሲ ሲ የሚለው ችሎት ፊት ቀርበው ንጸህናቸውን በነጻ የፍትሕ ስርአት ያረጋግጡ ነው እንጂ ወንጀለኞች ናቸው ብሎ አልደመደመም፡፡ የሁለቱ ባለስልጣናት በአጥጋቢ ውጤት ከመመረጣቸው ጋር የተሰነዘረባቸው ተጠርጣሪነት አንዳችም ግንኙነት የለውም፡፡ ጥያቄው በ2007-08 በስልጣን ላይ በነበሩበት ግዜ ተፈፀሙ በተባሉ ወንጀሎች ነው፡፡ ኬንያታና ሩቶ የሃገሪቱ መሪዎች መሆናቸው ከሕጉ ጋር የሚያገናኘው ሰበብ የለውም፡፡ የሮም ስምምነት አንቀጽ 27 ማንኛውም ተጠርጣሪ አይሲሲ ችሎት ቀርቦ ንጽህናውን ማረጋገጥ ይጠበቅበታል ይላል፡፡ ስምምነቱ ማንንም በእኩል ደረጃ ይመለከታል፡፡ ማንንም ከማንም በስልጣን ደረጃ አያመዛዝንም ለአይ ሲ ሲ ምንኛውም ተጠርጣሪ እኩል ነው፡፡ ተመራጭ ፕሬዝዳንትም ይሁን የፓርላማ አባል የመግስት ባለስልጣንም ሆነ ተራ ዜጋ ለአይ ሲ ሲ ችሎትና መመርያ ሁሉም እኩል ናቸው፡፡
በኬንያታና በሩቶ ላይ የተመሰረተው ስንኩል ክስ (የተባበሩት መንግሥታት ሴኩሪቲ ካውንስልና በኬንያም መንግሥት ወንጀል መስራታቸው ሳይተላለፍለት ነው) በአግባቡ ምርመራና ማጣራት ሳይካሄድበት ነው ይላሉ፡፡ የአይ ሲ ሲ ክስ ተቀባይነት የሌለው ምስክሮቹንም አስጠንተው ያቀረቧቸው ናቸው፡፡ ተጠቂ ነን ብለው የቀረቡትም ሃሰተኞች አለያም ተመርጠው የተሰየሙ ናችው፡፡ የምስክርነት ቃላቸውም ደካማና የማያሳምን ነው፡ በማለት ካሙ ይከራከርላቸዋል፡፡ ምስክሮች በመደለያ የተገዙ ያንንም ነው አይደለም ብሎ የሚወስነው የአይ ሲ ሲ ችሎት ነው፡፡ ምናልባትም ምስክሮቹ ተአማኒነት የሌላቸው በጥቅማ ጥቅም የተገዙ ናቸው የሚባልም ከሆነ የካሙስ መንግስት ማስረጃውን በማቅረብ ሊቃወም ይችላል፡፡
የአቃቤ ሕግ ቢሮ ሚዛናዊ ባልሆነ መልኩ በኬንያታና በሩቶ ላይ የክስ ምስረታውን ተከሳሾቹን በሚጎዳ መልኩ እያካሄድ ነው ለፍትሕ በእኩል መልኩ የተከናወነ አይደለም በማለት ተጠርጣሪዎቹን ተከሳሾች ፍትሕ በአግባቡ ነጻ ናቸው አይደሉም ከማለቱ ይልቅ አይ ሲ ሲንና የአቃቤሕግ ቢሮን በሃሰት በመወንጀልና ፍትሕ ገደል ይግባ ለኛ በሚመቸን መልኩ የማይሰራም አይ ሲ ሲ ፍርስርሱ ይውጣ የሚል ነው የካማው ቅጥ ያጣ ሙግት፡፡ ፍትሕ ለመዛባቱ የካማው መንግስት ማስረጃ ካለውና በፊትም ሆነ አሁን ኬንያታንና ሩቶን ፍትሕ ይነፍጋቸዋል ብሎ ካሰበ ወደ ፍርዱ መድረክ በማቅረብ ሕዝብ እንዲያውቀው ሊያደርግ ይገባዋል፡፡ በተቃራኒው ካማውና የአፍሪካ መሪዎች ሊያደርጉና ለማድረግም በመጣር ላይ ያሉት አንዳችም እውነትነት የሌለው የክስ ዳውላ በመዘርገፍና እርፍት የለሽ የድረሱልን ጥሪ በማሰማት ዓለምን ሊያሳምኑ በመጣር ላይ ናቸው፡፡ እውነት ካላቸው እነካማው አለን የሚሉትን የፍትህ ግድፈት አደባባይ ያውጡት፡፡
አይ ሲ ሲና የአቃቤው ሕግ ቢሮ ማንም የማይቆጣጠረውና ከሕግ ውጪ ለማንም ተጠያቂ ያልሆነ ባለሥልጣን ነው ለመጀመርያ ጊዜ ቋሚ ዓለም አቀፋዊ ተቋም የሃገራትንና የዜጎቿን ሕጋዊ ግዴታ ለመመልከትና ለመወሰን ወንጀልም ሲያገኝባቸው በአግባቡና በስርአት ቅጣት ለመጣል ተመስርቷል፡፡ አይ ሲ ሲ ብቃቱን በተመለከተ በማንኛውም መልኩ ለዓለም አቀፍ ሕግጋት ምን እንደሚያስፈልገው ሲረዳ የመከራከሪያው የመጨረሻ ቃላት አይ ሲ ሲ ሲወስን በማንኛውም መንግስት ቁጥጥር ስር አለያም ትእዛዝ ሳይሆን ዓለም አቀፍ ሕግጋት በሚመሩበት ስርአት ብቻ መሆኑን ነው፡፡ ካሙ የሚያውቀውና የሚለውም ሆነ አይ ሲ ሲ ያድርግ የሚለው አለቆቹ በሚወነጀሉበት ጥፋታቸው ሁሉ አስቀድሞ እነሱ የሚያዙት ችሎታቸው ጉዳዩን ይመርምር ነው፡፡ የሚያውቀውና የሚከተለው አሁን ምርመር ይደረግባቸው የተባሉት አለቆቹ ሲያስሩ ሲገድሉ ሲያሰቃዩ ፍርድ አልነካቸውምና አሁን እንዳይነካቸው ይደረግ ነው፡፡ ካሙ ችግሩና በሽታው አለቆቹ የሚመሩበት ያልተጻፈ ሕግና ያልተሰጣቸውን ስልጣን መጠቀም ስለሆነ በዚያው መሰረት ይዳኙ ነው፡፡ አይ ሲ ሲ የሚታዘዘውም ሆነ የሚመራው በዓለም አቀፉ የፍትሕ ስርአት ነውና ማንንም አይጠላም ማንንም ከማንም አስበልጦ አያፈቅርም፡፡ ካሙ ለምን አንድ አቃቤ ሕግ ብቻውን ያጣራው ጉዳይ ተቀባይነት ያገኛል ነው፡፡ አይ ሲ ሲ ደግሞ አቃቤ ሕግ ግድፈት አለበት የሚል ማንኛውም ተጠርጣሪ አለያም ዜጋ መስረጃውን አቅርቦ ሊሞግተው ይችላል ነው፡፡
የአፍሪካን ዲክታተሮችና ጭፍሮቻቸው ስለ ‹‹ቁጥጥር አልባ ሥልጣን›› ሲያወሩ ማዳመጥ የአዞ እንባ እንዲሉ አይነት ነው፡፡ የኬንያን ባለስልጣነት መጠን የለሽ የስልጣን ክልል በመጠኑም ቢሆን ለመቆጣጠር ያስቻለው በ2010 የወጣው ሕገመንግስት ነው፡፡ በኬንያ ስርአት አልበኝነትን ሕገወጥነትን ለመከላከል ሲባል የወጣው አዲሱ ሕገመንግስት ነው መሰረት የጣለው፡፡ ማንም ሊረዳው የሚገባው አዲሱ የኬንያ ሕገመንግስት በ2007 በተከሰተው የምርጫ ውዝግብ ሳቢያ በተካሄደው ውይይት ላይ ተመስርቶ መረቀቁና መጽደቁ ነው፡፡ ኬንያታና ሩቶ በዚያው ሕገመንስት ደንብና ስርአት ውስጥ በተካተተው መመርያ መሰረት ነው ለፍርድም ሊቀርቡ ማዘዣ የወጣባቸው፡፡
በአፍሪካ የሕግ የበላይነት እነ ካማው መሰረተ ቢስ የሆኑ በርካታ ጥያቄዎችን በማንሳት ሕዝብንና መንግስታትን በማታለልና መንገድ በማሳት አለቆቻቸውን ነጣ ለማድረግ ይጥራሉ፡፡ እነ ሃይለማርያም ደሳለኝ የአይ ሲ ሲ አካሄድ ማንም ግፈኛና ወንጀለኛ ከነጉድፉ ተሸሽጎ እነዳይኖርና ግፍና በደሉን በማር ቀብቶ ለማስመሰያነት እንዳዋለ እንዳይኖር የማድረግ ስልጣኑ ማነህ ባለሳምንት ይለናል በማለት አስቀድመው ለራሳቸው የሚጠቅም ከለላ ለመፍጠር ነው ጥረታቸው፡፡ የዓለም ሕግ ተፋለሰ ሲሉ እስከ ዛሬ ድረስ እነዚህ የኡኡታ አሰሚዎች የፈጸሙትን የሕግ መፋለስ በመዘንጋት ሳይሆን አውቀው ትክክለኛ መስለው ለመታየት እንጂ በአይ ሲ ሲ አካሄድ የተፋለሰ አንዳችም ሕግ የለም፡፡ አለ ከተባለ ደግሞ ከነማስረጃው ማቅረብ እንጂ ከንቱ የጋጋኖ ጨኸት የትም አያደርስም፡፡ የአፍሪካ አንድነት ደንብም ቢሆን በአፍሪካ ውስጥ ሰብአዊ መብት ሊከበርና ሊጠበቅ እንደሚገባው ይደንግጋል፡፡ ስለመልካም አስተዳደርም በደንቡ ላይ አስፈሯል፡፡ ማንም ከወንጀል ነጻ ሊሆን እንደማይችል ደንቡ ያናገራል፡፡
በኦክቶበር 13 ለቁጥር የሚጣክቱት መሪዎች ከሮሙ ስምምነት ለመውጣት ማሴር ማለት ሕግ አልበኝነትና የራሳቸው የአፍሪካ አንድነት የሚተዳደርበትን ደንብ መጣስ መሆኑን መዘንጋት ነው፡፡ ተጠያቂነትን ያወጁ ሃገራት ተጠየቁ ሲባሉ ሕጉን ያወጣነው ሕዝብን ለመቅጣት እንጂ እኛ ልንጠየቅበት አይደለም ማለት ምን የሚሉት፡፡ በጣም ቀላል የሆነና የማይቀር ምርጫ አለን፡፡እነዚህን በአፍሪካ ሕዝብ ጫንቃ ላይ ሆነው ግፍን በመፈጸምና ሃላፊነትን አላግባብ በሚጠቀሙ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች ከሮም ውልና ስምምነት የመውጣት አድማቸው ላይ አቋም በመያዝ መመጎት ቢያንስ የነዚህን እኩዮች አድማ የሚቃወሙትን ተቆርቋሪ ወገኖች ማገዝ ነው፡፡ ለዓለም አቀፉ የወንጀል ችሎት መቆምና መወገን ማለት አፍሪካ ውስጥ በመግዛትና ግፍ በመፈጸም ያሉትና ባለስልጣናት መሞገት ነውና አብረን ሆነን ከአፍሪካ ጫንቃ ላይ እንዚህን ጋሬጣዎች እንንቀስ! አይ ሲ ሲን የመደገፊያው ወቅት አሁን ነው::