በኩራት ተሞልቼ ሁለንተናዬ ሰማያዊ

ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

Blue Party Ethiopia10‹‹በየቀኑ በየቀኑ ሰማያዊዎች አሉኝ›› (ሰማያዊ ወይም “ብሉስ” አፍሮ አሜሪካውያን የሚታወቁበትና ይዘውት የተሰደዱት የንጉርጉሮ ባህላዊ ሙዚቃቸው ነው)  አለ ዘማሪው ቢቢ ኪነግ  በሚወዳት ክራር “ሉሲል” ላይ፡፡ እኔም በየቀኑ በየቀኑ ላለፉት ስምንት ዓመታት የ‹‹193/763 ሰማያዊዎች›› ነበረኝ:: “አስከ 25ኛው ሰአት ድረስ አላቋርጥም ምክኛቱም አሁን የምኖረው በሰማያዊ ተስፋ ላይ ነውና” አለ ዘማሪው ኤሪክ ክላፕተንም!፡፡እኔም በበኩሌየሰማያዊውን ሃይል እየተጎናጸፍኩ ነው::

እኔም ሰማያዊና ደስተኛ ነኝ፡፡ ማለትም ሰማያዊ እንደ ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች ሰማያዊ ፓርቲ በኢትዮጵያ፡፡ሰማያዊን ቀለም የመረጡበትም ምክኒያት የአንድነታቸውን መሰረት፤ ሰላምን ተስፋን በኢትዮጵያ  ለማጠናከር ነው፡፡ ሰማያዊ ሲባል ልክ እንደ ተባበሩት መንግሥታት ሰማያዊ ለሁሉም ሕዝቦች፤ በወደፊቱ ተስፋና ሠላም ላይ ለመተባበር ላለሙት ሁሉ ሰማያዊ  አይነት ነው፡፡ ልክ እንደ አውሮፓ ሕብረት ሰማያዊ፤ ወደ 24 የሚጠጉ ሃገራት ለትክክለኛው የኤኮኖሚና ለፖለቲካዊ ጥምረት እንደሚሰሩት አይነት ሰማያዊ ነው፡፡ ልክ
እንደኢትዮጵያዊያን ሰማያዊ ሁሉ፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በሕብረት ላይ እንደተሳሰሩትና በ21ኛው ክፍለ ዘመን በሰላማዊ፤ ተስፋ በለመለመበት ለመተባበርና አንድ ለመሆን እንዳቀዱት አይነት ሰማያዊ ነው፡፡ ወደፊት ሰማያዊ! ቀጥሉ!!! በርቱ!!!

ሰማያዊውን መስመር ተከተሉ

ላለፉት ዓመታት እንደምታስታውሱት ስለኢትዮጵያዊያን ኦቦሸማኔዎች (የወጣቱ ትውልድ ማለት ነው) ስናገር፤ ስጽፍም  ነበር:: ስለ ኦቦሸማኔ፤ ትውልድ ለበርካታ ዓመታት ሳነሳ ነበር፡፡ አሁን ይፋ ማውጣት እፈልጋለሁ፡፡ የዘመናት ልዩነትን ጨርሼ ወደ ኦቦሸማኔዎች ዋሻ ለመግባት ተሻገሬያለሁ፡፡ ነውና አዎን ከዳሁ! ጉማሬዎችን (ማለትም ወጣት ያልሆነው መንቀሳቀስ የተሳነው አጅ አግሩ የተሳሰረው የደነዘዘው ትውልድ) ጥያቸው ሄድኩ:: እኔ አሁን ‹‹ኦቦ-ጉማ›› ነኝ:: (ማለትም የጉማሬ ወገን ከኦቦሸማኔዎች ጋር መወገን የመረጠ)::

ጉዳዩ አንደዚህ ነው፡፡ ኦቦ ሸማኔዎች እየተፈናጠሩ ሲነሱ ክፍ ከፍ ሲሉ ፤ እስከላይኛው ጠርዝ ድረስ ሲምዘገዘጉና ከፍ ሲሉ አየኋቸው፡፡ በቅርቡም መንገዶቹን ሲሞሉ፤ ሳያነገራግሩ ፈራ ተባ ሳይሉ ሲተሙ ጎዳናውን ሞልተው አየኋቸው፡፡‹‹እንዴት ደስ የሚያሰኝ ትዕይንት ነው›› አልኩ፡፡ በጎዳናዎቹ ላይ ሲፈሱ መሰከርኩ፡፡ (ኦቦሸማኔዎች ስለ ሠላም፤ ስለፍትሕ፤ ስለነጻነት፤ እና ስለሰብአዊ  መብት ሲያቀነቅኑ ሲዘምሩ አጋጥሟችሁ ያውቃል?) እንዴት ደስ የሚልና ስሜት ያመቀሰቅስ ድምጽ ነበር! የኔ ዜማ እየዘመሩልኝ ነበር  እኮ!!፡፡›› ከእንግዲህ እኔ ከኦቦሸማኔዎች ጋር ነኝ፡፡ ከፈጣኖቹና ከአስፈሪዎቹ ቆራጥ ኦቦሸማኔዎች ኋላ አየተጎተትኩም ቢሆን እጉኣዛለሁ፡፡

አቤት እስቲ እይዋቸው ኦቦ ሸማኔዎች ሲሮጡ!  እስቲ እንደ ንጋት ጸሃይ ሲወጡና ሲያበሩ ተመልከቷቸው! ‹‹እንደንስር አሞራ አክናፎች እየመጠቁ ፤ እየፈጠኑ፤ ድካም ሳይሞክራቸው፤ እርምጃቸው ሳይቋረጥ፤ ሳይዝለፈለፉ ይራመዳሉ፡፡ ‹‹እስቲ ይታያችሁ እንደ ጉማሬዎች መንገላወድ፤ መዳህ ሳይሆን፤ አቦሸማኔዎች ሲጀግኑ፤ ማየት አያስደሰትም፡፡ ያስገርማል! አይደለም እንዴ?

በዐመቱ የመጀመርያው ጦማሬ ላይ፤2013 ‹‹የኢትዮጵያ ኦቦሸማኔዎች ትውልድ ዘመን›› ብዬ ሰይሜ ነበር፡፡ ያ ያልኩትዓመት ደሞ ይሄው  የአሁኑ ወቅት ነው፡፡ አንዳንድ ጉማሬዎች ተቃውሞ ነበራቸው፡፡ ‹‹ኦቦሸማኔዎችን ተዋቸው፤ እነሱብልጭታና ምንዛሪ ናቸው›› ብለው ነበር፡፡እኔ ደግሞ እስቲ በመስታወቱ ውስጥ ተመልከቱ አልኩ፡፡

የኢትዮጵያን አቦ ሸማኔዎች ‹‹ስንት ሰአት ነው? ግዜው ምንድነው?›› አልኳቸው፡፡ በነጎድጓዳ ድምጻቸው ‹‹የኦቦሸማኔዎች ሰአት ግዜ ነው›› ሲሉ መለሱ፡፡ አልተሰማኝም! ‹‹የኦቦሸማኔዎች ሰአት ግዜ ነው!!›› ብለው በድጋምሜ አናጉት:: አስቲ ድምጻችሁን ከፍ፤ ኮራ ብላችሁ በሉት! ‹‹የኦቦሸማኔዎች ሰአት ግዜ ነው!!!›› ወደፊት!!!!

በ2013 አመት መጀመርያ የኢትዮጵያ ኦቦሸማኔዎች ከፍ ብለው መጥቀው በአዲስ ከፍታ ላይ ያንጸባርቃሉ ብዬ ነበር፡፡ ከፍ አድርገው ኢትዮጵያችንን ያነሷታል፡፡ ያን እያደረጉ ነው፡፡ እነዚህ ኦቦሸማኔዎች እንማን ናቸው? የኢትዮጵያ የኦቦሸማኔዎች ትውልድ ምሩቃኑና የሰለጠኑ  ባለሙያዎች ብቻ ሳይሆኑ፤ ‹ብልሆቹንና ብሩሆቹን› ብቻ ሳይሆን፤ የተጨቆኑትን ወጣቶች ለነጻነት ዓየር እንዲበቁ፤ በመደለል፤በማግባባት በሙስና የተታለሉትን፤ ለጭቆና የተዳረጉትን ሰብአዊ መብት በመደፈሩ ድማጻቸውን ስላሰሙ የተወገዙትን፤ ሁሉ ያካትታል፡፡የኢትዮጵያ ኦቦሸማኔ ትውልድ ማለት፤ የእስክንድር ነጋና የሰርክዓለም ፋሲል ትውልድ ማለት ነው፡፡የአንዱዓለም አራጌ፤ የርዕዮት ዓለሙና የውብሸት ታዬ፤ የበቀለ ገርባ፤የኦልባና ፈይሳ እና የሌሎችም መሰሎቻቸው ትውልድ ነው፡ ኦትዮጵያን ሰቅዞ ከያዛት የብረት አምባገነናዊና ጨቋኝ ገዢ የሚያላቅቃት የኦቦሸማኔ ትውልድ ብቻ ነው፡፡

ኢትዮጵያን ጊዜው ካለፈበት ከሻገተና ከነቀዘ የበሰበሰ፤ በሃሰትና በቅጥፈት ላይ ከተመሰረተ፤ገዢ መንግስት አላቆ፤ ወደ ሕዝባዊ ስርአት የሚያስገባት የኦቦሸማኔው ትውልድ ብቻ ነው፡፡ በጃንዋሪ 2013 የግሌን ‹‹የኦቦ ጉማ››ቃል ገብቼ ነበር፡፡ ‹‹በ2013 የኢትዮጵያን ወጣቶች ባለኝ አቅምመና ችሎታ ለማስተማር ለማማከር ለመምከር እሞከራለህ ብዬ ቃል ገብቼ ነበር፡፡ ያን ቃሌን አላፈረስኩም፡፡ ቁጥራቸው ባዘቀዘቀ ወቅትም መረት ላይም ወድቀው 1,2 ,3,… ተነሱ ሲባል የኢትዮጵያ ኦቦሸማኔዎች እንዲነሳሱ ሲቆጠርም አልተለየሁም፡፡ ተነሱ ኦቦሸማኔዎች! ተነስታችሁ የኢትዮጵያን ብርሃን አሳዩ! በማለት ቃሌን ጠብቄአለሁ::

እቅጩን  መናገር አስፈላጊ ነው፡፡ጉማሬዎች ከኦቦሸማኔዎች ጋር ቃል አፍርሰዋል፡፡ ኦቦሸማኔዎች በጉማሬዎች ክህደት ደርሶብናል ይላሉ፡፡ኦቦሸማኔዎች መገለልና ልዩነት ተሰርቶብናል ይላሉ፡፡ኦቦሸማኔዎች፤ ታማኝነታቸውና አክብሮታቸው እንደ ማንቋሸሽና ብልግና ድፍረት ተወስዶብናል ይላሉ፡፡ ኦቦሸማኔዎች በርካታ ቅሬታዎችን ባነሱዋቸው ነጥቦች ላይ የጉማሬዎች ቸል ባይነት ያደረሰባቸውን ግድየለሽነት ከዚያም ያስከተለውን ዝግመት በቁጭት ያነሳሉ፡፡ ኦቦሸማኔዎቹ ጉማሬዎችን ተጠያቂነትን ተቀበሉ ባልን ተገፍተናል፤ ሃሳባችንን በነጻ በመግለጻችን በዘምተኞቹ ጉማሬዎች አርፈን እንድንቀመጥና ትንፍሽ እንዳንል ተደርገናል ይላሉ፡፡

ዛሬ ዛሬ የኢትዮጵያን ኦቦሸማኔዎች ሳይ መላ ሰውነቴ ሰማያዊ ይላበሳል፡፡ አሁን ሰማያዊ የምመርጠውና የምወደውቀለም ሆኗል፡፡ የኢትዮጵያ ሰማያዊ ኦቦሸማኔዎች ከአፍሪካ ሁሉ የተለዩ ብርቅዬ ኦቦሸማኔዎች ናቸው፡፡ሰማያዊ ኦቦሸማኔዎችን ሳይ ሰላምና ተሰፋ ይታየኛል፡፡ ሰማያዊ ኦቦሸማኔነት ሲሰማኝ መከፋፈል አይሰማኝም፡፡ አንድ ሕዝብ ነዋ የሚታየኝ፡፡ከምር ሰማያዊን እመርጣለሁ፡፡ አረንጓዴ ቢጫ ቀይን ግን እወደዋለሁ ከዚያ አኳያ ሺህ ጊዜ ከሰማያዊ ይበልጥብኛል፡፡ እስቲ ታዘቡ! አረንጓዴ ቢጫ ቀይ በውብ ከፈይ ሰማያዊ ተጠቅልሎ! ወድድድድ አደርገዋለሁ፡፡

ሰማያዊውን በአንድነት ሰማያዊውን መስመር እንከተል እላለሁ፡፡ በሰማያዊው ባቡር ላይ ተሳፈሩ፡፡ የመጀመርያው መቆሚያ ጣቢያ፤ ፍትሕ፤ ሁለተኛው ዴሞክራሲ፤ ሶስተኛው መቆሚያ፤ ሃሳብን በነጻነት መግለጽ/ የፕሬስ ነጻነት፤ አራተኛው የፖለቲካ እስረኞች ነጻ መሆን፤ አምስተኛው መቆሚያ የዕምነት ነጻነት፤ ስድስተኛው …ሰባተኛው……ስምንተኛው…….ከእንግዲህ የሚያቆመን የለም፡፡

እነዚህ ኦቦሸማኔዎች መነሻ መድረሻቸውን ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ ኦቦሸማኔዎች ዘመናዊው መንገድ መመርያ ጂ ፒ ኤስ ሲኖራቸው እኛ ገና አቅጣጫ ጠቋሚ ኮምፓስ ነው ያለን፡፡ እነሱ የተቀየሰ መንገድ ሲኖራቸው እኛ ግን ዘዋሪ ጎዳና ነው ያለን፡፡ አነጋገራችንም በአዙሪት ነው፡፡ እነሱ ሲራመዱም ሲናገሩም ትክክልና ቀጥ ያለ ነው፡፡ እኛ ደሞ መቀኘትና ተረት ተረት እናበዛለን፡፡ ኦቦሸማኔዎች አንድ ጊዜ ጠፍተው ነበር አሁን ግን ተገኝተዋል፡፡እኛ ደሞ እስከናካቴው ላንገኝ ጠፍተናል፡፡ በቀስተደመናው መጨረሻ በፈዘዙና ባረጁ ዓይኖቻችን የወርቅ ማሰሮ እንፈልጋለን፤ ኦቦሸማኔዎች ግን ሕዝባዊ ቀስተደመናን በብሩህ ዓይኖቻቸው ይመለከታሉ፡፡ ይሁኑበት ጃል! አንተውላቸው!! ሽማግሌዎች፤ያረጀን፤ወቅት ያለፈብን ፤ ባለ አሮጌ ካርታ ባለቤቾች ነን፡፡ አሁን አዲስ ቀን ነው፤ሰማያዊ ቀን ነው፡፡ ውቅቱ ዘመናዊ መመርያ ጂ ፒ ኤስ የያዙት የኦቦሸማኔዎች ነው፡፡ በሰማያዊው ባቡር እንትመም! ሁኑበት ወደፊት በሉለት በሉ ሰማያዊ ኦቦሸማኔዎች፡፡

ተገቢው ዝና እንደአስፈላጊነቱ ሊሰጥ የግድ ነው

በኢትዮጵያ ስላለው ገዢ ፓርቲ ሚዛናዊነት አስተያየት እንደምነሳ ይነገራል፡፡ አምርሬ ስለመንቀፌም ይነገራል፡፡ ገዚውን ፓርቲ አንዳችም ወቅት ፋታ መተንፈሻ አልሰጠህምም ተብያለሁ፡፡ ለምንም ተግባራቸው መልካም ተናነግረህ አታውቅም ብለውኛል፡፡ያ ሁሉ እውነት ከሆነ እንግዲህ አሁን ለውጥ አለኝ፡፡ (አስተሳሰቡንና ተግባሩን መለወጥ የማይችል ማንም ቢሆን ለለውጥ አይበቃምና) ሲያጠፉ ጥፋቸውን ካጋነንኩ: መልካም ሲያደርጉ ደግሞ ያለምንም እቀባ ድጋፌ አይጓደልባቸውም፡፡ ሰኔ 1 ቀን ሰላማዊ ሰልፍቻውን እንዲደርጉ ሲፈቅዱላቸው መልካም አድርገዋል፡፡ ለሃይለማርያም ደሳለኝና ለቡድኑ፤ የማይቻል ነው ብሎ በርካታ ሰው ያሰበውን የሚቻል በማድረጋቸው ድጋፌ ጨርሶ አይለያቸውም፡፡ያደረጉትና የወሰዱት እርምጃ ቀላል እንዳልበረ እገነዘባለሁ፡፡ ከባድ ጫናም እንደነበረባቸው ይሰማኛል፡፡መልካም እሳቤ የሌላቸውና እኩይ ምግባር ብቻ ሙያቸው የሆኑት ባልደረቦች፤‹‹አታሞክረው፤ በኋላ ታዝናለህ፡፡ አሁን ሰላማዊ ሰልፉን ብንፈቅድ ሰማይ ይደረመሳል፤ ከዋክብትም ወደ ምድር በመውረድ ይከሰከሳሉ… ይልቁንስ በ2005 እንዳደረግነው ሁሉ የማይረሳ ትምህርት እንስጣቸው›› ብለውት እንደነበር ይሰማኛል፡፡ ሃይለማርያም ደሳለኝ ሠላማዊ ሰልፉ እንዲካሄድ በመፍቀዱ አክብሮቴን እገልጻለሁ፡፡ እሱና የሃሳቡ ደጋፊዎች መልካም አድርገዋል፡፡ ሚዛነዘዊነት አስፈላጊ በመሆኑ ሊመሰገኑ የግድ ነው፡፡(ልዩነት ካለኝ ሰዎች ጋር ትክክል ሲያደርጉ ማመስገን ካልቻልኩ በሚዛናዊነት አላምነም ማለት ነው::) ሃይለማርያምና ደጋፊዎቹ ይህን ውሳኔ ለመወሰን ብዙ ወኔ ጠይቋቸዋል፤ ይህ ነው አመራር ማለት፡፡ የተሳሳተን መንገድ መምረጥ ቀላል ቢሆንም ትክክለኛውን ማደረግ ደግሞ ከባድ ነውና: ከባዱን በመወጣታቸው ምስጋና ይገባቸዋል፡፡ የበለጠ ጉልበት እንዲያገኙና ትክክለኛውን ለማድረግ እንዲያበቃቸው ምኞቴ ነው፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች አባላትና ደጋፊዎች እጅግ ሊመሰገኑ ይገባል፡፡ የፓርቲው አመራሮች አልበገሬነታቸውን አሳይተዋል፡፡ የሚፈልጉትን እንደሚያውቁ አረጋግጠዋል፡፡ ምን ማድረግ እንደነበረባቸውም አስመስክረዋል፡፡ መልእክቶቻቸውን ላመስተላለፍ የረጉና የበሰሉ ነበሩ፡፡አንዳችም የቁጣ መንፈስ የእርግማን ቃላት የማውገዝና የጠበኝነት መንፈስ አላሳዩም፡፡ ወደሠላማዊ ሰልፉ ሽርፍራፊ ነገር ተሸክመው አልመጡም፡፡ በትከሻቸው ያነገቡት ዓላማቸውን ብቻ ነበር፡፡ ጠብና ትንኮሳም ዓላማቸው አልነበረም፡፡ መነሻና መድረሻቸው ሁሉ የሰብአዊ መብት መከበር ብቻ ነበር፡፡

የፓርቲው አመራሮች፤ አባላትና ደጋፊዎቻቸው ሁሉ፤ መልካም አርአያ የነበራቸው ናቸው፡፡ ለስነስርአት የተገዙና የረጉ ነበሩ፡፡ አንድም ሰው ድንጋይ አልወረወረም፡፡ አንድም ጠብ አልታየም፡፡ በማንኛውም መልኩ ሰብአዊ መብታቸውን ማስከበር ብቻ ነበር ዓላማቸውና ያንን ነው የተከተሉት፡፡ ለጥበቃ የተመደቡትም የፖሊስ አባላት ቢሆኑ የተለየ ሁኔታ ስላጋጠማቸው ዳር ዳሩን ከመቆም  ባሻገር ሌላ ምርጫ አልነበራቸውም፡፡ ጥቂቶቹም ግንብ ተደግፈው በማፋሸግ እንቅልፋቸውን ለማባረር ነበር ጥረታቸው፡፡ ሠላማዊው ሰላማዊ ሰልፍ ሠላማዊነቱ ይህን ይመስል ነበር፡፡ ለዓለም ያሳዩትም በሰላማዊ በክብርና በጨዋ ደንብ ተቃወሞን ማሳየት እንደሚቻል ነው፡፡ የሰማያዊ ፓርቲና አመራሮች አባላትና ደጋፊዎች ለማመስገን ቃላት ያጥሩኛል፡፡ ምንግዜም ከግጭት የወጣና ሰላማዊ መንገድ ከግጭትና ጠብ ጫሪ መንገድ እንደሚበልጥ ያለኝን ቋሚ እምነቴን አረጋግጠውልኛል፡፡

ስለ (ሰብአዊ መብት) ትክክለኛነት አስብ፤ (ሰብዊ መብትን) በትክክለኛ መንገድ ተግባር ማንም ያድርገው ማንም እኔ ምን ጊዜም በእውነተኛው ወገን በኩል ነኝ፡፡ ትክክለኛ ያልሆነውን መንገድ ማንም ያድርገው ማንም አልደግፈውም፡፡ ስለተግበሪው ሳይሆን፤ ስለትግበራው ነው፡፡ስለሃጢአቱ እንጂ ስለሃጢአተኛውአይደለም፡፡ መልካም ተግባር ሊመሰገንን ሊደፋፈር ይገባል፡፡ መጥፎውም ውግዘትና እርግማን ይገባዋል፡፡ በጁን 1 ሰማያዊ ፓርቲም ገዢው መንግስትም ትክክለኛውን ጉዳይ ተግብረዋል፡፡ ስለሰብአዊ መብት ትክክለኛነት በመተግበር ስህተት አይፈጸምም፡፡

ደህና እስከመሰለኝና  እስካመንኩት ድረስ የተሳሳተ መንገድ ቢመስልም መልካም ነገር ማድረግን እመርጣለሁ፡፡ የዋህነህ የሚሉኝ የኔ አይሆንም ባዮች አሉኝ፡፡ ‹‹እነዚህን ሰዎች አታውቃቸውም ይሉኛል፡፡›› እየቀለዱ ነውይላሉ፡፡ አንድ ነገር ስላደረጉ ልታምናቸው አይገባምና ትንሽ ጠብቃቸው ይሉኛል፡፡ እኔ ግን ጨርሶ አልጠብቅም፡፡ እንደአመጣጡ እቀበለዋለሁ፡፡ቆይተው ጠባያቸው ሲለወጥ ያን ጊዜ ደሞ ሃሳቤን እገልጻለሁ፡፡

‹‹ታዲያ ቢቀልዱስ?›› ከሃሳብ የበለጠ ተግባር፤ድርጊት ይመሰክራል፡፡ ምናልባትም ይህ የአሁኑ ድርጊታቸው ለለውጥ የሚደረገውን ሂደት አባሎቻቸውና ደጋፊዎቻቸው ላይ የሚፈጥረውን ስሜት ለማየት ያደረጉት ሙከራ ሊሆን ይችላል፡፡ ላሞቹ ወደ ጋጣ እስኪገቡ ድረስ ለሰማያዊ ፓርቲ ሰልፉን የፈቀዱበትን ምክንያት ላንሰላሰል ሳወጣ ሳወርድ መዋል እችላለሁ፡፡ ያ ደሞየራሳቸው ጉዳይ ነው፡፡ በኔ አመለካከት፤በፓርቲው ውስጥ በተሰባሰቡትና በተቃዋሚ ማሃል ያለውን ርቀት ለማጥበብ ለሰማያዊ ፓርቲ ሰልፉን መፍቀዳቸው ጥሩ ጅማሮ ነው፡፡ በተፎካካሪዎች ማሃል ያለመተማመን በበረታ ቁጥር፤ በድንገትም ቢሆን ለመግባባት የሚያስችል ዘር ማቆጥቆጥ ሲጀምር ያንን መንከባከብና ማበረታታት አስፈላጊ ነው፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ሰላማዊ ሰልፋቸውን በተሳካ መንገድ ሲያካሂዱ፤ለሰማያዊ ፓርቲና ለገዢው መንግስት፤የዕውነት ወቅት ነበር፡፡ ለሁለቱም የተሰነዘረ የፍተሸ ወቅት ነበርና ሁለቴም ወገኖች ፈተናቸውን በሰማያዊ ቀለም አልፈዋል፡፡

ዕቅድህ ለሰላም ይሁን  እንጂ ክፋትን አታስብ፤ መልካም አስተዳደርንና ዴሞክራሲን በተመለከተ ለስር ነቀል ለውጥ እና ለመሻሻል ጣር

የተሰማኝን በመናገሬና እውነትን በመተንፈሴ ደስተኛ ነኝ፡፡ ለዚህ ነው የግል ድሀረ ገፅ ‹‹ለሰብአዊ መብትተሟገት፡፡ እውነትን ለሃያላን አስታውቅ›› የሚለውን ጥቅስ የያዘው፡፡ እውነትን እንደማየው፤ እንደምናገረውና እንደሚሰማኝ፡፡ ይህ ደግሞ የኔ ጎራዴና ጋሻዬ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ እውነት መራር ፍሬ የሚሆንበት ወቅት አለ፡፡ አስቸጋሪም ሊሆን ይችላል፡፡ ከዚያም በተለየ፤ የእውነት ውጤት ጣፋጭ፤ ነጻ አውጪ፤ ብርሃናማና ፍላጎታችንን የሚያሟላ ሊሆን ይችላል፡፡ መለስ ባለፈ ጊዜ፤ ለስንብቱ ለመለስ ወራሾች አንድ የእውነት ሙግት አዘል ጥያቄ
አቅርቤ ነበር፡፡

መለስ ስለ ሰብአዊ መብት ረቀቅ ባለ መልኩ በትንሹም ቢሆን ምልከታ እንዳለው ገምቻለሁ፡፡ የጥርጣሬ ማመሳከሪያ ያህል ላምነው እፈልጋለሁ፡፡ መለስ በ2007 ከአልጀዚራ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ላይ፤ ‹‹የኔ ስጦታ (ቅርስ) የተሳካና የተስተካከለ ልማት በማካሄድ ኢትዮጵያን ለዘመናት ከኖረችበት የችግርና የመከራ እስር ነጻ ማውጣትና የተረጋጋ ሃገር እንዲኖር ማድረግ ነው፡፡ መልካም አስተዳደርንና ዴሞክረሲን በተመለከተ መሰራታዊና ስር ነቀል ለውጥ ማድረግ ነው: እናም እኔ ወደ ጡረታ በምገለልበት ጊዜ ያልኳቸው ጉዳዮች ሁሉ ተግባራዊ እንደሚሆኑ ተስፋ አደርጋለሁ› ብሎ ነበር፡፡

‹‹መልካም አስተዳደርንና ዴሞክረሲን በተመለከተ መሰራታዊና ስር ነቀል ለውጥ ማድረጊያው›› ወቅት አሁን ነው፡፡ መሰራታዊ የሆነ የኋልዮሽ ሂደት አምባገነናዊ አስተዳደር፤ማንአለብኝነትና ጭቆናን ተመልክተናል፡፡ ‹‹ያ‹‹ መለስ የወደፊቱ ያለው ጊዜ አሁን ነው›› ሁላችንም በአንድነት ሆነን የዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር መሰረታዊ ለውጥ ምኞቱንና ሃሳቡን ተግባራዊ ለማድረግመስራት አለብን፡፡ ወራሾቹ የሆኑት የመለስ ሹመኞች ይህን የመለስን የውርስ ምኞት በመቀበል ከሌሎች ተቃዋሚዎች ጋር በጥምረት ለመስራትና የመለስን የምኞት ጥማት መወጣት አለባቸው፡፡

የ “መልካም አስተዳደርና የዴሞክራሲ ስርነቀል መሰረታዊ ለውጥ” የሚጀምረው የፖለቲካ እስረኞችን በመፍታትና የሽብርተኝነትንና የእርዳታ ሰጪዎችን ድርጅቶች ሕጎች መለወጥና ማስተካከል፤ የሕግን የበላይነትም ባረጋገጠ መልኩ እንዲተገበር መንገዱ ሲጠረግ ነው፡፡ የዘመን መለወጫው እየተቃረበ እንደመሆኑ፤በመሰረታዊው ስር ነቀል ለውጥ መልካም አስተዳደርና ዴሞክራሲ መሻሻል ሁላችንም በአዲሱ ጎዳና ላይ መራመድ መጀመር ይኖርብናል፡፡

መለስ በቃላት ደረጃም ቢሆን ሲመኝ እንደነበረው፤ ሰማያዊ ፓርቲም ፍላጎቱ የመልካም አስተዳደርና ዴሞክራሲ ስርነቀል ለውጥ ነው፡፡የመለስም ወራሾች ይህን ስር ነቀል ለውጥ እንደሚፈልጉት አልጠራጠርም፡፡ በተቃዋሚውም ጎራ ያሉት ሌሎችም ይህ ነው ፍላጎታቸው፡፡ሁሉም ከተስማማበት ቀላሉ ጥያቄም፤ ይህን ለውጥ እንዴት ማምጣት ይቻላል የሚለው ነው፡፡

ለውጥ ፈለግነውም ጠላነውም በጊዜ መምጣቱ አይቀሬ ነው፡፡ ለውጥ በትክክለኛው መንገ ድ አለያም በሌላ መልኩ መምጣቱ የግድ ነው፡፡ስለዚህም ለውጥን በሰላማዊው መንገድ ብንቀበለው እንጂ ካልሆነ በከፋ መልኬ ስለሚመጣብን ቀናውን እንምረጥ፡፡ በኢትዮጵያ ለውጥን ወጣቱ እየተራበውና እየተጠማው እየፈለገው ስለሆነ መምጣቱ አያጠራጥርም፡፡ወጣቱ የራሳቸውን አመለካከትና  ሁኔታ ለውጠዋል፡፡ ከእንግዲህ የሚቀበሉት አይደለም በቅቷቸዋል፡፡ ስለሃገራቸው እጣ ፈንታ ግንባር ቀደም መሆናቸውን ታሪክ ስላስረከባቸው ምንም ሃይል ሊያቆማቸው ከቶ አይችልም፡፡

ለውጥ ለሚፈሩትና ለሚያገሉት በእጅጉ ጨካኝ ነው፡፡ እነዚህ እምቢ ባዮችና ለውጥን ለመቀበል ፍቃድ ሌላቸውየራሳቸውን ጥፋት ቀያሽ መሃንዲሶች ይሆናሉ፡፡ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ስለ ለለውጥ ተመክረው ያንን ለመቀበል ፍቃደኛነት አጡ፡፡ መንግስታቸው እራሱ በእራሱ አጠፋ፡፡ የጁንታው መንግሥቱ ኃይለማርያምም ስለለውጥ ተመክሮነበር፡፡ መልሱ ግን እብሪት ነበር፡፡ እሱም የእራሱን መንግስት አጠፋ፡፡ መለስም ስለለውጥ ተመከረ፤እሱም አሻፈረኝ አለ፡፡ ስለዚህ አሁን ያሉት ወራሾቹ ሃሳቡ የነበረውን የመልካም አስተዳደርና የዴሞክራሲን ለውጥ በስርነቀል መልኩ የመተግበር ሃላፊነት አለባቸው፤ ያንን የማይቀበሉ ከሆነ ደግሞ የታሪክን ፍርድ መቀበል ነው ምርጫቸው፡፡ ያ ደግሞከፋ ነው:: “ከታሪክ ለመማር ፍቃደኛ ያልሆኑ ሁሉ፤ያለፈውን ሰህተትመድገም ግዴታቸው ይሆናል፡፡”

ለውጥን መፍራት በሰብአዊ ፍጡር ውስጥ ያለ ጉዳይ ነው፡፡ ሰዎች በአንድ ወቅት ኤሌክትሪክ ሃይልንና በዓየር ላይ የሚበሩትን አውሮፕላኖች ይፈሩ ነበር፡ በጋሪና በፈረስ የሚጠቀሙትም: የሰው ልጅ እንዲበር ቢያስፈልግ ኖሮ ክንፍ ይበጅለት ነበር ብለዋል፡፡ አንድ ጊዜ ግን ከፍርሃታቸው ከተገላገሉ በኋላ ለውጦቹን የህይወታቸው አካላት አድርገዋቸዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ያሉት ባለስልጣናት በሙሉ ለውጥን በእጅጉ የሚፈሩና ስለለውጥም  መስማት የማይፈረቅዱ ናቸው:: ስልጣናችንን ምቾታችንን አናጣለን ብለው ይፈራሉ፡፡(አንዳንዶችም  ከምራቸው በስልጣን ላይ ለ100 ዓመታት እንቆያለን ብለው ያስባሉ፡፡ የሚያሳዝኑ ሃሳበ ምስኪኖች!) አንዳችም ዕድል ለለውጥ ለመስጠት አይፈቅዱም፡፡ ለውጥን የሚጠይቁትም ቢሆኑ የራሳቸው የሆነ ፍሃትና ጥርጣሬ አላቸው፡፡ለውጡ ምን ሊያስከትል እንደሚችል፤ ምን ይዞ እንደሚመጣ አያውቁትም፤ ሆኖም ግን ለለውጥ ቅድሚያ ሰጥተው ያሻው ይሁን ግን ለውጥ እንፈልጋለን ይላሉ፡፡ ፈላጊዎችም ሆኑ እምቢተኞች የለውጥ የፍርሃት እስረኛ ሊሆኑ አይገባቸውም፡፡ ከፍርሃት እስር ከልባቸው ውስጥ
ከተቋጠረው ድፍረት ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘው ለውጥን ማስተናገድ አለባቸው፡፡

አፍሪካ ሞቶ በተወለደ አለያም በጨነገፈ ለውጥ ቆሽሻለች፡፡ በአፍሪካ ውስጥ ቀን በቀን ልዩነት ለውጥ እያየንነው፡፡ የአፍሪካ ፈላጭ ቆራጭ ጭንጋፍ ገዢዎች እንደበጋና ክረምት ይመጣሉ ይሄዳሉ፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ እንደ ሃይለኛ አውሎ ነፋስ በሚልፉበት ያለውን ሁሉ እያጠፉ ይሄዳሉ፡፡ ሌሎች እንደበረሃ ንዳድ ይቃጠላሉ፡፡ ጥቂቶች ደግሞ እነደ ጭጋግ ጉም የጨለሙ ናቸው፡፡ እውነተኛው ለውጥ በአፍሪካ ግን የማይጨበጥ ሆኖ አለ፡፡ እውነተኛ ለውጥ የመሪዎች ብቻ ውጥ አይደለም፡፡ የንዳንዱ ገለ ሰብ ልብና የሕሊና ለውጥ ያስፈልገዋል፡፡

ለውጥን ለመልካምነቱ ልናቅፈውና ልንቀበለው ይገባናል እንጂ ልንፈራው አይገባንም፡፡ የኢትዮጵያ ወጣቶችም ለጥሩና አስፈላጊ ለሆነው ለውጥ ነው የተነሳሱት፡፡ ዛሬ ኢትዮጵያ እያኮበኮበች ያለችው ልዩ ለሆነው ለውጥ ነው፡፡ ከለምለሙ የወጣቶች ሕሊና የሚፈልቀውን ለውጥ ነው፡፡የቀድሞዋ ኢትዮጵያ በዘር በተጠላለፈ፤ የነጋድ መጠቃቀም በቀደመበት፤የጎሳ ውስብስብ ባደራበትና በተረሳ የኋልዮሽ የፖለቲካ ስርአት  መሰረት ላይ እንድትገነባ አይሹም፡፡ የጻታ እኩልነትን ይሻሉ፡፡ የሚፈልጓትን ኢትዮጵያ የቀረጹበት የራሳቸው ንድፍ አላቸው፡፡ እኛ የራሳችን ነበረን: እነሱስ የራሳቸው ሊኖራቸው አይገባም? ትክክለኛ ፍርድ ነው፡፡

አደረግነውም አላደረግነውም፤የኢትዮጵያ ኦቦሸማኔዎች ትውልድ አሸናፊነት የተረጋገጠ ነው፡፡ ነፋሱ ወደነሱ አድልቷል፡፡ ቁጥሩም የነሱ ነው:: 75 በመቶው የአትዮጵያ ሕዝብ እድሜው ከ35 በታች ነው፡፡ታሪክ ከነሱ ጋር ወግኗል፡፡ ከነሱ በፊት የነበሩት በሚሊዮን የሚቆጠሩት ወጣት ኢትዮጵያዊያን ደማቸውን አፍሰው፤በላብና በደማቸው ፍጹም የሆነች ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት የጣሩት፡፡ የዓለማችን ሃይሎች የሆኑት ፍትህ፤ነጻነት፤ዴሞክራሲ ከነሱ ጋር ግምባር ፈጥረዋል፡፡ እኛም ከነሱ ጋር መሆን ይገባናል፡፡ ለውጥ በመሳርያን በጉልበት ሊገታ አይችልም፡፡‹‹ጊዜው የደረሰውን ሃሳብ ማንም አያቆመውም::›› የአዳዲስ ሃሳቦች ወቅት፤የትኩስ ወጣቶች ገጽታ በኢትዮጵያ፤ ጊዜው አሁን ነው፡፡

በለውጥ ሂደት የሚተርፉት ባለመሳርያዎቹና ባለገንዘቦቹ አይሆኑም፡፡ ለለውጥ ፈቃደኛነትን ያሳዩ ፤ከለውጡ ጡጫ ጋር አብረው በመንከባለል፤ፈንጂውን የሚከላከሉት ናቸው፡፡ ስሕተት ላይ የሚጥሉትን ነገሮች በማሰላሰል ዘመን ላስቆጥርእችላለሁ? 2005 በ2013 ሊመጣ ይችላል? ስለትክክለኛው ማሰብ ያለብን ቀላል ስለሆነ ሳይሆን፤ አስቸጋሪና ፈታኝስለሆነ ነው፡፡ ስህተትን መፈጸም ምንጊዜም ትክክለኛውን ከማከናወን የበለጠ አስቸጋሪ ነው፡፡

እንደሰብአዊ መብት ተሟግቻነቴ፤ እውነትን በመደገፍ ስህተትን ማውገዝ ተግሬ ነው፡፡ አንድ ሰው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ሊሆን ሲወስን ሊወስደው የሚገባው ምርጫም ይሄው ነው፡፡ ስለሰዎች ሰብአዊ መብት እጨነቃለሁ እንጂ ስለፓርቲ  ፖለቲከኞች ስለ ፖለቲካ ዘይቤ ወይም መሰሎች አይደለም፡፡ ሥላጣን ወሳኙ ሳይሆን አመላካች ቅያስነው፡፡ ጥሩም መጥፎም ሊሆን አይችልም፡፡

ከዓመታት በፊት በሰላማዊ መንገድ መብታቸውን ለማስከበር የወጣቱት ንጹሃን ዜጎች በመጨፍጨፋቸው ሰበብ ወደሰብአዊ መብት ተሟጋችነት ስቀላቀል፤ከ8000 ቃላት ያላነሰውንና አድርጌው የማላውቀውን ‹‹ግዙፉ ሲነቃ›› በሚል ርዕስ ረጂሙን ንግግሬን አነበነብኩ፡፡ በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ኢትዮጵያዊያን አሜሪካኖች በሃገራቸው ጉዳይ ልዩነት ማምጣት ይችላሉ?(እዚህ ይገኛል) ያንንም በአጭሩ ላስረዳ እችላለሁ፡፡ ‹‹የዓላማችንን ትክክለኛነትየምናረጋግጠው በደም በጨቀየና የሙታን በድን በሞላበት በጦር ሜዳ ሳይሆን፤ በወንዶችና ሴቶች ቋሚ ልቦቻችንና በማሰቢያ ሕሊናችን ነው፡፡›› አሁንም መመርያዬ ይህ ቀላል እሳቤ ነው፡፡

ከሰማያዊ ፓርቲ ሕዝባዊ ሰላማዊ ትእይነተ ሕዝብ ብዙ የምንማረው ጉዳይ አለ፡፡ ዋነኛው ነገር ሰላማዊ ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ የሚፈራ ሳይሆን የሚደገፍና ተቀባይነት ያለው መሆኑን ነው፡፡ ምናልባት ከሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ጋር በጎዳናው ላይ ልንተም አንችል ይሆናል፤ ከሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ጋር በጋራ መቆማችንንና መወገናችንን ግን ለማሳወቅ መጠራጠርና ማፈግፈግ የለብንም፡፡በሰማያዊ ፓርቲ ውስጥ ያሉት ወጣቶች ብቻቸውን ሊያከናውኑት አይችሉም፡፡ ‹‹እኛ›› በሥልጣኑ ላይና ከሥላጣኑ ውጪ ያለነው ሁሉ እንጂ፡ ከሚነሱት ኦቦሸማኔዎች ጋር መነሳት ብቻ ሳይሆን ከጎናቸው መቆምም ይጠበቅብናል፡፡

ኢትዮጵያዊያኖች በመስቀለኛው መንገድ ላይ ናቸው፡፡ አክራሪነታችንን እሹሩሩ እያልን፤በጥላቻ መረቃችንን እየቀቀልን፤ በብጥብጥ፤ ግጭትና አምባጓሮ  በመስቀለኛው መንገድ ላይ ቆመን መቅረትን መምረጥ እንችላለን፡፡ አማራጩ ደግሞ ሰማያዊውን ጎዳና በመምረጥ ሰማያዊውን ስብስብ በመከተል፤ ወደ እርቀ ሰላም መግባባት መወያየት ማምራት እንችላለን፡፡ ሁላችንም ወደ ሰማያዊው ጎዳና መሰባሰብ ይኖርብናል እላለሁ ምክንያቱም እስካሁን በጥቂት የተሄደበት የተጎደነበት በመሆኑ የወደፊቱ መጓዣም ስለሆነ::

‹‹ሠላማዊ ለውጥን የማይቻል የሚያደርጉት: የሁከትን ለውጥ አይቀሬ ያደርጉታል::›› ጆ ኤፍ ኬ

በኔ አስተያየት ደግሞ‹‹ሰማያዊ ለውጥን የማይቻል የሚያደርጉት የሁከትን ለውጥ አይቀሬ ያደርጉታል::››


*የተቶረገመው ጽሁፍ (translated from):
ttp://open.salon.com/blog/almariam/2013/06/10/ethiopia_rise_of_the_blue_cheetahs

(ይህን ጦማር ለሌሎችም ያካፍሉ::) ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮችን  ለማግኘት እዚህ ይጫኑ::

http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/category/al-mariam-amharic

http://ethioforum.org/?cat=24

 

Similar Posts

Leave a Reply