ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ ጉዳዩ የምርጫ ብቻ አይደለም እኮ ባለፈው ሴብቴምበር ስለ ፕሬዜዳንት ባራክ ኦባማ ድጋሚ መመረጥ ድጋፌን ገልጬ ነበር፡፡ ለታዳሚዎቼ እንዳስነበብኩት በ2008 ምርጫ ተወዳዳሪ ባራክ ኦባማን ደግፌ…
It’s Not Just About an Election In September, I expressed my support for President Barack Obama’s re-election. I told my readers that I enthusiastically supported candidate Obama in 2008…
ስለስልጣን ብልግና አለያም ስለ ስልጣንን በማንአለብኘነት አለ አግባብ ስለ ከመጠቀም ከመናገር ይበልጥ አስቸጋሪ የሆኑ bezu ነገሮች yelum፡፡ ለ31 ዓመቷ ወጣት ኢትዮጵያዊት አይበገሬ ርዕዮት ዓለሙ ግን፤ የመጻፍ ነጻነት፤ የመናገር ነጻነት፤ ሃሳብን በነጻ የማንሸራሸር ነጻነትን ድምጻቸው በመሳርያና በስለላ መዋቅር ለታፈነባቸው ድምጽ ከመሆን ምንም አይነት ጋሬጣ ቢደረደር ሊያደናቅፋት ጨርሶ አይችልም፡፡ አሁንም ቢሆን ባለችበት ክፉ ሁኔታም ሆና ስለግፍ ስልጣን ቁልጭ ያለ ሃቅን ትናገራለች፤ ‹‹ለጥንካሬዬ ዋጋ እንደምከፍል ብገነዘብም የሚቃጣብኝን ለመቋቋም ዝግጁ ነኝ››፡በማለት ካለችበት ገሃነማዊ የቃሊቲ ጉረኖ ባመለጠው የእጅ ጽሁፏ መልእክቷን ለአለም አስተላልፋለች፡፡
ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ ስለስልጣን ብልግና አለያም ስለ ስልጣንን በማንአለብኘነት አለ አግባብ ስለ ከመጠቀም ከመናገር ይበልጥ አስቸጋሪ የሆኑ bezu ነገሮች yelum፡፡ ለ31…
There are few things more difficult or dangerous than speaking truth to abusers of power. But for Reeyot Alemu, the 31 year-old young Ethiopian heroine of press freedom, no price…
ወርሃ ኦክቶበር (ጥቅምት)በአለም የጡት ካንሰር ማሳሰቢያና ማስገንዘቢያ ወቅት ነው፡፡ ወሩን በሙሉ በዓለም ላይ ሕዝባዊና የግል ድርጅቶች የፕሮግራሞቻቸውና የእንቅስቃሴዎቻቸው ትኩረት ሁሉ በጡት ካንሰር መንስኤ ላይ በማትኮር፤ አደጋውን ለመቀነስ፤ ቅድመ ጥንቃቄ ስለማድረግ፤ ህክምናና ምርምር በማከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡ በእርግጠኝነት በተረጋገጠው መሰረት በአብላጫ በዓለም ላይ ሴቶችን በማጥቃት ላይ ያለው የጡት ካንሰር ነው፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሴቶች በበሽታው በየዓመቱ ሲለከፉ ከነዚህም መሃል በሢ የሚቆጠሩት ለሞት ይዳረጋሉ፡፡ኮመን ፎር ዘ ኪዩር የተባለው የአሜሪካ ድርጅት እንደአስቀመጠው በአሜሪካን የሚገኙ አብላጫዎቹ አፍሮ አሜሪካውያን መሃል ሁለተኛው ገዳይ በሽታ የጡት ካንሰር እንደሆነ ያረጋግጣል፡፡ በአፍሪካ ስለዚህ ገዳይ በሽታ የታማሚ መጠንና ስለሚያደርሰውም አደጋ አያም ስለሚሰጠው ትኩረትና ህክምና በትክክል እንዲህ ነው ለማለት ዘገባም ሆነ መግለጫ ስለሌለ ብዙ ማለት ያስቸግራል፡፡ በአፍሪካ የበሽታው ሁኔታ ሊታወቅ የሚችለው ታማሚው በበሽታው ተይዞ ለህክምና ወይም ለመመርመር ወደ ጤና ጣቢያ አለያም ህክምና ማእከል ሲሄድ ብቻ ነው፡፡ አብላጫው የሴቶች ቁጥር በሚኖርበት የገጠሩ ክፍል ስለበሽታው ሁኔታ መዝግቦ መያዝና ማስረጃዎችን ማሰባሰቡ በብዙም የተለመደ ወይም ሁኔታ የተፈጠረለትም አይደለም፡፡ ስለበሽታው ሁኔታ ክትትልና ዘገባም ሆነ ስለበሽተኞቹ ሁኔታ ጥናት ማካሄድን ከምር ይዘው በማስኬድ ላይ የሚገኙት ጥቂት የአፍሪካ ሃገራት ናቸው፡፡
ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ ወርሃ ኦክቶበር (ጥቅምት)በአለም የጡት ካንሰር ማሳሰቢያና ማስገንዘቢያ ወቅት ነው፡፡ ወሩን በሙሉ በዓለም ላይ ሕዝባዊና የግል ድርጅቶች የፕሮግራሞቻቸውና የእንቅስቃሴዎቻቸው ትኩረት ሁሉ በጡት ካንሰር መንስኤ ላይ…
ኢትዮጵያ በመልካም ስሟም፤በአስከፊ ገጽታዋም ትታወቃለች:: ኢትዮጵያ በመልካም እንግዳ ተቀባይነቷና አስተናጋጅነቷ፤በሕዝቦቿ መልካም ባሕሪ፤ በመልክአ ምድሯ ውበት፤እና በግሩሙ ቡናዋና በማይደፈሩት ጅጋኖች ረጂም ርቀት ሯጮቿ ትታወቃለች፡፡ ተወዳዳሪ በሌለው የሰብአዊ መብት ጥሰት፤የፕሬስ ማፈኛ ተቋሟም፤በአፍሪካ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የፖለቲካ እስረኞች የሚገኙባት ሃገርም ሆና ኢትዮጵያ ትታወቃለች፡፡ በሚያሳዝን ሁኔታ ችጋር (ኤክስፐርቶቹ እንደሚሉት፤ “ሥር የሰደደ የማይነቀል የምግብ እጥረት”) ከውቢቷ ኢትዮጵያ ጋር ከተሳሰረ ዘመናት አልፈዋል፡፡ የሆነው ሆኖ አትዮጵያ ከጭቆና የፈላጭ ቆራጭ አስተዳደር ወደ ዴሞክራሲ ጉዞዋን ጀምረለች፤ ወይስ ኢትዮጵያዊያኖች ከአምባገነኖች አገዛዝ ወደ ነጻነት እየሮጡ ነው ብል ይሻላል?
ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ ኢትዮጵያ በመልካም ስሟም፤በአስከፊ ገጽታዋም ትታወቃለች:: ኢትዮጵያ በመልካም እንግዳ ተቀባይነቷና አስተናጋጅነቷ፤በሕዝቦቿ መልካም ባሕሪ፤ በመልክአ ምድሯ ውበት፤እና በግሩሙ ቡናዋና በማይደፈሩት ጅጋኖች ረጂም ርቀት ሯጮቿ ትታወቃለች፡፡ ተወዳዳሪ…
