አሜሪካ ከጀግኖች አፍሪካውያን ጎን ትቆማለች ?

ከፕሮፌሰር  ዓለማየሁ  ገብረማርያም
ትርጉም  ከነጻነት ለሃገሬ


magl3

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

ታሪክ ከጀግኖች አፍሪካውያን  ጋር ከወገነ፤  አሜሪካስ  ለምን  አትወግንም ?

ፕሬዜዳንት ኦባማ አክራ፤ ጋናን በ2009 ሲጎበኙ ሁለት አስቸኳይና አስፈላጊ መልዕክቶችን አስተላልፈው ነበር፡፡ ‹‹ታሪክ ከጀግኖች አፍሪካውያን ጋር ወግኗል›› ሲሉ: ለአፍሪካ መሪዎችና ገዢዎች ደግሞ ጠበቅ ያለ መልክት ኣስተላፈው ነበር፡፡

………እንዳትሳሳቱ፡ ታሪክ ወገናዊነቱ ከጀግኖቹ አፍሪካውያን ጋር እንጂ በሥላጣን ላይ እራሳቸውን እንዳነገሱ ለማቆየት መፈንቅለ መንግሥት ከሚያካሂዱ ጋር አለያም ሕገ መንግሥታቸውን እንዳሻቸው ከሚለዋውጡት ጋር አይደለም፡፡ አፍሪካ የሚያስፈልጓት ጡንቻቸው የፈረጠሙ መሪዎች ሳይሆን የዳበሩ ተቋሞች እንጂ … የሕዝቦቻቸውን ፈቃድ ከማያከብሩት እጅጉን በበለጠ  ሕዝባቸውን የሚያከብሩ መንግሥታት የከፍተኛ ሃብታም፤ በጣም የተረጋጉ እና የበለጠ የተዋጣላቸው ይሆናሉ… የልማት መሰረቱ  መልካም አስተዳደር ነው፡፡ በበርካታ ቦታዎች እጅጉን ለረዘመ ብዙ ጊዜ ጎድሎ የነበረው ቅመም ይህ ነው፡፡ ይህ ነው የአፍሪካን እምቅ ችሎታ ሊያወጣው የሚችለው፡፡ ይህም ሃላፊነት በአፍሪካውያን ብቻ ነው ግቡን ሊመታ የሚችለው፡:

ለአፍሪካውያን ህዝቦች የላኩት መልእክት አነሳሽ ተስፋ ሰጪ፤አደፋፋሪ ነበር፡፡

መሪዎቻችሁን በተጠያቂነት ለመያዝና ለሕዝቡ አስፈላጊውን ግልጋሎት የሚሰጡ ተቋማትን ለመገንባት ስልጣኑ አላችሁ፡፡ በመንደራችሁ አገልግሎት መስጠት ትችላላችሁ፤ አቅማችሁንና እውቀታችሁን አዲስ ሃብት መፍጠሪያ፤ ከሌላው ዓለም ጋር መገናኛም ልታደርጉት ትችላላችሁ:: ከመሰረቱ አንስታችሁ የእርስ በርስ ግጭትን፤ በሽታን በማጥፋት  ለውጥ ማምጣት ችላላችሁ፡፡ ያንን ማድረግ ትችላላችሁ፡፡ አዎን ይቻላል! ምክንያቱም በዚህ ሰአት ታሪክ በመገስገስ ላይ ነውና፡፡

ፕሬዜዳንት ኦባማ በተጨማሪም የተከበረና የረጋ ቃል ለአፍሪካ ህዝቦች ገቡ፡

አሜሪካ በማንም ሕዝብ ላይ ምንኛውንም አይነት የመንግስት ስርአት ለመጫን ፍላጎት የላትም፡፡… ማድረግ የምንፈልገው፤ ትኩረታችንን በመልካም አስተዳደር ላይ፤ የስልጣንጣን  መባለግን በሚቆጣጠር  እና ተቃዋሚ ሃይላት ድምጻቸው እንዲሰማ በሚያደርግ፤ የሕግ የበላይነት ለሚያስከብር፤ የፍትሕ ስርአቱን አስተዳደር በእኩል መብት በሚያካፍል፤ የሕዝባዊ ማሕበራት ተሳትፎን በሚያረጋግጥ ፓርላማ ላይ፤ ወጣቱ ትውልድ በስፋት የሚሳተፍበትን በሙስና ላይ ግልጽ አቋም የሚይዝ፤ ከሕጉ ጋር የተያያዘ ቁጥጥር፤ አግልግሎቶችን በማፋጠን፤ ሃላፊነት ለሚሰማቸው ግለሰቦችና ተቋማት፤ ተጠያቂነትንና ግልጽነትን ለሚያረጋግጡ ሁሉ ድጋፋችንን መጨመር ነው እቅዳችን፡፡

አሁን ግልጽ በሆነው የፕሬዜዳንት ኦባማ ሁለተኛው የስልጣን ዘመናቸው ላለፉት ጥቂት ዓመታት ያስተላለፍናቸውን አንዳንድ አስቸጋሪ ጥያቄዎችን ማንሳት ይኖርብናል፡፡ ከ2009 ይልቅ በ2012 በአፍሪካ የበዙ ባለ ጡንቻ መሪዎች አሉ? በየጎዳናውና በየወህኒ ቤቱ ጠንካራ የአፍሪካ ልጆች በ2009 ከነበረው በ2012  ያሉት ኣይበልጡም?  አፍሪካ በ2009 ከነበሯት ደካማ ተቋማት አሁን ያሉት ይበዛሉ? በ2009 ከነበሩት የሕዝባቸውን ፍቃድና ፍላጎት የሚያሟላ የአፍሪካ መሪዎች የበለጡ አሁን አሉ? በአፍሪካ በ2009 ከነበረው የእርስ በርስ ግጭት አሁን ያለው ያንሳል? አሁን አፍሪካ መልካም አስተዳደር አላት? በርካታ የተቃዋሚዎች ድምጽ ይሰማል?  ሕዝባዊ ተሳትፎስ በርክቷል? የወጣቱስ ተሳትፎ በ2009 ከነበረው አሁን ተሸሏል? የታሪክስ ሂደት ወደ ዴሞክራሲ፤ወደ ነጻነት፤ ሰብአዊ ምብት፤በመራመድ ላይ ነው? ወይስ አፍሪካ የኋሊት ፈላጭ ቆራጭነት ወደ ነገሰበት የጭለማው ዘመን፤ ወደ ማን አለብኝነትና የጭቆና አገዛዝ፤ አምባገነናዊ አስተዳደር እየተጓዘች ነው?

አሜሪካ ዛሬ ከጠንካራ አፍሪካውያን ጋር በጥንካሬ ቆማለች ወይስ ከነዚያ አምባገነን ገዢዎች ጋር ተቃቅፋ ኣልጋ ላይ ተጋድማለች?

ፕሬዜዳንት ኦባማ  ሲያነሳሱዋቸው የነበሩት  የአፍሪካ ጀግና ልጆችስ የት ገቡ?

እንደ አሜሪካው ስቴት ዲፓርትመንት የሰብአዊ መብት ትግበራ የ2011 (ሜይ 2012) ዘገባ እነዚያ ፕሬዜዳንት ኦባማ ያሏቸው በርካታ ‹‹ጠንካራ አፍሪካውያን›› አሁን በወህኒ ቤት፤ በመከራ መቀበል፤ በስቃይ በመገረፍ፤ በመለጎም፤ በሽሽት ላይ፤ በሞት በመቀጠፍ፤ አለያም በስጋት ማቅ ተሸፍነው፤ ወከባውን በመሸሽ፤ በዘፈቀደ በየቦታው መያዝን፤ ከፍርድ በፊት በወህኒ መማቀቅን፤ስቃይን፤ ዱላን፤ ኢሰብአዊ  መከራን፤ለሕይወት አስጊ የሆነውን እስራት፤ በንግግ ር ነጻነት መገደብን፤ የፕሬስ ነጻነትን ማጣት፤ ሕገ ወጥ ብርበራን፤ ይህና ሌሎችም መሰል ስቃዮች ናቸው የአፍሪካውያን የእለት ተእለት ሕይወት፡፡ የአፍሪካ ማሕበረሰብና ተቋማት በምግባረ ብልሹ ባለስልጣናት፤ በሙስና፤ ግልጽነት በመጥፋቱ፤በማያስፈልግና ወደኋላ ጎታች፤በሆነ ቢሮክራሲ ማነቆ ተይዘው፤ ማንኛውም ጉዳይ በገዢዎቹ መዋቅር ውስጥ ባሉትና ትዕዛዝ ተቀብለው በሚተነፍሱ፤ በፖለቲካ ቁጥጥር ስር በሆኑ የፍትህ መዋቅሮች፤የተባሉትን ብቻ እሺ በሚሉና በራሳቸው ህሊና በማይገዙና በማይመሩ የፓርላማ አባላት ተከበው በጭለማ ውስጥ በመዳከር ላይ ናቸው፡፡  የአፍሪካውያን ማሕበረሰብ በሚያለያይ በሽታ ተከትበው፤በዘር፤ በነገድ፤ በጎሳ፤ በመንደር፤በጾታ፤ በቋንቋ፤በሃይማኖት፤በባህል፤በወረዳ ተለያይተው ነው ያሉት፡፡

የሰብአዊ መብትን ከሚደፍሩ ሃገራት ሁሉ ድፍረቱ በእጅጉ የበዛባት ሃገር ኢትዮጵያ ነች፡፡ በሜይ 2010 ገዢው ፓርቲ በፓርላማ ካሉት 547 ወንበሮች 545ቱን (99.6%) መቀመጫዎችን ‹‹አሸነፈ››:: በዚያ የምርጫ ወቅት የሁዋይት ሀውስ መግለጫ ያሳየው ጉዳዩ ‹‹አሳሳቢ››  የሚል ነበር:-

ፍትሃዊና ነጻ ምርጫን ለማካሄድ ሁኔታው ከምርጫው ቀናት አስቀድሞም የተመቻቸና ትክክል አልነበረም፡፡ በቅርብ ዓመታት የኢትዮጵያ ገዢ መንግስት የፖለቲካወን ምህዳር በማጥበብ የተቃዋሚዎችን አካሄድም ለመስንከል በማስፈራራትና በማዋከብ፤የራሱን ሜዳ እያሰፋ በማመቻቸት የሲቪክ ማሕበረሰቡን በማግለል፤የነጻ መገናኛ ብዙሃንንም ተግባራቸውንና ክዋኔያቸውን በመቀነጣጠስና በማገድ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች ደግሞ ሃሳብን በነጻ የመግለጽን ሂደት በእጅጉ የሚገድቡ ሲሆኑ ገዢው መንግስት እራሱ ከተቀበለውና ከፈረመው የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎች ጋር ጨርሶ የሚጻረርና ተለዋዋጭ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ያለው የሰብአዊ መብት ሁኔታ ‹‹ያሳስባል›› ከሚል በጨዋነት ከተሰነዘረው  የበለጠ ግንዛቤ የሚያስፈልገው ነው፡፡ድርጊቱ ቁጣን ሊያጭር ከድርገቱ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ና ከዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎች ጋር የሚዛመድ እንዲሆን ግፊት ያስፈልገዋል፡፡  በቅርቡ በወጣው ኢትዮጵያን የሚመለከተው የዩ ኤስ ስቴት ዲፓርትመንት የሰብአዊ መብት ዘገባ (ሜይ 2012) ‹‹ ከ100 የሚበልጡ የፖለቲካ ሰዎች፤ጋዜጠኞች፤እና የድረገጽ ተሳታፊዎች (በዓለም አቀፍ በተወገዘው የጸረሽብርተኝነት ሕግ) መንግስት የፕሬስን ነጻነት ገደበ፤የመያዝና የመጠቃት ፍርሃት ጋዜጠኞች እራሳቸውን እንዲቆጣጠሩ አስገድዷቸዋል፡፡ የእርዳታና የሰብአዊ ግልጋሎት ሰጪዎች  (CSO law)  አሁንም የጠነከረ እገዳ በማድረግ የማሕበረሰቡና የእርዳታ ሰጪ ድርጅቶች እንቅስቃሴዎች ከመዳከም ወደ መቆም እየተጓዙ ነው፡፡በጣም አሳሳቢ የሚባሉት የሰብአዊ መብት ችግሮች፤ ድብደባን በደህንነት ሰዎች መሰቃየትን፤ወህኒ ማጎርን፤በጣም የተበላሸ የወህኒ ሁኔታን፤ የሴቶችን ሕብረተሰባዊ  ልዩነትን፤…… በጁንና ሴፕቴምበር (2011) የተካሄደው ሁለተኛው ዙር አፈናና እስር፤በርካታ ስመጥር ጋዜጠኞችን፤የፖለቲካ ተቃዋሚ አባላትን፤ንቁ የፖለቲካ ተሳታፊዎችን፤አንዱዓለም አራጌን የአንድነትለፍትሕና ለዴሞክራሲና የመድረክን ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር ጭምር፤ታዋቂውን የድረገጽ ጸሃፊና ተሟጋች እስክንድር ነጋ፤ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ አባልን ናትናኤል መኮንንን ያካተተ ነው;;›››››››››

ካረን ጄ ሃንራሃን የዴሞክራሲ ቢሮ፤ የሰብአዊ መብትና የሌበር ዲፒዩቲ ምክትል  ጸሃፊ ለብሔራዊ አንዳውመንት በኦክቶበር 2012 ባደረጉት ንግግር

….በኢትዮጵያ ግብግብ ገጥሞናል፡፡ መሰረታዊው ጥየቄም ገዢው መንግስት በፖለቲካና ማሕበረሰቡ ተቋማት ላይ ጫናውን ሲያበዛና ገደቡ ልክ ሲያጣ፤ዴሞክራሲንና የሰብአዊ መብትን በአግባቡ ማራመድ የሚቻለው እንዴት ተብሎ ነው፡፡ ይህም በሲቪል ማሕበረሱ ላይ የሚደረግ ጫና፤የሜዲያዎች ነጻነት ማጣት፤በጸረ ሽብርተኝነት አዋጅ ሰበብ ጋዜጠኞችን የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት አፈናና ማሳደድ፤ለአእስር መዳርግ የሚያካትት ነው፡፡ ወደፊት መራመዱ ለመንግስትም ቢሆን የተቃዋሚዎችንና የሲቪል ሕበረሰቡን እድገት የሚያስከትል ይሆናል፡፡ኢትዮጵያዊያን ዜጎች መብቶቻቸውን ሙሉ በሙሉ ለመጠቀም ማስቻል ብቻ ሳይሆን የአሜሪካንና የኢትዮጵያ መንግስታት ሁለቱም የመረጋጋትና የልማት እድገትና ዋስትና ያገኛሉ፡፡

የአሜሪካን መሪዎች ምናልባትም ቀደም ሲሉ በቦታው ከነበሩትና ከፈላጭ ቆራጭና አምባገነኖች ተመሳሳይ ጥሪ የአሁኖቹ የአሜሪካ መሪዎች ሊማሩ ይችሉ ይሆናል፡፡ አንድ ወቅት ላይ ፕሬዜዳንት ትሩማን እንዳሉት፡‹‹ የተቃዋሚውን የመናገር ነጻነት ለማፈን የቆረጠ መንግስት የጉዞው አቅጣጫ አንድ ብቻ ነው፤ተደራራቢ ወደ ሆነና ለሁሉም ዜጎች የሽብርና ሁሉም በፍርሃት የሚኖርበት አካባቢ እንዲሆን በማድረግ አምቆ የመግዛት ስርአት፤›› ይህ ነው በኢትዮጵያ ያለው የማያከራክርና የማይካድ ሕይወትና ‹‹ጥሪ›› ‹‹አሳሳቢ›› የሚሉ ባዶ ቃላት አንዳችም ፋይዳ ሊናራቸው ሁኔታዎችን ሊቀይሩና የዜጎችን ሕይወት ሊለውጡ አይችሉም!

ዛሬ በአፍሪካ ያለው ያሜሪካ መምሪያ ብዙ ጉድለቶች ኣሉት

በዩ ኤስ ዲፓርትመንት ኦፍ ስቴት የአፍሪካ ጉዳዮች ሃላፊ የሆኑት ጆኒ ካርሰን አባባል  በአፍሪካ ውስጥ ሊያገለግሉ የሚችሉ ‹‹አምስት የአሜሪካንን ፍላጎት የሚያሟሉ ምሶዎች አሉ›› ይህም የሚያካትተው፤ (1) ዴሞክራሲውን የሚያግዙ እና የዴሞክራሲ መዋቅሮችን፤ ነጻ፤ ፍትሃዊና ግልጽ ምርጫዎችን የሚያጠናክሩ፤ (2) የአፍሪካን እድገት ልማት የሚያግዝ፤ (3) ግጭቶችን መከላከል፤ ማቅለል እና ውሳኔዎችን ማስፈጸም (4)ፕሬዜዳንታዊ ጅማሮዎችን እንደ ዓለም አቀፍ የጤና ጅማሮዎችን መደገፍ፤የወደፊቱን መመገብ፤ዓለም አቀፍ የዓየር ንብረትን ጅማሮዎችን መደገፍ (5) ከአፍሪካ ሃገርና ሕዝብ ጋር በሽግግር ሂደቶች ላይ እንደ አደንዛዥ እጽ ቁጥጥርን፤ ሕግ ወጥ የገንዘብ ዝውውርን፤ የሰዎች ሽያጭን›› ያካትታል:: እንደ ካርሰን አባባል ‹‹በአሁኑ ወቅት›› የዩ ኤስ ፖሊሲ በአፍሪካ በኮት ዲ ቩዋር በጊኒ፤በናይጄር፤መንግስታዊ ሰላማዊ ሽግግሮችን ረድቷል፡፡በናይጄርያ የተሳካ ምርጫ እንዲካሄድ አድርጓል፤የደቡብ ሱዳንን ነጻነት አረጋግጧል፡፡ በዴሞክራቲክ ኮንጎም የጾታንና የወሲባዊን ሁከቶችን ለማቆም በንቃት በመንቀሳቀስ ላይና በመካከለኛው አፍሪካ በመላው በመንቀሳቀስ ላይ ያለውን የሎርድ ሬዚስታነስ ሠራዊት ለማክሸፍም በጽናት በመንቀሳቀስ ላይ ነው፡፡ የወደፊቱን መመገብ የሚለው የዩ ኤስ ዓለም አቀፋዊ የምግብ ዋስትና ጅማሮ 12 የአፍሪካ ሃገራትን ያካትታል፡፡

የዩ ኤስ ዲፓርትመንት ኦፍ ስቴት የሰብአዊ መብት ዘገባ (ሜይ 2012)  የሂላሪ ክሊንተን ገለጻ፡ “እንደሃገር አስተዳደሪነቴ በዓለም ዙርያ ባደረግሁት ጉዞ የሰብአዊ መብትን ለማስከበርና የፍትሕና ስርአት ለማስከበር ሲሉ የራሳቸውን ሕይወት ለአደጋ ያጋለጡ በርካታ ሰዎች አጋጥመውኛል፤ በትልቁም ይሁን መጠኑ ባነሰ መልክ መንግስቶቻቸውን ተጠያቂ እንዲሆንና ለዓለም አቀፉ ሰብአዊ መብት ድንጋጌ ተገዢነት ይሞግታሉ፤ ቆራጥነታቸውና ድፍረታቸው ለሰላማዊ  መሻሻል አነሳሥ ነው፡፡ይህ ዘገባ ድፍረትና ጥንካሬያቸውን በሚገባ ዕውቅና በመስጠት እንደማሳሰቢያነትም ያገለግላል፡ ዩናይትድ ስቴትስ ሰብአዊ ክብርን ለማራመድ ከሚጥሩ ጋር አብሮ በመቆም በጥረታቸውም ላይ የዓለም ትኩረትና ድጋፍ ብርሃን እንዲያበራ ከማድረግ አንቆጠብም፡፡”

እነዚህ መጠነኛ ክንዋኔዎች ፕሬዜዳንት ኦባማ ከሰነዘሩዋቸው እነዚያ ግዙፍ፤ ተስፋ ሰጪ ቃላቶች ጋርና አስተዳደራቸው መልካም አስተዳደርንና ሰብአዊ መብትን በማስከበሩ ረገድ በአፍሪካ የተደረገው  ሲመዘን እጅጉን ተራርቀውና በማይመጣጠን ደረጃ ኣንሰው ይገኛሉ፡፡ አሁን ጊዜው ያለፈውን በማንሳት መወነጃጀያ፤ ጥርስ ማፋጪያ፤ ሆድ ማከኪያ፤ እና ጣት መቀሳሰርያ ግዜ አይደለም፡፡ ወደ ፕሬዜዳንታችን የትግል ጥሪ በመመልከትና ትኩረታችንን በማገናኘት ‹‹ወደፊት እንቀጥል›› በማለት የሞረሽ ጥሪ ማድረግ ነው የሚገባን፡፡

አሜሪካኖች በአብዛኛው የሚታወቁበት በቀጥታ አነጋገራቸው አካፋን አካፋ በማለታቸው ነው፡፡ እኔ ዘወትር በተራ አሜሪካውያንና በጥቂት ታላላቅ መሪዎቻቸው የማደንቅላቸው ባሕሪያቸው ነው፡፡የሚሉትን ያደርጋሉ የሚያደርጉትን ይላሉ፡፡ ‹‹ቀጥተኛ ተናጋሪው›› የሚባሉት ፕሬዜዳንት ሃሪ ኤስ ትሩማን ‹‹ለማንም መከራና ስቃይ አልመኝም፡፡ እውነቱን በምናገርበት ጊዜ እነሱ ግን መከራ ነው ይላሉ::›› ስለዚህም እኔም ትንሽ ቀጥተኛ ንግግር አደርገ ለሁ፡፡ ስለ ሰብአዊ መብት ጉራና እወጃ በቂ ያህል ሰምተናል፡፡ የአፍሪካን የሰብአዊ መብት ችግር ስለ መቅረፍ፤ በአፍሪካ መልካም አስተዳደርን ስለመገንባት ‹‹ስለ ግጥሚያው ጥሪ ወይም ስለፍላጎት ቅስቀሳው›› ‹‹ችግሮች‹› ‹‹አከራካሪ ጉዳይነት›› ስለሁሉም ርዕሶች በሚገባ እናውቃለን፡፡ በዲያስፖራው ኢትዮጵያዊያንም አሜሪካ መልካም አስተዳደርን ለማስፈንና ዴሞክራሲና ሰብአዊ መብትን ለማረጋገጥ ስላደረገውና ሳያደርገው በቸልታ ስለታለፈው፤ በቂ ጉርምርምታም፤ መነጫነጭ፤እንዲሁም ምሬት በበቂ አድምጠናል፡፡ ከእንግዲ ምንም የጎንዮሽ ንግግር አያስፈልግም ግልጡን በቀጥታ እና ቀጥተኛ የሆነ ድርጊት ማሳየት ብቻ ነው፡፡ በፕሬዜዳንት ኦባማ ሁለተኛ የስልጣን ዘመን፤በአፍሪካ መልካም አስተዳደርንና ሰብአዊ መብትን በሚገባ ተግባራዊ ለማድረግ ሁለት ምርጫዎች ብቻ ናቸው ያሉት፤ በቃን ብሎ በቁርጥ ‹‹ብድግ‹‹ : አለያም  እጅን  ኣጣጥፎ ኣፍን ለጉሞ ጭጭ በማለት ነው:: በሌላ አነጋገር: አሜሪካ ቆርጦ ከጠንካራዎቹ አፍሪካውያን ጋር በመቆም ትልቅነቱን ያስመሰክራል::  ካልሆነ ደግሞ ተሸመድምዶ በመድከም በ ምጽዋት፤በዓለም ባንክ፤ በአይ ኤም ኤፍ ገንዘብና ብድር በአፈሙዝ ሃይል ሥላጣን ይዘው ከሚገዙት ከጨካኞቹ ፈላጭ ቆራጭ የአፍሪካ መሪዎች ጋር ተቃቅፎ በውርደት መጋደም ነው፡፡

ጀግኖች  ኢትዮጵያውያን  መርጃው መንገድ፡ የት  ይጀመር?

በርካታ ልምድ ያካበቱት ኢትዮጵያዊያን ሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ኤች አር 2003ን  (“Ethiopia Democracy and Accountability Act of 2007”) በሚገባ ያስታውሱታል፡፡ያ የሕግ ረቂቅ በኣመሪካን ምክር  ቤት ቀርቦ ነበር፡፡ (H.R. 4423 “Ethiopia Consolidation Act of 2005”) በቅድሚያ በኮንግሬስማን በኒው ጀርሲው ክሪስ ስሚዝ የአፍሪካን የውጭ ጉዳይ ንዑስ ኮሚቴ በሚመሩበት ጊዜ የቀረበ ነው፡፡(ረቂቁ ቆየት ብሎ  በውጭ ጉዳይ ኮሚቴ H.R. 4423 and H.R. 5680 ብሎ ተሰይሞ ነበር፡፡) በ2007 የኒው ጀርሲው ኮንግሬስማን ዶናልድ ፔይን የኮሚቴው ሰብሳቢ ሲሆኑ ጉዳዩን ተረክበው  የ85 የኮንግሬስ አባላትን ድጋፍ ለማግኘት ችለዋል፡፡ ረቂቁ በ2007 የቤቱን ድጋፍ ቢያገኝም ወደ ሴኔት ቀርቦ ድምጽ ሊያገኝ አድል ኣልነበረዉም፡፡ በረቂቁ ሕግ ውስጥ በርካታ ለመልካም አስተዳደር፤ ለተጠያቂነት፤ ስለሰብአዊ መብት መከበረና መረጋገጥ፤ ስለዴሞክራሲ፤ ስለፍትህ መከበርና ስለ ሕግ የበላይነት ስለነጣ የፍትህ ስርአት፤ ስለፍትህ ባለሙያዎች ስልጠና፤ስለምርጫ ቦርድ ነጻና ገለልተኛ መሆንና ሌሎችንም አስፈላጊ የሆኑ ሕዝባዊና ሃገራዊ ጉዳዮችን ያቀፈ ነበር፡፡

የኢትጵያን ‹‹ማግኒቲስኪ  ሕግ”  

ፕሬዜዳንት ኦባማ በ2009 በአክራ ባደረጉት ንግግር አፍሪካውያን ‹‹በሽታንና አለመግባባትን ሊያሸንፉ፤ከመሰረቱ ጀምሮ ወደ ላይ ለውጥ ማምጣት ይችላሉ፡፡ ማድረግ ትችላላችሁ፡፡ ምክንያቱም በዚህ ሰአት ታሪክ እየገሰገሰ ነው›› አዎን ትችላላችሁ ብለው ለኣፍሪካኖች ተናግረው ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ሕግ በአሜሪካ ኮንግሬስ ማለፍ የሚገባው አሁን ነው፡፡በሁለቱም ወገኖች የፓርቲ አሰላለፍ በኩል ስምምነቱ አለና፡፡ በዴሞክራቶችም ሆነ በሪፓብሊካንስ የሰብአዊ መብት ጉዳይ ቅድሚያ የአየተሰተጠው ነዉ፡፡ የማግኒቲስኪ ሕግ ተብሎ ኣዲስ የዎጣው አመላከችና  ፈር ቀዳጅ የሆነ የሰብአዊ መብትን መደፈር የሚያስከብር ድንጋጌ ነው፡፡ይህን ሕግ በቅድሚያ ያነሱትና ያቀረቡት እንዲሁም በተዘዋዋሪ መልክ ድጋፋቸውንና በመጨረሻም ድምጻቸውን በመስጠት ያሳለፉት ሊመሰገኑ የሚገባቸው ናቸው፡፡ (* የለነገሩ ኦባማ አስተዳደር የንግዱን ሕግና የሰብአዊ መብቱን ድንጋጌ ማቀላቀል አያስፈልግም  የሚል አቋም ቢይዝም በመጨረሻው ላይ ግን ተስማምቷል::)

“የማግኒቲስኪ ሕግ”  በጣም ከፍተኛ የሆነ የሪፓብሊካኖች ድጋፍ ነበረው፡፡ የሪፓብሊካኑ አሪዞና ሴኔተር ጆን ማኬይን ‹‹ ስለማግኔቲስኪ ግፍና በደል ለመናገር፤ እንዲሁም ሌሎችም አሁን በሕይወት ያሉና በሩስያ ወህኒ ቤቶች አለ አግባብ በመሰቃየት ላይ ስላሉት መታገልና ለነጻነታቸው መቆም  አሜሪካ የሞራል ግዴታ አለበት››  በማለት አሳስበዋል፡፡ ‹‹ለቭላድሚር ፑቲንና ለሩስያ የሰርቆት መንግስት እንዲህ አይነቱ ኢሰብአዊ ድርጊትና የዜጎች በተለያየ መልኩ መብቶች መገፈፍና ለእስር መዳረግ፤ በወህኒ ስቃይ ማየትን እኛ አሜሪካውያን ልንቀበለው የሚገባን አለመሆኑን የምናሳውቅበት ነው፡፡ ይህ ሕግ ደግሞ ጸረ ሩስያ አይደለም፡፡ይልቅስ ሩስያን ደጋፊ ሕግ ነው:: እኔ ስለነሱ ግፍ ስተፈጸመባቸው እጨነቃለሁ፤በጸሎቴም አስባቸዋለሁ፡፡›› የአሪዞናው ሴኔተር ጆን ማኬን፤ ይህ ሕግ በሁሉም ሃገራት ላይ ተፈጻሚ ሊሆን ይገባል፡፡ የዴሞክራቲኩ ኒው ሃምፕሻየር ሴኔተር ጂያን ሻሂን አሜሪካ በሁሉም ቦታዎች ስለሰብአዊ  መብት ትኩረት ያደርጋል፤ ‹‹ስለ ሃገራቸው የሙስና ዝቅጠት ደፍረው ከሚናገሩት ጋር አብረን እንቆማለን፤ ይህ ሕግ በዓለም ላይ ላሉት ማግኒቲሰኪዎች ሁሉ ነው፡፡›› ሕጉ በዓለም አቀፍ ሁሉ እንደ ምሳሌ የሚወሰድ ነውና በየትም ቦታ እንደሚከበር እምነት አለኝ፡፡ ሁዋይት ሀውስም በዚህ ጉዳይ ላይ መግለጫ አውጥቶ ፕሬዜዳንቱ እንደሚፈርሙት ጠቁሟል፡፡  ‹‹አስተዳደሩ በሩስያ የዴሞክራሲ እውነታና የህግን የበላይነት ለማረጋገጥ ከሚሹና በዓለም አቀፍ ደረጃም እውን እንዲሆን ከሚጥሩ ከኮንግሬስና ከአጋሮቻችን ጋር መስራቱን ይቀጥላል›› ብለዋል ኦባማ::

ማግኒትኪ የሩስያ መሪዎች ሙስና ያጋለጠ ወጣት ጠበቃ ነበር፥ በዚህ ምክኒያት ባለስጣኖችጭ ኣስረው ኣሰቃይተው በስር ገደሉት:: የየሩስያ ፕሬዜዳንቱ ነጻ ካውንስል ለሲቪል ማሕበረሰብ ልማትና ሰብአዊ መብት ዋስትና በደረሰበት ማጣራት መሰረት፤ የማግኒቲስኪ ተይዞ መታሰር ከሕግ ውጪ የተፈጸመ መሆኑን አረጋግጧል፡፡  የፍርድ ቤቱ ሂደትም ማግኒቲስኪ በሩስያ ፌዴሬሽን ፍትህ በፍርድ ቤቱ፤ በአቃቤ ሕጉ፤ እንደተነፈገውና ምርመራ የተካሄደበትም በስርቆት በወነጀላቸውና ማንነታቸውን ይፋ ባወጣባቸው ግለሰቦች ነበር፡፡ በእስር ላይ በነበረበት ጊዜም አስፈላጊ የሆነውን የህክምና እርዳታ እንዳያገኝ ሆኖ በ8 የወህኒ ቤቱ ጠባቂዎች በመጨረሻው የሕይወቱ ሰአት በግፍ እንደተደበደበ ተገሎኣል፡፡ ድርጊቱንም ባለስላጣናቱ ከመካዳቸውም ባሻገር አንዳቸውም በድርጊታቸው የተነሳ ለጥያቄ እንኳን ወደ ፍርድ ቤት አልቀረቡም፡፡

ፍትሕን ተነፍገው በወህኒ በመሰቃየት ላይ ያሉ በርካታ ‹‹ኢትዮጵያዊያን ማግቲሰኪዎች›› አሉ፡፡ በ2005 በተካሄደው ምርጫ ወቅት ባዶ እጃቸውን ዴሞክራሲንና ሰብአዊ መብትን ለማስከበር ገዢው መንግስት እራሱ ያጸደቀውን ሕገ መንግስት እንዲከበር ለመጠየቅ ሰላማዊ ሰልፍ ያደረጉትን ንጹሃን 200 ዜጎች በፖሊስና በደህንነት አባላት ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር በተሰጠ ቀጥታ ትዕዛዝ በጥይት ተደብድበው መሞታቸውና ከ800 የማያንሱት በጠና መቁሰላቸው ተረጋግጦ እያለ፤ ይ ህንንም  በቀጥታና በተዘዋዋሪ የፈጸሙት ይከበርልኝ የዜግነት ክብሬ አይደፈር በማለቱ የተፈጸመበት የሰብአዊ መብት መገርሰስ ዓልም ሊፋረደው የሚገባ እንጂ በሕግ ማውጣትና በማስፈራራት ብቻ ሊታለፍ የሚገባው ሊሆን አይገባም፡፡ የነዚህና የሌሎችም በግፍ የተገደሉና ለመከራ የተዳረጉ ኢትዮጵያዊያን ድምጽ ከያሉበት ከፍ ብሎ ይጣራልና ሰሚ ሊያጣ አይገባውም፡፡

በዩ ኤስ ኮንግሬስ ለውጥ ማየት ታላቅ ደስታ ነው፡፡ በሰብአዊ መብትና በመልካም አስተዳደር አዲስ አስተሳሰብና አመለካከት ያለ ይመስላል:: እነዚህ ሁነቶችም የዓለም አቀፉ ድንጋጌዎችና የሰለጠነ ሕብረተሰብ አንድ አካል ናቸው፡፡ ለምንግስት ብቻ ሊተው የሚገባም አይደለም››:: ሰብአዊ መብት የሁሉም ሰብአዊ ፍጡር የጋራ ጉዳይ ነው፡፡ለሩስያው ጀግና  ሰርጂ ማግኒቲስኪ ጥሩ የሆነው  ህግ ለኢትዮጵያዊያኖቹ ጀግኖች ለ 16 ዓመቱ መለስካቸው አላምነውም ፤ ለ22 ዓመቱ ሃድራ ኦስማንም፤፤ለ50 ዓመቷ እቴነሽ ይማምም፤ለ23 ዓመቱም ቴዎድሮስ ግደይ፤ ለ24 ዓመቱም ጋሻው ሙሉጌታ፤ለ21 ዓመቱም ሌቺሳ ፋታሳም…..  በግፍ የተገደሉ ሰማታት ተገቢ ነው፡፡

ፕሬዜዳንት ኦባማ በ2009 በአክራ ‹‹አሜሪካ ራዕዩን (መልካም አስተዳደርና ሰብአዊ መብት መከበርን) በቃላት ብቻ ሳይሆን የአፍሪካን አቅም ሊያጠናክር በሚገባ መልኩ የማሻሻልና ቅድሚያ የመስጠት ሃላፊነት አለበት፡፡ በሞስኮ የዓለምአቀፋዊ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎች ሊከበሩ የሚገባበት ማስገደጃዎች ሊኖሩ እንደሚገባና እነዚህ ድንጋጌዎች መፋለስም እንደሌለባቸው በማሳሰብ ንግግር አድረጌያለሁ፡፡›› ብለው ነበር፡፡ ታሪክ በሂደት ላይ ነው! ‹‹የኢትዮጵየዊያን ማግኒቲስኪ ሕግ›› ሊኖረን ተገቢ ነው፡፡ይህም ከወዳጆቻችንና አጋሮችቻን በምናገኘው ትንሽ ድጋፍ እውን ይሆናል!

በትክክለኛው የአፍሪካ የሰብአዊ መብት ጎን መቆም ማለት በትክክለኛው የታሪክ ጎን መቆም ማለት ነው፡፡

ፕሮፌስር ዓለማየሁ ገብረማርያም በካሊፎርኒያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ሳን በርናርዲኆ የፖሊቲካ ሳይንስ መምሀርና የህግ ጠበቃ ናችው።

*የተቶረገመው ጽሁፍ (translated from):

http://open.salon.com/blog/almariam/2012/12/15/will_the_us_stand_by_the_side_of_brave_africans

(ይህን ጦማር ለሌሎችም ያካፍሉ::) ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮችን  ለማግኘት እዚህ ይጫኑ::

http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/category/al-mariam-amharic

http://ethioforum.org/?cat=24

 

Similar Posts

Leave a Reply