የሃይማኖት ነጻነት ጥብቅና በኢትዮጵያ

ከፕሮፌሰር  ዓለማየሁ  ገብረማርያም

ትርጉም  ከነጻነት ለሃገሬ

ለውድቀት የተዳረገው የሃይማኖት ነጻነት በኢትዮጵያ

በዚህ ባለፈው ሰኔ ወር ላይ ‹‹ አንድነት ለሃይማኖት›› በሚል ጽሁፍ በኢትዮጵያ ስለሚካሄደው የሃይማኖት ነጻነት ገፈፋ ያለኝን ስጋት ገልጬ  ነበር፡፡ በዚህም ሳቢያ ኢትዮጵያ ዉስጥ አዲሱ የሰብአዊ መብት መጣስ  አካሄድ በሃይማኖት ነጻነት ላይ ማነጣጠሩን አሳስቤያለሁ፡፡ ስጋቴን  ትንሽ ቀለል ያረገልኝ ስርአት የተላበሱት የክርስቲያኑና የሙስሊሙ የሃይሞነት መሪዎች በሃይማኖት ውስጥ የሚሞከረውን አግባብነት የሌለውን ጣልቃ ገብነት ጠንክረው መቃወማቸውን በማየቴ ነበር፡፡ መጣጣፌ ላይ አንዳልኩት ‹‹ላለፉት በርካታ ዓመታት›› ኢትዮጵያ የወንጀል፤ የጥቃት፤ የሰብአዊ መበት መደፈር፤ተፈጥሮ የቸረውን መብት መርገጫ ማዕከል ሆና ኖራለች፡፡ አሁን ደግሞ የኢትዮጵያ የሃይመኖት አባቶች ኢትዮጵያ የሃይማኖት ነጻነት የሚገፈፍባት ሃገር ሆነች እያሉ ያማርራሉ›› ፡፡  የሙስሊሙና የክርስትና ሃይማኖት መሪዎችና አማኞች፤ ጠንክረውና እጅ ለእጅ በመያያዝ በአንድነት ሆነው፤ ለዕምነታቸው ነጻነት ለማስገኘትና መብትቸውን ለማስጠበቅ ሕሊናቸው በሚያዛቸው መንቀሳቀስ እንዲችሉ በሰላማዊ አምቢታ ጸንተው ቆመዋል፡፡

የገዢው መንገስት ባለስልጣናት ይህን በሕገ መንግስቱ ላይ በግልጽ የተቀመጠውን ድንጋጌ በመዘንጋት አለያም አውቀው አናውቅም በማለት በቸልተኝነትና በማንአለብኝነት ይህን የነጻነት የእምነት በነጻ የመንቀሳቀስ ሂደት በአክራሪነት በገዲድ በመተርጎም እንቅስቃሴውን ለማዳከም በመጣር ላይ ናቸው፡፡በቅርቡ ያለፉት መለስ ዜናዊ፤ ሲናገሩ ‹‹በቅርቡ በተከናወነው የጌታችን መድሐኒታችን የጥምቀት በዓል በተከበረበት ወቅት አንዳንድ የክርስቲያን እምነት ተከታዮች የክርስቲያን መንግስት ይቋቋምልን በማለት መፈክር ይዘው ወጥተዋል፤ እንዲሁም እምነታቸውን በነጻ ሃይማኖታቸውም ከጣልቃ ገብነት የጸዳ እንዲሆን ያነሱትን የሙስሊሙን ጥያቄ፤ ይህን ጥያቄ የሚያነሱት የአልቃይዳ ተባባሪ የሆኑ የ‹‹ሳላፊ›› ጥገኞች›› በማለት ታርጋ ለጥፈውባቸዋል፡፡ መለስ ውንጀላቸውን ቆርጠው በመቀጠል ‹‹ለመጀመርያ ጊዜያት የአልቃይዳ ሴል በኢትዮጵያ ታየ በማለት፤ አብዛኛዎቹም በባሌ፤እና በአርሲ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ ይህ ማለት ግን በኢትዮጵያ ያሉት ሳላፊስ በሙሉ አልቃይዳ ናቸው ለማለት አይደለም፡፡ አብዛኛዎቹ አይደሉም፡፡ሆኖም ግን እነዚህ ሳላፊዎች ትክክለኛውን (የሙስሊም) ሃይሞኖታዊ ትምህርት ሲያፋልሱ ታይተዋል ብለው ነበር››፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ዓለምአቀፋዊ የሃይሞኖት ነጻነት ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ  (ዩ ኤስ ሲ አይ አር ኤፍ)  ላይ ባለፈው ወር ይህን አክራሪ ናቸው የሚለውን አባባል ማጣጣል ብቻ ሳይሆን፤ በኢትዮጵያ ባሉ ኢትዮጵያዊያን ላይ የሚደረገውን የሃይማኖት ተጽእኖና ጭቆና እያሳሰበው መሆኑንም፤ ጥየቄያቸው ግን እንደሚባለው ሳይሆን በሃገሪቱ ላይ ባሉት የሙስሊም አማኞች ላይ በሚደረግ የጉልበትና የግፍ አካሄድ እምነቱ ከሚፈቅደውና ሙስሊሙ ሕብረተሰብ ከሚያምንበትና ሲከተለው ከነበረው አካሄድ ውጪ በሆነ አዲስ መጥ ስርአት እንዲያምን ለማስገደድ ሰለሆነ መንግስት ከድርጊቱ እንዲታቀብ አሳስቧል፡፡ ሲዘግቡም፥

የኢትዮጵያ ገዢ መንግስት ፍላጎቱ አልሃበሽ የሚባለውን የዕምንት አመለካከት በሙስሊሙ ማሕበረሰብ ላይ በግዴታ በመጫን ለዝንተዓለም ሲከተሉት ከነበረው የሱፊ አመለካከትና ስነስራት ለመለየት እያስገደደ ነው፡፡ ገዢው መንግስት ከዚህም ባሻገር የሙስሊማኑ የሃይማኖት አባቶችን ከባለዕምነቶቹ ፍላጎትና ፈቃደኝነት ውጪ፤ ምርጫውን በራሱ በማካሄድ ሹመኞቹን ጭኖባቸዋል፡፡ ቀደም ሲል በነጻነት የሚንቀሳቀስ ተጽእኖ የሌለበት በመባል ሲታወቅ የነበረው የኢትዮጵያን እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤትን አሁን ገዢው መንግሰት በራሱ ምደባ ስልጣን በያዙት ለገዢው መንግስት አገልጋይና ጉዳይ አስፈጻሚዎችን አስቀምጦበታል፡፡ የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ ብሎ የሙስሊሙ ሕብረተሰብ ያስቀመጣቸውን ወኪሎቹን ለኔ መመርያ ካልተገዛችሁ በሚል አመለካከት፤ ሰብስቦ በተፈጠረና አንዳች የእውነት ፍንጣቂ የሌለበት በተደጋጋሚ በንጹሃን ላይ ሲለጠፍ ያለውን ሽብርተኛ በማለት ወደ ወህኒ ማውረድ በሃገሪቱ ባሉት ሙስሊማን ላይ ተጽእኖ ለማድረግና ለመቆጣጠር አንመች ያሉትን በማስፈራራት ማግለል ይዞዋል፡፡ በዚህ ሰበብም በኦክቶበር 29 ላይ የኢትዮጵያ ገዢ መንግስት 29ኙን የሙስሊሙ ማሕበረሰብ ወኪሎችና ሰላማዊ ተንቀሳቃሾች ሽብርተኞችና እስላማዋ መንግስት ለመመስረት የተነሳሱ ናቸው በማለት ወንጅሏቸዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ዓለምአቀፋዊ የሃይሞኖት ነጻነት የዩናይትድ ስቴትስ ዓለምአቀፋዊ የሃይማኖት ነጻነት ኮሚሽነር አዚዝ አል ሂብሪ በግልጽ ሲናገር:

ይህ የወቅቱ መሰረተ ቢስ ክስና ውንጀላ የኢትዮጵያ መነግስት ተቃዋሚዎቹን ዝም ለማሰኘትና ለማሰር፤ የሙስሊሙም ሕብረተሰብ ያነሳውን ሰላማዊና ሕገመንገስታዊ የዕምነት ነጻነት ጥያቄ በሰበብ አስባቡ ለማጨናገፍና ዓለም አቀፋዊ የሆነውን የዕምንት ጥያቄ ለማክሰም የሚጠቀምበት ዘዴ ነው፡፡ እነዚህ በቁጥር አነስተኛ የሆኑት ለእስር ቢዳረጉም የዓላማው ደጋፊዎች የሆኑት በሺህ የሚቆጠሩ ናቸው በሰላማዊ መንገድ ጥያቄውን አንስተው እንደመጥ ያሉት፡፡ የኢትዮጵያ ገዢ መንግስት በሙስሊም ዜጎቹ እምነት ውስጥ ጣልቃ መግባቱን ማቆም አለበት፡፡አለአግባብም ባልሰሩትና ባልፈጸሙት ውንጀላ የታሰሩትንም ሊለቅ ተገቢ ነው ብሏል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ዓለምአቀፋዊ የሃይሞኖት ነጻነት ኮሚሽንም ያነሳቸውን ጭብጦች በተመለከተ ሊተኮርባቸው የሚገቡ ጉዳዮች አሉ፡፡ በቅድሚያ ይህ የዩናይትድ ስቴትስ ዓለምአቀፋዊ የሃይሞኖት ነጻነት ኮሚሽን ድርጅት መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት፤የሰብአዊ መብት ተሟጋች፤ ወይም የመንግስት አፈቀላጤም  አይደለም፡፡ የ1998 ዓመቱን ዓለም አቀፍን ሃይማኖታዊ ነጻነት ድንጋጌ አስመልክቶ በዩናይትድ ስቴትስ ምከር ቤት (ኮንግሬስ) የተቋቋመ ነጻ የሆነ ኮሚሽን ሲሆን ተግባሩም በዓለም አካባቢ ባሉ ሃይማኖታዊ ክስተቶች ስለሚከናወኑትና ስለነጻነታቸው ሁኔታ ዘገባ እያጠናቀረ፤ አስፈላጊ ሲመስለውም የፖሊሲ ሃሳብ ለፕሬዜዳንቱ፤ለሃገር አስተዳደር፤ እና ለኮንግሬሱ ማቅረብ ነው፡፡  ይህን ኮሚሽን ለመምራትም ዕውቅና ያላቸውና በዓለም አቀፉ ሃይሞኖታዊ እውነታዎችን ስርአት ላይ በቂ ዕውቀትና ግንዛቤ ያላቸው ግለሰቦች፤ ስለውጭ ግንኙነት፤ዓለም አቀፋዊ ስለሆነው የሰብአዊ መብት ጠንቅቀው የተረዱና ግንዛቤያቸውም የሰፋ የሆኑት ተመርጠው የሚካተቱበትና ስራውን የሚያካሂዱበት ነው፡፡ ይህ ኮሚሽን ማንኛቸውንም በዓለም ተቀባይነት ያላቸውን ድንግጌዎች ሁሉ በማክበር የማስከበር ሃሳብ ለሚመለከታቸው በማቅረብ ተግባራዊ እንዲደረግ ይጥራል፤ ይሟገታል፡፡

የዚህ (የ ዩ ኤስ ሲ አይ አር ኤፍ) የዩናይትድ ስቴትስ ዓለምአቀፋዊ የሃይሞኖት ነጻነት ኮሚሽን ማስረጃና ምስክርነት በኢትዮጵያ ውስጥ የሃይሞነታዊ እምነት ነፃነት መጣሱን መንግስታዊ ጥቃትም እየደረሰበት እንደሆነ በሚገባ ያረጋገጠ ነው፡፡

የኢትዮጵያ  ዓለም አቀፋዊና  ሕገመንግስታዊ  ግዴታ  የሃይማኖት  ነጻነትንም  ያካተተ ነው

የገዢው መንግሥት ባወጣውና ባጸደቀው ሕገመንግስት መሰረት የሃይማኖት ነጻነትን የማክበር ግዴታ እንዳለበት ደንግጓል፡፡ በዚህ ድንጋጌውም ገዢው መንግስት ጣልቃ በመግባት ነጻ አንደሆነ በሚገባ ተቀምጧል፡፡ የኢትዮጵያ መንገስት ዓለማዊ መንግስት ነው እንጂ መንፈሳዊ መንግስት አልተመሰረተበትም:: የህገ መንግስቱ አንቀጽ 11 በሃይማኖትና በመንግስት መሃል ደንግጎ መንግስትም በሃይሞነቱ ሃይማኖቱም በመንግስት ውስጥ ጣልቃ እንዳይገቡ ያግዳል፡፡ አንቀጽ 27ም እንደ የሃይመኖቶች የነጻነት አንቀጽ ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡ በመሆኑም ‹‹ሁሉም እንደየእምነታቸውና ፍላጎታቸው በነጻ የማሰብን፤እና የሃይማኖት ነጻነትን›› ያረጋግጣል፡፡ ማንም ሃይማኖትን መቀበልም ሆነ ወይም ወዳሰኘው ሃይማኖታዊ እምነት መዞርን፤ በግልም ሆነ በቡድን አለያም በመሰባሰብ ተደራጅቶ ማምለክን በምርጫው ማከናወንን ይፈቅዳል፡፡

የአንቀጽ 11 እና 27 ሕገመንግስታዊ ቋንቋ አጠቃቀም በቀጥታ ቃል በቃል ከዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌ የተገለበጠ ነው፡፡ይህም በዲሴምበር 10 1948 በኢትዮጵያ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ አንቀጽ 18 የዓለም አቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ቃል ኪዳን፤በጁን 11 1993 በኢትዮጵያ ተቀባይነት አግኝቶ ጸድቋል፡፡ በዚህም ድንጋጌ መሰረት ማንም ቢሆን የሃይማኖት የሰብአዊ መብትና በነጻ የማሰብ መብቱ ይጠበቅለት ዘንድ የግድ ነው፡፡ የአፍሪካውም (ባንጁል) ቻርተር ከዓለም አቀፋዊው ድንጋጌ ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡በየድንጋጌውም ላይ የዓለም አቀፉን ድንግጌ በማክበር መተግበር እንዳለበት ያረጋግጣል፡፡ ኢትዮጵያም የሁለቱም ቻርተሮች ፈራሚ ነችና ድንጋጌዎቹን በተቀረጹበት መልክ ማክበርና ሕዝቦቿም ተጠቃሚ እንዲሆኑ  ቃሏን ማክበር ስላለባት ገዠው መንግስትም ከዚህ ውጪ ትርጓሜ ሊሰጥበት አይችልም፡፡

የኢትዮጵያ ዢው መንግስት ለዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች በገባው ግዴታ መሰረት በራሱ ሕገመንግስት ላይ ያሰፈራቸውን መብቶች መከበርና ሳይሸራረፉ ለሕዝቡ መቆማቸውን ማረጋገጥ ይጠበቅበታል

ግዙፍ የሆነና በነጻ ወገኖች የተረጋገጠ፤ በቂና ታሪካዊ ማስረጃ ያለው፤ የድርጊቱ ሰለባ ከሆኑትና ከሌሎችም የተጠናቀረው እውነታ የሚያሳየው መንግስታዊ የሆነ የሃይማኖት ነጻነት ጥሰት መኖሩንና ጉልህ የሆነ የሰዎች የእምነትና ሕገመንግስታዊ መብትም መጣስ መኖሩን የሚያስረዳ ነው፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ከሃይማኖቱ ተከታዮች ፍላጎትና መሪዎቻቸውም ባላመኑበት መንገድ ጫና በመፍጠርና ሃይልና ማስገደድ ባለው ሂደት መሪዎች መርጦ ከማስቀመጡም ባሻገር አዲስ ስርአት በማምጣት የአልሃበሽን የእስልምና ወገናዊ እምነት ለመጫን ነው ዓላማው፡፡በሃይማኖታዊው ዋና ፍሬ ነገር ላይ በማትኮር የሃይማኖት አባቶች በማለት የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ካውንስልን እንዲመሩ መንግስት መርጦ  በተለያዩ የሙስሊሙ ኮሙኒቲ አባልታ ባሉበት ሁሉ 11 የሪጂኖች የእስልምና ከውንስል ብሎ ማስቀመጡ  አግባብነትም ሆነ ተቀባይነትም የሌለው ተግባር ነው፡፡ መንግስት በመስጊድ ሊደረግ የሚገባውን የምርጫ ሂደት በማፋለስ በመንግስት ቁጥጥር ስር ባሉ ስፍራዎች እንዲካሄድ ማደረጉ  የሚፈልጋቸው አገልጋዮቹ ያለአግባብ ስልጣኑን ይዘው እንዲያገለግሉት ለማድረግ ብቻ ነው፡፡ ይህን ሂደት አንቀበልም ሃይማኖታዊ ስርአትም የተከተለ አይደለም በማለት ተቃውሞ ያቀረቡትንም በማግለል፤ ከቦታቸው እንዲነሱ አድርጓል፡፡ ከተነሱም በኋላ ለእስራት ዳርጓቸዋል::  በንጸህናና በሰላማዊ መንገድም የተበላሸው እንዲስተካከል አላግባብ የተከናወነውም ምርጫ እንደቀየር ሃሳብ ያቀረቡትን ከማሰርም አልፎ ቀሪዎቹንም ሱገቡና ሲወጡ በደህንነቶች ቁጥጥርና ክትትል እንዲደረግባቸው በማድረግ ሰላሙን ሁሉ በማደፍረስ ላይ ነው፡፡ በመንግስት ተመርጠው የተቀመጡትም አገልጋዮች ተቀባይነት አጥተው ከቢሮ ማቀፍ አላለፉም፤ ይልቁንስ የመንግስት መጠቀሚያ ሰላዮች ተብለው በብዙሃኑ የሙስሊም እምነት ተከታዮች ከመፈረጅ ውጪ ያገኙት አንዳችም ነገር የለም:: ያገኙት ነገር ቢኖር የመንግስትን ግልጋሎት ማከናወን ብቻና ከመንግስት የሚቸራቸውን ነው፡፡ በዚህም መሰረት የሙስሊሙን ህብረተሰብ ወደማያምንበትና ወደተበላሸ እምነታዊ ስርአት ማካተት ጨርሶ የማይቻል ጉዳይ ነው፡፡

ገዢው መንግስት በጣልቃ ገብነቱ ላይ ተቃውሞ ባነሱት ሙስሊማን ላይ  በለጠፈው ሽብርተኝነት የወንጀል ክስና  ሌላም ክህደት ለሞላው ውንጀላው አንዳችም ማስረጃ ማቅረብ አልቻለም፡፡  እነዚህ በከንቱ ለእስር የተዳረጉት የነጻነት ተሟጋቾች፤ከውጭ ሃይል ጋር አላቸው ስለተባለው ግንኙነት፤ ሥልጣን ለመያዝ ተብሎም ስለተነሳው ጉዳይ፤ የሙስሊም መንግስት ይቋቋም ብለዋል ስለተባለበትም ቢሆን ወንጃዩ መንግስት አንዳችም ማሰረጃ ለማቅረብ አልበቃም፡፡ ማንኛቸውም ነጻ ወገኖችና ታዛቢዎች ቢሆኑ ያረጋገጡት፤ ሕገመንግስታዊ መብታቸውን በሰላማዊ መንገድ ለማስከበር መንቀሳቀሳቸውን፤ የራሳቸውን መሪዎችና የእስልምና ጉዳዮች የካወንስል መሪዎች እንምረጥ ከማለት ውጪ አንዳችም ሌላ ሁኔታ እንዳላዩ ነው፡፡ ይሄ ደግሞ ተገቢያልሆነ ጥያቄ አይደለም፡፡ ሕገመንግስታዊ መብታቸው ነው፡፡ መንግስት መርጦ ያስቀመጣቸው ሹማምንት ሊያገለግሏቸውም ሆነ መብታቸውን ሊያስጠብቁላቸው የማይችሉና፤ በምርጫውም የሙስሊሙን ይሁንታ ያልተሰጡ በመሆናቸው አይረቡንም ነው አባባላቸው እናም ልክ ናቸው፡፡ እነዚህ የተመረጡባቸው ሹመኞች እንቅስቃሴያቸው የሙስሊሙን ሕብረተሰብ ለመከፋፈል፤ ሰላማዊውን ሕብረተሰብ ለማበጣበጥ፤ በሃገር አቀፍ ደረጃ በሙስሊሙ ሕብረተሰብ ዙርያ ሰላም እንዲጠፋ ማድረግ ነው፡፡

ገዢው መንግስት ‹‹የጸረሽብርተኝነት ሕግ›› ከጥቅም ውጪ ጅራፉን የማጮህ አርማውን  የማውለብለብ  ሱስ  አለበት

ገዢው መንግስት የሃይማኖት ነጻነትን፤የጽሁፍና የፕሬስ (ብዙሃን) ነጻነትን፤የሕዝቡን ሃሳቡን በነጻ የመግለጽ ነጻነትን ባገደና በጣሰ ቁጥር የራሱን ሕገመንግስት እየጣሰ መሆኑን እያወቀ ይክዳል፡፡ በትንሹ ለእስር የዳረጋቸውን 29 የሙስሊሙን ታጋዮች፤ በሽብርተኝነት ሲወነጅል ያው በተደጋጋሚ የታየውን የፈጠራ ሽብርተኝነትን ታርጋ መለጠፉን በመቀጠል ሲያደርገው የነበረውንና በብዙ ማስረጃዎች ሊረጋገጥበት የሚችለውን የሃሰት ውንጀላ መድገሙ እንጂ አዲስ አይደለም፡፡ ይህም የዚህ መንግስት መታወቂያው ሆኗል፡፡ አሁን ያለውን የኢትዮጵያ ምስቅልቅል ሁኔታ ለማስተካከል ይሄ በሽብርተኝነት ነጻና ሰላማዊ ሰዎችን መወንጀልና ማሰር መፍትሔ ሊሆን አይችልም፡፡ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ሊገነዘቡት ያልቻሉት የውሃ ቅዳ ውሃ መልስ የሞኝ ጨዋታቸው ‹‹ጸረሽብርተኝነት›› ለገዢው መንግስት ያተረፈለት ነገር ቢኖር ችግሮችን፤ የሚነሱ ሃሳቦችን፤ህዝባዊ ፍላጎቶችን፤ እውነትን ለማየት እንዳይችል አይኑን መጋረድ ብቻ ነው፡፡ ሕዝቦች ሰብአዊ ክብርን ይሻሉ፤ በስልጣን ላይ ባሉ ሁሉ ሕዝብ ሊከበርና ሰብአዊ መብቱም ሊጠበቅለት ተገቢ ነው፡፡ ሕገመንግስታዊ መብታቸውን ባነሱ ቁጥር በስልጣን ላይ የተጣበቁት እየደነበሩ ሊወንጅሏቸው ጨርሶ ተገቢ አይደለም፡፡

የመንግስቱ መሪዎች‹‹ጸረ ሽብርተኝነትን ሕግ›› እንደጋሻ አንጠልጥለው ሰላማዊ ቅዋሜ አንሺዎችንና በሃይመኖታችን ጣልቃ አትግቡብን በማለት ለሰልፍ የሚወጡትን መኮነንንና ማሰርን ማንገላታትን መፍትሔ አድርገው ማሰብ ከጀመሩ ሰነበቱ፡፡ አንድ የማይታያቸው ክፉ ነገር ግን በሕዝቡ ሕሊናና ልብ ውስጥ እየሰፋና እያደገ፤ ምሬቱም እየከረፋውና እየጎፈነነው በመሄድ ላይ ያለውን የህዝብ ብሶት ማወቅ አለመቻል ወይም ችላ ማለታቸው ነው፡፡ ከትምህርት ደረጃ መውደቅና ጨርሶም ለመማር አለመቻል፤ ሥራ አጥነት፤ እና ተስፋ መቁረጥ ጭርሱን ሰብአዊነታቸው ከመሰረቱ እንዲጎዳና ለችገር እንዲጋለጡ በመዳረጋቸው ወጣቱ ትውልድ እራሱን ለማሻሻልም ሆነ ለሃገሩ ልማታዊ እድገት ተሳትፎ ለኑሮው የሚሆን ስራ ላይ እንዳይሳተፍ በመደረጉ ልቡ ለጊዜው ዝም ያለ ቢሆንም እያመረቀዘ አንድ ቀን የሚፈነዳ ነው፡፡ አሁን በስልጣን ላይ ያሉት አሁን ረጋ ያለ የሚመስላቸው ይህ የወጣት ብሶት ምሬት መከራ፤ ግለቱ ጨምሮ ሲፈነዳና ወጣቶቹም ከተጫነባቸው ፍርሃት ሲላቀቁና ፍርሃት አልባነት ሲነግስላቸው፤ የተስፋ መቁረጥ ክረምት ወጥቶ የተስፋና የመልካም ራዕይ ጸደይ ሲመጣ ልክ እንደ ‹‹አረቡ ጸደይ›› ያ የታሰበውና ታፍኖ የነበረው መብት ነጻነት እኩልነት አብቦ ሃገሩን በአዲስ አበባዎችና ልምላሜ እድገት ያለብሰዋል፡፡ የዚያን ጊዜ ታዲያ ያ ሽብርተኝነትና የጸረሽብር አዋጅ ፍለጋውን ወደ እውነተኞች አሸባሪዎችና ሕጉን መቀለጃና ሃጢአት መሸፈኛ ወዳደረጉት ያለፈባቸው በማድረግ ሃቃዊ ስራውን ማከናወን ይቀጥላል፡፡

ይህ አሁን በመኩራራትና በማን አለብኝነት እየተኮፈሰ ያለው ሞኝ ስብስብ ከሁለቱ የአሜሪካን መንግስት ከፍተኛ የህግ ዳኞች ሊማሩ ይችሉ ይሆናል፡፡ ‹‹የራሱን ህግ ማክበር ከተሳነው መንግስት የበለጠ የመንግስትን መሰረት የሚጥል የለም፡፡ የኛ መንግስት በራሱ ምሳሌነት ሕዝቡን ሀሉ ለህግ እንዲገዛ ያስተምራል፡፡ መንግስት እራሱ ሕግ አፍራሽ ከሆነ፤ ሕግን መናቅን መጣስን ነው የሚዘራው፡፡በዚህም ሁሉም ሰው ሕግን በእጁ እንዲያደርግና እንደፈቀደ እንዲሆን በመጋበዝ መተረማመስ (አናርኪ) እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡››

የዩናይትድ ስቴትስ ዓለምአቀፋዊ የሃይሞኖት ነጻነት ኮሚሽን እንዳለው: መንግስት ያገታቸውን የሙስሊሙን መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትና ሌሎቹንም ታጋቾች በመፍታት፤በሃይማኖት ላይ የጣለውን እግድ ማንሳት ኣለበት፡፡

መንግሥት በራስ ሕግ አፍራሽ ከሆነ፤ የራሱን ውድቀት ያፋጥናል፡፡

የተቶረገመው ጽሁፍ (translated from): http://open.salon.com/blog/almariam/2012/12/02/in_defense_of_religious_freedom_in_ethiopia

(ይህን ጦማር ለሌሎችም ያካፍሉ::) ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮችን  ለማግኘት እዚህ ይጫኑ::

http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/category/al-mariam-amharic

http://ethioforum.org/?cat=24

 

Similar Posts

Leave a Reply