አስታውሳለሁ! እንዴት እረሳለሁ!!

አስታውሳለሁ! እንዴት እረሳለሁ!!

ከፕሮፌሰር  ዓለማየሁ  ገብረማርያም

ትርጉም  ከነጻነት ለሃገሬ

በ ሰኔ 6-8 እና በ ህዳር 1-4 2005 (እንዳሮፓ አቆጣጠር) በ በግንቦት 2005 የተካሄደውን ምርጫ ተከትሎ ኢህአዴግ ያወጣውን ሕገ መንግሥት በማመን ባዶ እጃቸውን ወደ አደባባይ የወጡ ንጹሃን ወንዶች፤ሴቶች፤ሕጻናት ኢትዮጵያዊያን በቅርቡ ሕይወታቸው ባለፈው በመለስ ዜናዊ ቀጥተኛ ትእዛዝና ቁጥጥር ሕይወታቸው በአሰቃቂ ሁኔታ በጥይት ተደብድበው ተገድለዋል። በአቶ መለስ ዜናዊና በፓርላማው ሕጋዊ ሆኖ የተዋቀረው የአጣሪ ኮሚሽን  አጣርቶ እንደዘገበው እውነታ፤ “ባዶ እጃቸውን በሕገ መንግሥቱ ላይ በጸደቀው መብታቸው መሰረት ወደ አደባባይ ከወጡትና ሰላማዊ ሰልፍ በማካሄድ ላይ ከነበሩት መሃል 193ቱ፤ እና እንዲሁም በመንግሥት ወህኒ ቤት ታስረው ባሉት በርካታዎች ላይ ከፖሊስ በተተኮሰ ጥይት ሕይወታቸው አልፏል 763ም ቁስለኛ ሆነዋል፡፡ አጣሪ ኮሚሽኑ ሁኔታውን በአግባቡና ከወገንተኛነት ነጻ በሆነ መንፈስ በማጣራት የንጹሃኑ ደም አለ አግባብ መፍሰሱን ሕይወታቸውም መቀጠፉን ዘግቧል፡፡ ገዢው መንግሥትና የገዢው መንግሥት መገናኛ ብዙሃን፤ እንዲሁም ወንጀሉን የፈጸሙት ፖሊሶችና ሌሎች የጦሩ አባላት የሰነዘሩትን ክስ ኮሚሽኑ በማጣራት ሂደቱ ጨርሶ ተአማኒነት የሌለው ፈጠራ ነው ብሎ አጣጥሎታል፡፡ በአጣሪው ዘገባ መሰረት “በሰላማዊ ሰልፈኞቹ በንብረት ላይ የደረሰ አንዳችም ጥፋት አለመኖሩን አረጋግጧል፡፡ አንድም ሰልፈኛ ሽጉጥም ሆነ ቦምብና ሌላም መሳርያ የያዘ አልነበረም፡፡ ከመንግሥት ታጣቂ ሃይሎችም የተተኮሱት ጥይቶች ሰልፈኛውን አስፈራርቶ ለመበተን የተቃጡ ሳይሆኑ በማነጣጠር ለመግደል ሆን ተብለው መተኮሳቸውን የሚያሳየው ሟቾችና ቁስለኞች የተመቱት ደረታቸውንና ጭንቅላታቸውን መሆኑ ነው፡፡”

(ጠቃሚ መረጃ፡-  የኮሚሽኑ የ193 የሟች ዜጎች ዘገባ የሚያጠቃልለው ሰኔ 6-8 እና በ ህዳር 1-4 2005 (እንዳሮፓ አቆጣጠር) ያለውን ግድያ ብቻ ነው፡፡ የ2005ቱን ምርጫ ተከትሎ በግልጽ ከተመዘገበው ግድያ ውጪ በመንግስት የጦር ሃይሎች ለሞት የተዳረጉት ቁጥራቸው እጅጉን የናረ ሲሆን ይህም የግድያዎቹ ዘገባ ኮሚሽኑ ዘገባውን ከሚያቀርበበት ከተወሰነው ወቅት ካለፈ በኋላ በመታወቃቸው ነው፡፡)

አስታውሳለሁ: እንዴትስ ይረሳል!

የሰማእታት ዝርዝር:

ረቡማ እሸቴ እርጋታ 34  ግንበኛ፡፡ መልሳቸው ደምሴ አላምነው 16 ተማሪ፡፡ ሀድራ ሹክራ ኡስማን 22፤ ስራዋ ያልታወቀ፡፡ ጃፈር ሰይድ ኢብራሂም 2፤8 አነስተኛ ነጋዴ፡፡መኮንን 17 ስራው ያልታወቀ፡፡ ወልደሰማያት: ስራ አጥ፡፡ ባሕሩ  ምን ላርግህ ደምለው  ስራው ያልታወቀ፡፡ፈቃደ ነጋሽ፤ 25 ሜካኒክ፡፡ አብራሃም  ይልማ፤ 17 ታክሲ ረዳት፡፡ ያሬድ በላቸው እሸቴ፤23 አነስተኛ ነጋዴ፡፡ ከበደ ወ/ጊ/ሕይወት፤17 ተማሪ፡፡ ማቲያስ ግርማ ፍልፍሉ 14 ተማሪ፡፡ ጌትነት አያሌው ወዳጆ፤ 48 አነስተኛ ንግድ፡፡ እንዳልካቸው መገርሳ ሁንዴ፤18፤ ስራው ያልታወቀ፡፡ አልዩ ጠዩሱፍ ኢሳ 20  የቀን ሰራተኛ፡፡ ሳምሶን ንጉሴ ያዕቆብ 23 የህዝብ ትራንስፖርት፡፡ አለበለው አሸናፊ አበበ፤18 ተማሪ፡፡ በልዩ ባዩ ዘአ፤ የትራንስፖርት ረዳት፡፡ ዩሱፍ አብደላ ጀማል፤23 ተማሪ፡፡ አብርሃም ስሜ ወ/አገኘሁ፤23 የትራንስፖርት ረዳት፡፡ ሞሃመድ ሁሴን ቤካ፤ 45 ገበሬ፡፡ ረደላ ክንባዱ አደል፤19 የታክሲ ረዳት፡፡ ሃብታሙ አመንሲሳ ኡርጌሳ፤ አነስተኛ ንግድ፡፡ ዳዊት ፈቃዱ ጸጋዬ፤ 19 ሜካኒክ፡፡ ገዛኸኝ መንገሻ ገረመው፤ 15 ተማሪ፡፡ ዮናስ አሰፋ አበራ፤24 ስራው አልታወቀም:: ግርማ  ዓለሙ ወልዴ፤38 ሾፌር፡፡ ወ/ሮ ደስታ ኡማ ብሩ፤38 አነስተኛ ንግድ፡፡ ለገሰ ቱሉ ፈይሳ፤ 60 ግንበኛ፡፡ ተስፋዬ ድልገባ ቡሽራ፤ 19 ጫማ አዳሽ፡፡ ቢኒያም ደንበላ ደገፋ፤ 18፤ ሥራ አጥ፡፡ ሚሊዪን ከበደ ሮቢ፤32 የትራነስፖርት ረዳት፡፡ ደረጀ ዳመና ደኒ፤24 ተማሪ፡፡ ነቢዩ ዓለማየሁ ሃይሌ፤ 16 ተማሪ፡፡ ምትኩ ኡድማ ሚሶንዳ፤ 24 የቤት ሰራተኛ፡፡ አንዋር ኪያር ሱሩር፤ 22 አነስተኛ ንግድ፡፡ ንጉሴ ዋበኝ፤36 የቤት ሰራተኛ፡፡ ዙልፋ ሱሩር ሃሰን 50 የቤት እመቤት፡፡

ዋሲሁን ከበደ፤ 16 ተማሪ፡፡ ኤርሚያስ ፈቃዱ ከተማ፤ 20 ተማሪ፡፡ 00428፤ 25 ስራው ያልታወቀ፡፡ 00429፤26 ስራው ያልታወቀ፡፡00430 30 ስራው ያልታወቀ፡፡ አዲሱ በላቸው፤ 25 ስራው ያልታወቀ፡፡ ደመቀ ካሳ አበበ፤  ስራው ያልታወቀ፡፡00432፤ 22፤ ስራው ያልታወቀ፡፡00450፤20፤ ስራው ያልታወቀ፡፡ 13903፤25፤ ስራው ያልታወቀ፡፡ 00435 30፤ ስራው ያልታወቀ፡፡13906፤25፤ ስራው ያልታወቀ፡፡ ተማም ሙክታር፤ 25 ስራው ያልታወቀ፡፡በየነ ኑር ቤዛ፤ 25፤ስራው ያልታወቀ፡፡ ወሰን አሰፋ፤ 25፤ ስራው ያልታወቀ፡፡ አበበ አንተነህ፤ 30 ስራው ያልታወቀ፡፡ ፈቃዱ ሃይሌ፤ 25፤ ስራው ያልታወቀ፡፡ ኤልያስ ጉልቴ፤ ስራው ያልታወቀ፡፡ብርሃኑ አሸሞ ወረቃ፤ ስራው ያልታወቀ፡፡ አሸብር ዓየለ መኩሪያ፤ ስራው ያልታወቀ፡፡  ዳዊት ፈቃዱ ሰማ፤ ስራው ያልታወቀ፡፡ መርሃ ጽድቅ ሲራክ፤ 22፤ ስራው ያልታወቀ፡፡ በለጠ ጋሻው ጠና፤ ስራው ያልታወቀ፡፡ በሃይሉ ተስፋዬ፤ ስራው ያልታወቀ፡፡ 21760፤18፤ ስራው ያልታወቀ፡፡ 21523, 25፤ ስራው ያልታወቀ፡፡11657, 24,  ስራው ያልታወቀ፡፡21520, 25  ስራው ያልታወቀ፡፡ ; 21781, 60 ስራው ያልታወቀ፡፡ጌታቸው አዘዘ፤ 45 ስራው ያልታወቀ፡፡; 21762, 75 ስራው ያልታወቀ፡፡ 11662,45, ስራው ያልታወቀ፡፡21763, 25, ስራው ያልታወቀ፡፡  13087, 30, ስራው ያልታወቀ፡፡ 21571, 25, ስራው ያልታወቀ፡፡ 21761, 21, ስራው ያልታወቀ፡፡ እንዳልካቸው ወ/ ገብርኤል፤ 27 ስራው ያልታወቀ፡፡

ሃይለማርያም አምባዬ፤ 20 ስራው ያልታወቀ፡፡ መብራቱ ውብሸት ዘውዱ 27 ስራው ያልታወቀ፡፡ ስንታዬሁ እስጢፋኖስ በየነ፤ 14 ስራው ያልታወቀ፡፡ ታምሩ ሃይለሚካኤል፤ ስራው ያልታወቀ፡፡ አድማሱ ተገኝ አበበ፤ 45 ስራው ያልታወቀ፡፡ እቴነሽ ይማም፤50፤ስራ ያልታወቀ፡፡ ወርቄ አበበ፤ 19፤ስራ ያልታወቀ፡፡ፍቃዱ ደግፌ 27 ስራ ያልታወቀ፡፡ ሸምሱ ካሊድ፤25፤ስራ ያልታወቀ፡፡አብዱዋሂድ አህመዲነ፤30፤ ስራ ያልታወቀ፡፡ ተክሌ ደበሌ፤ 20 ስራ ያልታወቀ፡፡ ታደሰ ፈይሳ 38፤ ስራ ያልታወቀ፡፡ ሰሎሞን ተስፋዬ 25፤ ስራ ያልታወቀ፡፡ ቅጣው ወርቁ፤25፤ ስራ ያልታወቀ፡፡ እንዳልካቸው ወርቁ፤ 25፤ ስራ ያልታወቀ፡፡ ደስታ አያሌው ነጋሽ፤ 30፤ስራ ያልታወቀ፡፡ ይለፍ ነጋ፤ 15፤ ስራ ያልታወቀ፡፡ዮሐንስ ሃይሌ፤20፤ ስራ ያልታወቀ፡፡ በሃይሉ ተሸመ ብርሃኑ፤30፤ ስራ ያልታወቀ፡፡ሙሉ ኩምሳ ሶሬሳ፤50፤ የቤት እመቤት፡፡ ቴዎድሮስ ግደይ ሃይሉ፤ 23 ጫማ አሻሻጭ፡፡ ደጀኔ ይልማ ገብሬ፤18 ሱቅ ሰራተኛ፡፡ፀጋ ሁን ወልደ ገብርኤል፤18፤ተማሪ፡፡ ደረጃ ማሞ ሃሰን፤27፤ አናጢ፡፡ ረጋሳ ጉቱታ ፈይሳ፤55፤ ላወንድሪ ሰራተኛ፡፡ቴዎድሮስ ገብረወልድ፤28 የግል ስራ፡፡

መኮንን ደስታ ገ/ እግዚአብሔር፤20፤ ሜካኒክ፡፡ ኤልያስ ገ;ጊዮርጊስ23 ተማሪ፡፡ አብርሃም አሰፋ መኮንን፤ 21፤ የቀን ሰራተኛ፡፡ጥሩወርቅ ገ/ ጻድቅ፤ 41፤ የቤት እመቤት፡፡ሄኖክ ቀጸላ መኮንን፤ 28፤ ስራ ያልታወቀ፡፡ ጌቱ ሸዋንጉስ መረታ፤ 24፤ ስራ ያልታወቀ፡፡ ወ/ሮ ክብነሽ መልኬ ታደሰ፤ 52፤ ስራ ያልታወቀ፡፡ መሳይ አዲሱ ስጦታው፤ 29፤ የግል ስራ፡፡ ሙሉዓለም ንገሤ ወየሳ፤ 15፡፡ አያል ሰው ማሞ፤23፤ ስራ ያልታወቀ፡፡ ስንታየሁ መለሰ፤ 24፤ የቀን ሰራተኝ፡፡ ወ/ሮ ጸዳለ ዓለሙ ቢራ፤50፤ የቤት እመቤት፡፡ አባይነህ ሳራ ሰዴ፤ 35፤ ልብስ ሰፊ፡፡ ፍቅረማርያም ቁምቢ ተሊላ፤ 18፤ ሾፌር፡፡ ዓለማየሁ ገርባ፤ 26፤ ስራ ያልታወቀ፡፡ ጆርጅ ጌትዬ አበበ፤ 36፤ የግል ትራንስፖርት፡፡ ሃብታሙ ዘገየ ቶላ፤ 16፤ ተማሪ፡፡ ምትኩ ዘለቀ ገ/ሥላሴ፤24፤ ተማሪ፡፡ ምትኩ ዘለቀ ገ/ ስላሴ፤ 24 ፤ ተማሪ፡፡  ትእዛዙ ወግል ሰራተኛ፡፡ ፍቃዱ አመላ ዳልጌ፤ 36፤ ልብስ ሰፊ፡፡ ሸዋጋ በቀለ ወ/ ጊዮርጊስ፤ 38፤ የቀን ሰራተኛ፡፡ ዓለማየሁ ኢፋ ዘውዴ፤ 32፤ ጨርቃ ጨርቅ ሰራተኛ፡፡ ዘልዓለም  ቀጸላ ገ/ጻድቅ፤ 31፤ ታክሲ ነጂ፡፡ መቆያ መብራቱ ታደሰ፤ 19 ተማሪ፡፡ ሃይልዬ ግርማ ሁሴን፤ 19፤ ተማሪ፡፡ ወ/ሮ ፍስሐ ጣሰው ውሩፋ፤  23፤ ፖሊስ፡፡ ወጋየሁ ዘርይሁን አርጋው፤ 26 ሥራ አጥ፡፡

መላኩ መኮንን ከበደ፤ 19፤ ስራ ያልታወቀ፡፡ አባይነህ ደዴ ኦራ፤ 25፤ ልብስ ሰፊ፡፡ ወ/ሮ አበበች በቀለ ሁለቱ፤ 50፤ የቤት እመቤት፡፡ ደመቀ  አበጀ ጀምበሬ፤  30፤ ገበሬ፡፡ ክንዴ መለሰ ወረሱ፤ 22፤ ስራ አጥ፡፡ እንዳለ እውነቱ ገብረመድህን፤ 23፤ የግል ሰራተኛ፡፡ ዓለማየሁ ተሸመ ወልዴ፤ 24፤ መምህር፡፡ ብስራት ተስፋዬ ደምሴ፤ 24፤ መኪና አስመጪ፡፡ መስፍን ገ/ወልድ ሃብተ ጊዮርጊስ፤ 23 የግል ስራ፡፡ ወሊዮ ሁሴን ዳሪ፤ 18፤ የግል ስራ፡፡ በሃይሉ ግርማ ገብረ መድህን፤ 20፤ በግል ስራ፡፡ ሲራጅ ኑሪ ሰኢድ፤ 18፤ ተማሪ፡፡ ኢዮብ ገብረ መድህን፤ 25፤ ተማሪ፡፡ ዳንኤል ወርቁ ሙሉጌታ፤ 25፤ የቀን ሰራተኛ፡፡ ቴዎድሮስ ከበደ ደገፋ፤ 25፤ ጫማ ፋብሪካ ሰራተኛታ፡፡ ጋሻው ታደሰ ሙሉጌታ፤ 24፤ ተማሪ፡፡ ከበደ በዳሶ ኢርኮ፤ 22፤ ተማሪ፡፡ ለቻሳ ከፈና ለታሳ፤  21፤ ተማሪ፡፡ ጃገማ በዳኔ በሻህ፤ 20፤ ተማሪ፡፡  ደበላ አኦለታ ጉታ፤ 15፤ ተማሪ፡፡ መላኩ፤ተረፈ ፈይሳ፤ 16፤ ተማሪ፡፡ ወ/ሮ እልፍነሽ ተክሌ፤ 45፤ ስራው ያልታወቀ፡፡ ሃሰን ዱላ፤ 64፤ ስራ ያልታወቀ፡፡ ሁሴን ሃሰን ዱላ፤ 25፤ ስራ ያልታወቀ፡፡ ጸሃይ ደጀኔ ደምሴ፤ 15፤ ስራ ያልታወቀ፡፡ ስሙ ያልታወቀ፡፡ ስሙ ያልታወቀ፡፡ ስሙ ያልታወቀ፡፡ አግደው ፤ 18፤ ስራ ያልታወቀ፡፡ ጌታቸው  አፈወርቅ ተረፈ፤ 16፤ ስራ ያልታወቀ፡፡ ደለለኝ ክንዴ ዓለሙ፤ 20፤ ስራ ያልታወቀ፡፡ ዩሱፍ ሞሃመድ ኡመር፤ 20፤ ስራ ያልታወቀ፡፡

መኩርያ ተፈራ ተበጀ፤ 22፤ ስራ ያልታወቀ፡፡ ባድሜ ሞገስ ተሻማሁ፤ 20፤ ስራ ያልታወቀ፡፡ አምባው ጌታሁን፤ 38፤ ስራ ያልታወቀ፡፡ ተሾመ  አዲስ ኪዳኔ፤ 65፤ የጤና ተቋም ሰራተኛ፡፡ ዮሴፍ ሙሉጌታ ረጋሣ፤ ስራ ያልታወቀ፡፡ አቢዩ ንጉሴ፤  ስራ ያልታወቀ፡፡ ታደሰ ሻሬ በሃጋ፤ ስራ ያልታወቀ፡፡ ኤፍሬም ጥላሁን ሻፊ፤ ስራ ያልታወቀ፡፡ አበበ ሐርቆ ሃማ፤ ስራ ያልታወቀ፡፡ ገበሬ ሞላ፤ ስራ ያልታወቀ፡፡ ሰይዲን ኑረዲን፤ ስራ ያልታወቀ፡፡ እንየው ጌታቸው ጸጋዬ 32፤ ትራንስፖርት ረዳት፡፡ አብዱራህማን ሁሴን ፈረጀ፤  32፤ አናጢ፡፡ አብዱል መናን ሁሴን፤ 28፤ በግል ሰራተኛ፡፡ ጂግሳ ቶላ ሰጠኝ፤ 18፤ ተማሪ፡፡ አሰፋ  አብሽሮ ነጋሳ፤ 33፤ አናጢ፡፡ ከተማ ኩቦ ኢንኮ 23፤ ልብስ ሰፊ፡፡ ክብረት ዕድሉ እልፍነህ፤ 48፤ ጥበቃ ሰራተኛ፡፡ ኢዮብ ገዛኸኝ ዘመድኩን፤ 24፤ ግል ሰራተኛ፡፡ ተስፋዬ ብርሃኔ መነገሻ፤ 15፤ በግል፡፡ ሻምበል ደበሳ ሰርቤሳ ቶሎሳ፤ 58፤ በግል ስራ፡፡ ትንሳኤ መንግስቱ ዘገየ፤ 14 ልብስ ሰፊ፡፡ ኪዳኔ ገብሬ ሽኩሮው፤ 25፤ የቀን ሰራተኛ፡፡ አንዱዓለም ሽበላው፤ 16፤ ተማሪ፡፡ አዲሱ ዳኜ ተስፋሀን፤ 19፤ በግል፡፡ ካሳ በየነ፤ 28፤ ባለ ልብስ ሱቅ፡፡ ይታገሱ ሲሳይ፤ 22፤ ስራ ያልታወቀ፡፡ ያልታወቀ፡፡ ያልታወቀ፤ 22፤ ስራ ያልታወቀ፡፡

የመንግስት ደህንነት ሰራተኞች ከቡድናቸው በተተኮሰ ጥይት የተገደሉ፤(እርስ በርስ የተገዳደሉ) ነጋ ገብሬ፤ ጀበና ደሳለኝ፤ ሙሊቶ ኢርኮ፤ ዮሐንስ ሰሎሞን፤ አሸናፊ ደሳለኝ፤ ፌያ ገብረመንፈስ፡፡

ኖቬምበር 2/2005 (እንዳሮፓ አቆጣጠር) በቃሊቲ ወህኒ ቤት ተዘግቶባቸው እያሉ የተጨፈጨፉ ፍርደኞችና ፍርድ በመጠበቅ ላይ የነበሩ፡፡

1. ጠይብ ሸምሱ ሞሃመድ፤ ዕድሜው ያልታወቀ፤የመሳርያ ትግል ሲያነሳሳ ተብሎ ክስ የቀረበበት፡፡2. ሳሊ ከበደ፤ዕድሜው ያልታወቀ፤ክስ ያልተመሰረተበት፡፡3. ሰፊው እንድሪስ፤ታፈሰ ወረዳ፤ ዕድሜያቸው ያልታወቀ በአሰገድዶ መድፈር የተከሰሱ፡፡ 4. ዘገየ ተንኮሉ በላይ፤ ዕድሜ ያልታወቀ፤በስርቆት የተከሰሰ፡፡ 5. ቢያድግልኝ ተማም፤ ዕድሜው ያልታወቀ፤ክሱ ያልታወቀ፡፡ 6. ገብሬ መስፍን ዳኜ፤ ዕድሜው ያልታወቀ፤ወንድ፤ ክሱ ያልታወቀ፡፡ 7. በቀለ አብርሃም ታዬ፤ዕድሜ ያልታወቀ፤ወንድ፤ 8. አበሻ ጉታ ሞላ፤ ዕድሜ ያልታወቀ፤ ወንድ ክሱ ያልታወቀ፡፡ 9. ኩርፋ መልካ ተሊላ፤ በማስፈራራት የተከሰሰ፡፡

10. በጋሻው ተረፈ ጉደታ፤ ዕድሜው ያልታወቀ፤ ወንድ፤ በሰላም ማደፍረስ የተከሰሰ፡፡ 11. አብዱዋሂብ አህመዲን፤ ዕድሜ ያልታወቀ፤በስርቆት የተከሰሰ፡፡ 12. ተስፋዬ አቢይ ሙሉጌታ፤ ዕድሜው ያልታወቀ፤ በመሳርያ ትግል ማነሳሳት የተከሰሰ፡፡ 13. አዳኔ ቢረዳ፤ዕድሜው ያልታወቀ፤ወንድ፤ በግድያ የተከሰሰ፡፡ 14. ይርዳው ከርሴማ፤ ዕድሜው ያልታወቀ፤ወንድ፤ ክስ ያልተመሰረተበት፡፡ 15. ባልቻ ዓለሙ ረጋሳ፤ ዕድሜው ያልታወቀ፤ወንድ፤ በስርቆት የተከሰሰ፡፡ 16. አቡሽ በለው ወዳጆ፤ ዕድሜው ያልታወቀ፤ ወንድ ክስ ያልተመሰረተበት፡፡ 17. ዋለልኝ ታምሬ በላይ፤ ዕድሜ ያልታወቀ፤ወንድ፤ በአስገድዶ መድፈር የተከሰሰ፡፡ 18. ቸርነት ሃይሌ ቶላ፤ዕድሜ ያልታወቀ፤ ወንድ፤ በስርቆት የተከሰሰ፡፡ 19. ተማም ሸምሱ ጎሌ፤ ዕድሜው ያልታወቀ፤ ክስ ያልተመሰረተበት፡፡

20. ገበየሁ በቀለ አለነ፤ ዕድሜው ያልታወቀ፤ ወንድ፤ ክስ ያልተመሰረተበት፡፡ 21. ዳኔኤል ታዬ ለኩ፤ ዕድሜ ያልታወቀ፤ ወንድ፤ ክስ ያልተመሰረተበት፡፡ 22. ሞሃመድ ቱጂ ከኔ፤ ዕድሜ ያልታወቀ፤ ክስ ያልተመሰረተበት፡፡ 23. አብዱ ነጂብ ኑር፤ ዕድሜ ያልታወቀ፤ ወንድ፤ ክስ ያልተመሰረተበት፡፡ 24. የማታው ሰርቤሎ፤ በአስገድዶ መድፈር የተከሰሰ፡፡ 25. ፍቅሩ ናትናኤል ሰው ነህ፤ ዕድሜው ያልታወቀ ወንድ፤  በማስፈራራት የተከሰሰ፡፡ 26. ሙኒር ከሊል አደም፤ ዕድሜው ያልታወቀ፤ ወንድ፤ በዋለጌነት የተከሰሰ፡፡ 27. ሃይማኖት በድሉ ተሸመ፤ ዕድሜው ያልታወቀ፤በማጭበርበር የተከሰሰ፡፡ 28. ተስፋዬ ክብሮም ተክኔ፤ ዕድሜው ያልታወቀ፤ ወንድ፤ በስርቆት የተከሰሰ፡፡ 29. ወርቅነህ ተፈራ ሁንዴ፤ ዕድሜ ያልታወቀ፤ ወንድ፤ ክስ ያልተመሰረተበት፡፡

30. ሲሳይ ምትኩ፤ በማጭበርበር የተከሰሰ፤ 31. ሙሉነህ አይናለም ማሞ፤ ዕድሜው ያልታወቀ፤ ወንድ፤ ክስ ያልተመሰረተበት፡፡ 32. ታደሰ ሩፌ የኔነህ፤ በማስፈራራት የተከሰሰ፡፡ 33. አንተነህ በዬቻ ቀበቻ፤ ዕድሜው ያልታወቀ፤ ወንድ፤ የመሳርያ ትግል በማነሳሳት የተከሰሰ፡፡ 34. ዘርይሁን መሬሳ፤ ዕድሜ ያልታወቀ፤ ወንድ፤ ንብረት በማውደም የተከሰሰ፡፡ 35. ወጋየሁ ዘርይሁን አርጋው፤ በስርቆት የተከሰሰ፡፡ 36. በከልካይ ታምሩ፤ ዕድሜ ያልታወቀ፤ወንድ፤ ክስ ያልተመሰረተበት፡፡ 37. የራስወርቅ አንተነህ፤ዕድሜ ያልታወቀ፤ በማጭበርበር የተከሰሰ፡፡ 38. ባዘዘው ብርሀኑ፤ ዕድሜ ያልታወቀ፤ በሶዶማዊ ተግባር ማነሳሳት የተከሰሰ፡፡39. ሰሎሞን ኢዮብ ጉታ፤ዕድሜ ያልታወቀ፤ በአስገድዶ መድፈር  የተከሰሰ፡፡

40. አሳዩ ምትኩ አራጌ.ዕድሜ ያልታወቀ፤ወንድ፤ በማስፈራራት የተከሰሰ፡፡ 41. ጋሜ ሃይሉ ዘዬ፤ዕድሜ ያልታወቀ፤ ወንድ፤ ጸጥታ በመንሳት የተከሰሰ፡፡ 42. ማሩ እናውጋው ድንበሬ፤ዕድሜ ያልታወቀ፤በአስገድዶ መድፈር የተከሰሰ፡፡ 43. እጅጉ ምናሌ፤ ዕድሜ ያልታወቀ፤ ወንድ፤ በመግደል ሙከራ የተከሰሰ፡፡ 44. ሃይሉ ቦስና ሃቢብ፤ዕድሜ ያልታወቀ፤ ወንድ፤ መደበቂያ በመስጠት የተከሰሰ፡፡45. ጥላሁን መሰረት፤ዕድሜ ያልታወቀ፤ ክስ ያልተመሰረተበት፡፡46. ንጉሴ በላይነህ፤ ዕድሜ ያልታወቀ፤ ወንድ፤ በስርቆት የተከሰሰ፡፡ 47. አሸናፊ አበባው፤ ዕድሜ ያልታወቀ፤ወንድ፤ ክስ ያልተመሰረተበት፡፡ 48. ፈለቀ ድንቄ፤ ዕድሜ ያልታወቀ፤ወንድ፤ ክስ ያልተመሰረተበት፡፡49. ጀንበሬ ድንቅነህ ቢለው፤ዕድሜ ያልታወቀ፤ጸጥታ በማወክ የተከሰሰ፡፡

50. ቶሎሳ ወርቁ ደበበ፤ዕድሜ ያልታወቀ፤ወንድ፤ በስርቆት የተከሰሰ፡፡ 51. መካሻ በላይነህ ታምሩ፤ዕድሜ ያልታወቀ፤ ወንድ፤ በዱር አዳሪነት የተከሰሰ፡፡ 52. ይፍሩ አደራው፤ ዕድሜ ያልታወቀ፤ ወንድ፤ ክስ ያለተመሰረተበት፡፡ 53. ፋንታሁን ዳኜ፤ ዕድሜ ያልታወቀ፤ ወንድ፤ ክስ ያልተመሰረተበት፡፡ 54. ጥበበ ዋኬኔ ቱፋ፤ ዕድሜ ያልታወቀ፤ወንድ፤ የመሳርያ ትግል በመቀስቀስ የተከሰሰ፡፡ 55. ሰሎሞን ገብረዓምላክ፤ ዕድሜ ያልታወቀ፤ ወንድ፤ ቡር አዳሪነት የተከሰሰ፡፡56. ባንጃው ቹቹ ካሳሁን፤ ዕድሜ ያልታወቀ፤ወንድ፤በስርቆት የተከሰሰ፡፡ 57. ደመቀ አበጀ፤ ዕድሜ ያልታወቀ፤ ወንድ፤ በመግደል ሙከራ የተከሰሰ፡፡.58. እንዳለ እውነቱ መንግስቴ፤ወንድ፤ክስ ያልተመሰረተበት፡፡ 59. ዓለማየሁ ገረባ፤ ዕድሜ ያልታወቀ፤ወንድ፤በ2004 በተካሄደው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንቅስቃሴ በማነሳሳት የተከሰሰ፡፡60. ሞርኮታ ኢዶሳ፤ ዕድሜ ያልታወቀ፤ ወንድ፤ ክስ ያልተመሰረተበት፡፡

[ለታሪክ መዝገብ፡- ቢያንስ የ237 በዚህ ግድያና ጭፍጨፋ በቀጥታ ተሳትፈው የነበሩት የተረጋገጠ የፖሊስና የደህንነት አባልት ስም ዝርዝር  በመዝገብ አለ፡፡  በአስቸኳይ ወደ ፍርድ ሊቀርቡ ይገባል፡፡

የሰባዊ መብት ተምዋጋች የኔ ሰው ገብሬን አስታውሳለሁ

በ 11/11/11 (እንዳሮፓ አቆጣጠር) መምህርና የሰብአዊ መብት ተሟጋች የነበረው የ 29 ዓመቱ የኔ ሰው ገብሬ በዳውሮ ዞን፤ተርቻ ቀበሌ በደቡብ ኢትዮጵያ በሕዝብ መሰብሰቢያ ቦታ እራሱን በእሳት አቃጥሎ ተሰዋ፡፡ በቃጠሎው በደረሰበት ጉደት የተነሳ በ3ኛው ቀን ሕይቱ አለፈ፡፡ የኔ ሰው እራሱን በእሳት ከማያያዙ በፊት፤ በቦታው ለተሰበሰቡት ሰዎች ‹‹ሕግና መልካም አስተዳደር በሌለበት፤ ሰብአዊ መብት በሚጣስበት ሃገር፤ እነዚህ ወጣቶች በነጻ እንዲለቀቁ ስል እራሴን እሰዋለሁ›› በማለት ተናገረ፡፡ የኔ ሰው ገብሬን አስታውሳለሁ::

አስታውሳለሁ! እንዴት እረሳለሁ!!

‹‹ ተስፋን ላለማጣት አንድ ሺህ አንድ ሰበቦች ለመፍጠር እየታገልኩም፤ ገዳዮቹን አስታውሳለሁ፤ ሟቾቹን አስታውሳለሁ፡፡ ምክንያቱም እያስታወስኩ ፤እሰቃያለሁ፡፡ስለማስታዉስም ተስፋ አደርጋለሁ::›› ኤሊ ዌይሴል: ከሆሎኮስት የተረፈና የኖቤል የሰላም  ሽልማት ተቀባይ::

አስታውሳለሁ!

እንዴት እረሳለሁ!!

ሁሌም ተስፋ አደርጋለሁ!!!

ሁላችንም ልናስታውስ እንጂ መርሳት አንችልም፡፡

እንዳይደገም!!!

የተቶረገመው ጽሁፍ (translated from):

http://open.salon.com/blog/almariam/2012/11/12/i_remember

(ይህን ጦማር ለሌሎችም ያካፍሉ::)

ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮችን  ለማግኘት እዚህ ይጫኑ::

http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/category/al-mariam-amharic

http://ethioforum.org/?cat=24

 

Similar Posts

Leave a Reply