በኢትዮጵያ ወቅቱ ወደፊት መራመጃ ነው (ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም)

Click here for PDF

ከፕሮፌሰር  ዓለማየሁ  ገብረማርያም
ትርጉም  ከነጻነት ለሃገሬ

በኢትዮጵያ ወቅቱ መጥረቢያውን ቀብሮ ወደፊት መራጃ ነው፡፡ ኔልሰን ማንዴላ እንዳስተማሩት ‹‹ከጠላትህ ጋር ሰላምን መመስረት ከፈለግህ፤ከጠላትህ ጋር አብረህ መስራት አለብህEthiopian flag (Alemayehu G. Mariam) በዚህን  ጊዜ ጠላትህ አጋርህ ይሆናል፡፡›› እኔ ደግሞ ትንሽ ላክልበትና፤ጠላትህ ወዳጅህና ተባባሪህ ይሆናል፡፡ከታሪክ እንዳየነው፤ ብሔራዊ አሜሪካኖች (አሜሪካን ኢንዲያንስ) በመሃከላቸ ሰላምን ሲፈጥሩ፤መጥረቢያቸውን፤ መቁረጫቸውን በመሬት ውስጥ ይቀብሩታል:: ይህም በመሃላቸው ተነስቶ የነበረውን አለመግባባት መቋጨቱን ማረጋገጫ ነው፡፡ዛሬ ለኢትዮጵያውያን ሁሉ ያንን የጎሳ ክፍፍሉን፤የሃይሞኖት ልዩነቱን፤የሰብአዊ መብት ጥሰትን እርግፍ አድርገው ማጥፋታቸውን ለማረጋገጥ መጥረቢያቸውን መቅበር ይገባቸዋል እላለሁ፡፡ አሁን እጅ ለእጅ ተጨባብጠን፤እርስ በርሳችን ተቃቅፈን፤ሁለንተናችንን ለአዲሲቱ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ፤ የሕግ የበላይነት የተከበረባት ኢትዮጵያ፤ሰብአዊ መብት የተጠበቀባትና ዴሞክራቲክ ስነስራት የተከበሩባት ኢትዮጵያን ለመገንባት መዋል ይገባናል፡፡

በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ በመክፈት ጥላቻንና ቂም በቀልን ወደ ኋላ በመተው የምንቀጥልበት ወቅት ነገ ሳይሆን ዛሬ ነው መሆን ያለበት፡፡ እራሳችንን ካለፈው የመከራ ሸክምና ካሰረን የሰንሰለት ቋተሮ አላቀን ለትውልድ ሲያመን የነበረውን ቁስል በማከምና በማዳን ከእንግዲህ ፈጽሞ ያለፈውን በማመንዠክ የምንም ሁኔታ እስረኞች ላለመሆን ለመጪው ትውልድ ልናረጋግጥለት የሚገባን ዛሬ ነው፡፡ ማንዴላ ‹‹በእልህ  የጠጡት መርዝ ጠላቴን ይገድልኛል ብሎ እንደማሰብ ነው››  ብለው ነበር፡፡ ማንዴላ የእልህን መርዝ በመጠጣት አይደለም አብዛኛዎቹን ‹‹ከጠላቶቻቸውን››ይበልጥ በመኖር ያሸነፉት::  አሁንም በሕይወት ቆይተው 94ኛውን የዕድሜ ክልላቸውን እያጣጣሙት ነው፡፡ ዛሬ በኢትዮጵያ አካባቢና በዲያስፖራው አካባቢ በርካት እልሆች አሉ፡፡ በአብዛኛዎቹ ውስጥ ለጊዜው ዝም ያሉና ያንቀላፋ በመቁሰልና በሽንፈት የተበለጡ የሚመስላቸው በርካቶች አሉ፡፡ በሌላ ጎን ደግሞ በድል አድራጊነት ተኮፍሰው፤በሌሎች ችግር ጮቤ የሚረግጡና የሚደነፉ አሉ፡፡ ከዚያ ባለፈ ደግሞ ምንም አይመለከተንም በሚል ወደጎን ዞር ብለው የሚኖሩ ይገኛሉ፡፡ ያለፈውን ሁሉ ትቶ  ታሪካዊ ጥላቻን ከውስጥ የማውጫው ቀን አሁን ነው፡፡ ምሬትን ከውስጣችን አውጥተን መጣያው ቀን ነገ ሳይሆን ዛሬ ነው፡፡ ተፎካካሪዎቻችንን ወደሰላማዊ አንድነት መጥሪያችን ነገ ሳይሆን ዛሬ ነው፡፡ መግባባት መጀመር ያለበት ነገ ሳይሆን ዛሬ ነው፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ አፋጣኝ የመልካም አስተዳደርንና የዴሞክራሲን እውነታ መገንባት የሚገባን ነገ ሳይሆን ዛሬ ነው፡፡

ዛሬ አፋጣኝ መሻሻልን በመልካም አስተዳደርና በዴሞክራሲ ግንባታ ላይ እንጀምር

የቀድሞው ጠቅላይ መኒስትር መለስ ዜናዊ በ2007 ዓም ‹‹ራዕያቸው(ስጦታቸው) ኢትዮጵያን አንቆ ከያዛት የድህነት አረንቋ ማውጣት የሚቻለው በተመቻቸና ቀጣይነት ያለው ልማት ብቻ ሳይሆን በመልካም አስተዳደርና በዴሞክራሲ ግንባታ ነው›› ብለው ነበር፡፡ ከምርና በዕውነት እነዚህን የመለካም አስተዳደርና የዴሞክራሲ ግንባታ ፈጣን መሻሻሎች መጀመር ያለብን ዛሬ ነው፡፡ እነዚህ መሻሻሎችም ፍጥነታቸው ከሁሉም የፖለቲካ እስረኞች መፈታት ጋር መጀመር ያለባቸውና: ጸረ ሽብርተኝነት የሚለውን አዋጅም በማስተካከል የሲቪል ማሕበረሰቡንና ሌሎችንም የሲቪል ማሕበረሰብ አሳሪ ህጎች በማሻሻልና በማስተካከል ለሕግ የበላይነት መከበር መጀመር ያለብን ዛሬ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች መለቀቅ አለባቸው፡፡ሁኔታቸው በአሜሪካን መንግሥት ሰበአዊ መብት ሪፖርት፤በተባበሩት መንግስታት የተለያዩ ሰብአዊ መበት ተሟጋች ድርጅቶች ዘገባ ውስጥ በገሃድ ተቀምጠው ታይተዋል፡፡ የአሜሪካን ስቴት ዲፓርትመነት የሰብአዊ መብት ሪፖርት (ኤፐሪል 2011) ባሰፈረው እውነታ መሰረት፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ባሉት ወህኒ ቤቶች ያለውን ሕገ ወጥ ግድያ፤ ስቃይ፤ድብደባ፤የታሳሪዎችን አለአግባብ መሰቃየት፤የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት በፖሊስ የሚደርስባቸውን ወከባና ግፍ የተሞላው አበሳ፤ በልዩ የፖሊስ ሃይልና ሚሊሺያዎች የሚሰነዘረውን ሕገ ወጥ ድርጊት፤ በወህኒ ቤቶቹ ያለውን ዝቅተኛና መኖር የማያስችል ሁኔታ፤የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎችና መልካም አሳቢዎች አለአግባብ በዘፈቀደ መያዝ፤ያለፍርድ ለረጂም ጊዜ በወህኒ ቤት መሰቃየት……..›› በዝርዝር ተዘግቧል፡፡

በ2010 የሁማን ራይትስ ዎች የዓለም አቀፍ ዘገባ ስለ ኢትዮጵያ፤ በኢትዮጵያ የፖሊስ ሃይል፤በጦር አባላትና በሌሎችም ተመሳሳይ አባላት፤በደህንነት አባላት በቅጣት መልክ በተቃዋሚ ደጋፊዎችና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም ላይ የሚፈጸመው ስቃይና የእስረኞች የአያያዝ ሁኔታ አሳሳቢነትና መከራ የከፋ ከመሆኑም ባሻገር በሚስጣራዊ ማጎሪያዎች፤ በወታደራዊ ካምፖች ውስጥ በእስር የሚገኙት ንጹሃን ዜጎች ሁኔታ አሳሳቢነቱ በየጊዜው እየከፋ የሚሄድ መሆኑን በግልጽ አስቀምጧል፡፡

የተባበሩት መንግስታት የጸረ ቶርቸር(የስቃይ አያያዝ) ኮሚቴ (ኖቬምበር 2010) ዘገባው በፖሊስ አባላት በወህኒ ቤት ሃላፊዎች፤በደህንነት አባላት፤እንዲሁም በወታደራዊው ክፍል አባላት የሚደርሰውን ግፍና መከራ፤በፖለቲካ ተቃዋሚ አባላትና ደጋፊዎች፤በተማሪዎች ላይ፤ሽብርተኞች ተብለው በሚፈረጁ ላይ፤የተቃዋሚ ሃይላት ደጋፊዎች (የኦ ኤነ ኤል ኤፍን) እና የኦ ኤል ኤፍ ተጠርጣሪ ደጋፊዎች የተባሉትን ሁሉ በተለያዩ ቦታ በማጎር የሚደርስባቸውን ስቃይ በአግባቡ በመዘገብ ይፋ አድርጓል፡፡ ማጎሪያዎቹ ከታወቁት ማጎሪያዎች በተጨማሪ፤ ፖሊስ ጣቢያዎች፤ ወታደራዊ ካምፖችና ይፋ ያለሆኑ ቦታዎች ጭምር ዜጎች በግፍ እየታፈኑ እንደሚሰቃዩ ሪፖርቱ ጨምሮ ይፋ አውጥቷል፡፡

በኢትዮጵያ ምን ያህል እስረኞች እንዳሉ ለማወቅ አስቸጋሪ ነው፡፡ዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ መበት ተሟጋቾች ሁኔታውን እንዲያዩም ሆነ ታሳሪዎችን እንዲያነጋግሩ አይፈቀድላቸውም፡፡የተለያዩ አካላት ግምታዊ ቁጥር ሲያስቀምጡ፤ ከብዙ መቶዎች እስከ አሰርት ሺዎች እንደሚደርሱ ይገምታሉ፡፡በቅርቡ የወጣው የጄኖሳይድ ዎች ሪፖርት የፖለቲካ እስረኞችን ብዛት በመቶ ሺህ አድርጎ አስቀምጦታል፡፡በየቀኑ የፖለቲካ ሰዎች፤ያለውን መንግስት የሚተቹ፤ተቃዋሚ ሃይላት፤ለእስር በመዳረግ ላይ ናቸው፡፡ባለፉት ዓመታት የኦ ኤፍ ዲ ኤም፤ የኦሮሞ ሕዝቦች ኮንግሬስ፤በፖለቲካ አመለካከታቸው ሳቢያ የተነሳ ቁጥራቸው የበዛ አባላት ለእስር ተዳርገዋል፡፡ሌሎችም የፖለቲካ ፓርቲ ተቃዋሚ አባላት አባሎቻቸው ለእስር እንደተዳረጉ አስታውቀዋል፡፡ ባለፉት ጥቂት ወራት ብቻ ጋዜጠኞች፤የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ቆራጥና አልበገር ባዩን የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ አመራሩን አንዱ ዓለም አራጌን፤ዓለም አቀፋዊ ክብርና ሞገስ የተሰጣቸውን እስክንድር ነጋንና ርዕዮት ዓለሙን ኤዲትር ውብሸት ታየን ጨምሮ፤የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎች፤የረጅም ዓመታት እስር ተፈርዶባቸዋል፡፡

የመልካም አስተዳርና የዴሞክራሲ አፋጣኝ ግንባታ ጸረ ሽብርተኝነት ተብሎ የተቀመጠውንም አዋጅ ቁ›. 652/2009 በሚገባ  መስተካከል ይገባዋል፡፡ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ይሄ ሕግ የፖለቲካ ተቃዋሚ አባላትን ደጋፊዎችን አመራሮችን የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን ለማገትና ወደ ወህኒ ለመጣል በመሳርያነት ያገለገለ ነው፡፡ ሕጉ በሁሉም ዓለም አቀፋዊ ድርጅቶች ተወግዟል፡፡የሁማን ራትስ ዎች ሕጉን ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ለማፈን፤በነጻ የመንግስትን ፖሊሲ የሚተቹትን፤የሰብአዊ መበት ተሟጋቾችን ለማስደንገጫና ለማሰርያ መጠቀሚያ ነው በማለት አጣጥሎታል፡፡‹‹የጸረሽብርተኛነት ሕግ የተባለው ሕግ ሳይሆን መንግስት የሚፈራቸውንና ለስልታኔ አደገኞች ናቸው፤ ይቀናቀኑኛል ብሎ የሚያስባቸውን ንጹሃን ዜጎች ዝም ለማሰኛ የተቀረጸ የገዢው መንግስት የብረት መሳርያ ነው ይለዋል፡፡ ማንኛውንም ያለውን መንግስት ሂደትና ተግባር በገምቢ ጎኑም ሆነ መታረም በሚገባው አለያም ሕጸጹን በማንሳት የሚተቸውን በሙሉ ሽብርተኛ በማለት እየኮነነ ለእስር የሚያበቃ ነው ይለዋል፡፡

ይህ ህግ እንደሚለው: ማንኛውንም አይነት ጽሁፍ  ሽብርተኝነትን የሚያበረታታ ከሆነ ለእስር ያስዳርጋል፡፡ ማንኛውም ግለሰብ በሽብርተኝነት ከተጠረጠረ ሰው ጋር የዋለ ወይም ያነጋገረ አለያም የሱን ሃሳብ የደገፈ እራሱም እንደሽብርተኛ ይፈረጃል፡፡ ማንኛውም ሰው በተጠረጠረ ሰው ላይ አዎንታዊ አስተያየቱን ቢያሰፍር አለያም ሕጉ አላግባብ ነው የተተረጎመው በሚል አስተያየቱን ቢሰጥ እሱም ሽብርተኛ ነው ይላል ሕጉ፡፡ማንኛውም ቤተሰብ ጎረቤት ሽብርተኛ ብሎ የጠረጠረውን ወዲያውኑ ለፖሊስ ሳያሳውቅ ቢቀር በ10 ዓመታት እስር ይቀጣል ይላል ሕጉ፡፡ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች ከሽብርተኛነት ተጠርጣሪ ጋር ሆነው ከተገኙ ለሽብርተኝነት እንዳሴሩ ተቆጥረው በሽብርተኝነት ይፈረጃሉ ይላል ሕጉ፡፡

በዚህ ጸረ ሽብርተኝነት አዋጅ መሰረት አንድ ፖሊስ ማንንም የጠረጠረውን ዜጋ ያላንዳች ማስረጃና የፍርድ ቤትም የመያዣ ትዕዛዝ በዘፈቀደ ጠርጥሬዋለሁ፤ መስሎኛል፤ አይነ ውሃው አላማረኝም፤ በሚሉ ነጥቦች ሳቢያ በቁጥጠር ስር ሊያውለውና ለበርካታ ቀናት ሳምንታት ወራት በእስር ስር ሊያቆየው ሕጉ ይደነግግለታል፡፡ በዚህም መሰረት አንድ ፖሊስ የጠረጠረውን ሰው ንብረት፤ቤቱን፤የስልክ ጥሪዎቹን፤የሞባይል ግንኙነቶቹን፤ሬዲዮ፤ ፖስታ፤እና መሳይ ግንኙነቶችን የመጥለፍ የመቅዳት መብት በሕጉ ተደንገጎለታል፡፡ ፖሊስ ማንኛቸውንም የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ባለስልጣን፤ባንክን እና የግል ድርጅቶችን፤ወይም ግለሰብን፤ዶኩሜንቶችን እንዲያስረክብ፤ምስክርነት እንዲሰጥ፤ያስገድደዋል፡፡አንድ የሽብር ተጠርጣሪ ያለፍርድ በወህኒ ቤት ለአራት ወራት ሊማቅቅ ደንቡ ያዛል፡፡ማንኛቸውም በመንግስት አቃቤ ሕግ የቀረበ ማስረጃ ሁሉ፤የማይታበል ሃቅ ተብሎ ተቀባይነት ያገኛል፡፡ እንዲሁም ከተጠርጣሪው ላይ በማሰቃየትና በግርፊያ በድበደባ የተገኘ የ‹‹እምነት›› ቃል ምርጣሪውን በማሰቃየት የተገኘም የግፍ ወለድ ማስረጃም ቢሆን ተቀባይነት ያገኛል ይላል ሕጉ፡፡

ቀደም ብዬ የጸረ ሽብርተኝነት አዋጅ ላይ ባሰፈርኩት አስተያየት፤ ሕጉ ዴሞክራሲያዊ የሲቪል ማሕበረሰብን መኖርም ጭምር የሚጻረር መሆኑን ጠቅሼያለሁ፡፡ አለመስማማትም ሽብርተኝነት ነው፡፡ማሰብም ሽብርተኝነት ነው፡፡በለካው አገዛዝ ላይ ስህተቱን መናገርም ሽብርተኝነት ነው፡፡የራስ ሕሊና ባለቤት መሆንም ሽብርተኝነት ነው፡፡ሰላማዊ ተቃውሞም ሽብርተኝነት ነው፡፡እራስን አለመሸጥና በአቋም መጽናትም ሽብርተኝነት ነው፡፡ለሰብአዊ መብትና ለዴሞክራሲ ጥብቅና መቆምም ሽብርተኝነት ነው፡፡ ለሕግ የበላይነት መቆምም ሽብርተኝነት ነው፡፡በሃገር ላይ ለሚሰነዘር ሽብርተኝነትም በሰላማዊ መንገድ መቃወምም ሽብርተኝነት ነው፡፡ማንም ቢሆን ስለሽብርተኝነት በቂ ግንዛቤ ሊኖረው ተገቢ ነው፡፡ኔልሰን ማንዴላ በደቡብ አፍሪካ በነበረው አፓርታይድ አገዛዝ ለ27 ዓመታት ሽብርተኛ ተብለው ነው ወደ ወህኒ የተጣሉት፡፡ ከእስር ሲለቁቅም ‹‹ትላንት ቴሬሪስት (ሽብርተኝ) ተብዬ ነበር፤ ከእስር ስለቀቅ ግን ሀለኩም ወገኖቼ አሳሪዎቼም ጭምር አቅፈውኝ ነበር፡፡ደጋግሜ እናገር እንደነበረው ሁሉ ለነጻነታቸው የሚታገሉ ሁሉ በሃገራቸው መሪዎች ሽብርተኞች ይባላሉ፡፡ እኔም ትላንት ሽብርተኛ ነበርኩ፤ዛሬ ግን ትላንት ሽብርተኛ ብለው በፈረጁኝ ሰዎች እደነቅ አያለሁ ነው ያልኳቸው፡፡ የ‹‹ጸረሽብርተኛ ሕግ›› የሚባለው ‹‹ሕግ›› መወገድ አለበት፡፡

የልግስናና ሕብረተሰብ አዋጅ ቁ. 621 2009 መወገድ አለበት፡፡ይህ ሕግ በመላው የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ የደረሰበት አዋጅ ነው፡፡ ደንቡ መንግስታዊ ያልሆኑ እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች በሰብአዊ መበት ጉዳይ እንዳይነቀሳቀሱ፤በጾታ ጥቃት ጥብቅና ላይ መንቀሳቀስን፤በሃይማኖት እኩልነት ጉዳይ፤አለመግባባትን በማስወገድ ሂደትና እንቅስቃሴ፤የፍትሕ ስርአቱን በተመለከተና የምርጫን ጉዳይ ሚዛናዊነትንም አስመልክቶ እንዳይንቀሳቀሱ ያግዳል፡፡ ማንኛውም ሃገር በቀል የእርዳታ ድርጅት ከ10 በመቶ በላይ ድጋፍ ከውጪ አካላት ካገኝ እንደውጪ ድርጅት ይቆጠራል ይላል፡፡ሃገር በቀል የሆኑት የእርዳታ ድርጅቶች ከሃገር ውስጥ ለእንቅስቃሴያቸው በቂ ገንዘብ ማግኘት ስለማይችሉና መንግስትም ለነዚህ ድጋፍ ሰጪ ድርጅቶች የገንዘብ ድጎማ የሚያደርጉ ድርጅቶችንም ሆነ ግለሰቦችን በተቃዋሚ ደረጃ ስሚፈርጃቸው፤ ለእንቅስቃሴያቸው የሚሆነውን ገንዘብ ከውጪ ከማግኘት ሌላ አማራጭ የላቸውም፡፡ በአጠቃላይ ሕጉ የሃገር ውስጥም ሆኑ የውጪ መንግስታዊ ያልሆኑ የእርዳታ ለጋሽ ድርጅቶች በብቃትና በነጻነት እንዲሁም የቆሙለትን ዓላማና ተረጂውን ሕዝብም ድጋፉን በበቂ እንዳያገኙ የሚያደርግ ሕግ በመሆኑ ድርጅቶቹን በደፈናውና በአጣቃላይ ሽባ የሚያደርግ ደንብ ነው፡፡ ከዚህ በመነሳትም ሕጉ ሲታይ በሥራ ላይ ያለውን ሕገመንግስት የሚቃረንና የማያከበር ደንብ ነው፡፡ ይህ ሕግ አብዛኛዎቹን የሕገመንግስቱን ደንቦች፤ሃሳብን በነጻ የመግለጽን መብት በነጻ መሰብሰብን በማሕበር መደራጀትን፤መንፈጉን በርካታ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች የተጩበት ጉዳይና ሕግ ነው፡፡

ዛሬ ኢትዮጵያ በመስቀለኛው ጎዳና ላይ ቆማለች፡፡ አፋጣኝ የዴሞክራሲ እድገት፤መልካም አስተዳደርን፤አስተማማኝ እርምጃዎችን በመጀመር በዴሞክራሲ መንገድ መጓዝ ይገባል፡፡ አለያም የኢትዮጵያ ምርጫው  የኋልዮሽ በመንሸራተት ወደባሰው የጭቆና አምባገነን ስርአት መጓዝ ይሆናል፡፡ ወይም በነጻ ዝላይ መልክ ወደምስቅልቅልና ብጥብጥ ትገባለች፡፡ ምርጫው የእኛ ነው፡፡ ሁላችንም ልንማረው የሚገባን እጅጉን አስፈላጊ ትምህርት አለን፡፡ አሁን በስልጣን ላይ ያሉትም ህሊናቸው ጋር ተገናኝተውና ተስማምተው ለሕሊናቸው ተገዢነትን ማረጋገጥ መቻል አለባቸው፡፡ ‹‹ሰላማዊ የለውጥ አብዮትን የማይቻል የሚያደርጉ ከሆነ፤የግዴታ አብዮትን አይቀሬ ማድረጋቸውን ሊገነዘቡት የግድ ነው፡፡” ሌሎችም ማርቲን ሉተር ኪንግ በአንድ ወቅት ለታዋቂው የጥበብ ሰውና የሰብአዊ መበት ተሟጋች ለሃሪ ቤላፎንቴ ስለዘሮች አንድነት መዋሃድ የተናገሩትና ማስታወስ ይኖርባቸዋል፡፡ ‹‹ፍርሃቴ ሕዝቦቼን በመቃጠል ላይ ቀዳለ ቤት እያወሃድኳቸው ነው፡፡ በዚህ አባባል ማርቲን ሉተር ኪንግ ያሳሰቡት የዘር ልዩነትን በማጥፋት ሂደት ሊከሰት የሚችለውን አለመግባባትና ብጥብጥ ማለታቸው ነበር፡፡ቤላፎንቴም ‹‹ታዲያ ምን ማድረግ ይኖርብናል›› ሲሏቸው፤‹‹እኛ የእሳት አደጋ ሰራተኞች ልንሆንና ቤቱን ከቃጠሎ ማዳናችን ተገቢ ነው›› በማለት ነበር ኪንግ የመለሱት፡፡‹‹ሁላችንም ኢትዮጵያውያን የእሳት አደጋ ተከላካዮች በመሆን ፈጣኑን እድገትና መልካም አስተዳደር እንዲሁም የዴሞክራሲን እውነታዊነት ጎዳና ማረጋገጥ ያለብን ነገ ሳይሆን ዛሬ ነው!››

Translated from Ethiopia: Time for Radical Improvements

(ይህን ጦማር ለሌሎችም ያካፍሉ::)

ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮችን  ለማግኘት እዚህ ይጫኑ::

http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/category/al-mariam-amharic

http://ethioforum.org/?cat=24

Leave a Reply