ኢትዮጵያ የኛ፥ የምጽዋት ምርኮኛ? ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

የምጽዋት ምርኮኛ

‹‹ቦንዴጅ›› ከንግሊዚኛ ሲተረጎም በውጭ ሃይል በምርኮኝነት መታገት ወይም መያዝ ማለት ነው፡፡ ሕዝቦች ለእዳ ሲዳረጉ ያን ጊዜ የዕዳ ምርኮኛነት ይሆናሉ:: ተገደውUSAID assistance program in Ethiopia አለፈቃድኘት ሲያገለገሉ  በባርነት ገበሩ ማለት ነው::  በ1960ው አመታት በፊት አፍሪካ የቅኘ አገዛዝ ምርኮኛ ነበረች::   አፍሪካውያን በባርነት ቀንበር ውስጥ ነበሩ፡፡ አሁንስ ግን አፍሪካ የርዳታ ‹‹ቦንዴጅ›› ምርኮኝነት (ለምሳሌ በዓለምአቀፍ የእርዳታ ምርኮ ዘመን እንደ አዲስ ቃል መጠቀሚያነት) ሆና ትገኛለችን?

የዓለም አቀፍ ድጋፍ ሰጪ ደርጅቶችን፤የተባበሩት መንግስታትን የእርዳታ ኤጀንሲን፤ዩ ኤስ ኤይድስን፤የዓለም ባንክንና አይ ኤም ኤፍን ያካተተውን ‹‹ኢንዱስትሪ›› ግራሃም ሃንኮክ ‹‹የችጋራሞች ጌቶች›› በሚለው መጽሃፉ ምንነታቸውንና ማንነታቸውን ከነተግባራቸውና ከሃብታምነት ወይም የጌትነታቸውን መሰረት ቁልጭ አድርጎ አስነብቧል፡፡ደፋር አቀራረቡ ብዙዎችን ‹‹የዓለም አቀፍ መጽዋቾችን›› ቢያበሳጭም  ሃቁን መካድና እውነትን መሸሽ የሚቻል አልሆነም፡፡የደራሲው መሰረታዊው ክርክሩ፤ ‹‹የዓለም አቀፍ እርዳታ የጊዜም፤የገንዘብም ብክነት›› ከመሆኑም አልፎ፤ተረጂ ምጽዋተኞችን የሚጎዳ በመሆኑ በአስቸኳይ፤ ሊቆም ይገባል ነው፡፡በ1989 የተመጸወተው 60 ቢሊዮን ዶላር ጉዳቱን ፤ለመድረስ በቂ መሳርያ ከመሆኑም አልፎ እጅጉን ጎጂና በፍላጎታቸው ላይም ጫና የሚፈጥር ማሰርያ ነው፡፡በከፍተኛ ደረጃም ከባቢውን አየር በማይታመን የጥፋት ዘመቻው አብክቶታል፤በተመጽዋቾቹ ላይ ሶምሶማ እየጋለበ የሚጨፍርባቸውን አስከፊ ገዚዎችንም ህጋዊነት እየሰጠ ሕዝቡን ግን በቸልታ በመመልከትና ለጩኸታቸውም ጆሮ በመንፈግ ይቅር የማይባል በደል አድርሶባቸዋል ይላል ሃንኮክ ፡፡

የሃንኮክ አስተያየትና አባባል፤‹‹ዓለም አቀፍ እርዳታ››‹‹በታክስ ስም ከምሰኪኖቹ የሃብታም ሃገር ሰዎች የሚሰበሰበው ገንዘብ፤ ለሃብታሞቹ የድሆች ሃገር የግፍ ገዢዎች እየተመዘዘላቸው ተመልሶ ለክፉ ቀናቸው መቋቋሚያ እንዲሆን ወደ ሃብታም መጽዋቾች ሀገር በወጣበት መንገድ ባይሆንም ተመልሶ ግን በባንክ ይቀመጥላቸዋል፡፡‹‹ዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ››እና‹‹ መቆም አይገባውም ምክኛቱም ድሆቹ ችጋራም ተምዋቾች ካለሱ ሊኖሩ አይችሉም›› የሚለው አባባል ጥቂት የዝናብ ጠብታ ታህል እውነትነት እንኳን ቢኖረው እነዚህ በድህነት የችጋር አረንቋ ውስጥ ያሉት ችግርተኞች እርዳተው ከመምጣቱ ከዘመናት ቀደም ብለው ከነበሩበት ሁኔታ ተለውጠው መታየት ነበረባቸው፡፡ያም ሆኖ ከሆነ ምጽዋቱ በአሁኑ ጊዜ መቆምና ማንንም ለጉዳት ሳይዳርግ ከገባበት ሁሉ እንደአመጣጡ ውልቅ ብሎ መሄድ በተገባው ነበር፡፡

ሃንኮክ ሲጽፍ: አስቀያሚው እውነታ ደግሞ የዚህ የምጽዋት ነገር ችግሩ ቀጥተኛ ተረጂዎቹ ሕዝቦች ይህን እርዳታ ይቀንስ ይጨምር፤ማወቅ ቀርቶ ምጽዋት ተብሎ በስማቸው ከሚጎርፈው ገንዘብ ድርሻቸውን ቀርቶ ርዝራዡን ማግኘት ቀርቶ ከረጂው ድጅት ተወካዮች ጋር እንኳን በአጋጣሚም ሆነ በድንገተኛ መገጣጠም ተያተውም አያውቁ፡፡በቢሊዮኖች ዶላር በሚቆጠረው እርዳታ አላስፈላጊ በሆኑ የመጽዋቹ ሃገር ፍብረካዎች ምርት ደረጃው ያዘቀዘቀ ምርታቸውን ከማፍሰስ ባሻገር፤ በረጂዎቹ ብልጣ ብልጥ ደላላዎች፤ አገናኞች፤ኤክስፐርት በሚባሉት፤በአጭበርባሪ ጉዳዩ በሚመለከታቸው የተረጂ ሃገራት ሚኒስትሮች፤አመኔታ በሌላቸው ስራውን አከናዋኞች፤በማይታመኑ አሻሻጭና ደላላዎቻቸው፤በጉቦና በጋጠወጥነት ማግበስባስ፤በፕሬዜዳንቶቹ ራስ ወዳድነትና ንፍገት፤የሕዝብ አሉታ ሳያገኙ በጉልበትና በማን አለብኝነት በስልጣን ጣራ ላይ በተጎለቱ ገዢዎች፤ ስለሃገራቸው ጉዳይ ከሕዝብ ጋር ፈጽሞ ምክክር ማድረግን ከማይፈቅዱ መሪዎች ጋር  አገልጋዮቻቸው ጋር ለሕዝብና ለሃገር በተሰነዘረ ችሮታ እነሱ ሕዝብ ነን በማለት እንዲንደላቀቁበትና የገንዘቡን ባለዐጭዳ ሕብረተሰብ እያደኸዩና እያሰሩ፤ እያሰቃዩና እየገደሉት እንዲኖሩ ይፈቅዱላቸዋል፡፡

ሊያሻሽሉትና ሊያስተካከሉት፤ ከፍ በማድረግ ሕዝቡን ከመከራና ሰቆቃ ሊያወጡት ሲገባ እነሱ እነዚህ በጣም ታዋቂና አዛኝ የሚባሉት ዓለም አቀፍ መጽዋቾች ሃገር በቀል የሆኑና ለወገኖቻቸው ተቆርቋሪና አዛኝ መስለው የሚቀጠሩትን በመያዝና በስራው መስክ ቢያሰልፉም እነዚህ ሃገር በቀሎች ግን ከህብረተሰቡ ጋር ተገናኝተው ችግሩን በመቅረፍ ፈንታ፤የቀን ከቀን ግንኙታቸውን ቸል በማለት ሊቀረፍ የሚገባውን ችግር ይብሱን ያሳድጉታል፡፡ ከመጠን በላይነሃ ከተግባራቸው እጅጉን በናረ መልኩ የሚከፈላቸው ምጽዋት ሰጪ ተወካዮች በሃገራቸው በኢንዱስትሪ ማእከል አለያምበንግድ ዘርፍ ተቀጥረው ከሚያገኙት የበለጠ ያገኛሉና፤በተቸሪዎቹ ሕይወትና ሃገር ላይ ምዝበራቸውን ያመቻቻሉ፡፡በትክክለኛው አጠራር ሙያቸው ‹‹ሰብአዊነት›› ቢሆንም የድርጊታቸው ሁኔታ የሚያሳየው ግን‹‹ሽያጭ›› ‹‹ኢንጅነሪንግ›› ሊባል የሚገባው ሲሆን፤በማይወጡትና እውቀቱና ግንዛቤያቸው የሚያተኩረው ወደ ራስ ጥቅም በመሆኑ፤የተሰማሩበትን የዕርዳታ ድርጅት ውጤት በቁጥር ሊሰፈር በሚችል ሚዛን ጨርሶ ማሳየት አይችሉም፡፡እነዚህ እራሳቸውን በቅራቅንቦ የከበቡ አንዳችም ጠቀሜታ ጠብ የማይላቸው ከንቱ የምስኪኖች ሎርዶች የዘመኑ ውዳቂዎች ሆነው ግና ለማንም ተጠያቂነት የሌለባቸው ሆነው ያላቅማቸው ስልጠን የተጫነባቸው ናቸው፡፡

ምጽዋት፡ ምርኮኛ በኢትዮጵያ ‹‹ለግፈኛውና ለጨካኙ›› ይሁንታና  እውቅና መስጠት?

በዚህ መጣጥፌ ሃንኮክ ስላነሳው አስተያየት ማንሳቴ ለተቅላላ ግነዛቤ ብቻ አይደለም፡፡ ሃንኮክ አመለካከት ላይ በመመስረት፤በቅርቡ ለኢትዮጵያ ይፋ የሆነውን የአሜሪካንን የ1.54 ቢሊዮን ዶላር ምጽዋት ‹‹የዓለም አቀፉን የምጽዋት ድርጅት›› ስመረምረው ሳወጣና ሳወርደው ለጭፍንና ማን አለብኝ ግፋዊ ገዢዎች እውቅና መስጠት ነው፡፡ በኢትዮጵያ የዩኤስ ኤይድ ሚሲዮን ዳይረክተር ቶማስ ስታል የ1.5 ቢሊዮን ዳረጎት በተመለከተ እንዳሉት ‹‹ይህ ምጽዋት በሁለቱ ሃገሮች መሃል የነበረውን ግንኙነት በማሳደግ ከረጂ ተረጂነት፤ ወደ ኤኮኖሚ ተባባሪነት ያሳድገዋል›› ነበር ያሉት፡፡‹‹ይህ ታላቅ ስምምነት›› የሚያነጣጥረው በትምህርቱ መስክ፤ጤና፤እርሻ፤መልካም አስተዳደርን በማሳደግ በኩል እያገዘ በተለይም የኢትዮጵያን እድገትና ትራንስ ፎርሜሽን ስትራቴጂ አጋዥ ሃይል ይሆናል፡፡ ከ2011-2012 ድረስ ባለው ጊዜ ለኢትዮጵያ ከአሜሪካ የሚደረገው የምጽዋት መጠን፤ወደ 675 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በማደግ በአራት  ቅድሚያ በሚሰጣቸው ላይ ያተኩራል፡፡ አራተኛው ግብ ደግሞ፤መልካም አስተዳደርን በማሻሻልና በማሳደግ ላይ ያተኮረና በሁሉም ሴክተሮች በኩል ተጠያቂነትንና የግጭቶችን ማስወገጃ ዘዴ ማስተማርያ ይሆናል፡፡ በዚህስ በተነደፈው ግብ የአሜሪካን መንግስት የመለስ ዜናዊን ግፈኛና ጨቋኝ ፈላጭ ቆራጭ ገዢነት እውቅና ይሰጣል?

የዩኤስ ኤይድ ሪፖርት እንደሚለው:

ከሞላ ጎደል ነጻ ማለት በሚቻለውና ኢህአዴግ ተወዳጅነቱን ከመጠን በላይ እርግጠኛ የሆነበትና በምርጫው ወቅት ግን በሚያሳፍር ሁኔታ ድምጽ የተነፈገበትና ለምርጫ ውርደትና የታየውን የዴሞክራሲ ጭላንጭል አውድሞ የጨዋታ ፈረሰ ዳቦ ተቆረሰ ያልበሰለ ባህሪ ያሳየበት የ2005 ምርጫ ነበር፡፡ ከዚያው ጋር ተያይዞም የተቃዋሚው ጎራ ተከፋፍለው በመፈረካከሳቸው የኢህአዴግ ገዢ መንግስትም የግዛት ዘመኑን በማራዘም የግፍ አገዛዙንም አዳበረ፡፡ የሲቪል ማህበረሰቡን እንቅስቃሴ በመቅጨት፤ሚዲያውን ተስፋ በማስቆረጥ፤ የሽብርተኝነት ሕግ በማውጣትና ተግባራዊ በማድረግ መያዝና ማሰርን ስራው አድርጎ መንቀሳቀሱንና አፈናውን ማካሄድ ቀጠለ፡፡ ያወጣውም የሽብርተኝነት ሕጉ እንዳሻው ለማሰር ለማፈንና ለማስፈራራት ተቃዋሚውን ጎራም ቀልቡን አሳጥቶ ዝም ማሰኛ መሳርያው አድርጎ ያለአንዳች ይሉኝታ በሃፈርትና በቅሌት የተመላውን ድርጊቱን ቀጠለ፡፡ በ2010 በተካሄደውም ተወዳዳሪ አልባ የምርጫ ወቅት መራጭም ተመራጭም፤ አስመራጭም አስፈጻሚም፤ሕግ አውጪም ተግባሪም በመሆን ይሉኝታ እንኳን ለስሙ ያህል ያላሳየበትን የምርጫ አታሞ ደልቆ ከማንም ይበልጥ እራሱን በማታለልና፤ ለምን ፤እንዴት የሚል ጥያቄ የማያውቁትን የአቤት ጌታየ እሺ ጌታዬ አባላቱን 99.6 በመቶ አሸነፍን በማለት የፓርላማውን ወንበር በድፍረት ተቆጣጠረው፡፡ ከ2010 ምርጫ በኋላ የታሰሩት የፖለቲካ እስረኛች የተፈቱ ቢሀንም፤የታቃዋሚዎችን እንቅስቃሴ ገዚው ፓርቲ በመቆጣጠርና የፖለቲካ ሜዳውን በማጥበብ፤የሲሰቪል  ማህበረሰቡን እንቅስቃሴ በማዳከም ፤ በጠበበ የፖለቲካ ሜዳ፤በተደቆሰ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጎራ የግፍ እስር መቀጠል እንዳለ በሆነበት ወቅት በምጽዋት ስም 1.5 ቢሊዮን ዶላር? በአጠቃላይ በ2009 የልማት ድጋፍ ስም 3.8 ቢሊዮን ዶላር?

ዩ ኤስ ኤይድ በዴሞክራሲ ግንባታው፤በአስተዳደር ማሻሻሉ፤በችግር አፈታት ብልሃቱ ላይ ከፌዴራል ጉዳየች ቢሮ ጋር በቅርቡ በመስራት ላይ ነበር፡፡ኡን እንግዲህ የ2010 ምርጫ በማብቃቱ የፖለቲካ ውጥረቱ በመጠኑ ረገብ ማለትን አሳይቷል፤ የሃይለኛ ተቃዋሚ ጎራ አባላትም ተፈትተዋል ቢባልም በሺህ የሚቆጠሩ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት አሁንም በእስር ፍዳቸውን በማየት ላይ ናቸው፡፡

በገዢው መንግስት በኩል ታላላቅ መጽዋች ሃገራት ስለ አሳሳቢው የዴሞክራሲ ሁኔታ፤አስተዳደር የተደረገው ውይይት፤ በሚታየው የገዢው ሕግ አልባነት፤የአስተዳደር በደል፤ የሕገመንግስቱ ጥሰት አንዳችም የመግባባትና የተፈለገውን ሕዝባዊ መብት ለማስገኘት አልተቻለም፡፡ የዓለም ባንክ፤ዩ ኤን ዲ ፒ፤ዲ ኤፍ አይ ዲ፤ሲ ዳ(ካናዳ)፤ ዩ ኒ ሴፍ፤ኢ ዩ፤ ሲዳ(ስዊድን)አይር ላንድ፤ጀርመንና ሌሎችም በጥምር ሆነው ያለውን ችግር ለመፍታትና ገዢውን ፓርቲ ወደ ትክክለኛው አካሄድ መምራትና ሕገመንግስቱ በሚያዘው ስርአት ውስጥ ማካተት እንዴት ሆኖ አቃታቸው?

ዩ ኤስ ኤይድ በሚሰጠው የችሮታ ድጋፍ በሁሉም ደረጃ ያሉትን ተቋማት በአጠቃላይ (በተለይም የአካባቢ የፌዴራል ጉዳዮች) በአካባቢ ለሚነሱ ግጭቶች በደህንነት አባላቱ መፍትሄ ማስገኘትን ቸል በማለት፤ችግሮቻችሁን በራሳችሁ ክልል በኩል ፍቱት በሚል የመሸንገያ ዘዴ ‹‹ጉዳት አታድርሱ›› ‹‹አትጎዳዱ›› በሚል የህብረቱ መጽዋች አባላት የተነሱበትን ዓላማ ቸል በማለትና ገዢውን ፓርቲም ላለማስከፋት ሥልጠናውን ዘግተው፤ ሰልጣኞችንና ቀሪውን የሕብረተሰብ አባላት ላበዱ ተናካሽ ውሾች አስረክበው ወጡ፡፡

የመጽዋች ሃገሮች ኢትዮጵያን የችጋር ዋነኛ ሰለባነት በማረጋገጥ በመደጎምና፤ታላቅና በዋናነት ለሃገሪቱና ለሕዝቦቿ አስፈላጊነቱ በተረጋገጠውና ቅድሚያም ሊሰጠው ተገቢ በሆነው የዴሞክራሲ፤ ሰብአዊ መብት ገፈፋን ማስወገድ የሲቪል ማህበረሰቡን እንቅስቃሴ ገደብ ማሸነፍን፤ በሕገመንግስቱ የተረጋገጠውን ሃሳብን በነጻ የመግለጽ መብትን ማስከበርን፤ የኢንፎርሜሽን በነጻ የማግኘትን መብት ማስከበርን በተመለከተ ተከፋፍለው ይገኛሉ፡፡እነዚህ የመጽዋች ሃገሮች፤በውስብስብ ማስመሰያ የቃላት ጨዋታ ሁኔታዎችና በሚታየው የገሃዱ የፖለቲካ ጭቆና፤የገዢዎች በኤኮኖሚው በኩል የበላይነትና የሰብአዊ ደራሽ አደጋዎችን በሌላ ጎን በማሰለፍ ችግር ውስጥ ይታያሉ፡፡በዚህ ባለሁለት ስለት ሰይፍ ሁኔታ ወስጥ መጽዋች ሃገራት ቀጥተኛ ባይሆንም የጎንዮሽ የማረሚያ ሃሳብ ማቅረብና እምቢተኛውን የጉልበት አዋቂና ግፍ አድራሽ ለመቅጣትም አቅሙ ቢኖራቸውም ፈቃደኛነቱ ግን ርቋቸዋል፡፡ ምናልባትም ሼክስፒር እንዳለው ከነዚህ አፈ ቅቤ ልበ ጩቤዎች መጠንቀቅን እወቁበት ይመስል ይሆን?

የውድድር ምርጫና ሌሎች የዴሞክራሲ ሂደቶች በሌሉበትና ገዢው መንግስትም የዜጎቹን ፍላጎት ጨርሶ በናቀበትና የባለመብቶቹን ጉዳይ ገደል ይግባ በማለት በቋጨበት ሂደት ላይ፤አንዳችም የፖለቲካ መተንፈሻ ማየት በጣሙን አስቸጋሪ ነው፡፡ አዲሱ የኢትዮጵያ የልማትና እድገት ትራንስፎርሜሽን እቅድ፤ውስን የሆኑ የአስተዳደርን ጥቃቅን እዚህ ግቡ የማይባሉ ጉዳዮችን ለይቶ ያካተተ ነው፡፡ ማለትም ወሳኝ የሆኑና ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡትን በንጉሱና ደርግ ዘመን ጠፍተው የነበሩትን ሕዝባዊ እሴቶች አሁን ባለው የአብታዊ ዴሞክራሲያዊ በሌላው ዓለም ተቀባይነት ያጣ የግዛት ስርአት ውስጥ ማግኘት ያቻላል ማለት ከንቱ ውዳሴ ነው፡፡ታዲያ የመለስ ዜናዊ መንግስት ከ21 ዓመታት የፈላጭ ቆራጭ የግፍ አገዛዝ ዘመናት በኋላ ማሳየት ያልፈቀደውን የዴሞክራሲ ስርአት ባለፉት ስርአቶች ወቅት አልነበሩም ለማለት የሚያበቃ ድፍረት ሊኖረው ይችላል? እንዴት ተቀለደ እባካችሁ ብቃት ያለውና ወገናዊ ያልሆነ የፍትህ ስርአት መኖር የግሉን ኢንቬስትመነት አካላትና ግለሰቦችንና መጽዋቾችን የሚያስፈራራ ውሳኔ ውስጥ የሚያሰልፋቸው ሁኔታ ነው፡፡ በሌላ ወገን ደሞ በፖለቲካው ሜዳ ታማኝነታቸውን ያረጋገጡ የንግዱ ተጠቃሚዎች የተቀመጡትን ህጎችና ድንጋጌዎች በምርኩዝ ተስፈንጥረው በመዝለል ግባቸውን ማሳካታቸው ነው፡፡ይህ በገዢው መደብ ስር ያለ ህግም እነዚህን በልዩነት የሚመለከትና ህገወጥነትን የሚተገብር ስርአት አራማጅ መንግስት ውስጥ ሁኔታውን ማየት የለት ተለት ተግባር ነው፡፡ ለፍትህና ለዴሞክራሲ ለዘብ ያለ ወገናዊነት? ሑኔታው ሁሉ እኮ በገዢው መደብ ፈቃደኝነት ላይ ብቻ የተመሰረተና የሚተገበር እኮ ነው፡፡ ይህ ተሰምቶ ያውቃል?

የኢትዮጵያው/ዩ ኤስ ኤይድም በነጻ የመወዳደርያ መድረክ በሌለበት ሁኔታ አንዳችም የፖሊሲ ፕሮግራም ማከናወን አለመቻሉን ያምናል፡፡በመካሄድ ላይ ያለው የግለሰቦች፤ የውጭ የእርሻው መስክ ኢንቬስተሮች፤ የመሬት ሽሚያ ሁኔታ በሚጨምርበት ሁኔታ ፖሊሲው የመሬትን አጠቃቀም ስርአት ማበጀትንና መፈናቀልን በማስወገድ በኩል የነዋሪውን መብት በመጠበቅና በማክበር ሚዛናዊ አድግትን ያረጋግጣል መባሉስ…………. ለግለሰብ የእርሻው ዘርፍ ኢንቬስተሮች‹‹መሬትን መስጠት››! ተሰምቶ ይታወቃል!

ወዳለፈው 2004፡ ያን መልካም ወቅት እንደነበረው ማስቀመጥ

በ2004 ዩ ኤስ ኤድ ‹‹የምግብን ማጣት ውድቀት አዙሪት መስበር፡ በኢትዮጵያ ችጋርን መከላከል›› አስተዳዳሪው አንድሪው ኤስ ናስቲዮስ ባሰፈረው ዘገባ ውስጥ ከተካተተው በቅንጭቡ የሚከተለው ነበረበት፡

….ኢትዮጵያ በሚታየው የምግብ አቅርቦት ችግረና በችጋሩ ሁኔታ ብቻዋን የቆመች ሃገር አይደለችም፡፡በመሆኑም ብቻዋናም ውጤቱ ዘንድ መድረስ አትችልም፡፡ጎረቤቶቿና የእድገት አጋሮቿ በአንድነት ይህን የችጋሩን ሂደት ማስወገድ፤ የምግብ እጦቱን ሂደት በመቀየር፤ ቀዳኒነት ሊሰጥ የሚገባውን የሕዝቦችን ጤናና የኤኮኖሚ ሁኔታ ማሻሻል፤ ለአሁኑና ለተተኪው ትውልድ አስፈላጊ ቢሆንም ወደዚያ ግብ መድረስ ቀርቶ መጠጋትም አልተቻለም፡፡ይህንንም ሁኔታ በአግባቡ ለመቋቋም የኢትዮጵያን ገዢ መንግስት ፈቃደኝነት፤ቁርጠኝነት፤ለለውጥ መነሳሳትን ይጠይቃል፡፡በኢትዮጵያ ያለው እውነታ አሳማኝና ግልጽ ነው፡፡ከሌሎች የአፍሪካ ሃገሮች ያነሰ በተለይም ከምስራቅ አፍሪካ ሃገሮች ጋር ሲወዳደር የወደቀ መሆኑን ያለፉት ዓመታት ያሳያሉ፡፡የዚህ የኢኮኖሚ ውድቀት ሰበቡም ድርቅና የችጋሩ ሁኔታ ሳይሆን በሃገሪቱ ላይ የሚታየው የአስተዳደር ድህነትና እጦት፤ የምግብ አቅርቦት ማነስ ሳይሆን  ይልቁንስ ስትከተለው በነበረው ደካማ የኤኮኖሚ ፖሊሲ አነስተኛ በሆነው የኢንቬስትመንት የኤኮኖሚና የእርሻ እድገት፤የሌሎችም ምርቶች መቀነስ ናቸው፡፡ የኤኮኖሚው መውደቅም የሶሻል ደረጃውንም መድከም አባብሶታል፡፡የህ ደሞ ገዢውን መንግስት ስርአት ባለው ሁኔታ መምራት አላስቻለውምና ለችግር መዳረግ አማራጭ የለውም፡፡

በሜይ 2012 የወቅቱ ዩ እስ ኤይድ ዳይረክተርና የጂ8 ሀገራት በዋሽንግቶን የምግብ ዋስትና ስብሰባ ወቅት ለመለስ ዜናዊ  በመግቢያ ንግግሩ ላይ፡

……ብዙ ሰዎች ስለኢትዮጵያ ያላቸው አመለካከት በችጋር ላይ ያነጣጠረ ቢሆንም በተወሰደው የእርሻ ኢንቬስትመንት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን በቅርቡ ከተከሰተው የድርቅ  ሁኔታ ከችጋር በማዳን ከምግብ ተመጽዋችነትና ከእርዳታ ምግብ ልመና አድነሃቸዋል፡፡ምንም እንኳን አሁንም የግሉን ማህበረሰብ ያካተተ አዲስ የምግብ ዳረጎት ስርአት እየነደፍን ቢሆንም፤ከስብሰባው ውጪ በግል ካነሳነውና አስተያትህን ከሰነዘርክበት ሃሳብ አኳያ በገባነው ቃል ላይ መጽናት ምን ያህል ጠቀሜታ እንዳለው ያልከውን ልታካፍለን ትችላለህ?

መለስ ቃል አልወጣውም አንደበቱ ተያዘ ተሳሰረ፡፡

ባለፉት ዘመናት ሁለ፤ ኢትዮጵያ የአሜሪካ እርዳታ የተባለው ሁሉ ተጠቃሚ ነበረች፡፡‹‹የኤኮኖሚ እርዳታ›› ‹‹የልማት እርዳታ›› ‹‹ወታደራዊ እርዳታ›› ‹‹ቴክኒካ፤ እርዳታ›› የድንገተኛ አደጋ እርዳታ›› ‹‹የችግር ማስወገጃ እርዳታ›› ‹‹የሰብአዊ እርዳታ›› እኛ የሌሎችም እርዳታዎች ተጠቃሚ ናት፡፡‹‹የባንድ ኤይድ›› እና ‹‹የላይቭ ኤይድም›› ምጽዋት አካል ነበረች፡፡ ዛሬ ዛሬ ደሞ ኢትዮጵያ ለዘለቄታው ‹‹በቦንድኤይድ›› ተጠፍንጋለች!

(ይህን ጦማር ለሌሎችም ያካፍሉ::)

ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮችን  ለማግኘት እዚህ ይጫኑ::

http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/category/al-mariam-amharic

http://ethioforum.org/?cat=24

Similar Posts

Leave a Reply